የልብ ወግ
Статистика"ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም" (መክ 1:9) ስለሕይወት በውስጣችሁ የያዛችሁትን ሃሳብ፣ ጭንቀትና ጥያቄ የምታጋሩበት መድረክ ነው። የሚገጥሙን ፈተናዎች ሁሉ ሌሎችም ያለፉባቸው ናቸውና እዚህ በነፃነት ምክርና መፍትሄ ታገኛላችሁ። @yeneTarik_bot
- Последний пост
- 1 февр.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ትንቢተ ኢሳይያስ እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ፤ ድሃውንም በጡጫ ትመታላችሁ፤ በምትጮኹበት ጊዜ ድምፃችሁ እንዲሰማ ለእኔ ትጾማላችሁ? ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም። እኔ ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለሁም፤ እንደዚችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያሳዝን፥ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፥ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም፤ ይህ ጾም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም። 58÷4-5 መልካም እለተ ሰንበት @minenamakrot
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰለ ጋብቻ ከተናገረው ወጣቶች ትዳራቸው፥ ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንዲኾንላቸው ከፈለጉ ከኹሉም አስቀድመው ሊያደርጉት የሚገባቸው ልክ እንደ ቃና ዘገሊላው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጋቸው ዕለት እንዲገኝ ማድረግ ነው፡፡ ወቅቱ የሰርግ ነውና ጋብቻችሁን የምትፈጽሙ መልካም ጋብቻ
መልካም በዓል
🕊 ምስጢራዊ ታሪክ (ID 21): ሰላም። 26 አመቴ ነዉ። በእዚህ እድሜዬ እንኳን ሰዉ መቅረብ አልፈልግም ። ቶሎ ይሰለቹኛል። ብቻዬን ስሆን ዝም ስል ብቻ ሰላም አገኛለሁ። ከዚህ በፊት በሰራሁት ስህተት ምክንያት ራሴን እወቅሳለሁ። ያንን ስህተት ባልሰራ ኖሮ እኮ ነገሮች ጥሩ ይሆኑ ነበር ብዬ አስባለሁ። ስህተቴት ጥፋቴን በንሠሀ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለኝ ባምንም ለራሴ ግን ይቅርታ አድርጌ አዲስ ህይወት መጀመርም ሆነ ያንን ነገር መርሳት አልቻልኩም። ጠዋት ስነሳ ራሴን ከ 8 ወይም 10 ዓመት በፊት ባገኘሁት ብዬ እመኛለሁ። ፀፀት ሰላም አሳጥቶኛል። ራሴን መዉቀስ ስልችትት ብሎኛል። ያለፈዉን መርሳት እፈልጋለሁ። ማስመሠል፣ መዋሸት ስልችትትት ብሎኛል ። በቃ ዝም ማለት ብቻዬን መሆን ብቻ ነዉ የምፈልገዉ። አሁን አሁን ብስቅ ብጫወትም still ባዶነት ይሰማኛል ። ብቻዬን የምሆንበት ሰዓት ይናፍቀኛል። የልቤን የማማክረዉ ሰዉ ከንሠሀ አባቴ በስተቀር የለኝም። እንዲህ ሆንኩ ብዬ ብናገር ሰዉ የሚረዳኝ አይመስለኝም ። judge የምደረግም ስለሚመስለኝ እፈራለሁ። በዚህም ምክንያት ምንድን ነዉ እንደዚህ የሚያስተክዝሽ፣ ለምን ሰዉ አትቀርቢም ምናምን ሲሉኝ እዋሻለሁ ፣እስመስላለሁ። ወይም ለይምሰል ወሬ አበዛለሁ በቃ ዝም ብዪ እለፈልፋለሁ። ግራ ገብቶኛል 😣😖 ለፀሎት እንኳን ስቆም እግዚአብሔርን እንደ ቅርብ አባት እመቤቴን እንደ እናት እንደ ጓደኛ ላወራት አስብና ከእናቴም ከአባቴም ጋር እንደዛ አይነት ቀረቤታ ስለሌለኝ ስሜቱን ሰለማላዉቀዉ ሞኝ የሆንኩ ወይም እግዚአብሔር እያሞኘሁት ይመስለኛል ። ቤተክርስቲያን ሄጄም ምን እንደምፀልይ አላዉቅም አቡነ ዘበሰማያት ብዬ ከዛ ዝም ብዬ ቁጭ እላለሁ። የማስበዉን አላዉቅም የምፈልገዉን አላዉቅም ።የደነዘዝኩ ይመስለኛል ። ትናንት ላይ stuck እንዳደረገ ሰዉ አይይይ ይሄኔ እኮ ምናምን እያልኩ አስባለሁ። የኔ ችግር መፍትሔ አለዉ ይሆን ካለዉ ንገሩኝ🙏🙏 ። በዛዉም አርምሞን እንዴት ልለማመድ፣ ዉሸት ፣ሀሜት፣ ማስመሰል እና ወሬ ማብዛት ነዉ(ዝም አለማለት) ። ከነዚህ ሀጢአቶች እንዴት ልላቀቅ ? እባካችሁ መፍትሔ ስጡኝ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እንደተለመደው ያላችሁን የሕይወት ተሞክሮ @yeneTarik_bot ላይ /advice 21 ብላችሁ ላኩልን ። አልያም ፦ @petros2
ሰላም እህቴ መጀመሪያ ሳነበው ደነገጥኩ ሰው እንዴት በዚህ ልክ ይመሳሰላል ብዬ ስሜን አልጠቀሽም እንጂ የኔ ታሪክ በይው ነገሩን አላብዛብሽ መፍትሄ የመጀመሪያ ከመሬት ተነስቶ ዝምተኛ መሆን የማይቻል ነው ቢቻል እንኳን ከባድ ነው ሰውንም ማስደንገጥ ነው ምን መሰለሽ ወደ ስራ ስትሄጂ መንገድ ላይ ትኩረትሽን ለመሰብሰብ በስልክሽ መዝሙር አልያም ስብከት download አድርገሽ ከቤትሽ ስራ ቦታ ድረስ እሱን እየሰማሽ ሂጂ አንድም ለነፍስሽ ቃለ እግዚአብሔር ሕይወት ነውና አንድም ደግሞ ስራ ስትገቢ መንገድ ላይ እንዲ ተፈጥሮ ከሚለው ወሬ አንድ ደረጃ ቀነሽ ሌላው ትልቁ መፍትሔ ቀልድ ሊመስልሽ ይችላል ግን trust me ይጠቅምሻል ያው ስራ ስንገባ የምናውራው የተወሰነ ሰአት ነው ያው ስራ ስለምንሰራ አንቺ ምን ታደርጊያለሽ መሰለሽ ጾም ያልሆነ ቀን ከረሜላ አፍሽ ውስጥ አድርጊና ቀኑን ዋይ ልክ አውሪ አውሪ ሲልሽ አፍሽ ውስጥ ከረሜላ ስላለ እንደ ቀፍሞ ያለ ልክ ከማውራት ትንሽም ቢሆን ይጠብቅሻል ማውራት ስታቢ ከረሜላውን ለምን አፋሽ ውስጥ እንዳለ ታስተውያለሽ ከጠቀመሽ ብዬ ነው አንቺ በጣም ጎበዝ ሴት ነሽ ምክንያቱም ችግርሽን ለይተሽ ስላወቅሽ አውቀሽም መፍትሄ ስለጠየቅሽ ደግሞ እግዚአብሔር ይህን ስሜት ያይልሻል ከዚህ ለመላቀቅ ያደረግሽውን ይቆጥርልሻል ችግርን ማወቅ ለመድኅኒቱ 50% መጠጋት ነው የቅዱሳን አምላክ ካንቺ ጋር ይሁን ሁሉም የምታይው ሰው የራሱ ደካማ ጎን አለው ምናልባት እሱና እግዚአብሔር ብቻ የሚያውቁት ይሄኔ አሁን ችግር ነው ባልሽው ነገር ሰው ታድላ ተጫዋች ናትኮ እያለም ይቀናል ስለዚህ አትጨነቂ የቆረበ ሰው አይስቅም አይጫወትም የሚል ህግ የለም ነገርን ሁሉ በልክ ያድርግ እንጂ 😊 የጸሎቱን ነገር ዘነጋሁት ምን መሰለሽ በአንድ መንደር እያለፍሽ ነው እንበል imagen that እና ሰዎች ሀይለኛ ውሻ አለ በጣም ይጮሀል ከሱ አለፍ እንዳልሽ ደግሞ የተኛ ውሻ አለ ቢሉሽ በትር (ዱላ) ይዘሽ የምታልፊው በሚጮኸው ወይስ በተኛው ?