Islamic post
Статистика- Последний пост
- 8 авг. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ እናንተም የበላዮች ስትኾኑ ምእመናን እንደኾናችሁ አትስነፉ፤ አትዘኑም፡፡(አል ኢምራን 139) መድከም፣ ተስፋ መቁረጥና እጅና እግርን አጣጥፎ መቀመጥ አቅቶን አይደለም ወዳጆቼ። ግና የባሰ እንጂ የተሻለ ነገር አይመጣም ብለን እንጂ። ለሽይጧንና ለተስፋ አስቆራጮች መድረኩን ትተን አንወጣም ብለን እንጂ። አንዳንዱማ የሞት የሞታችንን ስንፍጨረጨር ጠንካራ እንደሆንን ያስበናል። ወዳጆቼ ! በአላህ መንገድ ላይ ተፍጨርጨሩ፣ እጅ አትስጡ፣ አትድከሙ። ©️ ABX ❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️ ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን ለሞቱት ሸሂድነትን የሚወፈቁበት በሰለዋት በካህፍ በዱዓ የታጀበ ጁምዓ ይሁንልን
▬ ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ➢ ከዱዓዎች ሁሉ በላጭ ዱዓ ➢ የአረፋቀን ዱዓ ነው (ዚል ሂጃ 9ኛው ቀን) 📚 حسنه الألباني في صحيح الترمذي - 3585 ነገ ሐሙስ ዚል ሂጃ 9ነኛው ቀን ነው እና በዚህ ውድ ቀን እንጠቀምበት Copy
ያ ኢስማኢል በርግጥ ያኔ አንተ ሸሂድ በሆንክበት ወቅት ህዝቦችህን ጭፍጨፋ እንጅ ረሀብና ጥም ያን ያክል አልጎዳቸውም ነበር። ዛሬኮ ቀና ብለህ ብታያቸው ሁሉም ጠውልገዋል። የሚቀምሱት ሽራፊ ምግብ የሚጠጡት እፍኝ ውሀ የላቸውም። ህፃናቶች የእናቶቻቼው ጡት ደርቆባቸው በዚያው እያሸለቡ ነው። ያ ኢስማኢል አንተ ህዝቤ ነፃ ቢወጣ ብለህ ቢያርፍ ብለህ ሙሉ ሀያትህን ደክመሀል። መላ ቤተሰቦችህን ቀድመህ አጥተህም ፀንተህ ነበር። ፅናትህ ለጉድ ነበር። ቃላት ከቶ አይገልፁትም ነበር። ያኔ በርካታ ልጆችህ ሸሂድ ሆኑ ተብሎ ሲነገርህ ሰው እንደት እናፅናናህ ብሎ ሲጨነቅ አንተ ግን ስብር ብትልም ሱብር ብለህ ስለ ህዝብህ ስዲንህ መጓዝን የቀጠልካትን አንረሳውም። ዛሬ ግን መሶበር ትችል አይመስለኝም። መላው ህዝብ በከበባ ውስጥ ሆኖ በረሀብ እየተገረፈ ከላይ እሳት እየነደደበት ሞቱን እየቆጠረ ሲጓዝ ትሶብር ይሆን? አውቃለሁ ፅኑ ነህ! ቃላት መግለፅ የሚከብዳቸውን መከራ አስተናግደህ የፀናህ! ግና አሁንኮ እንኳን አንተ ከሩቅ ያለው ባእድም መሶበር አቃተው! ለሂክማው ነው እንደ ቀድሞ የወሰደህ ኢስማኢል ? አዝኖልህ ነው እንዴ እስከዛሬ ያየከው ፈተና ይበቃል ከዚህ በሗላ አረፍ በል ብሎ የመረጠህ? ብቻ ታሳዝነኛለህ ወሏህ! ደግሞ ያ በሻሻ ፊትህ ያ ደግም ጀግናም ፊትህ ይናፍቀኛል! እነዚያ ጣፋጭ ልብ ሰርስረው የሚገቡ ንግግሮችህ ብቻ ምን ልበልህ! ዱኒያ ፊቷን በናንተ ላይ አጨለመች ! በዚህ ሁኔታ እንድትኖሩና እንድትሞቱ እጣፈንታችሁ ሆነ! እንደናንተ የተፈተነ ፣ እንናንተ የተከዳ ፣ እንደናንተ ብቻውን የተተው ከቶ ማን አለና!!! አላህ ያውቃል!
