tgindex

♏ሜዲካመንት️

Статистика
@medicament02французский

Let's discuss about our health!

Последний пост
24 нояб. 2024 г.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
французский
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
92
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
168
20 постов
Вовлечённость
182,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 24 нояб. 2024 г.9232из sostmaezen

    አንድን ሰው ሁለቴ አታገኙትም። ስሜቱ ተቀያይሮ፣ አስተሳሰቡ ከፍ/ዝቅ ብሎ፣ እድሜው ጨምሮ፣ አዲስ ልምድ(experience) ኑሮ ነው የሚጠብቃችሁ። ያም ሆኖ "እኔኮ በደንብ ነው የማውቃችሁ" የሚሉ ማሞ ቂሎዎች ይገጥማችሁዋል። I love you too! በሏቸው። ✍ዌሻፕት

  • 22 нояб. 2024 г.85из wanawtena2013

    የዓይን መቅላት መንስኤዎችና ምልክቶች 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 የአይን መቅላት የተለመደና የብዙ ሰው ችግር ነው የአይን መቅላት አይን ውስጥ ያሉ የደም ስሮች ወደ ላይኛው የአይን ክፍል በተለያዩ ምክንያቶች ተለጥጠው (dilated) በሚወጡበት ወቅት ይፈጠራል፡፡ የዓይን መቅላት ገጽታ ሊለያይ ይችላል። በነጩ የዓይን ክፍላችን ላይ ሮዝ ወይም ቀይ መስመሮች ያሉ ይመስላሉ ወይም ሙሉውን ሮዝ ወይም ቀይ ሆኖ ሊታይ ይችላል። ምልክቶች፡- የአይን መቅላት ፤ማሳከክ ፤ አይን ማዝ መያዝ ፤ ዉሃ የመሰለ የአይን ፈሳሽ( እንባ መብዛት) ፤ ማቃጠል ፤ ድርቀት ፤ ህመም ፤ ብርሃን አለመቻል ፤ የዓይን ብዥታ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናችው። መንስኤዎቹ ፡- ለፀሐይ ብርሃን ከመጠን በላይ መጋለጥ ፤የአይን መድረቅ ፤ የዓይን አለርጂዎች፤ የዓይን ብግነቶች (conjunctivitis) ፤ የአየር ብክለት ፤ የተለያዩ ጭሶች ደረቅ አየር ፤አቧራ ፤ የኬሚካል ተጋላጭነት ፤ ለእረጅም ሰዓት ስክሪኖችን መጠቀም ፤ በሃኪም ያልታዘዙ የዕይታ መነፅሮችን መጠቀም የመሳሰሉት እንደሆኑ ይነገራል። የዐይን መቅላት ካለብዎት የሚከተሉትን ይጠንቀቁ፡ - ዓይን አለማሸት፤ ችግር ያለበት ዓይን ነክቶ ሌላኛዉን ዓይን አለመንካት ፤ አለርጂ ካለብዎ የአይን መዋቢያዎችን አለመጠቀም ፤ ምንም ዓይነት የባህል የዓይን መዳኒት አለመሞከር ፤ በሃኪም ያልታዘዘ ምንም አይነት የዓይን ጠብታ አለመጠቀም ፤ አለርጂ ከሚሆኑቦት ነገሮች መራቅ ይመከራል። ችግሩ ከጥንቃቄ በላይ ከሆነ ቅርብ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ ማማከር ይገባል። #amharahealthbereau t.me/wanawtena2013

  • 6 нояб. 2024 г.772из sostmaezen

    ማሳሰቢያ ⚠️ ሰሞኑን በቴሌግራም መልዕክት የተለያዩ ሊንኮች እየተላኩ የብዙ ሰዎች የቴሌግራም አካውንት እየተጠለፈ ሲሆን ራሳችሁን እነዚህን ማስፈንጠሪያ ሊንኮች ባለመንካት ጠብቁ፤ እነዚህ ማስፈንጠሪያ ሊንኮች የቴሌግራም Login Page በማስመሰልና ስልክ ቁጥራችሁን እና ሌሎች መረጃችሁን በመቀበል አካውንታችሁን እስከመጨረሻው ይወስዱታል፡፡ Warning ⚠️ Recently, many people's Telegram accounts are being hacked by sending various links via Telegram message chats. These hacking links will impersonate the Telegram Login Page and take your phone number also other information to take over your account.

