ቤተ አቡነ አብቢ መንፈሳዊ ሚድያ
Статистика🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/ortodx27 የቅዱሳን ታርካቸውን እንዘክራለን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡ ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ ለሃሳብ አስታየት @amanuelye21lij
- Последний пост
- 15 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 49
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ቅዱሳን አባቶቻችን "ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው" ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን፡፡ ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፎአል፡፡ ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው፡፡ (አረጋዊ ታዴዎስ)
በንጹህ ልብ እና በቅን ልቦና ለመኖር ምረጥ። ደግነት ምንም ዋጋ የለውም፣ ነገር ግን የአንድን ሰው ሕይወት ለዘላለም ሊለውጥ ይችላል። ከህመም እና ከጉዳት ይልቅ ተስፋን እና ከሐዘን ይልቅ ፈውስን የሚያመጣ ሰው ሁን። ቃላትህ እና ድርጊቶችህ በሌሎች ላይ ያላቸውን ተጽእኖ ሙሉ በሙሉ ላታስተውል ትችላለህ፣ ስለዚህ ጠባሳ ሳይሆን ምቾትን ትተው እንዲሄዱ ፍቀድላቸው። እያንዳንዱን ልብ ካገኘኸው በላይ በተሻለ ሁኔታ ተወው። Amari La
ትግሬኛ ወይም ኤርትራዊ ቋንቋ ምትችሉ አናግሩኝ ለትረካ ተፈልጋችሁ ነው
"ነገ ሐምሌ 9 ፃድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ናቸው። ሙት የሚስምሩ ፃድቁ አባታችን የሞቱትን ነፍስ ያስምሩልን።እኛንም ለንስሐ ሞት ያብቃን🙏💙
📘#ፃድቁ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ📕🌹 📌💫•••ወር በገባ በ 9 የጻድቁ አባታችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡ አባታችን የእስትንፋሰ ክርስቶስ ተአምር ይህ ነው ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ከእለታት በአንድ ቀን አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በዋሻ ውስጥ እየጸለዬ ሣለ ሰይጣን በመነኩሴ ተመስሎ ወደ እርሱ መጥቶ አንተ መነኩሴ ለአንተ ሰላምታ ይገባሃል በዚህን ዘመን አንቸንተ የሚጋደል መነኩሴ ማነው ማን አለ ብሎ በውዳሴ ከንቱ ለመግባት ቢሞክር ያን ጊዜ አባታችን እስትፋሰ ክርስቶስ በመስቀል ምልክት አማተበበት ወዲያውኑ እንደ ጢስ ተኖ እንደ ጉም በኖ ጠፋ አንድ አንድ ቀን እየመጣ ደቀ መዛሙርቱን ይፈትናቸው ነበር። ከዚህ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዱን መነኩሴ ይዞት ያሣብደው ጀመር ወደ መምህራችሁ አትውሰዱኝ እርሱ ያጠፋኛል ያሳድደኛልና አለ ደቀ መዛሙርቱም ይህን በሰሙ ጊዜ አሰረው ወስደው ከአባታችን ዘንድ አደረሱት ሰይጣኑም ለምን ታሳድደኛለህ በቤትና በእንጨት ሥር በተራራ ላይና በየኮረብታው በእንስሳና በሰው ላይ እዳላድር አሳደድከኝ ይል ጀመር አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስም ከፀሎት የትኛውን ትፈሩታላችሁ ብሎ ጠየቀው እርሱም መልሶ የምንፈራው በንፅህና ሆኖ የሚያገለግል ካህንን ነው ከመዝሙረ ዳዊት እግዚአብሔር በሰባ ዘመን ይነሣ ጠላቶቹም ከፊቱ ይበተኑ የሚለውንና ኪዳናትን ወንጌልን ስመ ሥላሴን ይህን ከሰማን አፍረን