tgindex
ቅዱሳን ክቡራን

ቅዱሳን ክቡራን

Статистика

እግዚአብሔር ከፈቀደ የእለቱን የቅዳሴ ምስባክ እና ጠቃሚ መንፈሳዊ ቪድዮችን እንለቃለን አንድ አንድ ጥያቄዎችም እንጠይቃለን @EMNE_TSYON @unitte_bot

Последний пост
17 июл.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
591
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
207
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
43
40 постов
Вовлечённость
20,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 591
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://www.facebook.com/share/r/1BZjKinVZA/ አሩሲ 🕯

  • без подписи

  • без подписи

  • ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኳን ለአባቶቻችን ቅዱሳን 12ቱ ደቂቀ ነቢያት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ ✞✞✞ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት ✞✞✞ =>ነቢይ ማለት ከእግዚብሔር ተመርጦ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን): መጻዕያትን (ለወደፊቱ የሚደረገውን) የሚያውቁ ሰዎች ሲሆኑ ሕዝቡን እንዲመሩ: እንዲገስጹም ይላካሉ:: ሕይወታቸውም በቅድስና የተለበጠ ነው:: ነቢያትን በቁጥር መግለጽ ከባድ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን እንድንረዳቸው እንዲህ ትከፍላቸዋለች:: =>በኩረ ነቢያት_አዳም =>ሊቀ ነቢያት_ሙሴ =>ርዕሰ ነቢያት_ኤልያስ =>ልበ አምላክ_ዳዊት =>15ቱ ነቢያት (ከአዳም ጀምሮ እስከ ሳሙኤል) =>4ቱ ዐበይት ነቢያት (ኢሳይያስ: ኤርምያስ: ሕዝቅኤልና ዳንኤል) =>12ቱ ደቂቀ ነቢያት ደግሞ ከሆሴዕ እስከ ሚልክያስ ያሉት ናቸው:: +በዚህች ቀን ታዲያ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት በአንድነት ይታሠባሉ:: እነዚህም:- 1.ቅዱስ ሆሴዕ (ኦዝያ) 2.ቅዱስ አሞጽ 3.ቅዱስ ሚክያስ 4.ቅዱስ ኢዩኤል 5.ቅዱስ አብድዩ 6.ቅዱስ ዮናስ 7.ቅዱስ ናሆም 8.ቅዱስ እንባቆም 9.ቅዱስ ሶፎንያስ 10.ቅዱስ ሐጌ 11.ቅዱስ ዘካርያስ እና 12.ቅዱስ ሚልክያስ ናቸው:: +ቅዱሳኑ ደቂቀ ነቢያት የተባሉት 1.የነቢያት ልጆች በመሆናቸው 2.የጻፏቸው ሐረገ ትንቢቶች በንጽጽር ከዐበይቱ (ከነኢሳይያስ) ስለሚያንስ ነው:: +በምግባር: በትሩፋት: በአገልግሎት ግን ያው ናቸው:: ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እሊህን ነቢያት "እለ አውኀዙ ተነብዮ በእንተ ስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ" ይሏቸዋል:: ( ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መውረድ: መወለድና የማዳን ሥራ የትንቢት ጐርፍን ያፈሰሱ እንደ ማለት ነው :: ) +ቅዱሳኑ ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ባሻገር ዓለማችን ላይ ከነበሩበት ዘመን እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሊደረጉ ያላቸውን ነገሮችም ተናግረዋል:: የነበሩበት ዘመን በአማካኝ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ከ900 እስከ 500 ነው:: በትንቢት ደረጃም እንደነ ሆሴዕና ዘካርያስ 14 ምዕራፎችን: እንደነ አብድዩም አንዲት ምዕራፍ ብቻም የጻፉ አሉ:: +በሕይወታቸው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያሻቸው ናቸውና በየጊዜው ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገሩ የእርሱን ድምጽ ለእሥራኤል (አንዳንዴም ለአሕዛብ) ያደርሱ ነበር:: ፊት አይተው የማያዳሉ ናቸውና ሕዝቡንም ሆነ ነገሥታቱን ስለ ኃጢአታቸው ይገሰጹ ነበር:: በዚህም ምክንያት ከነገሥታቱና ከሕዝቡ አለቆች መከራ ደርሶባቸዋል:: አልፎም ያለ አበሳቸው ሕዝቡ በኃጢአቱ ሲማረክ አብረውት ወርደዋል:: +በመጨረሻ ሕይወታቸውም አንዳንዶቹን ክፉዎች ሲገድሏቸው አንዳንዶቹ ደግሞ በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል:: ዛሬ ነቢያት ከእነርሱ ባሕርይ በተገኘችና ብዙ ትንቢትን በተናገሩላት በእመቤታችን ምክንያት ክርስቶስ ድኅነትን ፈጽሞላቸው በተድላ ገነት ይኖራሉ:: ስለ እኛም ይማልዳሉ:: =>" ናጥሪ እንከ ትሕትና ዘምስለ ንጽሕና" (እንግዲህ እንደ ነቢያት ትሕትናን ከንጽሕና ጋር ገንዘብ እናድርግ) "እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" (ነቢያት መንፈስን ንጹሕ በማድረግ እግዚአብሔርን አይተውታልና: ፊት ለፊትም ተያይተዋልና) /ቅዳሴ ማርያም/ =>ከአባቶቻችን ቅዱሳን ነቢያት በረከት ይክፈለን:: =>ሐምሌ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1."12ቱ" ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት 2.ቅዱስ ሶፎንያስ ነቢይ (ዕረፍቱ) 3.ቅዱሳን ሰማዕታት አቡቂርና ዮሐንስ (ቅዳሴ ቤታቸው) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ /ወንጌላዊው/ 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ /ሰማዕት/ =>+"+ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት:: በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በሁዋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሠከረ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር:: +"+ (1ዼጥ. 1:10) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn

  • "" ንስሓ ግቡ ! "" (ሐዋ. ፪፥፴፰) (ግንቦት 28 - 2018)

