tgindex
ምርጥ ምርጥ አባባሎች 😇😇

ምርጥ ምርጥ አባባሎች 😇😇

Статистика

ምርጥ ምርጥ አባባሎችን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇 @Mirt_ababal ላይ join bemalet tagegnalachu ምርጥ ምርጥ የተመረጡ እና የሚጣፍጡ የሕይወት አስተማሪ ታሪኮችን በአንድ Channel ታገኞላቹ 👉👉 @Mirt_ababal ኑ ተቀላቀሉን 😘😘😘✊።።። ችግር እና ኮመንት ካላቹ ብቻ 👇👇👇👇👇 @Reuben_afropia

Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
1 184
−1 за сутки
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 002
20 постов
Вовлечённость
169,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
259
1/48двое суток
296
1/72трое суток
320

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ሰዎች ሲሳሳቱ! በሕይወታችን በሚዛናዊነት ልንይዛቸው ከሚገቡን ወሳኝ ነገሮች መካከል በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች፣ በተለይም የየእለት የኑሮ ስምሪታችን የሚያገናኘን ሰዎች ስህተት ሲሰሩ የምንሰጠው ምላሽ ቀንደኛው ነው፡፡ ከሰዎች ጋር የምናሳልፈው ጊዜ በበዛ ቁጥር ሰዎቹ ስህተት ሲሰሩ ማየታችን አይቀርም፡፡ የቤተሰብ አባሎቻችን፣ የትዳር አጋራች፣ የቅርብ ጓደኞቻችን፣ የስራ ባልደረቦቻችን፣ አለቆቻችን፣ የሃገር መሪዎቻችንና . . . ካለማቋረጥ ስህተትን ይሰራሉ፡፡ ለዚህ አይቀሬ ግላዊም ሆነ ማሕበራዊ ሂደት የምንሰጠው ምላሽ ሚዛናዊነት ለግልም ሆነ ለማሕበራዊ ስኬታችን እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛዎቻችን ከአስተዳደጋችን ለስህተታችን ምህረት ሳይደረግልን ከላይ ከላዩ ተጠብጥበን ስላደግን ሁኔታው አሁን ለሰዎች ስህተት ምህረት-የለሽ እንድንሆን ተጽእኖ አድርጎብናል፡፡ ስለዚህም፣ ለሁሉም ስህተት ጨከን ማለት ሚዛናችንን ስለሚያስተን መቼ ጠንከር፣ መቼ ደግሞ ለስለስ ማለት እንደሚገባን ማሰብ ታላቅ ሚዛናዊነትን ይሰጠናል፡፡ በቃ! የለመድነው መውቀስና መወቀስ፣ መምታትና መመታት፣ ማማትና መታማት፣ ስም ማጥፋትና ስም መጥፋት . . . ስለሆነ ስህተትን አይቶ በቀላሉ የማለፍን ጉዳይ ሆን ብለን ለራሳችን ካላስተማርነው በስተቀር ያስቸግረናል፡፡ ምንም ስህተትን በማያሳልፍና በተሳሳተን ሰው ላይ ልክ እንደወደቀ ዛፍ ሁሉም ሰው መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ሕብረተሰብ መካከል ስንኖር የምህረት፣ የይቅርታና አንዳንድ ጊዜ “ይሁን” ብለን አለፍ የምንል አይነት “አብሪ ኮከቦች” እንድነሆን የሚከተሉት ሃሳቦች ያግዙናል ብዬ አስባለሁ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ስህተት በሰሩ ሰዎች ላይ የመጨከን ዝንባሌችን የሚገናኘው ከማናውቃቸው ነገሮች የተነሳ ነው፡፡ ሶስቱን ዋና ዋና የማናውቃቸውን ነገሮች እንመልከት . . . 1. ይህ ሰው ይህንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገለ አናውቅም፡፡ ሰዎች ስህተትን ሲሰሩ ያንን ስህተት ላለመስራት ምን ያህል እንደታገሉና እንደሞከሩ ብናውቅ ትንሽ ለስለስ እንልላቸው ነበር፡፡ እኛው ራሳችንም ብንሆን አንዳንድ ጊዜ አንድን ስህተት ላለመስራትና ላለመድገምም ጭምር ብዙ ታግለን ስላቃተን ብቻ ራሳችንን ስህተት ላይ እንደምናገኘው ማሰብ አለብን፡፡  2. ይህ ሰው ይህንን ስህተት እንዲሰራ ጫና ያሳደረበትን ከአቅሙ በላይ የሆነን ሁኔታ አናውቅም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንድን ስህተት እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው የራሳቸው የሆኑ ሁኔታዎችና የሚያልፉበት ነገር ይኖር ይሆናል፡፡ የሰዎቹ ጾታ፣ የእድሜ ደረጃ፣ የገንዘብ አቅም፣ የእውቀት ብቃት፣ ያለፈ ልምምድና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የራሱ ውህደት (Chemistry) ስላለው ማንም ሰው ያንኑ ችግር በእነሱ ሁኔታ ሊጋፈጠው አይችልም፡፡ ይህንን ማሰብ ትንሽ ሰፋ እንድንልና ሚዛናዊ እንድንሆን ያግዘናል፡፡ 3. ይህ ሰው በሚያልፍበት በተመሳሳይ ሁኔታ ብናልፍ እኛ ራሳችን ምን ያህል ስህተት ልንሰራ እንደምንችል አናውቅም፡፡ ሰዎች በመሪነት የውሳኔ ስህተት ሲፈጽሙ እኔ እንደ አንድ ዜጋ የፍርድ ቃል መናገር ሊቀለኝ ይችላል፤ መሪ ስላለሆንኩኝ፡፡ እኔ መሪ ብሆንና እሱ በሚያልፈበት ሁኔታ ባልፍ ግን ምን አይነት ስህተት እሰራ እሆን? በተመሳሳይ ሁኔታ ባልና ሚስቶች፣ ሴቶችና ወንዶች፣ መሪና ተመሪዎች፣ ነጋዴዎችና ገበያተኛዎች . . . ሊያስቡ የሚገባቸው እነሱ በዚያኛው ሰው ቦታ ቢሆኑ ሊሰሩ የሚገደዱት ስህተት ሊኖር የመቻሉን ጉዳይ ነው፡፡ በተቻለን መጠን ስህተትን ላለመስራት የመታገላችንን ጉዳይ ስናሰምርበት፣ ከዚያው ጋር በተቻለን መጠን ሰዎች ስሀተት ሲሰሩ የፍርድና የወቀሳ ሃሳብ ከመሰንዘራችን በፊት ግራና ቀኙን የማየት ሰፊነት የማዳበርንም ጉዳይ እንድናሰምርበት አሳስባለሁ፡፡ ✍ዶ/ር እዮብ🙏

  • ❗️ሰዎች ሲሳሳቱ🥺

  • 12 апр.1 73013

    እንኩዋን ለክርስቶስ ትንሳኤ መታሰብያ በዐል ለ ፋሲካችን በሰላም አደረሳቹ 😊🙌🙌🙌

  • 3 апр.1 860101

    видео или голосовое, без подписи

  • 29 мар.1 87014

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 янв.2 59375

    የተስፋ ወሳኝነት በአሁን ሰዓት አንድን የጀመራችሁትን ነገር ተሳክቶ ለማየት ባላችሁ ጉዞ ያላችሁ ምርጫ ሁለት ነው፡- 1) በተስፋ ቀና ብሎና ተነቃቅቶ መገንባት፣ 2 ) በተስፋ መቁረጥ አቀርቅሮና ግድየለሽ ሆኖ መገንባት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ዝንባሌዎች አንድ አይነት ውጤት እንደማይኖራቸው አትዘንጉ፡፡ ጉዞው ምንም ያህል ቢከብድም ተስፋን ሳይጥሉ መቀጠል በየእለቱ ከሚነሱ እንቅፋቶች ባሻገር በመመልከት ከመጨረሻው ዋና ዓላማ አንጻር እንድንገሰግስ ያደርገናል፡፡ በተቃራኒው፣ በሂደቱ በመዛል ተስፋ በመቁረጥ መጓዝ ጥራትና ውጤት-ተኮር ከመሆን ይልቅ ላይ ላዩን ሰርተን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡ በእጃችሁ ያለውን ነገር በተስፋ ገንቡት! የነገን ውጤት አይታችሁ ገንቡት! “እንደጀመርኩት እጨርሰዋለሁ” በሚል የመነሳሳት መንፈስ ገንቡት! “ለጊዜው ቢከብደኝም እንደምንም አጠናቅቀዋለሁ” በሚል ዝንባሌ ገንቡት! የዛሬ ትግል ነገ ዋጋ እንዳለው በማሰብ ገንቡት! በተስፋ ወደፊት ከመገስገስ ውጪ ሌላ ምርጫ እንደሌላችሁ ራሳችሁን በማሳመን ገንቡት፡፡ @mirt_ababal

  • 9 янв.2 220167

    አንዳንዴ ለኛ ቀልድ መስለውን የወረወርናቸው ቃላቶች ምናልባት ሌሎች ጋር ሄዶ የእውነት ዲንጋይ ሆኖ ልባቸውን ሊጎዳ ይችላል ......... እና ምን ልላቹ ፈልጌነው መሰላቹ ...... ......ከ አንደበታችን ምንናገረውን እየተጠነቀቅን እንናገር😊🙌🙌🙏🙏 እወዳቹሃለው 🥰🥰🙏🙏😊 .....የናንተው ሮቢ....... @mirt_ababal

  • 4 янв.2 24283

    እሁድ - ምስጋና ምስጋና ስሜት ብቻ አይደለም፤ ልብህን ከጭንቀትና ከአሉታዊ አስተሳሰቦች የሚጠብቅ ጋሻ እንጂ። ባለህ ነገር ላይ ስታተኩር፣ ተጨማሪ መልካም ነገሮችን ወደ ራስህ ትስባለህ። ዛሬ ቀኑን የምንጀምረው ለህይወት ስጦታና እንደገና ለመጀመር ላገኘነው ዕድል በማመስገን ይሁን። ጥያቄ፦ ዛሬ ጠዋት እንደ ቀላል የምታያቸው ነገር ግን በእውነት የምታመሰግንባቸው ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው? Saturday - Gratitude Gratitude is not just a feeling; it is a shield that protects your heart from stress and negativity. When you focus on what you have, you attract more of it. Today, let’s start the day by being thankful for the gift of life and the chance to start over. Question: What are three things you often take for granted but are truly grateful for this morning? @mirt_ababal

  • 24 дек.2 17393

    የጭንቀት ሱስ የጭንቀት ሱስ ማለት፣ “ሁሉም ነገር አሁኑኑ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል” በማለት የመጨናነቅ ልማድ ማለት ነው፡፡ ከዚህ አይነቱ የጭንቀት “ሱስ” ለመላቀቅ በየዕለቱ የሚገጥሙንን ሁኔታዎች ከፋፍሎ ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ 1. አፋጣኝ ትኩረት የሚፈልጉ ነገሮች፡- ትኩረት ሰጥተን መፍትሄ ካላገኘንላቸው አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች፡፡ “ምን አስጨነቀኝ” በሚል ሰበብ እነዚህን ሁኔታዎች ችላ ካልን ጊዜው ከዘገዬ በኋላ እንባንናለን፡፡ ለምሳሌ፣ እንደ ህመም ያለ፣ ወይም ደግሞ የልጆች ባህሪይ ሲበላሽ እንደማየት ያሉትን ሁኔታዎች እያዩ ከመጨነቅም ሆነ ከመዘናጋት ይልቅ በቶሎ መፍትሄ የሚገኝበትን መንገድ መፈለግ ተገቢ ነው፡፡ 2. ትንሽ ጊዜ የሚሰጡን ነገሮች፡- ከእነሱ ለባሱ ነገሮች ትኩረት ብንሰጥ ጊዜን የሚሰጡን ሁኔታዎች፡፡ ከአስቸኳይ ሁኔታዎች እኩል ለእነዚህ ሁኔታዎች መጨናነቅ መስመር ወደሳተ ስሜታዊነት ይጨምረናል፡፡ ለምሳሌ ከአንድ አመት በኋላ የሚከፈል መጠኑ አነስተኛ የሆነ ብድር ካለብን አሁን በእጃችን ላይ ያሉ ሌሎች አጣዳፊ ሁኔታዎች ላይ ለማተኮር ጊዜ ሊሰጠን ስለሚችል ከመጨነቅ ይልቅ እቅድ ማውጣቱ ተመራጭ ነው፡፡ 3. ዝም ብንላቸው በራሳቸው ጊዜ መስመር የሚይዙ ነገሮች፡- መጨነቅም ሆነ ምንም ምላሽ ልንሰጣቸው የማይገባን ሁኔታዎች፡፡ አንዳንድ ሁኔታዎች የራሳቸውን ጊዜ ጨርሰው እስኪተነፍሱ ድረስ መተው ያለብን ነገሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ በየጊዜው የሚቀያየር ባህሪይ ያላቸው ሰዎች ይህ እንደነፋስ እየመጣ የሚሄደውን ባህሪያቸውን እያሰቡ ለመፍትሄ ከመጨነቅ ይልቅ ዝም ብሎ በሌሎች ወሳኝ ነገሮች ላይ ማተኮር ይበጃል፡፡ እነሱ ሲበቃቸውና ሲሰለቻቸው ያቆማሉ፡፡ ✍ ዶ/ር እዮብ