ከሰው ላይ ፈርተን ተንቀጥቅጠን ሸሽተን እንሄዳለን አለው። ያን ጊዜ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም የጸለየበትን ውኃን ረጨው አንተ እርኩስ መንፈስ ውጣ እነሆ አወገዝኩህ በሐዋርያት ሥልጣን የተለየህ ሁን አለው በዚያን ጊዜ እንደተናገረው ወጥቶ በኖ ሄደ አነደገና ታላቅ ድንጋይ ተሸክሞ መጥቶ አጥፍቻለሁና ይቅር በለኝ ማረኝ አለው አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስም ለተንኮል አመጣጡን አውቆበት ሄደህ ከገደሉ ወደታች ቁልቁል ወረወረውና ወስዶ ከገደሉ በታች ቁልቁል ዘቅዝቆ ሰቅሎ በጸሎቱ አሰረው ሰይጣንም በእዚሁ በገደል መካከል ተሰቅዬ የምኖረው እስከመቼ ድረስ ነው ብሎ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጠየቀው አባታችን እስተንፋሰ ክርስቶስም አምዬሀለሁ አሰርኩህ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን አወገዝኩህ ከገደሉ በላይ ልጆቸ ካሉበት አትውጣ ከገደሉም አትውረድ ፈጣሪዬ ክርስቶስ እስኪመጣ ድረስ በዚሁ ኑር ብሎ ገዘተው ፈጣሪዬ ክርስቶስ እስኪመጣ ድረስ በዚሁ ኑር ብሎ ገዘተው ያም ሳይጣን እስከ ዛሬ ድረስ በገደል መካከል ተሰቅሎ ይኖራል እንደዚሁ የሚዋጉንን አጋንንትን ፈፅሞ እስከ መጨረሻው በጸሎቱ ይሠራቸው ያጥፋቸው በእውነት ያለ ሐሰት ይደረግልን። (ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ) ☞https://t.me/Orthodoxtewahdoc
видео или голосовое, без подписи
📕#አቡነ_ብፁእ አምላክ ያደረጉት ተአምር🌹📘 📘•••ወር በገባ በ9 ታስበው የሚውሉ የአባታችን የአቡነ ብፁዐ አምላክ ታአምር ይህ ነው፡ ልመናውና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ከአቡነ ዮሐንስ በኃላ በተሾመው በአባ ሠረቀ ብርሃን ዘመን ወደ ደብረ ቢዘን ከአባቱና ከወንድሞቹ ጋር በገባ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምረው ዘንድ ለአባ ጴጥሮስ ተሰጠ፡፡ ☞የትምህርት ቤት ለጆች ወንድሞቹ ቀኑበት፡፡ ለምን ከእኛ ጋራ እየተማረ እንደ እኛ አይፈጭም አሉ፡፡ አባ ጴጥሮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ብፁዐ አምላክ ሆይ እዳያዝኑብህ እንደ ወንድሞችህ የምትፈጨውን ውሰድ አለው፡፡ ☞የዋህ የሆነ ብፁዐ አምላክም እሺ አምላክህ በጸሎትህ ያስችለኝ አለ፡፡ የሚፈጨውንም ወሰዶ ተኛ በነቃም ጊዜ ተፈጭቶ አገኘው እግዚአብሔር አመሰገነ ለሰውም አልተናገረም፡፡ ☞ለብዙ ጊዜ እንዲህ በሆነበት ጊዜ ጓደኞቹ የተማሪዎች አለቃ ከፈጩት ዱቄት የሚሰጠው አለ ብለው ተጠራጠሩ፡፡ እስኪ መጣም ሦስት ሦስት ሁነን እንጠብቅ ከመካከላችን ነቅቶ እህል ወስዶ ዱቄትን የሚሰጠው አለ አሉ፡፡ ሦስት ሦስት ሁነው ሲጠብቁ የፈጭታዎች መንቂ ደረሰ፡፡ ☞የእየራሳቸውንም ሊፈጩ እሳትን አበሩ፡፡ የብፁ አምላኮ እህል ግን ተፈጭቶ አገኙት፡፡ ተደንቀውም አትናገሩ፡፡ ሁለትኛ ሦስተኛ እንዲህ የሚሆን እንደሆነ እንይ አሉ፡፡ እንዲህም ሆነ፡፡ በምሽት በየተራቸው ለብፁ አምላክ የተከፈለውን እህል ያስቀምጣሉ፡፡ ☞ ሦስት ሦስት ሁነውም ይጠብቃሉ፡፡ በነቁም ጊዜ ተፈጭቶ ያገኙታል፡፡ ከዘህ በኃላ ለመምህሮቻቸው ተናገሩ፡፡ ☞እነሱም እንደ ልጆች አድርገው ሦስት ሦስት ሆነው ጠበቁትና ሥራውን እንግለጥበት አሉ፡፡ ግን ሥራውን አስትተን የቤተ ክርስቲያን ተልኮና መጻሕፍትን ማንበብ እናዝዘው አሉ፡፡ ☞እሱም ጌቶቼ በመፍጨቴ ካልተደስታችሁ ምግብ ማብሰል ወይም ሌላ ሥራ የወደዳችሁን በቤተ ክርስቲያን ምልከታ ላይ እና መጻሕፍትን ማንበብን እዘዙኝ አላቸው፡፡ ☞ውሃ መቅዳትን አዘዙት፡፡ አባታችንም ብፁዐ አምላክ ቀድቶ ሊሸከም ባነሣው ጊዜ ውሃው ከራሱ ላይ አንድ ክንድ ከፍ ከፍ አለ ይህን አይተው አደነቁ፡፡ ☞ዳግመኛ ዕንጨትም ሊለቅም ሄደ፡፡ በጸሎት ሰዓት ሊጸልይ ሲቆም ዕንጨቶች የሚበቃውን ያህል ይሰበሰቡለታል፤ ሊሸከምም ሲያስር አንድ ክንድ ከራሱ ላይ ከፍ ከፍ አለ፡፡ ]ወደ ኀላ ባለጊዜም ሊጠብቁት ወንድሞቹ ተመለሱ፡፡ ይህንንም አይተው አደነቁ መክረንም እስክናዝዝህ ድረስ ታገስ አሉት፡፡ ብሩክ ሁን መንፈስ ቅዱስ እንደሰየመህ ብፁዕ ሁን አሉት፡፡ ]☞የብጹ አቡነ አምላክ ወዳጆቹን እግዚአብሔር በጸሎቱ ይቅር ይበላቸው ለዘላለሙ አሜን፡፡ ☞(ገድለ አቡነ ብፁዐ አምላክ) ☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ ☞ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ቤተሰብ ይሁኑ
видео или голосовое, без подписи
📌#ቅዱስ_ዞሲማስ_ጻድቅ_ማን ነው⁉ 🌹ወር በገባ በ9 የቅዱስ ዞሲማስ ወርኀዊ በዓሉ ነው📕 ❖ይህም ጻድቅ ከፍልስጥዔም ሰዎች ወገን ነው፤ ወላጆቹም ደጋጎች ክርስቲያኖች ናቸው ይህንን ጻድቅ በወለዱት ጊዜ አምስት ዓመት አሳደጉት፤ ከዚያም የቤተክርስቲያን ትምህርትን የሃይማኖትንም ምሥጢር ሕግና ሥርዓትንም እያስተማረ እንዲያሳድገው ለአንድ ሽማግሌ መምህር ሰጡት። ❖ ያ ሽማግሌም ተቀበሎ ልጁ አደረገው ትምህርቱንም ሁሉ አምላካዊ ጥበብ ሃይማኖትንም አስተምሮ አመነኰሰው ዲቁናም አሾመው በበጎ ሥራም አደገ ትሩፋት መሥራትንም አበዛ እግዚአብሔርንም ሁል ጊዜ ያመሰግነዋል በቀንና በሌሊትም መጻሕፍትን ያነባል፤ ሥራ ሲሠራ ሲበላም ቢሆን ሁል ጊዜ ከአፉ ምስጋናዎችን አያቋርጥም፤ በዚያ ገዳም አርባ አምስት ዓመት በተፈጸመለት ጊዜ ቅስና ተሾመ ተጋድሎውንም ጨመረ። ❖ ከዚህ በኋላም እየተጋደለና አገልግሎት በመጨመር በቅስና ሹመት ዓሥራ ሦስት ዓመት ሲሆነው በዘመኑ ካሉ ተጋዳዮች ሁሉ እርሱ በገድሉ ከፍ ከፍ እንዳለ ተቃራኒ ጠላት ዲያብሎስ በልቡ ክፉ ሀሳብ አሳደረበት በልቡም ከበጎ ሥራ እኔ ያልሠራሁት የቀረኝ አለን ይል ጀመር፤ ነገር ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልተወውም መልአኩን ልኮ በዮርዳኖስ ወንዝ አቅራቢያ ወደ አለ ገዳም ይሔድ ዘንድ እንጂ፤ ያን ጊዜም ተነሥቶ ሔዶ ወደዚያ ገዳም ደረሰ በገድላቸው ፍጹማን የሆኑ ዕውነተኞች አገራውያንን አገኘ እርሱ ከእርሳቸው እንደሚያንስ አወቀ እርሱ በዓለም ውስጥ ነው የኖረውና ስለዚህ ከእርሱ ይሻላሉ። ❖ በዚያ ገዳም ከሳቸው ጋር ኖረ ብዙ ዘመናትም አብሮአቸው ሲጋደል ኖረ፤ ለዚያ ገዳም መነኰሳትም ልማድ አላቸው ታላቁ ጾም በደረሰ ጊዜ የመጀመሪያውን አንድ ሱባዔ በአንድነት ይጾማሉ በቅድስት እሑድ ሥጋውንና ደሙን ይቀበላሉ በማግሥቱም ሰኞ ጥዋት ሃያ ስድስተኛ መዝሙር እግዚአብሔር ብርሃነ ረድኤቱን ሰጥቶ ያድነኛል የሚያስፈራኝ ምንድነው የሚለውን እሰከ መጨረሻው እየዘመሩ ይወጣሉ በሚወጡም ጊዜ ወደ በሩ ተሰብስበው በአንድነት ጸልየው እርስ በርሳቸው ሰላምታ ይሰጣጣሉ የገደሙ አበ ምኔትም ይባርካቸዋል። ❖ ከዚህም በኋላ እየአንዳንዱ ወደ በረሃ ይበተናሉ አንዱም አንዱ ባልንጀራውን ያየ እንደሆነ እንዳያየው ወደ ሌላ ቦታ ይሔዳል፤ ቅዱስ ዘሲማስም በየዓመቱ ከሳቸው ጋራ ወጥቶ በበረሀው ውስጥ ይዘዋወራል የሚጽናናበትንም ይገልጥለት ዘንድ እግዚአብሔርን ይለምነው ነበር፤ ሲዘዋወርም በበረሀ የምትኖር ግብጻዊት ማርያምን አገኘ ከእርሷም በልጅነቷ ወራት በእርሷ ላይ እንዴት እንደሆነና በበረሃም የሆነውን ኑሮዋን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተረዳ። ❖ ከዚህ በኋላም በሁለተኛው ዓመት