tgindex
Berhanu Ahmed View የብርሀኑ አህመድ እይታ

Berhanu Ahmed View የብርሀኑ አህመድ እይታ

Статистика

ይህ የአቶ ብርሀኑ አህመድ ወቅታዊ ፣ ሞራልንና ማህበራዊ ጉዳይን የተመለከቱ ሀሳቦችን የሚንጸባረቁበት እንዲሁም ህጎች የሚተነተኑበት ቻናል ነው። it is Berhanu Ahmed's reflection channel on current, moral and legal issues.

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
10
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
187
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
40
22 постов
Вовлечённость
21,4%
к подписчикам
Постов в день
1,4
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
20
1/48двое суток
22
1/72трое суток
24

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የታሪካዊው የቦይንግ አደጋ አዲስ ውሳኔ፡ የ29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደ በኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰው አሰቃቂ የቦይንግ 737 MAX አደጋ የሞቱት የአለም ምግብ ድርጅት (WFP) ባልደረባ የነበሩት የማይክ ርያን ቤተሰቦች 29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈላቸው የአሜሪካ ፍርድ ቤት ወሰነ። የዜናው ዋና ዋና ነጥቦች፡ 🔹 አደጋው፡ እ.ኤ.አ. በ2019 በቢሾፍቱ አቅራቢያ በደረሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መከሰከስ ምክንያት የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል። 🔹 ምክንያቱ፡ ለወራት ከተደረገ ምርመራ በኋላ አደጋው በአውሮፕላኑ የቴክኒክ ጉድለት ምክንያት በመከሰቱ ቦይንግ ሙሉ ተጠያቂ ሆኗል። 🔹 የፅናት ውጤት፡ አብዛኞቹ ቤተሰቦች ከፍርድ ቤት ውጭ ድርድር ሲያደርጉ፣ የ39 ዓመቱ ማይክ ርያን ባለቤት ናኦይሴ ርያን ግን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እስከ ህግ መጨረሻ ድረስ በመታገል ይህንን ውሳኔ አግኝተዋል። 🔹 ቀደም ሲል፡ የቺካጎው ፍርድ ቤት ባለፈው ግንቦት ወር በተመሳሳይ አደጋ ለሞተችው የ24 ዓመቷ አሜሪካዊት ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መወሰኑ ይታወሳል። 🕊️ለሟቾች ሙሉ እረፍትን፣ ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ መፅናናትን እንመኛለን።

  • የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክከር ህጋዊ መሰረቶችና ፋይዳዎች ክፍል 1

