MESFIN MAGO TULAMO
СтатистикаEducation Consultant and Tranair (ECT) https://www.youtube.com/@mesfin_12
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Видео
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 21
- 1/48двое суток
- 24
- 1/72трое суток
- 25
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሰውን መላዕክት አድርገህ ፍጹም አትቀበል፤ ሰይጣን አድርገም አትጥላ። ሚዛን ጠብቀህ በልኩ "እንደ ሰው" ተቀበል።
ራስህን ሁን! በአለማችን 8 ቢልየን የሰው ብዛት አለ የሚያስገርመው የሁላችንም የእጅ አሻራ የተለያየ ነው:: ሁሉም ነገር የሚጀምረው ራስን ከመሆን ነው። የሆነን ሰው ለመሆን በሞከርን ቁጥር ብዙ ነገራችንን እያጣን እንመጣለን። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ራስህን ሁን! ውስጥህን አፅዳ!
መልካም ነገሮችን ለማየት እይታህን ቀይር! አየህ አንተ በምትሄድበት መንገድ የምታየው የውስጥህን ነው። ማለትም ውስጥህ ሠላም ከሆነ ሠላምን ታያለህ ደስታ ከሆነ ደስታ የሚያመጡ ነገሮችን ታያለህ ፍቅር፣ ሀብት ሌሎችም እንደዚያው ስለዚህ አንተ የምታየው የሆንከውን ነው! ራስህ ላይ ስራ እይታህን ቀይር! ዛሬን ኑር!
https://youtube.com/@mesfin_12?si=fOCoLi4tTggxZ8Mx👈 please, subscribe it
ደሜን ለወገኔ፣ በሚተካው ደም የማይተካውን የሰውን ልጅ ሕይወት ማዳን ከእርካታ በላይ ነው።
ደሜን ለወገኔ፣ በሚተካው ደም የማይተካውን የሰውን ልጅ ሕይወት ማዳን ከእርካታ በላይ ነው።
ማንም አይፈልገኝም፣ ሰው እረስቶኛል ለምትሉ ሁሉ “ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም” (ዮሐንስ 14፥18) ✨ይህ ቃል ልብን ከማሞቅ አልፎ እቅፍፍ አድርጎ ይደግፋል። መተው፣ መረሳት የሰው ልጅ ብርቱ ህመም ነው። እኛ ብዙዎችን እንደረሳነው ሁሉ እኛም በሌሎች ዘንድ እንረሳለን። የረሳናቸውን አስታውሰን ከምንፀልይላቸው ይልቅ የረሱንን አስታውሰን እናዝናለን። ✨ ሀብታም ብትሆንም ትረሳለህ: ድሀ ብትሆንም ትረሳለህ፣ ትንሽ ብትሆንም ትረሳለህ : ትልቅ ብትሆንም ትረሳለህ፣ ወንድ ብትሆንም ትረሳለህ ሴት ብትሆኚም ትረሺያለሽ። ላለመረሳት፣ ላለመተው ምንም ዋስትና የለንም። እኛ እንኳን አጠገባችን ያሉ ሰዎችን ይቅርና እግዚአብሔርን የምንረሳ ደፋሮች፣ አዝለነው የምንዞረውን ሞትን የምንረሳ ምስኪኖች ነን። ✨ እናቴ በቀን ውስጥ በትንሹ ሁለት ጊዜ ትደውላለች። ምግብ በላህ? ራስህን ጠብቅ፣ አታምሽ በጊዜ ና! የሁልጊዜ ድምጿ ነው። ወደቤት እስክገባ ደጅ ደጅ እያየች ትጠብቀኛለች፤ ከለመደችው ሰዓት ገፋ ብሎ ካመሸሁባት ልብስ ይዛ አደባባይ ቆማ ትጠብቀኛለች። ለቤተሰብ ሁሉ ደውላ ልጄ ጠፋ ብላ ታስጨንቃቸዋለች። የእርሷ እንዲህ መጨነቅ ራሷን መጉዳት ለኔ ቢከብደኝም እውነተኛ ፈላጊዬ እንደሆነች ሳስብ ደግሞ ደስታ ይሰማኝ ነበር። እርሷን ካጣሁ በኋላ ስልኬ ላይ ስልኳ መጮህ ሲያቆም፣ በር በር አሻግሮ የሚጠብቀኝ ሳጣ ልቤ ያዝናል። እኔ እናቴን በሞት አጥቼ ነው ልበ አምላክ ዳዊት ግን በህይወት እያሉ ነው የረሱት የዘነጉት እግዚአብሔር ግን አስታዋሽ አባትና እናት ሆነው። ✨ ዛሬም ይህ ስሜት የሚሰማችሁ ሰዎች ትኖራላችሁ። አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችሁ ብቻችሁን የቀራችሁ ይመስላችኋል። ሰዎች ሊተዉን ይችላሉ፣ ጓደኞች ሊርቁን ይችላሉ፣ ሁኔታዎችም ልባችንን ሊያስጨንቁ ይችላሉ። ነገር ግን ኢየሱስ የሰጠን ተስፋ ከሁሉ በላይ ነው፤ “አልተዋችሁም” ይለናል። ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ነው ፈፅሞ ከህይወታችን አይለይም ማለት ነው። ✨በደስታችንም ሆነ በሐዘናችን፣ በስኬታችንም ሆነ በፈተናችን እርሱ አይለየንም። እኛ እርሱን ስንፈልገው ይቀርበናል፣ ስንጸልይ ይሰማናል፣ በቃሉም ያበረታታናል። ምንም ዓይነት ችግር ቢኖር እግዚአብሔር አይተወንም። እርሱ የታመነ አምላክ ነው። ሰው ከጎናችን ቢሆን ጊዜያዊ ነው ጊዜያዊ ያልሆነው አምላክ ለዘላለም ከእኛ ጋር ነው። ✨ አንድ ፅሁፍ ሳነብ የወደድኩት ነው። "አንድ በእድሜ የገፉ አባት የእጅ ስልካቸውን ይዘው ሰሪ ቤት ይወስዱታል። ልጄ ይቺ ስልክ ተበላሽታብኝ ነው እባክህ አስተካክልልኝ ይሉታል። ልጁም ተቀብሎ ስልኩን ሲፈትሸው ስልኩ ምንም አልሆነም ይሰራል። አባቴ ስልኩ እኮ ምንም አልተበላሸም ይሰራል አላቸው። እኙህም አባት ታዲያ ለምንድነው ልጆቼ ደውለውልኝ የማያውቁት አይፈልጉኝም ማለት ነው" ብለው ልባቸው እያዘነ ስልካቸውን ይዘው ተመለሱ። ልጅ ወላጁን ይተዋል፣ ይረሳል፤ ወላጅም ልጁን ይረሳል። ለአፍታ ግን አይኖቹን ከእኛ ላይ የማይነቅል፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ የማይተወን አልተዋችሁም ብሎ ቃል የገባልን ጌታ አለ። ✨ የመተው፣ የመረሳት ስሜት ሲሰማችሁ ይህን አስታውሱ የማይረሳው ጌታ ከእኔ ጋር ነው በሉ!! ✍አዶኒ
✍️ ልጁ አባቱን "የህይወት ዋጋ ስንት ነው?" ብሎ ጠየቀው። አባቱም አንድ የሚያምር ድንጋይ ከሰጠው በኋላ የተለያዩ ቦታዎች እንዲወስድ ከነገረው በኋላ እንዲህ አለው። "ማንም ዋጋውን ቢጠይቅህ ምንም እንዳትናገር፤ ሁለት ጣቶችህን ብቻ ወደ ላይ አንሳ።" ... ልጁ በመጀመሪያ ወደ ገበያ ሄደ፡ አንዲት አሮጊት "ስንት ነው?" ስትለው ሁለት ጣቱን አሳያት። እሷም"ሁለት ብር? እሺ እገዛዋለሁ" አለችው። ... ቀጥሎ ወደ ሙዚየም ሄደ፡ እዚያም ዋጋውን ሲጠይቁት ሁለት ጣቱን አሳየ። "ሁለት ሺህ ብር? እሺ እገዛዋለሁ"አሉት። ... በመጨረሻ ወደ ከበሩ ድንጋዮች መደብር ሄደ፡ ባለሱቁ ድንጋዩን ሲያይ ደንግጦ "ይህ እኮ በአለም ላይ ድንቅ የሆነ የከበረ ድንጋይ ነው! ስንት ነው ዋጋው?"አለው። ልጁ አሁንም ሁለት ጣቱን አሳየ። ባለሱቁም "ሁለት መቶ ሺህ ብር? አሁኑኑ እገዛዋለሁ!" አለው። ... ልጁ እየሮጠ ወደ አባቱ ተመልሶ ሁኔታውን ነገረው። አባቱም ልጄ የህይወትህ ዋጋ የሚወሰነው ራስህን በምታስቀምጥበት ቦታና በምትመርጣቸው ሰዎች ነው። በአንዳንዶች ዘንድ ዋጋህ 'ሁለት ብር' ብቻ ሊሆን ይችላል፤ ዋጋህን በሚያውቁ የከበሩ ሰዎች ዘንድ ደግሞ 'ክቡር' ነህ።" #NB ዋጋችንን በሚያቃልሉ ሰዎች ዘንድ መገኘት ልክ አይደለም፤ ራስህ በትክክለኛው ቦታ ያስፈልጋል።
видео или голосовое, без подписи
⭐️የንስር አሞራ አስገራሚ ባህሪ እና አንተ 🔤 አንቺ እና 🔤 እኔ 🔤 ✅ስለ ንስር አሞራ ስነግርህ ከሚገርም መሳጭ ታሪክ ጋር ነው ... እውነት እውነት እልሃለሁ የንስር አሞራ ታሪክ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለና ከራስህ ጋር እያዛመድክ ካነበብከው መጨረሻህን ድል ድል ታሸተዋለህና በፍቅር ተከተለኝ። ➖➖ልጀምርልህ ➖➖ ✅ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ጸሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው የአለማችን ፍጥረት ነው ። አንድ ንስር በመብረር ላይ እያለ ቁራወች ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሁነው ከበው ሲጮሁበት ወደጸሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ጸሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋቸዋል!! ✅ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል ፣ ✅ ንስር ከ5-7 ኪሜ ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣ ✅ ንስር ለአደን እስከ 120 km አካሎ ይበራል፣ ✅ ንስር መመጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሁኖ ሃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣ ✅ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣ ✅ንስር ሲታመም ጸሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣ ✅ ንስር 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣ ✅ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ... ✅የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ... ✅ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ... ✅ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል። ✅እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። ⭐️1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ? ⭐️2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ? ⭐️የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል። ✔️፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል። ✔️፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል። ✔️፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡ ✔️፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል። ✔️፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ✔️ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡ 🔣 🔣 🔣 ወዳጄ ሆይ:- ✔️ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ...በቃ! ... ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ... ፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ... ፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ... 🔤 አስተውል 🔤 ✅ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ... ✅፩ኛ. ራስህን ከመጥፎ ነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ...ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል። ✅፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ። ✅፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ። ✅፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ። ✅፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በኋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል። 🥰ሲጠቃለል ... ✅አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በኋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል። ✅ለዚህ ነው ንስር የጥንካሬ የአይበገሬነት እና የከፍታ የመታደስ የአትኩሮት የሐያልነት ምልክት የሆነ ልዩ ፍጡር በመሆኑ በርካታ ሐገሮች ንስርን ምልክታቸው በማድረግ የሚጠቀሙት!! 🔤ንስር እንሁን 🔤 ✍️መልካም ጊዜ!
видео или голосовое, без подписи
በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች፣ በተለያዩ ደረጃዎች ለተመረቃችሁ ለቀድሞ ተማሪዎቼ እና ጓደኞቼ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ! Congratulations 🎉🎉🎉
