- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 341
- 1/48двое суток
- 390
- 1/72трое суток
- 421
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በዚህ ክረምት የተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ለሰመር ካምፕ ሥልጠና እንዳዘጋጅላቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር። የምማረው ጊዜ የሚነሣውን ሜድስን ሆነና ግን የአንዳቸውንም ጥያቄ ሳልቀበል ቀረሁ። እንደ ጌታ ፈቃድ የአሁኑ አታችመንቴን ፈተና ከ1 ሳምንት በኋላ ጨርሳለሁ። ከዚያም ከቀጣዩ አታችመንት በፊት የአምስት ቀን እረፍት አለችኝ (የሴሜስተር እረፍት መሆኑ ነው በነገራችሁ ላይ😢) ስለዚህ (ከነሃሴ 20 እስከ መስከረም 20) ባለው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሚመጡ ቤተ ክርስቲያናት በሁለት ርእሶች ላይ ሥልጠና የመስጠት እቅድን ይዣለሁ። እነዚህም፦ 1. ወሲባዊ ቅድስና 2. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወንድነት እና ሴትነት ስለዚህ በተጠቀሱት ቀናት እና ርእሶች ላይ ሥልጠና እንድሰጥላችሁ የምትፈልጉ ሁሉ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ፦ @Kenu_Lemma
እውነተኛው የክርስትና ምሥጢር በአጭሩ እንዲህ ይገለጻል፦ ለመጽደቅ አለመሳተፍ፤ ለመቀደስ ደግሞ በንቃት መሳተፍ! የብዙዎችን መንፈሳዊ ጎዳና ስንቃኝ ግን ከመስመር የሳቱ ሁለት ተቃራኒ ዝንባሌዎችን እናያለን። በአንድ በኩል “ለመጽደቅ ልሳተፍ” በሚል የሥራ ጽድቅ የሚባክኑ ''ሃይማኖተኞችን''፣ በሌላ በኩል ደግሞ “ለመቀደስ አልሳተፍ” በሚል ስንፍና ውስጥ የተሸሸጉ ''አማኝ ነን'' ባዮችን እንመለከታለን። እነዚህ ሁለቱም ከእውነተኛው አስተምህሮ የራቁ ናቸው፡፡ ከ የፖርኖሲስ ትውልድ መጽሐፍ የተወሰደ!!
ከፖርኖግራፊ እና ከመሰል የልምምድ ኀጢአቶች ነጻ የሚያወጣችሁ እውነት ይህ ነው፦ የተስፋ ግብግብ👇👇 https://vt.tiktok.com/ZS4gokmnA/ ለብዙዎች ይደርስ ዘንድ ሼር አድርጉት፤ ተባረኩ
የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈለንን አገልጋይ ከነዓንን ጌታ አብዝቶ ይባርክው፡፡ የክፍል 5ን ማስታወሻም ደግሞ እንድናነብ ይሁን! @HUfellow #ለመንግስቱ_መትጋት
መኖርን ከመሆን ክፍል 5 እኛ በትዳር የ1ኛ ጴጥሮስ መልእክት ተከታታይ ትምህርት አገልጋይ ከነዓን ለማ @HUfellow #ለመንግስቱ_መትጋት
በመንግሥተ ሰማይ እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፤ በወሰን የለሽ፣ ሊደረስበት በማይቻል እና ለዘላለም በሚኖር ፍቅር በአንድነት ይኖራሉ። 👉 በዚያ እግዚአብሔር አብ፣ የምሕረት አባት በዚህም የፍቅር አባት የሆነው እርሱ፣ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ አንድያ ልጁን አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ የወደደው አባት እግዚአብሔር ይኖራል። 👉 በዚያ የእግዚአብሔር በግ፣ የሰላምና የፍቅር መስፍን የሆነው፣ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ ደሙን ያፈሰሰውና ነፍሱን ለሰዎች እስከ ሞት አሳልፎ የሰጠው ክርስቶስ ይኖራል። በዚያ መለኮታዊ ፍቅር ሁሉ ወደ ሰዎች የተገለጠበት፣ ታላቁ መካከለኛ ይኖራል። በዚያ ክርስቶስ በሁለቱ ባህሪያቱ፣ በሰውነቱና በመለኮትነቱ፣ ከአባቱ ጋር በአንዱ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ይኖራል። 