ኦርቶጲያ
Статистикаበዚህ ቻናል በኪነ ጥበብ እያዋዛን ሀሳብ እንለዋወጣለን ። ግጥም ✍️ ወግ✍️ አጫጭር ልቦለዶችን✍️ ጥቅሶችን🌉 ለእናንተ በማጋራት መልዕክቶቻችንን የምናስተላልፍበት አውድ ነው ። ቤተሰብ እንዲሆኑ ጋብዘኖታል ይቀላቀሉ... ስራችሁን ማጋራት የምትፈልጉ @sg2124 ላይ ይላኩ።
- Последний пост
- 25 июл.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 122
- 1/48двое суток
- 139
- 1/72трое суток
- 150
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ህፃን ነው ያልጠና ሲመዘን በስጋ እግዜር ቢገልጥለት የእምነቱን ዋጋ ተነሳ ሊገልጠው የአምላኩን ስራ ክርስቲያን ነኝ አለ ቅንጣትም ሳይፈራ ድምፁ ቢያስገመግም ቂርቆስ መች ታወከ ውሃው መድረክ ሆኖ አምላኩን ሰበከ የእምነት መምህሩ ዜናዌ ሐዲስ መድረኩ ላይ ቆመ ጉባኤ ሊቀድስ ✍ኤርሚ ግርማ
без подписи
ቀናኢ ለአምላኩ መስጠት እስትንፋሱ የተራበን ማብላት ቢሆንበት ሱሱ ድንኳኑ ይጨነቃል ካልያዘ እንግዳ ቤቱ ነበረና የመጣው ሰው ጓዳ . . የሐሰት አባቷ በክፋት ተነስቶ፣ ምን ቢዘጋጅ ወጥመድ የልቦናው ቅናት ሥላሴን ጋበዘ፣ ቤቱ እንዲስተናገድ እንደ አምላኩ መሰጠት ቢሆን ሁሌም ግብሩ የአብርሃም ተብለው ሥላሴም ተጠሩ! ✍ኤርሚ ግርማ
ልብሳቸው ሙት ቀስቃሽ ዓለምን ያበሩ እምነት እንዲለማ ደማቸውን ዘሩ ✍ኤርሚ ግርማ
የበርሃው ኮከብ መንገድ የሚያቀና አዋጅ የሚናገር ስለወንጌል ዜና መንግስቱ ቀርባለች ከሃጢያት ተፋቱ ዓለሙኒ ወንበረቱኒ ሃላፊ ውእቱ . . የብዙዎች ደስታ ክብሩ ከፍ ያለ ስብከት የጀመረ በማህፀን ሳለ ከዓለም ሳይሰማ ክብሯን ሰው ሳየነግረው መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶት በደስታ አዘለለው ከዓለም ሳይቀዳ ክብሯን አስተማረን እንደ እሷ ንፅህት ዘር የለም ከሠው ወገን ✍ኤርሚ ግርማ
ውዳሴ ወግናይ ለእመ ዐዶናይ እሷ ብቻ ንግስት በምድርም በሠማይ
መኖሬ ጨለመ ስሆን እናት አልባ በሙት ልጅ ደጋፊው በሚካኤል ጠባ ሚካኤል የሚሉ ብዙ እናቶች ሲያልፉ አደራ ይወስዳል ሊያስድግ በእቅፉ ለሰው ልጆች ታዛዥ ለእውነት የሚወግን ከአምላኩ ፊት ቆሞ ምህረት የሚለምን ዓለም ሞት ስትደግስ ምስኪኑን ለትገድል ምህረት ይመጣል በሚካኤል በኩል ጎሳ ብሔር አይመረጥ ሲቀበል አደራ ማሳደግ ነው ግብሩ ከፊት እየመራ ✍ኤርሚ ግርማ
ሠው ሠውን ረግጦ ሰውነቱን ካበ የሠው እንቡጥ አጭዶ ለራሱ አበበ በእንባ ዲኮር ደምቀው፣ ጮቤ እየረገጡ ስለ ዛሬ ብለው ስንቶች ነገን ሸጡ አልታይ ቢላቸው የመኖር መሐሉ በማያቁት ነገ የሠው ቀብዲ በሉ መሐሉ ሰፊ ነው አለው ብዙ ጓዳ መሐሉ ሞት አለው የሚከፈል እዳ ሰዉ ምን ሆኖ ነው? የማይቀር እያለ ለሚቀር የተጋ ምንስ ተረግመን ነው? ነፍሳችንን ትተን የሞትን ለስጋ . . ዐዋቂው የሠው ልጅ፣ ብዙ ተመራምሮ ክፋትን አሰላ የልፋቱ ውጤት ይኸው ደምቆ ታየ አንገት እየቀላ ግብራችንን አይቶ እግዜሩ ቢከፍለን ሰማይ እሳት ተፍቶ ዶግ አመድ ባረገን ✍ኤርሚ ግርማ