  • 30 окт. 2024 г.73из sostmaezen

    የህይወት ስንቅ #5 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፠፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ።

  • የሽንት መዝጋት 📍📍📍📍📍 #UROLOGY‼ ሽንት መዝጋት #TipsToAll °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° SHARE‼ Ahmed Abebe Muhammed በየአካባቢያችን አንድ ሰው ሽንቱን ዘጋው ከተባለ ከፍተኛ ስጋት ይፈጠራል። በተለይ እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ስለሽንት መዝጋት ከተነሳ በቀላሉ ሲተክዙ እንመለከታለን። እድሜው የገፋ ሰው ሽንት መዝጋት ለምን ያሳስበዋል? ★ሽንት መዝጋት ማለት በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሽንት መሽናት አለመቻል ማለት ነው። ስለዚህ ከአባባሉ ስንነሳ ሽንት በኩላሊት ከተመረተ በኋላ ወደ ውጭ ለመወገድ የሚያልፋቸው መስመሮች ጋር መዘጋት/መታገት/ ገጥሞታል ማለት ነው። ኩላሊት ላይ በተፈጠረ ሽንት ያለማምረት ችግር ምክንያት ከሆነ ስለሽንት መዘጋት አናወራም።ምክንያቱም ሽንት ስለሌለ። ★ሽንት የት ላይ ሊዘጋ ይችላል? 1)ኩላሊት ውስጥ ተመርቶ ካለቀ በኋላ ከኩላሊት ማጠራቀሚያ ክፍሎች (PCS) ማለፍ አለመቻል። Hydronephrosis ብዙጊዜ ዩሮሎጂስቱ ኩላሊትህ ውሃ ቋጥሯል ብሎ ከተናገረ በአብዛኛው ይሄንን ለማለት ፈልጎ ነው። 2)ከኩላሊት ወደፊኛ የሚወርዱት ሁለቱ ቀጭን ቱቦዎች (ureters) በሁለቱም ቱቦዎች ላይ በተፈጠረ መዘጋት (hydroureteronephrosis) 3) የሽንት ፊኛ ላይ ሆኖ ብዙ ጊዜ ከፊኛው አንገት (bladder neck) እና የሽንት መውጫ ቱቦ መገናኛ ላይ የሚፈጠር መዘጋት ሲሆን ብዙ ውስጣዊ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ(bladder outlet obstruction)። 4) የሽንት ቱቦ ላይ የሚፈጠር መዘጋት ሲሆን ከፊኛ አንገት መዘጋት ጋር ቀጥተኛ ዝምድና ስላለው ተመሳሳይ ስያሜን ይይዛል። ★ሌሎቹ የሽንት መዘጋት ሌላ ጊዜ የምናያቸው ሲሆን የሽንት ፊኛና የሽንት መውጫ ቱቦ ላይ በተከሰተ ደዌ የሚፈጠረውን የሽንት መዘጋት እንይ። ★መነሻ ምክንያቶች * የፕሮስቴት እድገት— ፕሮስቴት የሚባለው ሆርሞን ና ፈሳሽ አመንጪ እጢ በምስሉ እንደሚታየው የሽንት ፊኛ መውጫ ላይ ይገኛል። ሁሉም ወንዶች እድሜያቸው ከ50—60 በላይ ሲሆን ይሄ እጢ መጠኑ ይጨምራል። መጠኑ በሚጨምርበት ጊዜ ከፊኛ የሚነሳውን የሽንት መስመር አቅፎ በመያዝ ለመዘጋት ይዳርጋል። ሁሉም ሰው የሽንት መዘጋት ላይገጥመው ይችላል። ስለዚህ አሳሳቢ የሚያደርገው ማደጉ ሳይሆን ሽንት መዝጋት መቻሉ ነው። ምክንያቱም ማደጉ ከእድሜ መጨመር ጋር የሚመጣ ሁሉም ወንዶች ላይ የሚጠበቅ ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው። *የፕሮስቴት ካንሰር— ይሄ ክስተት ፕሮስቴት እጢ ከተፈጥሮአዊ እድገት በተለዬ መልኩ ወደ ካንሰር የተቀየረ ባህሪ ሲያመጣ ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ ሽንት መዝጋት ሊሆን ይችላል። *የሽንት መውጫ ቱቦ መጥበብ— ቱቦው ላይ በተከሰተ ቁስለት(inflammation) ወይም በተፈጠረ አደጋ ሊዘጋ ይችላል። በወጣትነት እድሜ አባለዘር ይዟቸው የነበሩ፣ ብልታቸው አካባቢ አደጋ የተፈጠረባቸው ፣ በተደጋጋሚ በሽንት መውጫ የህክምና መሳሪያ የተደረገባቸው፣ ባልታወቀ ሁኔታ(Idiopathic) ና ሌሎችም ይገኙበታል። ★ሽንት መዝጋት በሽታ ምልክቶች * የሽንት መጠን መቀነስ ወይም ከናካቴው መጥፋት *ሽንት ሲሸኑ መንጠባጠብ *የሽንት መቆራረጥ *የፍሰት ጉልበት ማነስ *ሽንት ማቃጠል፣ቶልቶሎ መምጣት *ሙሉ ሽንት ያለመውጣት ስሜት ★ሽንት የዘጋው ሰው ምን ማድረግ አለበት ሽንት የዘጋው ሰው በቀጥታ ወደ ሳይንሳዊ ህክምና መሄድ አለበት። ከቃሉ እንደምንረዳው የተዘጋ ነገር የዘጋውን ችግር ከማስወገድ ባለፈ በመንፈስም ሆነ በሌላ ዘዴ የተዘጋን ነገረ ማስወገድ አይቻልም። ★የህክምና መንገዶች ምንድናቸው የሽንት መዝጋት በሽታ እንደ አጣዳፊነቱና እንደመነሻ ምክንያቱ እንዲሁም ካመጣው መዘዝ(complication) አንፃር የተለያዩ ምርመራዎችና ህክምና ይደረግለታል። *ሙሉ በሙሉ የተዘጋ ሽንት አጣዳፊ ህመም ና የኩላሊት ጉዳት ስላለው በቀጥታ በሽንት መውጫ ቱቦ ወይም በሌላ አማራጭ በፍጥነት ሽንቱ እንዲወጣ መደረግ አለበት። *አጣዳፊ ያልሆነ የሽንት መዘጋት(ሙሉ በሙሉ አለመዘጋት) —የዘጋውን ምክንያት ምርመራ በማድግ መለየት —የፈጠረውንና ሊፈጥር የጋረጠውን መዘዝ መፈተሽ —ጊዜያዊ መፍትሄ ማስቀመጥ —ዋናውን የህክምና ዘዴ ማስቀመጥ ናቸው የሽንት ፊኛ አንገት ላይ የሚከሰተው የሽንት መዘጋት በዋናነት ምክንያቱ የፕሮስቴት እድገት በመሆኑ ዛሬ በክፍል ሁለት በሰፊው እንዳስሰዋለን። ★የተለመዱ የሽንት መዝጋት ስህተቶች *በባህላዊ ህክምና መዘናጋት ሽንቱ ወደ ኋላ በመመለስ ኩላሊትን ማዳን ወደ ማይችልበት አደጋ ላይ ይጥላል *የሽንት መዘጋት በሽታ የሚታከም መፍትሄ ያለው በአብዛኛው ህክምናው አስደሳች ውጤት ያለው መሆኑን አለመገንዘብ *ለጊዜያዊነት የሚደረገውን የሽንት ማስተንፈሻ ቱቦ( cathter) ከመጠን በላይ መፍራት፣ካቴተር የስንት ሰዎችን ህይወት ምን ያክል ኩላሊቶችን እንዳተረፈ ለባለሙያዎች እንተወው *የሽንት መዝጋት በሽታ ህክምናዎችን መካንነት የሚያመጡ ወይም የሩካቤ ስጋ ግድፈት የሚፈጥሩ አድርጎ ማሰብ * ሽንቴን ስለዘጋኝ ብሎ ውሃ መጠጣት ከማቆም የተዘጋውን ሽንት ማስወጣት t.me/wanawtena2013 Via #Dr.Ahmed Abebe

