Marawa news in አማርኛ
Статистика- Последний пост
- 26 янв. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 18
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#Tigray ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል። በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች ያካተቱ ሰልፈኞች ደግሞ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚነት (null and void እንዲሆን) እንዳይኖረው ፤ ጦርነት የሚፀየፉና ጅምር ሰላም እና ለውጡ እንዲቀጥል የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል። በሰሜናዊ ምዕራብ ፣ ማእከላዊ ዞኖች መቐለ ከተማ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት ብቻ የጠራቸው ሰልፎች ሲካሄዱ ፤ በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች በደጋፊ እና ተቃዋሚ በአንድ ጊዜ የተጠሩ ሰልፎች ተከናውነዋል። ትናንት ጥር 17/2017 ዓ.ም በደቡባዊ ዞን የተለያዩ ከተሞች " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚቃወም ጦርነት የሚያወግዝ ሰላምና ለውጥ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ የተካሄደ ሲሆን ዛሬ እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት የጠራው ሰልፍ በዞኑ አልተካሄደም። በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት በጠራው ሰልፍ የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ? - የፕሪቶሪያ ውል ይተግበር !! - የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !! - ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !! - የህወሓት ህጋዊነት በአስቸኳይ ይመለስ !! - ሰራዊታችን ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ አንቀበልም !! @marawa_ama
" ሁለት ፆታዎች ብቻ ነው ያሉት እነሱም #ወንድ እና #ሴት ናቸው " - ፕሬዝዳንት ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ እንደገቡ ከሚሰሯቸው ዋነኛ ስራዎች አንዱ በሀገሪቱ ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እውቅና መስጠት ነው። ይህም በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣን የመልቀቂያ ጊዜ ለትራንስጀንደር / ፆታቸውን ለሚቀይሩ ሰዎች የሚሰጠውን ከለላና ጥበቃ የሚሽር ነው። ለወንድ እና ለሴት ብቻ እውቅና መስጠት ትራፕም ከሚያስተላልፏቸው ትዕዛዛት አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ታውቋል። ትራምፕ ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ ፥ " ከዛሬ ጀምሮ / ከእንግዲህ ወዲህ / የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ እውቅና የሚሰጠው ለሁለት ፆታ ብቻ ነው እነሱም ወንድ እና ሴት " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል። የአሜሪካ መንግሥት ከአሁን በኃላ እውቅና የሚሰጠው ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እንዳሆነ የገለጹት ትራፕም ፤ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ብዝሀነት፣ እኩልነትና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ለማስወገድ የአፈጻሚ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ ተነግሯል። ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፤ ፆታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ትዕዛዝም ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትራምፕ " ሰዎች ተፈጥሯዊ ፃታቸውን መቀየር የለባቸውም " ብለው የሚያምኑ ሲሆን ከዚህ ቀደም ፆታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ መነገሩ ይታወሳል። 15 ሺህ ፆታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው። ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉ መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቪድዮው የፎክስ ኒውስ መሆኑን ይገልጻል። #USA #PresidentDonaldTrump @marawa_ama
ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎቱ ተቋረጠ ቲክቶክ ከደቂቃዎች በፊት በአሜሪካ መስራት አቁሟል። ከቻይና መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለው በአሜሪካ መንግስት ክስ የቀረበበት የቲክቶክ ዋና ድርጅት ባይት ዳንስ ማስተካከያ እንዲያደርግ ወይም የድርጅቱን የአሜሪካ ቅርንጫፍ ለአሜሪካ ኩባንያዎች እንዲሸጥ ተጠይቆ ነበር። ቲክቶክ አገልግሎቱ ለ175 ሚልዮን አሜሪካውያን ዛሬ ቢቋረጥም ሰኞ እለት ወደ ስልጣን የሚመጡት ዶናልድ ትራምፕ እገዳውን እንደሚያስቆሙት ይጠበቃል።
