tgindex
💞መንታ ልቦች💞

💞መንታ ልቦች💞

Статистика

ማፍቀር ስትችል ያፈቀርከዉን ነገር ማወቅ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ወደ አፈቀርከው ነገርም መሻገር ትጀምራለ።በዚህም አፍቃሪም፤ተፈቃሪም፤ፍቅርም አንድ ይሆናሉ ። የፍቅር :የትዝታ :የይቅርታ ግጥሞችንና ደብዳቤዎችን ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ ። ከናተ ሚጠበቀው Join እና share ማድረግ ነው ለማንኛውም አስተያየት እና ለ#cross @hunter_pic

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
10
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
440
+15 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,23%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
174
28 постов
Вовлечённость
39,5%
к подписчикам
Постов в день
1,4
всего 28
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
81
1/48двое суток
92
1/72трое суток
100

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.26из Birukwaverr1_bot

    ዛሬ ደሞ በአዲስ challenge 📲 መተናል Channel ቀድሞ 🏃💨 JOIN ላሉ ሰዎች Giveaway 🎁 እየሰጠን ነው ሳያልፋቹ 🚫 ተጠቀሙበት.. 😇 Channel ለማግኘት JOIN ሚለውን ተጫኑ...‼️

  • 14 авг.443из quotechennel

    " አቧራ የጠገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አይደለም ። የሰውን ድክመት የምትነግረውም ስህተቱን እንዲያርም እንጂ ሰውዬም በስራው ተስፋ እንዲቆርጥ አይደለም ። " / ቀደምት የአገራችን አበው ፍልስፍና / @quotechennel @quotechennel

  • ​​❦ ══ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦     🌹የፍቅር ንቅሣት♥ ክፍል 2⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅     ▶️  ታድያ እኔም ስልኩን ሽምድድ አድርጌ እቤት ገብቼ ስልኬ ላይ save አደረኩት።ከዛ እነ ሮቢ ዛፉን ቆርጠው ጨርሠው አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ።<ሮቢ fb ላይ እኮ friend request ልኬልሀለው accept አታረገኝም እንዴ>አልኩት ፈገግ እያልኩ እሡም <እንዴት accounten አገኘሽው>አለኝ እየተገረመ።<እንዴ ስልክህን አስገብቼ ነዋ search ያረኩት>ስለው አለማመን በሚመስል አነጋገር <እስቲ ስልኬን ንገሪኝ>አለኝ።እኔም ነገርኩት በጣም እደተገረመ ገና ከተዋወቅን 24ሰአት እንኳን ሣይሆነን ከየት እንዳመጣሁት ጠየቀኝ እኔም እያሾፍኩበት ወፏ ነግራኝ አልኩት።ሁለታችንም ከተሣሣቅን በኀላ accountun እንዳላገኘሁትና እሡ friend request እንዲልክልኝ ጠየኩት።እሡም ወዲያው ላከልኝና እኔም ተቀበልኩት።አጠገብ ለአጠገብ ተቀምጠን chat ማረግ ጀመርን። ሁላችንም ወደ ቤት ስንገባ ሮቢ እና የእናቴ ባል ስፖርት መስራት ጀመሩ።የእናቴ ባል ወደ ቤት ሲመጣ ስፖርቱን እንደጨረሡ ስለገባኝ ለሮቢ normal text ላኩለት።ሮቢም ወድያው መለሠልኝና ብዙ አወራን።እኔ እና ሮቢ የተዋወቅንበት ቀን እንዲህ አምሮበት አልቆ ቀጣዪ ቀን እሁድ መጣ።እሁድ በጠዋት ፍቅር እቤታችን መጥታ አስቱ እየጠራችሽ ነው ብላኝ ቤታቸው ይዛኝ ሄደች።ከዛ አስቱ ስገባ በሚያምር ፈገግታ ተቀብላኝ ከፊት ለፊቷ ያለውን የምግብ ጠረጴዛው ጋ ያለውን ወንበር በእጇ እያሣየችኝ ቁጭ እንድል ጋበዘችኝ።እኔም በ1 ቀን ውስጥ ከሁሉም ጋ በጣም ስለተግባባው እንደ ቤቴ አየሁት።አብረን ቁርስ ከበላን በኀላ እኔ ወደ ቤት ሄድኩኝ።እቤት መቀመጥ ስለደበረኝ ውጪ ወጥቼ ስቀመጥ ሮቢም ትንሽ ቆይቶ ወጣ ብቻችንን ስለነበርን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ሮቢ ደስ የሚል ልጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት።ከሮቢ ጋ ብዙ ከተጨዋወትን በኀላ ጠዋት አብረን ት/ቤት እንደምንሄድ ተነጋግረን ወደየ ቤታችን ገባን።ማታ በfb ብዙ አወራን።አይነጋ የለ ነግቶ እነ ማም ስራ ከሄዱ በኀላ እኔ ደሞ እነ ሮቢ ቤት ሄድኩኝ።እነ ሮቢ ቁርስ እየበሉ ነበር ደና አደራቹ ብያቸው እኔም አብሬያቸው ተቀመጥኩ።አስት ቁርስ ብዪ ስትለኝ አሁን ነው የበላሁት ብዬ ሻይ ብቻ ቀድቼ መጠጣትጀመርኩኝ።ለሚያየን ለብዙ አመት በፍቅር የኖርን ቤተሠቦች እንጂ በፍፁም የ1ቀን ትውውቅ ያለን አከራይ እና ተከራይ አንመስልም።እኔ እና ሮቢም ቦርሣችንን ይዘን ለመውጣት እየተነሣን አርብ ከት/ቤት መልስ እመጣለው ብያቸው አስቱን አቅፌያት ቻው ስላቸው ፍቅር መጥታ አቅፋ ሣመችኝና ቻው አለችኝ።እኔም ወደ ቤት ተመልሼ አያቴንና ትንሿን እህቴን ስሜያቸው ወጣው::    ከሮቢ ጋ መንገድ ጀመርን ........... ✎ ክፍል ሶስት (3) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ  Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ። ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄ ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 https://t.me/menta_llboch https://t.me/menta_llboch     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄

  • 14 авг.23из Birukwaverr1_botудалён 15 авг.

