tgindex
የማህበር ዝማሬ

የማህበር ዝማሬ

Статистика

ገና እንዘምራለን እንደመላእክቱ ብርሃንን ለብሰን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምህሮን ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮችን ከነዜማቸው በየቀኑ ወደ እናተ እናደርሳለን 👉መዝሙር ና 👉ንግሶችን እናሳዊቃለን ለኛ ለወጣቶች የሚሆን ትምህርት ቻናሉ ላይ ያገኛሉ https://t.me/ortodoks16 አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላቹ @nahel21 አናግሩኝ

Последний пост
4 июн.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
655
−2 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
176
29 постов
Вовлечённость
26,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✨ ጥራትና ውበትን ከእኛ ዘንድ ያግኙ! ✨ የሚወዱትን አይነት ልብስ፣ ጫማ፣ ኦሪጅናል ሽቶዎች እና ሌሎች ማንኛውንም እቃዎች በእርስዎ ፍላጎት መሰረት ካሉበት ቦታ እናቀርባለን። ጥራት እና ታማኝነት መለያችን ነው! 💯 📩 አሁኑኑ ይዘዙን፦ @dagi_212 📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0903348315

  • ከትንሳኤ በኋላ ያሉ ዕለታት         ማክሰኞ ቶማስ ይባላል እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው የሚያንቀላፋና የሚነቃ አድርጎ ፈጥሮታል፡፡ ማንቀላፋቱ የሞት ፤ መንቃቱ ደግሞ የትንሣኤ ምሳሌ መሆኑን ስናስብ ሁሌም ይደንቃል፡፡ አባቶቻችን የትንሣኤውን ምሥጢር በአበው እና በስነፍጥረትም ይመስሉታል፤ አቤል ከሞተ በኋላ በደሙ መናገሩ እና የሔኖክ ሳይሞት በእግዚአብሔር መሰወሩ የትንሣኤ ምሣሌ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ፀሐይ መውጣቷ የመወለዱ ፤ መጥለቋ የሞቱ እና ዳግመኛ መውጣቷ የትንሣኤው ምሣሌ ነው፡፡ አምላካችን ክብር ይግባውና በእርሱ ያመንን ሁላችን እንደምንነሳ የእርሱ ከሙታን መካከል በሥልጣኑ መነሳት ለሁላችን መነሳት በኩር መሆንና ማረጋገጫም እንደሆነ በቃሉም በተግባሩም ያስተማረን የትንሣኤ ጌታ ነው፡፡ በቃሉ "በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምጹን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል ፤ መልካም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ፤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ " (ዮሐ፭፡፳፱) እንዲሁም በተግባር የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን አስነስቷል፡፡(ዮሐ፲፩፡፵፫) የትንሣኤው ምሥጢር ሁላችን አምላክ የሆንበት ፤ በሁሉ ላይ ሥልጣን ያገኘንበት ፤ነጻ ወጥተን ነጻ አውጪ የሆንበት ፤ ከማይጠፋ ዘር እንደተወለድን ያረጋገጥንበት ፤ ሞትን የተዘባበትንበት ፤ ጨለማን የረታንበት ከዓለም እና ከዲያብሎስ እስራት ነጻ የወጣንበት ልዩ ክብር ኃይል እና ጸጋን ያገኘንበት ምሥጢር ነው፡፡ ይህቺ ዕለትም ይህንኑ ምሥጢር ነው የምትገልጥልን ሐዋርያው #ቶማስ ተብሎ ለምን ተሰየመ የሚለውን ከማየታችን በፊት ማነው የሚለውን ማየት ነገርን ከስሩ እንድንረዳው ይረዳናልና እውነት ሐዋርያው ቶማስ ማነው?        ሐዋርያው ቶማስ ሐዋርያው ቶማስ የስሙ ትርጓሜ ፀሐይ ማለት ሲሆን የቀድሞ ስሙ ዲዲሞስ ይባላል ትርጉሙም ጨለማ ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ፲፪ ሐዋርያት ነው፡፡ (ማቴ፲፡፫) (መዝገበ ታሪክ ክፍል ሁለት ገጽ፹፱) ፤ ሐዋርያ ማለት ደጅ አዝማች ፤ ቀላጤ ፤ ምጥው ፤ ፍንው ፤ ሂያጅ ማለት ነው፡፡(ወንጌል ቅዱስ ገጽ፻፶፱) ሐዋርያው ቶማስ አልዓዛር በሞተ ጊዜ ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደነበረው መቃብሩ ለመሄድ በተነሳ ጊዜ አይሁድ ሊገሉት ስለሚፈልጉ ሌሎቹ ሐዋርያት ክርስቶስ እንዳይሄድ ቢፈልጉም ቶማሰ ሌሎቹን ሐዋርያት በድፍረት እኛም ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ አብረን እንሂድ ያለ የእምነት ሐዋርያ ነው፡፡ (ዮሐ፲፩ ÷ ፲፮) ሐዋርያው ቶማስ ጌታችንን በእውነት እስከ ሞት ድረስ ያመነው ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ በ8ኛው ቀን እሁድ ሲሆን ሐዋርያት የነገሩትን ካላየው አላምንም ብሎ የተወጋ ጎኑን ከዳሰሰ በኋላ ነው፡፡ የእምነት ምስክርነቱም ጌታዬ አምላኬም ብሎ የገለጠው፡፡(ዮሐ፳፡፳፬) ሐዋርያው ቶማስ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ከተቀበለ በኋላ በ፵፮ ዓ.ም ገደማ በፋርስና በሕንድ እንዳስተማረ የተለያዩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይገልጣሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ ፤ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ፤ ቅዱስ አምብሮስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡በመጨረሻም ብዙ ተአምራት እና ድንቅን አድርጓል፡፡ የሐዋርያው ቶማስ ተአምር እና አገልግሎት ብዙ ተአምራትን ቢያደርግም ለአሁኑ አንዱን ብቻ እናያለን፡፡ የኸውም የሉክዮስ አገልጋይ ሆኖ በሕንጻ ማነጽ እና በሐውልት መስራት ተቀጥሮ በሚሰራበት ወቅት የሉክዮስን ሚስት ከእነ ልጆቿ እና አገልጋዮቿ አሳምኖ ያጠመቀ ሐዋርያ ነው፡፡ ሐዋርያው ቶማስ ለሕንጻ እና ለሐውልት ማሰሪያ ከሉክዮስ የተቀበለውን ገንዘብና ወርቅ ሁሉ ለነዳያን በመመጽወቱ ንጉሡ እጅና እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አሰፍቶ በአሸዋ ሞልቶ አሸክሞት ገበያ ለገበያ ሲያዞረው የሉክዮስ ሚስቱ አርሶንዋ ተመልክታ በድንጋጤ ሞታለች፡፡ ንጉሡም ለሚስቴ መሞት ምክንያት አንተ ነህ ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለው ሲለው ጌታችን ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነስታለች በዚህም ሉክያኖስ አምኖ ተጠምቋል፡፡ ሐዋርያው ቶማስ በራሱ ቆዳ በተሰራ ስልቻ እየተዘዋወረ ሙት አስነስቷል ፤ ድውያንን ፈውሷል አሕዛብን አሳምኖ አጥምቋል ፤ በቀንጦፍያ አንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆቹን ገድለውበት ሰባቱንም ከሞት አስነስቷል ፤ በኢናስም በቃሉ ትምህርት እና በእጁ ተአምራቱ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቋል፡፡     የሐዋርያው ቶማስ ሰማእትነት በሕንድ የነበሩት የብራሕማን እምነት ተከታዮች የቶማስ ትምህርት የእነርሱን እምነት የሚጻረር እና የሚያጠፋ መሆኑን ተገንዝበው ተነሱበትና በብዙ ስቃይ አሠቃይተው በ፸፪ዓ.ም በሰማዕትነት አርፏል፡፡ በሶርያ ትውፊት መሠረት የሐዋርያው የቶማስ አጽም በአንድ የሶርያ ነጋዴ ተወስዶ በኤዴሳ በክብር አርፏል፡፡ (የእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ በምድር ላይ አንደኛ መጽሐፍ ገጽ ፺፪)   ሐዋርያው ቶማስ ለምን ሰምቶ አላመነም? እንደ ወንጌል ትርጓሜ ሐዋርያው ቶማስ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላም ለእናንተ ይሁን ባለ ጊዜ አልነበረም ፤ በነገሩት ጊዜም አላመነም ያለማመኑ ምክንያት ሰዱቃዊ ስለነበር እና ሐዋርያቱ አይተው እርሱ ሰማው ብሎ ከሚያስተምር ማየት ወዶ ነው፡፡           "ጌታዬ አምላኬም" (ዮሐ፳:፳፰)

  • ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት     ሰኞ ሰኑይ ማእዶት ይባላል እንደ ቤተክርስቲያን ይትባሕል ከትንሣኤ እስከ ዳግማዊ ትንሣኤ ያለውን ሳምንት እንደ አንድ እሁድ እናከብራለን። ለዚህም ነው ዕለታቱን እንደ ሰንበት እናከብራቸው ዘንድ በፍትሐ ነገሥት ላይ አባቶቻችን ትእዛዝ የቀረጹልን። ማእዶት ማለት መሻገር ማለት ነው። አደወ ማለት ተሻገረ ማለት ሲሆን ማእዶት መሸጋገሪያ ማለት ሊሆን ነው። ማእዶት የትንሣኤ እሑድ ማግስት ጌታ ክርስቶስ በትንሣኤው ምዕመናንን ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገረበት ቀን የትንሣኤው ማሳሰቢያ ነው። (ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ ፻፶) መሻገር በዕብራይስጥ ፓሳሕ ከሚባለው ቃል ይመሳሰላል ትርጉሙም ፋሲካ መሻገር ማለፍ የሚል ትርጉም ይሰጣል። ሁላችን እንደምናውቀው እስራኤላውያን ከሚያክብሯቸው አበይት በዓላት አንዱም ፋሲካ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እግዚአብሔር ከሞተ በኩር ያሳለፋቸውን ዕለት ያስቡበታል። ቤተክርስቲያናችንም ይህንን በዓለ ትንሣኤን የፋሲካ በዓል የማክበሯ ምሥጢር ወይም የትንሣኤው ምሥጢር ነፍሳት በአምላካችን ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከአሳር ወደ ክብር ፣ ከሲዖል ወደ ገነት መሻገራቸውን በማሰብ አማናዊው ፋሲካ ወይም አሸጋጋሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብላ ታምናለች። እናምናለን። ቅዱስ ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን በታረደው የፋሲካ በግ (ዘዳ፲፮:፮) ምትክ አማናዊው ክርስቶስ እንደታረደልን እና ሞት ላያገኘን በሕይወት ለሕይወት እንዳሸጋገረን ሲገልጥ እንዲህ ብሏል:-"" እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤" (፩ ቆሮ ፭:፯) ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እርሾም ሆነ ስለ አዲሱ ሊጥ በምሳሌ የሚነግረን እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ፋሲካ ሲያከብሩ ያደርጉት የነበረ ስርዓትን ነው። ይኸውም ፋሲካን ያከበሩት ገና ከነጻነት በፊት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ከሞተ በኩር መቅሰፍት ለመዳን እና ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመዳን ነበር። በአዲስ ኪዳንም ያለን ክርስቲያኖች በተለይ ይህንን ዕለት ወይም ማእዶትን ስናስብ አምላካችን ከሞት ወደ ሕይወት እንዳሻገረን ፣ ከአሳር ወደ ክብር እንዳሳለፈን ፣ ከድካም ወደ ኃይል እንዳሻገረን ፣ ሁላችን ወደ መንግሥተ ሰማያት ፋሲካችን በሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሸጋገርን በማመን ሊሆን ይገባል። የፋሲካው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ እንድንዘባበትበት ሞትን ፣ ፍርሃትን ፣ ጭንቀትን ፣ ተስፋ መቁረጥን ፣ ሐዘንን ፣ ለቅሶን ፣ ትካዜን ፣ ድካምን ፣ ሥጋትን እና መቃብርን ሁሉ አጥፍቶ አሻግሮናል። ክብር ማዕዶታችን ለሆነ ለእርሱ ይሁን። አሜን ክብር ይግባውና አምላካችን የሰው ልጅ ሞትን እንዲሻገር ሁለት ነገሮች(እምነት እና ምግባር ) እንደሚያስፈልጉት በመዋለ ስብከቱ እንዲህ ሲል አስተምሮናል:- "እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።" (ዮሐ፭:፳፬-፳፭) ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ዕለቷ ፋሲካ እንደሆነችና እንደሰትባት ዘንድ የተገባች እንደሆነች እንዲህ ሲል በመዝሙሩ አዚሞታል:- " ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ (ይህቺ የፋሲካ ዕለት ልዩ ናት) ፣ ዛቲ ዕለት ንትፈሳሕ በቲ (በዚህ ዕለት ሐሴት እናድርግባት)..."

  • "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!" ይህ ሰላምታ ለሃምሳ ቀናት ይዘልቃል። የዚህ ሰላምታ ልውውጥ ታሪክ የሚጀምረው ከመጀመሪያዋ ምዕተ ዓመት ከነበረችው ከጥንት ክርስቲያኖች ጀምሮ ሲሆን ለትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ሲገናኙ አይሁዳውያን "ሻሎም" ወይም ሰላም ብለው ሰላምታ እንደሚለዋወጡት ሁሉ ክርስቲያኖቹም "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል" ብለው ሰላምታ ሲሰጡ መላሹ ደግሞ "በአማን ተንስአ እሙታን ፤በእውነት ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል" በማለት ይመልሳል። ይህ ሰላምታ በሁሉም በምስራቁም በምዕራቡም ኦርቶዶክሳውያን ብሎም በአንግሊካንም ቤተክርስቲያን ከትንሳኤው ጋር የፋሲካ ሰሞን ሰላምታ እንደሆነ ቆይቷል። አሁንም የሚተገበር ሰላምታ ነው። ነገር ግን መቼ እንደሆነ ባይታወቅም ሰላምታው ከዘወትር ሰላምታ ወደ ዘመነ ፋሲካ ብቻ ሰላምታ ተለወጠ። በምዕራቦቹ ክርስቲያኖች ሰላምታ ሰጪው Christ is Risen!" ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ወይም "The Lord is Risen!" እግዚእ ተንስአ እሙታን ሲል ሰላምታ መላሹም   "Truly, He is Risen," በአማን ተንስአ፤በእውነት ተነስቷል "Indeed, He is Risen," ወይም በእርግጥ ተነስቷል "He is Risen Indeed እርግጥ ነው ከሙታን ተነስቷል ይላል። Christ is Risen!" or "The Lord is Risen!", and the response is "Truly, He is Risen," "Indeed, He is Risen," or "He is Risen Indeed. ይህ ሰላምታ ከሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት የእኛ ቤተክርስቲያን የሚለየው ረዘም ብሎ "ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ ዓግአዞ ለአዳም፤ ሰላም፤ እምይእዜሰ፤ ኮነ ፍሰሀ ወሰላም በማለት በጥልቅ ሚስጢር ሰላምታ ላይ ይውላል። በዚህም የሀገርኛ ነገረ ክርስቶስ ትምህርት (Ethiopic Christology)እድገትን አንድ ማሳያም አድርገን መውሰድ እንችላለን። የጌታ ሞትና ትንሳኤ በቤተክርስቲያን ታሪክም ይሁን በነገረ መለኮት አስተምህሮ እድገት(Development of theological teachings) ትልቁን ስፍራ ይይዛል። በስልታዊ ነገረ መለኮት (Systematic Theology) ትምህርት ውስጥ "ዶግማ አይቀየርም ነገር ግን ያድጋል" የሚባለው ለዚህ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ በ367 ዓ.ም በዛሬዋ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፈው ቃለ ምዕዳን (ልፋፈ ጽድቅ) በ45ኛ ደብዳቤው  የኦርቶዶስክ ቤተክርስቲያን በቀኖና የምትቀበላቸውን በዝርዝር 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍትን መሆኑን ያወጀበት ቀን ነው። ከዚያም ወደ ሁሉም መንበረ ፕትርክናዎች (Patriarchate) ልኳል። Priest : Christ is risen from the dead! ካህን    : ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን! People : By the highest power and authority! ሕዝብ     : በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን! Priest : He chained Satan! ካህን    : አሰሮ ለሰይጣን! People : Freed Adam! ሕዝብ     : አግዐዞ ለአዳም! Priest : Peace! ካህን    : ሰላም! People : Henceforth! ሕዝብ     : እምይእዜሰ! Priest : Is! ካህን    : ኮነ! People : Joy and Peace! ሕዝብ     : ፍስሐ ወሰላም      መልካም በዓል!