Channel photo updated
#Update በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ከፍተኛ ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን እሳቱ አሁንም ሎስ አንጀለስን ማንደዱን ቀጥሏል። እሳቱ እስካሁን ካደረሰው ውድመት በላይ ሊያደርስ ይችላል ተብሏል። በአካባቢው ያለው የንፋስ ሁኔታ እሳቱን እያባባሰው ነው ተብሏል። ከተነሱት ሰደድ እሳቶች አንዱን ብቻ ነው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለው። ባለስልጣናት #ቀጣዮቹ ንፋሶች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የንፋስ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ በማለት መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል። እስከ ትላንት ባለው 24 ሰዎች ሲሞቱ 16 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። የግል ትንበያ ተቋም የሆነው " አኩዌዘር " እስከ ትላንት ባለው በእሳት ቃጠሎ የተነሳ የደረሰው ኪሳራ ግምት ከ250 እስከ 275 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል። @tikvahethiopia
ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ የ2025 ሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመረጠች ----------------------------------------- [ጥር 06፣ 2017 ዓ.ም] የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓመታዊ የስልጠና መርሃ ግብር፣ ከሁዋዌ ታዋቂ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የ2025 የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደሮችን መርጦ አሳውቋል። ከተመረጡት 12 አምባሳደሮች መካከል በኢትዮጵያ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው አሲያ ኽሊፋ ትገኛለች። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። https://www.facebook.com/share/p/1Cy3rb8nw4/
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ፎቶ ፦ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተመረቀ ነው። የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተመርቆ ታቦተ ሕጉ ጥንታዊነቱን ጠብቆ ወደ ታደሰው ካቴድራል በመግባት ላይ ይገኛል። በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎችና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍል ኃላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል። መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው። @tikvahethiopia
#FreeNaima " ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል " - ቤተሰብ በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት እየፈጸሙባቸው ይገኛል። ከእነዚህ ታጋቾች መካከል የሀገራችን ልጅ ነሒማ ጀማል አንዷ ናት። ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል፤ ሻሸመኔ በመሰደድ ነው ወደ ሊቢያ ያቀናችው። ' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' የተሰኘው ተቋም በኤክስ ገፁ እንዳስታወቀው ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች ' ኩፍራ ' በምትባለው የሊቢያ ግዛት በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ። ነሒማ በፎቶዎቹና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታያለች። የነሒማ ጀማል ቤተሰቦች ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ተልኮላቸው የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል። የነሒማ እህት ኢፍቱ ጀማል ፤ ነሒማ ከ8 ወራት በፊት ከሻሸመኔ ከተማ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ሊቢያ እንደተሰደደች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ተናግራለች። " ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ይልኩልናል። ስትሰቃይ ያሳዩናል። የድምፅ መልዕክትም ልከውልናል። እህታችን ' ገንዘብ ላኩላቸው ካልሆነ ይገድሉኛል ' ስትል ይሰማል " ስትል አስረድታችለች። ነገር ግን ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ አጋቾቹ የጠየቁትን ገንዘብ የመላክ አቅም የለውም። ' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' የተባለው ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው ተቋም እንዳለው የ20 ዓመቷ ነሒማ ጀማል ባለፈው ግንቦት ሊቢያ ከገባች ከቀናት በኋላ ነው በታጣቂዎቹ እጅ ውስጥ የገባችው። በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ስቃይ ሲደርስባት እና ስትደበደብ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ለቤተሰቦቿ ተልከዋል። ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ የተጠየቀውን ገንዘብ ለማሰባሰብ እርዳታ ቢጠይቅም እስካሁን ድረስ ሊሞላላቸው አልቻለም። ቤተሰቡ የነሒማን ድምፅ ከሰማ ሁለት ሳምንት እንዳለፈው እህቷ ተናገራለች። " ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል " ስትል አክላለች። ' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስቃዩ እና ማስፈራራቱ እንደተጠናከረ እና ይህ ደግሞ ቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሆነ ገልጿል። አጋቾቹ ለነሒማ ማስለቀቂያ የጠየቁት ገንዘብ 6 ሺህ ዶላር ነው። የነሒማ ቤተሰብ ይህንን ሁሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል። ለነሒማ ቤተሰብ የተላኩ ቪዲዮዎች በርካታ ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ያሳያሉ። ነሒማ እጅና እግሯ ተጠፍሮ፤ አፏ በጨርቅ ታፍኖ ትታያለች። ስቃይ ሲደርስባት እና ደም በደም ሆና የሚያሳዩ ቪዲዮዎች እና ፎቶዎችም አሉ። ድርጅቱ በለቀቃቸው ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ላይ ነሒማ ብቻ ሳትሆን 50 ገደማ ሌሎች የአጋቾቹ ሰለባዎች ከጀርባዋ ተደርድረው ይታያሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን የባርነት ንግድ ዓለም ረስቶታል ሲሉ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እየወቀሱ ናቸው። በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ወዳለችው ሊቢያ በስደት የተጓዙት ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች መጨረሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም። በርካታ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ስደተኞች ሕይወታቸውን ለመቀየር በሚል ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት ጉዞ የሜዲቴራኒያን ባሕርን ከማቋረጣቸው በፊት ሊቢያን ይረግጣሉ። መረጃው ከሪፊውጂስ ኢን ሊቢያና ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው የተገኘው። #FreeNaima @tikvahethiopia
የሶማሊያን አንድነት እና ሉአላዊነት የሚጋፋ ተናጠላዊ አርምጃን በጋራ እንከላከላን ሲሉ ግብጽ እና ኤርትራ አስጠነቀቁ የግብጽ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሀገራቱ መካከል በመሪዎች ደረጃ በተደረሱ ስምምነቶች ዙሪያ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በካይሮ ውይይት ማካሄዳቸው ተገለጸ። ውይይታቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ሚኒስትሮቹ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የሶማሊያን አንድነት እና ሉአላዊነት የሚጋፋ ተናጠላዊ አርምጃን በጋራ እንከላከላን ሲሉ መናገራቸውን ከአህራም ጋዜጣ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። "ለሶማሊያ መረጋጋት፣ ደህንነት እና የግዛት አንድነት ያለንን ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን፤ እንዲሁም የሶማሊያ መንግስት በአጠቃላይ የሀገሪቱ ግዛቶች ላይ የሚያካሂደውን ቁጥጥር እንደግፋለን፤ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚያደርገውን ጥረትም እናግዛለን” ብለዋል። የሶስቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጥር 3 ቀን ያካሄዱት የጋራ ውይይት የሀገራቱ መሪዎች በአስመራ ያካሄዱትን ውይይት ተከትሎ የተካሄደ የመጀመሪያው ስብሰባ መሆኑን የጠቆመው የአህራም ዘገባ በቀጣይ ግዜውን የጠበቀ እና ቀጣይነት ያለው ውይይቶች ለማድረግ መስማማታቸውን አስታውቋል። ቀጣዩ ስብሰባቸው በሞቃዲሾ እንደሚሆን አመላክተዋል። የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ “በቀይ ባህር ዳርቻ የድንበር ወሰን የሌላቸው ሀገራት የባህር ሀይልም ሆነ ማንኛውም ወታደራዊ ሰፈር ማቋቋም ተቀባይነት አይኖረውም” ሲሉ በድጋሚ ማስጠንቀቃቸውንም ዘገባው አካቷል። ከሶስትዮሽ ውይይታቸው በተጨማሪም የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳላህ እና ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ጋር በተናጠል ውይይት ማድረጋቸውም ተጠቁሟል። በቅርቡ የሀገራቱ መሪዎች ሁለተኛውን ስብሰባቸውን እንደሚያካሂዱም ተጠቁሟል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ነው የዘገበው። @sheger_press @sheger_press
Channel name was changed to «Marawa news in አማርኛ»
Channel name was changed to «Marawa news»
Channel created