መንፈሳዊ የሕይወት ምክሮች
Статистика" እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።"ዮሐንስ 13:35 ➭ሀሳብ አስተያየት እና ጥያቄ ካላችሁ 👉 t.me/Tsega_zeab1 ይህ ቻናል ብዙ ስነ ልቦናዊ፣አእምሮአዊ እና ማህበራዊ ችግር ለሚያጋጥማቸው ወንድሞች እና እህቶች መፍትሔ ለማምጣት የምንማማርበት፣ የምንመካከርበት እና የምንወያይበት ቻናል ነው። ↪️ግንቦት ፳፻፲፮ ዓ.ም ተከፈተ።
- Последний пост
- 31 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 125
- 1/48двое суток
- 143
- 1/72трое суток
- 154
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የአባታችን አቡነ ተክለ ሀይማኖት እረድኤት በረከታቸዉ ይደርብን❤️❤️❤️🤲.
https://www.facebook.com/share/196qXEW7mp/ የሙት ታሪክ ቆፋሪዎች እና የጃን ሜዳው ቁማር ሲጋለጥ😄 አንዳንዴ የዘመናችንን የአክቲቪስት ፖለቲካ ሳስተውል ነገሩ ልክ እንደ ጠላ ቤት ሰካራም ሙግት ይሆንብኛል። ትላንት ማታ የተፈጠረውን እረስተው ከሶስት መቶ ዓመት በፊት "አያትህ አያቴን በገልመጥመጥ አይቶታል" ብለው በትር ይማዘዛሉ። አሁን ደግሞAdugnaw Muche እናAhmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል የተባሉ የዘመናችን የቁርሾ ነጋዴዎች በታሪክ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ የዛገ ሚስማር ሲፈልጉ ውለው "ጃን ሜዳ የኛ ነውና ካልመለሳችሁ" የሚል አስቂኝ ኮሜዲ ይዘው ብቅ ብለዋል። የጥፋት ኦርኬስትራው፡ አህመዲን እና አዱኛ አህመዲን ጀበል ማለት እኮ ታሪክን እንደ ማር ሳይሆን እንደ መርዝ ሲያላምጥ የኖረ ሰው ነው። ሰው ቤተ-መጻሕፍት የሚገባው እውቀትና ጥበብ ፍለጋ ሲሆን እሱ ግን ማህደር የሚበረብረው አቧራ የጠጣ የጥላቻ ዶሴ አገኝ እንደሁ ብሎ ነው። አሁን ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ታቦት አውጥተው በዝማሬና በእልልታ የሚያከብሩበትን ጃን ሜዳ "የመውሊድ ሜዳችን ነው" ብሎ ካልነጠቅን እያለ ይደነፋል። ነገሩ እኮ "ለመስገድ ቦታ ጠፋን" የሚል የእምነት ጥያቄ አይደለም "እንዴት የሌላው እምነት ተከታይ በሰላም በዓሉን ያከብራል?" የሚል የአጋንንት ቅናት እንጂ። አዱኛ ሙጬ AKA የጀበሉ ቆለጥ ደግሞ የዚህ የጥፋት ኦርኬስትራ ታማኝ አታሞ መቺ ነው። አህመዲን በጨለማ የቆፈረውን የሙት ታሪክ አፅም አዱኛ በፌስቡክ አደባባይ እያጠበ ያሰጣዋል። "በልጅ እያሱ ጊዜ እንዲህ ነበር በምንሊክ ጊዜ እንዲያ ነበር" እያሉ መቶ ዓመት ወደኋላ ሊጎትቱን ሲታገሉ ሳይ ጤንነታቸው ያሳስበኛል። "በእንትና ዘመን የነበረው መሬት የእኔ ነው" ከተባባልንማ ሁላችንም ጓዛችንን ጠቅልለን ወደ አፋር በረሃ ሉሲ ጉያ ስር መግባታችን እኮ አይቀርም! ታሪክ ማለት መማሪያ እንጂ መጨራረሻ አታድርጉት። የሜዳው ጉዳይ ወይስ የሴራው ጉዳይ? እውነት ለአላህ ብሎ መሬት ለመስገጃነት ከፈለገ ከከተማው ጥግ እስከ ጫፉ ሜዳው ሞልቷል። ለነገሩ በኢትዮጵያ ያለቀው የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም እንጂ የፈጣሪ መሬት መች አለቀ? መንግስትን ጠይቆ ህዝብን አስተባብሮ ከጃን ሜዳ የሰፋ፣ ከጦር ኃይሎች ግቢ ያመረ የመስገጃ ቦታ ማሰራት እየተቻለ፣ ለምን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መዓዛ ያለበትን ቦታ ማማተር አስፈለገ? ምክንያቱም ግባቸው ሱጁድ ማውረድ ሳይሆን አጀንዳ ማውረድ ነው! አላማቸው በሰላም አብሮ የሚኖረውን ህዝብ፣ በእምነት ስም አጋጭቶ ዩቲዩብ ላይ ቪው (Views) ማለብ ነው። እነዚህ ሰዎች እኮ፣ ቤተክርስቲያን እና መስጊድ ተቃቅፈው ባዩ ቁጥር፣ ልክ እንደ እርኩስ መንፈስ በውስጣቸው ህመም የሚሰማቸው የእኩልነት ፀሮች ናቸው። "ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው" እንዲሉ ህዝቡ በረሀብና በኑሮ ውድነት እየተንገበገበ እነሱ ግን በጠገበ ሆዳቸው የሜዳ ክርክር ይገጥማሉ። ባጭሩ አዱኛ እና አህመዲን ከታሪክ መቃብር ውስጥ እያወጡ ሊግቱን የሚሞክሩት ፖለቲካ በውሃ ውስጥ እሳት የማንደድ ያህል ከንቱ ድካም ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የነቃው ሰሞኑን አይደለም መቻቻልን እና መከባበርን ከደም ስሩ ጋር ያዋሀደው የዛሬ ሺህ ዓመት ነው። ስለዚህ የጃን ሜዳውን ቁማር ትታችሁቭየራሳችሁን መንፈሳዊ ድህነት (Bankruptcy) የምትሞሉበት ሌላ የዩቲዩብ ኮንቴንት ብትፈልጉ ይሻላችኋል! ልኡል ነኝ ከወሎ ሰማይ ስር👍 #Follow and #Share my fb page. https://www.facebook.com/tsega.zeab1224
#ሐምሌ_19_ቅዱስ_ገብርኤል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል 💞 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” (ሉቃ. ፩፥፲፱) " እንደምን አደራችሁ ዛሬ ሐምሌ 19 ይህች ቀን ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ያወጣበት ቀን ነው።በረከታቸው ይደርብን እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!🙏 የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነትና ጥበቃ በሁላችንም ላይ ይደር🤲 የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃ፣ የጻድቃን ምልጃ፣ የሰማዕታት በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን🙏 ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶነ እሳት ያዳነ መልአክ እኛንም በመልአኩ ፈጣን አማላጅነት ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይጠብቀን፤ በሃይማኖትና በምግባር አጽንቶ ለክብሩ መንግሥት ያብቃን።
ስለአገር ባለቤትነት የእስልምና እምነት መምህራን ስለ አገር ባለቤትነት እያወሩ ነው። በጣም እናመሰግናለን! በሩ ተከፍቶልናል! እኛም እናውራ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች የአገር ባለቤትነታቸውን ማን ሰጣቸው? ከየት አገኙት? አገሩ የማነው? የመሠረታት ማነው? በምን መርኆች ላይ ተመሠረተች? "የክርስቲያን ደሴት" ለምን ተባለች? የተሟላ፤ የተተነተነ፤ የታወቀ፤ የተራቀቀ ታሪክና መልስ ስላለን፡ ስለአገራችንና እኛ ስለምናውቃቸው ባለቤቶቿ እናውራ። እኔ ቀድሜ ነው ማውራት የጀመርኩት። ኦርቶዶክሳዊ ኹሉ ማውራት አለበት። በሩ ተከፍቶልናል። ተፈቅዷል። አውሩ!! የባለቤትነት መብት መጠየቅ ይቻላል። ባለቤትም መኾን ይቻላል። ባለቤቶችም ነን። በኢትዮጵያዊነትና በአገር ባለቤትነት መብት፡ እኛን ጽዮናውያንን የሚቀድመን የለም። ለትንሽ ጊዜ ባለቤት መኾናችንን ረስተነው ነበር። አሁን እያስታወስን ነው። በገዛ እጃቸው ቆስቁሰው እያስታወሱን ነው። እንኳን የኢትዮጵያ፡ የአፍሪካ ባለቤቶች ነን። ኹልሽም በማርያም መቀነት ልትጠቀለዪ ነው፤ ተዘጋጂ። ©️Dr Meskerem Lechisa
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ ሐምሌ ፭ ቀን የዓበይት ሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስንና የቅዱስ ጳውሎስን የሰማዕትነት ዕረፍት መታሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ክብር ታከብራለች። #ቅዱስ_ጴጥሮስ ከቤተ ሳይዳ ዓሣ አጥማጅነት ተጠርቶ የሐዋርያት አለቃና የቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ፣ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ ቁልፍ የተቀበለ ታላቅ አባት ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ በልዩ ልዩ ሀገራትና በሮም አደባባይ ወንጌልን ሲሰብክ፣ ሙታንን በማስነሣት፣ ድውያንን በመፈወስና የጥፋት አገልጋይ የነበረውን ስምዖንን በማሳፈር አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል። በመጨረሻም በንጉሥ ኔሮን ትእዛዝ የሞት ፍርድ ሲፈረድበት፣ "እንደ ጌታዬ ቀጥ ብዬ ልሰቀል አይገባኝም" በማለት በትሕትና ቁልቁል በመሰቀል የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል። #ቅዱስ_ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን መብራት የተባለው ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ምእመናንን አሳዳጅ የነበረ ቢሆንም፣ በደማስቆ መንገድ በተገለጠለት የጌታችን ጥሪ ምርጥ እቃ የተባለ ሐዋርያ ለመሆን በቅቷል። በብዙ አገራት እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ወቅት መገረፍን፣ መታሠርንና በእሳት መቃጠልን የመሳሰሉ ጽኑ መከራዎችን በጸጋ በመቀበል፣ ድንቅ ተአምራትን በማድረግና ዐሥራ አራት መልእክታትን በመጻፍ ለክርስቲያኖች የሃይማኖት መሠረት ጥሏል። እርሱም በንጉሥ ኔሮን ትእዛዝ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል። የእነዚህ የሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ሕይወት፣ ትምህርትና ተጋድሎ እስከ ዘላለም ድረስ ለምእመናን የጽናት፣ የእምነትና የድኅነት መንገድ ሆኖ ይኖራል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳት ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸው የቅዱሳት ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
☦የከዳህን ሰው በተንኮል ለመበቀል አትጣጣር። በቀልን ለእግዚአብሔር ተወው። አንተ ክፋትን በክፋት ለመመለስ ስትነሣ፣ የጠላትን መንገድ እየተከተልክ ነው ማለት ነው። ክርስቲያን ግን ክፉ ላደረጉበት እንኳ መልካም ምኞትንና ጸሎትን በመስጠት ክፋትን በጥሩነት የሚያሸንፍ የብርሃን ልጅ ነው።" (ቅዱስ እንጦንስ)
ተወዳጆች ስለ ጊዜ አጠቃቀምና ስለ ንስሐ ቅዱስ ኤፍሬም የሰውን ሕይወት አጭርነትና የንስሐን አስፈላጊነት አስመልክቶ እንዲህ ሲል አጥብቆ ይመክራል፦ "ወንድሜ ሆይ! ዛሬ የምትሠራትን በጎ ነገር ለነገ አታስተላልፋት፤ ነገ የአንተ መሆኑን አታውቅምና። ሞት ሳያስበው እንደሚመጣ ሌባ ነው፤ አንተ በምቾትና በቸልተኝነት ተኝተህ ሳለ ሕይወትህ እንዳታበቃ ተጠንቀቅ። 'ነገ ንስሐ እገባለሁ፣ ነገ እመጸውታለሁ፣ ነገ እጸልያለሁ' እያልክ ራስህን አታታልል። ሰይጣን ዘወትር የሚጠቀምባት ትልቋ ወጥመድ 'ነገ' የምትባለው ቃል ናት። ዛሬ የምትሰማው የእግዚአብሔር ቃል ልብህን ይንካው። በምድር ላይ ስትኖር ለሥጋህ የምትጨነቀውን ያህል ለነፍስህ አትጨነቅም፤ ሥጋህ መሬት ገብቶ ትል እንደሚበላው እያወቅህ፣ ለማያልፈው ነፍስህ አንዳች ስንቅ ሳታዘጋጅ መቅረትህ እንዴት ያለ ዕውርነት ነው? ስለዚህ አሁኑኑ ተነሥ፣ ፈጣሪህን ማርኝ በለው፤ እሱ መሐሪ ነውና ወደ አንተ ይመለሳል።" እነዚህ ምክሮች በተለይ በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ፣ ራሳችንን እንድንመረምር የሚያደርጉ ናቸው። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ❣️ ✍️ / ጸጋ
без подписи
#ኪዳነ_ምህረት_እናቴ🥰 #አንቺ_ባትኖሪልኝ የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ የኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ የኃጢያት ሐረግ ሲንጠላጠልብኝ ሙቼ መራመዴ ለኔ ሲታወቀኝ ምን ይውጠኝ ነበር አንቺ ባትኖሪልኝ አልቅሼ ስነግርሽ አለሁሽ ባትዪኝ የመዳንን መድህን ልዑል ባትወልጂልኝ በምልጃ ፀሎትሽ ቤቴ ባይሞላልኝ በይቅር ባይነትሽ ኑሮ ባይቀናልኝ ማን ያስበኝ ነበር አንቺ ባታስቢኝ ኃጥያት ተፀይፈሽ ፊት ያላዞርሽብኝ ብርሃንን ወልደሽ ፀኃይ የሆንሽልኝ ለውለታሽ ገላጭ ምንም ቃላት የለኝ አማላጇ እናቴ ሁሌም ክበሪልኝ ድንግል እመቤቴ ከፍ ከፍ በይልኝ🥰 🥀የእናታችን ኪዳነ ምህረት ምልጃዋ እናትነቷ ፍቅሯ ጣዕሟ ፆሎት ልመኗ ምልጇዋ ጥበቃዋን አይለየን🙏 ☦️🥰
እንኳን ለሰኔ ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ሰኔ 🌟🌟 ቀን በቤተክርስቲያናችን ታላቅ ክብርና ደስታ የሚከበርበት፣ የቅዱስ ሚካኤልን ፈጣን ተራዳኢነትና አማላጅነት በጉልህ የምናይበት ልዩ ዕለት ነው። የዕለቱ ዋና ዋና ታሪካዊ መታሰቢያዎች፦ ✨የቅድስት አፎምያ መዳን፦ ቅድስት አፎምያ እግዚአብሔርን የምትፈራ፣ ለነዳያን የምትራራና የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል በቤቷ አኑራ በየወሩ የምታስብ ደግ ሴት ነበረች። ሰይጣን በምቀኝነት ተነሳስቶ በተለያየ መንገድ ሊያስታትና ሊያጠፋት ቢሞክርም አልተሳካለትም። በመጨረሻም በሰኔ 12 ቀን በብርሃን መልአክ ተመስሎ ሊያስታት ሲመጣ፣ እሷ ግን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አውጥታ በመስቀል ምልክት አማተበችበት። በዚህ ጊዜ ሰይጣኑ ተቆጥቶ ሊያንቃት ሲሞክር፣ የታመነው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ታይቶ ሰይጣኑን አሳዶ በመቅጣት ቅድስት አፎምያን ከሞትና ከመከራ አድኗታል። ✨የእስክንድርያ ጣዖት መፍረስ፦ በተጨማሪም በዚህ ዕለት በግብፅ እስክንድርያ የነበረው «መንበረ ሚካኤል» የተባለው ታላቅ ጣዖት በቅዱስ ቴዎፍሎስ አማካኝነት የፈረሰበትና ቦታው ተቀድሶ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተክርስቲያን የሆነበት ዕለት ነው። ከበዓሉ የምናገኘው ትምህርት፦ የቅድስት አፎምያ ታሪክ እንደሚያስተምረን፣ በፈተናና በጭንቅ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር የምናደርገው ጸሎትና የቅዱሳን መላእክት ጥበቃ መቼም ቢሆን ከጥፋት ይታደገናል፦ ✨"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።" (መዝሙር 34:7) ቅዱስ ሚካኤል በምልጃውና በጥበቃው ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን! መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
" ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።" (የዮሐንስ ወንጌል 14:3)❤️🙏
без подписи