  • የባከነ ጊዜ! “በአንድ በሚፈስ ወንዝ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ማቋረጥ አትችልም” ይባላል፡፡ እውነት ነው! ይህ አባባል ሲተነተን፣ አሁን በእግሮችህ ተራምደህ የገባህበት ወንዝ አልፏል፡፡ ስትገባበት የነበረው ውኃ ቀጥሎ ለሚፈስሰው ውኃ ስፍራውን ለቆ በመሄዱ ምክንያት ተመልሰህ ብታቋርጥ ሌላ ውኃ ነው የምታገኘው፡፡ ወንዙ አንድ ነው፣ ውኃው ግን የተለያ ነው፡፡ ፍሰቱ ተመሳሳይ ነው፣ ወንዙ ይዞት የሚመጣው ነገር ግን የተለያየ ነው፡፡ የአፈሳሰሱ ሂደት ያው ነው፣ የፈሰሰው የውኃው አካል ግን ሌላ ነው፡፡ የጊዜያችንም ጉዳይ እንደዚሁ ነው፡፡ ⏱️ የሰዓታት፡- ነግቶ እስኪመሽ የሚመጡትና የሚሄዱት ሰዓታት በተመሳሳይ ስም ይጠራሉ፣ ይዘውት የሚመጡትና ይዘውት የሚሄዱት ምርጫ ግን የተለያየ ነው፡፡ ⏱️ የቀናት፡- ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉን ቀናት በስም ተመሳሳይ ናቸው፣ ይዘው መጥተው የሚያሳልፉት እድል ግን ልዩ ልዩ ነው፡፡ ⏱️ የወራት፡- በየሰላሳ ቀናት የሚቀያየሩት ወራቶች መምጣትና መሄድ አንድ አይነት ነው፣ እነሱም ቢሆኑ ደግሞ የማይገኝ እድልን ይዘው መጥተው ጥርግ ብለው ይሄሉ፡፡ ጊዜ እንዲህ ነው! ሲመጣና ሲሄድ ያለው “አንድ አይነትነት” ያታልላል፡፡ የምንባንነው በወቅቱ ማድረግ የምንችለውን ነገር ማድረግ የማንችልበት ቀን ከመጣና ኋላ ከቀረን በኋላ ነው፡፡ በዶ/ር ኢዮብ ማሞ @mirt_ababal

  • ውድ የ ምርጥ አባባል ቤተሰቦች ☺️☺️ ለአዲሱ ዐመት እንኩዋን በሰላም አሰረሳቹ🙏🙏🙏🙏☺️☺️☺️😘😘 መልካም አዲስ አመት🙏🙌🙌🙌 @mirt_ababal

  • ብዥ ሲልብኝ . . .  ማመን የሚገባኝን ሰው ባለማመን፤ ፈጽሞ ማመን የማይገባኝን ሰው ደግሞ በማመን ብዙ እጎዳለሁ - እስኪገባኝ ድረስ! ሲገባኝ . . . 1.  ሰውን ከማመን ውጪ ሕይወት ትርጉም እንደሌላትና ምንም ነገር ለማድረግ እንዳልችል እገነዘባለሁ፡፡ 2.  ሰዎችን ከማመኔ በፊት ማጣራት የምችለውን ነገር ሁሉ የማጣራትና በማመኔ ምክንያት ላገኝ የምችለውን ጥቅማነ ሊደርስብኝ የሚችለውን ጉዳት አመዛዝናለሁ፡፡ 3.  ያመንኳቸው ሰዎች ሲጎዱኝ ምንም እንኳን ለጊዜው ስሜቴ ቢዛባም በእነሱ ምክንያት አልቆዝምም፣ ተስፋም አልቆርጥም፡፡ ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!  . . . ይቀጥላል! ዶ/ር እዮብ 🙏 @mirt_ababal

  • ብዥ ሲልብኝ . . . የሚወዱኝ ሰዎች የማይወዱኝ፤ የማይወዱኝ ሰዎች ደግሞ የሚወዱኝ እየመሰለኝ ራሴን ለብቻው አገኘዋለሁ - እስክባንን ድረስ! ስባንን . . . 1.  የማንነቴን መለኪያና የደስታዬን መጠን በወደዱኝና ባልወደዱኝ ሰዎች ላይ ማስደገፍን በማቆም ከሰውም ጋርም ሆነ ከሰው ውጪ ሙሉና ደስተኛ ሰው እንደሆንኩኝ አምናለሁ፡፡ 2.  ሰዎች ለእኔ የሚያሳዩኝ ሁኔታ እውነተኛ ሆኖ የሚፈተነውና የሚለየው በጊዜ እንደሆነ ስለማውቅ በችኮላ ለሰዎች ልቤን ከመስጠቴ በፊት በቂ ጊዜን እሰጣቸዋለሁ፡፡ 3.  ለሚወዱኝ ሰዎች ተመጣጣኝ ምላሽ በመስጠት መቅረብ፣ ለማይወዱኝን ደግሞ ለሰው ሁሉ የሚገባውን ክብር በመስጠት ርቀትን መጠበቅ፣ እየተለዋወጡ ግራ ለሚጋቡኝ ሰዎ ደግሞ ለወቅቱ ሁኔታቸው የሚመጥንን ጊዜያዊ ምላሽ በመስጠት አላማዬ ላይ አተኩራለሁ፡፡ ምንም አልሆንኩም! ንቁ ሰው ነኝ! አልፈዝምም አልደነዝዝምም!  . . . ይቀጥላል! ✍ ዶ/ር እዮብ 🙏 @mirt_ababal

  • በሕይወታችን ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰዎች እና ስለኛ አጥብቀው የሚጨነቁ ሰዎች አንዳንዴ በጣም ያሰቡልን መስሏቸው እና እና እኛን የሚጠቅመንን ነገር ነገር የደረጉ ይመስላቸውና ......ይልቁኑ እኛን ሚያስከፋ እና ሚያሳዝን ነገር ያደርጋሉ።😒😒 አዎ ስላንተም ጭምር ነው የማወራው ...... የምር የምትወደውን ሰው የጠቀምከው መስሎህ ምን አድርገሃል ? ? ይሄን ነገር ባደርግ ወዳጄን አሳርፈዋለው ወይስ ይህን እንዳደረኩ ካወቀ ያዝንብኝ ይሆን ብለህ አስበሃል ወይም አስበሻል?? የምር አንዳንዴ እሱን ወይም እሷን ይጠቅማታል ብለን ለኛ ልክ መስሎ የታየንን ሁሉ ከማድረጋችን እና ቦሃላ ከመፀፀት በፊት ........ይሄ ነገር ለሱ መልካም ነው ወይ ወይም ለሷ መልካም ነው ወይ ብለን ሁለቴ ብናስብ ጥሩ አሳቢ የሚያደርገን ይመስለኛል😕። ምናልባት የምናደርገው ነገር ደስታውን የሚያሳጣው/ት ወይም ከሃሳብ ብዛት እናሳርፈው ብለን ሌላ ሃሳብ ልንጨምርበት እንችላለን .....ስለዚህ ለምናደርገው ነገር ብንጠነቀቅ እና ድጋሚ በደምብ አስበን የምር ሚያስደስተውን ነገር እንፍጠር እላለው።😌🙏🙏🙏 ✍ሮቤል @mirt_ababal @mirt_ababal

  • A pen can do mistakes but a pencil can't because it has good friend eraser. Only a true friend can erase your mistakes and make you perfect.😊☺️☺️

  • #Part 2 ......መንገደኛው ሰውዬ ........አንድ ላም ያላቸውን ቤተሰቦች ነው የምተለኝ ?አሉ። አዎ አባባ እነሱን ነው በጣም ልረዳቸው እፈልጋለው አላቸው ። እሳቻውም መልሰው ፦ እነሱን መርዳት ከፈለክ ሂድና ላማቸውን ግደላት አሉት። እሱም በጣም ደነገጠ .......እንዴ ምን ማለት ነው በሷ እንደሚኖሩኮ ነግረውኛል ያለቻቸውም እሷ ብቻ ናት እንዴት እንደዛ አረጋለው ሲል እሳቸው፦ አዎ ልጄ አሁን ለመኖር ብቻ ነው ሚኖሩት ....ላሟ የምቾት ቀጠናቸው ናት እሷ እስካለች ድረስ ይሄ ቤተሰብ እንዳለ ነው ሚቀጥለው ስለዚ እነሱን መርዳት ምትፈልግ ከሆነ ሂድ ላሟን ግደላት ይሉታል። እሱም ብዙ ከራሱጋር ካወራና ከተሟገተ ቦሃላ ሰዎቹ ቤት ላሟ ወዳለችበት ክፍል ሄዶ ላሟን ገደላት😔😔። .. .. .. .. .. .. ከአመት ቦኋላ መንገደኛው ተመልሶ ወደዛ ሰፈር መጣ ......የነዛን ሰዎች ቤትም ፈልጎ ሊያገኘው አልቻለም ምክንያቱም ሰፈሩም ቤቱም በጣም ተለውጦ ነበር ......ስአፈሩ እና የሰዎቹ የመጀመርያ ቤት ፈርሶ ሌላ በጣም በሚያምር ቤት ተተክቷል። የዛ ቤት ሰውዬ ግን ከሩቅ ሆነው ሲያዩት ነበር እና ጠርተውት ሰላም አሉ ። መንገደኛውም ባየው ነገር በጣም ተገረመ ማመን እስኪያቅተው ........ ምክንያቱም ጠርተው ሰላም ያሉት ከአንድ ትልቅ ዳቦ ቤት ሆነው ነበር .....ዳቦ ቤቱም የሳቸው እንደሆነ ነገሩት .......እሱም ዪሄ እንዴት ሊሆን ቻለ አላቸው? እሳቸውም ፦"አይ ልጄ አንተ ከሄድክ ቦሃላኮ ላሟም ሞተች እና እኔና ልጆቼም ምንቀምሰው አተን በጣም ተሰቃይተን ነበር .....ከዛ እኔና ልጄ መንቀሳቀስ ጀመርን ከዛም ቀስቀስ እያልን ገቢያችን እያደገ መጣ ....ቤታችንንም አሳምረን ሰራነው እና ይሄን የምታያቸውን ሱቆችም ከፈትን ፈጣሪ ይመስገን ልጄ የላሟ መሞት ትልቅ ጥቅም ሆነን .........ለካ የላሟ የምቾታችን ስለነበረች ነበር መንቀሳቀስም መስራትም አቅቶን የነበረው'' አሉት። አያቹ........ወጣቶች አሁን ቤተሰብ ላይ ልንሆን እንችላለን ሌሎችም እንደዛው የሆነ ተማምነን ምንኖርበት የምቾት ቀጠና አለን ......ምናልባት እንበላለን ...እንጠጣለን ..ይሄ ስለሆነ ብቻ እየኖርን እንደሆነ ሊሰማን ይችላል ....የእውነት መኖር የምንጀምረው ግን ይሄንን የምቾት ቀጠናችንን ስንገድለው ብቻ ነው ። ውጡ ከምቾት ቀጠናቹ🙌🙌 እወዳቹሃለው ☺️😊 ከወደዳቹት ለሌሎች ማጋራት አትርሱ🙏 ✍ሮቤል https://t.me/mirt_ababal @mirt_ababal @mirt_ababal

  • ‼️"#ኢትዮጵያ ማለት ምን ማለት ነው ? #ኢትዮጵያ መጠሪያዋን ከየት አገኘች⁉️ #ኢትኤል አለም በተፈጠረች በ10ኛው ትውልድ የነበረ ኢትዮጵያዊ ካህን ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የአማርኛ ፊደላትን የቀረፀው ይህ ኢትኤል የተባለ ካህን ነወ። #በመፅሃፍ_ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው ሊቀ ካህኑ መልከፄዴቅ ሶስት ወንድ ልጆች ነበሩት ከነኛ ልጆች አንዱ ደግሞ #ኢትኤል ነበር ኢትኤል በመንፈስ ተመርቶ ካለበት ከሳሌም እስራኤል ወደ ጣና ላይ እንዲሰፍር ታዘዘ። ኢትኤል ጣና ሲደርስ ስሙን ቀይሮ #ኢትዮጵ እንዲባል ሆነ። ኢትዮጵ ማለት፦ ኢት - ስጦታ ማለት ሲሆን ዮጵ ደግሞ ቢጫ ወርቅ ማለት ነው። ኢትዮጵ የቢጫ ወርቅ ስጦታ! ኢትኤል ማለት ደግሞ የእግዚአብሄር ስጦታ ማለት ነው። የሃገራችን መጠሪያ የመጣው ከንጉስ ኢትዮጵ በኃላ ነበር ሀገራችን በኢትዮጵ ኢትዮጵያ፣ በአቢስ አቢሲንያ፣ በሀበሻት ሀበሻ ተብላለች። #ሃገራችን ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት #እንቆጳግዮን ተብላ ትጠራ ነበር። በነገደ ዮቅጣን አግአዝያን የሚባሉት አቡሳውያን እንቆጳግዬን የሚለውን ወደ እንቆጳፅዮን ቀይረውታል። እንቆጳግዮን - የአባይ ወርቅ ፤ እንቆጳፅዮን - የፅዮን ወርቅ ማለት ነው። #ንጉስ ኢትዮጵ በግዮን ወንዝ ዳርቻ ላይ የድንጋይ ወንበር አስቀምጦ የልጅ ልጆቹ በሚነግሱበት ግዜ ቅብኣ መንግስቱን እንዲነግሱበት ሲል በክብር አስቀምጦታል። ንጉስ ኢትዮጵ ከአባቱ መልከፄዴቅ የተረከባቸውን መፅሃፍት እየተረጎመ አስቀምጧቸዋል ለልጆቹም ስርአተ ክህነት እና የቅብአ መንግስትን ግብር አስተምሯቸው እስከወዲያኛው ድረስ እንዲተላለፍ አድርጒል። ኢትዮጵ የግዮን ወንዝ የሚደርስባቸውን መሬቶች በሙሉ የኢትዮጵያ ግዛት እንዲሆኑ ያደረገ ሃያል ንጉስ ነበር። ብዙ ሰዎች ንጉስ ኢትዮጵን ከ ኢትዮጲስ ጋር አንድ አድርገው ሲመለከቱ ይስተዋላል ስህተት ነው። ንጉስ ኢትዮጲስ ኢትዮጵ ከነገሰ ከብዙ ዘመናት በኃላ የነገሰ ንጉስ ነበር በ1856 አ.አ የነገሰ ንጉስ ነው። #የኢትዮጵያውያን ሁሉ አባት ኢትዮጵ በተወለደ በ150 አመቱ አርፏል። ልጆቹም አባቱ መልከፄዴቅ ካስፈለፈለው ዋሻ ውስጥ ወስደው እንደቀበሩት የታሪክ ድርሳናት ይዘግባሉ። #ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹 ለዘላለም ትኑር @mirt_ababal