https://t.me/REMEDANMUBAREke
የፈጅር ሶላት ሱናዋ ብቻ ዱንያ ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ እስከምትጠፋ ድረስ ካለው ነገር ሁሉ ትበልጣለች። የፈጅር ሱናዋ ብቻ ይህ ከሆነ የፈርዱ ምንዳ ምን ሊሆን ነው❔ የማህበራዊ ሚዲያ አንበሳ መሆኑን ትተን በተግባር ትክክለኛ የአሏህ ባረያ ለመሆን እንጣር። https://t.me/REMEDANMUBAREke
قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيه وَسَلَّمَ: [ أنا ﺯﻋﻴﻢٌ ﺑﺒﻴﺖِ ﻓﻲ ﺭَﺑَﺾِ ﺍﻟﺠﻨﺔِ ﻟﻤَﻦ ﺗَﺮَﻙَ ﺍﻟﻤِﺮﺍﺀَ ﻭﺇﻥ ﻛﺎﻥ ﻣُﺤِﻘًّﺎ، و بِبَيْتٍ فِي وَسَطِ الْجَنَّةِ لِمَنْ تَرَكَ الْكَذِبَ وَإِنْ كَانَ مَازِحًا ] 📚 رَوَاهُ أَبُو دَاوُد የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:- [ የእውነት ባለቤት እንኳን ቢሆን ሙግትን(ክርክርን) ለተወ ሰው በጀነት ዳር ላይ ቤት ዋስ(ተያዝ) እሆነዋለሁ። ውሸትን ለቀልድ እንኳን ቢሆን ለተወ ሰው ጀነት መካከል ላይ ቤት ዋስ እሆነዋለሁ።] [[📚አቡዳውድ ዘግበዉታል። ]] https://t.me/REMEDANMUBAREke
📃የተሳሳተ አባባል: ✖️ህይወት አጭር ናት ምንድነው መጨነቅ: እንደሰትባት ዘና ፈታ እንበልባት... 📃ትክክለኛው አባባል: ✔️የአኼራ ህይወት ጅማሬ እንጂ ፍፃሜ የለውምና: በዚች አጭርና ጠፊ በሆነችው የዱንያ ህይወት ሳንሸወድ: ✔️ለአኼራችን ጥሩ ስንቅ ሰንቀን የዘላለም ህይወታችንን ማርጀትና መታመም የሚባል ነገር ሳይነካን: ✔️በጀነት ውስጥ በመብሉ በመጠጡ: በሁረል ዒኖች: የጌታችን ፊት በማየት... ዘላለማዊ ደስታን እናጣጥም እንኮምኩም! https://t.me/REMEDANMUBAREke
አባት ከሱብሒ እንደተመለሰ "ተነሱ ስገዱ!" ይላል ትናንሽ ሴት ልጆቹን። ወንዱን ልጁን ሁሌ አብሮት ይዞ ስለሚሄድ በሱ አይደራደርም። እናት ደግሞ " ብርድ ነው ተዋቸው ትንሽ ይተኙ። በዚያ ላይ ደግሞ የዕረፍት ቀን ነው ትምህርት የለም።" ትላለች። በዚሁ መሃል ልጆች እስከ አንድ ሰዓት ይተኛሉ። በወላጆች "ይነሱ" እና "ይተኙ" ክርክር መካከል ስንት ልጆች አስተዳደጋቸው ይበላሻል!!። በተለይ በዚህ ዘመን "ይተኛ" ማለት ለልጅ ማዘን አይደለም። " አይሥራ" ማለትም ለልጅ አይጥቅምም። ልጅን የሚጠቅመው ይነሳ፣ ይልመድ፣ ይሥራ ... የሚለው ቃል ነው። ጠዋት ላይ የገሩት ልጅ ማታ ላይ አያለምጥም። ልጅን የሚጎዳው ብርድ ሳይሆን በዲን ታንፆ አለማደግ ነው። ለነገ ሕይወታቸው ስንል በዛሬ ሙቀታቸው እና እንቅልፋቸው ላይ እንጨክናለን። አባቴ አላህ ይዘንለት በጠዋት መነሳትን ስላስለመደኝ ይኸው ሱብሒ ሳይደርስ እነሳለሁ። ዲን መያዝ ፍም የመያዝ ያህል ከባድ በሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል። የዘመኑን ፈተና እንኳን ተኝተን ተነስተንም አልቻልነውም። የጊዜውን ማዕበል እንኳን ሥራ ፈተን ሥራ ይዘንም አንቋቋመውም። አላህ ሁሉን ነገር ያግራልን። https://t.me/REMEDANMUBAREke
መተናነስ ማለት አንድም ሙስሊም አታገኝም ካንተ የተሻለ እንደሆነ ስታስብ ነው ። ወዳጄ በማንም ላይ እንዳትኮራ ማንንም እንዳታሳንስ ኢብኑል ቀይም እንዳሉት ለሰወች እንደምትሆነው አላህ ላንተ ይሆንልሀል ለሰወች አዛኝ ሁን አላህ ያዝንልሀል https://t.me/REMEDANMUBAREke
ዱንያ እኮ ዩሱፍ(ዐሰ) የተሸጠባት ኑህ(ዐሰ) የተዋሸባት ኢብራሂም(ዐሰ)እሳት ላይ የተወረወረባት ሙሳ(ዐሰ)ጠንቅዋይ የተባለባት ሙሀመድ (ሰዐወ) በድንጋይ የተወገሩባት ናት እንደዛም ሁኖ ላንተ እንዲቀልልህ ትመኛለህ?? እናም መጠንከር ነው ወዳጄ https://t.me/REMEDANMUBAREke
ኢብኑል ቀይም አልጀውዚይ አሏህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል"የወንጀል መሰረቶች ባጠቃላይ ሶስት ናቸው። 1,ኩራት፦ይህ ኩራት የሚባለው በሽታ ነው ኢብሊስን የደረሰበት እንዲደርስ ያደረገው። 2,መጓጓት፦ይህ መጓጓት የሚባል በሽታ ነው አባታችን አደምን ዘወታሪ ከሆነችው አለም ገነት ያስወጣው። 3,ምቀኝነት፦ይህ ምቀኝነት የሚባል በሽታ ነው ከሁለቱ የአደም ልጆች አንደኛው ወንድሙን እንዲገድል ያነሳሳው። የእነዚህ ሶስት በሽታዎችን ተንኮል የተጠበቀ የሆነ ሰው በእርግጥ ተንኮል ከተባሉ ነገራቶችባጠቃላይ ተጠብቋል። የክህደት መነሻ ኩራት ፣የወንጀሎች መሰረት መስገብገብ ሲሆን ድንበር የማለፍና የበደል ምንጭ ደግሞ ምቀኝነት ነው። قال الإمام بن القيم رحمه الله كما في الفوائد "أصول الخطايا كلها ثلاثة 1، الكبر: وهو الذي أصار إبليش إلى ما أصاره. 2،والحرص: وهو.الذي أخرج آدم من الجنة. 3،والحسد وهو.الذي جرأ أحد ابني آدم على أخيه.فمن وقي شر هذه الثلاث فقد وقيدالشر، فالكفر من الكبر، والمعاصي من الحرص، والبغي والظلم من الحسد https://t.me/REMEDANMUBAREke
የ ሰዉ ልጅ ግን እንዴት ነዉ በአላህ ላይ ተስፋ ሚቆርጠዉ? https://t.me/REMEDANMUBAREke
በሰዎች መካካል ማስታረቅ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ألا أُخبِرُكم بأفضَلَ مِن درجةِ الصِّيامِ والصَّلاةِ والصَّدقةِ؟ قالوا: بلى، قال: إصلاحُ ذاتِ البَيْنِ، ﴾ “ከፆም፣ ከሶላት፣ ከሰደቃ በላጭና ደረጃው ከፍ ያለውን ተግባር አልነግራችሁምን? እንዴታ! ይንገሩን አሉ ሶሃቦች፦ ‘በሰዎች መካካል ማስታረቅ’ ነው አሉ።” 📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 4919 https://t.me/REMEDANMUBAREke
🏷 የጁመዓ ቀን ሱናዎች 🕌 سنن يوم الجمعة 🕌 ••••••••••••••••••••●✿⊱🍃⊰✿●•••••••••••••••• ❶ الغسل ❷ الطيب ❸ السواك ❹ لبس الجميل ❺ قراءة سورة الكهف ❻ التبكير لصلاة الجمعة ❼ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي •••••••••••••••••●✿⊱🍃⊰✿●•••••••••••••••••• • ገላን መታጠብ • ሽቶ መቀባት ( ለወንድ ብቻ) • ሲዋክ መጠቀም • ጥሩ ልብስ መልበስ • ሱረቱል ካህፍን መቅራት • ለጁመዓ ሶላት ቀደም ብሎ መሄድ • በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን ማብዛት •••••••••••••••••••●✿⊱🍃⊰✿●••••••••••••••••••• ● ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል : ❝ የጁመዕ ሌሊትና ቀኑ ለይ በኔ ሰለዋትን አብዙ ሶለዋታችሁ እኮ ለኔ ይቀርብልኛል ❞ اللَّهُمَّ صلِّ عَلَى مُحمَّدٍ وعلى آلِ مُحمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آل إِبْرَاهيم إِنَّكَ حَميدٌ مَجيد ❝ ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን ❞ 🔖 Share https://t.me/REMEDANMUBAREke
Today's hadith የመስቀል ምልክቶች ካረፈባቸው አልባሳቶች፣ ቁሳቁሶች ከመጠቀም ተጠንቀቅ! ከእናታችን አዒሻ (رَضِيَ ٱللَّٰهُ عَنْهَا) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፦ ﴿أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لَمْ يَكُنْ يَتْرُكُ فِي بَيْتِهِ شَيْئًا فِيهِ تَصَالِيبُ إِلَّا نَقَضَهُ.﴾ “ነብዩ (ﷺ) በቤታቸው ውስጥ አንድንም የመስቀል ስዕልን ያለበትን ነገር አይተውም ነበር፤ ቢያስወግዱት(ቢያፈርሱት ቢያጠፉት) እንጂ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5952 https://t.me/REMEDANMUBAREke
Ya allah 💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔😭😭😭😭🤲 https://t.me/REMEDANMUBAREke
..ከጀነት ሲወጣ ነጭ ድንጋይ ነበር.. «ወንጀል አጠቆረው» ----------------------- ተመልከተው እስኪ የወንጀልን ሞራል፡ እንኳን የሰውን ልብ ድንጋይ ይቀይራል፡ ነጭ የነበረውን አስተውል ያጠቁራል፡ ......ልባችንስ.እንደት ይሆን..⁉️ ነብያዊ ቃሉም እንደመሰከረው፡ ያውና ስታዩት እንደሚናገረው፡ ሀጀረል አስወድን ወንጀል አጠቆረው‼️ ድንጋይ ከቀየረ የወንጀል ክፋቱ፡ ልቤ ከድንጋዩ ጠብቋል በጥፋቱ፡ ነጭ የነበረውን ካደረገው ጥቁር ፡ እንደት ፀልማ ይሆን የልባችን ሽንቁር፡ የኢስላም ጎዳና እንደሚናገረው፡ እውነታውን በግልፅ እንደመረመረው፡ ያንን ነጭ ድንጋይ ወንጀል አጠቆረው!! ....ልባችን ምን ያክል ጠቁሮ ይሆን⁉️ .....ኑረዲን አል-አረቢ https://t.me/REMEDANMUBAREke
አላህ ተይቀኸዉ እምቢ አይልህም ለምነኸዉ አይከለክልም https://t.me/REMEDANMUBAREke
🪄ዛሬ በጥዋት ተነሳው :- አየተነፈስኩ ነው! እግሮቼ ይንቀሳቀሳሉ ልቤም ✨ እየመታ ነው ብርሀን እያየሁ ነው 👀 ከዚ በላይ ምን ቀረ‼️ አልሃምዱሊላህ ያ ረብ🥹 ᴀʟʜᴀᴍᴅᴜʟɪʟᴀʜ... https://t.me/REMEDANMUBAREke
ETHIOPIAN Muslims ❤️❤️❤️❤️ https://t.me/REMEDANMUBAREke