ሥጋውንና ደሙን ያመጣላት ዘንድ ፈለገች እንዳለችውም አደረገላት፤ ለዚህም ጻድቅ ብሔረ ብፁዓን ይገባ ዘንድ ተገባው እርሱም ገድላቸውን ጻፈ ሥራቸውንና ጽድቃቸውን ገለጠ፤ ዘጠና ሦስት የሚሆን መላ ዕድሜው በተፈጸመለት ጊዜ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። አርኬ ✍️ ሰላም ለዞሲማሰ ሶበ ጸለየ ወአበተብቍዐ። መጠነ ዓመታት አርብዓ። ብሔረ ብፁዓን በዊአ አምሳለ ማቴዎስ ቦአ። ኵሎ በሀየ እንተ ነጸረ ወሰምዐ። በውስተ ዓለም ከመ ይስብክ ወጽአ። https://t.me/Orthodoxtewahdoc
видео или голосовое, без подписи
🌹#ቅዱስ_አቡነ_ቶማስ_ዘመርዓስ ማን ናቸው⁉📘 ☞•••📕ወር በገባ በ 9 የሐዋርያው የአባታች አቡነ ቶማስ ዘመርዓስ ወርሐዊ መታሰቢ ነው፡፡አባታችን አቡነ ቶማስ የመርዓስ ሀገር ኤጲስ ቆጶስ ሲሆን ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሃይማኖት ምግባራቸው እጅግ የቀና ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ✞ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖቹን ሲያመቃዩ በነበረበት ወቅት ከንጉሡ መኳንንት አንዱ ወደ መርዓስ ሄዶ አቡነ ቶማስን በጭፍሮቹ አሲያሳቸው፡፡ ✞አባታችንን እንደያዟቸው ደብድበው በምድር ላይ እየጎተቱዋቸው ደማቸው እየፈሰሰ ወሰዷቸው፡፡ መኩንኑ ለአማልክት ስገድ አላቸው፡፡ አቡነ ቶማስም ከእግዚአብሔር በቀር የሚሰግዱለት አምላክ የለም አሉት፡፡ መኩንኑም እጅግ የበዙ ጽኑ ሥቃዮችን አሠቃያቸው፡፡ ❀የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በሰውነታቸው ላይ እንዲሁም በአፍና በአፍንጫቸው ጨመሩባቸው፡፡ ቶሎ እንዲሞቱ ሳይሆን በሥቃይ ሆነው እንዲቆዩ በማድረግ ለ22ዓመታት በጨለማ ውስጥ እያሰሩ አሠቃዩአቸው፡፡ ከሃዲያኑ በየዓመቱ ወደ እስር ቤቱ እየገቡ አንዱ አካላቸውን ይቆርጣሉ፡፡ ✞እጅና እግራቸውን በየተራ ቆራረጧቸው፡፡ አፍንጫቸውን ከንፈሮቻቸውን ጆሮዎቻቸውን ሁሉ በየተራ እየቆረጡ ለ22ዓመታት ጣዖታቸውን ሲያጥኑበት ኖረዋል፡፡ ☞አንዲት ደግ ክርስቲያን ሴት ግን የተጣሉበትን ጉድጓድ አይታ ሰለነበረ በድብቅ ሌሊት እየሄደች ትመግባቸው ነበር፡፡ ✞ደገኛው ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ይህች ሴት ሄዳ ስለ አቡነ ቶማስ ነግራችውና አባታችንን ከተጣሉበት ጉድጉድ አወጣቻቸው፡፡ ☞ቆስጠንጢኖስ የከበሩ 318ኤጲስ ቆጶሳትን በኒቅያ አገር እንዲሰበሰቡ ሲያደርግ አንዱ አቡነ ቶማስ ነበሩ፡፡ ☞ወደ ጉባዔውም ሲሄዱ ደቀ መዛሙርቶቻቸው በቅርጫት አድርገው በአህያ ጭነው ወደ ጉባኤ ኒቂያ ይዘዋቸው ሄደዋል፡፡ በመንገድም ሳሉ ዐላዊያኑ አግኝተዋቸው አህዮቻቸውን ሌሊት ራስ ራሳቸውን ቆርጠው ጣሉባቸው፡፡ ✞አቡነ ቶማስም ራሳቸው የተቆረጡትን አህዮች አምጡልኝ ብለው የጥቁሩን አህያ ራስ ከነጩ፥ የነጩን አህያ ራስ ከጥቁሩ ገጥመው ቢባርኳቸው ሁሉም አህዮች አሞት ተነሥተዋል፡፡ ☞ከጉባኤ ሲደርሱ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጽድቃቸው ዐውቆ አባቴ በረከትዎ ትድረሰኝ በማለት በዐላዊያኑ የተቆራረጠ አካላቸው ዳሶ ተባርኳል፡፡ ☞አቡነ ቶማስ ዘመርዓስ ከሌሎች ኤጲስ ቆጶሳት ሆነው አርዮስ መክረውና አሰብ ተምረው እምቢ ቢላቸው አውግዘውት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ወዲያው ነሐሴ 24 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ☞(መዝገበ ቅዱሳን) ☞የሰማዕቱ የጻድቁ የአባታችን የቶማስ ዘመርዓስ የጸሎታቸው በረከት እና ምልጃ አይለይን፡፡ ☞https://t.me/Orthodoxtewahdoc