ፍቅር የሌለበት ሕይወት ምንም ፋይዳ የለውም። ምን ዓይነት ፍቅር መፈለግ እንዳለብህ ራስህን አትጠይቅ፤ መንፈሳዊ ወይስ ቁሳዊ፣ መለኮታዊ ወይስ ምድራዊ፣ ምስራቃዊ ወይስ ምዕራባዊ... መለያየት ሁልጊዜ ሌላ መለያየትን ብቻ ነው የሚወልደው። ፍቅር ምንም ዓይነት ስያሜም ሆነ ትርጉም የለውም። እሱ እንደሆነው ነው፤ ንጹሕ እና ቀላል። ፍቅር የሕይወት ውኃ ነው። አፍቃሪ ደግሞ የእሳት ነፍስ ነው! እሳቱ ውኃን ሲወድ አጽናፈ ዓለም በተለየ ሁኔታ ይሽከረከራል።
||የሕይወት መርሆዎች || ለደስተኛ ሕይወት ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ። * * * * 1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ። ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ። 2. አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው፦ የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው ? ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና። 3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤ 4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት ጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር። 5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤ 6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤ 7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ብዙ ሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስጠው። 8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው።እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና? ዶ/ር ምህረት ደበበ
ሰኔና ሰኞ ሌላ ምንም የተለየ ተአምር የለም፡፡ ለየት ያደረገው የማህበረሰቡ እምነት ነው፡፡ እኔ ገና ህፃን እያለሁ በዚህ ቀን ቤተሰቦቼ ፍርሃት ውስጥ ሲገቡ አስታውሳለሁ፡፡ ገና 3ኛ ክፍል እያለሁ በ1990 ዓ.ም ሰኔና ሰኞ እንደተገናኙ አስታውሳለሁ፡፡ በጊዜው የእናቴን ፍርሃት አይቼ ሰኔና ሰኞ ከተገናኙ ምን እንደሚከሰት ስጠይቃት "ሰኔና ሰኞ ከተገጣጠመ፣ ረሃብ፣ ችግር፣ ሞትና መከራ የሚበዛበት ዓመት ይሆናል፡፡" ብላ መልሳልኛለች፡፡ አሁን በዘመነ መረጃ እና በኤ አይ (AI) ዘመን እንደዚህ ዓይነት ሀሳቦችን ለመቀበል በመረጃ ማስደገፍ አስፈላጊ ነው፡፡ መረጃዎችን ለማጣራት እንደሞከርኩት፣ የሆነ ጊዜ ሰኔ አንድ ሰኞ በሆነበት ወቅት በሀገራችን አንዳንድ ክስተቶች እንደተከሰቱ የአፍ ታሪክን ዋቢ በማድረግ በተለያዩ መጽሐፍት ተተርኳል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለማጥናት እንደሞከሩት ግን ድርጊቱ መሠረተ ቢስና የአፍ ታሪክ ብቻ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት የአፍ ታሪኮች ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ መጥተዋል፤ አሁን ግን መቆም አለባቸው፡፡ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት "ሰኔና ሰኞ" ብሎ በዩቱዩብ ፈልጎ ማየት ይቻላል፡፡ መጥፎ ይሆናል ብሎ ማመን መጥፎ ነገር ስለሚያስከትል ከጭፍን እምነት ወጥተን በጎ በጎውን ማሰብና መመኘት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ምድር በማንኛውም ጊዜ አስቸጋሪ ክስተቶች ይፈጠራሉ እንጂ ሰኔና ሰኞን ጠብቀው ባለመሆኑ አላስፈላጊ ፍርሃት ውስጥ መግባት ተገቢ አይደለም፡፡ ሰኔና ሰኞ በመገጣጠሙ የሚፈጠር ችግር አይኖርም፡፡ ሁሉም መልካም ይሆናል፡፡