👉 በዚያ የመለኮታዊ ፍቅር መንፈስ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ይኖራል፤ የእግዚአብሔር እውነተኛ ማንነት በፍቅር የሚፈስና የሚተነፍስ ሆኖ በእርሱ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አማካይነት በምድርና በሰማይ ባሉ ቅዱሳን ሁሉ ልብ ውስጥ የሚደርስበት እርሱ ይኖራል። 📌 በሰማይ፣ ይህ ከሥላሴ የሚፈስሰው ወሰን የሌለው ፍቅር ምንም ዓይነት እንቅፋት ሳይከለክለው ለዘላለም በሩ ክፍት ሆኖ ይኖራል። እኛም ይህን ሰማያዊ ርስት እንናፍቃለን፤ ጌታ በቸርነቱ ወደዚያ ያድርሰን🙏
ከሁለት አደገኛ ጽንፎች ራሳችንን እንጠብቅ! 👉 በአንድ በኩል—ራሳቸውን በክርስቶስ ቦታ ተክተው "በአምላክና በሕዝቡ መካከል መካከለኛ ነን" በሚል ለአምልኮ የቀረቡ መሪዎች (Cult of personality)፤ 👉 በአንጻሩ ደግሞ—"ከክርስቶስ ውጭ ማንም አያስፈልገኝም" በሚል ሽፋን ከቤተ ክርስቲያንና ከመንፈሳዊ አመራር ራሳቸውን የሚያገሉ መንፈሳዊ ግለኞች (Individualism)። 💥 እውነታው ግን ይህ ነው፦ * መንፈሳዊ መካከለኛ አያስፈልገንም፦ ወደ አብ ለመድረስ ብቸኛው መካከለኛቻችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። * መንፈሳዊ መሪ ግን ያስፈልገናል፦ ክርስቶስ ለአካሉ እድገትና ጥበቃ መሪዎችን (እረኞችን) ሰጥቷል። 📌 ስለዚህ፤ ከግለኝነትም (individualism) ሆነ ከግል አምልኮ (Cult of Personality) ጽንፍ በመራቅ በክርስቶስ አካል ውስጥ በሚዛናዊነት እንመላለስ።
ሕይወት ያለ ኢየሱስ ማለት መብራት በሌለበት ከሶኬት ጋር መታገል ማለት ነው። 👇👇👇👇 https://vt.tiktok.com/ZS4yufopY/
ትላንት ይህን ቪድዮ ቲክቶክ አጥፍቶት ነበር። እና Appeal አድርጌ ዛሬ ተመልሷል። የሚገርመው ብዙ ሰዎች በቪድዮው የቀረበው ሐሳብ የእነርሱን ሕይወት እንደሚወክል በውስጥ መስክረውልኛል። አንዳንዶቹ ደግሞ በማኅበራዊ ሕይወታቸው በቪድዮው በተዘረዘሩት መንገዶች መኖራቸው የፖርኖግራፊ ሱስ ውጤት እንደሆነ ገና አሁን መረዳታቸውን ገልጸዋል። እንግዲህ እንዲህ ጠቃሚ ከሆነ ተመልሶ እንዳይጠፋና ለብዙዎች እንዲደርስ ቪድዮውን አጋሩት። እና ኮፒ ሊንክ ይደረግ። https://vt.tiktok.com/ZS4UVJYgU/
ሰሞኑን ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ሲመላለስ ለተመለከትነው በ100K እርቃኔን ለማሳየት ዝግጁ ነኝ ለሚለው ቪድዮ የተሰጠ ምላሽ በቲክቶክ አስቀምጫለሁ። ምላሹ ልጅቷ ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን ከእርሷ ንግግር በመነሣት በዘመናችን ለወሲባዊ ቀውስ ምክንያት የሆኑ ሦስት ፍልስፍናዊ ውድቀቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በዚህ መልኩ ቪድዮ ሥሠራ የመጀመሪያዬ ነው😁 ተመልከቱት፦ https://vt.tiktok.com/ZS4AvJEUu/
ይህ የትምህርቱ ማስታወሻ ነው።
1ኛ ጴጥሮስ ተከታታይ ትምህርት ክፍል 4፦ መንፈሳዊ ብስለት (1፥22-2፥25) 👉 የመንፈሳዊ ብስለት ምንነት 👉 የመንፈሳዊ ብስለት አስፈላጊነት 👉 የመንፈሳዊ ብስለት አቅጣጫዎች