  • без подписи

  • 🌿እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ♱ቅዱስ ኤዺፋንዮስ 📝ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው። 💡ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው። ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ። በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ። ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው። 📝ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ። 📝ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር። 💡አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ። 📝ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ። በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ። 📝 እግዚአብሔርም ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች። 📝ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ406 ዓ.ም. ዐርፏል:: እድሜውም 96 ዓመት ያህል ነበር። 🤲አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን! 🗓 ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) 2. ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ 3. አባ ሉክያኖስ ጻድቅ 4. ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ) 3. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4. አባ ገሪማ ዘመደራ 5. አባ ዸላሞን ፈላሢ 6. አባ ለትጹን የዋህ 📖"የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል። እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው። እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም። ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም። ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ።'' (1ቆሮ. 9:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨

  • #አንድ_አምላክ_በሚሆን_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም አሜን እንኳን ለክብር ባለቤት #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ በዓለ #ዕርገት በሰላም አደረሰን! #ዕርገት: በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ #ዕርገት ከ #ጌታችና_ከአምላካችንና_ከመድኃኒታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ “ዕርገት” የሚለው ቃል “ዐርገ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከታች ወደ ላይ መውጣት፣ ክፍ ከፍ ማለት፣ ማረግ ማለት ነው፡፡ ዕርገት (Ascension) ሲባልም ማረግን፣ ከፍ ከፍ ማለትን፣ ወደ ላይ መውጣትን ያመለክታል፡፡ በዓለ ዕርገትም #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በዚህ ዓለም የነበረውን የማዳኑን ሥራ ጨርሶ ወደ ላይ መውጣቱና በቀደመ ክብሩ በ #አብ ቀኝ መቀመጡ የሚከበርበት በዓል ነው፡፡ ለዚህም መሰረት እንዲሆን አርዮስን ለማውገዝ በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን አበው “ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ…/ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ…” ብለው ዕርገቱን በቅዱሳት መጻሕፍት ዋቢነት አስረግጠው ደንግገዋል፡፡ #ዕርገቱ_የትሕትና_ሥራው_የመፈጸሙ_ምልክት_ነው #አምላካችን ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላ እና በሁሉም ቦታ የሚኖር) ነዉ። ስለዚህ #ጌታችን በባሕርይው መውጣት መውረድ የለበትም:: ‘ወረደ፣ ተወለደ’ ሲባል ፍጽም ሰው መሆኑን የትህትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም ከሰማያዊዉ ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም:: በምድር ላይ ሊሰራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ:: እንዲሁም #ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተክርስቲያን የተለየበት ጊዜ የለም። ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋዉ የተደረገዉን ዕርገቱን ያመለክታል። ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋዉ በምድር የስበት ቁጥጥር (Gravitational force) የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ አምላካዊ ስልጣኑን ያሳያል። #የጌታችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስ ዕርገቱ በምድር ላይ የሚሠራውን የትሕትና ሥራ የመፈጸሙ ምልክት ነው፡፡ ዕርገቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “ዐርገ #እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ/ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለ #ጌታችንና_ለመድኀኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ (መዝ ፵፮፥፭፡፮) እንዳለው በታላቅ ክብር እልልታና ምስጋና ነው፡፡ እንዲሁም “ዓረገ ውስተ አርያም ጼዊወከ ጼዋ፣ ወወሀብከ ጸጋከ ለእጓለ እመሕያው – ምርኮን ማርከህ ወደ አርያም ወጣህ፣ ለሰው ልጆችም ጸጋህን ሰጠሃቸው”(መዝ.፷፯፣፲፰) እንዳለው #ጌታችን የድል ዕርገትን ያረገው ወደ ባሕርይ አባቱ ቀኝ ነው፡፡ በእርሱ ዕርገት የጸጋ #መንፈስ_ቅዱስና የዳግም ምጽአት ተስፋዎች ተሰጥተውናል፡፡ የእርሱ ዕርገትም ለነፍሣችን ዕርገት /ለዕርገተ መንግሥተ ሰማያት/ አርአያ ሆኖናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በጻፈው ክታቡ ይህንን ሲያስረዳ “ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው #ጌታችንን በአየር እንቀበለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን” (፩ተሰ. ፬፡፲፯) ብሏል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ዝማሬ በተባለው መጽሐፍ የ #ጌታችንን ማዳን ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ብሎም እስከ ዳግም ምጽአቱ ከብሉያትና ከሐዲሳት እያጣቀሰ አምልቶና አስፍቶ በተናገረበት የምስጋና ክፍል “ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና / በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የ #ድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ/” ብሏል፡፡ ‘ዐረገ’ መባሉ የሌለበት ቦታ ኑሮ ካለበት ቦታ ወደ ሌለበት ቦታ ሔደ ማለት አይደለም፡፡ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ባሕርይ አባቱ መመለሱን፣ የማዳን ሥራውን መፈጸሙን፣ በሥጋ በክብር ማረጉን ለመግለጽ ነው፡፡ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በደመና ዐረገ ሲል በክብር ማረጉን፣ ልዕልናውን መግለጹ ነው፡፡ ደመና ክብሩ ልዕልናው ነውና። በደመና ዐረገ መባሉ በ #እመቤታችን ጀርባ መታዘሉን ለመግለጥ ነው። ደመና ተብላ የተገለጠችው #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ናትና። ከ #ማርያም በነሣው ሥጋ ዐረገ ማለት ነው። ነቢየ #እግዚአብሔር ኢሳይያስ “እነሆ #እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል” (ኢሳ.፲፱፥፩) ብሎ አስቀድሞ በትንቢቱ የተናገረላት ደመና #እመቤታችን ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ #ማርያም እንተ ጾረቶ ዲበ ዘባና፤ ደመናስ የሚላት አምላክን በጀርባዋ የተሸከመችው #ማርያም ናት” በማለት ያስረዳል። ስለዚህ በደመና ዓምድ ዐረገ ሲል ከድንግል #ማርያም በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ ማለት ነው። ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለ #እግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል”(መዝ.፷፯፥፴፫) ብሎ የዘመረው ይህንኑ ያጠይቃል፡፡ ምሥራቅ የተባለች የ #ድንግል ሥጋ ተዋሕዶ ዓርጓልና። #እስከ_ቢታንያም_አወጣቸው በዓለ ዕርገት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን (ከበዓለ ትንሣኤ አርባኛው ቀን) አይለቅም። የ #ጌታችን ዕርገት ከትንሣኤ በኋላ በአርባኛው ቀን (በስድስተኛው ሐሙስ) የሚከበረው ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ #እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው” (ሐዋ. ፩፡፫) በማለት የጻፈውን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም ይህንን ትምህርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች። #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል፡፡ ዕርገቱም የተፈጸመው ስለ ምጽአቱ ባስተማረበትና ዳግም ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት በደብረ ዘይት ተራራ ነበር፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ይህንን “እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ” (ሉቃ ፳፬፡፶) ብሎ በወንጌሉ እንዲሁም “በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው” ብሎ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩፡፩፪ አስፍሮታል፡፡ በልደቱና በትንሣኤው የተገኙትና ለሰው ልጆች መልካሙን ዜና ያበሰሩት ቅዱሳን መላእክት በዕርገቱም ተገኝተው ለአሥራ አንዱ ሐዋርያት የዳግም ምጽአቱን ነገር አሳስበዋቸዋል፡፡ ቅዱስ ሉቃሰ ይህንን ሲገልጽ “እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው #ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው ” (ሐዋ ፩፡፲-፲፩) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም እንደተናገረው እርሱ ዳግም ሲመጣ ሐዋርያቱ ብቻ ያይደለ የወጉት ጭምር ያዩታል (ራዕ ፩፡፯)፡፡ #ሐዋርያቱ_እያዩት_ከፍ_ከፍ_አለ