እጠብቅሀለሁ || በመምህር እዮብ ይመኑ Memihir Eyob Yimenu ምኩራብ ✍️ መልካም ዕለተ ሰንበት 🥰 ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ የምስጋና አባይ(-ጠብቆ ምድራዊው መላዕክ ያሬድ አባ ዓራራይ የኦርቶዶክስ እምነት የምስጋና ቋንቋ የምድር መድመቂያ የሰማይ ቤት ስንቋ ... መሠረተ አኮቴት መሠረተ ዜማ ምስጋናን የቀዳ ከመላዕት ከተማ የፅዮን ደስተዋ ያሬድ ጥዑመ ልሳን የሠማዩን ድግስ በአንተ በኩል በላን ✍ኤርሚ ግርማ
ጊዜ ምን ሆኖ ነው?ፍሬው ቀነጨረ ሠው ባበቀለ ግንዱ አውሬ አዘረዘረ ✍ኤርሚ ግርማ
#ልደታ_ለማርያም_🥰🥰🥰 ልደታ ለማርያም ልደታ ለድንግል አራት ነጥብ እርሷ ለዘረ አዳም ትግል ነሐሴ 7 ምሰ ፅንሰቷ አሀደ ግንቦት ገፀ ልደቷ ማርያም ! ቀጥቅጦ ጥሎታል ፍጥረቷ ጨለማን ከውልደቷ አንስቶ ማን ብርሃን ቀማን አለፍነው ወበቁን ተመርኩዘን እርሷን ድኅነት ተቀበልን ነክተነው ቀሚሷን ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ዓለም ከቅዱስ ማህፀንሽ ፈራ መድሃኒዓለም ምሩጠ ፍጡራን የእግዚአብሔር ስጦታ የመንግሰተ ሰማይ ሰፊ ንፁህ ቦታ . እሷ ብቻ ዓለም እሷ ብቻ ሰማይ እሷ ብቻ ብርሃን እሷ ብቻ ፀሐይ አጣጥማ ማታውቅ የደስታ ልኩን ትወልጃለሽ ሲላት አሜን! መልዓኩን ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ ባሪያ ነኝ ለአምላኬ ከገፁ ነውና የተቀዳው መልኬ ስትል ተቀብላ እሳት የታቀፈች ልደታ ለማርያም ንፅይት ተወለደች ! 🥰✨ልደታ ለማርያም✨🥰 [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#ልደታ_ለማርያም_🥰🥰🥰 ልደታ ለማርያም ልደታ ለድንግል አራት ነጥብ እርሷ ለዘረ አዳም ትግል ነሐሴ 7 ምሰ ፅንሰቷ አሀደ ግንቦት ገፀ ልደቷ ማርያም ! ቀጥቅጦ ጥሎታል ፍጥረቷ ጨለማን ከውልደቷ አንስቶ ማን ብርሃን ቀማን አለፍነው ወበቁን ተመርኩዘን እርሷን ድኅነት ተቀበልን ነክተነው ቀሚሷን ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ዓለም ከቅዱስ ማህፀንሽ ፈራ መድሃኒዓለም ምሩጠ ፍጡራን የእግዚአብሔር ስጦታ የመንግሰተ ሰማይ ሰፊ ንፁህ ቦታ . እሷ ብቻ ዓለም እሷ ብቻ ሰማይ እሷ ብቻ ብርሃን እሷ ብቻ ፀሐይ አጣጥማ ማታውቅ የደስታ ልኩን ትወልጃለሽ ሲላት አሜን! መልዓኩን ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ ባሪያ ነኝ ለአምላኬ ከገፁ ነውና የተቀዳው መልኬ ስትል ተቀብላ እሳት የታቀፈች ልደታ ለማርያም ንፅይት ተወለደች ! 🥰✨ልደታ ለማርያም✨🥰 [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
ጣዕረ ሞት ተሰይሞ የነፍስ ሲቃ ገዝፎ በዓለም ምህረቲቱ ተወለደች የአዳም ተስፋው እንዲፈፀም ግንቦት የወር ንጉስ ግንቦት የቀን ጀንበር በአንተ ተገለጠች አማናዊት የፀሐይ በር የመላዕክት እህት የመድሃኒት ሙዳይ ይኸው ተወለደች ማርያም አርዓራይ ... የተረገመ የተዋረደው የሰው ልጅ እንዲከበር ተወለደች መርገም ያልነካት ንፅህይት ዘር አፍጣኒተ ረድኤት የተዋህዶ ትምክህት የስላሴ ምስጢር ማርያም ርህሪት ... ሽርጉድ በምድር ሽርጉድ በሰማይ ስትወለድ ድንግል እሙ ለአዶናይ የጭንቅ ቀን የምትገላግል ተወለደች አንዲት ድንግል!! ❤️❤️❤️ ✍ ኤርሚ ግርማ