  • 25 окт. 2024 г.441из sostmaezen

    የህይወት ስንቅ #4 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፠፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ማር የምትፈልግ ከሆነ የንብ ቀፎውን መምታት አይኖርብህም። እንዲሁም አንዳንድ የህይወት ገጠመኞች ትግስት እና ብልሃት የሚጠይቁ ናቸው።

  • 22 окт. 2024 г.543из sostmaezen

    የህይወት ስንቅ #3 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፠፨፨፨፨፨፨፨ ሰው ምን ይለኛል🤔 ብለሽ ከተጨነቅሽ በህይወትሽ ምንም ነገር ማሳካት አትችይም። ምንም ነገር ብታደርጊ ሰው የሚለው አያጣም። ለነገሩ ምንም ባታደርጊም የሆነ ነገር መባልሽ አይቀርም። Bear in mind this always, የሰው ስራ #ማለት ነው❗ ይሉኝታ ሊይዝሽ የሚገባው ከፈጣሪና ከህሊና ነው። ✍ Moamin https://t.me/sostmaezen

  • ራስ ማዞር( funny turns) , መጨለም(feeling faint), ለመውደቅ ማለት፣ አዙሮት መወደቅ ሁሉም አይነታቸው ቢለያይም በተለያዩ ሰዎች የሚቀርቡ አሳሳቢ ሁነቶች ናቸው። ብዙ ሰዎችበዚህ ምክንያት በማህበረሰብ ፊት መፍራት ና ስራ መታወክ ይደርስባቸዋል። ስለዚህ እነዚህ ችግሮች በትክክል በባለሙያ መጠናትና ምንነታቸው መታወቅ አለባቸው። ለዚህም ምክንያታችን ከልብ ፣ከደም፣ከአእምሮ፣ከስነልቦናና ከሰውነት ተግባራት ጋር የተያያዙ ከመሆናቸው አንፃር ሲሆን ለዛሬ በጣም የተለመዱትን ሁለቱን እናውራ። 1) ከሰውነት አቋቋም የሚመጣ የደም እንቅስቃሴ መቀነስ(orthostatic/postural hypotension) ይህ ሁነት እንደሚከተለው ይተረጎማል። አንድ ሰው ከመቀመጫው ወይም ከመኝታው ድንገት ሲነሳ /ሲቆም ባሉት 3 ደቂቃዎች ውስጥ ተመጣጣኝ የሆነው የደም ግፊት ከ20/10 ያክል መቀነስ እና የመጨለም፣ማዞር አንዳንዴም የመውደቅ ክስተት ነው።ድንገት ቀጥ በምንልበት ጊዜ ልብ ከልብ በታች ያለውን ደም በፍጥነት መልሶ ወደስራ ማስገባት አለመቻልም አለበት። ★እድሜያቸው የገፋ ሰዎችና ግፊት ያለባቸው ላይ ከአስሩ ሶስት ላይ ሲከሰት ከ50 አመት እድሜ በታች ያሉት ግብ ከ10 ሰው በአንዱ ሊከሰት ይችላል። ከግፊት ጋር ያልተያያዘ ከሆነ ደግሞ በአንዳንድ መድሃኒቶች፣ ደም ከለገሱ በኋላ ከፍተኛ ፈሳሽ የሚያሳጡ ተግባራት ላብ፣ተቅማጥና ትውኪያ፣እንዲሁም በዝቅተኛ የፈሳሽ አጠቃቀም ምክንያት ሊሆን ይችላል። መፍትሄ:— ሃኪም ጋር በመሄድ ትክክለኛ መነሻውን በምርመራ ማረጋገጥ ዋነኛ ስራ ሲሆን ፈሳሽ ማብዛት፣ የራስን ተመጣጣኝ የደም ልኬት ማወቅና መድሃኒት አጠቃቐም ላይ በቂ ምክር ማግኘት ናቸው። 2)የስነልቦና ሁነቶች(psychological causes) 2.1—የተራራ ወይም ፎቅ ፍርሃት ማዞርና ጭልም ማለትን ሊያስከትል ይችላል( agoraphobia) 2.2—በአጠቃላይ የመደበትና መጨናነቅ ስሜት ውስጥ መገኘት(Anxiety disorder) 2.3—ለድንገተኛ ክስተቶች ተጋላጭ የሆነ መደናገጥ(panic attacks) 2.4—hysteria ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ካሉና ወይም ከመከሰታቸው በፊት ብዥታና የመጨለም ስሜት ሊከሰት ይችላል። መፍትሄ: ሁኔታውን ከስነልቦና ነርስ ወይም ሃኪም ጋር መወያየት እና ምክር ማግኘት ። ማሳሰቢያ: ከ40 አመት በታች ያሉ ሰዎች ላይ ግፊት የተለመደ ስላልሆነ የደም ግፊት መለካት መነሻው ምን እንደሆነ ለማወቅ ብዙም ላይጠቅም ይችላል። © ዶ/ር አህመድ አበበ - Urology sub

