tgindex

እንሳቅ እንወቅ እንዝናና

Статистика

በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ አስተማሪ፣ አዝናኝና ቁብ ነገር አዘል ጽሑፎች ይቀርባሉ።

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
29
Всего постов
33
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
145
+1 за 1 дн.
Сутки
+1
+0,69%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
14
33 постов
Вовлечённость
9,7%
к подписчикам
Постов в день
4,1
всего 33
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
20
1/48двое суток
22
1/72трое суток
24

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • ደኅና እደሩ

  • Get Tough Zer ሰውየው "ቀቢ ቀቢ ድርርር!" ይልና መሃል አስፋልት መንገድ ውስጥ ሮጦ ይገባል። እንዲህ የሚለው ሰው ከአሊ ቢራ አደባባይ ወደ ዩኒሳ አደባባይ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ ያለ አንድ ትራፊክ ፖሊስ ነው። እንዲህ ያለ ሁኔታ ያየሁት ድሮ ገጠር እናቴ አገር ሄጄ እረኞች ሲጫወቱ ነው። ይሄ ሰውዬ የፍጥነት መለኪያ ራዳር ይዟል። መኪኖች ለመንገዱ ከተወሰነው ፍጥነት በላይ ተጉዘው ሲያገኝ ደስታው ለጉድ ነው። "ቀቢ ቀቢ ድርርር" ይልና መሃል አስፋልት ውስጥ ሮጦ ገብቶ መኪና ያስቆማል። የትራፊክ ፖሊሱ ሁኔታ ሳትወዱ በግድ ያስቃል። የሆነ ሰርከስ ጨዋታ ውስጥ ያለ ይመስላል። ለሱ ነገሩ ጨዋታ ሆኖለታል። ለIsuzu ሾፌሮች ግን ትልቅ ቅጣት ነው። 1500 ብር ይቀጣቸዋል። አንዳንዱን ደግሞ ጓዱን ልኮ ትንሽ አውርተው ይሳሳቁና "ሳይቀጣው" ይለቀዋል። ያው ሁላችንም ነገሩ ይገባናል። እንዲያው ግን የመኪና ፍጥነት ምልክት የሚያስቀምጡትና እነዚህን ትራፊኮች የሚመድቡት ሰዎች ዓላማቸው ምን ይሆን? መኪና በፍጥነት እንዳይሄድ ካስፈለገ መንገዱ ላይ የፍጥነት መቀነሻ ማድረግ እንጂ የትራፊክ ራዳር መፍትሔ አይደለም። ለዚህ ማሳያው ደግሞ ሁሉም ሾፌር ከራዳር መለኪያው በኋላ ፍጥነቱን ጨምሮ እብስ ማለቱ ነው። ይህን ያየ አንዱ "ሰዉ ከራዳሩ በኋላ ፍጥነት ከጨመረ ታድያ የራዳሩ ጥቅም ምንድን ነው?" አለ። ሌላው ሲመልስ "ራዳሩማ የገንዘብ መብያ፣ የጉቦ ምንጭ እና ህዝብን ማሰቃያ ነው" አለ። እውነት ነው። ይህንን ማስተባበል አይቻልም። ለመሆኑ መኪና በ30 እና በ50 ኪሎ ሜትር በሰዓት ንዱ የሚል ምልክት ነጻ ጎዳና ላይ ለጥፋችሁ፣ መኪና በረረ ብላችሁ መሃል ስትገቡ መኪናው ወድያው እንደሚቆም አምናችሁ ነው አይደል? ታድያ በቀላሉ ለሚቆም መኪና ፍጥነት ቀንስ ማለትን ምን አመጣው? ከ80 ኪሎ ሜትር በሰዓት በታች ፍጥነትን መገደብ የመኪና ኢነርሽያን አለማገናዘብ ነው። ኋላ ላይ ሰውየው "ቀቢ ቀቢ ድርር" እያለ ሲያስቆም የቆሙ መኪኖችን ከርቀት እያዩ ሌሎች ሾፌሮች ነገሩ ገባቸውና ዝግ ብለው መምጣት ጀመሩ። ይሄኔ ለቅጣት ከወረዱት መካከል አንዱ ሾፌር "መኪኖቹን አሰልፈህ የቀብር ነው የሠርግ አጃቢ አስመሰልካቸው እኮ?" ሲለው የተሰበሰበው ሁሉ ሳቀ። ፖሊሱም ተናዶ "አንተ ሰውዬ ከዚህ ዞር በልልኝ" አለና የቆመትን እንዳያባርራቸው ለክፍያ የቆሙ ናቸው። አንዳንዴ እንዲህ ያለ ወጊ ያጋጥማል። የትራፊክ ፖሊስ ዓላማ አደጋ እንዳይደርስ መኪኖችን ማስተላለፍ እንጂ ቅጣት መጻፍ አልነበረም። በኩሽ ምድር ግን "#ትራፊክ_ፖሊስ" ወደ "#ፔናሊቲ_ፖሊስ" ተቀይሯል። ፔናሊቲ ፖሊስ ዓላማው መኪኖች ማስተላለፍ ወይም አደጋ መቀነስ አይደለም። ፔናሊቲ ፖሊስ ዓላማው በቅጣት ብዙ ገንዘብ መሰብሰብ ነው። ፔናሊቲ ፖሊስ ብዙ ሰው ሲቀጣ ደስ ይለዋል። ሰው ሲቀጣ ፔናሊቲ ፖሊስ "ቀቢ ቀቢ ድርርር" ይልና መሃል አስፋልት ውስጥ ይገባል። ይህንን የፍጥነት ወሰን ጉዳይ ሳይ ሁሌም ትዝ የሚለኝ ጣልያን ሮም ውስጥ ወደ ፉሙቺኖ አየር ማረፊያ ያደረግሁት ጉዞ ነው። እኛ በፍጥነት እየተጓዝን እያለ ሌላ መኪና በአጠገባችን እንደጥይት ተተኩሶ አለፈ። ይሄኔ የእኛን መኪና ፍጥነት ሳይ 120 ይላል። ያኛው ከ150 ኪሎ ሜትር በሰዓት በላይ እየሄደ እንደሆነ ለመገመት አልከበደኝም። ይሄ ቀቢ ቀቢ የሚለው ትራፊክ እዚያ ቢሆን አየር ላይ ተሰጥቶ ይሆን እንደነበር ሳስብ ዘገነነኝ። ነገሩ በዚህ ከቅጠለ የአቡሴራ አየር መንገድ ሥራ ሲጀምር መኪኖቹ በዚህ የፍጥነት ቁጥጥር ምክንያት ዝግ ብለው ከሄዱ ብዙ ሰው ከበረራ መሰናከሉ አይቀርም። ነገርን ማገናዘብ፣ ህዝብን ማክበርና feedback ሰምቶ ህግን ማሻሻል ከሚያስብ ሰው የሚጠበቅ ነው። ፍጥነት ጥቅምም ጉዳትም አለው። ነገር ግን ፍጥነት ጉዳት አለው ተብሎ አውሮፕላን በ50 km/H ብቻ ብረር ቢባል አውሮፕላኑ ከመሬት አይነሳም። መኪናም ከ180 እስከ 220 km/H የሚያሳይ የፍጥነት ጌጅ የተገጠመለት በምክንያት ነው። 30 የሆነው በምክንያት ነው የሚለው አባባል አይሠራም። እስኪ ይህንን ምክንያት ለአውሮፕላን አድርጋችሁ አሳምኑን? ቴክኖሎጂን በትክክል የሚረዱ የትራፊክ አስተዳዳሪዎች እና አስተናባሪዎች እስኪመጡ ድረስ በዚህ አስቸጋሪ ህግ ህዝብ እያዘነ መጓዙ እስከ መቼ ይቀጥላል? እኔ ግን እንዲህ ሆኖ ብዙ የሚቀጥል አይመስለኝም። አይቀጥልም! የትራፊክ ፖሊስን አስፈላጊነት የሚያስቀር ቴክኖሎጂ ይመጣል። ያውም በቅርቡ! ያኔ ህዝቤ "እፎይ" ይላል። እስከዚያው ግን "ቀቢ ቀቢ ድርርር" ማለት ይቀጥላል። ሁሌም እንደምለው ነጻ አውጪያችን ቴክኖሎጂ ነውhttps://t.me/mk219s

  • አትሌት የሚቀበለው ሰው አጥቶ ፖርትላንድ የሚኖር ፍራኦል የሚባል የአትሌቲክስ ወዳጅ ተቀብሎት ማረፊያቸው ድረስ እስከመውሰድ ደርሷል፤ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ ስለሌለ ከአዘጋጅ አካሉ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ዋጋ ተከፍሏል፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ፌዴሬሽኑ ስኬታማ ነበርን የሚል አቋም ይዞ ሲሸላለም መዋሉ ያስደነግጣል፤ ከአትሌቶቹ በላይ አመራር ቦታ ላይ የተቀመጡት ሰዎች የሚሰሩት ፊልም ያሳቅቃል፤ ሌላው ሃገር ቢሆን በራስ ፍቃድ ስልጣን እስከመልቀቅ የሚደርስ ውሳኔ የሚያስወስን ቢሆንም የእኛዎቹ ገሚሱ በቡድን ተደራጅቶ፥ አንዱ በግል ትዕዛዝ እያስተላለፈ፥ ቀሪው በውጭ ጉዞ ፍቅር ተጠምዶ፥ ሌላው በብሄሩና በመንግስት ስር ተሸጉጦ፥ በካሜራ ፊት ግን እየተሳሳቁ ስለ ቀጣዩ አለም ሻምፒዮናና ኦሊምፒክ እቅድ ሲያወጡ ማየት ያማል፤ የአትሌቲክሱ መውረድ፥ የአትሌቶቹ እንባ፥ የባለሙያው ብሶት ለእነሱ ግድ አይሰጣቸውም! (ታምሩ ዓለሙ)https://t.me/mk219s