ንጉሱ አወጀ ክርስቲያን ነኝ ማለት ነውር እንደሆነ ለጊዜው ቢሆን በሆዳም አማኞች እውነት ተሸፈነ ክርስትና ከስሞ አምለኮተ ጣዖት በዓለሙ ናኘ በጨለማው ሰፈር ክርስቲያን ነኝ የሚል ፣ አንድ ሰው ተገኘ በስጋ አዋቂዎች መሳሪያ አዘጋጁ ስጋን የሚገድል ስለ አምላኩ ቆመ ስጋውን የካደ ፣ ጊዮርጊስ መስተጋድል ... ጠቢባነን ያሉ ስንት ችንካር ሳሉ የማይሞትን እውነት በመጋዝ ሊገድሉ ስንቱ ክርስቶስን ክዶ ስጋውን ሲሸልም ጊዮርጊስ ይዞ ፀና'የማይሞተውን ስም ... ዓለም በአንድ ሆኖ ታጋለ ተዋህዶን ሊጥል የአምላኩን ስም ይዞ ረታ!ጊዮርጊስ መስተጋድል የጊዮርጊስን ክብር ሊያዳፍኑ ሰዎች ዝም ቢሉ ዛፎች አፍ አውጥተው ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ አሉ ... መክብበ ሰማዕት የልዳው ገናና ጠማማ ስጋዬን በምልጃህ አቅና ✍ኤረሚ ግርማ
ወሠን አልባው ትህትናሽ፣ልቆ ቢገኝ ከፍጥረቱ የትዕቢት ልጅ ተቃጠለ፣ሰይፍ ሆንሽበት ለህይወቱ ህይወት ወልደሽ ብትሰጭን፣የሞት ዕዳን የሚከፍል ጠላት ግብሩ መለፍለፍ ነው፣ዝም ማለት ስለማይችል! ✍ኤርሚ ግርማ
ስሟን ጠርቼ ብዙ ተቀብያለሁ ፤ ስሟን ጠርቼ ብዙ ሸኝቻለሁ ፤ ስለ ስሟ ለብዙ ምያለሁ ፤ ስለ ስሟ እምነት ተቀብያለሁ የደረስኩለት ፣ የሮጥኩለት ፣ በስሟ ላይተወኝ ቃል የገባልኝ ሁሉ ሲሸሽ አንድ እሷ ቀረች..... ✨ በህይወት ዘመኔ ብሆን የሰው መሀን አንቺ ከእኔ ጋር ነሽ እናቴ እመ ብርሀን ✨ ባትኖሪልኝ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር ...አልቅሼ እንኳን ዳግም ምስቀው ባንቺ ነው [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
ግብሩ ነው መታመን አለቃ በራማ የምስራችን ቃል ለእናቱ ያሰማ ዓለም ለገፋቸው ሀቅን ለተቀሙ የእንባቸው ጠበቃ ገብርኤል ነው ስሙ ፍሱሐ ገፅ ያለው የአምላክ ምስጢረኛ ገብርኤል ፈራጅ ነው የምስኪኖች ዳኛ ✍ኤርሚ ግርማ
ክርስቶስ ተንሥአ ሙታን በአብይ ኃይል ወስልጣን ነቅተህ ስትፈልገን ከበረትህ ታጣን ! አሰሮ ለሰይጣን አጋዞ ለአዳም ዐለቱ ልባችን ፍቅርህን አይረዳም ! ሰላም እምይዜሰ ነፍስ እንዳልነበረ እንደዛ ያለቀሰ ! ማረኙ ይቅርና ከመቅደስህ ደጃፍ የለም የደረሰ . ኮነ ፍስሐ ወሰላም ተቋጨ ሰቆቃ ስጋ እየደለበ ነፍስ ለእስር በቃ ደስታ ነው ብንባል በበዓለ ሀምሳ ተደሰቱ ያለው ክርስቶስ ተረሳ [ ጥሩቤል ] እየጠፋን ነው እናስተውል ! @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
✝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሓ ወሰላም "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና" ፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን። ✝ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ✝ ዲ/ን የአብስራ https://t.me/God2929