видео или голосовое, без подписи
ሰይጣንም ተንኰሉ በከሸፈበት ጊዜ በደጋጎች መነኰሳት ተመሰለ ሊአስቱትም ወደርሱ ሔዱ በመስቀል ምልክትም በማተበ ጊዜ አፍረው ተበተኑ ። የዕረፍቱም ሰዓት በቀረበ ጊዜ ቀድሞ ተገልጸውለት የነበሩ እነዚያ ሦስት ሰዎች መጥተው ገድሉን ጻፉ ባረፈ ጊዜም ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ዕብል ለብእሲ ምእመን። እንተ ይሰመይ ኅልያን። ከመ ግዕዘ ምስለ ሠለስቱ ዕዶው ኅብረ ፀዓዳ ልቡሳን። ያብርህ ሎቱ በውስተ መጽልም መካን። እምበትረ እዴሁ ወጺኦ መስቀል ዘብርሃን። ፨፨፨ =>በዚችም ቀን የመብራጣንና የቀፈሐላ ኤጲስቆጶስ የንድራኦስ መታሰቢያቸው ነው የግብጻዊው የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሴ ቤት ነው። ዳግመኛም ከአባ ኤሲ ጋራ በሰማዕትነት የሞቱ የአምስት ሽህ አምስት መቶና የአራት ጭፍሮች መታሰቢያ ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። =>የቅዱሳን አምላክ ለእኛም የአባቶችን ረድኤት ይላክልን:: =>ሐምሌ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ ኅልያን ገዳማዊ 2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር) 3.ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት 4.ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ (በንስሃ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች) =>ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) 3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) =>+"+ ጌታ ኢየሱስም "አትግደል: አታመንዝር: አትስረቅ: በሐሰት አትመስክር: አባትህንና እናትህን አክብር: ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ" አለው:: ጐበዙም "ይህንማ ሁሉ ከሕጻንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ:: ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?" አለው:: ጌታ ኢየሱስም "ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሒድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ:: መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ:: መጥተህም ተከተለኝ" አለው:: +"+ (ማቴ. 19 ፥ 18) ፨፨፨፨ ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ፨፨፨፨ ( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።) ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ ፱ † ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት(ዘሐምስቱ አሕጉ) =>አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዘጠኝ በዚች ቀን የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ዲዮቅልጥያኖስም በካደና ጣዖትን በአመለከ ጊዜ ምእመናንን ያሠቃዩአቸው ዘንድ መኳንንቱን ወደ ሀገሮች ሁሉ ላከ። ለጣዖትም እንዲሰግዱ ያስገድዷቸው ነበር። ✞ ስሙ ፍላጦስ የሚባል አንድ መኰንንም ወደ አፍራቅያ አገር መጣ። በዚህም