  • ፊልመኞቹ፥ በአሜሪካ የቀሩ አትሌቶች አስገራሚ ድራማ‼️ ከአንድ ቀን በፊት ማክሰኞ ነሀሴ 5/2018፥ በአሜሪካ ፖርትላንድ ኤርፖርት ውስጥ የኢትዮጵያን መለያ የለበሱና ከ20 አመት በታች የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፉ የኢትዮጵያ ልዑካን ያሳዩት ድራማዊ ትዕይንትና ትርምስ አስገራሚ ነበር፤ የአሰልጣኞችና የአትሌቶች ልዩ ትወና፥ የአመራሩ ሩጫና ግርግር ሙሉ ፊልም የሚወጣው ክስተት ሆኖ አልፏል፤ ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሻል ሰባት የቡድኑ አባላት የመኮብለላቸውን ዜና ይፋ ካደረገ በኋላ ጉዳዩ እስካሁን መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል፤ ይህንን ዜና ተከትለን እኛም ጥልቅ ማጣራት አድርገን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን ቀርበናል፥ እነሆ የፊልመኞቹ ድራማ፦ 🔷 የአሰልጣኞቹ መሰወር፦ አራት አሰልጣኞች ወደ አሜሪካ ሄዱ፤ ኢንስትራክተር መሰረት መንግስቱ፣ ሀብታሙ ግርማ፣ ድሪባ ለገሰና አማረ ሙጬ ከቡድኑ ጋር አብሮ የተመለሰው ግን ኢንስትራክተር መሰረት መንግስቱ ብቻ ነው፤ ሁለቱ አሰልጣኞች ሀብታሙ ግርማና ድሪባ ለገሰ ፖርትላንድ ኤርፖርት ድረስ ከቡድኑ ጋር አብረው በአንድ መኪና ተጉዘው ነበር፤ ሀብታሙ ዘመድ ጋር ለአንድ ሳምንት መቆየት እፈልጋለሁ ብሎ ትኬቱን አራዝሟል፤ በአንድ ኤርፖርት ስለምንሳፈር አብሬ ልሂድ ብሎ የቡድኑ የመኪና ጉዞ አንዱ አካል ሆነ፤ አሰልጣኝ ድሪባ ግን ወደ አዲስ አበባ ተመላሽ ነበር፤ ልዑኩ ወደ ውስጥ ሲገባ ሁለቱ አሰልጣኞች ማንንም ሳይሰናበቱ ተሰወሩ፤ የመጀመሪያ ፈር ቀዳጆች እነሱ ሆኑና ቡድኑ ውስጥ ድንጋጤ ተፈጠረ አሰልጣኝ ሀብታሙ እንደሚመለስ ለፌዴሬሽኑ ማሳወቁ ተሰምቷል፤ ሆኖም ለውድድሩ የሄደበት መንገድ በስራ አስፈፃሚው ዘንድ ግርታን ፈጥሯል፤ የሁሉም ተሳታፊ ልዑካን ትኬትና ሌሎች አቅርቦቶች ስራ አስፈፃሚው አምኖባቸው በፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ዶ/ር አመንሲሳ ከበደ በኩል የተፈፀሙ ናቸው፤ የሀብታሙ ግን በፕሬዝዳንቱ ኮማንደር ስለሺ ስህን ግላዊ ውሳኔ የተከናወነ በመሆኑ ስራ አስፈፃሚዎቹ ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል፤ እኛ መሄዱን አናውቅም፥ አልወሰንም እያሉ ነው፤ የሀብታሙ መመለስ አልያም አለመመለስ ግን ከአንድ ሳምንት በኋላ ይታወቃል ወደ አዲስ አበባ ተመላሽ የነበረውና ከፖርትላንድ ኤርፖርት ደጃፍ የተሰወረው አሰልጣኝ ድሪባ ለገሰ በክለቡ ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ከአራት ወራት በላይ ደሞዝ ያልተከፈለውና በተለያዩ አሰራሮች ቅሬታ ያለው በመሆኑ ከማይመለሱት ውስጥ እንደሆነ ተሰምቷል፤ ሁለቱን አሰልጣኞች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ሶስተኛው አሰልጣኝ አማረ ሙጬ ኤርፖርት ድረስ አልሄደም፤ ቀደም ብሎ ቤተሰብ ጥየቃ በሚል ከቡድኑ ማረፊያ ተለይቶ ወጥቷል፤ አሰልጣኙን በስልክ አግኝተን አነጋግረነዋል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሃገር ቤት እንደሚመለስ ይህንንም ለፌዴሬሽኑና ለክለቡ ማሳወቁን ነግሮናል፤ የአትሌቶቹን አስገራሚ ድራማ ደግሞ እንቀጥል፦ 🔷 መፀዳጃ ቤት ገብቶ ያልተመለሰው፦ ነጋሄ እያሱ የአዳማ አትሌቲክስ ክለብ አትሌት ነው፤ በውድድሩ በ800 ሜትር ተሳትፏል፤ በመጀመሪያው ዙር አንደኛ ቢወጣም በግማሽ ፍፃሜው ሰባተኛ ሆኖ አጠናቆ ለፍፃሜው ሳይደርስ ቀርቷል፤ በጉዞው እለት ፖርትላንድ ኤርፖርት ውስጥ ገንጠል ብሎ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲሄድ አንድ አመራር ያየውና ወዴት ነው ይለዋል፤ መፀዳጃ ቤት ነኝ ብሎ ሻንጣውን አስቀምጦ ገባ፤ አልተመለሰም፤ በሌላ በር ወጥቶ ሄደ፤ አትሌቱ እንደኮበለለ የተረዱት አመራሮች ሌሎቹ ላይ ትኩረት ማድረግ ጀመሩ፤ አስገራሚው ነገር አትሌት ነጋሄ ኤርፖርት ድረስ እየገፋ ይዞት የመጣው ሻንጣ ባዶ ነበር፤ ባዶውን ሻንጣ ትቶላቸው ሄዷል፤ ፊልም መሳይ ክስተት 🔷 ፈጣኗ የኤርፖርት አትሌት፦ እመቤት ጥላሁን በ5ሺህ ሜትር ተሳትፋ ስድስተኛ ሆና ያጠናቀቀች አትሌት ነች፤ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን አትሌቷ ባለ ባዶ ሻንጣውን ነጋሄን ተከትላ ከኤርፖርት ከጠፉት አትሌቶች ሁለተኛዋ ሆናለች፤ እሷ ግን ሻንጣዋን ይዛ ነው የወጣችው፤ አመራሮቹ ቀድሞ የጠፋውን አትሌት ለመፈለግ ሲበታተኑና ለኤርፖርት ፖሊስ በማሳወቅ ላይ እያሉ ፈጣኗ የኤርፖት አትሌት እልም ብላ ተሰውራለች፤ ሁለቱም አትሌቶች ውጪ የሚጠብቃቸው ቤተሰብ ስለነበር ሊገኙ አልቻሉም 🔷 ትኬት ያሰረዘችው አትሌት፦ ፃድቃን መኮንን በውድድሩ ግፍ ከተሰራባቸው አትሌቶች አንዷ ነች፤ በ3ሺህ መሰናክል ትሮጫለሽ ተብላ ብትመጣም ሳትሳተፍ ቀረች፤ ባለመሮጤ ደብሮኛል፤ ሜዳሊያ በማግኘታችን ግን ደስ ብሎኛል ብላ ለልዩ ስፖርት አስተያየቷን ሰጥታ ነበር፤ በዚህ ክረምት ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ተመርቃ ኢትዮ ኤሌክትሪክን የተቀላቀለችው ወጣቷ ፃድቃን በስሟ ባጅ ስላልተዘጋጀላት በሌላ ሰው በወንድ ስምና ፎቶ ባጅ ነበር ስታዲየም ስትገባ የቆየችው፤ አትሌቷ ቺካጎ ዘመድ ስላለኝ ቆይቼ ልምጣ ብላ ጥያቄ ብታቀርብም ፌዴሬሽኑ ከለከላት፤ ትኬቷን ለዘመዶቿ ልካ ከቺካጎ ወደ አዲስ አበባ በራራዋን አሰረዘች፤ ከፖርትላንድ እስከ ቺካጎ ከቡድኑ ጋር ሄዳ ቺካጎ ቤተሰቦቿ ጋር ለመቆየት ወሰነች፤ ይህንን ለማንም አልተናገረችም፤ ፖርትላንድ ኤርፖርት ትኬቷ ሲታይ ግን ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል፤ ስትጠየቅ ያሰረዝኩት ከቺካጎ አዲስ አበባ ያለውን ብቻ ነው አለች፤ እዛው ትኬት ቢፈለግ ጠፋ፤ ከሸኚዎቹ መካከል ለነበሩ የአትሌቶች ማናጀሮች በአደራ ተሰጥታ ፖርትላንድ ቀረች፤ መመልስ አለመመለሷ ገና አለየም 🔷 በእርምጃ ተሳትፎ በእርምጃ የቀረው፦ ነገሮ አዱኛ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አትሌት ነው፤ በሻምፒዮናው በ5ሺህ ሜትር እርምጃ ተወዳድሮ 19ኛ ሆኖ አጠናቋል፤ የመጨረሻው ኮብላይ እሱ ሆኗል፤ የቡድን መሪዋ አትሌት መሰረት ደፋርና የቴክኒክ መሪው ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃ እንዲሁም ሸኚ የነበሩት ማናጀሮችና የአትሌቲክሱ ወዳጆች ቀደም ብለው የጠፉትን ፈልገው ካጧቸው በኋላና ለኤርፖርቱ የፀጥታ ሀይሎች ካሳወቁ በኋላ ከፖርትላንድ ወደ ቺካጎ ለመብረር ለቦርዲንግ ፓስ በተሰለፉበት ወቅት መጨረሻ ላይ ተሰልፎ የነበረው የእርምጃ ተወዳዳሪው ነገሮ አዱኛ በእርምጃ ወደ ኋላ አፈግፍጎ እሱም ከቡድኑ ተለየ፤ አራቱ አትሌቶች በተለያየ ግን በደንብ በተጠና የፊልም ስክሪፕት መሰል ክስተት ከአዲስ አበባው ጉዞ ቀሩ እዚህ ላይ ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎች ይነሳሉ፤ አንደኛው አትሌቶቹም ሆኑ አሰልጣኞቹ ፓስፖርታቸውና ትኬታቸው ራሳቸው ጋር ስለነበር ለመቅረት ከፈለጉ ለምን ኤርፖርት ድረስ ሻንጣቸውን እየጎተቱ መጡ? እዛ የነበሩት አመራሮችስ ተራ በተራ ሲጠፉ ሆን ብለው በቸልተኝነት አልፈዋቸው ነው ወይስ ካቅማቸው በላይ ሆኖባቸው ነው? የሚቀሩ አትሌቶችና ባለሙያዎች እንደሚኖሩና ዝግጅት እያደረጉ እንደነበር አዲስ አበባ ያሉትም አሜሪካ የሄዱትም የፌዴሬሽኑ አመራሮች እያወቁ ለምን ትኩረት አልሰጡትም? በነገራችን ላይ 17 አትሌቶችን ለመምራት የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ዶ/ር አመንሲሳ ከበደ፣ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንትና ዋና ቡድን መሪዋ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ምክትል ቡድን መሪዋና ስራ አስፈፃሚዋ አትሌት በላይነሽ ኦልጅራ፣ የቴክኒክ መሪው ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃ በውድድሩ ቦታ ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ባሉበት ከኩብለላው በተጨማሪ የሜዳሊያ ሽልማት ፕሮግራምን ረስተው ስልክ ሲደውል ባለመመለሳቸው አትሌቶቹ በሌላኛው ቀን ለመሸለም ተገደዋል፤ የህክምና ባለሙያ ባለመሄዱ ወድቀው ጉልበታቸውን የተጎዱ አትሌቶች ህክምና ሳያገኙ ቀርተዋል፤ ምግብ ያልተስማማቸው አትሌቶች ከነ ህመማቸው ሮጠዋል፤ የማሳጅ ባለሙያ ስላልሄደ አትሌቶቹ እርስ በእርስ ማሳጅ ሲደራረጉ ሰንብተዋል፤ ቡድኑ ከገባ በሁለተኛው ቀን የደረሰ

