- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 202
- 1/48двое суток
- 231
- 1/72трое суток
- 249
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
❝እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።❞ ዘፍጥረት 16: 13
እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። ሮሜ 8:13-14
❝ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፦ ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው። በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ፦ ተጸጸትሁ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።❞ ሉቃስ 17፥3፡4
❝አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።❞ ኢሳይያስ 6: 3
እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነት ይሽራል፤ ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቈርጣል፥ በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል። መዝሙር 46:9
"እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተ ማድረግ የሚገባችሁ ጸጥ ብላችሁ ሁኔታውን መጠበቅ ብቻ ነው።” ዘጸአት 14:14
без подписи
без подписи
ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤ ማንም ግን እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱ በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው። 1 ቆሮንቶስ 8:2-3
❝ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ የወይራ ሥራ ቢጐድል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።❞ ዕንባቆም 3-17:18
❝የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል።❞ —ምሳሌ 1: 33
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። ሮሜ 6:23
❝እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።❞ 1ኛ ሳሙኤል 2: 9
በቃላት ሊገለጥ ስለማይቻል ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። 2 ቆሮንቶስ 9:15
❝ያድናል ይታደግማል በሰማይና በምድርም ተአምራትንና ድንቅን ይሠራል ዳንኤልንም ከአንበሶች አፍ አድኖታል።❞ ዳንኤል 6: 27
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። ዘዳግም 6:5
❝አቤቱ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ አንተ ግን ትኖራለህ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ ይለወጡማል አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።❞ መዝሙር 102-25:27
የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1 ቆሮንቶስ 7:31
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘላለም ታላቅ ይሁን፤ የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን። 2 ሳሙኤል 7:26