شفعنا (صلی الله علیه وسلم )
Статистика🌸 أیها المشتاقون لنور جماله , صلو علیه وسلمو تسلما ﷺ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2
- 1/48двое суток
- 2
- 1/72трое суток
- 2
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ያስለቀሰኝ ታሪክ😢 . . .. ከሼይኮች አንዱ ባለቤቱ ሞተችበት አላህም ለሚስቱ ምህረትን ያብዛላትና ሸይኹ በጣም አዘነ.. ሀዘኑም በእሷ ላይ የበረታ ሆነ, እናም አንድ የባለቤቱ ጓደኛ ትዕግስት (ሰብር) እንዲሰጠው ብላ መልእክት ላከችለት እና ደብዳቤዋ እንዲህ ይላል... "ሰላም ለእናንተ ይሁን ሼክ እኔ ከሚስትህ ጓደኞች አንዷ ነኝ ስለ ውድ ሚስትህ ኡሙ ሙዓዝ ሞት ተነገረኝ። ያለፍክበት ሀዘንህን ሰምቻለሁ.. እና ታሪኬን አንብብ ... ስለ ማጣት እና ህመም የተከሰተ የመጀመሪያው ታሪክ አይደለም. እንደ እኔ በህመም እና በእጦት የሚሰቃዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሉ። አንዱ ወላጆቹን አጥቶ፣ ወይም ወንድሞቹንና እህቶቹን፣ ወይም ሁለቱንም አጥቶ የሚኖር አለ። ታሪኬ የጀመረው በረመዷን 27ኛው በቀኑ የመጨረሻ ሰአት ላይ ነው። በእለቱ ሁላችንም በአንድ መኪና ተሳፍረን ዑምራ ለማድረግ ወደ ተከበረው የአላህ ቤት ልንሄድ ተስማማን። ወንድሞቼ በየራሳቸው መኪና መምጣትን ትተው ከኛ ጋር በ አንድ መኪና ለመሄድ መፈለጋቸው የ አላህ ውሳኔ ነው ... ስምንት ሰዎች ነበርን... እኔ፣ ወላጆቼ፣ እህቶቼና ወንድሞቼ.. መኪናውን ሚነዳው አባቴ ነበር እና እናቴ ከጎኑ ነበረች። በዚያን ጊዜ እያንዳንዳችን ቁርኣንን ይዘን ሀረም እስክንደርስ ድረስ ሙሉ ቁርዓኑን ቀርተን (አንብበን) ለመጨረስና ዱኣ ለማድረግ ተስማማን ። እናም በዝምታ እና በተመስጦ ማንበብ ቀጠልን ዳግመኛ ማንበብ እንደማንችል ነገር ይመስላል አቀራራችን። እህቴ እያነበበች ታለቅሳለች ሌላኛዋም ወደ እኔ እያየች እያለቀሰች ዱኣ ታደርጋለች... እንባው ለምን እንደሆነ ጠየኳቸው..? ከመካከላቸው አንዷ፡- እያነበብኩ ሳለ የአላህ ድምፅ ወደ እኔ ቅርብ ነው አለችኝ ። በዛን ጊዜ .. ይመስለኛል አባቴ አላህ ይዘንለትና እንቅልፍ አሸነፈው .. መኪናው ከ ኮረብታው ጫፍ ላይ ተንሸራተተ.. ይህ ኮረብታ በተራራው አናት ላይ ነበር የነበረው. መኪናው ከረጅም ርቀት ወደ ሸለቆው ውስጥ ያስገባን ጀመረ.. እና ገለበጠን መኪናው በተንከባለለ ቁጥር አንድ ሰው ከመኪናው ውስጥ ተወርውሮ ይወድቃል .. እኔ ዛፍ ላይ ወደቅኩኝ የቀሩት በሸለቆው ውስጥ ወደቁ.. አደጋው በደረሰበት ሰአት የመግሪብ ሰላት አዛን እየተጣራ ነበር እና ፆመኞች ነበርን..ከዛ... ራሴን ሳትኩኝ ብዙ ደማሁኝ.. አስታውሳለሁ ከእንቅልፌ እንደነቃሁ እየጮህኩኝ ፈልጌያቸው ነበር። ስብራት እና ጉዳት ቢደርስብኝም አንድ ጊዜ እየተራመድኩ አንዴ ደግሞ ተኝቼ እየተሳብኩ እነሱን መፈለግ ጀመርኩኝ ። መኪናው ሲወድቅ ማንም አላየንም ነበር። እነሱ ጋር እስክደርስ ድረስ መጎተት ጀመርኩ ከዛም እህቶቼን አገኘውና ልሸፍናቸው ሞከርኩ.. ሞተውም አገኘኋቸው እያንዳንዳቸውም የፊት ጣታቸው ከፋ አድርገው ነበር ነእና ምስጋና ለ አላህ ይሁን ሸሃዳ ይዘው ነው የሞቱት ። በአንድ ቦታ ሰበሰብኳቸው። ከዛ ጨለመ... የእንስሳት ድምፆችን እና ጨለማን መፍራት ጀመርኩኝ . ወንድሞቼን በጭራሽ ላገኛቸው አልቻልኩም ። እየተሳበኩ ስሄድ እናቴን ሞታ አገኘኋት። እሷም ሸሃዳ ይዛ ነበር ..