  • የምቾት ቀጠናችሁን ግደሉት🤫 አንድ መንገደኛ እየጎበኘ እየሄደሳለ በአንድ ቦታ ሲደርስ ደክሞት በተቀመጠበት ይመሽበታል .......... በ አከባቢው ሲቃኙ የነበሩ አንድ አባት ያዩት እና :-`` ልጄ ሳይህ በጣም የደከመህ ይመስላል ደግሞ መሽቶብሃል ናና እኛ ቤት አርፈህ ነገ ወደምትሄድበት ትሄዳለህ" ብለውት ወደቤታቸው አስገቡት ....ሚበላም አቅርበውለት ... ሚጠጣም ወተት ሰጡት። ሰውየውም በጣም ደስ ብሎት ቤቱን እያየ ነበር ..... ሲመለከት ሁለት ልጆች እና ሚስትም አሉት ስለዚህ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ተገንዝቦ አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው ....... '' አባባ በምንድነው ቤተሰቡን የምታስተዳድሩት " ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም :- ልጄ አሁን የምትጠጣውን ወተት የምትሰጣን አንዲት ላም አለችን ወተትዋን በመሸጥ ነው ምንተዳደረው ..... ላሟ የቤተሰባችን መኖርያ ናት ብለው መለሱለት። እሱም ይደነቃል ....... በነጋታውም ተነስቶ ተሰናብቷቸው ጉዞውን ቀጠለ ..... ከዛም አንድ የሰፈሩን አባት አግኝቶ " አባባ እዛ ቤት ያሉትን ቤተሰብ ልረዳቸው ፈልጌ ነበር እና እንዴት ልረዳቸው እችላለው ? ይላችሀዋል። እርሳቸውም ፦ አንድ ላም ያለቻቸውን ቤተሰብ ነው የምትለኝ ?አሉ። አዎ..................ይቀጥላል ...... ታሪኩ ከተመቻቹ እና ይቀጥል የምትሉ ከሆነ። ቢያንስ ከ 20 በላይ 👍 or❤️ በማድረግ ፍላጎታቹን አሳዩኝ 😊😊☺️ ✍የናንው ሮቢ @mirt_ababal

  • ውዶች ከአንድ ቦታ ያገኘሁትን ጠቃሚ ንግግር እዩልኝ #እባቡ #የማይተነፍስበት #ክልል #ውስጥ #ገብተናል" በበረራ ላይ እያሉ ሆስተሷ አውሮፕላን ውስጥ እባብ አይታ በጣም ደነገጠችና፣ እየጮኸች አብራሪው ጋር ሄዳ፤ "እባብ አውሮፕላን ውስጥ ገብቷል" አለችው። ፓይለቱም፤ "ችግር የለውም ተረጋጊ" አለና የሚበርበትን ጫማ ከፍታ በመጨመር፤ "አሁን ሄደሽ እይው" አላት። እሷም የተባለችውን አደረገን፡፡ እባቡ የለም፡፡  ሞቷል። ወደ ፓይለቱ ተመለሰችና፤ "እንዴት ሊሆን ቻለ?" ስትል ጠየቀችው፡፡ "እባቡ የማይተነፍስበት ክልል ውስጥ ገብተናል" ሲል መለሰላት፡፡ የነገሩ ማጠንጠኛ፦ በገጠመህ ሁሉ አትደንግጥ፤ ለሁሉም ነገር መልስ አትስጥ፤ ዝምብለህ ጉዞህን ቀጥልና ጠላትህን የሚያስጨንቅ ከፍታ ላይ ውጣ። መልካም ጊዜ!

  • ልክ እንደ ቀስት! “አንድ ቀስት ወደ ኋላ በተለጠጠ ቁጥር ወደ ፊት የሚወነጨፍበት ርቀት እየጨመረ ይሄዳል” ይባላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእኔ እና የእናንተም ሕይወት እንደዚያ ነው፡፡ ለጊዜው በተለያዩ ከአቅማችን በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ምክንያት ወደ ኋላ የሄድንና ጊዜያችን የባከነ ቢመስለንም፣ ከልምምዱ ካገኘነው ትምህርትና ካዳበርነው ጥበብ የተነሳ ረጅም ርቀት የመሄድ አቅም እናገኛለን - ተስፋ ካልቆረጥን!!! አንድ ቀስት አቅጣጫውን ይዞ ሲለቀቅ ወደተፈለገበት ኢላማ በፍጥነት እንደሚሄደው ሁሉ እኛም የተያዝንበት ከመሰለን ነገር ስንለቀቅ : ፍጥነታችን ይጨምርና ያሰብንበት ለመድረስ ብዙ አይፈጅብንም :በተወነጨፍንበት ፈጥነት ልክ እንጓዛለን።☺️😊😊 970± ቤተሰቦቼ ........ አመሰግናለው🙏🙏🙏☺️ @mirt_ababal

ምርጥ ምርጥ አባባሎች 😇😇 — tgindex