  • እነርሱ ሲያግቱ ሲገድሉ (ለመከላከያ ፣ ፖሊች እና ልዩ ሀይል ትንሽም ይሉኝታ ያላሳዩ) ፣ አርሶ አደርን ያልበቀለ ምርቱን ሲደርስ የሚከፍለዉን የሚሊየኖች ገንዘብ ተምነዉ የሚመጡ ፣ የብሄር ሽፋን ሰጥተዉ ታጋይ ነን እያሉ ህዝብ እርስ በርሱ እንዳይተማመን ሲያደርጉ ሀገርን ሲንዱ የእነርሱ ስራ በየትኛዉ ፍርድ ቤት የተወሰነ ዉሳኔ ሆኖ ነዉ ይህንን ሲያደርጉ የቆዩት? ለየትኛዉ ሰብዓዊ መብት ነዉ ጥቅና የቆምነዉ? የሚገደለዉ የምትደፈረዉ የሚሰደደዉ እንዳያለማ የሚከለከለዉ ሰብዓዊ ምበቱ አልተጣሰም? ለምን እንደምንደንዝ ናላችን ለምን ማገናዘብ እንደሚያቀተዉ አይገባኝም፡፡ አማራ ክልል ያበትን ሁኔታ አለም ያዉቀዋል፡፡ ሰዉ ሞቶ መቅበር አይቻልም፣ መንገድ ተዘግቷል ከተባለ አመታት የተቆጠረበት ስንት አካባቢ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ስንቱ ቄስ ፣ ስነቱ አማኝ ፣ ስንቱ ምእመን የተገደለዉ በመሰሎቻቸዉ ነዉ፡፡ አነዲት ሴት ተደፈረች ሲባል ግደሉት! ግደሉት! እያልን የምንወጣ ሰዎች ሀገር ያሰለቹ ሽፍቶች እርምጃ ተወሰደባቸዉ ሲባል አምንስቲ ፣ ሰብአዊ መብት ፣ ህምንግስት ገለመሌ ለማለት የህግ መአት ለማሰስ እንቆፍራለን እንደክማለን፡፡ ቢገባንማ አንዱ ቄስ መታረድ የስንቱ ክርስትያን ልብ አብሮ እንዳደማ በተገነዘብንና የሚደርሰዉን ቁጣ ምን ያህል እንደሆነ ለመገመት ማሰብ ብቻ ይበቃን ነበር፡፡ ዶ/ር አብይ አህመድ መግደል ሀሳብን አይገድልም ያለዉ ትክክል ቢሆን እኩይ ሀሳብን ግን የተነሰሰዉን እና የሚተገብረዉን ካላጠፋህ አታሰቆመዉም፡፡ መልካም ሀሳብ ብቻ ነዉ ሰዎችን በመግደል ማስቆም የማይቻለዉ፡፡ ነጻ ያልወጡ ነጻ አዉጭዎች ጫካ ገብተዉ የነተበ ሀሳባቸዉን ብህዝብ እያሰራጩ ሀገር ሰላም ዉላ እንዳታድር የሚሰሩ በሆነ ጊዜ መንግስት ብቻ ሳይን ሁሉም ሊታገለዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበዥጌ ወረዳ የተወሰደዉ እርምጃ መንግስት ሊመሰገን ይገባል፡፡

  • ጫካ ለጫካ እየዞረ በጠራራ ጸሀይ የሚዘርፍን እና የሚገድል ሽፍታ በሰላም የሚኖረውን መጤ እያለ ዘቅዝቆ የሚገድል ቡድንን ዛሬ ላይ ተበዳይ ነበርክ በማለት የቂቤ አንጓችነትና አይዞህ ባይነት ሚና በመጫወት አሁንም በርቱ ግደሉ ታጋዮች መባሉ የሚዲያው የአሸባሪ መጨፈርያነት ያሳያል። ትግሬን የማጥላላት የማሳደድ ዘመቻ ለመክፈት ታስቦ የሚፈጸም የሚዲያ ጨዋታ ፋና ብሮድ ካስት አየተጫወተ ይገኛል

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሩስያ በዩክሬን የሚገኝ የተባበሩት መንግስታት የአለም የጤና ድርጅትን መጋዘን ደበደበች