ቅዱስ ለክርስቲያን ወገን መምህር እንደ ሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ ለአማልክት እንዲሠዋ አዘዘው። ✞ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትተን ጣዖት ማምለክ አይግባንም። መኰንኑም በውኑ አርጤምስንና አጵሎንን አርዳሚስንም ሌሎች አማልክትንም ያይላቸዋልን ሌላ ነውን አንተ ይምትናገርለት አምላክ ካለ እነዚህስ አማልክት አይደሉምን አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም መልሶ አዎን አማልክት አይደሉም ክብር ይግባውና ከአንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም እርሱም ለፍጥረቶች ሁሉ ፈጣሪያቸው ነው አለው። ✞መኰንኑም ኃይለ ቃል ስለመመለሱ ተቆጥቶ አርባ ቀን በግርፋትና በስቅላት በእሥራትና በመንኰራኲራት እንዲአሠቃዩት አዘዘ። እርሱ ግን ትእዛዙን አልሰማም ከሥቃዩም የተነሣ አልፈራም። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ለቴዎድሮስ ዘተሠፍዎ አባለ። አርብዓ መዋዕለ። በዝንቱ ኲሉ ድኅረ ተጋደለ። ወሶበ ሐመ በመዋቅሕት ወበዕለት ዘበሰይፍ ተቀትለ። በመንግሥተ ሰማይ አድምዐ ወነሥአ አክሊለ። ፨፨፨ ✞ ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት ✞=> በዚችም ቀን ከቆጵሮስ አገር ቅዱስ ታኦድሮስ በሰማዕትነት አረፈ ከእርሱም ጋራ ሣስት ሴቶችና ያሠቃዩት የነበሩ ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ አረፉ። ይህም እንዲህ ነው ይህን ቅዱስ ወደእነዚህ መኰንኖች በከሰሱት ጊዜ እርሱ ክርስቲያንና የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ እንደሆነ ሰምተው ወደ እነርሱ አቀረቡት ስለሃይማኖቱም ጠየቁት። እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመነ በበትሮችም እየደበደቡና እየገረፉ ቀጡት እርሱም እየዳኸ ሒዶ ጣዖቱን ረገጠው ከመንበሩም ላይ ገልብጦ ጣለው። እሊህ ሁለቱ መኳንንትም ተቆጥተው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ ጨውና ኮምጣጣ ነክረው ፋቁት እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበረ። ሁለተኛም ምላሱን ቆረጡት። ያን ጊዜም በዚያ ከነበሩ ሴቶች አንዲቱ ምላሱን አንሥታ ወሰደች። ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንንትም አይተው አደነቁ። ሉክዮስም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ያን ጊዜም መኰንኑ ድግናንዮስ ተቆጥቶ ከቅዱስ ታኦድሮስ ኋላ ይከተሉ የነበሩ ሦስት ሴቶችን ገደላቸው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ታኦድሮስ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ዎፍ በርረው ሔዱ ድግናንዮስም አደነቀ ሉክዮስም የክርስቲያን ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች አስረዳው ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። ከዚህም በኋላ ሁለቱ መኰንኖች ከቆሮንቶስ አገር በመርከብ እስከ ቆጵሮስ ሔዱ በዚያም ክርስቲያኖችን ሲአሠቃያቸው ሌላውን መኰንን አገኙ ሉክዮስም ከድግናንዮስ ተሠውሮ በመኰንኑ ፊት ቆመ የጣዖታቱንም መንበር ገለበጠ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረው። ከዚህም በኋላ ድግናንዮስ በመኰንኑ ፊት ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ይህንንም በሰይፍ ራሱን ቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ፨፨፨ አርኬ ሰላም ዕብል ለታኦድሮስ ጽኡር። ዘዘበጥዎ በበትር። ወዘፈሐቁ ቊስሎ በአጽርቅተ ጸጒር። ወሰላም ለክልኤ መኳንንተ ጥበብ ወምክር። ወምስለ ሠላስ አንስት ዘሎቱ ማኅበር። ፨፨፨ +"+ አባ ኅልያን ገዳማዊ +"+ =>በዚችም ቀን መስተጋድል አባ ኅልያን አረፈ። የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ዲስጣ የእናቱ ስም ካልሞና ነው የአገሩም ስም ዐይነ ፀሐይ ይባላል። እርሱም ቀድሞ በወጣትነቱ ጊዜ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር በሥራውም የተመሰገነ ነው። በአንዲት ቀንም ከዐረብ አገልጋዮች አንዲት ሴት መጥታ ለጆሮዎቿ ጉትቻ እንዲሠራላት ለመነችው ከሠራላትም በኋላ የሠራበትን ዋጋ ከእርሷ ፈለገ። በፊቱም ራሷን ዘንበል አድርጋ ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም አለችው። ይህንም በሰማ ጊዜም አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ ፊትሽንም አታሳይኝ አላት። ከዚህም በኋላ ሞትና ፍርድ መኖሩን ለነፍሱ እያሳሰባት በማደሪያው ውስጥ ጥቂት ቆየ። ተነሥቶም ለድኆችና ለችግረኞች ገንዘቡን መጸወተ ከገንዘቡም ከፍሎ ለእናቱ ሰጥቷት ተሰናበታት። ለሦስት ቀን የሚበቃውንም ስንቅ ይዞ ወደ ገዳም ሔደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ንጽሕና ስለ አየ መራው የራቀውን ቦታ ወደ እርሱ አቀረበለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻም በአንዲት ቀን ደረሰ። ቆሞ ሳለም ነጭ ልብስ የለበሱና እንደ ፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኰዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለት አነቁትና ከእሳቸው ጋራ ወሰዱት ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት። በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ ከሰገደበትም ራሱን ቀና ባደረገ ጊዜ ከእርሳቸው ያገኘው አልነበረም በመለየቱም አዘነ አለቀሰም። ከዚህም በኋላ ከአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየበላ ውኃም ከርሷ እየጠጣ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ። ወደ ቦታዎችና ወደ ዋሻዎች ለመሔድ የፈለገ እንደሆነም በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር። የረዘመውንም መንገድ ትጠቀልልለት ነበር ልብሱም ከእነዚያ ዛፎች ቅጠል ነበር። የተረገመ ሰይጣንም ተጋድሎውን በአየ ጊዜ ሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ሔደ እንዲህም ብሎ ነገራቸው በእገሌ በረሀ የተሠወረ ገንዘብ አለ የሚጠብቀውን ከያዛችሁት ታገኛላችሁ ወደዚያ ወንዝ ማዶም መርቶ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ መሻገሪያ መንገድ አጡ። እጅግም ተጠምተው ነበርና ውኃውን እያዩ ወደ ውኃው መድረስ ተሳናቸው። ሁለተኛም በሚያስፈራ ዘንዶ ተመስሎ ቅዱስ ኅልያንን ውኃ ሲጠማቸው አንተ ለባልንጀሮችህ እንዴት አትራራም እንዴትስ ውኃ አታጠጣቸውም አለው በዚህ የሚይዙት መስሎት ነበርና። ለቅዱስ ኅልያንም በአውሬ አንደበት እግዚአብሔር የዘለፈው መስሎት ውኃ ቀዳላቸው ያጠጣቸውም ዘንድ ተሻገረ። እነርሱም ድኃነቱን አይተው ራሩለት ልብስ ሊሰጡትም ወደዱ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም ወደ በዓቱም ተመለሰ።