  • 20 окт. 2024 г.66из sostmaezen

    የህይወት ስንቅ #2 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፠፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ለሞኝ ሰው ድክመቱን ብትነግረው ወይም ከተቸኸው ይጠላሃል። ጠቢብ ሰው ግን ያደንቅሃል። ያም ሆኖ ጉዳዩ በቀጥታ አንተን የሚነካ ካልሆነ በቀር ማንንም ባትተች ይመረጣል። የትችት ውጤቱ ብዙ ግዜ አሉታዊ ነው። https://t.me/sostmaezen

  • 18 окт. 2024 г.66из sostmaezen

    የህይወት ስንቅ #1 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፠፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ #አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ ይበልጥ ተከታተላቸዉ። ተከታተላቸው - ወይ በመልካምነታቸው ደስ ትሰኛለህ፣ ይበልጥ ትቀርባቸዋለህ። አሊያም ተንኮል ሲሸርቡ ዳር ቆመህ ትታዘባቸዋለህ። ምንም የማታውቅ ቢመስላቸውም አንተ ግን Tv አብርተህ ፊልም እንደምታየው እንደዛው እየተመለከትካቸው ነው። ከዚያም ከህይወትህ ላይ እስከ ወዲያኛው ታሰናብታቸዋለህ።

  • ወቅታዊ #ጉንፋንና ጉንፋን መሰል የመተፈንሻ አካላት ህመምን አሰመልክቶ የተሰጠ መግለጫ‼️ 🐤የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮንና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ። 🐤ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ሙከስ መምብሬን” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡ 🐤ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው። 🐤የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል። ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣ ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ። 🐤በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከ2003 ዓ ም ጀምሮ የእንፍሉዌንዛ እና መሰል የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች እየተሰራ ይገኛል። ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። 🐤አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል1፡፡ በተጨማሪም የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 🐤ጉንፋን መሰል በሽታን ከምንከላከልባቸው መንገዶች መካከልም የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግና በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት እና የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡ 🐤ለተጨማሪ መረጃ በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል የሚቻል መሆኑን እያስታወስን ሕብረተሰቡ ሊከተላቸው የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ እና መረጃዎችን በየጊዜው የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን። የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