  • #የግንቦት_13_ግጻዌ_ዘበዓለ_ዕርገት ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_13_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ (1) ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ (2) ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ (3) እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ (4) ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል። (5) ከመላእክትስ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም። እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል (6) ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ። የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል። (7) ስለ መላእክትም። መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ (8) ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። (9) ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ (10) ይላል። ደግሞ። ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ (11) እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ (12) እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም (13) ይላል። ነገር ግን ከመላእክት። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ (14) ከቶ ለማን ብሎአል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን? ወደ ዕብራውያን 1:1-14 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ (18) ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ (19) በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤ (20) ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም። (21) ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤ (22) እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:18-22 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ (1 - 2) ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤ (3) ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው። (4) ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን። ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ (5) ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ። (6) እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለው ጠየቁት። (7) እርሱም። አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ (8) ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። (9) ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። (10) እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ (11) ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። የሐዋርያት ሥራ 1:1-11 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_13_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "ዐርገ #እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ"። መዝ.6÷5-6 #ትርጉም፦ "አምላክ በእልልታ፥ #እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ"። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_13_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️(14) ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ። (15) እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። (16) ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። (17) ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ (18) የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። (19) ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። የማርቆስ ወንጌል 16:14-19 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ መልካም የዕርገት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