  • Senedu Gebre የብር ነገር በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር ከምንሮጥላቸው አያሌ ነገሮች መካከል «ገንዘብ» ግንባር ቀደሙ ነው። አንዳንዴ ይገርመኛል፤ ያለ ገንዘብ ዓለም የምትቆም፣ ህይወትም ያለ እሱ ጭራሽ የማትቀጥል የሚመስላቸው በርካታ ሰዎች አሉ። ከጧት እስከ ማታ በውክቢያ የሚያሳድዱት፣ ህይወታቸውን በሙሉ ለሱ የሚገብሩ የቁሳቁስ እስረኞች… እኔም «ብር አልወድም» ብዬ አልዋሽም። ገንዘብ መጠለያ ነው፣ ነጻነት ነው፣ የዛሬ ጉርስ የነገ ስጋት መከላከያ ጋሻ ነው። ነገር ግን እውነቴን ነው የምላችሁ—እስካሁን በኖርኩበት ህይወቴ ለብር ብዬ ነፍሴን ያስጨነቅኩበት፣ ሰላሜን አጥቼ ያደርኩበት አንድም ቀን የለም። ቅዱስ መጽሐፉም ቢሆን «ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነው» ይላል። ችግሩ «ገንዘቡ» ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ለገንዘብ የሚሰጠው የስግብግብነት ፍቅርና አምልኮ ነው። ብር የህይወት አገልጋያችን ሲሆን ህይወት ያምራል፤ ጌታችን ሲሆን ግን ነፍሳችን ትታሰራለች። በነገራችን ላይ… ዛሬ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ግንዛቤ ቀን (National Financial Awareness Day) ነው። ይህ ቀን የሚያስታውሰን ሰብስበን ስለመንቀባረራችን ወይም ስለ ሳንበላው አከማችተን ስለመሞታችን ሳይሆን፤ ቆም ብለን የህይወት መንገዳችንን፣ ቁጠባችንንና የገንዘብ አመራራችንን በጥበብ እንድንፈትሽ ነው። አላስፈላጊ የነፍስ ጭንቀትን አስወግደን ለነገ በግልጽ እንድንቀይር የሚጠቁም መልካም አጋጣሚ ነው። ስለ ገንዘብና ስለ ሰው ልጅ ነፍስ ስያስብ ሁልጊዜ ትዝ የሚለኝ አንድ ድንቅ የዓለም ክላሲክ መጽሐፍ አለ—የፈረንሳይኛ ደራሲ የሆኖሬ ደ ባልዛክ «ጎሪዮ አባት» (Le Père Goriot) የተሰኘው ድቅ ስራ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ «አባት ጎሪዮ» የተባሉ ሀብታም ሰው ነበሩ። ልጆቻቸውን ከመውደዳቸው የተነሳ ያላቸውን ንብረትና ብር በሙሉ አካፍለው ሰጧቸው። ልጆቻቸው ግን አባታቸውን ሳይሆን የሚወዱት የነበረው የኪሳቸውን ብር ነበር። የሰውየው ሀብትና ብር ሲያልቅ፣ ልጆቹ በጨካኝነት ጥለዋቸው ጠፉ፤ አባት ጎሪዮም በመጨረሻ በብቸኝነትና በድህነት ታመው ህይወታቸው አለፈች። ይህ ልብ የሚነካ ታሪክ አንድ ትልቅ እውነት ያስተምረናል፦ ገንዘብ የሰዎችን ልብ ሊገዛ ወይም ሊያራራቅ ይችላል፤ ነገር ግን እውነተኛውን የህይወት እሴትና ሰብአዊነት በፍጹም ሊተካ አይችልም። ስለዚህ ወዳጆቼ… ለነገዓችን እናቅድ፣ ገንዘባችንን በጥበብ እንያዝ፤ ነገር ግን በፍጹም ነፍሳችንን ለብር ባሪያ አንደብቃት። እውነተኛው ሀብታም በኪሱ ብዙ ብር ያለው ሳይሆን፣ በነፍሱ ሙሉ ሰላም ያለው ሰው ነው! መልካም ምሽት ለሁላችሁም!https://t.me/mk219s

  • Senedu Gebre መንኩሺ ይሉኛል .. ተዝካሬን ሊበሉ ፣ በቁሜ እንዳለሁ ፣ ጎብጬ ብታይም፣ እኔ መች አረጀሁ፣ ጭኔ ከበረደ፣ ዐመታት ቢነጉዱም፣ ልቤ መች አረፈ፣ ያተጋዋል ጉዱን፣ መንኩሺ ይሉኛል ፣ ከስጋ ታቀቢ፣ እንዲሁ እንደቀለድሽ ፣ ሲኦል እንዳትገቢ፣ ድመት መንኩሳhttps://t.me/mk219s

  • "‎ስለመጠበቅ ምን ታስባላችሁ?" Fanta Emu 🤗❤ ናት ያለችው። ‎ ‎ለእኔ መጠበቅ በዝምታ ውስጥ የሚካሄድ የሰው ልጅ ትልቁ ውይይት ነው። ‎ ‎ሰው ሲጠብቅ በውጭ የሚታየው ምንም ነገር የለም። ቁጭ ብሎ ሊሆን ይችላል፤ መንገድ ላይ ሊሆን ይችላል፤ ስልኩን በየደቂቃው እየከፈተ ሊሆን ይችላል። ግን በውስጡ አንድ ትልቅ ነገር እየተካሄደ ነው፤ ከጊዜ ጋር እየተደራደረ ነው። ‎ ‎“ገና አልመጣም…” ‎ ‎“ምናልባት ይመጣ ይሆናል…” ‎ ‎“ምናልባት ዛሬ…” ‎ ‎“ምናልባት ነገ…” ‎ ‎እንዲህ እያለ ሰው የሚጠብቀው ነገርን ብቻ አይደለም፤ የራሱን ተስፋ ነው የሚጠብቀው። ‎ ‎ምናልባት ስለዚህ መጠበቅ ከመጥፋት የበለጠ ይጎዳል። የጠፋ ነገር እንደጠፋ እናውቃለን። የምንጠብቀው ግን ገና እንዳልጠፋ እናስባለን። በዚህ መካከል ተስፋና እውነታ እየተጋጩ ይኖራሉ። ‎ ‎አንድ ሰውን ስንጠብቅ ሰውዬውን ብቻ አንጠብቅም። ከእርሱ ጋር የነበረንን ስሜት እንጠብቃለን። የሚመለሰውን ሰው ሳይሆን፣ ያለፈውን ጊዜ እንደገና እንዲመልስልን እንፈልጋለን። ‎ ‎የምንጠብቀው መልዕክት አይደለም፤ ያ መልዕክት የሚሰጠንን ማረጋገጫ ነው። ‎ ‎“አስታውሶኛል።” ‎ ‎“አስፈልጌዋለሁ።” ‎ ‎“አልረሳኝም።” ‎ ‎“አሁንም ይወደኛል።” ‎ ‎እነዚህን የማንሰማቸውን ቃላት ከአንድ ትንሽ የስልክ ማሳወቂያ ለማግኘት እንጠብቃለን። ‎ ‎ነገር ግን መጠበቅ አንድ አስገራሚ ባህሪ አለው፤ በምንጠብቀው ነገር ላይ እየተጠመድን፣ በሚመጣው ነገር ላይ ሕይወታችንን እንሰቅላለን። ‎ ‎“ሥራ ካገኘሁ…” ‎ ‎“እሱ ከተመለሰ…” ‎ ‎“እሷ ካስታወሰችኝ…” ‎ ‎“ነገሮች ከተሻሻሉ…” ‎ ‎“አንድ ቀን ደስተኛ እሆናለሁ…” ‎ ‎እናም ዛሬን ለነገ እንሰጣለን። ‎ ‎ይህ ግን መጠበቅ ብቻ አይደለም፤ የአሁኑን ሕይወት ለወደፊቱ መስዋዕት ማድረግ ነው። ‎ ‎ግን ሁሉም መጠበቅ ስህተት አይደለም። ‎ ‎ዘር ዛሬ ዛፍ እንዲሆን አንጠብቀውም፤ እንዲያድግ ጊዜ እንሰጠዋለን። ልጅ እንዲያድግ እንጠብቃለን። ቁስል እንዲድን እንጠብቃለን። ልብ እንደገና መውደድን እንዲማር እንጠብቃለን። ‎ ‎እዚህ ላይ መጠበቅ ተስፋ ይሆናል። ‎ ‎ስለዚህ ጥያቄው “መጠበቅ አለብን ወይ?” አይደለም። ‎ ‎ጥያቄው፦ “እየጠበቅን ያለነውን ነገር ስንጠብቅ፣ እራሳችንን እየጠበቅን ነው ወይስ እያጣን ነው?” የሚለው ነው። ‎ ‎አንዳንድ ጊዜ መጠበቅ ፍቅር ነው። አንዳንድ ጊዜ ትዕግሥት ነው። አንዳንድ ጊዜ ተስፋ ነው። አንዳንድ ጊዜ ግን ከራሳችን የምንሸሽበት ሰበብ ነው። ‎ ‎ምናልባት ትልቁ ጥበብ መጠበቅን ማቆም ሳይሆን፣ መጠበቅ የማይገባንን ነገር መለየት ነው። ‎ ‎ሰው ሊመጣ ይችላል። መልዕክት ሊደርስ ይችላል። ዕድል ሊከፈት ይችላል። ‎ ‎ግን ያ ሁሉ እስኪመጣ ድረስ ሕይወትህን አቁም ማለት አይደለም። ‎ ‎የሚመጣውን እየጠበቅክ፣ ያለውን አትርሳ። ‎ ‎ምክንያቱም ምናልባት አንድ ቀን ወደኋላ ስትመለከት፣ የምትጸጸተው ያልመጣውን ነገር በመጠበቅህ ሳይሆን፣ እየጠበቅክ ያሳለፍከውን ሕይወት በማጣትህ ሊሆን ይችላል። ‎ ‎መጠበቅ ማለት ጊዜን ማቆም አይደለም። ‎ጊዜ ሲሄድ እንዳትጠፋ መጠንቀቅ ነው። ©️ የሶሪት ማስታወሻhttps://t.me/mk219s

  • Jemal Abdulaziz ፈስ፦ ከሆድ የሚወጣ እስትንፋስ (ፈስው ፈስ ([ግዕዝ]) ፈስዑን ፈስ ([ዐረቢኛ])። ጀርመንኛ - ፉርስ ኖርዌጅኛ - ፊስhttps://t.me/mk219s