    ለፍቅረኛችሁ 💖ምን ብዬ text 📩 ላድርግ ብላችሁ ከተጨነቃችሁ 🤔 ከታች Join ሚለውን በመጫን የተለያዩ የፍቅር ቃላቶችን ያግኙ😍 ...👍 Wave : @Bura_23e

  • @Esmu1188

  • 14 авг.692из kum_negr

    ከታች ማስቀምጥላቹ ሊንክ በመጫን ብር መስራት ትችላላቹ https://t.me/+gkmxObZtLY5hMzY0

  • 14 авг.5из Birukwaverr1_botудалён 15 авг.

    🎵🎵ምን ማዳመጥ ይፈልጋሉ ⁉️ ሃይማኖታዊ ነክ ወይስ ሙዚቃ ❓ እንግዲያውስ እናንተ በምትፈልጉት መልኩ ይዘን መተናል 🙂 ከናንተ የሚጠበቀው መርጦ ማዳመጥ ብቻ ነው 🎵👌

  • 13 авг.27удалён 15 авг.

    💖User: hunter_pic 💖ID: 05660928000 🌐Invite your friends and receive 0.0625 TON for each one. 🔗Invite: https://t.me/TonAutomaticallyRobot?start=05660928000 💖Invited friends: 9 💎TON Balance: 0.5625

  • 13 авг.27удалён 15 авг.

    💖User: hunter_pic 💖ID: 05660928000 🌐Invite your friends and receive 0.0625 TON for each one. 🔗Invite: https://t.me/TonAutomaticallyRobot?start=05660928000 💖Invited friends: 9 💎TON Balance: 0.5625

  • ​​ተከታታይ ልቦለድ          🌹የፍቅር ንቅሣት♥               ክፍል 1⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅        ▶️  የካቲት 5/2010አ.ም ለኔ ልዩ ቀን ነበረች።ለኔ ብቻ ሣይሆን ለሮቢዬም እንደዛው ርብቃ እባላለው።የካቲት 5 ከሮቢዬ ጋ የፍቅር ጊዜያችንን ሀ ብለን የጀመርንባት የቀኖች እና የፍቅራችን የመጀመሪያ ቀን ሠኞ ነበረች።ከሮቢዬ…

  • ​​ተከታታይ ልቦለድ          🌹የፍቅር ንቅሣት♥               ክፍል 1⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅        ▶️  የካቲት 5/2010አ.ም ለኔ ልዩ ቀን ነበረች።ለኔ ብቻ ሣይሆን ለሮቢዬም እንደዛው ርብቃ እባላለው።የካቲት 5 ከሮቢዬ ጋ የፍቅር ጊዜያችንን ሀ ብለን የጀመርንባት የቀኖች እና የፍቅራችን የመጀመሪያ ቀን ሠኞ ነበረች።ከሮቢዬ ጋ የተዋወቅንበት አጋጣሚ እነሆ እናት አና አባቴ ስለተለያዩ እኔ የምኖረው ከአባቴ ጋ ነው ይሁንና የሣምንቱን መጨረሻ የእረፍት ቀነሠቶች እናቴ ገረ ነበር ማሣልፈው እኔ እና ሮቢ በተገናኘንበት ጊዜ እናቴ ከአባቴ በኀላ ካገባችው ባሏ ከአንድ ልጃቸው(ከእህቴ) እና ከእናቷ(ከአያቴ) ጋ እነ ሮቢ ግቢ ተከራይተው ነበር ሚኖሩት።እለተ ቅዳሜ ነበር ህዳር 23/2010አ.ም እናቴ እነ ሮቢ ቤት በቅርቡ ስለሆነ የተከራየችው እኔ ስለማላውቀው ልትወስደኝ ነበር ከአባቴ ጋ ምኖርበት ቤት የመጣችው ከእናቴ ጋ ተያይዘን ወደ አዲሡ ቤታቸው ሄድን።ስንደርስ በሩን የከፈተችልን ሮቢ ልክ እንደ እህቱ የሚያያት ፍቅር ነበረች።ማም ከፍቅር ጋ ካስተዋወቀችን በኀላ ወደ ውስጥ ገባን።ወደ ውስጥ ስንገባ የት/ቤት ልብስ ታጥቦ ተሠጥቶ ነበረ።የዩኒፎርሙ አሠፋፍ የወንድ ይመስል ነበር ደሞ አልተሣሣትኩም የሮቢ ነው።እቤት ገብቼ ትንሽ አረፍ እንኳን ሣልል ፍቅር ብዙ ደብተሮች ይዛ መጥታ አስጠኚኝ አለችኝ።ይሄ የማም ስራ ነው።ሁሌ በሄደችበት ሁሉ ከአባቴ ስለወረስኩት ት/ት ላይ ስላለኝ ጉብዝና ታወራለች።ለነገሩ ፍቅር የ3ተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች።እናም ፍቅርን እያስጠናሇት እቤት ውስጥ፡ስለሞቀን ወደ ውጪ ወጣን።ውጪ ሮቢ ልብስ እያጠበ እናቱ ደግሞ ቡና እየወቀጠች ነበር።ከዛ እናቱን ሄጄ ሠላም አልኳት ተዋወቅን አስቴር እባላለው ስትለኝ ርብቃ አልኳትኝ።<ሮቢ ና ተዋወቃት የሚሚ ልጅ ናት እኮ>አለችው።ከዛ ከሮቢ ጋ ተዋወቅን።የኔና የሮቢ የመጀመሪያ ትውውቃችን እንዲ ነበር።እኔም ፍቅርን ማስጠናት ጀመርኩኝ።ሮቢ ልብሡን አጥቦ ሲጨርስ አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና አንድ አንድ እያልን በደንብ መተዋወቅ ጀመርን።ሮቢ ልክ እንደኔ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነበር።ወደ አመሻሹ ላይ ሁሉም ውጪ ተቀምጦ እኔ ቡና አፈላው።ስጨርስ ሮቢ እና የማም ባል ዛፍ መቁረጥ ጀመሩ።ሮቢ ሲቆርጡ ስልኩ እንዳይወድቅበት ብሎ ዘፈኑን እንደከፈተው lock አድርጎት ለፍቅር ሠጣት።ከዛ ፍቅር አጠገቤ መጥታ ተቀመጠች ድንገት ዞር ስል emergency call ሚለው ላይ ስልክ እየፃፈች ነበር የማነው ፍቅር ስላት የሮቢ ነዋ አለችኝ ታድያ እኔም ሰልኩን ሽምድድ አድርጌ እቤት ገብቼ ስልኬ ላይ save አደረኩት። ይቀጥላል...     ✎ ክፍል ሁለት (2) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።       ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 https://t.me/menta_llboch         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄

  • видео или голосовое, без подписи

  • የደም ባህር ቀዘፍኩ በሚዘንብ እሳት ውስጥ አለፍኩ ግን ተነጥዬ ፤ ብቻዬን ተረፍኩ... እንደወትሮው አይሞቅም የክንዶቼ እቅፍ ተይው አይናፍቅም የአንድ ሌሊት እንቅልፍ አይ የጦርነት ግፍ! የአባቴን ድል ወርሼ የሞት አዚሙን አፍርሼ ለናፈቅነው ግንቦት በቅቻለሁ ቃሌን ጠብቄ ሳልሞት መጥቻለሁ ። ነፍሴ አልወጣችም ፥ አካሌ አልጎደለም ልቤ ብቻ ግን ፥ ከቦታው የለም። ትዝ ይልሻል? 'የመጨረሻውን ሟች ፥ ማነው  የሚቀብረው?' ብለሽ ጠይቀሽኝ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ፥ አስቀሽኝ የነበረው? ...ዛሬ ትዝ ብሎኝ አልቅሻለሁ። እናትሽ 'ፈሪ ለእናቱ!'  ትል ነበር ትርፉ ለማን ነው ፥ የጀግናስ ነገር? የእኔ አይነቱ ጦረኛ ውጊያ ላይ ወድቆ ካልተኛ መኝታው ውጊያ ይሆናል ሞቶ ማለፍም ብቻን መትረፍም ያሳዝናል። የድል ማግስት ለጌቶች ነው ድግሱ አሳብ ትራሳቸው ነው አፈር ያልተንተራሱ። ሺ ገዳይ መሆን ለአሞራ እንጂ ፌሽታው ለጀግና አይምሰልሽ በድን ነው የሚያየው አይንሽ እንባ ነው ሚጠጣው አፍሽ። ሰው እንደንጨት ነድዶ ሲቃጠል ገላ እንደወረቀት ሲገነጣጠል ቁስለኛ ሲጮህ መድፍ ሲያጓራ ምድር ደም ለብሳ በባሩድ ታርሳ ፥ ስትነፈራ ያየ ሰው ፥ መዳን አያጓጓውም የሲጋራን ታህል የቆንጆ ከንፈር የአበባ ቀለም አያባባውም። ሞት ለጎበኛት ነፍስ ፥ ሰላም ያስፈራል ጠመንጃ ዝም ሲል ልብ ይጀምራል። እንደባረከ አያኖር እንደሰራ አይገድል ጥይት መጮህ አለበት ህሊና ዝም እንዲል። እርምሽን አውጪ አቅፈሽኝ ለቅሶ ተቀመጪ አብረሽኝ አካሌ ተቀብሮ እንደውስጤ እስኪፈርስ የሞት ድምጽ አሻግሮ እስኪጠራኝ ድረስ። እንደወትሮው አይሞቅም የክንዶቼ እቅፍ ተይው አይናፍቅም የአንድ ሌሊት እንቅልፍ ብትስሚኝ በድን ነኝ ፥ እያለሁ የለሁም ከእንግዲህ ጀግና እንጂ ፤ ሰው አይደለሁም። ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ

  • ከ Hi እስከ Hiሎጋ😁 ትዝ ይልሻል ያኔ ,,,,,,, ሀይ ብየ ጀምሬ ቴክስት ልኬልሽ አይተሽ እንዳላየ ፀጥ ነበር መልስሽ ካንዴም ሁለት ሶስቴ ልኬ ሳይሰለቸኝ መልስ እየጠበኩኝ ዝምታሽ ሲደርሰኝ ባንቺ እልክ ተውጨ ሌላዋን ሀይ አልኩኝ እሷ ግን እንዳንቺ አይታ ዝም ሳትል ሀይ ብላ መለሰች ወዲያው አድሮ ሳይውል እኔም በሷ ምላሽ እልክሽ ወቶልኝ የባጡን የቆጡን ብዙ አወጋጋሁኝ አንዱ ጨዋታችን ሌላ እየወለደ ምንም ሳናስበው ለሊቱ ነጎደ አቤት እርጋታዋ ቀልድ አዋቂነቷ እንዴት ደስ እንደሚል ደሞ ስርአቷ ከዛ ቀን ጀምሮ ኦላይን ሳገኛት ደስ ብሎኝ ነበረ እኔው hi የምላት ደሞ ሳትኖር ስቀር አቤት ስናፍቃት እየዋል እያደር ብዙ ስንግባባ መላመድ ጠንክሮ መውደድ ሲገነባ ባካል ተገናኝተን አይን ላይን ተያየን ጥሩና መጥፎውን አመል ተወያየን ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ልናይ አብረን ያጋጣሚ ነገር ተገጣጠመና መንገዱ ሲቀና እቅዷና እቅዴ ሀሳቧ ካሳቤ ተመሳስሎ ቢገኝ የሂወታችን ዘይቤ አብሮነት ወሰንን ልኖር ባንድ ጎጆ እኔም የሷ ልሆን እሷም የኔ ቆንጆ ከዛማ ምናለ ......😂 በወጉ መሰረት ቤተሰብ አውቆልን ለፊታችን ህዳር ሰርጉን ቆረጡልን ይገርመኛል ታዲያ ቆም ብየ ሳስበው ያኔ ለወግ ያክል በ Hi የጀመርነው ዛሬ ወግ ሊያሳየን Hiሎጋ ሊባል ነው እናም ውዴ ዛሬ ይህን ስፅፍልሽ እንድትቀኝ አይደለም ወይ ደሞ እንዲቆጭሽ ግን ግን ከሰማሽኝ እንሆ ልንገርሽ እንደው ከዚህ ወዲያ Hi ብሎ ለሚልሽ አንችም Hi በያቸው ካንጀቴ ልምከርሽ እንደኔ አይነት # ሸጋ ዳግም እንዳያልፍሽ😄