  • 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 የግንቦት ልደታ ለማርያም ስርዓተ ማኅሌት ትርጓሜ ከነ ማብራሪያው ክፍል ፫ 🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱 መልክአ ማርያም (ሰላም እብል ለድንግልናኪ) ​"ሰላም እብል ለድንግልናኪ እጽው፤ እንተ እምኔሁ ሠረቀ ፀሐየ መለኮት ሕትው፤ ማርያም ድንግል ዘሥነ ንጽሕኪ ፍትው፤ ለኀዲር በበፍናው በአህጉር ወበድው፤ ዕቀብኒ ወለቶሙ ለሄራን አበው፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም የመለኮት ፀሐይ ለወጣብሽ ለተዘጋው ድንግልናሽ ሰላም እላለሁ፤ የንጽሕናሽ ውበት የተወደደ ድንግል ማርያም ሆይ፤ በየመንገዱ፣ በየሀገሩና በበረሃው ስኖር፤ የደጎች አባቶች (የነቢያት) ልጅ ሆይ ጠብቂኝ። @EOTCmahlet ​ማብራርያ ድንግልናዋ "እጽው" (የተዘጋ) መባሉ፣ ጌታን ከመውለዷ በፊትም፣ በወለደች ጊዜም፣ ከወለደች በኋላም ድንግል መሆኗን ለመግለጥ ነው። ነቢዩ ሕዝቅኤል ያያት "የተዘጋች በር" ምልክት ናት። @EOTCmahlet ​ምሥጢር "ፀሐየ መለኮት" የተባለው ክርስቶስ ሲሆን፣ እርሱም ያለ ዘርዐ ብእሲ (ያለ ወንድ ግንኙነት) ከእርሷ መወለዱን ያረጋግጣል። የነቢያት ተስፋ ፍጻሜ በመሆኗ "ወለቶሙ ለሄራን አበው" ተብላለች። @EOTCmahlet ​ዚቅ (ወለቶሙ ለነቢያት) ​"ወለቶሙ ለነቢያት ይእቲ ማርያም እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ ማርያም ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ እደ ሰብእ፤ ዕፁበ ግብረ መናሥግተ ሥጋ ኢያርኃወ ዕፁበ ግብረ፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም ማርያም የነቢያት ልጃቸው ናት፤ ማርያም የሐዋርያት እናታቸው ናት፤ የሰው እጅ ያልሠራት ፍጽምት ድንኳን (መቅደስ) ናት። የሥጋን ደጅ (ማኅፀንን) ሳይከፍት መወለዱ ድንቅ ሥራ ነው፤ በእውነት ድንቅ ሥራ ነው። @EOTCmahlet ​ማብራርያ ሊቁ እዚህ ላይ የድንግልን የዘር ሐረግና የመንፈሳዊ እናትነት ክብር ያሳያል። "ኢገብራ እደ ሰብእ" (የሰው እጅ ያልሠራት) መባሏ፣ ጌታ ሥጋዋን የነሳው በመንፈስ ቅዱስ ግብር እንጂ በምድራዊ ጥበብ እንዳልሆነ ለመግለጽ ነው። @EOTCmahlet ​ምሥጢር "መናሥግተ ሥጋ ኢያርኃወ" (የሥጋ መዝጊያውን አልከፈተም) የሚለው ቃል፣ ልደቱ ድንቅ መሆኑንና ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ የሚመሰክር ትምህርት ነው። @EOTCmahlet ​ መልክአ ማርያም (በዝንቱ ቃለ ማኅሌት) ​"በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ ለዘይስእለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ መንዳቤ፤ ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ ማርያም እንቁየ ክርስቲ ሎቤ ወምእዝተ ምግባር እምከርቤ፤ ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም በዚህ በምስጋና ቃልና በዚህ በደስታ ድምፅ፣ መከራ በደረሰበት ጊዜ ለሚለምንሽ ሰው፤ የሚለውን ሰምተሽ ፈጥነሽ ድረሺለት። ማርያም ሆይ! የከበርሽ እንቁ ነሽ፤ ከከርቤ ይልቅ ምግባርሽ የሚሸት ነው፤ ማኅፀንሽ የሚናገር መዓዛን (ክርስቶስን) አፍርቷልና። @EOTCmahlet ​ማብራርያ ይህ ቃል አማላጅነቷን በጽኑ የሚያስረዳ ነው። ጸሎታችንን ወደ ልጅሽ አሳርጊልን የሚል የልጅነት ልመና ነው። @EOTCmahlet ዚቅ (ርግብ ፀዓዳ) ​"ርግብ ፀዓዳ ዘእንቊ ድዳ ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ፤ ተወልደት ዮም በምድረ ይሁዳ፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም ነጭ ርግብ፣ የእንቊ መሠረት፣ የጳዝዮን (የከበረ ዕንቊ) አዳራሽ የሆነችው፤ ዛሬ በይሁዳ ምድር ተወለደች። @EOTCmahlet ​ምሥጢር ርግብ የየዋህነትና የሰላም ምልክት ናት። ድንግል ማርያም "ነጭ ርግብ" መባሏ ከጥንተ አብሶ ነጻ መሆኗንና ለዓለም የሰላምን ርግብ (ክርስቶስን) ያስገኘች በመሆኗ ነው። @EOTCmahlet ሰላም ለልደትኪ (ሰላም ለኪ ሐመልማላዊት) ​"ሰላም ለልደትኪ እማኅፀነ ድክምት ሥጋ፤ ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ፤ ማርያም ሥመሪ ወጸሐቂ እንበለ ንትጋ፤ ለማየ ንጽሕኪ ትረስዪኒ ፈለጋ እስመ ንጽሕ ይሁብ ሞገሰ ወጸጋ፡፡ ሰላም ለኪ ሐመልማላዊት ዕፅ ሙሴ ዘርእያ በደብረ ሲና፤ እግዝእትየ ሙዳዩ ለመና ተወልደት ዮም እምነ ኢያቄም ወሐና፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም ወጣትነት ካለፈ በኋላና እርጅና ከመጣ በኋላ፣ ደካማ ከሆነ ሥጋ ማኅፀን ለሆነው ልደትሽ ሰላም ይሁን። ማርያም ሆይ! ያለ ስንፍና ውደጅኝና ፈጥነሽ ድረሺልኝ፤ ንጽሕና ሞገስንና ጸጋን ይሰጣልና ለንጽሕናሽ ውኃ ምንጭ አድርጊኝ። ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ሐመልማላዊት ዕፅ ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን፤ የመና መሶብ እመቤቴ ሆይ፤ ዛሬ ከኢያቄምና ከሐና ተወለደች። @EOTCmahlet ​አንገርጋሪ ወአመላለስ ​"ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም እምሐና ወኢያቄም፤ ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ፤ አማን ተወልደት እመ ብርሃን፡፡" አመላለስ፦ "አማን በአማን ተወልደት እመ ብርሃን፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም ነቢያትንና ጻድቃንን ትታደጋቸው ዘንድ፣ ከሐናና ከኢያቄም በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ፤ የእውነት የብርሃን እናት ዛሬ ተወለደች። በእውነት፣ በእውነት የብርሃን እናት ተወለደች። @EOTCmahlet እስመ ለዓለም ​"ልሳንየ ላዕላዕ ይሴብሐኪ እግዝእትየ እብለኪ፤ አዳም ንባብኪ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ እጓለ አንበሳ በከርሥኪ ጾርኪ እምአንስት ቡርክት አንቲ፤ ለመሠረትኪ የኃትዎ እንቊ ክቡር አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር ዘኀረያ ፀባዖት አማኑኤል፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም እመቤቴ እልሻለሁ፣ ዲዳ (ተብታባ) የሆነው አንደበቴ ያመሰግንሻል፤ ንግግርሽ ያማረ ነው፤ አንቺ የዓለም መሠረት ነሽ። የአንበሳን ልጅ (ክርስቶስን) በማኅፀንሽ ተሸከምሽ፤ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ። ለመሠረትሽ የከበረ እንቊ ያበራለታል፤ የሠራዊት ጌታ አማኑኤል የመረጣት ንጽሕት ሱፍ (ጸምር) እና መንፈሳዊት ሀገር አንቺ ነሽ። @EOTCmahlet ​ማብራርያ "እስመ ለዓለም" ማለት "ለዘለዓለም" ማለት ሲሆን፣ ይህ ምስጋና የድንግል ማርያምን ክብር ለዘለዓለም የማይለወጥ መሆኑን ያበስራል። "ልሳንየ ላዕላዕ" (ተብታባው አንደበቴ) የሚለው ቃል፣ የሊቃውንቱን ትሕትና ያሳያል። የሰው ልጅ አንደበት የእርሷን ክብር ለመግለጥ አቅም ቢያቅተውም፣ በፍቅር ግን ሊያመሰግናት እንደሚገባ ያስተምራል። @EOTCmahlet ​ምሥጢር "መሠረቱ ለዓለም" (የዓለም መሠረት) መባሏ፣ ዓለም ዳግመኛ በልጇ ደም እንዲታደስ ምክንያት ስለሆነች ነው። "እጓለ አንበሳ" (የአንበሳ ግልገል) የተባለው ደግሞ ድል አድራጊው ክርስቶስ ነው። እርሷም ይህን ኃያል አምላክ በማኅፀን የተሸከመች "መንፈሳዊት ሀገር" (ደብረ ጽዮን) ተብላ ትጠራለች። ​ማጣቀሻ ​መዝሙር ፹፮፥፭ "ሰው እናታችን ጽዮን ይላታል" ​ራእይ ፭፥፭ "ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ ድል ነሣ" ይህ ሥርዓተ ማኅሌት ዘግንቦት ልደታ፣ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ "እስመ ለዓለሙ" ድረስ ያለው ምስጋና፣ የድንግል ማርያምን ከኢያቄም ወሐና መገኘት፣ የንጽሕናዋን ልዩ ባሕርይ፣ እና ለዓለም ድኅነት ምክንያት መሆኗን የሚያበስር የቤተክርስቲያን ረቂቅ ትምህርት ነው። ​ሊቃውንቱ ይህንን ምስጋና ሲያቀርቡ "እንደ ርግብ የዋህ፣ እንደ ንጽሕት ደመና ነጭ፣ እንደ ዕፀ ጳጦስ ቅድስት" እያሉ መሆኑን ልብ ይሏል። ዛሬ በእውነት የብርሃን እናት ተወልዳለችና ዓለም ሁሉ ደስ ይበለው። ​ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን። 🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈                  👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹       @EOTCmahlet     # Join & share #