  • “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥20 ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዓዞ ለአዳም፤ ሰላም፤ እምይእዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሃ ወሰላም። እንኳን ለጌታችንና ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ፤ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳቹ መልካም በዓል🙏🙏🙏

  • እንደሚመጡና ‘ሰማይና ምድር ያልፋል፤ ጌታ ይመጣል፤ ትንሣኤ ሙታን ይደረጋል፤ ያላችሁት የት አለ?’ እያሉ የሚክዱና የሚያስክዱ ሰዎች እንደሚመጡ አስቀድሞ ነግሮናል። (2ኛ ጴጥ 3፥1-18)።  እንዲሁም ጌታችን በወንጌሉ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ”(ዮሐ 11፥25)። ብሎ የሰበከውን ህያው ቃል ያልተገነዘቡ የቅዱስ ጴጥሮስንና የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት እንዳቃለሉና እንዳፌዙ ሁሉ ዛሬም በዘመናችን ስለትንሣኤ ሙታን፣ ስለ ዘላለማዊ ህይወት ሲነገራቸውና ሲሰበክላቸው የማያምኑ ብዙ ሰዎች መኖራቸው እንግዳ ነገር እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባናል። እኛ ግን ይልቁንም ቅዱሳት መጻፍትን በማንበብና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን በመጠየቅ ይበልጥ ስለትንሣኤ ልንረዳና በመጨረሻው ስዓት የክብር ትንሣኤ ባለቤት እንድንሆን መትጋት ይኖርብናል። በትንሣኤ የምናምንም የማያምኑም ለፍርድ መነሣታችን አይቀርምና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሙታን ትንሣኤ በሚገባ ቋንቋ አብራርቶ በምሳሌ ሲያስተምር «ነገር ግን ሰው፥ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል፡፡» ብሎ ከጠየቀ በኋላ፥ «አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፡፡» ብሏል፡፡ ከዚህም አያይዞ «የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው፡፡ በመበስበስ ይዘራል÷ ባለመበስበስ ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል÷ በኃይል ይነሣል፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል÷ መንፈሳዊ አካል ይነሣል ፤ ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ፡፡ እንዲሁ ደግሞ፡- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም (ክርስቶስ) ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው። ሁለተኛው ሰው ( ክርስቶስ ) ከሰማይ ነው፡፡ መሬታዊው እንደሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲህ ናቸው÷ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው ፡፡ የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን፡፡» ብሏል። ፩ኛቆሮ ፲፭÷፴፭-፵፱፡፡  በአጠቃላይ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እኛን የወደደበት ሕይወቱን እስከ መስጠት ደርሶ ቤዛ የሆነበትን ምሥጢር የሰው ሕሊና መርምሮ ሊደርስበት የሚችል አይደለም፡፡ ተነጻጻሪ ተወዳዳሪ አቻ ወይም አምሳያ የሌለው ልዩ ነውና፡፡ ስለሆነም የትንሣኤ ሙታንን ምሥጢር ተረድተን በክርስቲያናዊ ምግባር መኖር አለብን። በትንሳኤ ሙታን ጊዜ ስንነሣ በጌታችን ፊት እንዳናፍር በትዕዛዙና በሕጉ ጸንተን ጌታችን "ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፣ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ" (ዮሐ 6፥54)፤ እንዳለ የክብር ትንሣኤ አግኝተን ከምርጦቹ ጋር በቀኙ እንዲያቆመን የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን በመቀበል ለክብር ትንሣኤ ተዘጋጅተን ሊሆን ይገባል። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች እንደጻፈልን በ፩ኛቆሮ ፲፭÷፳-፳፫፡፡«አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል፡፡ ሞት በሰው (በቀዳማዊ አዳም) በኵል ስለመጣ፥ ትንሣኤ ሙታን በሰው (በተዋሕዶ ሰው በመሆኑ ዳግማዊ አዳም በተባለ በክርስቶስ) በኩል ሆኗልና፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኵራት ነው፤»  እንዲል የትንሣኤያቸን በኩር ክርስቶስን አብነት አድርገን፣ ቃሉን ሰምተን፣ ሕጉን ጠብቀን፣ ትዕዛዙን አክብረን፣ ትንሣኤ ልቡና ተነሥተን፣ ሥጋውን በልተን፣ ደሙን ጠጥተን፣ በንስሐ ተሸልመን፣ በፍቅረ እግዚአብሔርና በፍቅረ ቢፅ (ወንድምን በመውደድ) ጸንተን ብንኖር የትንሣኤውን ትርጉም አውቀነዋል፣ ገብቶናል ማለት ነው፡፡ ከትንሣኤ ሥጋ ትንሣኤ ልቡና ተነሥተን፣ በንስሐ ታጥበን ሥጋውና ደሙን ተቀብለን፣ ተዘጋጅተን እንድንኖር የአምላካችን ቸርነት የወላዲተ አምላክ የድንግል ማርያም፣ የቅዱሳንና የቅዱሳን መላእክት አማልጅነትና ተራዳኢነት አይለየን። አሜን! መልካም በዓል!

  • ትንሣኤ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሓ ወሰላም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በከብቶች በረት ከተወለደበት ሰዓት ጀምሮ ለሰው ልጅ ድኅነት ሲል ከመሰደድ እስከ ሞት፤  ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልትና ግርፋትን ተቀብሎ፤ በጲላጦስ ከወንበዴዎች ጋር ተፈርዶበት፤ በቀራንዮ አደባባይ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፤ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ አዳምንና ዘሩን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከባርነት ወደ  ነፃነት መልሶ በሦስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል፤ በማቴ28፥5 ላይ “እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ወረደ፣ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፣ እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና። እንደ ተናገረው ተነስቷልና በዚህ የለም ኑና እዩ አላቸው።” ተብሎ እንደ ተገለጸው፤ ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ስልጣን በክብር ተነስቷል።  ማጽናናትና የምሥራችን ለሰው ልጆች ማብሰር ልማዳቸው የሆኑ መላእክት ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመለአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት አምላክን እንደምትወልድ እንዳበሰራት ሁሉ እነሆ ጌታም ሞቶ በተቀበረ በሦስተኛው ቀን የትንሣኤውን ብስራት በሌሊት ወደ መቃብሩ ስፍራ ለመጡ የገሊላ ሰዎች በእግዚአብሔር መለአክ አማካኝነት ተነገረ። አስቀድሞ በነብዩ ቅዱስ ዳዊት አማካኝነት ስለ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በመዝ.77፥6 “እግዚአብሔር ይነሣል ጠላቶቹም ይበተናሉ፤ እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው ጠላቶቹንም በኋላው መታ” እንዲሁም በመዝ.3፥5  “እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም እግዚአብሔር አሥነስቶኛልና ተነሣሁ” በማለት የክርስቶስን ከሙታን መነሣት  በትንቢት ተናግሯል፡፡   ሌሎች ነብያትም ክርስቶስ እንዲሞት በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ  በተለያየ ጊዜያት በትንቢትና በምሳሌ ገልጸዋል፡ ፡ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ስለትንሳኤው በምሳሌ አስተምሯል እንዲሁም በመጨረሻም እንደተናገረው በተግባር መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በስልጣኑ ተነስቷል። ሐዋርያትም በስብከታቸው እና በመጽሐፋቸው ስለ ትንሣኤው ምስክርነት በመስጠት አረጋግጠው አስፍተውና አምልተው አስተምረዋል፤ ጽፈዋል። (ዮና.2፥1፣ ሆሴ.13፥14፣ ማቴ.12፥4ዐ ማቴ 28፣ ማር 16፣ ሉቃ 24፣ ዮሐ 20 ወዘተ)። ይሁን እንጂ የጌታችን ትንሳኤ በነዚህ ሁሉ ትንቢታትና ምሳሌዎች፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት፣  እንዲሁም በጌታችን በራሱ በትምህርትም በተግባርም  የተገለፀ  ቢሆንም ስለ ትንሣኤው ለማመን ያዳግታቸው ብዙ ሰዎች ነበሩ። ከሐዋርያትም መካከል የሆነው ቅዱስ ቶማስ የተቸነከሩትን እጆቹንና እግሮቹን፣ በጦር የተውጋውን ጎኑን ካላየሁ፣ ካልዳሰስሁ የክርስቶስን መነሣት አላምንም ብሎ ጌታችን በዝግ ቤት ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ የተወጋውን ጎኑን አሳይቶ በክብር መነሣቱን እስከሚያረጋግጥለት ድረስ የጌታችንን ትንሣኤ ለማመን እንደተቸገረ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል (ዮሐ 20፥24) ይሁን እንጂ የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በስሙ ላመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ትንሣኤ ነው፡፡ ክርስቶስ ለሙታን ሁሉ በኲር ሆኖ ተነሥቶአል፡፡ የሙታንን ሁሉ መነሣት የሚያረጋግጥልን የጌታ ትንሣኤ ነው፡፡ የክርስቶስም ትንሣኤ መርገመ ሥጋ፥ መርገመ ነፍስ፤ ሞተ ሥጋ፥ ሞተ ነፍስ የተሻረበት ርደተ ገሃነም ጠፍቶ፥ በአዳም የተፈረደው ፍርድ ሁሉ ተደምስሶ፤ ፍጹም ነፃነት፣ የማይለወጥ ደስታ፣ የተገኝበት ስለሆነ ፋሲካ ይባላል፡፡ ፋሲካ ደስታ ነው እስራኤል ከግብጽ ባርነት ነፃ የወጡበትን ቀን ፋሲካ ብለውታል፡፡ የእርቅ፣ የሰላም፣ የድኅነት ቀን ነው። ከሞት ከመነሣት ከመቃብር ጨለማ ከመውጣት ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከመላቀቅ፥ ከሲኦል እስራት ከመፈታት የሚበልጥ ምንም ደስታ ሊኖር አይችልምና  ፋሲካችን እንለዋለን። ስለሆነም የጌታችን ትንሣኤ ለኛ በኩራችን ነው፡፡ እርሱን በኩር አድርገን እንነሣለንና። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች እንደጻፈው በ1ኛ ቆሮ.15፥20 “አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአል በሁለተኛው ሰው ትንሣኤ ሙታን ሆነ” እንዳለ የጌታችንን የትንሣኤውን በዓል ስናከብር የእኛም ትንሣኤያችን መሆኑን አውቀንና  ተረድተን በትንሣኤ ልቡና ተነሥተን መልካም ሥራ በመሥራት መሆን አለበት። እኛ ትንሣኤ ልቡናን ሳንነሣ በየዓመቱ ትንሣኤን ብናከብር ፈሪሳውያንን ወይም ትንሣኤ የለም ፈርሰን በስብሰን እንቀራለን ብለው የሚያምኑ ሰዱቃውያንን መምሰል ይሆናል፡፡ እንደሁም በቆላ.3፥1-4 “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኛ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ የላይኛውን አስቡ በምድር ያለውንም አይደለም እናንተ ፈጽማችሁ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ የተሠወረች ናትና ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ያን ጊዜ ከእርሱ ጋር በፍጹም ክብር ትገለጣላችሁ” ተብሎ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆላስያስ ሰዎች እንደተጻፈው የክርስቶስ ትንሣኤ ትንሣኤያችን ነው ብለን ለምናምን ሁሉ ከምድራዊ ሀሳብ ነጻ ሆነን ተስፋ የምናደርገው ትንሣኤ እንዳለን በማሰብ ከሞት በኋላ ሕይወት ከትንሣኤም በኋላ የዘለዓለም ሞት መኖሩን ሳንዘነጋ መኖር እንደሚገባን ይመክረናል፡፡ በተጨማሪም  በዮሐ.5፥28 እንደተገለጠው በትንሳኤ  ለማያምኑ ወይም ከሞት በኋላ ስላለ ሕይወት ስለማያስቡ፣ መልካም ሥራ ለማይሰሩ ሰዎች ትንሣኤ ምን እንደሚመስል ጌታችን መድኅኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር  “በመቃብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ስለዚህ አታድንቁ መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉ የሠሩም ለፍርድ ትንሣኤ ይነሣሉ” ብሏል፡፡ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የቅዱስ ቶማስን ዓይኖች ዓይኖቻችን አድርገን፤ የእርሱን ጆሮዎች ጆሮቻችን አድረገን፤ የእርሱን እጆች እጆቻችን አድርገን ትንሣኤውን በፍጹም ልባችን አምነን መኖር ይገባናል። እንዲሁም ጌታችን ለቶማስ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ብሎ እንደ ተናገረ እኛም ትንሣኤውን በመንፈስ የተረዳን ሁሉ ከትንሣኤው ብርሃን በረከትን ለማግኘት የጌታችንን ትንሣኤ ላልተረዱ ሁሉ እነርሱም እንደኛ የትንሣኤውን ብርሃን እንዲያዩ በሕይወታችን በቃልም በምግባርም ልንመሰክርላቸው ይገባል። በዘመናችንም በትንሳኤው የማያምኑ እንዳሉ ይልቁንም፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ትንሣኤ በአቴና ከተማ ሲያስተምር ትምህርቱን ባለመረዳት እንዳፌዙበት ሁሉ በአሁኑም ወቅት የሙታን ትንሣኤ ሲነገር የሚቀልዱና የሚዘብቱ ብዙዎች አሉ። (የሐዋ 17፥32)። ቅዱስ ጳውሎስ የአቴና ሰዎችን ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እንዲመለሱ፣ በጌታችን ትንሣኤ አምነው በትንሣኤው ክብርን እንዲወርሱ ቢያስተምራቸውም ብዙዎቹ ግን ድኅነትን ከመፈለግ ይልቅ ፌዝን መረጡ። ቅዱስ ጳውሎስ “ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?” (ገላ 3፥1)። ብሎ እንደ ተናገረው ዛሬም የትንሣኤውን እውነት መስማትም ሆነ መናገር የማይፈልጉ ተረፈ ሰዱቃውያን አሉ፤ ወደፊትም ይኖራሉ። እንደነዚህ ስላሉት ሰዎች ቅዱስ ጴጥሮስም በመጨረሻው በዚህ ዘመን ብዙዎች ዘባቾች

  • የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ቅዳሜ ✅ ቀዳም ስዑር ✅ ዐባይ ሰንበት ✅ ቅዱስ ቅዳሜ 🌿 ለምለም ቅዳሜ

  • ቀዳም ስዑር የማይሞተው አምላካችን በፈቃዱ ቅድስት ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላካችን እኛን ያስነሳ እና ነጻነት ይሰብከን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ነጻ ሲያወጣ በአካለ ሥጋም ያለመለያየት በመቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ሙስና መቃብር ሳያገኘው ቆይቷል። ይህንን ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል"ነፍሱን በሲኦል አልተወም ሥጋውንም ሙስና መቃብርን አላየም መለኮቱ ከሁለቱም አልተለየም ሁለንተናው ከነፍስ ጋር በሲኦል ነበር። በሲኦል ለጻድቃን የምሥራችን አበሰረ፤ ሁለንተናው ከሥጋ ጋር በመቃብር ነበር እንጂ በቦታው ሁሉ ምሉዕ ነውና" (ሃይ. አበ ዘቄርሎስ ፸፩:፲፭-፲፮)   ለሁላችን የማያልፍ ድኅነትን ፣ ሥርየተ ኃጢአትን ፣ ቅድስናን ፣ አሸናፊነትን እና ይቅርታን ይሰጠን ዘንድ ሞታችንን ሞተ፤ የነገረንን ትንቢት ፈጸመ።" ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።" እንዲል። (ማቴ፲፪:፵) ጌታችን ከዐርብ ሠርክ እስከ እሁድ መንፈቀ ሌሊት ድረስ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በመቃብር ዐርፏል። እነዚህ ቀንና ሌሊት የራሳቸው ትርጉም አላቸው። የነገረ ክርስቶስ መጽሐፍ ጸሐፊ መጋቤ ሐዲስ ክቡር ዶክተር ሮዳስ ስለ ሶስት ምክንያት እንደሆነ ይጠቅሳሉ:- ፩. ለአዳም ፣ ለሔዋን ፣ ለሕጻናቱ ሊክስ ፪. ለሥጋ ፣ ለነፍስ ፣ ለደመ ነፍስ ሊክስ ፫. ሞትን ፣ ፍዳን ፣ ኃጢአትን ሊያጠፋ ጌታችን ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በመቃብር ዐርፏል። (ነ.ክርስቶስ ገጽ፻፸፰) ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር 3 ቀንና 3 ሌሊት አደረ፡፡ ይኸውም ነቢዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ እንዳደረው (ዮና 2÷1-2) ራሱም መድኅን ዓለም ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በ3 ኛው ቀን አነሣዋለሁ ብሏል፡፡ (ዮሐ2÷19-22 ) የተሰቀለ አርብ 6 ሰዓት ነፍሱን ከሥጋው የለየው አርብ 9 ሰዓት ወደ መቃብር የወረደ አርብ 11 ሰዓት የተነሣ ቅዳሜ ለእሁድ ሌሊት 6 ሰዓት ነው፡፡ ይህ 3 ቀንና 3 ሌሊት እንዴት ተባለ? ቢሉ የመጀመሪያው ብርሃኑን “ቀን” ጨለማውን “ሌሊት” በማለት የሚቆጠረው አቆጣጠር ነው፡፡ ይኸውም ሦስቱ ቀኖች:- 🕕 አርብ ከነግህ/ጠዋት እስከ ቀን 6 ሰዓት ብርሃን ነበር 🕘 ከ9 ሰዓት እስከ ሰርክ ብርሃን ነበር 🕛 ቅዳሜ መዐልት/ቀን ሦስቱ ሌሊቶች:- 🕕 አርብ ከቀን 6 ሰዓት እስከ ቀን 9 ሰዓት አምላክ በመስቀል ላይ ሳለ ጨለማ ሆነ 🕛 አርብ ለቅዳሜ ሌሊት 🕛 ቅዳሜ ለእሁድ ሌሊት ሌላው በእዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ዓርብ ሌሊቱን እሁድ ቀኑን ይስቡና ይቆጠራል፡፡ ይኸውም:- ሌሊቶቹ 1.ሐሙስ ለአርብ  2.  አርብ ለቅዳሜ 3.  ቅዳሜ ለእሁድ ቀኖቹ ደግሞ  1.  አርብ ቀኑን 2.  ቅዳሜ ቀኑን 3. እሁድ ቀኑን ቆጥሮ ነው፡፡ ጌታችን ቀድሞ አዳምን፤ ሔዋንን አርብ ፈጥሮ ቅዳሜ እንዳረፈ ሁሉ አሁንም ያጡትን ገነትን ባጡበት አርብ ዕለት ሰጥቶ ቅዳሜ በመቃብር አርፎባታል ስለዚህም የተለየች ቅዳሜ ናት። አራቱ ስያሜዎች፦ ፩. ቀዳም ስዑር ስዑር ማለት የግእዝ ግስ ሆኖ በአማረኛ የተሻረ ማለት ሲሆን በአንድ ላይ ሲነበብ የተሻረ ቅዳሜ የሚል ትርጓሜ እናገኛለን። ምክንያቱ እንደ ቀደመቺቱ ሰንበት የማናርፍባት ይልቁንም ደቀመዛሙርቱን አብነት አድርገን በጾም በሀዘን ህማሙን እያሰብንባት የምናሳልፋት ቀን በመሆኗ ቀዳም ስዑር ተብላለች። ፪. ዐባይ ሰንበት አምላካችን ሃያ ሁለቱን ስነ ፍጥረት ፈጥሮ እንዳረፈባት የማዳኑንም ስራ በመስቀል ላይ ፈጽሞ በአዲስ መቃብር ዐርፎ ውሎባታልና ዐባይ ሰንበት ተብላለች። ፫. ቅዱስ ቅዳሜ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ ነፍሳትን አድኖበታል ፣ ሲዖልን በዝብዟል ፣ ምርኮን ለራሱ ጨምሯል ፣ ዲያብሎስን አሳፍሯል ፣ የዕዳ ደብዳቤያችንን ደምስሷል ከሌሎች ቀናት ሁሉ የተለየች በመሆኗ ቅዱስ ቅዳሜ ተብላለች። ፬. ለምለም ቅዳሜ በዚህ ዕለት በኖኅ ዘመን የጥፋቱ ውኃ ማለቁን የሰላም አብሳሪ እርግብ ለኖኅ ቄጤማ እንዳመጣችለት አሁንም የጥፋቱ ሞት ራቀልን ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገርን ፣ አንቀጸ ገነት ተከፈተልን ሲሉ ካህናት አባቶቻችን የቅዳሜው የነግህ ጸሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ለምዕመኑ ለምለም ቄጤማ ስለሚሰጡ ምዕመናንም በግንባራችን ላይ አድርገን ትንሣኤውን ስለምናከብር ለምለም ቅዳሜ ተብላለች። "ዲያብሎስ ታሰረ ጌታ ተመረመረ"

  • 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ! ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ! (የይሁዳ ልጁና የልጅ ልጁም ይደምሰስ!) ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ! ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ! 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊

  • 🩸ኦ የማይሞተው ሞተ🩸 ኦ የማይሞተው ሞተ/፪/ ሔደ ቀራንዮ እየተጎተተ ወድቆ እየተነሳ እንዲያ እየቃተተ ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ/፪/ እጅ እና እግሩ ታስሮ ሄደ አደባባይ እየተገረፈ ታግሶ ስቃይ አለቀሰች ቁማ ድንግል ማርያም ተሰቅሎባት ልጇ መድኃኔዓለም አዝ--- በአይሁድ አደባባይ ፍርድ ተንጋደደ ወንበዴ ተለቆ ንፁህ በግ ታረደ የማይሞተው ሞተ ለሰው ፍቅር ብሎ ዋለ ቀራንዮ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ አዝ--- ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ስጋውን ለመኑ እንዲፈቅድላቸው ሄደው ከመስፍኑ ገንዘው ቀበሩት በአዲስ መቃብር{፪} ቅዱስ ቅዱስ ኃያል እያሉ በክብር{፪}    በሊ/መ ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

  • без подписи

  • የሰሙነ ሕማማት ዕለታት        ዓርብ ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡ የስቅለት ዓርብ ይባላል የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለም ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል።  (ማቴ 27፡35) መልካሙ ዓርብ ይባላል ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡ † 13ቱ ሕማማተ መስቀል 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይመውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድመረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋርመላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት) † ጌታችን ከ6-9 ሰዓት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት 1ኛ.ኤሎሄ ኤሎሄ ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ ማቴ.27፤46 2ኛ. እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ፡፡ ሉቃ.23፤43 3ኛ.አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራእሰጣለሁ፡፡ ሉቃ.23፤46 4ኛ.አባት ሆይየሚያደርጉትን አየውቁምና ይቅር በላቸው፤ሉቃ.2334 5ኛ. እናትህ እነኋት፤ እነሆ ልጅሽ፤ዮሐ.19፤26-27 6ኛ. ተጠማሁ፤ ዮሐ.19፤30 7ኛ. ተፈጸመ፤ ዮሐ.19፤30 † ጌታችን በመስቀሉ ከ6-10 ሰዓት በመስቀልላይ ሳለ የተፈጸሙ 7ቱ ተአምራት፤ 1ኛ. ፀሐይ ጨለመች 2ኛ. ጨረቃ ደም ሆነች 3ኛ. ከዋክብት ብርሃናቸውን ነሱ 4ኛ. የቤተመቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ 5ኛ. ዐለቶች ተሰነጣጠቁ 6ኛ. መቃብራት ተከፈቱ 7ኛ. የሞቱት ተነሡ፤ ማቴ.27፤45-46 5ቱ ቅንዋተ መስቀል ችንካሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ። 1. ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት 2. አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት 3. ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት 4. አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት 5. ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ(እብርቱ) አጣብቆ እንዲይዝ የተቸነከረበት ============================= ☞ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ መከራን ታገሰ ☞ሁሉን የያዘውን እርሱን ያዙት ☞ሁሉን የሚገዛውን እርሱን የአምላካችንን እጅ አሰሩት ☞ኃጥአትን የሚያስተሰርይ እርሱን ኃጢአተኛ አሉት ☞የማይገረፍ አምላክ እርሱን የሰውን ሥጋ በመልበሱ ገረፉት ☞እንደ መብረቅ የሚያንፀባርቀውን ነጭ ልብስ የሚያለብስ አምላክ እርሱን ቀይ ግምጃ አለበሱት። ☞በእሳት በተጋረዱ ዙፋን ላይ የሚቀመጥ እርሱን በመዘባበቻ ወንበር ላይ አስቀመጡት። ☞እንደ ድንኳን ሰማይን የዘረጋ እርሱን በመስቀል ላይ ሰቀሉት ☞የመላእክትን አለቆች በፊቱ በመፍራት የሚቆሙለት እርሱን በጲላጦስ ፊት አቆሙት ☞በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን እንደበደለኛ ተፈረደበት ☞ዓለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በሥጋው ሞተ በመለኮት ሕያው ሆነ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን! ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን!

  • ጉልባን እና ምሣሌው ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡ ❖ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡ ባቄላው ይከካል ቅርፊቱ ይላጣል ምሳሌውም የጌታችንን መከራ እና አይሁዳውያን ልብሱን አውልቀውት ነበር የዚያ መታሰቢያ ነው። ❖ በሊቃውንቱ ትምህርት ጉልባን ከስንዴ እና ከባቄላ ይዘጋጃል፤ ባቄላው ይታመሳል፣ ይፈተጋል፣ይከካል ስንዴው ግን አይከካም ፣ አይፈተግም፣ አይታመስምም ይኸውም ምሳሌነቱ ስለእኛ በተዋህዶ ለከበረው አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መታሰቢያ ነው። ማለትም ባቄላው የስጋ ስንዴው ደግሞ የመለኮት ምሳሌ ነው። ምንም እንኳን መለኮት ከሥጋው ያልተለየው አምላክ ቢሆንም ሕማሙ ግን መለኮትን አላገኘውም። የተዋህዶ መዶሻ የተባለ ቅዱስ ቄርሎስ እንዳስተማረው ነገረ ተዋህዶን በጋለ ብረት እንዳስተማረው ብረን ከእሳቱ ውስጥ ቢጨምሩት ብረቱ እሳቱን ይመስላል እሳቱም የብረቱን ቅርፅ ይይዛል ብረቱን ቢመቱት ይለዝባል የማይጨበጠው እሳትም ከብረት ስለተዋሀደ አንጥረኛው ይመተዋል እሳቱን ግን አያገኘውም። መለኮት የተዋሀደው ሥጋ መከራን ተቀበለ በሥጋም ሞተ ፤ ለመለኮት ግን ሕማም ድካም ሞት አይስማማውም፤ ይኸውም መለኮት ከሥጋው አንደተዋሀደ በነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ምርኮን ማረከ ነፍሳትን ነፃ አወጣ ገነትም አስገባቸው ፤መለኮት የተዋሀደው ሥጋ ወደ መቃብር ቢወርድም በሦሥተኛውም ቀን በታላቅ ኃይል በስልጣን ክርስቶስ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ። መልካም በዓል

  • без подписи

  • "ደብረ ዘይት" ለፍርድ ይመጣል አምላካችን ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን ለፍርድ ይመጣል አምላካችን ዋጋ ሊከፍል ለሥራችን በኃይል በስልጣን ይገለጣል የወጉትም ሁሉ ያዩታል ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን አንደበትም ሁሉ ዝም ይላል የተከፈተ አፍ ዲዳ ይሆናል መጻሕፍት ሁሉ ተዘርግተው ይገለጣል የሁሉ ሥራው ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን ዓለም በኃጢአቱ ይቀጣል የትዕቢቱ ኩራት ይሻራል ይዋረዳሉ ጨካኞቹ ይከበራሉ ትሁቶቹ ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን ለአሕዛብ ሊሆን ምሥክር የመንግሥቱ ወንጌል ሲነገር ቅዱሱ ወንጌል ይህን ብሏል ፍጻሜ ዘመን ያኔ ይሆናል ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን እንዲወጣ መብረቅ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ እንዲዘልቅ የጌታ መምጣት እንደዚህ ነው መንግሥትና ፍርዱ በእጁ ነው ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን እንጠብቀው ተዘጋጅተን ልባሞች ሆነን መብራት ይዘን አናውቅምና ቀኒቱን የሙሽራውን መምጫውን አናውቅምና ሰዓቱን የሙሽራውን መምጫውን ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን ©በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

  • ቅዱስ ጳዉሎስም “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸዉን እየለወጡ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞ ሠራተኞች ናቸው። ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለዉጣልና” ብሏል /2ቆሮ.11፥13-15/። ሐዋርያት ሁሉ በየመልእክቶቻቸው ከሐሰተኞች አስተማሪዎች እንድንጠበቅ ደጋግመው አሳስበዋል። ብዙ ሰው ግን በየዋሕነት ስለሚጓዝ የነዚህ ተኩላዎች ሰለባ ሆኗል። ጊዜው ክፉ ነውና የሐሰተኞች ነቢያት መረብ ጠልፎ ወደ ሐሰተኞች ክርስቶሶች እንዳይወስደን በጥንቃቄ መጓዝ ይጠበቅብናል። ሐዋርያዉ ቅዱስ ይሁዳም በመልእክቱ ቁ.3  “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ሲል እንደመከረን በተቀደሰ እምነታችን እስከመጨረሻ ጸንተን እንጋደል። በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫ እስከ ፍጻሜ -፪ኛ ጴጥ ፫፥፯-፲፭ -የሐዋ ሥራ ፳፬፥፩-፳፪ ምስባኩም፦ መዝ ፵፱፥፫ "እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ" "እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል" ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፬፥፩-፴፮

  • ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ እሑድ(ሳምንት) (የዐብይ ጾም እኩሌታ) ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:- ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሠረት ነገረ ምጽአቱን እንድናስታውስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነው። ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች ከፍሎ ጽፎልናል፡፡ ፩. ሃይማኖታዊ ምልክቶች "እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ" /ማቴ 24፥5/፡፡ ፪. ፖለቲካዊ ምልክቶች “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ” /ማቴ 24፥6/ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና” /ማቴ 24፥7/ ፫. ተፈጥሯዊ ምልክቶች “ረሐብም ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” /ማቴ.24፥7/ ከላይ ያየናቸውን ምልክቶች በዓለማችን ላይ ዕለት ዕለት የምናየው የምንሰማው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸውን ምልክቶች የቤተ ክርስቲያናችን አራት ዐይና ሊቃውንት የወንጌሉን ገጸ ንባብ እንዲህ ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ “እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸው” /ማቴ.24፥8/ ምጥ ሲመጣ አስቀድሞ የምጡ መጀመሪያ ሕመም (ጣር) እንዳለ ሁሉ የዓለምም ፍጻሜ በጣር ነው የሚጀምረው። ይህንንም ጌታችን በግልጽ አስረድቶናል፦ ጦርና የጦር ወሬ መሰማት፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሳት፣ ርሃብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መታየት ለዓለም ፍጻሜ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸዉ። እነዚህ ነገሮች በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ ላይከሰቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብዙ ዘመናት ታይተዋል፤ እየታዩም ናቸው። “ስለ ስሜ በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” /ማቴ.24፥9/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ስሜ ክርስቲያኖች በመሆናችሁ በዓለም ዘንድ ትጠላላችሁ" ብሎናል። ዓለም ክፉ ስለሚሠራ የጥሩ ነገር ተቃራኒ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። ጌታችን “ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፣ሥራዉም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” /ዮሐ. 3፥19-21/ እንዳለን በክፉ ሥራ ውስጥ ያለው ይህ ዓለም በጎ ሥራ የሚሠሩትን የክርስቶስን ተከታዮች ይጠላል። ጨለማ ብርሃንን ብርሃንም ጨለማን እንደሚጠላ፤ ይህ ዓለም እኛን እንዲጠላን፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ዓለም ልንጠላው ይገባል። አሁን ባለንበት ዘመን ክርስትና እየተጠላ፣ እየተናቀ ነው ያለው። “ባደጉት” ዓለማት ባዶ አብያተ መቅደሶች ቀርተው እነሆ እንመለከታቸዋለን፤ ትውልዱ በዓለም ስሜትና በሥጋ ፈቃድ ብቻ እየሔደ ነው። ክርስቲያን ነን በሚሉትም አውሮፓውያን ዘንድ የአንገት በላይ የማስመሰል ክርስትና እንጂ እንደ ቅዱስ ቃሉ የሚጓዝ አማኝ ማግኘት አይቻልም። እውነተኞች አይወደዱም፤ ይገፋሉ፤ ይናቃሉ። ሁኔታው የዘመኑ ፍጻሜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን በእርግጥ ያስረዳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም በላይ “ስለ ስሜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል” ብሏል። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ማንንም ሳይበድሉ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀገራት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን እስከ አሁን ድረስ እየተቀበሉ ነው፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ  “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” /ሮሜ 8፥36/ እንዳለው። ይህ በቅዱሱ በክርስቶስ ስም መጠላትና መከራ መቀበል ከዓለም የሚጠበቅ የፍጻሜዉ ዘመን ምልክት መሆኑን አውቀን መዘጋጀትና ከሐዋርያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” /ሮሜ 8፥37/ እያልን በእምነታችን ጸንተን መጋደል ይገባናል። የክርስቲያኖች ቁጥር እያነሰ መምጣት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ሰው ሰው የሚያሰኘውን ክብርና ሞገስ ትቶ በግብሩ እንስሳትን ሲመስል የቅድስና ሕይወት ሲጠላና ሲናቅ፤ በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ ለረከሰው ለዚህ ዓለም ምኞትና ፈቃድ ሲገዛ ስናይ የዚህ ዓለም ፍጻሜ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን አውቀን፤ ኖኅ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቢኖርም ራሱን በቅድስና ጠብቆ እንደኖረ /ዘፍ.6-8/፤ ሎጥም እንዲሁ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ሲኖር በነርሱ ኃጢአት እንዳልተባበረ /ዘፍ. 19/ ከዚህ ዓለም ክፉ ሥራ ተለይተን ራሳችንን በቅድስና በመጠበቅ እንጋደል። ዓለሙ ስለ እምነታችን ቢጠላንም እኛም ስለ ክፉ ሥራው ንቀነው መኖር የግድ መሆኑን እንወቅ እንጂ ስለ እምነት፣ ስለ ቅድስናም ከዓለም በጎ ነገር አንጠብቅ። በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርሱብንን ፈተናዎች ሁሉ በትዕግስት እንቀበላቸው እንጂ በማማረር አንዘን፤ ምክንያቱም ስለ ስሜ በዓለም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ተብለናልና። “የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል!” ማቴ.24፥15/ ዓለም ራሱን በማርከስ ብቻ ሳይወሰን በፍጻሜ ዘመን በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሳይቀር የጥፋትን ርኩሰት ያቆማል። የተቀደሰው ስፍራ የተባለው በተቀደሰ ሃይማኖት የሚኖሩትን ሀገራት፣ ሕዝቦች የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ዲያብሎስ በመልእክተኞቹ ላይ አድሮ በብዙ ርኩሰት ተፈታትኗቸዋል፤ እየተፈታተናቸውም ነው። የየሀገራቱን እምነትና ታሪክ ለማጥፋት ጥሯል፤ ብዙውንም የቅድስና ሥርዓት በርዟል፤ የቻለውንም ከነጭራሹ አጥፍቶታል። አሁን እንኳ አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምባቸዉ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክንያት የጥፋት ርኩሰት አዉጇል። ይህም የፍጻሜ ዘመኑ አንዱ ምልክት ስለሆነ አንባቢዉ ያስተዉል እንደተባለ የዘመኑን መፍጠን የጊዜውን መድረስ በመረዳት መዘጋጀት ይገባናል። “ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥11/፡፡ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመኑ ተነስተው እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን ታግለዋታል፤ ሊያጠፏት ባይችሉም እንኳን ብዙ ልጆቿን ነጥቀው ወስደውባታል። የነዚህን ሐሰተኞች ሠራተኞች አመጣጥ ከባድ የሚያደርገው በተአምራትና በድንቅ ምልክቶች መምጣታቸው ነው። ጌታችን እንደተናገረ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” /ማቴ.24፥24/ ስለዚህ በምትሐታዊ ምልክቶቻቸው የብዙ የዋሃንን ልብ በማታለል ከተቀደሰ እምነታቸው እያስኮበለሉ አጥፍተዋቸዋል፤ በማጥፋትም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ  “ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነዉ እንደሆነ መርምሩ”/1ዮሐ 4፥1-3/ አለን።