  • 🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻 💙  የልቤ ትርታ  🔸 ‍ ​​                     ❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️            ❤️የመጨረሻው ክፍል  ❤️ ...🖌እነመቅደስም መሞቱን አምነው ሀዘን ሲቀመጡ መቅደስ እራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሀሉም በንባ ታጥበው ነበር............. .........ቢያንስ መቅደስ ከሶስቴ በላይ እራሷን ልታጠፋ ስትል እየደረሱ አድነዋታል በዚህም የተነሳ ብቻዋን ጥለዋት ወተው አያውቁም ዛሬ ግን አጋጣሚ ሆነባቸውና ቅብጥብጡን ብሩክን አደራ ብለውት ከፊቷ እንዳይጠፋ አስጠንቅቀውት ጉዳይ ስለነበረባቸው ሁሉም ወጡ እንደእብድ ያረጋት መቅደስ አሁንም የጌዲዮን መሞት ስታስብ መሞት አማራት ከዛ ብዙ ኪኒን ለመዋጥ ስታስብ ብሩክ አለ ከዛም ሱቅ ልትልከው አስባ ብሩኬ ስትለው ወዬ አላት ሱቅ ሄደህልኝ ና አለችው አረ ላሽ በይ እነ ማሚ ጥዬሽ እንዳልሄድ አስጠንቅቀውኛል ሲላት ሴት እኮ ነኝ ታዲያ ልበላሽ አላሳዝንህም ስትለው ምንድነው የምገዛልሽ አላት እ .እ. እንትን ልክ እንደፈራች ሆና መርበትበት ጀመረች ደሞ ከዚህ ውጪ ምንም ቢሆን እንደማሄድላት ታውቃለች ከዛም ካፏ ቀበል አርጎ እየሳቀ ሲስቱ ብዙ አትጨናነቂ ገባኝ የሴቶች ፓንፐርስ ነዋ ሲላት ሂ ሞዛዛ ብላ በጥፊ አለችው ከዛም አደራውን እረስቶ ሊያመጣላት ተስማማና ብር ተቀብሏት ሄደ እንደሄደም ኪኒኑን ሰብስባ ልትውጠው ስትል የቤታቸው ስልክ ጮኸ ዝም አለችው አሁንም ልትውጥ ስትል ጮኸ አሁንም ዝም አለችው ከዛም አሁንም ልትውጥ ስትል ሞባይሏ ጮኸ በንዴት አንስታ ሄሎ ስትል ሀይ መቅዲዬ ቅዱስ ነኝ በቤትስልክ ስደውል የሚያነሳ የለም ደንዝዛ ቀረች በዛ ላይ የቅዱስ ድምፅ ፍፁም ልክ አልነበረም መልስ ልትሰጠውም አንደበቷ አልፈታም አለ ከዛም በዛ በተዘበራረቀ ድምፁ አሁን ኤርፖርት ነኝ ነገ ማታ 12 ሰአት ስለምንደርስ ኤርፓርት ጠብቁን አላት ጌዲስ ሞተ አይደል ብላ ልትጠይቀው አስባ ካፏ ሳታወጣው ስልኩ ተቋረጠ እንባ ካይኖቿ ዱብ ዱብ እያለ ብቻዋን ስታወራ ብሩክ ተመልሶ መጣ ሲያይት ደንግጦ ምን ሆንሽ አላት መልስ አልሰጠችውም ክፍሏ ገብታ ተኛች ማታ ቤተሰቦቿ መጡ.......... ተሰብስበው ሳሎን ቁጭ ባሉበት ያለወትሮዋ መጥታ መሀላቸው ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም አይን አይኗን ማየት ጀመሩ ምክንያቱም አብራቸው መሆን ካቆመች ቆየች መሬት መሬቱን እያየች ቅዱስ ነገ ይመጣል አለቻቸው ምን አሏት አዎ 12ሰአት ተቀበሉኝ ብሏል ስትላቸው ጌዲዮስ አሏት እኔንጃ አላቅም ብላ ተመልሳ ወደክፍሏ ሄደች...... ......መድረስ አይቀርምና የመምጫቸው ሰአት ሲደርስ ሁሉም ተሰብስበው የኤርፖርቱ በር ላይ በሁለት ስሜት ይጠባበቁ ጀመር ግማሹ ተሳፋሪ ወጣ ቡሀላም ቅዱስ ወደነሱ ቀረበ ግን እሱን ሳይሆን ሁሉም የሚያዩት ባይናቸው የሚፈልጉት ጌዲዮን ነበረ ቢሆንም አጡት አባትየው ቀስ ብሎ መቅደስን ደገፋት ሁሉም ልባቸው ቀጥ ልትል ምንም አልቀራትም ተስፋቸው ተሟጦ የጌዲዮን ሞት አምነው ለመጮህ እራሳቸውን ሲያዘጋጁ በስተመጨረሻ ባልጋ እየተገፋ ቻው ብሏቸው የሄደው ጌዲዮ ድኖ ጋቢ ለብሶ ከቅዱስ ቡሀላ እየተራመደ መጣ........... ............ሁሉም በህልም አለም ያሉ መሰላቸው መቅደስ በጩኸት ዘለለች ሌሎቹም እየተንበረከኩ በምስጋና ላምላካቸው መስገድ ጀመሩ መቅደስ እንደጨቅላ ፍየል እንደንቦሳ ጥጃ ከዛ ከዚህ መሯሯጥ ጀመረች የታመነችለት ፍቅር ታመነላት ጌዲዮን አሳልፎ ለሞት አልሰጠባትም ከሩቅ ገና ሲያያት ጌዲዮ እየተንደረደረ ወደሷ መጣ እሷም እየሮጠች ወደሱ ስትሄድ መሀል ላይ ተገናኙ ከዛም ሊያቅፋት ሲል ተመልሳ ወደቤተሰቦቿ ተንደረደረች ጌዲዮ ደነገጠ እሷን እሷን እያየ እንባውን አዘራ እሷም እያለቀሰች እየዘለለች አባ አባዬ እሱ ነው ጌዲዮ አልሞተም እኮ እያለች እውን የሆነውን ህልሟን ትተርክ ጀመር በሁኔታዋ እንኳን ቤተሰቦቿ ያያቸው የተመለከታቸው አለቀሰ ከዛም ወደጌዲዮ ተመለሰች አሁንም ሳታቅፈው ተመለሰች ጌዲዮ ደስታዋ መሆኑን ሲያውቅ ከመሬት ተንበርክኮ በንባ ታጠበ ፈጣሪውን አመሰገነ ለሶስተኛ ጊዜ ስትመጣ አሁንም እንዳትመለስ ሁልቱን እጆቿን ጭምቅ አርጎ ይዞ ጉንጮቹ ላይ አረጋቸው የናፈቀው አይኗ የናፈቃት አይኑ ተፋጠጡ ፍቅር የተራበው ልባቸው በሀሴት ጮቤ እረገጠ ከንፈራቸው ተንቀጠቀጠ ናፍቆትና ፍቅር የጋረደው አይናቸው በዙሪያቸው የሚመለከታቸውን ህዝብ አላስትዋሉም ጌዲዮም ቤተሰቦቿ መኖራቸውን እረሳው ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ ሳማት የተባለ ይመስል ያኔ የመጀመሪያ ቀን እንደሳማት ግጥም አርጎ ከንፈሯን ጎረሰው አቤት ሲያምሩ አቤት ሲያስቀኑ መፋቀርስ እንደነሱ ፀጉሯን እየዳበሰ እሷም አንዴ ጉንጩን አንዴ ወገቡን አጥብቃ እየያዘችው እያገላበጠ ያለምንም ፍራት ይሳሳሙ ጀመር ቡሀላም አለመላቀቃቸውን ቀበጡ በረከት ሲያይ ጠጋ ብሎ እህህ እህህ አረ እኛንም ሰላም በለን ናፍቀኸናል እኮ ሲለው ጌዲ ደንገጥ አፈር ብሎ መቅደስን ለቀቃትና ከመጣህ ትመልስልኛለህ ብላ ያጠለቀችለትን ያንገቷን ማህተብ አውልቆ አጠለቀላት ከዛም ግንባሯን ስሞ ሁሉንም እያቀፈ በንባ ሰላም አላቸው.............. .............ወደቤትም እንደሄዱ እራት በሉ ቡናም እየጠጡ እናቱን ጠየቃቸው ከዛም ገዳም እንደሆኑ እሱ ሲሄድ እንደሚወጡ ነገሩት መቅደስ ከቅፉ አልወጣችም ነበረ በቃ ከናንተ ጋር ናፍቆቴን ይህን ያክል ካሳለፍኩ ነገ እሄዳለሁ እሜ እጅግ በጣም ነው የናፈቀችኝ አላቸው ከዛም የመቅደስ እናት በቃ መቅደስም አብራህ ትሂድ ባይሆን ጓደኞቿ እሁድ ስለሚውምመረቁ በዛውን የደስታችንን ድግስ አብሬ እደግሳለሁ ቅዳሜ እናትህን ይዛችሁ እንድትመጡ ሲሉት እንዴ መቅዲስ አትመረቅም አላቸው መቅደስ ቶሎ ብላ አይኗን ከመሬት ተከለች አባቷም አይ ጌዲ እንኳን ከትምርት ከራሷም አለም ወታ ነበር እኮ ብለው የተፈጠረውን ተራ በተራ አስረዱት ጌዲዮ የመቅደስ ፍቅር ካቅሙ በላይ ሆኖበት ከውስጡ ሸሸጋት....... ........ከዛም አገር ቤት ሲሄዱ አገር ምድሩ ተቀበላቸው እናቱም በልልታ ፀሎቷን የሰማት አምላኳን እያመሰገነች ልጇን ከቅፏ አስገባችው የናቱም ያባቱም ዘመዶች ጎረቤቱም ሳይቀር ከግሩ ተንበርክከው ይቅርታ ለመኑት እሱም ይቅር ለእግዚብሄር አላቸውመረገጣቸው መገፋታቸው ለበጎ ሆነ አሸናፊዎቹ ተሸነፉ ተሸናፊዎቹ አሸነፉ!!!!!...........       🔻 ❤️ 💝  ተፈፀመ🔻 ❤️ 💝                  ❤️ 💝አብራችሁን በመሆን  ስለተከታተላችሁን ከልብ እያመሰገን  በቅርቡ በሌላ ታሪክ እንመለሳለን  ሀሳብ አስተያዬት እንዲሁም መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች  commnet ላይ አሳውቁን  .. አብራችሁን ለሆናችሁ በእውነት በቻናላችን ስም ከልብ ❤ እናመሠግናለን🙏🙏 🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀 እኔን ማናገር ለምትፈጉ 👉  ‌@hunter_pic

  • 🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻 💙  የልቤ ትርታ  🔸 ‍ ​​                     ❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️                        #ክፍል_2️⃣7️⃣ ...🖌የንስሀ አባታቸውም ብዙ አስተማሯቸው ስለይቅርባይነት ብዙ ነገሯቸው በስተመጨረሻም እግዚያብሄር ሊፈትነኝስ ቢሆን ብለው አሰቡና ልጄን አትርፍልኝ እንጂ እንኳን ይሄንን ስንቱን ችያለሁ ብለው ይቅር ለግዚያብሄር አሉ ሰላም ወረደ ገዳምም ገብተው ፆም ፀሎታቸውን ተያያዙት................. .........መቅደስ አዘውትራ የምትሄደው ጌዲዮ የሚያጠናበት ጫካ ነው ነገ ትምርት ጨርሰው ወደየመጡበት ይበተናሉ ያመጣችው ውጤት ምንም ከሷ የማይጠበቅ ነው ይሄ ወር ደግሞ ያምስተኛ አመት ተማሪዎች የጌዲዮ ጓደኞች ምርቃት ነው ህመሟን ጨመረው ስለምርቃቱ ጓጉቶ የነገራት እያስታወሰች በተለይ ምን ታመጪልኛለሽ ሲላት ያገር አበባ ያለችው ብቻ ሁሉንም እያስታወሰች በንባ እየታጠበች ነው........ .....እውነትም አልቀረም የምርቃታቸው ቀን ደረሰ የዛ ቀን መቅደስ በጠና ታመመች ሀኪም ቤትም እንዳትወሱዱኝ አለች ከዛም እቤት ድረስ ዶክተር አመጡ ዶክተሩም አክሞ ሲጨርስ በጣም በናፍቆት ተጎድታለች ምግብም ካለመመገቧ የተነሳ እራሷን መቆጣጠር ተስኗታል በተቻላችሁ አቅም የናፈቀችውን ሰው ብታገናኟት ጥሩ ነው ሲላቸው አይ ዶክተር ይሄማ መች ጠፋን ለማንኛውም እናመሰግናለን አሉት..... በቃ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ጭራሽ ከክፍሏ አልወጣም አለች ያምስተኛ አመት ትምርቷንም ልክ እንደጌዲዮ አቆመች ቤተሰቦቿ እግሯ ላይ ቢወድቁም አልማርም አለች ግዜም መሄዱ አይቀርምና ጌዲዮ ሁሉንም ቀዶ ጥገና በወዳጆቹ ፀሎትና በፈጣሪ ፍቃድ በሰላም አጠናቆ የመጨረሻው ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቀጠሮው ደርሶ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል አስገቡት......ብሩክ ከዚህ ቡሀላ ጌዲዮ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ አልቻለም አንድም መልስ የሚሰጠው ዶክተር አጣ ይሙት ይኑር ምኑን አውቆት ቤተሰቦቹም አስጨነቁት ግራ ቢገባው ሞቶም ከሆነ ቁርጤን ንገሩኝ አላቸው የህክምናው ክፍል መግባት አይቻልም መልስ የሚሰጠው አጣ ለምን የሚል ጥያቄ ጭንቅላቱ ውስጥ ተፈጥሮበት በከፍተኛ ሀዘን ተዋጠ ለብዙ ሳምንታትም የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቢሸውዳቸውም በስተ መጨረሻ ግን አልቻለም ሁሉም አፋጠጡት ስልኩን ሙሉ ለሙሉ ኦፍ አረገው በቃ ከዚህም ቡሀላ ቤተሰቡ ሀዘን ተቀመጠ መቅደስ ካንዴም ሁለቴ እራሷን ልታጠፋ ስትል ደርሰው አዳኗት እንኳን የጌዲዮን የብሩክን ድምፅ ከሰሙ ወራቶች ተቆጠሩ... .....ጌዲዮና መቅደስ ከትውውቅ ጀምሮ እስካሁን በጣም ብዙ ፈተናና መከራ አሳልፈዋል ከምንም በላይ ግን ያለፈው ግማሽ አመትና ይሄ አመት በሳት የተፈተኑበት ወቅት ነው ትምርቷን አቁማ ከቤት አልወጣም ካለች ይኸው አመት ሊሞላት ነው ብትወጣ እንኳን አምላኳን ልትለምን ቤተክርስቲያን ብቻ ነው የጌዲዮ እናትም ገዳም ገብተው ሱባኤ ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ የመቅደስ ቤተሰቦችም የጌዲዮ ጓደኞችም ብቻ የሚያውቁት ሁሉ በፀሎት አልተለዩትም እንደምታስታውሱት በክፍል ሀያ አምስት ላይ ጌዲዮ የመጨረሻውን ቀዶ ጥገና ሊያደርግ ከገባበት ወቅት አንስቶ አስታማሚው ቅዱስ ስለሱ ሁኔታ የሚነግረው አጥቶ ተስፋ ሲቆርጥ ቤተሰቦቹም እየደወሉ እንዴት ሆነ ሲሉት ስልኩን ሙሉ ለሙሉ ሲያጠፋ... 🔻ክፍል 2️⃣8️⃣የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ። 🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀       ‌‌‌‌