  • ስለ #በለስ መፅሃፍ በጥቂቱ:- መጽሓፏ ስለ ተላላፊ በሽታዎች መንስዔ፣ምልክቶች፣ የምርመራ አማራጮች፣ የመከላከያ መንገዶች ታትታለች። መጽሓፏ በዶ/ር ዑመር አብዱ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም ተጽፋለች ። ዶ/ር ዑመር አብዱ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የውስጥ ደዌ ትምህርት ክፍል ከ2005 እስከ 2011 ድረስ መጀመሪያ በሌክቸረርነት ከዚያም በረዳት ፕሮፌሰርነት ሰርተዋል። በመቀጠልም እስከ 2016 ድረስ በጋምቢ አጠቃላይ ቲቺንግ ሆስፒታል ሲያገለግሉ ቆይተዋል። አሁን ላይ አዲስ አበባ ቤተል በሚገኘው አል ዓፊያ ስፔዣላይድ የህክምና ማዕከል እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መፅሃፉ 60 የሚሆኑ በኢትዮጵያ የተለመዱ ተላላፊ በሽታዎችን በስድስት(6) ምዕራፍ ከፋፍሎ አስቆምጦልናል፤ ስዕላዊ መግለጫ ያለው መሆኑም ማራኪ፤ ለመረዳት ቀላል አድርጎታል። ምዕራፍ-1: የፕሮቶዞዋ በሽታዎች ምዕራፍ-2: የሆድ ትላትልና ተዛማች በሽታዎች ምዕራፍ-3: የባክቴሪያ በሽታዎች ምዕራፍ-4: የቫይረስ በሽታዎች (የDNA virus በሽታዎችና የRNA virus በሽታዎች) ምዕራፍ-5: ኤች አይ ቪ ኤድስ እና ግብር አበሮቹ ምዕራፍ-6: የፈንገስ በሽታዎች የጤና ባለሙያዎችና የጤና ተማሪዎች በዋናነት ይሄ መፅሃፍ ሊያልፋችሁ አይገባም። መፅሃፉ የስራና የንባብ ልምድ ባለው ሲኒየር ሀኪም በአማርኛ ቋንቋ በጥንቃቄ የተዘጋጀ በመሆኑ፤ ከ115 በላይ ዋቢዎችን(References) የተጠቀመ በመሆኑ ለጥናትና ምርምር ጨምሮ ለተለያየ ነገር ልትጠቀሙት ትችላላችሁ። ሸምድዳችሁ ሳይሆን ገብቷችሁ ማህበረሰባችሁን ታገለግሉበታላችሁ። መፅሃፉ አሁን ላይ አዲስ አበባ እና ባ/ዳር ይገኛል። ወደፊት በሁሉም የክልል ከተሞች የሚደርስ ይሆናል። ባ/ዳር ላላችሁ በ ስ.ቁ:- 09 23 45 20 62 / 09 94 22 17 14 ደውላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ። መፅሃፉ ባላችሁበት ይደርሳችኋል።

  • በዶ/ር ዑመር አብዱ (ረ/ፕሮፌሰር) የተዘጋጀችው << በለስ: በኢትዮጵያ የተለመዱ ተላላፊ በሽታዎች>> የተሰኘችው መፅሃፍ ባ/ዳር ደርሳለች። አንባቢያን በ09 23 45 20 62 / 09 94 22 17 14 ይደውሉ፣ ይዘዙ፣ ያንብቡ!

  • 29 сент. 2024 г.782из sostmaezen

    አንድ ጀለሴ በህይወቴ ነፍ ስህተት ሰርቻለሁ አለኝ። እናም አሁን ከስህተቶቼ ብዙ ተምሬያለሁ። በቀጣይ ህይወቴም ቢሆን ብዙ መማር ስለምፈልግ ብዙ ስህተት መስራት አለብኝ አለ። ብዙ ስህተት መስራት የሚቻለው ብዙ ነገር በመሞከር ነው። ካልሞከርክ አትሳሳትም #ትወድቃለህ እንጂ። ይህ #የፍርሃት ውጤት ነው። ከሞከርክ ግን ይሳካልሃል ወይም ስህተት ሰርተህ ትማራለህ። ይህንን #መኖር(ኑረት) እንለዋለን። እያወቁ መሳሳት አውቆ አጥፊነት ነው። ለማወቅ፣ለመስራት፣ለማሳካት መሳሳት ግን ሰው መሆን ነው። መልካም እሁድ🙏