አባያዋም እንደ ከፈን ተጠቅልሎባት፣ጣቷ ብቻ ከሷ ላይ ይታይ ነበር ፣እናም ሸሃዳ ይዛለች...የተሸፋፈነቺው እንኳን አልወደቀም።በእቅፏ ላይ ሆኜ እሷ እንድትሰማኝ ለማድረግ ሞከርኩ.. ግን ምንም ውጤት የለም .. አባቴ ጋር ደረስኩ፣ እሱ አሁንም በህይወት አለ እና እየደማ ነበር። እኔ ህይወትሽን አደራ እልሻለሁ .. እዚህ ለረጅም ጊዜ እንዳትቆዪ.. ወደ ተራራው ውጪ እና የሚረዳሽን ሰው ጥሪ.. ወንድሞችሽን እና እናትሽን እርጂያቸው አለኝ. ያን ጊዜ የውሻዎችን ድምፅ ፈራሁ፤ በዚህ በድቅድቅ ጨለማ አላህ በዙሪያዬ አቆየክ ብዬ በአባቴ እቅፍ ላይ ቆየሁ.. ደም እየደማሁ ነው እናም መንቀሳቀስ እንደማልችል ነገርኩት እና ከአንተ ጋር እቆያለሁ አልኩት.. በዚያን ጊዜ ደረቱ ላይ ወሰደኝ.. በገባው ቃል መሰረት እንድሆን መከረኝ .. ዱኣ ያደርግልኝም ነበር.. እሱም እየመከረኝ እያለ በዛው ህይወቱ አለፈች.. እራሴን ስቼ እስከምወድቅ ድረስ ብቻዬን እያለቀስኩ ዱኣ እያደረኩኝ ቆየሁ..ራሴን አልተሰማኝም, በጣም ደም ስለፈሰሰኝ እራሴን ሳትኩኝ.. በ ዓይነ ህሊናህ አስበው እስኪ በሁለተኛው ቀን እስከ አስር ድረስ ማንም አላየንም ነበር አንድ ሙሉ ቀን ማንም አላየንም።ከዛ ቡሃላ አንድ እረኛ አገኘን.. ለአከባቢ ጠባቂዎች አሳወቀ..ከዛ የመከላከያ ቡድኑ ከአውሮፕላን እና ከመኪና ጋር መጡ.. በቡድን ተጎተትን.. ከዚያ በኋላ እስከ አምስት ወር ድረስ ከኮማ አልነቃሁም ነበር። እና የሆነውን ነገር ገባኝ.. እንደ ቅዠትና ህልም ይመስል ነበር.. ሁለት አመት በካናዳ በህክምና ውስጥ አሳለፍኩ። በጭንቅላት፣ አንገት፣ ጀርባ፣ ዳሌ፣ ብዙ ቦታዎች ላይ ከባድ ስብራት ነበረብኝ። በደም መፍሰስ ምክንያት እናት የመሆንን ፀጋ አጣሁ። በዶክተሮቹ በኩል ብዙ ሙከራዎች ቢደረጉም አልተሳካም. ስለዚህ ምርጫው ወይ ሕይወቴ ማጣት ነበር...ወይ ደግሞ የልጆችን የማግኘት በረከት ሊያሳጣኝ የሚችለው ቀዶ ጥገና... ምርጫው ከባድ ነበር ... እና ብዙ አሰቃየኝ ... አሁን ደህና ነኝ እና ጤነኛ ነኝ (አልሃምዱሊላህ) አላህ ይመስገን። ያ ሸይኽ እኔም ሆን ብዬ ታሪኬን የነገርኳቹህ በጣም የምትወዱትንና የምትሳሱለትን ሰው ያጣቹት እናንተ ብቻ እንዳልሆናችሁ እንድታውቁ ነው። እና አለም ከነሱ አንዳቸውን በማጣት እንደማያበቃ...ነገር ግን የ ኢማን መሟለት ምንክያት በሆነው በአላህ ቅድመ ውሳኔ (በቀደር) መታገስ አለብን። እና አላህ ይመስገን እነሆ ወደ ስራዬ ተመልሻለው ..ወደ ሪያድ ተዘዋውሬ ከአዲሱ ህይወቴ ጋር መኖር እና መኗኗር ጀምሪያለው.... ስለ ሁሉም ነገር አላህ ይመስገን.. ሳልነግራችሁ ረሳሁት...የእህቶቼ ሰርግ ሁለት ሳምንት ቀርቶት ነበር...ከሰርጋቸው በፊት ዑምራ ለማድረግ ፈልገን ነበር። እስከ አሁን ድረስ የሰርግ ልብሳቸው ከእኔ ጋር ነው እኔም እስክሞት ድረስ እጠብቃቸዋለሁ ። 