видео или голосовое, без подписи
"" ጻድቃንን ከኀጥአን ጋር አታጥፋ "" (ዘፍ. ፲፰:፳፫) "በዓለ ሥላሴ፥ ወጻድቅ አብርሃም ወአባ ጊዮርጊስ" (ሐምሌ 7 - 2015) ዲ/ዮርዳኖስ አበበ /ገብረ መድኅን ገብሩ ለቅዱስዳዊት ንጉሠ እስራኤል ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር። " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
#ጻድቁ_አባታችን_አባ_ኪሮስ "ወር በገባ በ8 መታሰቢያቸው ነው በ8 ዓመታቸው ያላቸውን ገንዘብ ትተው ምድራዊውን ሳይሆን ሰማያዊውን ጊዜያዊ የሆነውን ሳይሆን ዘላለማዊውን የእግዚአብሔርን መንግስት ሽተው ወደ አባ በብኑዳ ገዳም ገብተዋል። እስከ 17 ዓመታቸው ረድዕ ሆነው እያገለገሉ ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩ፤ ከተረዱ በኋላ የምንኩስናን ማዕረግ ተቀብለዋል። ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እንዲሁም ስለ ሰው ልጆች ይቅርታ 40 ዓመት በመሬት ላይ ተኝተው ስጋቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ ሣር እስኪበቅልባቸው ድረስ ጸልየዋል። ጌታችንም ስለ መታመናቸው እና ስለ ተጋድሏቸው አክብሯቸዋል ። 👉 ቃል ኪዳናቸውም ፦ ልጅ ለሌላት መኻኒቱ ፣ በገድላቸው ብትባረክ ፣ ጸበላቸውን ብትጠጣ፣ በጻድቁ ምልጃ ቃልኪዳን ፤ እንደ እግዚብሔር ምህረት እና ቸርነት ልጅ ታገኛለች። ታህሳስ 8 በዓለ ልደታቸው ሐምሌ 8 ቀን በተወለዱ በ 270 ዓመታቸው አርፈዋል። የጻድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ ምልጃና በረከታቸው አይለየን 🙏🙏🙏 አሜን አሜን አሜን በቅንነት ቴሌግራም ይቀላቀሉ https://t.me/Orthodoxtewahdoc
видео или голосовое, без подписи
✞#አርባዕቱ_እንስሳ ማለት⁉ ♨ወር በገባ በ8 ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣ 📌እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው። የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል። የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም። ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት። የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ። ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል። በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው። እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል። ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው። ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ። በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ። ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና። ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና። https://t.me/Orthodoxtewahdoc
видео или голосовое, без подписи