መልሱ ይታወቃል በሚጮኸው ውሻ በኩል ነው ሰይጣንም እንዲሁ ነው የማይጸልይ የማይጾም በተለይ ቅዱስ ቁርባን የማይቀበል ሰው ለሱ እንደተኛ ውሻ ነው በትር የተባለ (ፈተና ወይም መከራ) ማንሳት አይጠበቅበትም ምክንያቱም ተኝቷል ግን በበጎ መንገድ የሚሄደው ሰው ልክ እንደሚጮኸው ውሻ ነው ያስደነግጠዋል ለዛል በትር የተባለ መከራ ፈተና ችግር ያዘንብበታል የሱን ጩኸት ዝም ለማሰኘት አንቺ ስጋዊ ምላስሽን ዝም አሰኚ እንጂ ቅዱስ ቁርባን ጸሎት መንፈሳዊ ነገር እንዳትተይ አንቺን ተስፋ ለማስቆረጥ እሱ አይደክምም በተረፈ መንፈሳዊ መጽሐፍትን አንብቢ አርጋኖን የተሰኘ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፍ ላይ ሰይጣን ከበጎ ምግባራት አብዝቶ የሚጠላው ጸሎትን ነው ጸሎት ፍላጻ ነው አይኑን ያጠፍዋል ሰይፍ ነው እራሱን ወገቡን ይሰነጥቀዋል ከሚጸልይ ሰው አንደበት እሳት ወጥቶ ያቃጥለዋል በጸሎት በርቺ ክርስቲያን ሲጸልይ የግድ ሰይጣንን አባርራለሁ አቃጥላለሁ ማለት የለበትም አምላኬን ላመስግንበት ብሎ ነው ማሰብ ያለበት ይቅርታ አበዛሁት😊
/advise<story_9> ይገርማል የኔን ህይወት የሚኖር ሌላ ሰው አገኘሁ ምንም ነገር ሳይጨመር ሳይቀነስ እኔም እንዳንቺው ነኝ( ሴት ነሽ ብዬ አስቤ ነው) ሁሌም በራሴ በጣም ነው የምናደደው።ብቻ ከጠቀመሽ እኔ እያረኩ ያለሁትን ነገር ልንገርሽ። 1) በፊት እኔም በቃ ፀሎት ማድረግ እየፈለኩ እሰንፋለሁ እና አንድ ቀን ካቋረጥኩት ወር ምናምን ነው የማቋርጠው ከዛ ምን መፍትሄ አሰብኩ መሰለሽ ፀሎት መቀነስ 2 ሰአት ሙሉ ነው የምፀልየው የነበር በቃ ያገኘሁትን ሁሉ ፀሎት መፀለይ አሁን ሲገባኝ ቀስ እያልኩ እደርስበታለሁ ለጊዜው ግን ፀሎቴን ቀስ ብዬ እንድለማመደው ውዳሴ ማርያም ብቻ እፀልያለሁ ጭንቅላቴም ብዙ ነገር ነው ብሎ ስለማያስብ አይሰላችም። 2) አርምሞ እኮ ፀጋ ነው ፀጋን ደግሞ የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው።አየሽ ሰይጣን ሁሉንም ሰው አንድ አይነት ነገር አይደለም የሚፈትነው አንዳንዱን በገንዘብ አንዳንዱን በጤናው እንደኔና እንዳንቺ አይነቱን ደግሞ ራሱን እንዲወቅስ ተራ ነሽ እኮ ምንም ለውጥ አታመጪም መቼም አትለወጪም መቼም ጥሩ ክርስቲያን መሆን አትችይም እያለ ራስሽን እንድትወቅሺ እንድትጠይ ያደርግሻል የመጀመሪያው ይሄን መረዳት ነው ከዛ ግን ፃፊው እውነት እንደዚ መጥፎ ስሜት ሲሰማሽ ፃፊውና ከዛ ለራስሽ እግዚአብሔር መቼም እንደማይተውሽ ፅፈሽ ጨርሺ እኔን በጣም ነው ያገዘኝ እንደዚ ማድረጌ 3)ጌታችን ቃና ዘገሊላ በሰርጉ ቤት ተገኝቶ እያለ ወይን አልቆብናል ሲሉት ውሃ ቅዱ ሲላቸው አስተናጋጆቹ ግራ ገብቷቸው ነበር የጠየቁት ሌላ አርጉ የሚላቸው ሌላ ግን ግራ እየገባቸውም ምንም sense ሳይሰጣቸውም አደረጉት አይደል እንዴት እንደሆነ አያውቁም ግን ውሃውን ወደ ወይን ቀይሮ አስደሰታቸው የኛም ህይወት እንደዚ ነው አንዳንዴ አንቺ ይሳካልኛል አንቺ በዚህ መንገድ ነው ይሄንን የማደርገው የምትይውን ትቶ ጭራሽ ትርጉም የማይሰጥ ነገር ህይወችሽ ላይ የምታደርጊበት አጋጣሚ ይፈጠራል እንደዚ አይነት ነገር እየኖርኩ መቼ ነው ይሄን የማገኘው በዚህ ህይወት እየኖርኩ መቼ ነው የተፈጠርኩበት አላማ የሚገባኝ ....ብቻ ብዙ መመለስ የማትችያቸውን እንደ አስተናጋጆቹ ብዙ ግራ የሚያጋቡሽ ነገሮች ይፈጠራሉ መፍትሄው ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?ለምን እንደተፈጠርሽ ባይገባሽም መቼ ራስሽን እንደምታገኚ ባይገባሽም ዝምብለሽ በንስሐ,በቅዱስ ቁርባን በማመን መኖር በቃ መኖር እመኚኝ ምንም ነገር ሳታስቢ ዝምብለሽ ዛሬ ብቻ እንደምትኖሪ አሁን ባለሽበት ጥሩ ክርስቲያናዊ ህይወት ኑሪ ቀስ በቀስ ራስሽን እየተለወጥሽ ታይዋለሽ ካበዛሁት ይቅርታ እኔንም ያጋጠመኝ ፈተና ስለሆነ ካገዝኩሽ ብዬ ነው
እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ ? 🕊 ምስጢራዊ ታሪክ (ID 9): ሰላም እንደምን አላችሁ። መንፈሳዊ ህይወቴ ላይ መበርታት እፉልጋለሁ ደካማ ነኝ። በተደጋጋሚ ንሠሃ እገባለሁ ።በየ 40 ቀናቱም ቅዱስ ቁርባንን እቀበላለሁ። እንደዚህ ሆኖ በተመሳሳይ ሀጢአት እወድቃለሁ። አብዛኛዉን ጊዜ ለፀሎት እሰንፋለሁ። ፀሎት ስግደት የማድረግ ፍላጎት የለኝም፣ ቤተክርስቲያን ጠዋት አልሄድም በቃ ከየት እንደመጣ የማላዉቀዉ እንቅልፍ ይጥለኛል። ሰላም የለኝም፣ ራሴን በጣም እወቅሳለሁ በትንሽ ነገር ፣ ሰዉ የበዛበት ቦታ መሆን አልፈልግም ብቸኝነት ይሰማኛል የሚረ'ዳኝ ያለ አይመስለኝም። በጣም ዝም ማለት እፈልጋለሁ ግን አልልም ። ለምን እንደሆነ አላቅም ግን በቃ አወራለሁ ። ስራ ቦታ ጓደኞቼን አስቃቸዋለሁ እጫወታለሁ ። ያልተፈጠረ ታሪክ እየፈጣጠርኩ አስቃቸዋለሁ ምናምን። ዝም ማለት ወሬ መቀነስ እየፈለኩ ግን አልልም። በዚህ ምክንያት ከራሴ ጋር እጣላለሁ። ራሴን እወቅሳለሁ ። ግን መልሼ ያዉ ነኝ። ዝም ብል ከብዙ ሀጢአቶች አጠበቃለሁ እኮ ለምን ዝም እንደማልል ግን አላቅም። አንዳንዴ ደግሞ ቤተሰቦቼ እናት አባቴ እህቶቼ ጓደኞቼ ሁሉም ይሰለቹኛል ያስጠሉኛል። ቤተክርስቲያን ስሄድ ወይም ስራ ስሄድ ከቤት ሰወጣ ትንሽ ቅልል ይለኛል ም/ም ዉጪ እያስመሰልኩ ስለምቆይ።ሰዉ መቅረብ አልፈልግም። ዉጪ ደግሞ የተለያየ ሀሳብ አስባለሁ። ለምሳሌ ስሞት፣ ወይ አንድ ሰዉ መጥፎ ራሴን ፃድቅ እያደረኩ ታሪክ እየፈጠርኩ አስባለሁ ወይም የራሴን ትቼ የሰዎችን ሀጢያት አስባለሁ፣ እዲህ ባደርግ ኖሮ ምናምን አስባለሁ። በፊት የሠራሁትን ሀጢአቶች አስብና ; ያን ባላደርግ ኖሮ በቃ እንዳሰብኩት እኖር ነበር ፣ እንደዚህ አልሆንም ነበር እላለሁ፣ ራሴን እወቅሳለሁ። ያለፈ ታሪኬን ረስቼ ወደፊት ማሰብ አልቻልኩም፣ከራሴ ጋር መስማማት አልቻልኩም። ሌሎች ሰዎችኝ እመክራለሁ ለኔ ሲሆን ግን ምክሩ አይሰራም። ስለራሴ አላዉቅም። ምንም አላዉቅም። ምን እንደምፈልግ፣ ምን እንደሚያስደስተኝ፣ Passion ኔን ፣ አላውቅም ለምን እንደምኖር ፣ለምን አላማ እንደተፈጠርኩ ባዉቅ ደስ ይለኛል። 1 የማዉቀዉ ነገር ቢኖር ዝም ማለት እና ብቻዬን መሆን እንደምፈልግ ብቻ ነዉ። ምን እንደማደርግ አላዉቅም። መፍትሔ ያላችሁትን ነገር ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እንደተለመደው ያላችሁን የሕይወት ተሞክሮ @yeneTarik_bot ላይ /advice 9 ብላችሁ ላኩልን ። አልያም ፦ @petros2
አንዳንድ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ሲሰናከሉ ወይም በሌሎች ስማቸው ሲጠፋ ወይም ከባድ በሆኑ በሽታዎች ሲያዙ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መንቀፍ ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ለበሽታው ሕመም አሳልፈው ይስጡ እንጂ ከሚገኘው ጥቅም ወይም በረከት ራሳቸውን ያራቁ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @minenamakrot
