- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 25
- 1/48двое суток
- 28
- 1/72трое суток
- 30
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Jesus without you im noting !!!
እግዚአብሔር እረኛችን ነው! 👉የሚያስፈልገንን ነገር በሙሉ በጊዜው ያሟላል። 👉በመቀጠል ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀናል እረኛ ያለውና የሌለው በግ ያስታውቃል ✍️መዝሙረኛው ዳዊት ታማኝ እረኛ ስለ ነበረ ነው ስለ በጎቹ ሲል ራሱን አጋልጦ ከአንበሳና ከድብ ጋር የገጠመው👈 🌈የእኛ እረኛ ደግሞ ነፍሱን ስለ እኛ አሳልፎ የሰጣ ክፉ እንዳያገኘን ቅድሚያ ራሱን የሚያደርግ እውነተኛ አፍቃሪ እረኛ ነው የዮሐንስ ወንጌል 10:10-11 --- ¹⁰ ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ። ¹¹ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል፤ 👉 ከእረኛችሁ የኮበለላችሁ፣ግጦሹ(የዚህ አለም ነገር) ተመችቷችሁ ከእረኛችሁ የኮበለላችሁ እርሱ ስለ እናንተ ግድ ይለዋልና ወደ እርሱ ተመለሱ🙏 ከ99 ይልቅ የእናንተ መመለስ እረኛችሁን ደስተኛ ያደርገዋልና የሉቃስ ወንጌል 15:10 --- ¹⁰ እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።” 🔥ወደ ፈረሰው መሰዊያ ከነድካማችሁ ተመልሱ በፍቅሩ ይጠግናችኃል እርሱ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የእውነተኛ ፍቅር መገኛና ምንጭ ነው❤ 👉ሰይጣን በውድቀታችሁ እና በድካማችሁ አየከሰሳችሁ እንዳይሰርቃችሁ ወደ ጌታቹ በፍጥነት ተመለሱ🏃♂ 👉ጌታ አይምረኝም ኃጢአቴ ብዙ ነው ብላችሁ ከእረኛችሁ አትሽሹ ለእናንተ በመስቀል ላይ የተከፈለው ዋጋ ውድ እና የማይገኝ ነው ስለዚህ እርሱ ዛሬም ለዘላለም አልተለወጠም አይለዋወጥም!!! 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:9 --- ⁹ ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃ ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው። በእርግጥ ዮርዳኖስን ስሻገር🔥
ዮሐንስ 14 (John) 26፤ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ 15 (John) 26፤ ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤ ዮሐንስ 16 (John) 7፤ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። 8፤ እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤ 9-10፤ ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤ 11፤ ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው። 12፤ የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። 13፤ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። 14፤ እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። 15፤ ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፡— ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ። Join /Sher https://t.me/robhot https://t.me/robhot