  • "መጻጉዕ" ሰው የለኝም ያለ በሰው የተረሳ፣ የዳነው መጻጒዕ ያዳነውን ረሳ። በአምስቱ እርከኖች በአዕማደ ሚስጥራት፣ ቤተ ሳይዳ ላለች ከመቅደስ ላኖርካት፣ በበደል ለምናዝን ምሕረትን ፍለጋ፣ በንሰሐ ማረፍ ከዐራተ ዝንጋኤ ከኃጢአት አልጋ።         አዝ= = = = = በጠበሉ ደጃፍ ለጸኑት የሚላክ፣ ለቀድሶተ ማይ የሚወርደው መልአክ፣ በመንገድ ጠብቆ ሞትን የሚያሳልፍ፣ ዛሬም ይድረስልን ቀድመው ከገቡት ጋር ነፍሳችን እንድታርፍ።         አዝ= = = = = አልጋው ተሸክሞት ደክሞ ለሚጨነቅ፣ አልጋን አሸክመህ ሕመም የምታርቅ፣ ደዌያችንን ነስተህ ቆስለህ የምትፈውስ፣ የመጻጒዕ ረዳት የነፍሳት መጠጊያ መድኃኒት ክርስቶስ።         አዝ= = = = = የባሰ እንዳያየው ቃሉን ያልጠበቀ፣ እጁን ሰዶ ጸፍቶ ከደዌው ታረቀ፣ 'ሰንበት የሻረ' ከሚሉት እንዳንውል፣ ለትንሣኤው ደስታ የሰንበትን ጌታ አርብን እንከተል።         በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

  • መጻጉዕ የዐብይ ጾም አራተኛ እሑድ(ሳምንት) መጻጉዕ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ላይ ታሪኩ የተጻፈው ለ፴፰ ዓመት አልጋ ላይ ተኝቶ የኖረ በቤተ ሳይዳ/በቤተ ዛታ ስፍራ ይዞ የመልአኩ መምጣት ፤የውሃው መባረክ፤ የውሃው መናወጥ እና ድኅነቱን በተስፋ የሚጠብቅ ግን ድኅነቱ በሳምንት አንዴ እርሱም አንድ ሰው ብቻ ስለሆነ የሚያገኘው ይህን እድል ማግኘት ያቃተው ተሸክሞ ወደ ውሃው የሚያደርሰው በተባረከ ጊዜ እንዲድን የሚያግዘው ሰው አልባ ህመምተኛ ነው። ጌታችንም ወደ ቤተ ሳይዳ መጥቶ የልቡን ሃሳብ ያውቃልና "ልትድን ትወዳለህን?" አለው ጌታችን መጻጉ የሚፈልገው ጠፍቶት ሳይሆን 'ሙሉ ሰው ነህና መስክር ፍላጎትህ ከአንደበትህ ይውጣ' በሚል ነው። ይህም ታማሚ እዛጋ ለብዙ ዘመን ያየው የነበረው በሰዎች ተረድተው ወደ ተቀደሰው ውሃ ገብተው ድነው ሲወጡ ነበርና ብቸኛ መሆኑን መዳን እየቻለ ግን ወደ ውሃው የሚያደርሰው ጎረምሳ ስለፈለገ "ሰው የለኝም" አለ። አንድም ጌታችን ገና የ፴ ዓመት ወጣት ነበርና 'ተሸክሞ ያደርሰኛል' ወይም ከርሱ ጋር ብዙ ሰዎች ነበሩና 'ሰው ቢያዝዝልኝ' በሚል ሰው የለኝም አለ። ጌታችንም "ለ፴፰ ዓመት አልጋህ አንተን ተሸክማለችና አሁን ተነስ አልጋህን ይዘህ ሂድ" አለው። ያላሰበው ደስታ አደናግሮት ማን እንደ አዳነው እንኳን ሳያውቅ ነበረ የተነዳው በዚህም ገጠመኝ በሰንበት ስራ አይሰራም የሚሉ አይሁዶች ያዙትና "እንዴት በሰንበት አልጋ ትሸከማለህ?" ብለው ያዙት ፴፰ አመት ሲተኛ ግን ማንም አልጠየቀውም።  "ያዳነኝ እርሱ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ" ብሎ መለሰላቸው። "ማን ነው ያዳነህ?" ይህ ምላሽ እርሱ ባይመልስም ለእነርሱ ግልጽ ነው በዛ ሰአት ከእርሱ ከመድኃኔዓለም ውጪ እንዲህ አይነት ተግባር የሚሰራ አነበረምና። መጻጉ በውስጡ ዘወትር ማን ነው ያዳነኝ የሚለውን ጥያቄ አንግቦ ጌታም በመቅደስ አግኝቶት "ኃጢአትህ ተሰርዮልኻል ግን ዳግመኛ ከዚ በላይ እንዳያገኝህ ደግመህ አትበድል" ሲለው ምስክር አይሉት ፈጥኖ ሄደና ለአይሁድ "ያዳነኝ እርሱ ነው" ብሎ ተናገረ። ሕማማተ መስቀል ላይ አባቶቻችን የጌታ ፊት በጥፊ ጸፍቶታል ይላሉ። ከ፴፰ አመት በላይ አልጋ ላይ የነበረውን "ከዚህ በላይ እንዳያገኝህ" ሲል  'ሲኦል እንዳትገባ ከዚ የከፋ ስቃይ እሳት እንዳያገኝህ ደግመህ አትበድል' ሲል ነው። እኛ ስንቶቻችን ዳግማዊ መጻጉዕን ሆነናል!?: በቤቷ ኖረን፣ የስጋችን ፈውስ ከፀበል ከእምነቱ ተደባብሰን ድነን፣ ለነፍሳችን ንስኃ ከአባቶች አግኝተን፣ ስጋውንም በልተን ደሙንም ቆርሰን ዛሬ ግን ከእርሷ ርቀን፣ በውሸት መስክረን ሁለተኛው ንጉስ ገንዘብን ያነገስን ዳግማዊ መጻጉ ሆነን የተገኘን! ዛሬ ካለው መከራ የባሰ የወደፊቱ የቆየው መከራ ሳያገኘን ሮጥ ብለን እንድናመልጥ አምላካችን ይርዳን። በዚህ ሳምንት መጻጉዕ ብቻ ሳይሆን ጌታችን በመዋለ ስጋዌ ዘመን ያዳናቸው ድውያን ሁሉ ይታወሳሉ። እኛም የስጋ የነፍስ በሽታ አለብንና እርሱ በቸርነቱ ይታደገን ይፈውሰን አሜን። በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -ገላ ፭፥፩ እስከ ፍጻሜ -ያዕ ፭፥፲፬ እስከ ፍጻሜ -የሐዋ ሥራ ፫፥፩-፲፪ ምስባኩም፦ መዝ ፵፥፫-፬ "እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ ወይመይጥሎቱ ኩሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣህለኒ" "እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል መኝታውን ሁሉ ለበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ" ወንጌሉም፦ ዮሐ ፭፥፩-፳፭