ለባልንጀራህ ያለህ ፍቅር ሲቀዘቅዝ ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ግንኙነትም አደጋ ላይ መውደቁን እውቅ። ቅዱስ ባስልዮስ @minenamakrot
ሥጋውያን የምንሆን እኛ ግን የሥጋን ሕግ እናስባለን፧ የሥጋንም ሥራ እንሠራለን፧ በሥጋ መንገድም እንሔዳለን፧ አንተ ግን የመንፈስን ሥራ አስተምረን፧ የመንፈስንም ሕግ አስረዳን፧ የመንፈስንም መንገድ ምራን። ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ መልካም ዕለተ ሰንበት @minenamakrot
ዝም ብለን አብረን ዝም አንበል @minenamakrot
ኃጢአት ከጣለችው ይልቅ ውዳሴ ከንቱ የጣለችው ሰው ይበዛል (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) @minenamakrot
መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች ታሪክ መጽሐፍ ነው፡፡ አታላዩ ያዕቆብ እስራኤል ተብሎ አባት ሆነ ፣ ነፍስ የገደለው ሙሴ ትሑትና ነጻ አውጪ ሆነ ፣ ስምኦን ጴጥሮስ ሆነ ፣ ሳውልም ጳውሎስ ሆነ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች የታሪክ መጽሐፍ ነው (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) @minenamakrot
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም የገና በዓል!" 🌟✨ 🎉🎉
የልብ ወግ pinned a photo
እርሶ ቢሆኑ ? በእርሶ ቢሆኑ ፕሮግራማችን ለተለያዩ ምክር ለሚሹ ሰዎች ሁላችንም የሰውን ችግር ችግራችን አርገን <<እኔ ብሆን እንዲህ አረግ ነበረ >> እያልን ምክርን እንሰጣለን ። # ምክር ፈላጊዎች ፦ @yeneTarik_bot በዚህ bot የገጠማችሁን ችግር በማንኛውም ቀንና ሰአት ትነግሩናላችሁ እኛ ለአንባብያን እናቀርባለን ። አንባብያን ችግሩን አጢነው ምክርና ማጽናኛ @yeneTarik_bot ይሰጣሉ ። የተመረጡ ምክሮችን ለአንባብያን እናቀርባለን ።
ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @minenamakrot
без подписи
👇👇👇👇👇 @geeZzlekulu ⌲ ˢʰᵃʳᵉ @geeZzlekulu ⌲ ˢʰᵃʳᵉ 👆👆👆👆👆 #Join & share
ጌታ የተገረፈው 6,666 ጊዜ ነው ለእድሜው ቁጥር (33) ሲካፈል 202 ጊዜ ይመጣል ...እድሜውን ሙሉ በዓመት 202 ጊዜ የተገረፈ ያህል መከራ ተቀብሏል !!! ቆዳው ከኣካሉ እስኪላጥ ...ሥጋው እስኪያልቅ አጥንቱ እስከሚታይ ድረስ ተገርፏል!!! ሥጋው በጅራፍ ጫፍ እስኪበተን ደሙ ምድር ላይ እስኪረጭ ድረስ ተገርፏል!!! የኛ ጌታ!!! “ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።” — ኢሳይያስ 53፥7 👉እኛ ግን እድሜ ዘመናችንን የአንዱን ግርፋት ስቃይ እንኳን በማሰብ መረዳት አልቻልንም😭 ጌታ ሆይ በምሕረትህ ማረን!!! ፍቅርህን በልቡናችን አኑርልን!! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው @minenamakrot