ከአላህ ጋር - مع الله
Статистика"የህይወት ግብህ የአላህን ውዴታ ማግኘት ይሁን 🤍" ,,ربِّ أدعوك أنَّ تُلهمني ثباتًا لاتدكّه معاول الزمانِ،، ለሃሳብ አስተያየት☺️👉 @Nesr_A2
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 45
- 1/48двое суток
- 51
- 1/72трое суток
- 55
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እንዴት አዳራችሁ የአላህ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን ለራሳችሁ የሆኑ ሰዎችን ብቻ ተጠባባቂ ያላደረገ ህይወት ፍጠሩ። ዓለም ሲከብዳችሁ ነፍሳችሁን የሚመልሱላችሁ ነገሮች ይኑሯችሁ ዳጋግማችሁ የምትሉት ዚክር የምትጠጉበት መጽሐፍ መናገር ያቀታችሁን የምታፈስሱበት ብዕር ከሰማይ ስር የሚደረግ ረጅም እግር መንገድ በአላህ ፍጥረት ላይ ማሰላሰል እረፍታችሁን የምትመልሱበት ሶላት ጸጥታውን የምትወዱት ጠዋት በእጆቻችሁ የምትሠሩትና አሁንም መፍጠር እንደምትችሉ የሚያስታውሳችሁ ሙያ ህይወት ከአንድ ሰው የልብ መቆያ ክፍል የበለጠ ሰፊ መሆኗን የሚያስታውሳችሁ በዛፎች መካከል የሚደረግ ሽርሽር ወይም ከራሳችሁ ውጪ ሌላ ነገር እንድትሆኑ የማትጠየቁበት ትንሽ ቦታ ይኑራችሁ። ብቸኝነታችሁን ባዶነት ሳይሆን ከራስ ጋር የሚደረግ ውብ ግልለኝነት ዝምታችሁን ጭንቀት ሳይሆን ምታስቡበትን የሌሎች ሰዎችን መራቅ ደግሞ ከራሳችሁ ጋር እንደገና የምትገናኙበት እድል ማድረግን ተማሩ። አንድ ሰው ብቻ የደስታችሁን ቁልፎች በሙሉ እንዲይዝ አታድርጉ ሳታውቁት ህይወታችሁን የመክፈት ወይም የመዝጋት ጉልበት ትሰጡታላችሁና። ሰዎች ይቀየራሉ ልቦች ይገለባበጣሉ እስከ ህይወት ፍጻሜ ይቀጥላሉ ብለን ያሰብናቸው መንገዶች ባልተሳሰብነው መታጠፊያ ላይ ሊያበቁ ይችላሉ የምንወዳቸውም ሰዎች ሊሄዱ ይችላሉ ይህም ውዴታቸው ሀሰት ስለነበር ሳይሆን ውብ ነገሮች አላፊዎች ሆነው ስለተፈጠሩ ነው። የአንድ ሰው መሄድ ከራሳችሁ እንድትርቁ አያድርጋችሁ። መራቅና መለየት መሰረታችሁን እንዳይነቀለው በራችሁ ራሳችሁን ሙሉ ማጣት ወደ ባዶነት እንዳይቀየር ከራሳችሁ ጋር ታረቁ ከምንም በላይ ደግሞ ልባችሁን ከአላህ ጋር እሰሩ ፊቶች ቢቀያየሩ እንኳ በውስጣችሁ የማይቀየር አቅጣጫ ይኖራል። ለራሳችሁ ብዙ የህይወት ደጆች አበጁ የእውቀት ደጅ የውበት ደጅ የዒባዳ ደጅ የወዳጅነት ደጅ የሕልም ደጅ የብቸኝነት ደጅ እና የተስፋ ደጅ። በአንድ ደጅ ላይ ብቻ የተገነባች ህይወት ያ ደጅ ሲዘጋ ዓለም ያበቃ ይመስላታልና። በነፍሱ ውስጥ ትርጉም ያላቸው ከተሞችን የገነባ ግን በእንግድነት የሚመጣ መራቅ አያፈርሰውም ሊያዝን ሊናፍቅ ሊያልቅስ ይችላል ነገር ግን ወደራሱ ይመለሳል ከዚያም ጉዞውን ይቀጥላል። ለራሱ ሀገር መሆንን ያወቀ ሰው አንድ ሰው በራቀ ቁጥር አባት እንደሌለው ልጅ ተናግቶ አይቀርምና። ሁሌም ለራሳችሁ ምርጥ ወዳጅ ሁኑ 😊
باسمك بدأت، وبك أستعين! ✍ ...የት እንደሚኬድ፣ ምን እንደሚደረግና እንዴት እንደሚዳን ለመለየት የሚያዳግት አስቸጋሪ ወቅት ላይ ነን! እርግጥ ነው.. የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ሁለቱን የህይወት ብርሃን (ቁርአንና ሀዲስ) ትተዉልን አልፈዋል። የነገሮች መፍትሄ ሁሉ ከሁለቱ ምንጮች ይቀዳ ነበር። ነገር ግን መአበሉ በረታ፣ ፈተናዉ በረከተ፣ ዱንያ ድሯን አደራችብን፣ የዲን ለዛ ጠፋብን፣ ሀሞታችን…
باسمك بدأت، وبك أستعين! ✍ ...የት እንደሚኬድ፣ ምን እንደሚደረግና እንዴት እንደሚዳን ለመለየት የሚያዳግት አስቸጋሪ ወቅት ላይ ነን! እርግጥ ነው.. የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ሁለቱን የህይወት ብርሃን (ቁርአንና ሀዲስ) ትተዉልን አልፈዋል። የነገሮች መፍትሄ ሁሉ ከሁለቱ ምንጮች ይቀዳ ነበር። ነገር ግን መአበሉ በረታ፣ ፈተናዉ በረከተ፣ ዱንያ ድሯን አደራችብን፣ የዲን ለዛ ጠፋብን፣ ሀሞታችን ፈሰሰ፣ ሞራላችን ተሰባበረ፣ አእምሯችን ዋለለ። ሩብ ክፍለ ዘመን አሳልፈናል፤ ዳሩ ግን ሁኔታችን እያደር ወደታች፣ እያደግን ወደ ትንሽነት፣ እየበዛን ወደ ጥቂትነት.. ሆነ ነገሩ!! ታዲያ ወደ አላህ እንጂ ወደ ማን ይከጀላል! አንተዉ ድረስልን ብሎ ከሱ ፊት መዋደቅ እንጂ ሌላ ምን መፍትሄ ይኖራል! ጌታየ! የእኛ ድክመት እያደር ጨምሮ፣ የፈተናው አቅም ደግሞ እለት ከእለት እየበረታ ማንነታችንን ሰባብሮ ሳይጨርሰዉ አንተዉ ድረስልን። አንተ ካላሳየኸን ማየት አንችልም። አንተ ካልመራሃን የትም አንደርስም። አንተ ካላّሰማሃን መስማት አይሆንልንም። ~ የአሁኑ ዘመን ፊትና በምቾት ቀጠና ዉስጥ ተብትቦ አቋምን የሚሸረሽር፣ ያለ አንዳች ተግባር እድሜን የሚጨርስ፣ ሀብት የበዛበት ስግብግብነት የነገሰበት፣ የስሜት ባርነት የገነነበት፣ የመረዳትን ኃይል የሚገድል፣ የማወቅን ፍላጎት የሚያከስም፣ የቱን ረግጠህ የቱን እንደምትዘል ለይተህ ለመጓዝ የሚያስቸግር ዉስብስብ የፊትና ዘመን ነዉ። ~ ደህና ነኝ እያልክ በቁም የሚቀብር፣ ሰላም ነኝ እያልክ ሰላም የሚያሳጣ፣ በሌለ ተግባቦት እንደተግባባህ የሚያስመስል፣ በዉድቀት አካሄድ እድገትን የሚያስመኝ፣ ተጨባጭና ምኞት ያልተጣጣሙበት፣ እቅድና እዉነታ የተራራቁበት፣ ሀሜትና ምክር የተደበላለቁበት፣ የቃላት ዶፍ ዘንቦ የተግባር ጠብታ የጠፋበት፣ የአጥፊ ስህተት በሌላ ጫንቃ ላይ የሚጫንበት ዘመን። ~ ጌታየ አንተዉ እንደፈጠርከን ገደብ በሌለው ጥበብና ችሎታህ ነገራችንን አሳምርልን። ትናንት .. በዚያ ቅን ትዉልድ ወቅት ነገሩ ሁሉ የተቃና፣ የተባረከ፣ የተቀደሰና የፀዳ ነበር። በመካከላቸዉም የአለሙ እዝነት [ታላቁ የረህመት ሰው] ነበሩ። ግራ የገባው ሰዉ ወደሳቸው ሃሳቡን ያቀርባል። ችግሩን ይተነፍሳል። ለሱ የሚገባዉንና የሚመጥነውን መፍትሄ ያገኛል። በወህይ ተርቢያ፣ በሀዲስ ኩትኮታ፣ በነቢዩ መሪነት፣ በተግባር ፍሬ የደመቀ ታላቅ ክፍለ-ዘመን። አሁንማ .. ነገሩ ሁሉ የቀን ጨለማ፣ መድሃኒት ያልከው መልሶ በሽታ፣ መፍትሄ የተባለው እንደ አሮጌ ጨርቅ በአንድ ጎኑ ሲሰፋ በሌላ ጎን የሚቀደድ ሁኖብናል። ያ አላህ ! ‛ወህነን ዓላ ወህን’ የሆነ ነገር። አላህ በረህመቱ ያካብበን🤲
. ብርታት ሀዘን ሲበረታ በህይወት ኮረብታ መራመድ ሲከብደን የተረታን ለታ መከራው ሲጠና ሲመታን በአጠና ህይወት ብርቱ ሆና ሲከበን ፈተና ሃሉ አልሆን ብሎ ሲሄድ ግራ ግራ ጭንቁ ሲያጥነን ሲጠና መከራ አንዳች ነገር እመን ወዳጄ አደራ ዩስራ እንዳለልህ ከመከራ ጋራ ዳግም እንስቃለን በሙሉ ልባችን ያለምነው ተሳክቶ በብርቱ ጌታችን ተስፋ አትቁረጥ…
. ብርታት ሀዘን ሲበረታ በህይወት ኮረብታ መራመድ ሲከብደን የተረታን ለታ መከራው ሲጠና ሲመታን በአጠና ህይወት ብርቱ ሆና ሲከበን ፈተና ሃሉ አልሆን ብሎ ሲሄድ ግራ ግራ ጭንቁ ሲያጥነን ሲጠና መከራ አንዳች ነገር እመን ወዳጄ አደራ ዩስራ እንዳለልህ ከመከራ ጋራ ዳግም እንስቃለን በሙሉ ልባችን ያለምነው ተሳክቶ በብርቱ ጌታችን ተስፋ አትቁረጥ በራህማኑ ጌታ ካንተ ጋር ነውና በየ ሁሉም ቦታ አብዝተህ ተጠራ ከሰበቡ ጋራ ይሾመሃልና ከመጅቡሮች ተራ አይዞን ኡኸያ መከራን ያለየ በህይወት ፈተና ዓለሙ ያልጋየ ከዚያም ያልሶበረ በውስጥ ህመሙ አይገበውም ፍፁም የሀያት ትርጉሙ አብሽር በመልካሙ ሁሉ እስኪሞላ ይሰጥሃል አላህ ሚትሸውን ሁላ ቸርስ አይደለ ወይ እሱ ያንተ መውላ 🥹 እሱን ብቻ ከጅል ጠይቀው ከለላ ማን አለህ ሚረዳህ ከሱ ውጭ ሌላ ?