💡 💡 መልእክት ፡ በዙሪያቸው ካለው ነገር ሁሉ ምኞታቸው ለዘገየባቸው ሁሉ ጥቂት አመታት መታገስ ምንም ችግር የለውም በዩሱፍ (ዓለይሂ ሰላት ወሰላም) ላይ የሆነው ነገር ሁሉ ታጋሽ በሆኑት ላይ ሁሉ ይፈጠራል ። አላህ የወሰደው ለጥበብ ነው፣ ያስቀረው ለምህረት ነው ... በእርግጥም የሚሰጠን ነገር መጠኑ ሊጨምር ሲል ምኞቶቻችን ይቆያሉ ። ስለዚህ በ አላህ ላይ ያላቹን እምነት አስተካክሉ። ሶስት ዱኣዎችን ሱጁድ ላይ ስትሆን ማድረግን አትርሳ፡- ጌታዬ ሆይ የ ኻቲማን ማማር እለምንሃለሁ ጌታዬ ሆይ ከሞት በፊት ቅን ንስሐን ስጠኝ አንተ ልቦችን የምትገለባብጥ የሆን አምላኬ ሆይ ልቤን ዲንህ ላይ አፅናት። ይህን መልእክት እንኳን ሼር ለማድረግ ካሰብክ፤ ንያህን በመልካም ነገር አሳምረው ፤ ምናልባት አላህ ከቅርቢቱና ከኋለኛይቱ ዓለም ጭንቀት ሊገላግልህ ይችላል። . አልሀምዱሊላህ Share..➤https://t.me/+N72Awjj_X75kM2Y0
ቀኑ ማክሰኞ ቀን ነበር በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር.. "አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣ አንድ ወጣትን ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየው፡፡ ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል አካላቱ ተቆርጠዋል፣ እግሩም ጭምር ተቆርጧል እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል "መሞት አልፈልግም፣በጣም ፈርቻለሁ ፣ እሳት ነው ምገባው እኮ" ይለዋል እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔኮ አልሰግድም ነበር ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም፣ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል ሰወችም ተሰበሰቡ፣ እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ፣ በጣምም ፈርቻለሁ፡፡ በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ ጩኸቱም _ ቀጠለ ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ፡፡ ሊያድኑት ግን አልቻሉም አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሀዳ በል ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም አላሁ አክበር፣ በጣም ፈርቶ ነበር፣ ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ ግን....ግን ሸሀዳውን ማለት አልቻለም ነበር ከዚያም አልተንቀሳቀሰም፣ ሰውነቱም ደርቆ ቀረ ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት፡፡ ዘጋቢውም ይለናል፦" በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው፣ ሰላታችሁን ግን ጠብቁ፣ በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡ የመጨረሻ ቀናችሁ መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም እኔም ከዚህ ክስተት ቡሃላ መተኛት አልቻልኩም እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...” እሰግዳለሁ፣ ወላሂ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ መሞት ግን አልፈልግም..….”😭😭 ያ አላህ መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን @rim_han
🌸 اللهم صلی علی محمد عدد ما ذکره الذاکرون وغفل عن ذکره الغافلون.
ወረቢ ሙሐመድ … ዱንያ ላይ እንደ "ሙሐመድ" የምወደው ስም የለም ። ስሜ ባለመሆኑ ግን በጣም ደስ ይለኛል ። ከንቱነቴ ለስሙ አይመጥንም ፣ ረሱል (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በተሰየሙበት ስም ተሰይሜ እኔን ብሆን ፤ ዝቅ ያደረኳቸው ነው የሚመስለኝ ፣ የሆነ የሰደብኳቸውና ያሰደብኳቸው አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ ። "ሙሐመድ" ከሚለው ስያሜ ጋር ተያይዞ የሚነገሩ ወርቃማ ታሪኮችን ሁሉ እንደማደበዝዛቸው እርግጠኛ ነበርኩ ። እናም ሙሐመዶች … እንደስማቹ መሆን ባትችሉም ፤ የስሙን ባለቤት ለመምሰልና ለመከተል ሞክሩ ። ያ ካልሆነ ግን ቢያንስ ስያሜውን ላለማርከስና ላለማቅለል ተጠንቀቁ ። ሙሐመድዬ… ሰሉ አለን ነቢይ🤍የአላህ ሰላትና ሰላም በእርስዎ ላይ ይሁን! 🖤 JOIN US: ❯❯ 𝓗𝓪𝓵𝓪𝓵 𝓕𝓴𝓻 ™
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህን ውሳኔ ምንም አይመልሰውም (ዱዓእ) ቢሆን እንጂ ፤ ዕድሜም አይጨምርም 'በመልካም' ስራ ቢሆንጂ። ☘ቲርሚዚ ዘግበውታል (2139)
ረሱል {ﷺ} እንዲህ ብለዋል "ከእኔ በፊት ለነበሩት ኡመቶች (ሕዝቦች) ከተሰጣቸው ዕድሜ አንጻር የእናንተ ዕድሜ (በዚህች ዓለም የምትቆዩበት) ጊዜ (ከአስር እስከ መግሪብ) ባለው ጊዜ መካከል እንዳለው ያህል ነው። ☘️ቡኻሪ ዘግበውታል (558)
➡ ️እውቀትን መደብቅ ያለው አደጋ❗️ ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿من سُئِلَ عن علمٍ فكتمَه، ألجمَه اللهُ يومَ القيامةِ بلجامٍ من نارٍ﴾ “ስለሆነ እውቀት ተጠይቆ የደበቀው ሰው አሸናፊውና የላቀው አላህ በቂያማ ቀን በእሳት ልጎም ይለጉመዋል።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 6284 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ✔️ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ ✈️Telegeram 📞 Whatsup 👤Facebook 📸Instagram 💬X 🎥Youtube 🎵Tik tok
ከጀነት ታግጃለሁ••• ኢብኑል ጀዘሪ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፡- «ሐሳን ኢብኑ አቢ ሱፍያን በሞተ ጊዜ በህልም ታየና፤ "አላህ ምን ፈረደብህ (ምን አደረገህ)?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ 'ተውሼ ለባለቤቷ ባልመለስኳት አንዲት መርፌ ምክንያት ከጀነት ታግጃለሁ (እንዳልገባ ተከልክያለሁ)።'» [አዝ-ዘህር አል-ፋኢሕ፡ 69]ከጀነት ታግጃለሁ••• ኢብኑል ጀዘሪ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፡- «ሐሳን ኢብኑ አቢ ሱፍያን በሞተ ጊዜ በህልም ታየና፤ "አላህ ምን ፈረደብህ (ምን አደረገህ)?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ 'ተውሼ ለባለቤቷ ባልመለስኳት አንዲት መርፌ ምክንያት ከጀነት ታግጃለሁ (እንዳልገባ ተከልክያለሁ)።'» [አዝ-ዘህር አል-ፋኢሕ፡ 69]
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿التَّثاؤُبُ مِنَ الشَّيْطانِ، فإذا تَثاءَبَ أحَدُكُمْ فَلْيَرُدَّهُ ما اسْتَطاعَ، فإنَّ أحَدَكُمْ إذا قالَ: ها، ضَحِكَ الشَّيْطانُ.﴾ “ማዛጋት ከሸይጣን ነው። አንዳችሁ በሚያዛጋችሁ ግዜ በቻለው መጠን ይከላከለው። አንዳችሁ በምታዛጉ ግዜ ‘ሐዓ’ በምትሉ ግዜ ሸይጣን ይስቅባችኋል።” 📚 ቡኻሪ (3289) ሙስሊም (2994) ዘግበውታል
⛔️ ከልክለዋል! ከጃቢር ቢን አብደላህ (⏩️) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦ ﴿نَهى النَّبيُّ 🤍 أن تُباعَ الثَّمَرةُ حتّى تُشَقِّحَ، فقيلَ: وما تُشَقِّحُ؟ قال: تَحمارُّ وتَصفارُّ ويُؤكَلُ منها﴾ “ነቢዩ (➡️) ፍራፍሬዎችን ሳያፈሩ መሸጥ ከልክለዋል። ‘የማፍራቱ ምልክት ምንድነው?’ ሲባሉ። እስኪቀላና ቢጫ እስኪሆን እንዲሁም ለምግብነት ዝግጁ ሲሆን በማለት መለሱ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 2196 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ✔️ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ ✈️Telegeram 📞 Whatsup 👤Facebook 📸Instagram 💬X 🎥Youtube 🎵Tik tok
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لا تغضبْ، ولَكَ الجنَّةُ﴾ “አትቆጣ ጀነት ይኖርሃል።” 📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 7374
سئل الشيخ ابن عثيمين رحمه الله ما الحكمة من صيام ست من شوال؟ فأجاب: الحكمة من صيام ست من شوال هي الحكمة في بقية النوافل التي شرعها الله لعباده لتكمل بها الفرائض، فصيام ستة أيام من شوال بمنزلة الراتبة للصلاة التي تكون بعدها ليكمل بها ما حصل من نقص في الفريضة، ومن حكمة الله تعالى أنه جعل للفرائض سُننا تكمل بها وترقع بها، فصيام ستة أيام من شوال فيه هذه الفائدة العظيمة. (CDفتاوى نور على الدرب النصية).
видео или голосовое, без подписи
ከሸዋል ፆምና ከረመዳን ካሉብን ቀዳዎች ማስቀደም ያለብን የቱን ነው???
видео или голосовое, без подписи
شفعنا (صلی الله علیه وسلم ) pinned a video
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи