Nur Online Academy
СтатистикаNur Academy (ኑር ኦንላይን አካዳሚ) 🎓 የትም ቦታ ሳይሄዱ፣ ጥራት ባለውና በዘመናዊ የኦንላይን ስርአት እውቀትዎን ያዳብሩ! 🌟 ውጤታማ እና ልምድ ባላቸው መምህራን የሚሰጡ የቀጥታ (Live) ስልጠናዎች። 📚 ለተማሪዎች፣ ለስራተኞች እና እራሳቸውን ማሻሻል ለሚፈልጉ ሁሉ የተዘጋጁ ኮርሶች።
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Криптовалюты (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 114
- 1/48двое суток
- 130
- 1/72трое суток
- 140
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
💫 "የሰብር መጨረሻ ሁልጊዜ ውብ ነው፤ ምክንያቱም አላህ የታጋሾችን እንባ አያጠፋም።" اللَّهُمَّ صَبِّرْ قَلْبِي وَعَوِّضْنِي خَيْرًا "አላህ ሆይ! ልቤን በሰብር አጽና፣ ከዚህም በተሻለ ነገር ተካልኝ።" 🤍🍃
"አንደበትህ የአላህን ዝክር ሲያጣጥም፣ ልብህ የዱንያን አቧራ ማራገፍ ይጀምራል።"⏳🤎 🤌
🌺በየቀኑ በእስላማዊ ጥያቄ እና ምልስ በመሳተፍ ሁሌም የካርድ ተሸላሚ ይሁኑ 🎁 ዛሬ 2 ሰዓት 50 ብር ካርድ ሽልማት አለ ወላሂ እውነተኛ ማስተወቂያ ነዉ🤌
. ያለ መድሀኒት ተኝተን ያለ ህመም ያለ ድካም ከተነሳን አልሀምዱሊላህ በትልቅ ኒዕማ ውስጥ ነን:: الحمدالله ❤️🩹
🌺በየቀኑ በእስላማዊ ጥያቄ እና ምልስ በመሳተፍ ሁሌም የካርድ ተሸላሚ ይሁኑ 🎁 ወላሂ እውነተኛ ማስተወቂያ ነዉ🤌
📚ኪታብ በነፃ መማር የሚፈልግ ብቻ 🎊 በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ በሪከርድ ማስተማር ተጀመረ 🌛 እንዳያመልጣቺሁ 🇪🇹
📚ኪታብ በነፃ መማር የሚፈልግ ብቻ 🎊 በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ ማስተማር ተጀመረ 🌛 ቦታ ሳይሞላ ፍጠኑ
የዕለቱ ሀዲስ /daily hadith #ከአብደላህ ቢን መስዑድ رضي الله عنه ተይዞ እንዲህ ይላል፦ ﴿أَيُّ الْعَمَلِ أَفْضَلُ؟ قَالَ: «الصَّلَاةُ لِوَقْتِهَا»﴾ “ለአላህ መልዕክተኛ ﷺ #በላጭ የሆነ ስራ የቱ ነው ተብለው ሲጠየቁ። ‘ሶላትን በወቅቱ መስገድ’ አሉ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 85
የዕለቱ ሀዲስ /daily hadith ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ አዋቂ ሁን ወይም ተማሪ ሁን አልያም አድማጭ ሁን አራተኛ አትሁን ትጠፋለህ‼️
ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ
ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ ~ ሱጁድ (ግንባርን መሬት ላይ ማሳረፍ) ለሁለት ይከፈላል። ንፁህ አምልኮታዊ ሱጁድ እና የሰላምታ (የአክብሮት) ሱጁድ። 1- አምልኮታዊ ሱጁድ:- የአላህ ብቻ ሐቅ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦ فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا "ለአላህም ስገዱ፣ ተገዙትም።" [ነጅም፡ 62] በተጨማሪም አላህ እንዲህ ብሏል፦ {لَا تَسۡجُدُوا۟ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِی خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِیَّاهُ تَعۡبُدُونَ} "ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ። ይልቁንም እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ሆናችሁ ለእዚያ ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ።" [ፉሲለት፡ 37] 2- የሰላምታ ሱጁድ:- ይህንንም ቢሆን ለፍጡር መስጠት እንደማይቻል የሚያሳይ ሐዲሥ አለ። ከመሆኑም ጋር ከፊል ሱፍዮች ለሸይኾቻቸው ሲፈፅሙት ይታያል። በርግጥ ቀደሞ የተፈቀደ ነበር። ለዚህም ማስረጃውም የላቀው አላህ እንዲህ ማለቱ ነው:- { وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰۤىِٕكَةِ ٱسۡجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوۤا۟} ''ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ።" [አልኢስራእ፡ 61] እዚህ ላይ የተጠቀሰው ሱጁድ አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። ይሄ ሱጁድ የአምልኮት ሱጁድ እንዳልሆነ ኢጅማዕ አለበት። [አሕካሙል ቁርኣን፣ ኢብኑል ዐረቢ፡ 1/127] [አልፈስል፣ ኢብኑ ሐዝም፡ 2/129] የዩሱፍ ታሪክ ላይ የተጠቀሰው የነብዩላህ ዩሱፍ ወላጆች ለዩሱፍ የወረዱት ሱጁድም ይሄው አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦ {إِذۡ قَالَ یُوسُفُ لِأَبِیهِ یَـٰۤأَبَتِ إِنِّی رَأَیۡتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوۡكَبࣰا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ رَأَیۡتُهُمۡ لِی سَـٰجِدِینَ} "ዩሱፍ ለአባቱ፡- 'አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም (በህልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው' ባለ ጊዜ (አስታውስ)።" [ዩሱፍ፡ 4] ከዘመናት በኋላ ይህ ህልማቸው እውን እንደሆነ ሲገልፅ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦ {وَرَفَعَ أَبَوَیۡهِ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ وَخَرُّوا۟ لَهُۥ سُجَّدࣰاۖ وَقَالَ یَـٰۤأَبَتِ هَـٰذَا تَأۡوِیلُ رُءۡیَـٰیَ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَعَلَهَا رَبِّی حَقࣰّاۖ} "ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው። ለእርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። 'አባቴ ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው። ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት።' " [ዩሱፍ፡ 100] ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ ሰበብ የሆነኝ ሰሞኑን እነዚህን አንቀፆች መነሻ በማድረግ ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ ይቻላል እያለ የፃፈ ስላየሁ ነው። የሚገርመው ሰዎች ከስር በኮመንት እየገቡ እናንተ አዋቂዎቹ ዝም ብላችሁ ነው የማንም መጫወቻ የምታደርጉት እያሉት ነበር። እንዲህ አይነት ችግር ነው የገጠመን። ቁንፅል ነገር ይይዙና መረጃዎችን በቅጡ ሳይፈትሹ፣ የዑለማእ ንግግሮችን ሳያገላብጡ አሳሳች መልእክት ያስተላልፋሉ። የራሳቸው ጥፋት አልበቃ ብሎ ሌሎችንም ያሳስታሉ። አቀራረቡ ራስን መኮፈስ፣ ሌሎችን መናቅ ሲታከልበት ደግሞ ጥፋቱ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ቢገባቸው ይሄ አካሄድ በራሳቸውም ጥፋት፣ በሚያሳስቷቸው ሰዎችም ወንጀል እጥፍ ድርብ ተጠያቂነትን ነው የሚያስከትልባቸው። ለማንኛውም በቀደምት ሸሪዐዎች የተፈቀደ የነበረው የሰላምታ ሱጁድ በነብዩ መሐመድ ﷺ ሸሪዐ ተሽሯል። ስለዚህ ምንም የማያጠራጥር ሐራም ነው ማለት ነው። ይህንን የሚጠቁመን ተከታዩ ዐብዱላህ ብኑ አቢ አውፋ ያስተላለፉት ሐዲሥ ነው። ሙዓዝ (ብኑ ጀበል ረዲየላሁ ዐንሁ) ከሻም ሲመለሱ ጊዜ ለነብዩ ﷺ ሱጁድ ወረዱ። "ምንድነው ይሄ ሙዓዝ?" አሉ። ሙዓዝም፡ "ሻም በሄድኩኝ ጊዜ (ክርስቲያኖች) ለጳጳሶቻቸውና ለፓትሪያርኮቻቸው ሱጁድ ሲወርዱ አገኘኋቸው። እናም ይህንን ላንተ ልፈፅመው በነፍሴ ወደድኩኝ" አሉ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፦ فَلَا تَفْعَلُوا، فَإِنِّي لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أَنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّهِ، لَأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسْجُدَ لِزَوْجِهَا ... "እንዲህ አታድርጉ። ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ እንዲወርድ አንድንም የማዝዝ ቢሆን ኖሮ ሴት ለባሏ ሱጁድ እንድትወርድ አዝ ነበር። ... " [ኢብኑ ማጀህ፡ 1853] ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ - ረሒመሁላህ - "ሐሰኑን ሶሒሕ" በማለት ለማስረጃነት የሚያበቃው ጥንካሬ እንዳለው ገልፀዋል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1515] ብዥታ የሚያነሳ ሰው እንዳይኖር የዑለማኦችን ንግግር ላስከትል:- 1- ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ وَأَجْمَعَ الْمُسْلِمُونَ عَلَى: أَنَّ السُّجُودَ لِغَيْرِ اللَّهِ مُحَرَّمٌ "ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ መውረድ የተከለከለ እንደሆነ ሙስሊሞች ወጥ ስምምነት አድርገዋል።" [አልመጅሙዕ፡ 4/358] በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦ فإن نصوص السنة، وإجماع الأمة: تُحرِّم السجودَ لغير الله في شريعتنا، تحيةً أو عبادةً، كنهيه لمعاذ بن جبل أن يسجد لما قدمَ من الشام وسجدَ له سجود تحية "የሱና መረጃዎችና የህዝበ ሙስሊሙ ወጥ ስምምነት በሸሪዐችን ውስጥ ሱጁድን ከአላህ ውጭ ለሌላ አካል ማድረግን ይከለክላሉ። ሱጁዱ ለሰላምታ (ለማክበር) ይሁን ወይም ለአምልኮም ይሁን ምንም ለውጥ የለውም። ልክ ሙዓዝ ብኑ ጀበል ከሻም ሲመጡ የደረጉትን ሱጁድ እንደከለከሏቸው። (ሙዓዝ) ያደረጉት ሱጁድ የሰላምታ ሱጁድ ነበር።" [ጃሚዑል መሳኢል፡ 1/25] 2- ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል፦ "وَهَذَا السُّجُودُ الْمَنْهِيُّ عَنْهُ : قَدِ اتَّخَذَهُ جُهَّالُ الْمُتَصَوِّفَةِ عَادَةً فِي سَمَاعِهِمْ، وَعِنْدَ دُخُولِهِمْ عَلَى مَشَايِخِهِمْ وَاسْتِغْفَارِهِمْ ، فَيُرَى الْوَاحِدُ مِنْهُمْ إِذَا أَخَذَهُ الْحَالُ ـ بِزَعْمِهِ ـ يَسْجُدُ لِلْأَقْدَامِ ، لِجَهْلِهِ ؛ سَوَاءٌ أَكَانَ لِلْقِبْلَةِ أَمْ غَيْرِهَا ، جَهَالَةً مِنْهُ ، ضَلَّ سَعْيُهُمْ وَخَابَ عَمَلُهُمْ" "ይህ የተከለከለው ሱጁድ አላዋቂ ሱፊያዎች በዜማቸው ላይ፣ ሸይኾቻቸው ዘንድ ሲገቡ እና ምህረትን ሲለምኑ ልማድ አድርገው ይዘውታል። ከእነሱ ውስጥ አንዱ - እንደሚሞግቱት - 'ሐሉ' ሲነሳበት ጊዜ በእግራቸው ላይ ሲወድቅ ይታያል። ይህን የሚያደርገው ባለማወቁ ነው። ወደ ቂብላ ቢዞርም ባይዞርም ያደርገዋል፤ ይህ ሁሉ ከእውቀት ማነስ የተነሳ ነው። ጥረታቸው ሁሉ ጠፋ፤ ስራቸውም ከሰረ።" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 1/294] https://t.me/yehak_mnged https://t.me/yehak_mnged
ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች የተዘጋጀ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ትልቅ ሰላምና ስኬትን ለማምጣት የሚረዳ ሰፊና ሁሉን አቀፍ ምክር። ይህ ምክር በሦስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ያተኩራል፦ ከፈጣሪ (አላህ) ጋር መገናኘት፣ ራስን ማሻሻል፣ እና ከማኅበረሰብ ጋር በሰላም መኖር። --- ፩. ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር ያለን ግንኙነት ማጠንከር (አቂዳና ዒባዳ) ሕይወታችን ትርጉም የሚኖረውና ውስጣዊ ሰላም የምናገኘው ከመሰረታችን ጋር ስንገናኝ ነው። * ዒባዳን በወቅቱና በጥራት መስገድ፦ ሰላት የሕይወታችን ማዕከል ነው። በወቅቱና በኹሹዕ (በትህትና/በሃሳብ መሰብሰብ) ለመስገድ መጣር በዕለታዊ ውሎአችን ውስጥ በረካና መረጋጋትን ይሰጠናል። * ቁርኣንን የዕለት ተዕለት ጓደኛ ማድረግ፦ ቁርኣንን ማንበብ ብቻ ሳይሆን ትርጉሙን ለመረዳትና በተግባር ላይ ለማዋል መሞከር። በቀን ውስጥ ጥቂት ገጾችንም ቢሆን አዘውትሮ መቅራት ልብን ያርሳል። * ዚክርና ዱዓ ማብዛት፦ ጠዋትና ማታ የሚባሉ የአዝካር ዱዓዎችን ልማድ ማድረግ። በደስታም ሆነ በጭንቅ ጊዜ ወደ አላህ እጅን መዘርጋት የውስጥ ጥንካሬን ይገነባል። * ተውበት (ንስሐ) ማዘውተር፦ ሰው በመሆናችን እንሳሳታለን፤ ዋናው ቁምነገር ግን በሰራነው ስህተት ሳንገፋበት ወዲያውኑ በዕውነት ተጸጽተን ወደ አላህ ምሕረት መመለስ ነው። --- ፪. ራስን ማሻሻልና ዕውቀትን መፈለግ (ነፍስን መግራት) እስልምና የዕውቀትና የስራ ሃይማኖት ነው። ራስን መለወጥ ሌላውን ለመለወጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። * ዕውቀትን መፈለግ፦ የሃይማኖት ዕውቀትን (ሸሪዓን) ማወቅ ግዴታ እንደሆነው ሁሉ፣ ለዚህች ዓለም ሕይወትና ለሙያችን የሚያስፈልጉ ጠቃሚ ምድራዊ ዕውቀቶችንም ማካበት ወሳኝ ነው። * ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፦ ጊዜ ውድ ስጦታ ነው። በማይጠቅሙ ወሬዎች፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ሱስና በትርኪምርኪ ነገሮች ጊዜን ከማባከን መቆጠብ። * ሃላል ሰርቶ መኖር፦ የምንበላው፣ የምንጠጣውና ለቤተሰባችን የምናቀርበው ነገር ሙሉ በሙሉ ከሀላል መንገድ የተገኘ መሆኑን ማረጋገጥ። ሀላል ምግብ ለዱዓ ተቀባይነት ትልቅ ሚና አለው። * እራስን መመርመር (ሙሐሰባ)፦ በየቀኑ ከመተኛታችን በፊት "ዛሬ ምን ጥሩ ነገር ሰራሁ? ምንስ ስህተት ፈጸምኩ?" ብሎ ራስን መጠየቅና ነገ የተሻለ ሰው ለመሆን ማቀድ። --- ፫. ከሰዎች ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር (አኽላቅ) ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት መልካም ስነ-ምግባርን ለመሙላት ነው። ሙስሊም ለአካባቢው ሁሉ እፎይታና ሰላም መሆን አለበት። * ለወላጆች መልካም መሆን፦ የአላህ ውዴታ ያለው በወላጆች ውዴታ ውስጥ ነው። እነሱን ማክበር፣ መታዘዝና መርዳት የሕይወት ስኬት ቁልፍ ነው። * የአንደበት ጥንቃሬ (ምላስን መጠበቅ)፦ ሰዎችን ከሚያቆስል ንግግር፣ ከሀሜት (ጊባህ)፣ ከውሸትና ከነገር ማዋሰድ መራቅ። "የእውነተኛ ሙስሊም መገለጫው ሰዎች ከምላሱና ከእጁ ሰላም የሆኑለት ነው"። * ታማኝነትና ቃልን ማክበር፦ በንግድም ሆነ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ታማኝ መሆን። የገባነውን ቃል ኪዳን መጠበቅና ሰዎችን አለማታለል። * ለጋስነትና መረዳዳት፦ የተቸገሩትን መርዳት፣ ሰደቃ ማብዛትና በሰዎች ደስታና ሀዘን ላይ አብሮ መገኘት። ሰዎችን ይቅር ማለትን መልመድ (ይቅር ባይነት የልብ ሰላም ይሰጣል)። --- "የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህች ዓለም አጭርና ጊዜያዊ መሻገሪያ ድልድይ ናት። ዋናውና ዘላለማዊው መኖሪያችን የአኺራ ቤት ነው። ስለዚህ ዛሬ በምናደርገው እያንዳንዱ ነገር ላይ አላህን በመፍራት (ተቅዋ) እና በታማኝነት በመስራት ለነገው ዘላለማዊ ሕይወታችን መልካም ስንቅ እናዘጋጅ።" https://t.me/yehak_mnged https://t.me/yehak_mnged
ውድ እህቴ! ትዳር በአላህ (ሱ.ወ) ጥበብ የተደነገገ፣ የሁለት ነፍሶች መረጋጋትና ሰላም መገኛ የሆነ ታላቅ የህይወት ምዕራፍ ነው። ይህንን የተቀደሰ ጉዞ በስኬትና በደስታ ለመምራት የሚረዱሽን ዋና ዋና ምክሮች ከዚህ በታች አዘጋጅቼልሻለሁ። 1. የትዳር አጋር ምርጫ እና መስፈርት - ዲንና ስነ-ምግባር፡ የትዳር አጋርሽን ስትመርጪ ከሁሉ አስቀድመሽ ለአላህ ያለውን ፍርሃትና ስነ-ምግባሩን ተመልከቺ። አላህን የሚፈራ ወንድ ቢወድሽ ያከብርሻል፣ ባይስማማሽ እንኳ አይበድልሽም። - እውነተኛ ዝግጁነት፡ ትዳር በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በፈተናም ጊዜ አብሮ መቆም መሆኑን ተረጂ። በትዳር ውስጥ ሃላፊነትን ለመሸከም ራስሽን በዕውቀትና በስነ-ልቦና አዘጋጂ። 2. ፍቅርና መተሳሰብ በቤት ውስጥ - የቤት ውስጥ ሰላም መሆን፡ ወንድ ልጅ ከውጪ ድካምና ውጥረት በኋላ ወደ ቤቱ ሲመጣ የሚፈልገው እረፍትንና ሰላምን ነው። ለባልሽ መረጋጋትንና ደስታን የምትለግስ ንጹህ መጠለያ ሁኚለት። - ምስጋና እና አድናቆት፡ ባልሽ ለቤትሽና ለአንቺ የሚያደርገውን ጥረት እውቅና ስጪ፣ አመስግኚው። መከባበርና መደጋገፍ ባለበት ቤት ውስጥ ፍቅር በቀላሉ አይጠፋም። - ይቅር ባይነት፡ ፍፁም የሆነ ሰው የለም። ትናንሽ ስህተቶችን ማለፍንና ይቅር መባባልን ልመዱ። ጭቅጭቅና አለመግባባቶችን በውይይትና በለስላሳ ንግግር መፍታት የብልህ ሴት መለያ ነው። 3. ሚስጥራዊነት እና ታማኝነት - የቤት ውስጥ ሚስጥር፡ በባልሽና በአንቺ መካከል የሚፈጠሩ ማናቸውንም ነገሮች (ምስጢሮችም ሆኑ አለመግባባቶች) ለሶስተኛ ወገን፣ ለቅርብ ጓደኛም ሆነ ለቤተሰብ አታውጪ። የቤትሽን ክብር በውስጥሽ ጠብቂ። - ታማኝነትና ክብር፡ ባልሽ ባለበትም በሌለበትም ሰዓት እራስሽን፣ ክብሩንና ንብረቱን በአግባቡ ጠብቂ። ይህ በአላህ ዘንድም ትልቅ አጅር (ምንዳ) የሚያስገኝ ታላቅ አማና ነው። 4. ከአማችና ከቤተሰብ ጋር ያለው ግንኙነት - መልካም ግንኙነት፡ የባልሽን ወላጆችና ዘመዶች እንደራስሽ ቤተሰብ አድርገሽ ተመልከቻቸው። ለእነሱ የምታሳይው መልካምነት በባልሽ አይን ውስጥ ያለሽን ቦታ በእጅጉ ከፍ ያደርገዋል። - በጎ መመኘት፡ በቤተሰብ መካከል አለመግባባት ቢፈጠር እንኳ በትዕግስትና በጥበብ እለፊው። መልካም ስነ-ምግባር ሁልጊዜም ያሸንፋል። ማጠቃለያ፡ ውድ እህቴ! መልካም ሚስት ማለት የዱንያ ትልቁና ውዱ ጸጋ ናት። ትዳርሽን በአላህ ፍርሃት ላይ መስርቺ፣ በትዕግስትና በደግነት አስውቢው። አላህ የተባረከና የሰላም ትዳር ይወፍቅሽ! https://t.me/yehak_mnged https://t.me/yehak_mnged
🍃 ከ ጨለማው ቡሃላ ባለው ንጋት ሳይሆን ጨለማ እና ንጋትን ባቀያየረው ጌታ ላይ ተስፋ ይኑራችሁ الله❤️🩹
አንድ ሰው በላጭ የሆነ ነገር አልተሰጠውም..... ሶብር ቢሆን እንጂ ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) አላህ ከሰብሮኞች ያድርገን አሚን🤲
አሊፍ ባ በስርአቱ ማለት ሳንችል ጊዜያችን በሶሻል ሚዲያ መግደል ማለት ትልቅ ክስረት ነው💔 🥹
🥹❤️🩹 "እንዴት ተረጋጋሽ🤷♀ "ወደ ማይተወኝ ተጠግቼ🥰 "ማን ነው እሱ🤔 "አላህ አላህ ነው🥹
ላለፉት 360 ቀናቶች ስንሰራው የነበረው ወንጀል እንዲማርልን ነገ (ዐሹራእ'ን) እንፁም! ወሩ ሙሀረም ቀኑ ሀሙስ ነገ የአጅር መሰብሰቢያ ቀን ነው እንዳያልፈን ኢንሻአላህ🥀
🥹❤️🩹 "እንዴት ተረጋጋሽ🤷♀ "ወደ ማይተወኝ ተጠግቼ🥰 "ማን ነው እሱ🤔 "አላህ አላህ ነው🥹
ምን ያምር ባሪያ! [ሷድ 44] በአላህ አንደበት እንዲህ መባል አይናፍቀንም? አላህ ለነብዩላህ አዩብ ነበር ይህን ያለው ለትዕግስቱ صبر❤️🩹