መልካም-ሰው....,,Visit Ethiopia🟢🟡🔴
Статистика#መልካም_ሰው 💚💚💛💛❤️❤️ ነገር ሁሉ ለበጎ እዲደርግ ነው ሰው መርዳት ምግባር ስራ አድርገው ለሰው ማሰብህ በቂው ደግነት ነው ይኑርህ አንተ ሰው ግብረገብነት ሀብት ቢቻው ለፍርድ አይሆን ዋስ ንብርት መልካም ሰው ሁን ያጎናፅፋል ባለፀጋነት @Halemikael 📥📥📥.Join.📥📥📥 ......... @Meku_24 ........... @Melikamenetlerasnew
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 84
- 1/48двое суток
- 96
- 1/72трое суток
- 103
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
የምትመለከቱዋት ወጣት ታዳጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በአጥንት ካንሰርን ህክምና ላይ ትገኛለች በሽታው ከታወቀ አንድ አመት ሆኗታል በበሽታው ምክንያትም አንድ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል ሆኖም ግን ኤልሮኢ ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን እየተከታተለች ነው አሁን ግን በሽታው ወደ ሳንባዋ በመሠራጨቱ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ Heal Venture Medical and Surgical Center በ ICU ትገኛለች ሆኖም ግን በአሁን ሰአት ላይ የሆስፒታሉ ወጪ በቀን ከ50.000ብር ነው ከቤተሰብ አቅም በላይ ስለሆነ የኛን እርዳታ ትሻለች CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay እህታችን ትፈልገናለች እንድረስላት 🙏
" በልቡ ውስጥ ፍቅር የሌለው ሰው ምንም ያህል ሀብታም ቢሆን በመንፈስ ግን ድሃ ነው።እግዚአብሔር የሚያድረው በትላልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ብቻ ሳይሆን ይበልጥ የሚያድረው እርስ በእርስ በሚዋደዱና በፍቅር በአንድነት በሚኖሩ ሰዎች ልብ ውስጥ ነው። ፍቅር ካለህ እግዚአብሔር ካንተ ጋር አለ። " ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
∞∞ ∞∞ ∞∞ ∞∞ ∞∞ ታምርህን ሰምቶ እንዳላመነህ፣ አብርሖትህን እንዳልለመነህ፣ ከጅህ በረከት እንዳልጠገበ፣ ባንተ ሲጎበኝ፧ ቤትና 'ደጁ እንዳልጠበበ፣ ° በክንድህ ስንቱን እንዳላለፈ፣ ጽልም እና ሞቱን እንዳልገፈፈ፣ ሃይልህን አይቶ እንዳልሰከነ፣ ከግሮችህ ትቢያ እንዳልመነነ፤ ° እንደተረሳ እንደማይጠቅም፣ ድንገት አብርቶ በሚጠፋ አቅም፤ ዘብ እንደሌለው እንደባይተዋር፣ አውታሩ ጎድሎ እንዳለ ክራር፥ ° በኑሮ ቅኝት እያቀለለህ፣ ሸርተት እያለ የተላቀቀህ፣ እንዲህ ያለ ሰው አይተ ታውቃለህ?! #እንደኔ_ያለ! [ ዓለም ]
በምድር ላይ ለዘላለም የሚኖር ምንም ነገር የለም። "ወፍ በህይወት እያለ ጉንዳኖቹን ይበላል ወፉ ሲሞት ደግሞ ጉንዳኖቹ ወፉን ይበሉታል" ጊዜ እና ሁኔታዎች በማንኛውም ጊዜ ሊለዋወጡ ይችላሉ። በህይወት ውስጥ ማንንም አታሳንስ ወይም አትጉዳ። ዛሬ ጠንካራ ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ጊዜ ከአንተ የበለጠ ጠንካራ መሆኑን አትርሳ! አንድ ዛፍ አንድ ሚሊዮን ክብሪቶችን ይሠራል፣ እና አንድ የክብሪት እንጨት አንድ ሚሊዮን ዛፎችን ያቃጥላል፣ ስለዚህ አንድ አሉታዊ ነገር በሚሊዮን የሚቆጠሩ በህይወትህ ውስጥ ባሉ አዎንታዊ ነገሮች ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድር… #ስለዚህ_መልካም_ሁን_መልካምም_አድርግ...