  • 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 የግንቦት ልደታ ለማርያም ስርዓተ ማኅሌት ትርጓሜ ከነ ማብራሪያው ክፍል ፪ 🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱 ምሥጢር በጌዴዎን ጸምር ላይ ጠል እንደወረደ፣ ቃልም በድንግል ማርያም ላይ ያለ ዘርዐ ብእሲ ማደሩን ያመለክታል። "መሠረቱ ለዓለም" መባሏ፣ ዓለም ዳግመኛ የተፈጠረባትና የታደሰባት መሠረት በመሆኗ ነው። ​ነግሥ (ክልኤቱ አዕሩግ) ​"ክልኤቱ አዕሩግ አመ በከዩ ብካየ ረከቡ ወለተ ዘታሥተሰሪ ጌጋየ፤ ለወንጌላውያን ኩልነ ዘኮነተነ ምጉያየ፤ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ፤ ሰማዮምኒ አሥረቀት ፀሐየ፡፡" ​ትርጉም ሁለቱ አረጋውያን (ኢያቄም ወሐና) ምርር ብለው ባለቀሱ ጊዜ፣ በደልን የሚያስተሰርይ ልጅን አገኙ። ለሁላችን ለወንጌላውያን መሸሸጊያ የሆነችን፤ ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱ፤ ሰማያቸውም ፀሐይን (ክርስቶስን) አወጣች። ​ማብራርያ እዚህ ላይ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ልመና ተሰምቶ፣ መካንነታቸው ተወግዶ ድንግል ማርያምን ማግኘታቸው ይነገራል። ድንግል ማርያም "ሰማይ" ተብላለች፤ ምክንያቱም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በእርሷ ወጥቷልና። ​ምሥጢር "ዘታሥተሰሪ ጌጋየ" (በደልን የምታስተሰርይ) መባሏ፣ እርሷ ራሷ ይቅር ባይ ሆና ሳይሆን፣ ይቅር ባዩን ጌታ ወልዳ በማቅረቧና በምልጃዋ ኃጢአታችን እንዲደመሰስ ስለምታደርግ ነው። ​፲፬. ዚቅ (ምሥራቀ መሥራቃት) ​"ምሥራቀ መሥራቃት ሙጻአ ፀሐይ እግዝእትየ ዘመና ሙዳይ፤ ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ፡፡" ​ትርጉም የምሥራቆች ምሥራቅ፣ የፀሐይ መውጫ፣ የመና መሶብ እመቤቴ ሆይ፤ ሁለተኛይቱ ሰማይ (ድንግል ማርያም) ዛሬ ተወለደች። ​ማብራርያ ሊቁ ድንግል ማርያምን "ምሥራቅ" ይላታል። ፀሐይ ሳይወጣ በፊት ጎህ እንደሚቀድድ ሁሉ፣ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ ሳይወለድ በፊት እርሷ ተወልዳ የድኅነትን ብርሃን አሳይታለች። "ዳግሚት ሰማይ" መባሏም ጌታ በዚያኛው ሰማይ እንደሚኖር ሁሉ በእርሷም ስላደረ ነው። ​ምሥጢር "ዘመና ሙዳይ" (የመና መሶብ) መባሏ፣ እስራኤላውያን በበረሃ የተመገቡት መና በመሶብ ውስጥ ይኖር እንደነበር፣ የሕይወት እንጀራ የሆነው ክርስቶስም በማኅፀኗ ስለኖረ ነው። ዛሬ የተወለደችው ይህችን መለኮታዊ መና የምታስገኝ ሰማይ ናት። መልክአ ማርያም (ሰላም ለዝክረ ስምኪ) ​"ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ እምነ ከልቤኔ ወቁስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሁ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡" ​ትርጉም ከከርቤና ከቁስጥ፣ ከሰንበልትም ይልቅ መዓዛው ለሚጣፍጥ ለስምሽ መታሰቢያ ሰላም ሰላም ይሁን። ታላቅ ትእዛዝን የለበስሽ (የታዘዝሽ) ድንግል ማርያም ሆይ፤ የፍቅርሽ ወይን የወንዝ ውኃ መልካሙን የአርዝ ዛፍ እንደሚያጠጣው ሁሉ በየቀኑ ያርጥበኝ (ያርካኝ)። ​ማብራርያ እዚህ ላይ የድንግል ማርያም ስም በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ያለውን ጣዕም ይገልጻል። ወንዝ ለዛፍ ዕድገት መሠረት እንደሆነ፣ የእርሷም ፍቅር ለሰው ልጅ መንፈሳዊ ጥንካሬ ምንጭ መሆኑን ያስረዳል። ​ ዚቅ (በሀኪ ማርያም) ​"በሀኪ ማርያም ዘገነት ኮል ዕፀ ጳጦስ መዝገቡ ለቃል፤ ዕለተ ልደትኪ ዮም በጽድቅ ናብዕል፡፡" ​ትርጉም የገነት ኩል (ውበት) የሆንሽ ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን፤ የቃል (የመለኮት) መዝገብና ዕፀ ጳጦስ ነሽ፤ ዛሬ የልደትሽን ቀን በእውነት እናከብራለን። ማብራርያ "የገነት ኩል" መባሏ ለገነት ውበቷና ክብሯ መሆኗን ያሳያል። "መዝገቡ ለቃል" መባሏ ደግሞ የጌታ ምስጢር የተሰወረባትና የተገለጠባት ግምጃ ቤት በመሆኗ ነው። መልክአ ማርያም (ሰላም ለልሣንኪ) ​"ሰላም ለልሣንኪ ሙሐዘ ሀሊብ ወመዓር ዘተነብዮ ወፍቅር፤ ማርያም ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር፤ ሕብዕኒ እምዓይነ ፀር ወአንጽህኒ እምነውር እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ ወምድር፡፡" ​ትርጉም ትንቢትና ፍቅር የሞላበት፣ የማርና የወተት ፈሳሽ ለሆነው አንደበትሽ ሰላም ይሁን። የትሑታን ተራራዎች ልጅ ድንግል ማርያም ሆይ፤ ከጠላት ዓይን ሰውሪኝ፣ ከነውርም አንጪኝ፤ በሰማይና በምድር ተስፋዬ አንቺ ነሽና። ​ማብራርያ ሊቁ እመቤታችንን "ተስፋዬ" ብሎ ይጠራታል። "ሙሐዘ ሀሊብ ወመዓር" (የወተትና የማር ፈሳሽ) መባሏ፣ ንግግሯ ለሰው ልቦና ሰላምንና ደስታን የሚሰጥ በመሆኑ ነው። ​ዚቅ (መሠረታቲሃ) ​"መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ፡፡" ​ትርጉም መሠረቶቿ በቅዱሳን ተራራዎች ናቸው፤ ሰውም በእርሷ ውስጥ ተወለደ። ​ማብራርያ ይህ ቃል "ሰው" የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፣ እርሱም በሥጋ ከድንግል ማርያም መወለዱንና እርሷም መሠረቷ በቅዱሳን (በነቢያት ትንቢት) ላይ የጸና መሆኑን ያመለክታል። ​መልክአ ማርያም (ሰላም ለአእዳውኪ) ​"ሰላም ለአእዳውኪ እሳተ መለኮት እለ ገሰሳ፤ አውቃፈ ብሩር ወወርቅ ለሥርጋዌሆን ኢሀሠሣ፤ ማርያም ድንግል ለመካን ሕንባበ ከርሣ፤ አንጽህኒ እግዝእትየ ለፍትወተ ዓለም እምርኩሳ፤ በዲበ ሥጋየ ኢትንበር ነጊሣ፡፡" ​ትርጉም የመለኮትን እሳት ለዳሰሱ እጆችሽ ሰላም ይሁን፤ ለጌጣቸው የብርና የወርቅ አምባርን አልፈለጉም። የመካኒቱ (የሐና) የማኅፀኗ ፍሬ ድንግል ማርያም ሆይ፤ እመቤቴ ሆይ ከርኩስ የዓለም ፍትወት አንጪኝ፤ በሥጋዬ ላይ ነግሣ እንዳትኖር። ​ምሥጢር የድንግል ማርያም እጆች ጌታን የታቀፉና የዳሰሱ በመሆናቸው፣ ከምድራዊ ጌጥ ሁሉ የላቁ ቅዱሳን ናቸው። በልደቷ ቀን ይህን ቅድስና እያሰብን ከሥጋ ፍትወት እንድንርቅ እንማጸናለን። ​ዚቅ ​"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ፡፡" ​ትርጉም ኦ ድንግል ሆይ! በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ በሆነ ርክብ ከሐና እና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ። ​ማብራርያ ይህ ቃል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከወላጆቿ ስትገኝ፣ እንደ ማንኛውም ሰው በሕግ በሆነ ጋብቻ መሆኑን ሲገልጥ፤ ነገር ግን ፅንሰቷ እንደ ሌላው ሰው በፍትወተ ሥጋ (በሥጋዊ ደስታ/በደነስ) ሳይሆን፣ መላእክት ባበሰሩት መሠረት በቅድስናና በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ያጠይቃል። @EOTCmahlet ​ምሥጢር "አኮ በፍትወተ ደነስ" (በክፉ ፍትወት አይደለም) መባሏ፣ እርሷ ለንጽሕና የተመረጠች፣ ከማኅፀን ጀምሮ በጸጋ የተጠበቀች መሆኗን ለመመስከር ነው። ይህም የልደቷን ልዩ ቅድስና ያሳያል። @EOTCmahlet ​ወረብ ​"እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ፤ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም ከሐና እና ከኢያቄም በሕግ በሆነ ርክብ ተወለድሽ፤ ከሐና እና ከኢያቄም ተወለድሽ። ​@EOTCmahlet ​ዚቅ (ዘመናሥግተ ሥጋ) ​"ወለቶሙ ለነቢያት ይእቲ ማርያም እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ ማርያም ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ እደ ሰብእ ዕፁበ ግብረ መናሥግተ ሥጋ ኢያርኃወ ዕፁበ ግብረ" @EOTCmahlet ​ወረብ ​"ወለቶሙ ለነቢያት እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ ማርያም፤ ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ እደ ሰብእ፡፡" @EOTCmahlet ​ትርጉም የነቢያት ልጃቸው፣ የሐዋርያት እናታቸው ማርያም ናት፤ የሰው እጅ ያልሠራት ፍጽምት ድንኳን እርሷ ናት። @EOTCmahlet ​ማብራርያ ይህ ክፍል ቀደም ሲል በዝርዝር የቀረበ ቢሆንም፣ በወረብ ደረጃ ሲታይ ግን የድንግልን "ደብተራ ፍጽምት" (ፍጽምት ድንኳን) መሆን ለብቻው አውጥቶ ያሳያል። ይህም ጌታ በሥጋዋ ሲያድር የሰው እጅ ሳይነካት (ያለ ዘርዐ ብእሲ) መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ​