  • видео или голосовое, без подписи

  • ከኹለት ዓመት በፊት ፌስቡክ ገጼ ላይ አጋርቼው እንደነበረ ማርቆስ አስታወሰኝ። እንዝናና እንጂ የሔዋን እናት... ! (ኤልቫን እንድታሸንፍልን የቋጠርንበት አንድ ዘመን🥰) ዝም ብዬ ስለ ሲፋን ሐሰን እያሰብኩ... ድንገት ኤልቫን (ሔዋን) አብይለገሠ ትዝ አለችኝ። ያቺ ለቱርክ ትሮጥ የነበረችው፣ ልክ እንደ ሲፋን ቀጭን አንጀት የራቃት (አንጀት የምትበላ) ግን ጎበዝ፣ አይበገሬ፣ ፈገግተኛ አትሌት ነበረችንኮ። ብዙ ሰው እንደሚያስታውሳት አስባለሁ። ያቺ ኤልቫንም እንደ ሲፋን ብዙ ድንቅ የሚባሉ የሩጫ ድሎች ነበሯት። በሆነ ወቅት የግማሽ ማራቶን ወርቅ ሜዳሊያን ወስዳ፣ እና የ5ሺ ይሁን የ3ሺ ሪከርዱን ሰብራ ሁሉ ነበረ። ልክ እንደ ሲፋን በየውድድሩ አትጠፋም ነበር ኤልቫንም! ታዲያ ኤልቫን የደብረብርሃን ልጅ ናት። ያኔ.. የዛሬ 20 ዓመት አካባቢ ማለት ነው.. የንግድ ባንክ ነገረፈጅ ሆኜ የሰሜን ሸዋ፣ የመራቤቴ፣ የፍቼ፣ ወዘተ አካባቢዎች ጉዳዮችን በኃላፊነት ወስጄ ፍርድቤቶች እቀርብ ነበረ። በዚያም ወቅት ብዙ ጉዳዮች በእንጥልጥል ላይ በመሆናቸው ለእነሱ በቶሎ እልባት እንድሰጥ ተብሎ (እና ተስማምቼ)፣ አለቆቼ አዲሳባ ሆነው፣ እኔ ደሞ ደብረብርሃን ላይ የማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ተከፍቶልኝ፣ ለ11 ወራት ገደማ ለቆየ ጊዜ ሠርቼያለሁ። በዚያ ወቅት፣ ያው ወጣትነትም አለ። ጭፈራውም። የጓደኞች መዓትም አለ። ብሩም ይመጣል። ይጠፋል። የሚገርም ዓለም ውስጥ ነበርን ከነጓደኞቼ። አንዳንድ ድሮ ሎውስኩል አብረን የተማርን ጓደኞቼም በደብረብርሃን በሚገኘው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድቤት በዳኝነት ያገለግሉ ነበሩ። የሚገርም ጊዜን አሳልፈናል አብረን። ታዲያ አንዳንዴ ኪሳችን የሚሞላውን ያህል፣ ስለማንሠርቅ ደግሞ፣ የዚያኑ ያህል በወሩ መጨረሻ ገደማ ደግሞ ኩ ኪሳችንን ድርቅ ይመታዋል። አንደኛችን ሌላኛችንን እስቲ ትንሽ ሳንቲም ይኖርሃል? የምንልበት ወሽመጥ ይቆረጥብናል። ምክንያቱም እንተዋወቃለና😀😊። እና በአንድ በጠብሽ በተወገርንበት አንዱ ክፉ ሰሞናችን፣ እግዜሩ አትሌት ኤልቫን ለገሠን በእጃችን ላይ ጣለልን። እንዴት? በየት በየት በኩል? ቀላል ነው። አስረዳለሁ። የኤልቫን ወላጅ እናት የደብረብርሃን ከተማ ነዋሪ ነበሩ። ነዋሪ ብቻ ሳይሆኑ በከፍተኛው ፍርድቤት የመዝገቤት ሠራተኛ፣ እና የችሎት አስተናባሪ ሆነው ይሠሩ ነበረ። አሁን ስማቸው ተዘነጋኝ። ስማቸውን ስለረሳሁ በጣም ራሴን ወቀስኩ። አልዛይመሬን😊!! እና ለቱርክ የምትሮጠዋ ኢትዮጵያዊት ቀጭኔ ተምዘግዛጊ አትሌት፣ ኤልቫን፣ የሆነ ዓለማቀፍ ውድድር ባሸነፈች ቁጥር፣ በቃ ለእናቷ ጫን ያለ ብር ትልክላቸው ነበር። እና ከመጠን በላይ ደስተኛ ነበሩ። ደሞ እኛ ፍርድቤት አካባቢ ያለነው፣ የኤልቫን እናት መሆናቸውን ስለምናውቅ፣ ኢትዮጵያውያንን ቀድማ ወርቃችንን በመንጠቋ ቆሽታችን ቢያርር ራሱ፣ እናቷን ግን በማግስቱ ስናገኛቸው "እንኳን ደስ አለዎት! ጀግና ልጅ አለችዎት!..." እያልን የእናትነት ደስታቸውን ለመቋደስ (በአራዳ ቋንቋ እናትየውን ለማመቻቸት) እንጣጣር ነበር። በሆነ ለደመወዝ በቀረበ አንዱ ሰሞናችን ታዲያ፣ ከየት እንበደር? እያልን መላ እየዘየድን እያለ... በድንገት አንድ የአትሌቲክስ ድል በጓደኛችን ቤት ቲቪ ላይ ተሰማ። ለቱርክ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት ኤልቫን አንደኛ ወጥታለች፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደሞ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል። ያንን እንዳየን እኔና ዳኛው ጓደኛዬ (ስሙን ልጥራው ይሆን?) በደስታ እርስበርስ ተያየን!😀 ቆይ ሰው ሀገሩ ወርቅ ተነጥቃ ምን ፈገግታ ያለዋውጠዋል? በማግሥቱ ይሁን በሳልስቱ "አንተ ጠይቃቸው፣ የለም አንተ ጠይቃቸው" ተባብለን ለኤልቫን እናት ሞቅ ያለ እንኳን ደስ ያለዎት መልዕክታችንን ካሰማን በኋላ... ፀጉራችንን እያከክን (አንደኛችን)... "ከሰሞኑ ደመወዝ ሲወጣ የሚመለስ ትንሽ ብር ይኖርዎት ይሆን... የኤልቫን እናት?" የምትለዋን ወሳኝ ጥያቄ እንደምንም አምጠን ተነፈስናት😀😀😀! መልሳቸው ከጀት የፈጠነ እሺታ ነበር! እንዴታ! ደሞ ምን ችግር አለ? ስጦታ አልጠየቃችሁኝ? ያውም ብድር? ደሞ ልጄ ልካልኛለች ቤትሽን አሳድሺ ብላ! አይዟችሁ፣ ሲቸግራችሁ እናታችሁ ነኝ፣ ጠይቁኝ፣ አትፍሩ...!?" ተብለን በነፍስ ወከፍ በጠየቅነው ልክ ብድር ተለቀቀብን😊😀😀! አቤት ደስታ? አቤት ፌሽታ?! ከማጣት በኋላ የምትገኝ ሲሣይ... አቤት በረከቷ?!🥰😊😀 ታዲያ ሁሌ ስለ ኤልቫን ሳስብ... በእናቷ በኩል... ደብረብርሃን ላይ.. ለጠብሽ ሰሞናችን እንደ አንዳች ሲሣይ ከሠማይ ወርዳ የደረሰችልንን እያሰብኩ... ሁሌ ፈገግ እላለሁ! ደሞ ጓደኞቼም ቀልደኞች ናቸው... አንዳንዴ ኧረ ሰሞኑን ድርቅ መታን እኮ... አሁንስ ሰበብ አጣን... ያቺ ኤልቫን ለገሠ ከሰሞኑ አንድ ውድድር አሸንፋ ይሆን? እንባባላለን። ሣቅ በሣቅ። ኧረ አልሰማሁም፣ አልሰማሁም ይላል ሌላው ሰው። ከዚያ ይቺ ጦልጧላ ማሸነፍ አቅቷት ነው አሁን? የማንን ጎፈሬ ስታበጥር ነው..? እኛ እሺ ምን እንሁን?? 😀😀😀 ሌላ ሳቅ! ብዙ ሳቆች! ጊዜዎችህ፣ ዘመኖችህ፣ ወራቶችህ፣ የፍፍስሃና የሃዘን ሰዓቶችህ፣ የጠብሽና የሃላል ቅፅበቶችህ ሁሉ አብሯቸው የተያያዘ አንዳች የሰው ታሪክ አላቸው። በዐድሜህ ሁሉ የሆነ አብሮህ የሚደሰት፣ አብሮህ የሚከፋ፣ አብሮህ ምች የሚመታ፣ አብሮህ ከሲሣይህ የሚቋደስ አንድ ሰው፣ ብዙ ጓደኛ፣ ብዙ ሰዎች አሉ። ይህ ነገር በተለይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን በብዛት ተለይቶ የተሰጠን ትልቅ የጋራ ህይወት፣ ትልቅ የተባረከ ዕፁብድንቅ ሥጦታ ይመስለኛል። ከሃገርህ ርቀህ ብዙውን ጊዜ፣ አጣህም አገኘህም፣ ተደሰትክም ከፋህም፣ ጨነቀህም አለፈልህም... ብዙ ጊዜ በብቻህ ጀልባ ላይ ነህ። ወቅቶችህ አኗኗሪ፣ ትዝታ ፈጣሪ፣ አዳማቂ ሰው የላቸውም። ሰው አልባ ህይወት፣ ትንፋሽ የለሽ ዕድሜ ይሆንብኛል። እና ሳልወድ በግድ የድሮውን መከራና ደስታ እናፍቃለሁ። ሳልወድ በግድ በድሮ ትዝታዎች ውስጥ ስመላለስ አገኘዋለሁ ራሴን። አሁንም ወደ ኋላ በትዝታ የመለሰኝ መነሻ ሃሳብ... የሲፋን ለኔዘርላንዶች መሮጥ ነበር። በሷ የተነሳ የጥንቷ የጠዋቷ ኤልቫን አብይለገሠ እና የደብረብርሃኗ ደግ፣ ደስተኛ፣ ትሁት እናቷ ትዝ አሉኝ! ጓደኞቼ ትዝ አሉኝ። ቀኖቻችን ትዝ አሉኝ። ያ ሁሉ ወጣትነት። ተስፈኝነት። ሃቀኝነት። የጋራ ደስታችን። የጋራ ድብርታችን። የጋራ ጎጇችን። የጋራ ሀገራችን። የጋራ ዓለማችን። የጋራ ላይፋችን። ብዙ ወርቃማ ትዝታዎች ተግተልትለው ወሰዱኝ በሃሳብ። የደብረብርሃን የኤልቫን እናት በዕድሜ፣ በጤና አሁንም እንደሚኖሩ ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ። ስለ ደግነታቸው፣ በአካል የራቀቻቸውን ልጃቸውን ድል በሰሙ ቁጥር፣ ደስታቸውን የሚጋራቸው ወገን ሲያገኙ... ከዓይኖቻቸው የሚፈልቁት የደስታ ጮራዎች አሁን ፊቴ ላይ ድቅን ይሉብኛል። ባሉበት መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ። ለሁሉም። ለሁላችንም። የሰው ሃገር ባንዲራ ይዘው እንዲሮጡ ህይወትና ዕጣፈንታ ያስገደደቻቸውን የእናት ኢትዮጵያ አፈር ያበቀለቻቸውን ውድ ልጆቻችንን ሁሉ... ለእነሱም። ፈጣሪ መንገዳችንን እንዲያቀናልን። መልካሙን ሁሉ እንዲያመጣልን ምኞቴ ነው። ፈጣሪ እናት ሀገራችንን፣ ሕዝባችንን፣ አብዝቶ ይባርክ! በረካ ሁኑ! ♥️ መልካም ጊዜ!!🙏 by assaf Hailu @wegoch @wegoch @paappiihttps://t.me/mk219s

  • አለት ጎጆ! አምነውሽ ለመጡ  የእጅሽን ጸጋ ለመስጠት ምትጓጊ, በውስጥሽ ለሚኖር የየእለት ምግቡን ፈጽመሽ ማትነፍጊ። በማንም በምንም የማትመሰዪ የህይወት እፎይታ, የሰዎችን ስሜት በልብሽ ያከበርሽ የሚስጥር ገበታ! የፈገግታሽ ፋኖስ በሀዘንተኛ ልብ ተስፋን የሚዘራ, ፭፭የሀዘንሽ እንባ  የሸፈተችን ነፍስ በፍቅር ሚጣራ። የተፋቀረ ልብ በንጽሁ እቅፍሽ የምታገናኚ, አለምን አስትተሽ በልዩ አለምሽ የምታስመንኚ። በየትኛው ቀለም በየትኛው ብእር ውለታሽን ጽፌ በውብ ቃል ልግለጽሽ? በቃላቴ መሀል, በስሜቴ መሀል,   ከሀሳቤ በላይ ጎልቶ ይሰማኛል ጥበብ ሆይ ውብ ድምጽሽ! ሩሀማ። ጥበብ ሁሌም ትንገስ!https://t.me/mk219s