እግዚአብሔር ሁን ያለውን ጉም አይጋርደውም፤ ድምጽን በድምጽ የሚሽር የበላይ ዳኛ ነው። እርሱ ያለው ከአድማስ እስከ አድማስ ያለከልካይ ይሆናል። #ተመስገን
"ሰዉ የፀለየዉን ይረሳ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ግን የሰማዉን አይረሳም የነገሩትን የማይረሳ የታመነ ረዳት ነውና።"
ስሚኝማ የኔ ቆንጆ😊 ብዙ የዘገዩ የምመስሉ ፀሎቶች የተረሱ የምመስሉ እምባዎች ልኖሩሽ ይችላሉ ግን በዚህ ማለዳ አንድ ነገር ልንገርሽ ይህ ልብሽን ይደግፈዋል የኔን እንደደገፈው ሁላ ማለት ነዉ ፀሎቶችሽ እምባሽ ዋጋ አለዉ እንድሁ አልባከነም🥹 ሰው የፀለየውን ይረሳ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ግን የሰማውን አይረሳም🙇። Amen🙏
አገር ንቆ..ሰው አይፀድቅም!
https://t.me/myPoems396
ህይወት ዘላቂ ሂደት ናት። በእያንዳንዱ ቀን የምታነበው፣ የምትሰማው ወይም የምታየው ነገር አንተን ማሻሻል አለበት። ዕውቀት ሀብት ነው፤ አጠቃቀሙ ደግሞ ጥበብ ነው። 🔗share - @mtuk_hasab እንዴት አረፈዳችሁ 🌅
መልካም-ሰው....,,Visit Ethiopia🟢🟡🔴 pinned a photo
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ° ብሸፍተም ሰው ስገድል.. ስትጠራኝ ሳትሸነግል.. ቀስቴን ጥዬ ተሸነፍኩኝ አንተን ሳይህ 'ረገፍኩኝ፨ ድንገት ራደች ሰዉነቴ፣ ተፈታልኝ ሰንሰለቴ፨ ° ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትለውጥ ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትጠራ፣ ጨካኙን ልብ ደግ ያልሰራ፣ ታኖራለህ ስታራራ፨፨ ° ለካ እንዲ ነህ ስታንኳኳ፣ ጻዲቅ ሆነ ገዳዩ እንኳ፨! [ዓለም]
በውነት ፈጣሪ የለም ❓❓ አንዳንድ ጊዜ በባዮሎጂ ትምህርት ስለ ዲ.ኤን.ኤ (DNA)🧬፣ ስለ ነርቭ ሲስተም🧠 ፣ ስለ ደም ዝውውር🫀 እና ስለ አተነፋፈስ ስርአት🫁... ስማር በጣም ይገርመኛል። በፊዚክስ ደግሞ ስለ ምድር ህግጋት 🌏 ስላጠቃላይ ዩኒቨርስ 🪐ስማር ደግሞ ‘አንተ ምን ያህል ጠቢብ ነህ❗’ ብዬ ፈጣሪን አደንቃለሁ። በ ኬሚስትሪ ደግሞ ስለ አቶም⚛ አወቃቀር ሳጠና ስራህ ግሩም እላለሁ። ሞትን⚰ሳስብ ደግሞ ይበልጡኑ ለማወቅ ጓጓለው.. በውኑ ይህ ሁሉ ግሩም ስርአት በዝግመተ ለውጥ (Evolution) ብቻ የመጣ ነው ❓ ይህ አባባል፣ አንዳንዴ ህፃናትን ለማሳመን የሚነገር ተረት ተረት ይመስለኛል። በውኑ ይህ ሁሉ ጥበብ በአጋጣሚ የመጣ ነው❓ወይስ አእምሮዬ ብቻ የፈጠረው ቅዠት❓ በፍፁም❗ ይህ ሁሉ በአእምሮዬ የተፈጠረ ከሆነ.. አእምሮዬ ራሱ የፈጣሪ ልዩ ጥበብ ውጤት ነው። በእሱ ተፈጥሮ መደነቅ እንጂ፣ የፈጣሪን መኖር መካድ አለመኖርን መስበክ ካለማሰብ ወይም በጣሙን ከማሰብ የመጣ ነው። የራስን እውነት ሰርቶ ትክክለኛውን እውነት መሸሽ ነው። አንዳንዶች በጣም እውነት ለማረግ ይሞክሩና ውሸት ይሆንባቸውል 😂 የናንተ ሃሳብ ይፈለጋል... 🔗share - @mtuk_hasab