  • << በለስ፥ የተለመዱ ተላላፊ በሽታዎች በኢትዮጵያ >> የተሰኘቸው መፅሃፍ በመጨረሻም ታትማ ለንባብ በቅታለች። ደራሲው ዶ/ር ዑመር አብዱ "የአብራኬ ክፋይ" ናት ያላት መፅሃፏ፤ ማንኛውም ሰው አንበቦ በቀላሉ ሊረዳው በሚችልበት ቀለል ባለ አማርኛ ተዘጋጅታ አንብቡኝ እያለች ነው። ያም ሆኖ ለጤና ባለሙያችና ተማሪዎች ላቅ ያለ አበርክቶን ይዛለች። ለማዘዝ በ 0977581422/0955196252 ይደውሉ።

  • ጉበት 75% ያክሉ እንኳን ተቆርጦ ቢወጣ ወይም ለሌላ ሰው ቢለገስ፤ የቀረው ክፍል ራሱን በማሳደግ የተለመደ ስራውን ያከናውናል። ያም ሆኖ የጉበት ስራ ብዙ ነው። ወደ ሰውነት የገባ ነገር ወደ ስር ገብቶ ጥቅም መስጠት ካለበት፤ መጀመሪያ የጉበትን የፍተሻ ኬላ ማለፍ ይኖርበታል። የምትወስዱት እንክብል መድሃኒት፣ የምትጎነጩት አልኮል በቀጥታ ጉበት ላይ ተፅእኖ ያሳድራል።እነዚህ ነገሮች ከልክ በላይ ከተወሰዱ ጉበታችሁን እስከወዲያኛው ከጥቅም ውጪ ያደርጉታል። ያኔ የሚታደስ የቀረ ጉበትም አይኖርም።

  • 22 сент. 2024 г.732из sostmaezen

    ሶቅራጥስ የፍልስፍና አባት። ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት ብዙ አመታት በፊት ምድር ላይ ተከስቶ፤ ማሰብን ኑሮ ያስተማረ ታላቅ ግሪካዊ ሰው ነው። ማሰብ ህይወትን መመርመር ነው። ያልተመረመረ ህይወት ሊኖር የሚገባው አይደለም እንዲል ሶቅራጥስ። ይህ ታላቅ ሰው thinkን ገሸሽ አድርገው tank ለሚያስቀድሙቱ ስጋት ነበር። ለዚያም ነበር በባለጥቅመኞች ሴራ በባለጊዜዎች መርዝ ከዚህ አለም የተሸኘው። እሱ ግን ድንጋይ ሲወረወርበት ፍሬ የሚመልስ ዛፍ ነበርና እየሞተም እንድናስብ አስተምሮናል። "ሳያስቡ ከመኖር እያሰቡ መሞት ይሻላል " በማለት።

  • 20 сент. 2024 г.701из sostmaezen

    ባለስልጣን ነህ? ባለሃብት...? ምሁር...? ቆንጆ ነሽ? የተስተካከለ የሰውነት አቋም አለህ? ተፅእኖ ፈጣሪ ነህ?.....በጣም አሪፍ ነው። I appreciate that! But remember this always...አንተ/ቺ/ ሰው ብቻ ነህ/ሽ/። ያለህ እና የሆንከው ነገር ይህን ተፈጥሮህን እንድትዘነጋ አያድርግህ።

  • 15 сент. 2024 г.651из sostmaezen

    ማይክል ሓርት (Micheal H.Hart) በ1978 ባሳተመው "The 100: A Ranking of the Most Influential Persons in History" በተሰኘው መፅሃፉ ላይ የአለምን ቅርፅ የቀየሩ ታላላቅ ስብእናዎችን በዘረዘረበት መፅሃፉ ላይ አንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው ነብዩ ሙሐመድን(570 - 632) ነው። በማስከተልም አይዛክ ኒውተን(1643 - 1727)፣ እየሱስ ክርስቶስ(4 - 30)፣ ቡድሃ...እያለ 100 ሰዎችን ያስቀምጣል። ይህን ደረጃ ለማውጣት 30 የሚሆኑ መስፈርቶችን ተጠቅሟል። ሙሐመድ ማን ነው/Who is Muhammed/? "The Best of Creation" በሚል በAmjad Mahmood ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው መፅሃፍ Muhammed ebn Abdellah የዛሬ 14 መቶ አመታት በዛሬዋ መካ ከተማ እንደተወለደ ይናገራል። የዘር ግንዱንም ወደኋላ ሲቆጥር የአብረሃም ልጅና የኢስሃቅ ወንድም ከሆነው ከእስማኤል ጋር ያገናኘዋል። ይህ ታላቅ ሰው በማህበረሰቡ ዘንድ አሚን (ታማኙ) እየተባለ ይጠራ እንደነበርም ያወሳል። ከዛ በኋላ ግን 40 አመት ሞልቶት ከአምላክ መለኮታዊ መገለጥ መጥቶልኛል ሲል ህዝቦቹ ብዙ እንግልት እንዳደረሱበትና ከአገርም እንዳስወጡት ታሪክ ያስረዳል። ይህ ታልቅ ሰው አለም ላይ ከተከሰቱ ታላላቅ ስብአናዎች ቀዳሚ ያደረገው በተለያዩ የህይወት ዘርፎች ላይ የተሳካ አሻራን በማስቀመጡ ነው። የሚፈራ የጦር ጀነራል፣ ከሚስቱ ጋር ሩጫ የሚወዳደር ተወዳጅ ባል፣ ልጆቹ በስስት የሚያዩት መልካም አባት፣ ህዝቦቹ ለመሰዋት የተዘጋጁለት የተዋጣለት መሪ፣ ለሴቶች መብት ትኩረት የሰጠ፣ በጎሳና በዘር መለያየትን ያጠፋ፣ ሃይማኖታዊ ህግን (Shari'a) ያፀና....ነው። In short, in every aspect of human life መልካም አርአያ መሆን የቻለ ሰው ስለሆነ አሁን ላይ ቁጥር አንድ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰው በሚል አለም ያስበዋል። ይህ ታላቅ ሰው በ63 አመቱ ከዚህ አለም በሞት የተለየ ሲሆን። በ23 አመት ወስጥ ከ100,000 በላይ ተከታይ ማፍራት ችሏል። አሁን ላይ የአለማችን ሲሶ ህዝብ ይከተለዋል። Prophet Muhammed(pbuh) የተወለደውም የሞተውም በአረቦች የቀን አቆጣጠር በRabi'al awol 12ኛ ቀን ላይ እንደሆነ ይነገራል። ነብዩ ሙሐመድ(ሰዐወ) የተወለዱበትን ቀን በፆምና በፀሎት ያሳልፉ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ References: 1) "The 100: A Ranking of the Most Influential Persons in History" by Micheal H.Hart published in 1978 2) Muhammad the best of creation; Sayyid Muhammad ibn Alawi al-Maliki al-Hasani; translated by Amjad Mahmod 3) Prophet of Mercy; Shaykh Abul Hasan Ali Nadawi 4) ረሂቀል መኽቱም; የነብዩ ሙሐመድ(ሰዐወ) የህይወት ታሪክ; ሁለተኛ እትም ሰኔ 2002

  • 14 сент. 2024 г.62из sostmaezen

    በእርግጥ ይህን ተግባሩን እንደ መልካም አርአያ ላትወስዱት ትችላላችሁ። ነገር ግን አሪፉ በቀል የስኬት ማማ ላይ መውጣት ነው ብለው ለሚያምኑ ሰዎች ተጨማሪ ማረጋገጫ መሆን ይችላል።