  • ተሽከርካሪ ይዘው ነፍጥ አንግበው ፣ የመንግስት እና የግል ድርጅት ሳይቀር በመረጃ ሰጭዎቻቸው ጠርንፈው መንግስት ባግባቡ ተጠናክሮ እንዳይሰራ በማፍረስ ህዝብ እንዳይተማመን ለምድረግ ሰው ማገትና መንግስትን ግለሰቦችን ገንዘብ አምጡ ማለት የአርሶ አደር ማሳ ሰብል ሳያሽት ሚሊየን እና መቶ ሺዎች ካልከፈልክ አታነሳም የሚል ለፓሊስ ፣ ሚሊሻ ፣ ልዩ ሀይል እና መከላከያ ምንም ሳይቀፈው ተኩሶ የገደለ ብዙዎች በወጡበት በማስቀረታቸው በመግደላቸው ቤተሰቦቻቸውን የበተኑ ኦሮሞም ይሁን አማራ ሀድያም ይሁን ጉራጌ ወይም ሌላ የድፍን ኢትዬጽያዊ ጠላቶች ናቸውና ሊጠፋ ይገባል። በሀገራችን ለሚከሰት ማናቸውም ችግር ዋና መሰረቱ የሰላም ያለ መኖርና የዜጎች መብት መጣስ ዋና ምክንያት ስለሆነ። ማናቸውም ብሄር ወክለናል ቢሉም ሀገሪቱ ውስጥ ሁሉም አቅጣጫ ሰላም እንዳይኖር የዜጎች መብት እንዲጣስ እና የህግ የበላይነት እንዳይኖር ቀን ከሌሊት የሚውጥኑ ሀይሎች ተላላኪ እንጅ ብሄሮቹን የሚገልጹ ወይም የሚታገሉላቸው ባለመሆናቸው መወገድ አለባቸው። መሰሎቻቸው እንዲማሩና ሰላም ወዳዱ ታታሪው ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ ተከታትሎ ማጵዳቱ መቀጠል አለበት። የተገደለው እኩይ ሀሳብ እንጅ ሰው አደለም!!

  • ከህግ ውጭ የሚፈጸም ግድያ፡ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ሀገራዊ መዘዙ መግቢያ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ «አገና» በተባለች ልዩ ቦታ ሶስት ንጹሃን ዜጎች (ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ) ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ የተሰማው ዜና በእጅጉ የሚያሳዝን እና ህግ የበላይነት ላይ የተደቀነ ትልቅ ስጋት ነው። ማንኛውም ሰው ወንጀል ፈጽሟል እንኳ ቢባል፣ ውሳኔ ማግኘት ያለበት በህጋዊ የፍርድ ሂደት እንጂ በሜዳ ላይ ፍርድ (Extrajudicial Killing) ሊሆን አይገባም። # አለም አቀፍ ድንጋጌዎች እና የህይወት መብት የሰው ልጅ የህይወት መብት ተፈጥሯዊ፣ የማይገፈፍ እና በምንም አይነት ሁኔታ (በጦርነት፣ በበጎ አድራጎት ወይም በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እንኳ) የማይገደብ መሰረታዊ መብት ነው። 1️⃣ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (UDHR - Article 3 & 11): ማንኛውም ሰው የህይወት፣ የነጻነት እና የደህንነት መብት አለው። እንዲሁም በወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው በህግ ፊት ነጻ ሆኖ የመገመት (Presumption of Innocence) መብቱ የተጠበቀ ነው። 2️⃣ የአለም አቀፍ የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች ቃል ኪዳን (ICCPR - Article 6): ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብት አለው። ይህ መብት በህግ ይጠበቃል። ማንኛውም ሰው በግፍ እና ከህግ ውጭ ህይወቱን ሊያጣ አይገባም። # የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ድንጋጌዎች የሀገራችን ህገ-መንግስትም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ የዜጎችን የህይወት እና የፍትህ ማግኘት መብት በግልጽ ደንግጓል፡- 1️⃣ አንቀጽ 15 (በህይወት የመኖር መብት): ማንኛውም ሰው በህግ ከተደነገገው ውጭ ህይወቱን አያጣም። 2️⃣ አንቀጽ 19 እና 20 (የተጠረጠሩ እና የተከሰሱ ሰዎች መብት): ማንኛውም የተከሰሰ ሰው ጥፋተኛነቱ በህግ አሰራር ጥፍተኝነቱ በማስረጃዎች ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ውሳኔ እስካልተሰጠበት ድረስ ነጻ ሆኖ የመገመት መብት አለው። ፍርድ የሚሰጠው በገለልተኛ እና በቋሚ የፍርድ ቤት አሰራር ብቻ ነው። ⚠️ የደቦ ፍርድ እና ከህግ ውጭ የሚፈጸሙ ግድያዎች ሀገራዊ ቀውስ አንድ መንግስት ወይም የፀጥታ አካል ህግን የማስከበር ሀላፊነት እያለው፣ ራሱ ህግ ጥሶ በሜዳ ላይ ፍርድ እርምጃ ሲወስድ የሚከተሉት አደገኛ ሀገራዊ ቀውሶች ይፈጠራሉ፡- # የህግ የበላይነት መሸርሸር፡ የፍትህ ስ ስርዓቱ በጉልበት ሲተካ ዜጎች በተቋማት ላይ ያላቸው እምነት ሙሉ በሙሉ ይጠፋል። # የበቀል እና የጥላቻ ዑደት፡ ከህግ ውጭ የሚፈጸሙ ግድያዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ቁጣን በመቀስቀስ ተጨማሪ የሃይል እና የበቀል እርምጃዎችን ይጋብዛሉ። # የዜጎች የደህንነት ስጋት፡ ማንኛውም ዜጋ በማንኛውም ጊዜ ያለ በቂ ማስረጃ የጥቃት ሰለባ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት እንዲያድርበት ያደርጋል። # የተጠያቂነት መጥፋት፡ ወንጀል የሰራ አካል በህግ ሳይጠየቅ ሲቀር፣ ወንጀል የመስራት ባህል እንዲስፋፋ በር ይከፍታል። ምንም አይነት ምክንያታዊነት ከህግ ውጭ ሰውን መግደልን ሊያጸድቅ አይችልም። መንግስት እና የፀጥታ አካላት ህግ የማስከበር ግዴታቸውን ሲወጡ በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ መሆን አለበት። ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን እንመኛለን፤ ድርጊቱም ገለልተኛ በሆነ አካል ተመርምሮ ፍትህ እንዲሰፍን እንጠይቃለን። Access to Justice Initiative - Ethiopia ፍትህ ለሁሉም የህግ የበላይነት ይከበር ነሀሴ 5/2018 አድስ አበባ - ኢትዮጵያ

  • видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.39из Ethiobooks

    ━ ስልታዊ ማፈግፈግ ━ (Strategic Retreat) ━━━━✦━━━━ ✍ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ' ስልታዊ ማፈግፈግ (Strategic Retreat) ማለት አንድን የጀመርነውን ነገር ርግፍ አድርጎ መተው ማለት አይደለም። ለወደፊት በብቃት ለመንቀሳቀስ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ በብልሃት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ማለት ነው። በሕይወት ውስጥ አንዳንዴ ለማሸነፍ ምርጡ መንገድ ወደ ፊት መግፋቱን መቀጠል ሳይሆን፤ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ሁኔታዎችን መገምገም፣ ከተጎዳንበት ነገር ማገገም እና እራስን እንደገና ማዘጋጀት ነው። ስልታዊ ማፈግፈግ ማለት ጥንካሬን ለመጠበቅ፣ ግልጽነት ለማግኘት እና ለወደፊት ለተሻለ ውጤታማነት ለመዘጋጀት ሆን ተብሎ የሚወሰን ጊዜያዊ ዝምታ፣ ከነገሮች ዘወር የማለት፣ የመውጣት፣ የመቆም ወይም አቅጣጫን የመቀየር ውሳኔ ነው። ይህ ማለት፦ ✔️ ማቋረጥ ሳይሆን፣ መስተካከል (recalibrating) ነው። ✔️ ፍርሃት ሳይሆን፣ ጥበብ ነው። ✔️ መሸነፍ ሳይሆን፣ ለተሻለ የላቀ ግስጋሴ መዘጋጀት ነው። "አንዳንዴ ትልቁን ስእል ለማየት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል" እንደሚባለው ማለት ነው። መቼ ነው ስልታዊ ማፈግፈግን ማሰብ ያለብን? 1. ወደ ፊት መቀጠል አላስፈላጊ ጉዳት ሲያስከትል፦ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታው ውስጥ መቆየት የስሜትን ወይም የአካልን ጥንካሬ ሲያሟጥጥ መለስ ማለት ጥሩ ነው። 2. ግልጽነት እና አቅጣጫ ስንፈልግ፦ አንዳንድ ጊዜ ሕይወት ግራ ሲያጋባን፣ “ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ነኝ?" ብሎ ለመጠየቅ ማፈግፈግ አስፈላጊ ነው። 3. ዝለት (Burnout) ሲሰማን፦ አንዳንድ ጊዜ ብዙ ለፍተን ጥቂት ስናገኝ፣ ከመሯሯጣችን የተነሳ ውስጣችን ሲደክም መረጋጋት ያስፈልጋል። 4. መርዛማ (Toxic) ሰዎች ሲበዙብን፦ አንዳንድ ጊዜ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ሲበዛና ጤና-ቢስ የሆነ ሃሳብና ተግባራቸው ሲበዛ ዘወር ማለት የግድ ነው። 5. ለታላቅ እድል ለመዘጋጀት፦ አንዳንድ ጊዜ እስካሁን በሰራነው ስራ፣ በሄድንበት መንገድና በድግግሞሹ የሕወት ለውጥና እድገት ካላገኘት ራሳችን ለማሻሻል የትኩረት ለውጥ ማድረግ ወሳኝ ነው። በስልታዊ ማፈግፈግ ወቅት ምን ማድረግ አለብን? ስልታዊ ማፈግፈግ ስናደርግ ከከባድ ሁኔታዎች በማምለጥ ዝም ብለን ገለል ማለት ሳይሆን የሚከተሉትን ልምምዶች ማዳበር ማለት ነው። ➢ ማሰላሰል (Reflect)፡ ምን ትምህርት ተምሬያለሁ? ➢ ማገገም (Recover)፡ አካላዊ፣ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ጥንካሬን መመለስ። ➢ እንደገና መገምገም (Re-evaluate)፡ ምን መቀጠል አለበት? ምን ማቆም አለበት? ➢ ቦታ መቀየር (Reposition)፡ ቀጣዩ ሥራዬ ወይም እድሌ የት ነው? ➢ እንደገና መገንባት (Rebuild)፡ አዳዲስ ልማዶችን፣ ሥርዓቶችን እና አመለካከቶችን ማዳበር። አንዳንዴ ጥንካሬ የሚገኘው ዝም ብሎ ወደ ፊት በመገስገስ ሳይሆን መቼ ወደ ኋላ ማፈግፈግ እንዳለብን በማወቅ፣ በመረጋጋት፣ ጸሎት በማድረግ፣ አመለካከትን በማስተካከል እና ለቀጣዩ የሕይወት ምዕራፍ በመዘጋጀት ነው። ━━━━━━━━ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks

  • ስድብ ትጠላለህ

  • ጨር ጥብጠማ

  • ኧገንበናኸ በገንበና ኢና ሰወኸ ኧገግዃ ትክ ይወራአካአር በአፈርሞኻ ኤነዳ። Non eat aflesh of his birth than the black and a tribe of mine.

  • አወዳደቅ ሲያምር ***** በመጫኛ ጣሏት ዶሮን ሲያታልሉ ጀግናን ሲያታልሉ አንተ ትችላለህ ጀግና ነህ እያሉ በጀርባው ላይ ሆነው ምላስ እያወጡ ፈጥፍጠውት ገቡ ስንቱ ሚያህሉ።

  • የገፊ ነገር! ****** የገፊ እጅ ነው ወተትን በትኖ ለስንት የከፈለ የገፊ አዋቂነት ሲያወሳስበው ምስቅልቅል አውጥቶ እንጀራ ሚያሳጣ ናላ እያሳተ ከእውነት እርቆ ተሰውነት ወቶ ክፉ ቀን እስቲያልፍ አድበናል እንጂ ገፊ መቼ ተኛ ለሶስት ስንከፈል በሚዞር ተቀምጦ ጥርስ ያገጣል እንጂ።