  • ‎አንዳንድ ጊዜ ሰው ከዓለም ሲሸሽ የሚፈልገው ብቸኝነት አይደለም፤ ከራሱ የሚያመልጥበት ቦታ ነው። በሰዎች መካከል መኖር እየከበደው ሲመጣ፣ የራሱን ድምፅ ከሌሎች ድምፅ ለመለየት ሲያቅተው፣ ወደ ውስጡ ይመለሳል። ግን ወደ ውስጥ መመለስ ሁልጊዜ ወደ ሰላም አይመራም። አንዳንዴ ውስጣችን ከውጭው ዓለም የበለጠ ጫጫታ አለው። ‎ ‎ይህንን ጫጫታ በጣም ጥልቅ በሆነ የሥነ-ልቦና ብዕር የጻፈው ፌዮዶር ዶስቶዬቭስኪ ነው። Notes from Underground ለእኔ የሰው ልጅ ከሌሎች ጋር ስለሚኖረው ግጭት ብቻ የሚናገር መጽሐፍ አይደለም፤ ከራሱ ጋር ስለሚያደርገው የማያቋርጥ ጦርነት የሚናገር መጽሐፍ ነው። ‎ ‎“Underground” የሚለው ቃል በራሱ የሚያመለክተው አንድ ጨለማ ክፍል ብቻ አይደለም። የሰው ውስጣዊ መደበቂያ ነው። ሰው ለሌሎች ማሳየት የማይፈልገውን ራሱን የሚያስቀምጥበት ቦታ። ቁጣውን፣ ቅናቱን፣ ፍርሃቱን፣ ኩራቱን፣ ድካሙን እና ሌሎች እንዲያዩት የማይፈልገውን የራሱን ፊት የሚያስቀምጥበት ቦታ። ‎ ‎ሰው በዚያ ቦታ ሲኖር ማንም አይፈርድበትም። ግን አንድ ፈራጅ አለ፤ እሱም ራሱ ነው። እኛም ይህን ሁኔታ እናውቀዋለን። ሌሎች ሰዎች የማያውቁትን ስለራሳችን እኛ እናውቃለን። ስለዚህ አንዳንዴ ከሌሎች ይልቅ ራሳችን በጣም እንፈራለን። ‎ ‎የUnderground ሰው ችግሩ ብቸኝነት ብቻ አይደለም። ችግሩ እጅግ ብዙ ማሰቡ ነው። አንድ ነገር ከመከናወኑ በፊት ያስባል፤ ከተከናወነ በኋላም ያስባል፤ ለምን እንዳደረገው ያስባል፤ ሌሎች ምን እንዳሰቡበት ያስባል፤ ከዚያም ስለራሱ ማሰቡን ይጀምራል። ‎እንዲህ ሲሆን ማሰብ ከእውቀት ወደ እስር ቤት ይቀየራል። ‎ ‎ምክንያቱም ሕይወት በሁሉን ነገር አስቀድመን እርግጠኛ እንድንሆን አትጠብቅም። መኖር ማለት አንዳንድ ጊዜ ሳናውቅ መሄድ፣ ሳንረጋገጥ መምረጥ፣ እንደምንሳሳት እያወቅን መሞከር ነው። ‎ ‎ነገር ግን የUnderground ሰው ይህንን አይቀበልም። እርግጠኛ ሳይሆን እርምጃ መውሰድ ይከብደዋል። እና በዚህ መካከል ሕይወት ከእጁ እያመለጠች ትሄዳለች። ‎ ‎ምናልባት የዘመናችን ሰውም ከዚህ በጣም አይርቅም። ‎ስለራሳችን ብዙ እንሰማለን። ስለ ስነ-ልቦና፣ ስለ ራስን ማወቅ፣ ስለ ድንበር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ራስን መውደድ እና ስለ ውስጣዊ ሰላም ብዙ እንነጋገራለን። ግን ራሳችንን ለመረዳት በምንሞክርበት ጊዜ አንዳንዴ ራሳችንን ከመኖር እንከለክላለን። ‎ ‎ራስን መተንተን መቼ ነው የሚበቃው? ‎ራስን መፈለግ መቼ ነው ራስን መደበቅ የሚሆነው? ‎ ‎ይህ የዶስቶዬቭስኪ ጥያቄ ዛሬም አልሞተም። ‎ከመጽሐፉ ውስጥ በጣም አስደናቂው ነገር ሰው ሁልጊዜ ለራሱ ጥቅም የሚሠራ ፍጡር አለመሆኑን ማሳየቱ ነው። ‎ ‎ሰው እንደሚጎዳው እያወቀ አንዳንድ ነገር ያደርጋል። የሚያጣውን እያወቀ ይሄዳል። የሚያሳዝነውን እያወቀ ይመርጣል። ‎ ‎ለምን? ‎ ‎ምክንያቱም ሰው በቁሳዊ ጥቅም ብቻ የሚመራ ማሽን አይደለም። ነፃነት ይፈልጋል። እና ነፃነት ማለት ትክክለኛውን ምርጫ ብቻ ማድረግ አይደለም፤ ስህተት የማድረግ መብትንም ያካትታል። ‎ ‎እዚህ ላይ ዶስቶዬቭስኪ ሰውን ከማሽን ይለያየዋል። ማሽን ትክክለኛውን ትእዛዝ ይፈጽማል። ሰው ግን አንዳንዴ ትክክለኛውን ነገር እያወቀ እንኳን ሌላውን ይመርጣል። ‎ ‎ምናልባት ይህ የሰው ድክመት ነው። ወይም ደግሞ የነፃነቱ ዋጋ። ግን ከዚህ በላይ የሚያሳዝነው ነገር አለ። ‎ሰው በሌሎች ሲጎዳ አንድ ቀን ሊረሳ ይችላል። በራሱ ሲጎዳ ግን ማምለጫ የለውም። ‎ ‎ምክንያቱም ከራስህ መሸሽ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ መሄድ አይደለም። ቦታ መቀየር አይደለም። ሰዎችን መቀየር አይደለም። ምክንያቱም የምትሸሸውን ሰው ሁሌም ከአንተ ጋር ነው ። ‎ ‎ከራስ መሸሽ የማይቻል ጉዞ ነው። ሰው አንድ ሰውን ሊተው ይችላል። ከቤቱ ሊወጣ ይችላል። ከከተማው ሊርቅ ይችላል። ስልኩን ሊዘጋ ይችላል። ማንነቱን እንኳን ሊቀይር ይችላል።ግን ከሁሉም በራቀበት ምሽት ብቻውን ሲቀር እንደገና የሚያገኘው ራሱን ነው። ‎ ‎የዶስቶዬቭስኪ ጥበብ ግን ሰውን እንደ አስቀያሚ ፍጡር በመሳል አይጠናቀቅም። በጨለማው ውስጥም የሰው ልብ ሙሉ በሙሉ እንዳልሞተ ያሳየናል። ‎Underground ሰው ከዓለም የራቀ ቢሆንም፣ አሁንም መታየት ይፈልጋል። መወደድ ይፈልጋል። መረዳት ይፈልጋል። ይህ ነው የሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ ተቃርኖ፦ “አትቅረብብኝ” እያለ፣ “እባክህ አትተወኝ” ብሎ በውስጡ መጮህ። ‎ ‎ምናልባት ብዙ ሰዎች እንዲህ ናቸው። በጣም እንዳይጎዱ በሩን ይዘጋሉ፤ ከዚያም ማንም ባለመግባቱ ይገረማሉ። ልብን ለመጠበቅ የሠራነው ግንብ አንድ ቀን እስር ቤታችን ይሆናል። ‎ ‎ምናልባት የሕይወት ጥበብ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ መረዳት አይደለም። ምናልባት እኛ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ እንደማናውቅ መቀበል ነው። ምክንያቱም ሰው የተጠናቀቀ ማንነት አይደለም። እየተፈጠረ ያለ ሰው ነው። ‎ ‎ዛሬ የምንጠላው ራሳችን ነገ ልንረዳው እንችላለን። ዛሬ የምንፈራው ነገር ነገ የምንወደው ሊሆን ይችላል። ዛሬ የምንሸሸው ማንነት ነገ የምንቀበለው ማንነት ሊሆን ይችላል። ‎ ‎ስለዚህ ከUnderground መውጣት ማለት ጨለማውን ማጥፋት አይደለም። ጨለማው እንዳለ እያወቅን በውስጡ ብርሃን መፈለግ ነው። ‎ራስን መውደድ ማለት ፍጹም መሆንን መጠበቅ አይደለም፤ የማንወደውን ጎናችንንም ለመሸከም መማር ነው። ‎ ‎ምናልባት በመጨረሻ የምንፈልገው ነፃነት ከሌሎች ሰዎች ነፃ መሆን ሳይሆን፣ ከራሳችን ፍርድ ነፃ መሆን ነው። እና ምናልባት የUnderground በር የሚከፈተው በውጭ በሚገኝ ቁልፍ አይደለም። ራሳችንን ያለፍርድ ለመመልከት በምንጀምርበት ቀን እንጂ። #Dostoevsky #NotesFromUnderground #Philosophy #Literature #BookReview #Psychology #SelfReflection ©️የሶሪት ማስታወሻ ‎https://t.me/mk219s

  • Senedu Gebre ስንቴ ትሞታለች ? ወፍ አለች—ቢጫ ወፍ እሸት የለመደች፣ ከጠባቂው ወንጭፍ ስንቴ ያመለጠች። ወርውሮ ቢስታት ቀስት አዘጋጀላት፣ እሸት ስትፈለፍል ጠርንቆ ሊጥላት። ድንጋይ ወረወረ፣ ቀስቱንም ወነጨፈ፤ ወፊቷ ተረፈች፣ በረረች ከነፈች። ካይኑ ተሰወረች፡፡ እሱ ግን አመነ ፣ እሱ ግን አወራ ወፊቷ እንደሞተች— «ከድንጋይ ብታመልጥ ከቀስት መች ተረፈች!» አለ አሉ ምስኪኑ ፣ ተኩሶ የሚስት ፣ የወሬ ደላላ ስንቴ ትሙትለት ፣ ለሱ ኢጎ ብላ ...https://t.me/mk219s

  • የቴፒዋ አይሻ «በዓለም በጋርድ ታሪክ ትልቅ ጀብድ የፈፀሙ 5 ጀግኖች» ደረጃ 1፡ የማይበገረው የሰይፍ ንጉሠ-ነገሥት—የሙሳሺ ሚያሞቶ ዘላለማዊ ታሪክ የሰይፍ ጫፍ ከነፍስ ጋር በሚገናኝበት በጥንታዊቷ ጃፓን ምድር፣ የሞት ጥላ እንኳ ስሙን ሲሰማ በረዓድ የሚርበደበድበት አንድ ወደር-አልባ ሰው ተፈጠረ። ሙሳሺ ሚያሞቶ። እርሱ ተራ ተዋጊ አልነበረም፤ ከስጋና ደም ይልቅ ከብረት እና ከነበልባል የተሰራ፣ በምድር ላይ የተመላለሰ እውነተኛ አውሎ-ነፋስ እንጂ። የጃፓን ኃያላን ሾጉኖችና ዳይሚዮዎች ደህንነታቸውን በሙሉ ሠራዊት ሳይሆን፣ በእርሱ ሁለት እጆች ላይ በተሰቀሉት ገዳይ ሰይፎች ላይ ጥለው በሰላም ይተኙ ነበር። የሙሳሺ የጥበቃ ሚስጥር ከተለመደው መከላከል እጅግ የራቀ ነበር፤ ለእርሱ ምርጡ ጥበቃ የጠላትን እስትንፋስ ገና ከመነሻው አምክኖ ማጥፋት ነው። ከስልሳ በላይ በሚሆኑ የሞት-ሽረት የሰይፍ ፍልሚያዎች ውስጥ አንገቱን ለሞት አጋልጦ ገብቷል፤ ነገር ግን አንዲትም ቀን አልተሸነፈም፣ አንዲትም ቅጽበት ወደ ኋላ አላፈገፈገም። በእርሱ ፊት የቆመ ማንኛውም ገዳይ ወይም ወራሪ፣ የሰይፉን ብልጭታ ከማየቱ በፊት ነፍሱ ከአካሉ ተለይታ ትበናለች። በአንዲት ጭጋጋማ ሌሊት፣ ታዋቂው የዮሺኦካ ጎሳ በሙሉ ኃይሉ የሙሳሺን መሪ ለመግደል እና ሙሳሺን ራሱን በአንድ ጀምበር ለመደምሰስ የክህደት ወጥመድ አዘጋጀ። በደርዘን የሚቆጠሩ ምርጥ ሰይፈኞች፣ ቀስተኞችና ጦረኞች ጫካውን ከበው በዝምታ ተጠባበቁ። ማንኛውም ሟች ሰው እንዲህ ያለውን ሰራዊት ሲመለከት ፍርሃት አጥንቱን ሰብሮት ይሸሻል፤ ሙሳሺ ግን ያንን ጨለማ የተቀደደው በፈገግታው ነበር። ሙሳሺ ብቻውን፣ በሁለቱ እጆቹ የያዛቸውን ታዋቂ ረጅም እና አጭር ሰይፎቹን—የኒተን ኢቺ-ርዩ ጥበቡን—መዞ ወደ ጠላት ማዕበል ውስጥ እንደ መብረቅ ተወረወረ። አየሩ በብረት ግጭት እና በደም ድምፅ ተናወጠ። ሙሳሺ ሲንቀሳቀስ እግሮቹ መሬት የሚነኩ አይመስሉም ነበር፤ የሰይፉ እንቅስቃሴ ከብርሃን ፍጥነት ጋር እየተሽቀዳደመ የጠላትን ሰይፍ ይሰብራል፣ አንገታቸውን እንደ እሸት ያጭዳል! ጠላቶች ሙሳሺን በአንድ አቅጣጫ ሊያስሩት ሲሞክሩ፣ እርሱ ግን በአንድ ጊዜ በግራና በቀኝ እጁ በሚያወዛውዛቸው ሰይፎች እንደ ዙሪያ-መለስ እሳት አውሎ-ነፋስ ሆነባቸው። ፍላጻዎች ሲዘንቡበት በሰይፉ ጫፍ እየቆረጠ አከሸፋቸው፤ ጦሮች ሲወረወሩበት በአየር ላይ እየተሽከረከረ ሰባበራቸው። ያንን እይታ የተመለከተ ማንኛውም ጠላት ከፊቱ ያለው ሰው ሳይሆን፣ የጦርነት አምላክ ራሱ እንደወረደባቸው አመነ። እያንዳንዱ እርምጃው የጥበቃ ጥበብን ወደ ፍፁም የጥበብ ደረጃ ያደረሰ ነበር። የተጣለበትን መሪ ለማዳን ሲል የጠላትን ዋና አዛዦች እየመረጠ በሰከንዶች ልዩነት ውስጥ መሬት ላይ ዘረራቸው። የጠላት ሠራዊት በቁጥር ብዛት ሊውጠው ቢሞክርም፣ ሙሳሺ ግን በወደቁት አስከሬኖች ላይ እየረገጠ ወደ ፊት ይገሰግስ ነበር፤ በእርሱ ፊት መቆም ማለት ራስን ወደ እቶን እሳት እንደ መወርወር ሆነ። በዚያች ሌሊት የፈሰሰው ደም የጫካውን ሳር ቀባው፤ የዮሺኦካ ጎሳ ምርጥ ተዋጊዎች አንድ በአንድ በሙሳሺ እግር ስር ወደቁ። የተረፉት ጥቂት ገዳዮች መሳሪያቸውን እየጣሉ በፍርሃት እያበዱ ወደ ጫካው ሸሹ። ሙሳሺ ብቻውን ቆሞ ሳለ፣ በዙሪያው የነበረው ጩኸት ጠፍቶ አስፈሪ ጸጥታ ነገሠ፤ የሰይፉ ጫፍ በጠላት ደም ተሞልቶ ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር። ሙሳሺ ሚያሞቶ ለጠበቃቸው መሪዎች የማይደፈር የብረት ምሽግ፣ ለጠላቶቻቸው ደግሞ የማይቀረው የፍርድ ቀን ነበር። እርሱ ጠባቂ ብቻ አልነበረም፤ የጦርነትን ህግጋት በራሱ መንገድ የፃፈ፣ በታሪክ ውስጥ "የሰይፍ ቅዱስ" (Kensei) ተብሎ የነገሠ የማይነካ አፈ-ታሪክ ነው። በህይወቱ ዘመን ሁሉ በሰይፍ ተፈትኖ ያልወደቀው ሙሳሺ፣ የመጠበቅን ትርጉም በታማኝነት ብቻ ሳይሆን በፍፁም የበላይነትና አቻ በሌለው አሸናፊነት ተርጉሞታል። የትኛውም የዓለም ሰራዊት፣ የትኛውም ገዳይ እርሱ የቆመበትን ደጃፍ ሰብሮ የማለፍ አቅም አልነበረውም። ዛሬም ድረስ በዓለም ታሪክ ውስጥ የሙሳሺ ሚያሞቶ ስም ሲጠራ፣ አንባቢን ከመቀመጫው የሚያስነሳው ያ ወደር-የሌለው ወኔ፣ ብቸኝነትን የናቀው የማይበገር ድፍረቱ እና ከስልሳ በላይ ውጊያዎች ያለምንም ሽንፈት የዘለቀው ዘላለማዊ የጀግንነት አክሊሉ ነው። እርሱ በጋርዶች ታሪክ አናት ላይ የተቀመጠው፣ ሊደገም የማይችል ቁጥር አንድ ታሪክ ነው!https://t.me/mk219s

  • የቴፒዋ አይሻ «በዓለም በጋርድ ታሪክ ትልቅ ጀብድ የፈፀሙ 5 ጀግኖች» ደረጃ 2፡ የሞት መልአክ የተሸነፈበት አውድማ—የዲያን ዌይ የማይሰበር ጽናት በጥንታዊቷ ቻይና የሶስቱ መንግስታት ዘመን፣ ከምድር በላይ እንደ ተራራ የገዘፈ፣ በሰው አምሳል የተፈጠረ አውሬ የሚመስል አንድ የግል ጠባቂ ነበረ—ዲያን ዌይ። እርሱ ለጦር አበጋዙ ካኦ ካኦ ቀን ከሌሊት እንደ ጥላ የሚከተለው፣ በሁለት ግዙፍ የብረት መጥረቢያዎቹ ጠላትን እንደ ቅጠል የሚያረግፍ የማይበገር ጋሻ ነበር። በዋንቼንግ ጦርነት ወቅት፣ ካኦ ካኦ ባልጠበቀውና በተንኮል በተሞላ ድንገተኛ ጥቃት በጠላት ኃይሎች ተከበበ። የካኦ ካኦ ወታደሮች ተደናግጠው ሲሸሹ፣ በዚያ የክህደት ምሽት ንጉሣቸውን ከእርግጠኛ ሞት ለማዳን የተዘጋጀው ዲያን ዌይ ብቻ ነበር። የእርሱ ዓላማ አንድና አንድ ብቻ ሆነ—ካኦ ካኦ ፈረሱን አስፈንጥሮ እስኪያመልጥ ድረስ መላውን የጠላት ሠራዊት በግቢው መግቢያ በር ላይ ብቻውን መግታት። ጠላቶች ዲያን ዌይን ለማዳከም አስቀድመው የሚዋጋባቸውን ታዋቂ የብረት መጥረቢያዎቹን በስውር ሰርቀውት ነበር። ነገር ግን እርሱ ያለ መሳሪያም ቢሆን መሳሪያ ራሱ ነበር። መጥረቢያዎቹ እንደሌሉ ሲያውቅ፣ ምንም ሳይደናገጥ ከወደቁት የጠላት ወታደሮች እጅ ሁለት ረጅም ሰይፎችን አንስቶ ወደ ጠባቡ መግቢያ በር አመራ። የጠላት ሠራዊት እንደ ማዕበል ወደ በሩ ሲጎርፍ፣ ዲያን ዌይ ብቻውን ቆሞ አገሳ። ያ ግሳት በምሽቱ ጨለማ ውስጥ የነጎድጓድ ያህል አስተጋባ። በሺዎች የሚቆጠሩ የጠላት ወታደሮች በአንድ ሰው ላይ ጦርና ሰይፋቸውን ሰብቀው ቢመጡም፣ ዲያን ዌይ ግን እንደ አንበሳ እየተወረወረ በአንድ ጊዜ በርካታ ወታደሮችን መሬት ላይ ይዘርር ጀመር። በእጁ የያዛቸው ሰይፎች የጠላትን ጋሻና ሰይፍ በመምታት ብዛት ተሰባበሩ። መሳሪያ አልባ የሆነው ዲያን ዌይ ግን አላፈገፈገም፤ ይልቁንም በባዶ እጁ የጠላት ወታደሮችን አንቆ በመያዝ፣ ሁለት የጠላት ወታደሮችን እንደ ዱላ እያወዛወዘ ሌሎቹን መምቻና መከላከያ መሳሪያ አደረጋቸው። ያንን እጅግ የሚያስፈራ ትዕይንት ያዩ የጠላት ወታደሮች በፍርሃት ሽባ ሆኑ። ከሩቅ የሚወረወሩ ፍላጻዎችና ጦሮች የዲያን ዌይን ግዙፍ አካል በየአቅጣጫው በሱት። በሰውነቱ ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ ጦሮች ተሰክተው ደሙ እንደ ፏፏቴ ቢፈስም፣ ዲያን ዌይ ግን መተላለፊያውን ለአንዲት ኢንች እንኳ ለቆ አልወጣም። እያንዳንዱ የተሰካበት ጦር የበለጠ የሚያቆመው እንጂ የሚያስተኛው አልሆነም። የጠላት ወታደሮች ወደ እርሱ ለመቅረብ ፈርተው በርቀት ቆመው በጦር ይወጉት ጀመር። ዲያን ዌይ በከፍተኛ የደም መፍሰስ ምክንያት ዓይኖቹ እየፈዘዙ፣ ጉልበቶቹ እየተንቀጠቀጡ ቢመጡም፣ በሩን ዘግቶ የቆመው አካሉ ግን እንደ ግራናይት ድንጋይ ሳይናወጥ ጸንቶ ቆመ። ካኦ ካኦ በሰላም ማምለጡን የሚያረጋግጥበት ጊዜ ድረስ ነፍሱን በብረት ቁርጠኝነት አገታት። በመጨረሻም፣ ከአቅም በላይ በሆነ የቁስል ብዛትና ደም መፍሰስ የዲያን ዌይ እስትንፋስ ቆመ። ነገር ግን እጅግ የሚያስደንቀው ክስተት የተፈጠረው ከሞተ በኋላ ነበር፤ ዲያን ዌይ ነፍሱ ከሥጋው ከተለየች በኋላም ቢሆን ወደ መሬት አልወደቀም! በሁለት እግሮቹ እንደ ቆመ፣ ዓይኖቹን በቁጣ ወደ ጠላት እንዳፈጠጠ በሩ ላይ ድንጋይ ሆኖ ቀረ። ጠላቶች ሞቷል ብለው ለማመን አልደፈሩም። ለረጅም ደቂቃዎች ማንም ሰው ወደ አስከሬኑ ለመቅረብ አልደፈረም፤ የሞተው ዲያን ዌይ እንኳ ከሺህ ሕያዋን ተዋጊዎች በላይ ያስፈራ ነበር። ዲያን ዌይ በዚያች ምሽት ህይወቱን ሰጥቶ ካኦ ካኦን አተረፈ።በታሪክ መዝገብ ውስጥም አንድ ሰው በባዶ እጁ፣ በቆመበት አስከሬኑ ጭምር ጠላትን በማስፈራት ለጌታው የቆመበት ወደር የሌለው የታማኝነትና የጀግንነት ታላቅ ተምሳሌት ሆኖ ተጻፈ።https://t.me/mk219s