አንድ ቀን ምን ማን እንደሆንክ ሁሉም ይረሱሃል እያንዳንዱ ቀን ደግሞ ወደዛች ቀን እየገፋህ ነው አታይም ጨልሞ ሲነጋ ሰዖቶች ተባዝተው የተወሰነልህን እድሜ ሲበሉት! ሰዎች ሁሉ በረሱህ ግዜ የማይረሰው አላህ እንዳይረሳህ አደራህን አሁን አስታውሰው وَٱذْكُرِ ٱسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا 🤍
без подписи
ዩሱፍ ቢን አስባጥ እንዲህ ይላል:- «ሱፍያን አስ-ሰውሪይ አላህ ይዘንላቸውና የዒሻን ሶላት ሰግደን እንደጨረስን፡ "እጅ መታጠቢያውን (የዉዱእ ዕቃውን) አቀብለኝ ልታጠብበት" አሉኝ። እኔም አቀበልኳቸው። ዕቃውን በቀኝ እጃቸው ያዙ ግራ እጃቸውን ደግሞ በጉንጫቸው ላይ አደረጉ። ከዚያም እኔ ተነሥቼ ሄጄ ተኛሁ። ፈጅር ሲወጣ ወደ እሳቸው መጣሁና" አባ አብደላህ ሆይ! ፈጅር ወጥቷል" አልኳቸው። እቃው አሁንም በቀኝ እጃቸው እንዳለ ነው ግራ እጃቸውም በጉንጫቸው ላይ እንደተደገፈች ናት! እሳቸውም "ዕቃውን ካቀበልከኝ ጊዜ ጀምሮ እስከዚች ሰዓት ድረስ ስለ አኼራ ሳስብ አደርኩ" አሉኝ🥺።» (ምንጭ፦ 📚አል-ዑዘማእ አቢ አሽ-ሸይኽ አል-አስበሃኒ – 1/318) በእርግጥም ሱብሐነላህ! አላህንና የመጨረሻዋን ዓለም በማሰብና በመፍራት ልባቸው ሙሉ በሙሉ የተጠመደ አስደናቂ ሰዎች ነበሩ።
سبحانك
без подписи
ባስተውል ዙሪያዬን የለም የጎደለኝ ረህማን ችሮታህ ነው ደግፎ ያቆመኝ ችሎ ማይቆጠር ደርሶ ማይነካ የትየለሌ ነው የስጦታህ ድካ በእዝነትህ ጥላ ስነቃ ተኝቼ ያነሰኝን የማይ ያለኝን ዘንግቼ የቆጡ ሚያጓጓኝ ይዤ በጉያዬ ባዶ እጄን የቀረሁ የያዝኩትን ጥዬ
без подписи
٫٫وكان في وجهه رضي الله عنه خطان أسودان من البكاء ،، 📚الزهد للإمام أحمد(١٢١/١) የተቅዋ እምባ ጎርፉ የቆፈረው መንገድ አውጥቶ ሲፈስ ያጦቀረው ሁለት መስመሮች ከፊቱ ነበረው https://t.me/rabiyessr
ሁሉም ይጓዛታል ያቺን የሩቅ ጉዞ የለለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ አይቻል ነገር ከጥሪው መቅረት መሄዱ ግዳጅ ነው የተጠሩ ለት እንዴት ሆኖ ይሁን የቀብሬ ነገር ብቻዬን ስገባ ከሙታን መንደር መልካም ስራ የለኝ ሚሆነኝ ጓደኛ ወየውልሽ ነፍሴ የኔ መከረኛ ቀጣዩ አንቺ የጉዘው ተረኛ ስንቅሽን አጥብቂ እርሙን ተንጠቀቂ ጌታሽን ተዛዢ ስሜትሽን ራቂ አሻፈረኝ ብለሽ እብሪተኛ ከሆንሽ ቀብርሽ የገባሽ ለት ልክሽን ታውቂያለሽ አሁን ነው መቶበት ወደ አላህ መመለስ አሁን ነው መቾኮል ጀነትን ለመድረስ እያለሽ ካልሆነ ከሞትሽማ ቀረ ቁጭት ብቻ ሆኖ ውስጥሽ እያረረ ቁርኣን ይዘክርሽ በሱ ተመከሪ ከደጋግ ባሮቹ ኋላ እንዳትቀሪ ጌታሽን አክብሪ ትዛዞቹን ስሪ ነፍስ ሆይ አደራ አኺራሽን ፍሪ