  • ከ3 ዓመታት የፍርስራሽ ስር ቆይታ በኋላ የ112ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት አሳዛኝ የጅምላ ቀብር በጋዛ 💔 የጋዛ ከተማ በጦርነቱ ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ልብ ሰባሪ እና ትልቁ ሊባል ለሚችለው የጅምላ ቀብር ስነ-ስርዓት በመዘጋጀት ላይ ትገኛለች። የቀብር ስነ-ስርዓቱ የ112 የአቡ ሻሪያ ቤተሰብ አባላትን በአንድ ላይ የሚያሳርፍ ነው። እነዚህ 112 የቤተሰብ አባላት በአል-ሳብራ ሰፈር ውስጥ ከሚገኝ አንድ የመኖሪያ ህንፃ ፍርስራሽ ስር የተገኙ ሲሆን አሳዛኙ ነገር ደግሞ በዚሁ ፍርስራሽ ስር ለሦስት ዓመታት ያህል ተቀብረው መቆየታቸው ነው። የሲቪል መከላከያ (የአደጋ ጊዜ) ሰራተኞች የተጎጂዎቹን አስከሬን ለማውጣት ለ136 ተከታታይ ሰዓታት ያለምንም እረፍት ፍርስራሹን ሲቆፍሩ አሳልፈዋል። ከፍርስራሹ ውስጥ ከወጡት አስከሬኖች መካከል አብዛኛዎቹ የህፃናት እና የሴቶች ናቸው። ይህ ክስተት ጦርነቱ ሙሉ ቤተሰብን እንዴት ከምድረ-ገፅ እያጠፋ እንደሆነ በግልፅ ያሳያል። አሳዛኙ ክስተት በወጡት 112 አስከሬኖች ብቻ አያበቃም። የነፍስ አድን ሰራተኞች እንደሚገምቱት ከሆነ አሁንም በአቅራቢያው በሚገኙ ሌሎች የፈረሱ ህንፃዎች ስር ወደ 200 የሚጠጉ ተጨማሪ የዚሁ ቤተሰብ አባላት ተቀብረው ይገኛሉ። የደረሰው የቦምብ ጥቃት መጠን እና ኃይል እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ ሟቾች ማንነታቸውን ለመለየት የሚያስችል ምንም አይነት የሰውነት አካል እንኳ ማግኘት አልተቻለም። ይህ ታሪካዊ የጅምላ ቀብር ጦርነቱ በጋዛ ነዋሪዎች ላይ ያደረሰውን እና አሁንም ከፍርስራሾች ስር በየቀኑ እየወጣ ያለውን ወደር የለሽ ሰብዓዊ ኪሳራና ስቃይ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።

  • видео или голосовое, без подписи

  • የህሊና ወ*ንጀል ነው። ይኼ ምግብ ሳይሆን የሕይወት አድን መድሐኒት ነው። ሰዎች ሳያዉቁ ገዝተው ሊመገቡ ይችላሉ። አንዳንዴም ቤተሰብ ለታመመችዋ ልጅ የታዘዘውን ሸጠው ለቤተሰብ ቀለብ የሚገዙ አሉ። በሞ*ት አፋፍ ላይ ካለ ህፃን ነጥቆ እንደመብላት ነው። በተለይ ክብደት ለመጨመር እየተባለ ለቅንጦት ከተራበች ነፍስ እየቀሙ እንደሆነ ይወቁ። ለጤናማ ሰው ምናልባትም ለጤና አ*ደገኛ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ምግብ ሳይሆን የምግብ እጥረት መድሐኒት ስለሆነ ነው። አይግዙ፤ አይሽጡ። ለታመሙት ብቻ እናውለው። በህሊና ብቻ ሳይሆን በመደበኛ የህግ ስርዓት ተጠያቂነት ሊያስከትል ይችላል

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

Berhanu Ahmed View የብርሀኑ አህመድ እይታ — tgindex