ወደ ፊት እኖራለሁ፤ ወደ ኋላ እረዳለሁ!! የፖርኖሲስ ትውልድ መጽሐፍን ስጽፍ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የምማረውን የሕክምና ትምህርት አቋርጬ ለረጅም ወራት በአዲስ አበባ በኪራይ ቤት ኖሬያለሁ። አቤት በወቅቱ የነበረው ፈተና!! ብቸኝነት፣ ግራ መጋባት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የቤት ኪራይና ተያያዥ ወጪዎቹ... ምኑ ተቆጥሮ ያልቃል። በወቅቱ የምሻገረው፣ የሚያልፍ ወይም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ያለ ከቶ አይመስልም ነበር! ዛሬ ላይ ቆሜ ወደ ኋላ ስመለከት ግን የእግዚአብሔርን መልካምነት እመለከታለሁ። እግዚአብሔር መልካም ነው የሚለው ቃል አሁን ለእኔ ሕያው የሆነ የሚነዝር ቃል ነው! እርሱ መልካም ነው ስል ያነበብሁትን አይደለም፤ በሕይወቴ ያየሁትን እያወራሁ እንጂ። የሚደንቀው ነገር አሁን በዛ ከባድ የሕይወት መስመር ውስጥ በማለፌ ጌታን አመሰግነዋለሁ። ብዙ ተሠርቼበታለሁና! አይገርምም? ስናልፍባቸው ያለቀስንባቸው፤ ወደ ኋላ ስንመለከታቸው የምናመሰግንባቸው መሆናቸው? የመከራ ዓመታት፣ የመብሰያ እሳት መሆናቸው አያስደንቅም? ፑሪታኑ ቶማስ ዋትሰን እንዲህ ይላሉ፦ አንዳንድ የእግዚአብሔር መንገድ እና ውሳኔዎች፣ ልክ እንደ ዕብራይስጥ ፊደላት፣ ወደ ኋላ (ከተፈጸሙ በኋላ) ሲነበቡ ነው የምንረዳቸው። ፈላስፋው ሶረን ኬርከጋርድ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፦ ሕይወትን የምንኖረው ወደ ፊት እየሄድን ነው፤ የምንረዳው ግን ወደ ኋላ ስንመለከት ነው።
አንድ ሰው ፖርኖግራፊ እንደሚመለከት ፍንጭ የሚሰጡ 5 ማኅበራዊ ባሕርያት (አምስቱ መ'ዎች) 👇👇 https://vt.tiktok.com/ZS4MFDcXD/
ዘመናችን የቀውስ ቋት ነው፤ እንደ ትውልድ የሚያተራምሰንም ብዙ ነው፡፡ በመካከላችን መርዛማ ፍሬ የሚያፈራ ክፉ ዛፍ ተተክሏል፡፡ ፖርኖግራፊ ታዲያ የዚህ ዛፍ ጎልቶ የሚታይ ታላቅ ፍሬ እንጂ ሥሩ አይደለም፡፡ የ‘ፖርኖሲስ ትውልድ’ መጽሐፍ ዋና ዓላማ የዛፉን መርዛማ ፍሬ መሬት ላይ ረግፎ እንዲጠፋ መታገል ብቻ አይደለም፤ የክፉውን ዛፍ ሥር ምሶ ከመሠረቱ መንቀል እንጂ! ፖርኖግራፊ በሰፊው የበቀለው በትውልዳችን ውስጥ ከሚታየው የማንነት፣ የምንነት እና የለምንነት ቀውስ ነው፡፡ እርሱ የታላቁ ፍልስፍናዊ ውድቀታችን መገለጫ እንጂ በተነጠለ ደሴት ላይ የቆመ ችግር አይደለም፡፡ የመጽሐፌም ዋና ዒላማ ችግሩን ከነሥር-መሠረቱ ማድረቅ ነው፡፡ የችግሩ መሠረት ታዲያ ምንድን ነው? ከተባለ ያለንበት የማንነት፣ የምንነት እና የለምንነት ቀውስ ነው። የፖርኖሲስ ትውልድ መጽሐፍም የችግሩን ጽልመት እና የመፍትሔውን ብርሃን ከዚሁ ጥልቀት ይነጽራል። ሁላችሁም ብታነቡት እጅግ ታተርፉበታላችሁ። 👉 መጽሐፉን ስታድየም በሚገኘው መሠረተ ክርስቶስ መጽሐፍ መደብር ታገኙታላችሁ። ወይም @Kenu_Lemma ላይ እኔን በማናገር ወደ ጥቁር አንበሳ በመምጣት (ሰዐቱን በውስጥ አሳውቃችኋለሁ) ከራሴው እጅ መረከብ ትችላላችሁ። https://t.me/Kenu_lemma/s/20
Click Instant view 🙏🙌 https://telegra.ph/Book-Review-bro-Kennan-Lemma-%E1%8B%A8%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%8A%96%E1%88%B2%E1%88%B5-%E1%89%B5%E1%8B%8D%E1%88%8D%E1%8B%B5-07-07
Click Instant view 🙏🙌 https://telegra.ph/Book-Review-bro-Kennan-Lemma-%E1%8B%A8%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%8A%96%E1%88%B2%E1%88%B5-%E1%89%B5%E1%8B%8D%E1%88%8D%E1%8B%B5-07-07
በክርስቶስ ያልሆነ በቀውስ ነው!! በክርስቶስ ያለን የተረጋጋ ማንነት! ሁላችሁም ተመልከቱት 👇👇👇👇 https://vt.tiktok.com/ZS4Rfcu5R/
📍ድሬደዋ የፖርኖሲስ ትውልድ መጽሐፍን ወደ ድሬደዋ ለመላክ ታቅዷል። ነገር ግን ለወላይታ ሶዶ እንዳደረግነው ቀድመው ላዘዙ ብቻ በቁጥር ስለምንልክ የመጽሐፉ ፈላጊዎች አሁኑኑ አናግሩኝ👉 @Kenu_Lemma
видео или голосовое, без подписи