السباق الحقيقي ليس سباقَ مالٍ ولا جاهٍ ولا شهرة، بل سباقٌ نحو الجنة، نحو رضا الله ودار الخلود كل ما في الدنيا من عملٍ، أو علمٍ، أو طموحٍ، أو سعيٍ للرزق إنما هو وسيلة لتعينك على هذا السباق. فالعاقل من جعل كل خطوةٍ في حياته طريقًا إلى الجنة، وسعى بقلبه قبل جسده، لا يُنافس الناس على دنيا زائلة! { وَسَارِعُوۤا۟ إِلَىٰ مَغۡفِرَةࣲ مِّن رَّبِّكُمۡ وَجَنَّةٍ عَرۡضُهَا ٱلسَّمَـٰوَ ٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ أُعِدَّتۡ لِلۡمُتَّقِینَ }
:
ሥራህን ኢባዳህን ማሳነስና ዝቅ አድርገህ ማየት ከፈለግክ አላህ በአንተ ላይ የዋለልህን ጸጋዎች አስብ ከአንተ በፊት የነበሩ ደጋግ ሰዎች ያደረጉትን የሥራ መጠን አስተውል አስተንትን አላህ በወንጀሎች ላይ የሚሰጠውን የቅጣት መጠን አስብ። አላህ በአደም ዐ.ሰ ላይ ያንን ያደረገው (ከጀነት ያወጣቸው) አንዲት ፍሬ ብቻ በመብላታቸው ነው አላህም «አደምም ጌታውን አመፀ ተሳሳተም» ብሏል። ኢብሊስም ከዚህ የዓቢድነት ቁንጮነት የተረገመና የተባረረ ሰይጣን የሆነው አንዲት ሱጁድ ለማድረግ እንቢ በማለቱ ምክንያት ነው። በተጨማሪም የቅዳሜን ሕግ እንዲያከብሩና ከማጥመድ እንዲከለከሉ ተነግሯቸው ሳለ በቅዳሜ ቀን ዓሳ በማጥመዳቸው ምክንያት አላህ ወደ ዝንጀሮ ቀይሯቸዋል። ስለዚህ የጀነትን ድሎት መንግሥቷንና ክብሯን በጥልቀት አስብ። እነዚህን ሁሉ ስታስብና ስታስተነትን እውነተኛ ማንነትህን ታውቃለህ ሥራህንም ዝቅ አድርገህ ታያለህ እንዲሁም የአላህ እዝነትና ይቅርታ ካልሸፈነህ በቀር ሥራህ ብቻውን ምንም እንደማይጠቅምህና እንደማያድንህ ትረዳለህ
መስጠት የማታቅ ከሆነ የህይወትን ጣዕም አታቃትም ።
መስጠት የማታቅ ከሆነ የህይወትን ጣዕም አታቃትም ።
قال الامام الآجري رحمه الله : فَإِنْ قَالَ قَائِلٌ: فَعَلَى مَا أُجَاهِدُ نَفْسِي حَتَّى أَغْلِبَهَا؟ قِيلَ لَهُ: تُجَاهِدُهَا حَتَّى تَلْزَمَ أَدَاءَ فَرَائِضِ اللَّهِ عز وجل، وَتَنْتَهِيَ عَنْ مَعَاصِيهِ. فَإِنْ قَالَ: صِفْ لِي مِنْ أَخْلَاقِهَا الَّتِي تَمِيلُ إِلَيْهِ مِمَّا لَا يَحْسُنُ، حَتَّى أَحْذَرَهَا، وَأَمْقُتَهَا، وَأُجَاهِدَهَا، إِذَا عَلِمْتُ أَنَّ فِيهَا شَيْئًا