ሕይወት ልክ እንደ ዛፎች ሁሉ የየራሷ ወቅቶች አሏት። ሁሉም ነገር ሞልቶ የተትረፈረፈ የሚመስልባቸው ጊዜያት አሉ፤ እንደዚሁም ሁሉም ነገር በዝምታ የሚረግፍባቸውና የሚበታተኑባቸው ጊዜያት አሉ። ምናልባት ሰዎችን፣ አጋጣሚዎችን፣ ዕቅዶችን ወይም በአንድ ወቅት ትተማመንባቸው የነበሩ የራስህን ክፍሎች ልታጣ ትችላለህ። በእነዚያ ወቅቶች፣ ሕይወት ያለህን ነገር ሁሉ የምትወስድብህ ይመስል ይሆናል። ነገር ግን ዛፎች አንድ ውብ ትምህርት ያስተምሩናል፦ ቅጠል መርገፍ የዛፉ መጨረሻ አይደለም፤ ለዕድገትና ለዕድሳት ዝግጅት እንጂ። ከአውሎ ነፋስና ከብርቱ ክረምት በኋላ እንኳን ባዶ ሆነው ቢቆዩም፣ ሥሮቻቸው ግን አሁንም በምድር ተተክለዋል፤ ታጋሽ ሆነውም እንደገና የሚያብባበትን ጊዜ ይጠባበቃሉ። ስለዚህ፣ ሕይወት በአሁኑ ሰዓት ከባድ መስላ ከታየችህ ይህንን አስታውስ፦ ጊዜያዊ መጥፋት ዘላቂ ሽንፈት ማለት አይደለም። አንዳንዴ ወቅቶች የሚመጡት ገና ባልተመለከትከውና ባልተረዳኸው መንገድ እንድታድግ ነው። እንዲህ የሚል የጃፓን ምሳሌ አለ፦ "ሁሉንም ነገር እያጣህ እንደሆነ ከተሰማህ፣ አስታውስ፤ ዛፎች በየዓመቱ ቅጠሎቻቸውን ያረግፋሉ፣ ነገር ግን አሁንም እንደቆሙ ናቸው እና የተሻሉ ቀናት እስኪመጡ ድረስ ይጠባበቃሉ።" #ታገስ! https://t.me/mesfeect
🚀 ታላላቅ መሪዎች የሚያደርጓቸው 10 ነገሮች ታላላቅ መሪዎች የሚለዩት በስልጣን ማዕረጋቸው ሳይሆን በሚያሳዩት የዕለት ተዕለት ልማዳቸው ነው። የላቁ መሪዎች በቋሚነት የሚያደርጓቸው 10 ነገሮች እነሆ፦ 💡 1. ግልጽ የሆነ ራዕይ ይፈጥራሉ ታላላቅ መሪዎች የት እንደሚሄዱ ያውቃሉ፤ ሌሎችም ይህንን ራዕይ እንዲያዩ ይረዳሉ። ለሰዎች አቅጣጫን እና ዓላማን ይሰጣሉ። 💡 2. በግልጽ እና በተደጋጋሚ ይነጋገራሉ ጥሩ አመራር ማለት ውስብስብ ንግግሮችን ማቅረብ አይደለም። ታላላቅ መሪዎች ግቦችን በግልጽ ያስረዳሉ፣ በጥሞና ያዳምጣሉ፣ እንዲሁም የሐሳብ ልውውጥን ክፍት ያደርጋሉ። 💡 3. በአርዓያነት ይመራሉ ሰዎች ከቃላት ይልቅ ለድርጊት የበለጠ ትኩረት ይሰጣሉ። ታላላቅ መሪዎች ከሌሎች የሚጠብቋቸውን መስፈርቶች፣ ዲሲፕሊን እና አመለካከቶች በራሳቸው ሕይወት በተግባር ያሳያሉ። 💡 4. እምነትን ይገነባሉ እምነት የሚመነጨው ከቋሚነት፣ ከሐቀኝነት እና ከኃላፊነት ነው። ታላላቅ መሪዎች የገቡትን ቃል ይጠብቃሉ፤ ስህተት ሲሠሩም በግልጽ ይቀበላሉ። 💡 5. አስቸጋሪ ውሳኔዎችን ይወስናሉ አመራር ማለት ብዙ ጊዜ በቂ መረጃ ሳይኖር ውሳኔዎችን መወሰን ነው። ታላላቅ መሪዎች ከውሳኔ መዘግየት ይልቅ፣ ለውጤቱ ኃላፊነት በመውሰድ እርምጃ ይወስዳሉ። 💡 6. ሌሎች ሰዎችን ያበረታታሉ (ስልጣን ይሰጣሉ) ሁሉንም ነገር በራሳቸው ከመቆጣጠር ይልቅ፣ ታላላቅ መሪዎች የሰዎችን ችሎታ ያዳብራሉ፣ ኃላፊነትን በሌሎች ላይ ይጥላሉ፣ እንዲሁም ሌሎች እንዲያድጉ ይረዳሉ። 💡 7. በጭንቀት ውስጥ ሳይቀር ይረጋጋሉ ቡድኖች እርግጠኛ ባልሆኑ ጊዜያት ወደ መሪዎቻቸው ይመለከታሉ። መረጋጋት፣ ጽናት እና ስሜትን መቆጣጠር ፈታኝ በሆኑ ጊዜያት መረጋጋትን ለመፍጠር ይረዳሉ። 💡 8. ይለማመዳሉ እና መማራቸውን ይቀጥላሉ ታላላቅ መሪዎች ሁሉንም ነገር እንደሚያውቁ አያስቡም። የማወቅ ጉጉታቸውን ይጠብቃሉ፣ ለውጦችን ይቀበላሉ፣ እና ያለማቋረጥ ራሳቸውን ያሻሽላሉ። 💡 9. ሌሎችን ያደንቃሉ እና ያከብራሉ ሰዎች ዋጋ እንዳላቸው ሲሰማቸው የተሻለ ውጤት ያመጣሉ። ታላላቅ መሪዎች ስኬቶችን ያከብራሉ፣ ምስጋናን በልግስና ይሰጣሉ፣ እንዲሁም የሰዎችን ጥረት ይገነዘባሉ። 💡 10. ከራሳቸው በላይ ለሆነ ትልቅ ዓላማ ይሠራሉ ምርጥ መሪዎች ትኩረት የሚያደርጉት በግል ጥቅማቸው ወይም ስልጣናቸው ላይ ሳይሆን በተልዕኮ፣ በዕሴቶች እና በሚያመጡት በጎ ተጽዕኖ ላይ ነው። አመራር ማለት በስልጣን ላይ መሆን አይደለም። አመራር ማለት ሰዎች በአንድነት ሆነው የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ማነሳሳት ነው።
видео или голосовое, без подписи
ከውቅያኖስ ፊት ለፊት ተቀምጠህ ማዕበሉን ስትመለከት፣ አእምሮህ ከውኃው ምት (ሪትም) ጋር መጣጣም እንደሚጀምር እና ሀሳብህ በተፈጥሮው እየረጋጋና እየሰከነ እንደሚሄድ የሚገልጽ አንድ ቲዎሪ አለ!" (ታይኒ ቡድሃ) ታላላቅ ውኃዎች ነፍሳችንን በሚጠሩበት መንገድ ውስጥ አንድ ረቂቅ እውነት አለ። በባሕሩ ዳርቻ ላይ ተቀምጠህ ዓይኖችህ በውቅያኖሱ ማብቂያ በሌለው እንቅስቃሴ ላይ እንዲያርፉ ስታደርግ፣ በውስጥህ አንድ ቅዱስ ነገር መሆን ይጀምራል። ውቅያኖስ አይቸኩልም። ዓለም ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦ በማያውቅ ጽኑ እና ጥንታዊ ምት ወደ ፊት እየተንከባለለ እና ወደ ኋላ እየተሳበ ይተነፍሳል፣ ያስተነፍሳል። በፊቱ ስትቀመጥ፣ አእምሮህ በተፈጥሮው ማዳመጥ ይጀምራል። የዚህችን ዓለም ከባድ ሸክም የተሸከሙትና የተጣደፉት ሐሳቦችህ፣ ያንን ዘላለማዊ መነሳትና መውደቅ ቀስ በቀስ መንጸባረቅ (መከተል) ይጀምራሉ። በአንድ ጥራዝ ባለው የውኃ ብርጭቆ ውስጥ ያለው ደለል ወደ ታች እንደሚሰምጠው ሁሉ፣ በውስጥህ ያለው መቅበዝበዝም መሟጠጥ ይጀምራል። አተነፋፈስህ ይጠልቃል፣ ትከሻዎችህ ይላላሉ፣ እና ሐሳቦችህ በተፈጥሮአቸው ይረጋጋሉ። ነፍስህ ከማዕበሉ ጸጥታና ጥንካሬ ጋር ስትስማማ፣ ወደ ራሷ የተፈጥሮ የሰላም ሁኔታ የምትመለስበትን መንገድ ታገኛለች። ውቅያኖሱ ታሪክህን አይቀይረውም፣ ነገር ግን ከላይኛው ገጽ ላይ ካለው ማዕበል በታች፣ አንተም ጭምር ሰፊና ጥልቅ የሆነ ጸጥታ እንዳለህ ያስታውስሃል።🌊🙏
በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰው፣ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑን መጸዳጃ ቤት መጠቀም ይጀምራል። በዚያው መሃል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚያች ቅጽበት አውሮፕላኑ በኃይል መገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀምራል። ሰውዬውም ደንግጦ “ወይኔ! ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ህዝብ ጨረስኩኝ!” ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ስራውን ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው “አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!” ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም፣ ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም። መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው በስጋት ቀስ ብሎ፣ “ይቅርታ፣ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻችሁ ነበር አይደል?” ይለዋል። ሰውዬውም “ኧረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያህል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይቀመጡም፤ ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። የአየሩ ሁኔታ ትንሽ አስቸጋሪ ስለነበረ ነው አውሮፕላኑ የተንገጫገጨው” ይለዋል። ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ፤ የሆነች ነገር ነክተው ህይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያህል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን፣ የህይወትህ ካፒቴን ክርስቶስ ኢየሱስ ጋር እንዳለ ነው። እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ፣ ያቺን ቀይ ነገር እየነካኩ ህይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና፣ እንደዚህ ያሉ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች በእሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል!