አንድ መንገድ.
Статистика“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 “Jesus saith unto him, I am the way, the truth, and the life: no man cometh unto the Father, but by me.” — John 14፥6 (KJV)
- Последний пост
- 10 мар.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 38
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ኢዮብ በሕይወቱ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ጊዜ ውስጥ ነበር። ብዙ መከራና ሥቃይ ቢያጋጥመውም የሚሆነው ሁሉ ለምን እንደሆነ ባይረዳም፣ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ግን አልተመለሰም፤ በመከራ ወቅት እግዚአብሔርን የሚጠበቀው በፀሎት ነው። ፀሎት ልብህን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ መንገድ ነው፤ ሲትደክም እርሱ ያጠነክርሀል፣ ሲጨንቅህ ያጽናናሀል። አሁን የምታልፍብት ሁኔታ ቢከብድም እግዚአብሔርን በፀሎት መጠበቅ በመጽናት እንድትኖር ያደርግሀል። ኢዮብ 23:12 ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም፤ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ። Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
Day 5፡ መጽሐፍ ቅዱሴን እወደዋለሁ ሰላምን ስለሰጠኝ! መጽሐፍ ቅዱሴን በመውደዴ ታላቅ ሰላም አለኝ፤ የእግዚአብሔርን ቃል መውደዴ እና ማንበቤ ለነብሴ መረጋጋትን ሰጥቶኛል። መጽሐፍ ቅዱሴን ማንበቤ እምነትቴን አጠንክሮታል፤ ልቤንም አረጋግቶታል። መጽሐፍ ቅዱሴን በመውደዴ እና በማንበቤ ከሁኔታዎች በላይ የሆነ ሰላም ውስጥ አርፌአለሁ። የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን መውደድ ማንበብ አእምሮዎን የሚያልፍ እና ልብን የሚጠብቅ ሰላም ይሰጦታልና ይሄን ህያው ቃል እንዲያነቡ እንጋብዞታለን። መዝሙር 119:165 ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም። #መጽሐፍ_ቅዱሴን_እወደዋለሁ!
видео или голосовое, без подписи
#የስሕተት_ትምህርት_እና_ልምምድ.... የክርስቶስን ወንጌል ሰባኪዎች እንዳሉ ሁሉ ልዩ ወንጌል ሰባኪዎችም አሉ፤ እውነተኛ ነቢያት እንዳሉ ሁሉ ሐሰተኛ ነቢያትም አሉ፤ እውነተኛ አስተማሪዎች እንዳሉ ሁሉ ሐሰተኛ አስተማሪዎችም አሉ። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ፈተና ከሆኑት መካከል የስሕተት ትምህርትና እንግዳ ልምምዶች መሆናቸው ተደጋግሞ በመነገር ላይ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው። ባለፉት ዓመታት የኑፋቄ ትምህርቶችና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት የጎደላቸው ልምምዶች የአብያተ ከርስቲያናት ደጆችን ሲያንኳኩ ከርመዋል። በአንዳንድ ቦታዎች ላይም ተሳከቶላቸው ደጅ አስከፍተው ወደ ውስጥ መዝለቅ ችለው ነበር። ይህም እንኳ ሆኖ ከሞላ ጎደል በአብያተ ከርስቲያናት መካከል ተመሳሳይ የወንጌል መልእከት ይተላለፍ ነበር ማለት ይቻላል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን፣ በተለይም ከኤሌክትሮኒክ ሚዲያው መምጣት ጋር ተያይዞ የስሕተት ትምህርቶቹ የቤተ ክርስቲያንን ደጅ ከማንኳኳት ይልቅ በቴክኖሎጂው ድጋፍ በቀጥታ ወደ አማኞች ቤት መዝለቅ ችለዋል። በዚህም አማኞች የትም ሳይሄዱ፣ ቤታቸው ቁጭ ብለው ከትምህርቶቹ ጋር የመተዋወቅ "ዕድሉ” ተፈጠረላቸው። እንግዲህ 'የአንድ ክርስቲያናዊ ሚዲያ ጎላፊነት የት ድረስ ነው? የሚለው ጥያቄ የሚነሣው እዚህ ላይ ነው። ገንዘብ ለከፈለ ሁሉ ሽፋን የሚሰጡ የሚዲያ "ባለቤቶች ባሉበት ሁኔታ ቤተ ከርስቲያንን ለማነጽ የሚሆን ጤነኛ ትምህርት በወጥነት ይተላለፋል ማለት እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል። በኤሌክቶሮኒክ ሚዲያው፤ በተለይም በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ሥርጭቶች "የነጻ ገበያ መርሕን” የሚከተሉ ይመስል ራሳቸውን ያለ ገደብ ለሁሉ ከፍት አድርገው ማቅረባቸው ጎላፊነት የጎደላቸው ለመሆኑ ማሳያ ነው። ከዚያም በላይ ጉዳዩን ገፋ አድርገን የተመለከትነው እንደ ሆነ፤ ከቶውንስ ግለ ሰቦቹና የሚመሩት ድርጅት ጤነኛ የሆነ አስተምህሯዊ አቋም አላቸው ወይ? ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። የእምነት እንቅስቃሴ የወለዳቸውና ለመጽሐፍ ቅዱስ እንግዳ የሆኑ ትምህርቶች ያለ ገደብ የሚያስተናግዱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና የፕሬስ ውጤቶች አየሩን ተቆጣጥረውታል። በመጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ሥልጣናዊነት ላይ ታምኖ እግዚአብሔርን ለመምሰል ራሱን ለሚያስለምድ አማኝ ማኅበረ ሰብ፣ 'ኀጢአት የሚባል ነገር የለም፤ በሥጋህ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ' የሚል ጥንት መጣሽ እኩይ ትምህርት (ኖስቲስዝም) ሕዝበ ከርስቲያኑን መረን ለማውጣት እየታገለ ነው፡፡ አንድ የከርስቲያን ሚዲያ ነኝ የሚል አካል፣ ከፉውንም ደጉንም ትምህርት እንደ ብፌ በአንድ ጠረጴዛ ላይ ዘርግቶ 'የፈለጋችሁትን ምረጡና ብሉ' ማለት ፈጽሞ አይገባውም፤ ባለ ዐደራነትንም መጣል ነው። ምንም እንኳ በወንጌላውያን ከርስትና እምነት (በተለይም በኢትዮጵያ የወንጌላውያን ኣብያተ ከርስቲያናት) መካከል በተወሰኑ ጕዳዮች ላይ በአመለካከት ደረጃ ያሉ መለስተኛ ልዩነቶችን በልበ ሰፊነት መቀባበሉ ተገቢ ቢሆንም፣ አስተምህሯዊ መናጋቶችን ለሚያመጡ ትምህርቶች የሚኖረን "ታጋሽነት” ግን ገደብ ሊኖረው ይገባል፤ አልያ ልናርመው ወይም ልንመልሰው ወደ ማንችለው ጥፋት መሄዳችን አይቀሬ ይሆናል። "ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰል እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ልቡና ተበላሽቶ ለክርስቶስ ካላችሁ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትወሰዱ እሠጋለሁ።" (2ቆሮ.1113) “ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤” — ራእይ 2፥20 ምንጭ፦ ከተሃድሶ ጥሪ ✍️24//62018 ተሙ®
ሸክሜን ❤ዳዊት ጌታቸው 🙏
#የመስቀሉ_ማእከልነት❤ ✍️መስቀል የሰውን ስቃይ እግዚአብሔር አምላከ የተካፈለበት፣ "አንተ የሥጋ ዐይን አለህን?” የሚለው የኢዮብ ጥያቄ ፍንትው ያለ ምላሽ ያገኘበት፤ ስቃይ ለእግዚአብሔር ባዕድ አለመሆኑ የተመሰከረበት፣ 'የእግዚአብሔር ፍቅር ስፋቱ፣ ከፍታው፣ ጥልቀቱ ከመታወቅ ያለፈ ነው' የሚለው በገሃድ የተገለጠበት ታሪካዊ እውነታ ነው። የመለኮት ጥምር ባሕርያት በአንድ ሁኔታ የተገለጠበት፣ ማለትም ምሕረቱና ፍርዱ፣ ሰው አፍቃሪነቱ እና ጎጢአት ጠልነቱ የታየበት፣ ጥበቡ የተንጸባረቀበት፣ ሞትና ሕይወት የተገናኙበት፣ ሽንፈትና ድል የተራከቡበት፣ ውርደትና ክብር፣ መፍረስና መታጎጽ የተተካኩብት ነው። ✍️ትላንት እና ነገ የተሸረቡበት፣ ምድርና ሰማይ የተጋጠሙበት፣ ሰማይ የተከፈተበት፣ "ምድር" ወደ "ሰማይ የወጣበት"፣ "ሰማይ” ወደ "ምድር" የወረደበት፣ የጥል ግድግዳ የፈረሰበት የአዲስ ኪዳን መካከለኛ የሆነው የክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል ነው። ✍️ከአምልኮተ ባዕድ ወደ አምልኮተ እግዚአበሔር ዘወር የሚባልበት፣ ከአምላክ ጠልነት ወደ አምላክ ቤተ ሰብነት፣ ከጨለማው አገዛዝ ወደ መንግሥት እግዚአብሔር፣ ወደ ሰማያዊ ዜግነት መፍለስ የተቻለበት ነው። ለከህነት፣ ለእግዚአበሔር መንግሥት ዜግነትና ለእግዚአብሔር ልጅነት የበቃንበት ከስተት ነው። ✍️በመስቀሉ ላይ የፈሰሰው ደም የኀጢአትና የበደል ስርየት መቀበያ፣ ጽድቅን መታደያ፣ ከሕግ ርግማንና ከከንቱ ኑሮ መዋጃ፣ በጎጢአት ጉልበት፣ በሞት ኀይልና በጨለማው ሥርዐት ላይ ድል መጎናጸፊያ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቲያ ነው። መስቀሉ የወንጌል እምብርት ነው፤ የመስቀሎም መንገድ የኑሯችን መርሕና ዘይቤ ነው፤ ማለትም በመስጠት ማግኘት የሚስተናገድበት፣ ከሁሉ ኋላ በመሆን ፊተኛ የሚኮንበት፣ በድካም ብርታት የሚታፈስበት፣ በውርደት ክብር የሚለበስበት ጣይ አንሽ (paradoxical) ቅኝት ነው። ❤ "መቼም አይሁድ ታምራዊ ምልክትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን... 1ቆሮ. 1:22-23 ❤ "እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ ለመሆኑ ማን መተት አደረገባችሁ? ኢየሱስ ከርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በፊት ለፊታችሁ በግልጥ ተሥሎ ነበር... ገላ. 3፥1 ❤“እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” ዕብራውያን 2፥14-15 ❤ራእይ 5፥9-12 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥ በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ። #ከተሐድሶ_ጥሪ መጽሐፍ የተወሰደ ✍️1/6/2018 ተሙ መልካም ምሽት ይላችኋል ❤🙌
ክርስቶስ ኢየሱስ ሁልጊዜም ለልጆቹ ቅርብ ነው። በጎቼ ብሎም የሚጠራው የሱ የሆኑትን ነው። ልጆቹ የሆኑትም ድምፁን ይሰማሉ። ደግሞም ይከተሉታል። የጌታ የኢየሱስ፣ ድምፅ ለመስማት፤ እርሱ በሚመራህም መንገድ ለመጏዝ ትፈልጋለህ? ዮሐንስ 10:27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
የአማኞች አንድነት የሚናጋባቸው አያሌ ምክንያቶች ቢኖሩም ዐበይት ከሆኑት መካከል እነዚህ ይገኙባቸዋል፡፡ አንዱ የአንድነት እንቅፋት ከልክ ያለፈ ግለኝነት ነው፡፡ ሁልጊዜ ስለ ራስ የግል ስጦታ፣ ስለ እኔ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ እኛ ቡድን፣ ስለ እኛ ብሔር፣ ስለ እኛ ራእይ የምናስብ የምናወራ ከሆነ አየሩ ይታፈናል፡፡ ባልንጀሮቻችንን በብረት አጥር ውስጥ እናስራቸዋለን፡፡ አንድነት የሚፋፋው የሌሎችን ስጦታ፣ የሌሎች ቤተ ክርስቲያን፣ የሌሎች ሰዎችን ብሔር የሌሎች ራእይ ለማወቅና ለማክበር ስንጥር ለማበልጸግም ስንሰናዳ ነው፡፡ “እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቊጠር" ይላል ሐዋርያው ጳውሎስ፡፡ ዘረኝነት፣ የብሔርና የቋንቋ ትምክህት፣ ያለአግባብ የተኮፈሰ የራስ ማንነት ወይም እጅጉን የደቀቀ የራስ ግምት እውነተኛ አንድነት እንዳይኖረን እንቅፋት ይሆናሉ። የክርስቲያን ማንነት መሠረት የዘር፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የትምህርት፣ የኑሮ ደረጃ መደብ ሳይሆን በመለኮት ጸጋ ምክንያት ያገኘነው የእግዚአብሔር ልጅነት ነው፡፡ ከዚህ የተደላደለ ማንነት ላይ ስንቆም የተቀሩትን መለያዎች ሁሉ አነስተኛ እናደርጋለን፤ እኛም በሰማያዊ የክብርመንፈስ ውስጥ እንሆናለን። ያን ጊዜ ሁሉን ለማቀፍ፣ አብሮም ለመብረር የሚችሉ ክንፎች እናበጃለን። አንድነታችንን የሚያናጋ ሌላው በሽታ ከሌሎች በላይ ለመሆን ያለን ጠማማ ጉጉት፣ ከፍተኛውን ወንበር ለመያዝ የምናደርገው ሽኩቻ የሚያስነሣው የጥላቻና የፉክክር አቧራ ነው፡፡ “ጠብና ጦር ከወዴት ይመጣሉ…” (ያዕ. 4፥1)። #ተቀላቀሉን🙏
#ለተወደዱ_ዜማ_መሪዎች! የመድረክ ዜማ መሪዎች መድረክ ላይ ማየትም ሆነ መስማት የምንፈልገው የእናንተን ዜማ የመምራት ብቃታችሁን፤ የድምጻችሁን ቅላጼ ሳይሆን መዝሙሩን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመረዳትና በማስተዋል እንድታዘምሩ ይሁን። ደግሞ እያንዳንዱ የምታዘምሩት መዝሙሮች አዝማች ብቻ ሳይሆን ቁጥርም ስላላቸው ከነቁጥሩ እንታዘምሩ፤ የያዝነው የመዝሙር ዳሰሳ ስላልሆነ። ስቀጥል ደግሞ እንዲህ አድርጉ ወዲህ ግቡ ከወዲህ ውጡ እያላችሁ ትዕዛዝ አታብዙ እባካችሁን ስቀጣጥል እናንተ ዜማ መሪ ናችሁ እንጂ ቃል ሰባኪዎች አይደላችሁምና በየመሐሉ እያስቆማችሁ ባትሰብኩን ይመረጣል። ደግሞ ሰዎች ካልዘለሉ እና ካልጮሁ ዜማ የመራችሁ የማይመስላችሁ እባካችሁን ከተግባራችሁ ታቀቡ፤ የምዘመረው ለጌታ እንጂ ለእናንተ ስላልሆነ። ሳጠቃልለው ለማስተላለፍ የፈለጋችሁ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ ለመረጣችሁት ርዕስ ግብአት ወይንም መልዕክት ተመሳሳይነት ያላቸውን አንድ ላይ አድርጋችሁ እንድትዘጋጁ ይሁን። #ከተሳሳትኩ_አርሙኝ🤲 መልካም ምሽት ይሁንላችሁ 19/05/2018 ከተሙ✌️
видео или голосовое, без подписи
ተስፋ በሚያስቆርጥ በዚህ አለም ስትኖር፣ ብዙ ድካም እና ሃዘን ደግሞም እረፍት የሚነሱ ነገሮች ይከብቡህ ይሆናል። አቅም ያጣህ እና የደከምክ በሚመስልህ ጊዜ ሁሉ አይኖችህን ወደ ተስፋህ አምላክ ወደ እግዚያብሄር አንሳ! በድካምህ ሃይልን፣ ባስጨነቀህም ነገር ፈንታ ሰላምን ይሰጥሃል። በእርሱ ለሚታመኑ ሃይል ከመንፈስ ቅዱስ እንጂ ከዚህ አለም ስላይደለ የሚቀጥል እና የሚበዛ ተስፋ ለእነርሱ አለ። በአምላክህ በእግዚያብሄርም በማመንህ ከእርሱ የሆነ ደስታ ሰላምም ሁሉ በቀኖችህ ሁሉ አይጎድልብህም። ስለዚህ እይኖችህን ከግዜያዊ ደስታ እና እርካታ ምንጮች ላይ አንሳ። ሁሉን ቻዩ አምላክ የዘላለም ደስታህ እንደሚሆንም ካመንክ በርግጥም ላንተ ፀደይ እየመጣ ነው። የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 15:13 Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
❝ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሰረገላ ላይ አስቀመጠችኝ።❞🙏 —መኃልየ. 6: 12
“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።” — ያዕቆብ 1፥16
ሕፃኑ መድኅን! ዓለም ከፍ ባለ ድቅድቅ ጨለማ ተሞልታ ነበር፤ ሁሉ ነገር ዝምጭጭ ብሏል። ከአራት መቶ በላይ ለሚሆኑ አመታት ከዚህቀደም የተለመዱት ድምፆች ሁሉ ቆመዋል። ከሰማይ ክፉምመልካምም መልእክት ተሰምቶ አያውቅም። ብቻ ሁሉእንዳመጣለት፣ እንደመሰለው ይመላለስ ነበር። መንፈሳዊሥርዓቶችም ቢሆኑ እንዲያው ለወጉ ልማዱን ተከትሎይከወናሉ እንጂ፣ ይህ ነው የሚባል መንፈሳዊ እርካታአልነበረም። በዚህ መካከል ተስፋ ቢስነት፣ የደኅንነት ምሥራች እጦት፣ የመንፈሳዊ ዓለም ዳፈና በሁሉ ስፍራ ገንኖ ነበር። ሌላኛውመደበኛ ሕይወት ግን እንዳለ ቀጥሏል። በዚህ መሐል ታዲያ፣ምድር በታሪክ የማይደገም አንድ ድንቅ ክስተት አስተናገደች። በአንዱ ስፍራ እረኞች በሌሊት መንጋቸውን እየጠበቁ ነበር። በብርሃን የተንቆጠቆጠ መልአክም ድንገት በመሐከላቸውተገለጠ። ነገሩ ያልተለመደ እና አስፈሪ ስለነበር፤ በታላቅ ፍርሀትተሞሉ። ክስተቱ ለምድር ብቻ ሳይሆን ለሰማይ ሰራዊቶች ሁሉ የደስታምክንያት ነበር፤ በመሆኑም ለሰዎች በሆነው በዚህ ምሥራች፣በሕፃኑ መድኅን ሰበብ ታላቅ ዝማሬ ሆነ። ሕፃኑ መድኅን የዓለሙ አዳኝ ሆኖ ከተገለጠ እንኾ ሁለት ሺህአመት አለፈ። የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ለዓለም ተስፋ የኾነውእውነተኛው ብርሃን ዛሬም በትኩስ ጉልበት ያድናል። ዛሬምይኽ የምሥራች ትኩስ ነው። ዛሬም ተስፋ ላጡ፣ በማን ያድነናልጭንቅ ውስጥ ላሉ፣ በድቅድቅ ጨለማ ለተዋጡ የዛሬ ሁለትሺህ አመት የተወለደው ክርስቶስ ጌታ እውነተኛ ተስፋ፣ ብቸኛአዳኝ፣ የማይደበዝዝ ብርሃን ነው። ወደ እርሱ የሚመጡትንፈጽሞ ያድናቸዋል። ዛሬም ወደእዚህ እውነተኛና ብቸኛ ተስፋኑ ብለን ጥሪ እናስተላልፋለን!! #ደስታ_ለዓለም #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
ተወለደልን ተስፋዬ ጋቢሶ - የልደት ዝማሬ
የዘላለም አባት የእግዚአብሔር አባትነት በጊዜ የተገደበ አይደለም። የስጋ አባት አባትንቱን የሚጀምረው በሆነ ወቅት ላይ ነው፤ የእግዚአብሔር አባትነት ግን ከዘላለም ነው። እርሱ የሕይወት ሁሉ ምንጭ፣ የሕዝቡ ታማኝ እረኛ ነው። የእግዚአብሔር የአባትነት ፍቅሩ ከእርሱ የራቀውን የሰው ልጅ ወደራሱ ለመመለስ ልጁን እስከመስጠት አድርሶታል። በቤተልሔም ከድንግል ማሪያም በተወለደው በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ መለኮታዊ አባትነት ለሰው ልጅ ሆኗል። ደስታ ለዓለም! ኢየሱስ ተወልዷል! #ደስታ_ለዓለም #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
ኃያል አምላክ! ኢሳይያስ የሚመጣው መሲህ ኃያል አምላክ ተብሎ እንደሚጠራ የተንበየለት፣ በቤተልሔም ከድንግል ማሪያም የተወለደው እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው፣ የምድር ነገስታት ጌታን ሚጠብቁት በሠራዊት ታጅቦ፣ በሀይል እና በማስፈራት ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር ኃይል የመጣው በግርግም ነው። ኢየሱስ ኃያል አምላክ ስለሆነ፣ በሕይወታችን፣ በእርሱ መተማመን እድል አለን። የሰማይ ኃያል እምላክ ወደ ምድር የመጣው በኃይል ለመግዛት ሳይሆን በፍቅር ለማዳን ነው። ደስታ ለዓለም! ኃያል አምላክ ተወልዷል! ኢሳይያስ 9:6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልናብ፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። #ደስታ_ለዓለም #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
በፍርሃት በሰፈነበት ቦታ፣ በለሊት፣ ከሰማይ የሆነ የምስራች! ሰማይ ለህዝብ ሁሉ የሚሆን ደስታን ሲያውጅ ፍርሃት ጠፍቷል ኢየሱስ ተወልዷል። #ቅዱስ_ሌሊት #ፍርሃት_የለሽ ተስፋ #ለህዝብ_ሁሉ #ደስታ_ለዓለም #tesfa #hope ሉቃስ 2:10 መልአኩም እንዲህ አላቸው፡— “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
ድንቅ መካር ይህ ድንቅ መካር ምክርን ብቻ የሚሰጥ አይደለም፤ ምክሩ እውነትን የሚያጸና፣ ልብን የሚያበራ፣ ቃሉ ሕይወትንና መዳንን የሚያመጣ ነው። ምክሩ ጥበብ የተሞላበት፣ መንገድን የሚያሳይ፣ ተስፋን የሚያደርግ የዘላለም ምክር ነው። ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረው የእስራኤል ቤዛ፣ የነቢያት ትንቢት ፍጻሜ፣ ይህ ድንቅ መካር በሰው ሥጋ ተገልጧል። ይህ ድንቅመካር በያዕቆብ ቤት ላይ ለዘላለም የሚነግሥ፣ የተስፋው የዳዊት ልጅ ነው። የይሁዳ ነገድ አንበሳ፣ የዳዊት ሥርና ዘር፣ የዳዊት ጌታ ሆኖ የዳዊት ልጅ ተብሎ የተጠራ ነው። ከድንግል የተወለደ፣ በመንፈስ ቅዱስ የተፀነሰ፣ ልደቱ በመላእክት የተነገረ፣ በብዙ የሰማይ ሠራዊት “ክብር ለእግዚአብሔር” ተብሎ የተዘመረለት ነው። ጌታ ሆኖ ግን በግርግም የተኛ፣ ኃይለኛ ሆኖ ግን ትሑትነትን የለበሰ፣ በእርሱ የእግዚአብሔር ጥበብ የተገለጠ፣ ድንቅ መካር ነው። ምክሩ ማለቂያ የሌለው፣ ፍቅሩ የማይወሰን፣ መምጣቱ ለሰማይና ለምድር ታላቅ ደስታን ያመጣ ነው። ነገሥታት በፊቱ የተንቀጠቀጡለት፣ ጠቢባን የሰገዱለት፣ ድሆች ተስፋን ያገኙበት፣ ዓለም ሁሉ መዳንን የቀበለበት ነው። ለሁሉም ድንቅ መካር የሆነው፣ የሕይወት ቃል የሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል። ደስታ ለዓለም! ደስታ ለዓለም! #ደስታ_ለዓለም #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” — ማቴዎስ 7፥15 ✍️ይህን ክፍል በደንብ ስንመለከት ሁለት የተለያየ ባህርይ ያላቸው በግ እና ተኩላ የተባሉ ፍጥረት እናገኛለን፤ እነዚህን ፍጥረት የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገር አሉ። ያ ማለት ግን ባህሪያቸው አንድ አይነት ነው ማለት አይደለም፤ ✍️ #የበግ_ለምድ_ለብሰው ማለት ማንነታቸው ያይደለ ነገር ግን የሌሎችን ማንነት ለጊዜያዊነት እየተጠቀሙ የሚኖሩ፤ ለጥቅም ብለው ማንነታቸውን ደብቀው ለመመላለስ የሌሎችን ማንነት ይጋራሉ በዚህም በዘመናችን እንዲህ አይነቶች አሉ #ሳይሆኑ ነገር ግን #መስለው የሚኖሩ #እንደ እስስት የሁሉንም ማንነት የራስ እያደረጉ ለጥቅማቸው ራሳቸውን መስለው የሚኖሩ አሉ So #ተጠንቀቁ ይለናል። #እንጠንቀቅ! ✍️ #በውስጣቸው_ግን_ግን_ነጣቂ_ተኩላዎች በዚህ በደንብ ማንነታቸውን መረዳት እንችላለን ምንም ያህል #መስለው ቢኖሩም ያ ማንነታቸው መገለጥ አይቀርም፤ እነሱም ለጊዜው አብረው እየኖሩ ምቹ ጊዜ ስያገኙ በጎችን የምናጠቁ ነፍስን የሚያጠፉ ከእውነተኛው #ህብረት #መንገድ የሚያስቱ እውነተኛ ያልሆኑ #ለጥቅም ብቻ የሚኖሩ ማንነታቸውም ለተንኮል ለማሳታ ያለቦታቸው በመገኘት ቦታቸው እንደኾነ እያስመሰሉ የሚኖሩ ማንነታቸው ግን ለጊዜው ደብቀው የራሳቸውን ክፉ ሰራ ከሚያሰሩ ከእነዚህ #ተጠንቀቁ ይለናል። #እንጠንቀቅ! ✍️So ውሎአችንን ገታ አድርገን እናሰላስል! የእውነት አብረውን ያሉትን እንፈትሽ! #ማንነታቸውን በእኛ ውስጥ ደብቀው የራሳቸውን #አጀንዳ እያስፈጸሙ እንዳይሆን...#እንጠንቀቅ! ✍️ቤተክርስቲያን ውስጥ እነማናቸው ያሉት ምንስ እያሉ ነው? እየተናገሩት ያለው እውነተኛ ማንነታቸው ወይንስ በሌሎች ውስጥ ራሳቸውን ሸሽገው ያሉ ተኩላዎች?... #እንጠንቀቅ! ✍️እስቲ ወደ ፊት ከመኸዳችን በፊት ቆም ብለን እናስብ፤ እናስተውል! #እንጠንቀቅ! ✍️ተኵላዎች የበግ ለምድ መልበስ ብቻ ሳይሆን፥ ገላቸው ራሱ የበግ ቢሆን፥ ልባቸው ግን የተኵላ ሆኖ ይኖራል። ከልባቸው ተኵላዎች ናቸውና። #እንጠንቀቅ! 24/4/2018 ✍️ተመስገን ብርሃኑ መልካም ምሽት! ከወደዳችሁ like &Share ይደረግ🙌