  • 💖User: hunter_pic 💖ID: 05660928000 🌐Invite your friends and receive 0.0625 TON for each one. 🔗Invite: https://t.me/TonAutomaticallyRobot?start=05660928000 💖Invited friends: 9 💎TON Balance: 0.5625

  • 5 авг.2391из TonAutomaticallyRobot

    💖User: hunter_pic 💖ID: 05660928000 🌐Invite your friends and receive 0.0625 TON for each one. 🔗Invite: https://t.me/TonAutomaticallyRobot?start=05660928000 💖Invited friends: 9 💎TON Balance: 0.5625

  • ቀጥረሽኝ....ፈላስፋ አደረግሽኝ ላገኝህ ስትዪኝ... በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ ደመናው ኬት መጣ? አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ ልብሴን በላዬ ላይ በእግር መንገድ ላደርቅ ስራመድ እየሮጥኩ መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡ ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ በምናብ ገፄ ላይ ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ ካንቺ ጋራ ስሆን... እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት ሰአቱ ገና ነው... ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡ ሊስትሮው... በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል ይለኛል ጫማዬ... "የህይወት ትንሽ ሽንቁር... ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡ ሰአቴን አየሁት ፣ ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡ እየተጣደፍኩኝ... ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ እስካገኝሽ ድረስ ቅድም ያጠረብኝ... እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ ሲሔዲ ሲሔዱ ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ... መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡ እፈላሰፋለሁ! ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል አሁን ላይ ስሔደው... ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡ ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ ሊስትሮው እጅ ላይ.... ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ የህይወትን ሽንቁር... ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡ እፈላሰፋለሁ... ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ በጣም ከቀደመ.... እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡ ሰው የሚሉት ፍጡር... ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡ እፈላሰፋለሁ... ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው እፈላሰፋለሁ! ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው እፈላሰፋለሁ!!! የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!      ✍️✍️✍️በላይ በቀለ ወያ

  • 🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻 💙  የልቤ ትርታ  🔸 ‍ ​​                     ❤️አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼❤️                        #ክፍል_2️⃣6️⃣ ‍ ‍​ ...🖌ጌዲዮ ለህክምና ውጪ ከሄደበት ቀን አንስቶ መቅደስ ሀሳቧን መሰብሰብ ተሳናት ቃሉን ለማክበር ስትል ወደ ግቢ ብትመለስም ከትምርቷ ይልቅ ሀሳቧ ስለጌዲዮ ሁኔታ ወንድሟ የሚልክላትን መረጃ ለማወቅ ነበር ጉጉቷ ያው ዶክተሩ እንዳለው ቀዶ ጥገናው ባንድ ጊዜ የሚከናወን ስላልነበረ ቀዶ ጥገና አለው ባላት ቁጥር በሀሳብና በጭንቀት ቀድማ የምታልቀው እሷ ነች........ .....አረ ጌዲዮስ ቢሆን የሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ሞትን የሚፈራ የመጀመሪያው ሰው እኔ ነኝ ብሎ እስኪያስብ ድረስ ሞትን ፈራው ዳግም የናቱንና የመቅደስን አይኖች አለማየቱን ሲያስብ ሞትን አብዝቶ እረገመው ከበሽታው በላይ ናፍቆት ጎዳው መለየቱ ህመም ሆነበት የመቅደስ ፈገግታ ጨዋታዋ ሳቂታነቷ ፍቅሯን መቋቋም አቃተው በተለይ አብራ የታመመችለት ህመሟ ከማንም አስበልጣ ተማርኮ የማረከው ፍቅሯ እህህህህ እያረገ ውስጥ ውስጡን ሌላ በሽታ ሆነበት......... በመመረቂያው ወቅት ሆስፒታል መተኛቱን እረስቶ መቅደስን አግብቶ ለናቱ የልጅ ልጅ ማሳየት አማረው ሌላ ተስፋ ምን አልባትም እውን የማይሆን ህልም...አለቀሰ አብዝቶ አነባ.......... .......ብርሀን ሰአዳ ወይንሸትም ብትሆን መቅደስ እንድትረጋጋ ዘና እንድትል ብዙ ጥረት እያረጉ ነው ቢሆንም እንዳሰቡት አልሆነላቸውም ምክንያቱም ከነሱ ጋር ከመሆን ይልቅ በፊት ጌዲዮ የሚሄድበት የሚያዘወትርበት ስፍራ እየተቀመጠች ብቸኝነቷን መርጣለች....ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ይሄ መዘዘኛ ብሎ አይደል የዘፈነው ጥላሁንስ ቢሆን........ .........የጌዲዮ እናት እነመቅደስ ቤት ትንሽ ከተቀመጡ ቡሀላ ወዳገርቤት መመለስ እንደሚፈልጉ ለቤተሰቡ ሲናገሩ የመቅደስ አባት ግራ በመጋባት ምን አጠፋን ሲሉ ጠየቋቸው የጌዲዮ እናትም አረ ምን ቦጣችሁና የናንተን ውለታ እኮ ነብሴንም ብሰጥ ከፍዬ አልጨርሰውም ግን ይህን መልካምነታችሁን እግዚያብሄር ነው በሰማይ የሚከፍላችሁ ሰው የለም ባልኩበት ወቅት ነው እናንተን አግኝቼ እውነትም የሰው መዳኒቱ ሰው ነው ያልኩት ስትላቸው ታዲያ ምን አርገን ነው ጌዲዮ ሳይመጣ ልሂድ የሚሉ ... አዪ እንጃ ብቻ አንድ ያለኝን ያይኔን ማረፊያ ዘሬን መተኪያዬን ልጄን እንዳላጣው ልቤ ፈራ ታዲያ እዚህ ሆኜ በሰቀቀን ከማልቅ ከቀያችን አንድ ገዳም አለ እዛው ሄጄ በሱባኤ ፈጣሪ ጨክኖ እንዳይጨክንብኝ ብለምነው ይሻለኛል ብዬ ነው..... እንደዛስ ከሆነ መልካም ፈጣሪ ጥሎ አይጥልም ይለመናል እውነት ብላችኋል የተናቀን ያከብራል የተረሳን ያስታውሳል አበቃለት የተባለን ታሪክ ይቀይራል አዎድ ይለመናል ........ ........እንዳሉትም በንጋታው የጌዲይ እናት ወዳገርቤት ተመለሱ አመሻሽ ላይ ስለነበር የደረሱት ቤታቸውን አዘገጃጅተው ነገውኑ ወደገዳም ገብቼ ሱባኤዬን እጀምራለሁ ብለው አሰቡና ኩርትምትም ብለው ጋደም አሉ የልጃቸው ነገር እያስጨነቃቸው በሀሳብ ተውጠው በዛው እንቅልፍ ወሰዳቸው ለሊትም በራቸው በሀይል ተንኳኳ እትዬ አስካል እትዬ አስካል የሚል ድምፅም ሰሙ በራቸው በመንኳኳቱ ቢደነግጡም የሰሙት ድምፅ የንስሀ አባታቸው መሆኑን ሲያውቁ ተረጋግተው በሩን ከፈቱ ስኪፍቱት ግን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሽማግሌዎች ጎረቤቶቻቸው እንዲሁም ለብዙ አመታት የራቋቸው የባለቤታቸውና የራሳቸው ቤተሰቦቻቸው ደጃቸውን ሞልተውት ነበር የጌዲዮ እናት በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ የልጃቸውን መርዶ ነጋሪዎች መሰሏቸው አንደበታቸው ተርበተበተ ሰውነታቸው ተንቀጠቀጠ ልባቸው ሄድ መጣ ይል ጀመር በሚቆራረጥ ድምፃቸውም ልጄ ልጄ ምን ሆነ አባ ሲሉ የንስሀ አባታቸውን ጠየቁ ነገሩ ግን ካሰቡት ውጪ ነበር ይሄ ሁሉ ሰው የተሰበሰበው ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሆነ ሲረዱ ነብሳቸው አረፈች ግን ለምን ሲሉም ጠየቁ የልጃቸው መታመምን ሰምተው እንደሆነም ሲነግሯቸው አለቀሱ በንባቸው መስታወትም ያሳለፉትን የመከራ ሃያ አመታት ወደኋላ መለስ ብለው አስታወሱ............ ........ጌዲዮን ከልጆቻቸው ጋር አንድም ቀን እንዲጮት ፈቅደውለት አያውቁም ለግዜር ሰላምታም ቢሆን ይፀየፏቸዋል በዛላይ አሽሙራቸው መጥፎ ንግግራቸው ከሰው መሀል ሆነው ሰው የተራቡበትን ጊዜያት ከማህበራዊ ኑሮ ተገለው የኖሩበት አመታት አረ ስንት መከራ ስንት ስቃይ ግን ይህን ሁሉ ጨክነው ነበር ጌዲዮን እዚህ ደረጃ ያደረሱት የሳቸው ቅስም እየተሰበረ የልጃቸውን ሞራል እየጠበቁ ታዲያ ምነው ዛሬ ተስፋቸው ሊሞት መሆኑን ሲሰሙ ለይቅርታ ሽማግሌ ሰበሰቡ የጌዲዮ እናት አሻፈረኝ አይሆንም ይቅርታችሁን አልቀበልም አሉ... 🔻ክፍል 2️⃣7️⃣ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ማድረግ አይርሱ። 🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀       ‌‌‌‌‌‌‌

💞መንታ ልቦች💞 — tgindex