  • የቴፒዋ አይሻ «በዓለም በጋርድ ታሪክ ትልቅ ጀብድ የፈፀሙ 5 ጀግኖች» ደረጃ 3፡ የአንድ ሰው ጦር—የሮበርት ብሩስ የብረት ግንብ የመካከለኛው ዘመን የቤተ-መንግሥት ኮሪደሮች በወርቅና በሐር የተሸፈኑ ቢሆኑም፣ በውስጣቸው ግን የሚርመሰመሱት ገዳይ እባቦችና የስልጣን ጥመኞች ነበሩ። በዚያ የሴራና የደም አውድማ ውስጥ፣ የንጉሡ ደህንነት በሠራዊት ብዛት ሳይሆን በአንድ ብርቱ ሰው ትከሻ ላይ አርፎ ነበር። እርሱም ስሙ ሲጠራ የጠላትን ልብ በፍርሃት የሚያርድደው፣ የንጉሥ ሄነሪ ታማኝ ጋሻና አፈ-ታሪካዊው ጠባቂ ሮበርት ብሩስ ነበር። በአንዲት ጨለማ የተከናነበች ሌሊት፣ በቤተ-መንግሥቱ ላይ የሞት ጥላ አጠላ። በንጉሡ ላይ ያመጹ፣ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁና ለደም የተጠሙ በርካታ ገዳዮች የቤተ-መንግሥቱን ውጫዊ ጥበቃዎች በጸጥታ ደምስሰው ወደ ንጉሡ መኝታ ክፍል አመሩ። ዓላማቸው አንድና አንድ ብቻ ነበር—ንጉሡን በአልጋቸው ላይ እንዳሉ አርደው አገሪቱን በግርግር መቆጣጠር። የብረት ሰይፎች ድምፅና የሞት ሹክሹክታ ከበሩ ጀርባ ሲሰማ፣ የሮበርት ብሩስ ስሜቶች እንደ ነብር ነቁ። ከፊቱ የተደቀነው አደጋ የተራ ውጊያ ሳይሆን፣ በቁጥር እጅግ የላቀ የታጠቀ ኃይል መሆኑን በቅጽበት ተረዳ። ነገር ግን በእርሱ ልብ ውስጥ ፍርሃት የሚባል ነገር ቦታ አልነበረውም፤ በእርሱና በሞት መካከል ያለው ልዩነት የተጣለበት ቅዱስ አደራ ብቻ ነበር። ሮበርት ንጉሡን በፍጥነት ከመኝታ ክፍሉ ውስጥ በሚስጥር ወደሚያወጣው መተላለፊያ ገፋቸውና በሩን ከኋላቸው ቆለፈው። አሁን በዚያ ጠባብና ረጅም ኮሪደር ውስጥ ንጉሡን ለማዳን የቀረው ጊዜ በጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የሚለካ ነበር። ሮበርት ብሩስ ወደ ኋላ አልሸሸም፤ ይልቁንም ግዙፉን የብረት ሰይፉን መዝዞ፣ ብቻውን እንደ ብረት ግንብ ኮሪደሩን ዘግቶ ቆመ። ገዳዮቹ ወደ ኮሪደሩ ሲገቡ ያዩት የተደናገጠን ጠባቂ ሳይሆን፣ ሞትን በፈገግታ የሚቀበል የአንበሳ መንፈስ የተላበሰ ተዋጊ ነበር። "ንጉሡን የምትፈልጉ ከሆነ፣ አስከሬኔን ረግጣችሁ ማለፍ አለባችሁ!" የሚል የሮበርት ኃይለኛ ድምፅ የቤተ-መንግሥቱን ግድግዳዎች አናወጠው። ያ ድምፅ ለገዳዮቹ የፍርሃት፣ ለንጉሡ ደግሞ የተስፋ አዋጅ ነበር። ውጊያው ሲጀመር ምድር የተናወጠች መሰለች። በርካታ ሰይፎች በአንድ ጊዜ ወደ እርሱ ቢወረወሩም፣ የሮበርት ብሩስ ሰይፍ ግን እንደ መብረቅ እየተወረወረ የጠላትን ጥቃት ይመክት፣ አጥቂዎቹንም አንድ በአንድ ይቆርጥ ጀመር። በዚያ ጠባብ ኮሪደር ውስጥ ቁጥራቸው ምንም አልጠቀማቸውም፤ የሮበርት አካልና ሰይፍ ሙሉውን መተላለፊያ ዘግቶት ነበር። ደቂቃዎች ወደ ሰዓታት ተቀየሩ። የሮበርት አካል በበርካታ የሰይፍና የጦር ቁስሎች ተተለተለ፤ ደሙ በድንጋዩ ወለል ላይ እንደ ወንዝ ፈሰሰ። ነገር ግን እያንዳንዱ የደረሰበት ቁስል ህመምን ሳይሆን፣ የበለጠ እብደትንና የበቀል እሳትን በውስጡ አቀጣጠለው። ቁስሉን ንቆ፣ ደሙን እየጠረገ፣ የወደቁትን ጠላቶች አስከሬን እንደ መከላከያ ግንብ እየተጠቀመ ውጊያውን ቀጠለ። ገዳዮቹ በድንጋጤና በፍርሃት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ጀመሩ። ከፊታቸው የቆመው ተራ ሰው ሳይሆን፣ ሊገደል የማይችል ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ጋሻ እንደሆነ አሰቡ። ሮበርት ብሩስ ብቻውን ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ምርጥ ገዳዮችን መሬት ላይ ዘርሮ፣ የቀሩትን ደግሞ በግርምትና በፍርሃት ሽባ አደረጋቸው። ንጉሡ በሰላም አምልጠው ተጨማሪ የንጉሥ ጦር አስከትለው ወደ ስፍራው ሲመለሱ ያዩት ትዕይንት ማንኛውንም ሰው የሚያስለቅስና የሚያስደንቅ ነበር። መላው ኮሪደር በጠላት አስከሬኖችና በደም ተሞልቷል፤ በመሃል ደግሞ ሮበርት ብሩስ በሰይፉ ተደግፎ፣በከባድ ቁስል እየደማ ነገር ግን ቆሞ ይጠብቃቸው ነበር። ሮበርት ንጉሡን በሰላም ሲመለከት፣ የድል ፈገግታ በደሙ በተጨማለቀው ፊቱ ላይ በራ። ያ ቀን አንድ እውነተኛ ጠባቂ በታማኝነትና በጀግንነት ሲቆም፣ መላውን ሠራዊት ብቻውን መመከት እንደሚችል ለዓለም ያስመሰከረበት ታሪካዊ ቀን ሆነ፤ የሮበርት ብሩስ ስምም እስከ ዛሬ ድረስ የማይበገረው የአንድ ሰው ጦር ተብሎ ይዘከራል።https://t.me/mk219s

  • የቴፒዋ አይሻ «በዓለም በጋርድ ታሪክ ትልቅ ጀብድ የፈፀሙ 5 ጀግኖች» ደረጃ 4፡ አይኑን የበላው ተዋጊ—የሺያሁ ዱን የማይበገር ጽናት በጥንታዊቷ ቻይና የሶስቱ መንግስታት ዘመን፣ ምድር በደም እና በጦርነት አቧራ በተሸፈነችበት ወቅት፣ ስሙ ሲነሳ ጠላትን የሚያንቀጠቅጥ አንድ ግዙፍ ተዋጊ ነበረ። ሺያሁ ዱን—የኃያሉ ወታደራዊ መሪ የካኦ ካኦ የቀኝ እጅ እና ዋነኛ ጥበቃ። ለእሱ ጦርነት የሕይወቱ እስትንፋስ ሲሆን፣ የካኦ ካኦን ደህንነት መጠበቅ ደግሞ ከራሱ ነፍስ በላይ የሚበልጥ ቅዱስ አደራው ነበር። በአንድ ወቅት በከባድ የጦር ሜዳ ውጊያ ላይ ሳሉ፣ አየሩ በፍላጻዎች ብዛት ተሸፍኖ ነበር። የጠላት ሰራዊት በካኦ ካኦ ላይ ያተኮረውን ከባድ ማዕበል ለመስበር ሺያሁ ዱን በግንባር ቀደምትነት ሰይፉን መዝዞ ይዋጋ ነበር። በዚያ ከፍተኛ ትርምስ ውስጥ ግን የጠላት አላሚ ፍላጻውን አዘጋጅቶ ወደ ሺያሁ ዱን አቃጣ። በቅጽበት የተተኮሰው ፍላጻ አየሩን ሰንጥቆ በመብረቅ ፍጥነት መጣ። ከመከላከል በፊት ፍላጻው የሺያሁ ዱንን ግራ ዓይን በቀጥታ ወጋው። የህመም ጩኸት እና የደም ፍሰት በጦር ሜዳው ላይ ሰፈነ፤ የጠላት ወታደሮች ታላቁ ተዋጊ ወደቀ ብለው በደስታ እልል አሉ። ነገር ግን በዚያች ቅጽበት የሆነው ነገር በታሪክ መዝገብ ላይ ታይቶ የማይታወቅ አስደናቂ ክስተት ነበር። ሺያሁ ዱን ከመሬት አልወደቀም፤ ይልቁንም በዓይኑ ውስጥ የተሰካውን ፍላጻ በገዛ እጁ ጨብጦ በኃይል ነቀለው። ከፍላጻው ጫፍ ጋር አብሮ የተነቀለው የራሱ ግራ ዓይን ነበር። በዙሪያው የነበሩ ወታደሮች በድንጋጤ ደነዘዙ። ሺያሁ ዱን ግን የራሱን ዓይን በእጁ ይዞ ወደ ሰማይ በመመልከት፣ “ይህ ከአባቴ የወረስኩት ደም፣ ከእናቴ ያገኘሁት አካል ነው፤ እንዴት አድርጌ ዝም ብዬ እጥለዋለሁ!” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ያለ ምንም ማንገራገር እና ፍርሃት፣ የተነቀለውን የራሱን ዓይን በቀጥታ ወደ አፉ ከተተው፤ አግበስብሶም ዋጠው። ያ ድርጊት ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ፍርሃት እና ህመም በላይ የሆነ፣ ከአለት የጠነከረ የመንፈስ የበላይነት ማሳያ ነበር። ዓይኑን ከዋጠ በኋላ፣ በደሙ የተጨማለቀውን ፊቱን ወደ ጠላት አዞረ። በአንዱ ዓይኑ ብቻ እያየ፣ ሰይፉን ወደ ሰማይ በማንሳት እንደ አንበሳ አገሳ። ያንን ያዩ የጠላት ወታደሮች ፍርሃት አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ ስለገባ እግራቸው ማምለጫ መንገድ መፈለግ ጀመረ። በአንድ ዓይኑ እየተመለከተ፣ ያንን ፍላጻ የተኮሰውን የጠላት አዛዥ በከፍተኛ ፍጥነት አሳዶ ደረሰበት። በጥቂት ሰከንዶች ውስጥም የገዳዩን አንገት በሰይፉ ቀስፎ በመቅላት የካኦ ካኦን ጠላቶች አበነነ። የካኦ ካኦን ሕይወት ከመስዋዕትነት አድኖ የጦርነቱን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ቀየረው። ከዚያች ቀን ጀምሮ ሺያሁ ዱን "አንድ ዓይናቸው ተዋጊ" ተብሎ መጠራት ጀመረ። አደጋዎች እና የሰውነት ጉዳቶች ለእሱ ማደናቀፊያ ሳይሆኑ የጀግንነቱ ማረጋገጫ አክሊሎች ነበሩ። እስከ ህይወቱ ፍጻሜ ድረስ ለካኦ ካኦ የነበረው ታማኝነት አልተናወጠም። የሺያሁ ዱን ታሪክ የሚያስተምረን እውነተኛ ጥበቃ ማለት አካላዊ ጥንካሬ ያለው ብቻ ሳይሆን፣ ህመምን እና ሞትን ንቆ ለተጣለበት አደራ እስከ መጨረሻው የሚቆም የማይበገር መንፈስ ያለው መሆኑን ነው። እርሱ በታሪክ መዝገብ ውስጥ የታማኝነት እና የመስዋዕትነት ትልቁ ምልክት ሆኖ ይኖራል።https://t.me/mk219s

  • የቴፒዋ አይሻ«በዓለም በጋርድ ታሪክ ትልቅ ጀብድ የፈፀሙ 5 ጀግኖች» --- ደረጃ 5፡ በበረዶ ላይ የተጻፈው የደም ማኅተም በ1905 ዓ.ም የቅዱስ ፒተርስበርግ አየር በበረዶ ግግር ብቻ ሳይሆን በስውር የፖለቲካ ሴራ እና በረቂቅ ስጋት የተሞላ ነበር። በሴንት ፒተርስበርግ ቤተ-መንግሥት አካባቢ የሚነፍሰው ቀዝቃዛ ንፋስ፣ የዛርስት ሩሲያ ግዛት የመጨረሻ ቀናት ከፊቷ እንደሚጠብቃት የሚናገር ይመስል ይጮኻል። በዚህ ታሪካዊና አስፈሪ አየር ሁኔታ ውስጥ ግን፣ ከአለት የጠነከረ፣ ከብረት የበረታ አንድ ሰው በዝምታ ይቆም ነበር—የንጉሡ ታማኝ ጥበቃ አሌክሳንደር ፕሮቶፖፖቭ። ለአሌክሳንደር፣ የሩሲያው ንጉሥ ዳግማዊ ኒኮላስ ጥበቃ መሆን የተራ ሥራ ወይም የደመወዝ ጉዳይ አልነበረም። ለእሱ ያ ኃላፊነት የሕይወቱ መመሪያ፣ የነፍሱ ጥሪ እና የተቀደሰ መሀላው ነበር። ንጉሡ በእያንዳንዱ እርምጃቸው የሩሲያን ዕድል ሲሸከሙ፣ አሌክሳንደር ደግሞ ያንን ዕድል ከማንኛውም አደጋ የመጠበቅን የታሪክ አደራ በጫንቃው ላይ ተሸክሞ ይጓዝ ነበር። ያ አስከፊ ቀን የመጣው ሳይታሰብ ነበር። ንጉሡ በሕዝብ መካከል በሚንቀሳቀሱበት ወቅት፣ የአየሩ ጸጥታ በድንገት ተሰበረ። ከተሰበሰበው ሕዝብ መካከል የጥላቻና የበቀል እሳት ያነደደ አንድ ገዳይ በእጁ የተደገነ መሳሪያ ይዞ ብቅ አለ። የጠመንጃው አፍ በቀጥታ ወደ ንጉሡ ዳግማዊ ኒኮላስ ደረት ተቃጣ—የሞት ጥላ በንጉሠ ነገሥቱ ላይ ጥሎ ለማለፍ ጥቂት ሚሊሰከንዶች ብቻ ቀሩ። በዚያች ቅጽበት ጊዜ የቆመ መሰለ። በዙሪያው የነበሩት ሰዎች በድንጋጤ ሲቀዘቅዙ፣ የሰው ልጅ አእምሮ ሁኔታውን ተረድቶ ውሳኔ ለመስጠት በሚታገልበት በዚያች አጭር ሰከንድ ውስጥ፣ የአሌክሳንደር ፕሮቶፖፖቭ መንፈስ ግን ቀድሞ ወስኖ ነበር። በእሱ እና በንጉሡ መካከል ያለው ርቀት በሰከንድ እጅግ አነስተኛ እጅግ የጠበበ ቢሆንም፣ ለእሱ ግን የዘላለም ያህል ረጅም ይመስል ነበር። ያለ ምንም ማንገራገር፣ ያለ ምንም ፍርሃት እና ስለራሱ ሕይወት አንዲት ቅጽበት እንኳ ሳያስብ፣ አሌክሳንደር አካሉን እንደ ጋሻ ወደ ፊት ወረወረ። ሰውነቱን በንጉሡ እና በገዳዩ ጥይት መካከል አጋደለው። ያ ውሳኔ ከአእምሮ ይልቅ በደሙ ውስጥ ከነበረው ጥልቅ ታማኝነት እና ጀግንነት የሚመነጭ ድንቅ ጥበብ ነበር። የጥይቱ ድምፅ አየሩን ሰነጠቀው። የቀዘቀዘው አየር በጋለ ጥይት እና በደም ጠረን ተሞላ። ጥይቶቹ የንጉሡን ደረት ሳይሆን የአሌክሳንደርን የብረት ያህል የጠነከረ አካል በሳሱት። እያንዳንዱ ጥይት ወደ ሰውነቱ ሲገባ ከፍተኛ ሥቃይ ቢያስከትልም፣ የእሱ ትኩረት ግን በጥይቱ ህመም ላይ አልነበረም። አሌክሳንደር ወደ መሬት ሲወድቅ፣ ደሙ በነጭ በረዶ ላይ እንደ ቀይ አበባ ተበተነ። ያ የቀይ ደም እና የነጭ በረዶ ውህደት፣ የታማኝነት እና የመስዋዕትነት ምስል ሆኖ በታሪክ መዝገብ ላይ ተቀረጸ። በሰውነቱ የገባው እያንዳንዱ ጥይት የጀግንነቱ ማኅተም፣ የደረሰበት ቁስል ደግሞ ለታማኝነቱ የተሰጠ ከፍተኛው ሜዳሊያ ነበር። ንጉሡ ዳግማዊ ኒኮላስ ምንም ሳይነካቸው በተአምር ከሞት አመለጡ። ገዳዩ ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ሲውል፣ የንጉሡ ዓይኖች ግን ወደ መሬት ወድቆ በደሙ ውስጥ ወደሚዋኘው ታማኝ ጥበቃቸው አተኮሩ። አሌክሳንደር በመጨረሻዎቹ የሕይወት ሰከንዶች ውስጥ ሆኖ ንጉሡ ደህና መሆናቸውን ሲያረጋግጥ፣ በፊቱ ላይ የነበረው የሕመም ስሜት በሰላምና በኩራት ተተካ። የአሌክሳንደር ፕሮቶፖፖቭ የልብ ምት ቀስ በቀስ እየቀነሰች መጣች፤ የሕይወቱ መብራት በቅዱስ ፒተርስበርግ በረዶ ላይ ጠፋች። ነገር ግን እሱ የሞተው እንደ ተሸናፊ ሳይሆን፣ የተጣለበትን የዘመናት አደራ በደሙ ያረጋገጠ ታላቅ ባለድል ሆኖ ነበር።የእሱ መስዋዕትነት የንጉሡን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የንጉሠ ነገሥቱን ክብር ታደገ። ዛሬም ድረስ በታሪክ መዝገቦች ውስጥ የአሌክሳንደር ፕሮቶፖፖቭ ስም ሲነሳ የሚታወሰው የሞተበት ቀን አይደለም፤ ይልቁንም ለታመነለት መሪ የራሱን ሕይወት አሳልፎ ለመስጠት ያሳየው የማይናወጥ ጽናት እና ተወዳዳሪ የሌለው ጀግንነት ነው። እሱ በበረዶው ላይ የተወው ደም፣ እስከ ዘላለም የሚያበራ የታማኝነት እና የራስ ወዳድነት አልባነት አርማ ሆኖ ይኖራል።https://t.me/mk219s

  • "ስለደጃዝማች ዑመር ስመጥር የሕይወት ታሪክ።" 🟢🟡🔴 አገሩን አፍቃሪ ፤ ንጉሠ ነገሥቱን አክባሪ ጠላት በመጣ ጊዜ ስለነፃነቱ ተጋዳይና ተከራካሪ ፥ አርበኛው ጀግና ክቡር ደጃዝማች ዑመር ስመጥር እስከ ጊዜ ሞታቸው ድረስ ለሀገሪቸውና ስለንጉሠ ነገሥታቸው ፤ ስለተወደደች ሰንደቅ ዓላማቸው እምነትና ከፍ ያለ የጀግንነት ሥራ ሲሠራ የኖሩ ናቸው። በኋላም በሀገራቸው በሱማሌ አገር የሡልጣን ዓሊ ዮሱፍ እንደራሴ ሆነው በናኢባነት በሱማሌ አገር የኤል ቡር ገዥ ሆነው ከ፳፭ ዓመት ጀምረው እስከ ፵፰ ዓመት አስተዳደሩ። ተጀምሮ እስቲጨርስ እግዚአብሔርን ፈሪ ፤ ንጉሥን አክባሪ ነበሩና የሚናገሩት ሁሉ እውነት ብቻ ነበር። ጭንቅም ቢመጣ አይዟችሁ ባይ ፤ የማይበሳጩ ልበ ሙሉ ነበሩ። በሚኖሩበት በኤል ቡር አውራጃ ኢጣሊያን ፮ ባታሊዮን ወታደር ይዞ ባስገደዳቸው ጊዜ ለጊዜው መሣሪያቸውን አስረከቡ። ነገር ግን ደጃዝማች ዑመር ስመጥር መሣሪያቸውን ባስረከቡ ባ፭ ወር ያነኑ ፮ ባታሊዮን ወታደር ፈጅተው ፤ መሣሪያቸውን ገፍፈው አምልጠው ከሀገራቸው ወጡና ሺላቦ ተቀመጡ። ከዚህ በኋላ ፥ እሺላቦ ድረስ ኢጣሊያ ጦር ሠርቶ ቢመጣ ለጦርነት የመጡትን ወታደሮች ፈጅተው ፥ ፈረንጁን አረዱት ፤ ፫ኛ በቆራሄ በረሃ ኢጣሊያ ወታደሩን አሰናድቶ ጦር ሠርቶ ቢመጣባቸው የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ድል አድርገው መለሱት። ፬ኛ ጠላት ከመሸገበት ገብተው ሲዋጉ ብዙ ሕዝብ ቢያልቅባቸውና የተረፈውም ሕዝብ ወደ ኢጣሊያ ቢገባ እሳቸው ምንም ቢሆን አልገባም ብለው ወደገሃቡር አምልጠው ሔዱ። በዚያም ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ፥ ደጃዝማች ገብረ ማርያም በተሾሙ ጊዜ ደጃዝማች ዑመር ስመጥር የሠሩትን የጀብዱ ሥራ ከተረዱ በኋላ ፤ በውጋዴ አውራጃ የሱማሌ ወታደር እንዲቀጥሩ ፈቅደውላቸው ብዙ ወታደር ሰበሰቡ። ወዲያው ከግርማዊነታቸው ፊታውራሪ ተባሉ። ግፈኛው ኢጣሊያን ሀገራችንን ሊወራት ባሰበ ጊዜ መጀመሪያ በወልወል ተዋጉ። ፪ኛ በገለጉቤ ተዋጉ ፫ኛ በቆራሄ ተዋጉ። ፬ኛ በሃነሌ ተዋጉ። ፭ኛ ከደጋሃቡርና ከጅጅጋ ማህል ተዋግተው ከደጃዝማች አፈወርቅ በታች ሆነው ሕዝቡን እያጽናኑ ጅጅጋ ገቡ። ማታ ጅጅጋ ገብተው ጧት ወራሪው ኢጣሊያ በገባ ጊዜ እየተታኰሱ ወደ ድሬዳዋ ሔዱ። ከዚያም አምልጠው ወደ ሐርጌሣ ሔዱ። ሐርጌሣም በገቡ ጊዜ የእንግሊዝ መንግሥት በማዕርግ ተቀብሏቸው በአደን አገር ሲኖሩ ባ፭ቱ በሥቃይ ዘመን በጸሎትና በኀዘን ለሀገራቸው ሲያለቅሱ ኢትዮጵያ ተቋቋመች ጠላቷንም ጣለች እሳቸውም ሀገራቸው ገቡ። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥታችን ይህን ልፋታቸውን አይተው የጅጅጋና የውጋዴ ገዥ አድርገው ደጃዝማች ብለዋቸው ሲኖሩ ጥንት በ፮ ጥይት ተመትተው ቆስለው የነበረው ቁስል እያመረቀዘ ስላመማቸው ፤ ሐረር መጥተው ሲታከሙ ቆይተው ባ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. በመጋቢት ፲ ቀን አረፉ። ስለ ቀብሩም በሐረር ከተማ አብደል መቃብር ልዑል መኰንን መስፍነ ሐረር መኳንንቶቻቸውን አስከትለው መሥሪያ ቤቱ ሁሉ ተዘግቶ ሕዝቡ ፥ ክርስቲያኑም እስላሙም ሳይቀር ወጥቶ ወታደር በመሣሪያ ተሰልፎ በሐረር ከተማ ባለው በእስላም መቃብር በታላቅ ክብር ተቀበሩ። ክቡር ደጃዝማች ጣሰው ዋለሉ የሐረር አውራጃ ዋና እንደራሴ ፤ የጀግንነታቸውን ዲስኩር እመቃብራቸው አፋፍ ቆመው አንብበው ልጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን ደስ አሰኙ። ትንሽ የለቅሶ እንጉርጉሮ። ተጋዳይ እወልወል እጠረፉ ዳር ፥ ተጋዳይ አፍዱግ ላይ እጠረፉ ዳር ፥ ተጋዳይ ቆራሄ እጠረፉ ዳር ፤ ተጋዳይ ሃነሌ እጠረፉ ዳር ፤ የመትረየሱ ቄስ የለበን መምህር ፤ ሞት ጠራህ አንተንም ዑመር ስመጥር። ከኀዘንተኛው አንዱ ባላምባራስ አብዶ ሐይድ። ሐምሌ ፳፮ ቀን ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. 🟩🟨🟥 🌼 🌸 🌻 🌹 🟢🟡🔴 🥰💚💛💕 ሞዓ አንበሳ 🦁 💚💛💕 አሸናፊው የይሁዳ አንበሳ 🦁 💞💞💞👑👑👑🙏🙏🙏 👑 💚💛❤️ 👑 ════༺❀༻༺❀༻════╗ 💚💛❤️ ✍ ዕዝራ ሱቱኤል የጥናትና ምርምር ማዕከል። ╚════༺❀༻༺❀༻════╝https://t.me/mk219s

እንሳቅ እንወቅ እንዝናና — tgindex