  • 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 የግንቦት ልደታ ለማርያም ስርዓተ ማኅሌት ትርጓሜ ከነ ማብራሪያው ክፍል ፩ 🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱 👉 ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet በቁም ከከበሮና ጽናጽል ጋር @EOTCmahlet 👉ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ 👉በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet በመረግድ 👉ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ 👉በአሐቲ ቃል። በቁም 👉ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet በመረግድ- 👉ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet በቁም 👉ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet በመረግድ 👉ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet በቁም 👉ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ "ልዑል" ብለው እንደጨረሱ እንደሌላው መልክዕ ስምዓኒ ተብሎ በመረገድ አይባሉም እዛው በቁም እንደተባለ ሁሉም ጽናጽሉን አስቀምጦ በጉረሮ 👇👇 👉ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet ትርጉም፦ 👉አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ ምስጋና አቀርባለኹ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ 👉ጩኸቴም በፊትኽ ይድረስ ምስጋና አቀርባለኹ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ 👉ፊትኽን ከእኔ አትመልስ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ 👉በችግሬ ጊዜ ጆሮኽን ወደ እኔ አድምጥ ምስጋና አቀርባለኹ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ 👉በምጠራኽ ጊዜም ፈጥነኽ ስማኝ ምስጋና አቀርባለኹ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። 👉 ለዘለዓለሙ ምስጋና አቀርባለኹ። ያ ማለት ያለ ልዑል እግዚአብሔርን እናመስግነው ማለት ነው። በአንዲት ቃል ዓለምን ኹሉ የፈጠረ አምላክ ፈጽሞ የተመሰገነ ነው። @EOTCmahlet ​፰. መልክአ ሥላሴ ​"ሰላም ለኩልያቲክሙ እለ እሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡" ​ትርጉም በአካል እኩል ለሆናችሁ ለባሕርያችሁ ሁሉ ሰላም ይሁን፤ ሥላሴ ሆይ! ዓለማችሁን ለይቅርታ በጎበኛችሁ ጊዜ፣ ከእናንተ አንዱ እግዚአብሔር ቃል በድንግል ማርያም የአባቶች ተስፋ ተፈጸመ፤ በቀራንዮም የመድኃኒት መስቀል ተተከለ። ​ማብራርያ የሰው ልጅ ድኅነት የተጀመረው በሥላሴ ፈቃድ መሆኑን ይገልጻል። የአዳም ተስፋ የተፈጸመው በድንግል ማርያም ልደትና እመቤትነት ነው። ​ምሥጢር "ተፈጸመ ተስፋ አበው" የሚለው፣ ከአዳም ጀምሮ ነቢያት "ሰማይን ሰንጥቀህ ውረድ" እያሉ የተመኙት ተስፋ፣ ድንግል ማርያም ስትወለድ ፍጻሜ ማግኘቱን ያበስራል። ዚቅ (ለማርያም ዘምሩ) ​"ለማርያም ዘምሩ ለማርያም ዘምሩ መስቀሎ ለወልዳ እንዘ ትጸውሩ፡፡" ​ትርጉም የልጇን መስቀል እየተሸከማችሁ ለማርያም ዘምሩ፤ ለማርያም ዘምሩ። ​ማብራርያ ይህ ቃል በክርስትና ሕይወት ውስጥ መስቀልን መሸከም (መከራን መታገስ) እና እመቤታችንን ማመስገን የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ያስገነዝባል። ​ምሥጢር ክርስቶስን መከተል መስቀልን መሸከም ነው፤ ያንን መስቀል ስንሸከም ደግሞ ድንግል ማርያም በምልጃዋ የጽናት ምንጭ ትሆነናለች። ​መልክአ ሚካኤል ​"ሰላም ለልሣንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ ምገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡" ​ትርጉም የቅዳሴ መዝሙር ለሆነውና እንደ እሳት ነበልባል ለሚነድደው ልሳንህ (አንደበትህ) ሰላም ይሁን፤ ለቃሉ የመንግሥቱ ቀንድ ለሆነው ጣፋጭ ድምፅህም ሰላም ይሁን። ለባለጸጋው ተላፊኖስ የክብሩ ሞገስ የሆንክ ሚካኤል ሆይ! በምሕረትና በይቅርታ ልማድ አንተን የሚመስል የለም፤ ከብቻዋ ከእኅትህ ከድንግል ማርያም በቀር። ​ማብራርያ ሊቁ እዚህ ላይ የሊቀ መላእክትን የቅዱስ ሚካኤልን ምሕረትና ርኅራኄ ይገልጻል። ቅዱስ ሚካኤል ለሰው ልጆች የሚራራ ቢሆንም፣ ከእርሱ በላይ የሚራራና የሚምር ግን ከእመቤታችን በቀር እንደሌለ በማነጻጸር የድንግልን ልዕልና ያሳያል። ​ምሥጢር "እኅትከ ማርያም" ማለቱ፣ ቅዱሳን መላእክትና ቅድስት ድንግል ማርያም በንጽሕናና በቅድስና አንድ ስለሆኑ ነው። ይሁንጂ የድንግል ማርያም ክብር ይበልጣል የሰው ልጅ በድንግል ማርያም አማካኝነት የመላእክት ወንድም/እኅት የመሆንን ክብር ማግኘቱን ያመለክታል። ​ዚቅ (ተውኅቦ ምሕረት) ​"ተውኅቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብስራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል፡፡ ​ትርጉም ለሚካኤል ምሕረት ተሰጠው፣ ለገብርኤል ብሥራት ተሰጠው፣ ለድንግል ማርያም ግን የሰማያት ሀብት (ክብር) ተሰጣት። ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒ ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ፡፡" ትርጉም ለልጅሽ ደም አምሳል ለሆነውና ጣዕሙ ድንቅ ለሆነው ለስምሽ መታሰቢያ ሰላም ይሁን። የሕይወት መሠረትና የቀድሞው የመድኃኒታችን መጀመሪያ ማርያም ሆይ፤ ዓለሙን ለማዳን አንቺን በጎ አድርጎ ፈጠረሽ፤ እግዚአብሔር ይባረክ፣ ስሙም ይመስገን። ​ማብራርያ ድንግል ማርያም "ወሀብተ ሰማያት" መባሏ፣ መላእክት ካገኙት ጸጋ በላይ እግዚአብሔርን በማኅፀኗ የመሸከም ጸጋ ስለተሰጣት ነው። "መሠረተ ሕይወት" መባሏ ደግሞ ለዓለም ሕይወትን ለሚሰጠው ለክርስቶስ መገኛ በመሆኗ ነው። ​ምሥጢር "ጥንተ መድኃኒ" የሚለው ቃል፣ የሰው ልጅ ድኅነት የታሰበው በድንግል ማርያም መሆኑን ያሳያል። ዓለም ሳይፈጠር በእግዚአብሔር ልቡና የታሰበች "ጥንተ መድኃኒት" እርሷ ናት። ​ዚቅ (ወመሠረቱ ለዓለም) ​"ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ እጓለ አንበሳ እጓለ አንበሳ በከርሥኪ ጾርኪ፤ እምአንስት ቡርክት አንቲ ለመሠረትኪ የኃትዎ እንቁ ክቡር፤ አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር ዘኃረያ ፀባዖት አማኑኤል፡፡" ​ትርጉም የዓለም መሠረት አንቺ ነሽ፤ የአንበሳን ልጅ (ክርስቶስን) በማኅፀንሽ ተሸከምሽ። ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ፤ መሠረትሽን የከበረ እንቁ ያበራዋል። የሠራዊት ጌታ አማኑኤል የመረጣት ንጽሕት ፀምር (ሱፍ) እና መንፈሳዊት ሀገር አንቺ ነሽ። ​ማብራርያ "እጓለ አንበሳ" የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሷን ደግሞ "መንፈሳዊት ሀገር" እና "ንጽሕት ፀምር" (ጌዴዎን ያያት ጸምር) በማለት ይገልጻታል።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ²⁰ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና። ²¹ ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። ²² በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ²³ በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም። ²⁴ ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም። ²⁵ ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው! ²⁶ እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። ²⁷ በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ²⁸ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። ²⁹ ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። ³⁰ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። ³¹ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ። ³² ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ ³³ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🕊የሚቀደሰው የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ ወይም የ #ቅዱስ_ዲዮስቆሮ_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ጊዮርጊስ የዕረፍት በዐልና የበዐለ ሃምሳ ሶሞን። ለሁላችንም ይሁንልን። 🕊 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