مِنْ تِلْكَ الْخِصَالِ. قِيلَ لَهُ: إِنَّ النَّفْسَ أَهْلٌ أَنْ تُمْقَتَ فِي اللَّهِ عز وجل، وَمَنْ مَقَتَ نَفْسَهُ فِي ذَاتِ اللَّهِ عز وجل رَجَوْتُ أَنْ يُؤَمِّنَهُ اللَّهُ عز وجل مِنْ مَقْتِهِ، كَذَا رُوِيَ عَنِ الْفُضَيْلِ بْنِ عِيَاضٍ كان الْفُضَيْلَ بْنَ عِيَاضٍ، يَقُولُ: «مَنْ مَقَتَ نَفْسَهُ فِي ذَاتِ اللَّهِ عز وجل أَمَّنَهُ اللَّهُ عز وجل مِنْ مَقْتِهِ» قَالَ أَبُو بَكْرٍالآجري: فَإِنْ قَالَ قَائِلٌ: فَبَيِّنْ لِي أَخْلَاقَهَا الْقَبِيحَةَ. قِيلَ لَهُ: هِيَ الْأَخْلَاقُ الَّتِي قَدِ اسْتَوْطَنَتْهَا النَّفْسُ، وَلَيْسَ تُحِبُّ مُفَارَقَتَهَا، وَهِيَ أَخْلَاقٌ كَثِيرَةٌ إِذَا تَصَّفَّحَ الْإِنْسَانُ نَفْسَهُ وَجَدَهَا كَذَلِكَ. فَإِنَّهَا نَفْسٌ مُتَّبِعَةٌ لِلْهَوَى. مُنْهُمِكَةٌ فِي لَذَّةِ الدُّنْيَا. بَاسِطَةٌ لِطُولِ أَمَلٍ عَنْ قَلِيلٍ يَنْقَضِي. قَلِيلَةُ الِاكْتِرَاثِ لِأَجَلٍ لَا بُدَّ أَنْ يُغْشَى رَاغِبَةٌ فِي حُبِّ دُنْيَا إِذَا أَحَبَّهَا قَلْبُ عَبْدٍ قَسَى. زَاهِدَةٌ فِي دَارٍ نَعِيمُهَا لَا يَفْنَى. مُحِبَّةٌ لِأَخْلَاقٍ تَعْلَمُ أَنَّهَا مُضَرَّةٌ بِهَا غَدًا. ضَاحِكَةٌ مُسْتَبْشِرَةٌ نَاعِمَةٌ بِمَا عَنْهُ مَوْلَاهَا نَهَى. نَفْسٌ تَحْزَنُ عَلَى مَا لَمْ يَجْرِ لَهَا بِهِ الْمَقْدُورُ مِمَّا أَمَّلَتْهُ مِنَ الدُّنْيَا صَبَاحَهَا وَالْمِسَا. نَفْسٌ يَخِفُّ عَلَيْهَا السَّعْيُ وَالْكَدُّ فِي طَلَبِ الدُّنْيَا، نَفْسٌ تَلَذُّ بِالْفُتُورِ عَنِ الْخَيْرِ الَّذِي إِلَيْهِ مَوْلَاهَا دَعَا. نَفْسٌ تَهُمُّ بِالنَّفَقَةِ فِي طَاعَةِ اللَّهِ، فَيُوعِدُهَا الشَّيْطَانُ الْفَقْرَ، فَتَمِيلُ إِلَى مَا إِلَيْهِ دَعَا. نَفْسٌ وَعَدَهَا اللَّهُ الْمَغْفِرَةَ، وَالْفَضْلَ فَلَمْ تَثِقْ، وَلَمْ تَرْضَ. نَفْسٌ تَثِقُ بُوعِدِ مَخْلُوقٍ، وَعِنْدَ وَعِيدِ مَوْلَاهَا تَتَلَكَّا. نَفْسٌ تُرْضِي الْمَخْلُوقِينَ بِسَخَطِ رَبِّهَا، وَعَنْ رِضًا مَوْلَاهَا تَتَوَانَى. نَفْسٌ نَدَبَهَا اللَّهُ إِلَى الصَّبْرِ عِنْدَ الْمَصَائِبِ، تَعْزِيَةً مِنْهُ لَهَا، فَلَا تَقْبَلُ الْعَزَا. نَفْسٌ تَتَصَنَّعُ لِلْمَخْلُوقِينَ بِوَفَاءِ الْوَعْدِ، وَفِيمَا عَهَدَ اللَّهُ الْكَرِيمُ إِلَيْهَا قَلِيلَةُ الْوَفَا. نَفْسٌ تَتْرُكُ الْمَعَاصِي بَعْدَ الْقُدْرَةِ عَلَيْهَا، حَيَاءً مِنَ الْمَخْلُوقِينَ، وَعِنْدَ نَظَرِ اللَّهِ الْعَظِيمِ إِلَيْهَا قَلِيلَةُ الْحَيَا. نَفْسٌ قَلِيلَةُ الشُّكْرِ لِلَّهِ الْكَرِيمِ عَلَى نِعَمٍ لَا تُحْصَى. نَفْسٌ تَسْتَعِينُ بِنِعَمِ اللَّهِ الْكَرِيمِ عَلَى مَعَاصِيهِ فِي صَبَاحِهَا وَالْمِسَا. نَفْسٌ يَخِفُّ عَلَيْهَا مُجَالَسَةُ الْبَطَّالِينَ، وَيَثْقُلُ عَلَيْهَا مُجَالَسَةُ الْعُلَمَا. نَفْسٌ تُطِيعُ الْغَاشَّ، وَتَعْصِي أَنْصَحَ النُّصْحَا. نَفْسٌ تُسَارِعُ فِيمَا تَهْوَى، وَهِيَ تَتَعَلَّلُ بِالتَّسْوِيفِ لِلتَّوْبَةِ الْيَوْمَ وَغَدَا. قَالَ أَبُو بَكْرٍ مُحَمَّدُ بْنُ الْحُسَيْنِ: مَنْ عَرَفَ مِنْ نَفْسِهِ هَذِهِ الْأَخْلَاقَ، وَغَيْرَهَا، سَارَعَ إِلَى رِيَاضَتِهَا، بِحُسْنِ الْأَدَبِ لَهَا؛ لِيَرُدَّهَا إِلَى مَا هُوَ أَوْلَى بِهَا مِنْ تَقْوَى اللَّهِ عز وجل، فِي السِّرِّ وَالْعَلَانِيَةِ، بِالنَّدَمِ الشَّدِيدِ، وَالنِّزُوعِ مِنْ قَبِيحِ مَا صَحَّ عِنْدَهُ مِنْ هَذِهِ الْأَخْلَاقِ، إِنْ فِيهِ شَيْءٌ مِنْهَا، وَإِصْلَاحِ مَا يَسْتَأْنِفُهُ فِي طُولِ عُمْرِهِ، وَاللَّهُ عز وجل الْمُوَفَّقُ لِذَلِكَ. أدب النفوس للآجري (٢٥٥-٢٥٦) شذرات العلم: t.me/shadharaat