እንዳትሰማ 🔐ሀገር ወልደህ፣ሀገር አሳድገህ፣ዋጋ ከፍለህ ለማዕረግ አብቅተህ ውለታህ ተንዝግቶ በገዛ ሀገር ላይ ባይተዋር የሆንከው፣የሥልጣኔ ፣የታሪክ፣የቅዱስ እሴት ባለቤት ሆነህ ሳለህ ለዕድገትና ለብልጽግና አትመችም ተብለህ ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ የተፈረደብህ 🔏ምሥራቅ አፍሪካን ሙሉ በሙሉ ለማስለም ለሚደረገው ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ሀገርህ የአክራሪ እስልምና ዋና ቤዝ እንድትሆን የተፈረደብህ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ ሆይ፣ 🔏በጅምላ እየታረድህ፣በጅምላ እየተገደልህና በበጅምላ እየተቀበርህ በግልጽ እየታየ ሰው አልሞተም " እየተባለ የሚላገጥብህ 🔏ስትሰደድ የሚያስጠልልህ፣ስትራብ የሚያበላህ፣ስትጮኽ የሚደርስልህ፣ስትገደል ለቅሶ የሚደርስልህ አንድም ዘመድ የሌለህ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ ሆይ፣ 👉 የቤተ ክህነቱን የማላገጫ ጋጋታ እንዳትሰማ 👉 እነ አቡነ እንትና ኮሚቴ አቋቋሙ የሚል የውሸት ፕሮፓንዳ እንዳትሰማ 👉ጳጳሳቱ ከሰላም ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ የሚለውን ማደንዘዣ እንዳትሰማ 👉"የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ"የሚባለውን የጸረ ኦርቶዶስ ተቋም የማላገጫ ጋጋታ እንዳትሰማ 👉 "ጥቃቱ የተፈጸመበት ቦታ ሄደናል "እያሉ ከአከበባቢው ላይ ሳይደርሱ ከተማ በርገር በልተው ውስኪ ተራጭተው የሚመለሱና የሐሰት ዘጋ ለሚያሰራጩ ምንደኛ መነኮሳትን እንዳትሰማ ብቸኛው መዳኛችን ኦርቶዶክሳዊ ኅብረታችንና ክንዳችን ነው።የማንንም ዲስኩር እንዳንሰማ ።እውነተኛ ካህናትና መምህራን በሚሰጡን አቅጣጫ በየአከባቢው ራሳችንን ለመታደግ እንነሳ። አሊያ ግን፦ 👉እንደ ኩርዳውያን ሀገር አልባ እንሆናለን 👉እንደ ቱርክና ሰሜን አፍሪካ ክርስቲያኖች ከምድረ ገጽ እንጠፋለን 👉እንደ ግብፅ፣እንደ ሶሪያ፣እንደ ኢራቅ፣እንደ የመን፣እንደ አርመንያ ክርስቲያኖች አናሳዎች እንሆናለን። በቃን!! @Justice_for_Christians
የቤተክርስቲያን ሚዲያ በዚህ ሰዓት ሚዘግበው😭
без подписи
በአርሲ አስኮ ወረዳ ጠለታ ጠፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ከተቃጠሉት አንዱ
без подписи
без подписи
በአርሲ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ቀድሞ የዘገበው መሰረት ሚዲያ ነው። በሰዓቱ 37 ኦርቶዶክሳውያን ተገደዋል በሚል። ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሰረት ከአይን ምስክሮች አገኘሁት ባለው መረጃ 49 ተገድለው 280 ደብዛቸው ጠፍቷል፤ የአካባቢው ነዋሪዎችም ተገደዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገለጸ። ሌላኛው ሚዲያ አዲስ ስታንዳርድ ከአይን እማኞች አገኘሁት ባለው መረጃ እስከ 40 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን ተገደዋል የሚል ዘገባ አወጣ። ሌሎች የአካባቢውን ነዋሪ ጠቅሰው የጻፉ ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር ከ50 በላይ አድርሰውታል። ብልጽግና ለምን ይወቀስ ባዩ የቤታችን ቁስሎች ከ48 ሰዓታት በኋላ "9 ምዕመን ሞተ" በሚል ዘገበ። ቀደም ብለን እንዳስቀመጥነው፣ አባ ሳዊሮስ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑ በኋላ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የብልጽግና ካድሬዎች መፈንጫ ሆኗል። አሁንም ቁጥር በማሳነስ ዜናውን በማድበስበስ ጉዳዩን ለማቃለል ሞክረዋል። ማርያማዊት ሄኖክ ለሜሳ
እኛ አሁን በህይወት ያለነው አርሲ ስላልሆንን ብቻ ነው