  • 🕊 #ሚያዝያ_23_ቀን_የዕለቱ_ግጻዌ🕊 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🕊 #ሚያዝያ_23_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታ🕊 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 2ኛ ቆሮ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ በአካይያ አገር ሁሉ ከሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ ጋር በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ ² ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ³ የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ⁴ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን። ⁵ የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና። ⁶ ዳሩ ግን መከራ ብንቀበል፥ ስለ መጽናናታችሁና ስለ መዳናችሁ ነው፤ ብንጽናናም፥ እኛ ደግሞ የምንሣቀይበት በዚያ ሥቃይ በመጽናት ስለሚደረግ ስለ መጽናናታችሁ ነው። ⁷ ተስፋችንም ስለ እናንተ ጽኑ ነው፤ ሥቃያችንን እንደ ተካፈላችሁ እንዲሁም መጽናናታችንን ደግሞ እንድትካፈሉ እናውቃለንና። ⁸ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ ⁹ አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር። ¹⁰-¹¹ እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፥ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፥ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶-⁷ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል። ⁸-⁹ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል። ¹⁰ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 14 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በኢቆንዮንም እንደ ቀድሞ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገብተው ከአይሁድና ከግሪክ ሰዎች ብዙ እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ። ² ያላመኑት አይሁድ ግን የአሕዛብን ልብ በወንድሞች ላይ አነሣሡ አስከፉም። ³ ምልክትና ድንቅ በእጃቸው ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል ስለ መሰከረው ስለ ጌታ ገልጠው እየተናገሩ ረጅም ወራት ተቀመጡ። ⁴ የከተማውም ሕዝብ ተከፍለው እኵሌቶቹ ከአይሁድ እኵሌቶቹም ከሐዋርያት ጋር ሆኑ። ⁵ አሕዛብና አይሁድ ግን ከአለቆቻቸው ጋር ሊያንገላቱአቸውና ሊወግሩአቸው ባሰቡ ጊዜ፥ ⁶ አውቀው ልስጥራንና ደርቤን ወደሚባሉት ወደ ሊቃኦንያ ከተማዎች በእነርሱም ዙሪያ ወዳለው አገር ሸሹ፤ ⁷ በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር። ⁸ በልስጥራንም እግሩ የሰለለ፥ ከእናቱም ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ፥ ከቶም ሄዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። ⁹ ይህም ሰው ጳውሎስ ሲናገር ይሰማ ነበር፤ እርሱም ትኵር ብሎ ተመለከተውና ይድን ዘንድ እምነት እንዳለው ባየ ጊዜ፥ ¹⁰ በታላቅ ድምፅ፦ ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም አለው። ብድግ ብሎም ተንሥቶ ይመላለስ ነበር። ¹¹ ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ፦ አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል አሉ፤ ¹² በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት። ¹³ በከተማውም ፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባን አክሊሎች ወደ ደጃፍ አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ። ¹⁴ ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ ¹⁵ እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን። ¹⁶ እርሱ ባለፉት ትውልዶች አሕዛብን ሁሉ በገዛ ራሳቸው ጐዳና ይሄዱ ዘንድ ተዋቸው። ¹⁷ ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም። ¹⁸ ይህንም ብለው እንዳይሠዉላቸው ሕዝቡን በጭንቅ አስተዉአቸው። ¹⁹ አይሁድ ግን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጡ፤ ሕዝቡንም አባብለው ጳውሎስን ወገሩ የሞተም መስሎአቸው ከከተማ ወደ ውጭ ጐተቱት። ²⁰ ደቀ መዛሙርት ግን ከበውት ሳሉ፥ ተነስቶ ወደ ከተማ ገባ። በነገውም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ወጣ። ²¹-²² በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ። ²³ በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🕊 #ሚያዝያ_23_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🕊 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78(79)፥10-11። #ትርጉም፦ “አሕዛብ፦ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ።” መዝ 78(79)፥10-11። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🕊 #ሚያዝያ_23_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበውን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🕊 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ማቴዎስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ¹⁷ ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ¹⁸ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። ¹⁹ አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