ዮም📚
ለፀሐይ ፍካት ማን ይፈግጋል? ለሰማይ ንጣት ማን ይደግሳል? ማን ግድ ብሎት ማን ስሜት ሰጥቶት? ከምድር አልፎ ሰማዩን አይቶት?¡ ዘልቋል ከውስጥኽ?ገብቶሃል ቅኔው? ምን ብትነጠፍ ሰማይ ብትሆነው የያዘው እክል እስካልለቀቀው፧ ከኑሮ አሻግሮ ግትር አንገቱን እስካላዞረው፧ መቼም አያይህ ያልቀናለት ሰው! //ከቀን የተቀዳ// [ዓለም]
በአሸዋ ላይ.... 🪢🪢🪢🪢🪢 በአንድ ወቅት ሁለት ጓደኛሞች በረሃ አቋርጠው በመጓዝ ላይ ሳሉ መንገድ ላይ በተፈጠረ ክርክር አንዱ ጓደኛ ሌላውን በጥፊ መታው። የተመታው ሰውዬ በጣም አዘነ ነገር ግን ምንም ሳይናገር አሸዋ ላይ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ዛሬ የቅርብ ጓደኛዬ በጥፊ መታኝ።" ጉዞአቸውን ቀጠሉ። በኋላም አንድ ትልቅ የውሃ ምንጭ አገኙ። ውሃው ውስጥ ሲገቡ ግን በጥፊ የተመታው ሰውዬ በድንገት መስጠም ጀመረ። የደበደበው ጓደኛው በፍጥነት በመድረስ ከሞት አዳነው። ሰውየው ከውሃው ሲወጣ በጣም ተደሰተ። በዚህ ጊዜ አንድ ትልቅ ድንጋይ አገኘና ድንጋዩ ላይ እንዲህ ብሎ ቀረጸ "ዛሬ የቅርብ ጓደኛዬ ከሞት አዳነኝ።" ይህንን የተመለከተው ጓደኛው በመገረም እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ "መጀመሪያ ስመታህ አሸዋ ላይ ጻፍክ፤ አሁን ደግሞ ስላዳንኩህ ድንጋይ ላይ ቀረጽከው፤ ለምን?" "ሰው ሲያስቀይመን በአሸዋ ላይ መጻፍ አለብን፤ ምክንያቱም የይቅርታ ንፋስ መጥቶ በቀላሉ እንዲሰርዘው። ነገር ግን አንድ ሰው መልካም ነገር ሲያደርግልን በድንጋይ ላይ መቅረጽ አለብን፤ የትኛውም የቂም ንፋስ ሊያጠፋው እንዳይችል!" አለው 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ሰላማዊ ሆናችሁ እንድትኖሩ ከፈለጋችሁ ቂም የያዛችሁበትን ነገር እና ሰው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቅር በሉና የራሳችሁን ኑሮ ኑሩ! ቂም ይዛችሁ ልባችሁን አታጨናንቁት! ይቅር በሉ፣ ይቅር እንድትባሉ! ╭══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╮ ቬነስያ ╰══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╯
ያለህን ስጥ 🪢💥🪢💥 አንድ እድሜያቸው የጠና ማየት የማይችሉ ሽማግሌ ሁል ጊዜ መንገድ ዳር ተቀምጠው ይለምኑ ነበር:: ሁሌም በሚለምኑበት ወቅት አንድ የማይለያቸው ጽሑፍ የያዘ ካርቶን ነበር:: በካርቶኑ ላይ " ማየት አልችልም እርዱኝ " ይላል ። አላፊው አግዳሚም ሰው ጽሑፉን እያየ በአጠገባቸው ያልፋል ፡፡ አንዳንዱ ያለውን ጣል ጣል ያረጋል የቀረው ደሞ ትቶ ያልፋል ፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን በጠዋት ይህ ተከሰተ ፡፡ ከዚህ በፊት የማያውቁት ሰው ወደ እሳቸው ቀረብ ብሎ ጽሑፍ የያዘውን ካርቶን አንስቶ ጫር ጫር አድርጎ መልሶ ካስቀመጠው በኋላ ምንም ሳይሰጣቸው ጥሎ ሄደ ፡፡ ሽማግሌው በሚሰሙት ነገር ግራ ተጋቡ ። ሰውየው አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ብዙ ብር ሊሰጣቸው አልያሞ ችግራቸውን ሊጠይቃቸው መስሎቸው ነበር:: ነገር ግን ምንም ሳይል ነበር ጥሎአቸው የሄደው ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን የሳቸውን ሁኔታ የሚቀይር ነገር ተፈጠረ ፡፡ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ያለውን እያወጣ ይሰጣቸው ጀመረ ፡፡ ከሳንቲም አልፎ ብዙ ሰዎች ብር በእጃቸው ይሰጡአቸው ጀመር ። ሽማግልው ግራ ተጋቡ ቆይ ያ ሰውዬ ምን አርጎ ነው የሄደው ብለው ራሳቸውን ሲጠይቁና ግራ ሲጋቡ ዋሉ ፡፡ በዛች ሰአት ብቻ ሰዎች የረዱአቸው ወር ሙሉ ለምነው ካገኙት ይበልጥ ነበር ፡፡ በዚህ ግርምት ቆይተው ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደሳቸው ቀረበ ፡፡ እሳቸውም በጥርጣሬ "ቅድም አንተ ነህ ጽሑፍ የጻፍከው ? ቆይ ምን ብለህ ነው የጻፍከው? " ልጄ አሉት ። ሰውየውም በደስታ " አባቴ በእርግጥ በገንዘብ አልረዳሆትም ነገር ግን ጽሑፉን እንዳየሁ የተጻፈው ነገር ሰዎች እንዲረዱዎት ብዙ እንደማያስችል ስላወኩ የተጻፈውን ነው የለወጥኩት ፡፡ መጀመሪያ "ማየት_አልችልም_እርዱኝ" ይል ነበር እኔ ደግሞ ከጀርባው "ዛሬ_ቀኑ_ደስ_ይላል_ግን_እኔ_አላየውም" ብዬ አስተካከልኩት ፡፡ አዩ አባቴ ሰው ይህን ሲያነብ የእርሷን አለማየት ሳይሆን የራሱን ማየት ስለሚያስብ በደስታ ለእርሶ ያለውን ይለግሳል ። አላቸው ፡፡ ሽማግሌው እጁን ከያዙ በኀላ እያመሰገኑት እጁን ይስሙ ጀመር ፡፡ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ሰውን በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሃሳብም መርዳት ይቻላል። ⊰ቬ⊱⊰ነ⊱⊰ስ⊱⊰ያ⊱: ╭══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╮ ቬነስያ ╰══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╯
ይቅር በላቸው[ፀሎት] የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሀብቶች... _ _ _ ሸንበቆ ድግፍ እፍኝ ትምክህቶች መውደቂያ ያጡ ድፍን ተምኔቶች! ይቅር በላቸው... የተጣደፉ ፈራጅ ከንፈሮች ያልተማከሩ ልብና አፎች! ያልደነገጡ ድንድን ስሜቶች ያልተረጋጉ ሰንካላ እምነቶች! ይቅር በላቸው! ይበልጥም... የሞገቱኝን ሽራፊ ቀኖች! ያስጀነኑኝን ጎዶሎ ሃብቶች! _ _ _ ያስመከቱኝን ውዥቅ ቀለማት ያስፎከሩኝን ግንጥል ድምቀታት! ይቅር በላቸው! አልደበቁኝም ልሽሽው ካልኩት አላስጣሉኝም ከተሯሯጥኩት አላወጡኝም ከሰው ትከሻ ወይ አልሰጡኝም ዝና ሙገሳ፨ ይቅር በላቸው! ማራቸው ያለህ ልቤ አስታኮ፧ አብረህ አስበኝ ሊልህ ነው እኮ፧፧ [ዓለም]