መገልገል እኖዳለን መጸለይ አኖድም ፣መገልገል እኖዳለን ቃሉን ማንበብ አኖድም ፣ያለ ጸሎትና ያለ እግዚአብሔር ቃል ጥናት አገልግሎት የለም ።
без подписи
https://t.me/robhot https://t.me/robhot
Jesus
The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 8 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
без подписи
📍የምናየውንና የምንሰማውን እኛ ካልመረጥን አለም ትመርጥልናለች🤷🤷 ሰው የሰማውን ያየውን የቆየበትን ይመስላል ። ማንን እየመሰልን ነው 🤔🤔
без подписи
ወጥመዱ ተገላቢጦሽ) አስገራሚ እውነተኛ ታሪክ ከእነዚህ ሰዎች አንዱ አንተ ነህ 🙄 በአንድ ወቅት በአንድ ተቋም ውስጥ አብረው የሚሰሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ። መኮንን የተባለው ሰው በጣም ሃይማኖተኛ እና ታማኝ ሲሆን፣ ደሳለኝ ደግሞ በመኮንን ስኬትና ቅንነት ቀንቶ "ከስራው ካላባረርኩት" ብሎ የቆረጠ ሰው ነበር። ደሳለኝ በመኮንን ላይ ያለው ምቀኝነት ገደብ አጣ። በመጨረሻም አንድ ክፉ ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ "ይህ ሰው በቃኝ ሊል ይገባል፤ ስራውም ይበላሽ፣ አእምሮውም ይናወጥ" ብሎ ብዙ ገንዘብ በመክፈል አስጠነቆለበት። ጠንቋዩም አንድ "የተደገመበት ክርና መርፌ" ሰጠውና "ይህንን መኮንን በማያውቀው ሁኔታ በቢሮው ወንበር ስር ሰክተህ ቅበረው፤ ህይወቱ ይበላሻል" አለው። በማግስቱ ጠዋት ደሳለኝ መኮንን ከመምጣቱ በፊት ወደ ቢሮው ገብቶ ድግምቱን መቅበር ጀመረ። በዚያው ቅጽበት ግን ደሳለኝ ድንገት በከባድ የደም ግፊት ህመም ተመታና እዚያው መኮንን ቢሮ ውስጥ ወድቆ መንፈራገጥ ጀመረ። መኮንን ወደ ቢሮው ሲመጣ ጓደኛው ደሳለኝ መሬት ላይ ወድቆ ሕይወቱ ልትወጣ ስትታገል አየው። መኮንን ክፋቱን አያውቅም፤ "ጓደኛዬ ሞተብኝ!" ብሎ በፍርሃትና በደግነት አቅፎት ወደ ሆስፒታል ወሰደው። ለቀናት ሆስፒታል ተኝቶ ደሳለኝን በገንዘቡም በጉልበቱም ሲንከባከበው ሰነበተ። ደሳለኝ ነፍሱ ተመልሳ ከሆስፒታል ሲወጣ፣ መኮንን ለደሳለኝ አንድ ነገር ሰጠው። እንዲህም አለው፦ "ደሴ፣ ያኔ ወድቀህ ስታገል ወንበሬ ስር አንድ እንግዳ መርፌና ክር አገኘሁ፤ ምናልባት ያንተ ሊሆን ይችላል ብዬ ይዤልሃለሁ" ብሎ መለሰለት። ደሳለኝ ያን መርፌ ሲያይ መቆም አቃተው። በደግነቱ ሊያጠፋው የሞከረውን ሰውዬ እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- "መኮንን ሆይ! እኔ ሰይጣን ቤት ሄጄ አንተን ልገድልህ አስጠንቁዬ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያች ቅጽበት አይቶኝ ፍርዱን ሰጠኝ። ላጠፋህ ስዘጋጅ እኔን አስመታኝ፤ አንተ ግን ክፋቴን ሳታውቅ በደግነትህ ሞትን አሸነፍክልኝ። እግዚአብሔር ካንተ ጋር መሆኑን ዛሬ አረጋገጥኩ።" 💡 የዚህ ታሪክ ትልቅ ትምህርት ማንም የቆፈረው ጉድጓድ ለራሱ ነው፦ መጽሐፍ "ጉድጓድ የቆፈረ ራሱ ይገባበታል" እንደሚል፣ ደሳለኝ በመኮንን ላይ ያዘጋጀው ወጥመድ በራሱ ላይ ደረሰ። ደግነት ድብቅ ጥበቃ ነው፦ መኮንን ጸልዮና በደግነት ስለኖረ፣ እግዚአብሔር ጠላቱ አጠገቡ መጥቶ ክፋት ሲሰራ አላስቻለውም። ጠንቋይ ቤት መሄድና ሰይጣንን መለመን የፈጣሪን አይን ሊሸፍን አይችልም። እግዚአብሔር ሁሉንም ያያል! ውድ የፌስቡክ ተከታዮቼ! ስለ እናንተ በስውር የሚመክሩ፣ በምቀኝነት የሚያስጠነቁሉባችሁ ሰዎች ቢኖሩ አትፍሩ። እናንተ በቅንነትና በደግነት ተጓዙ፤ የእናንተ ጠባቂ ደግሞ በድብቅ የተሰራውን ወጥመድ በባለቤቱ ላይ የሚመልስ "እግዚአብሔር" ነው። ሰው ቢረሳችሁ "እግዚአብሔር ያያል!"።
ታላቅ ዛፍ ወደዚያ ግዝፈት ከመምጣቱ በፊት በመሬት ላይ በወደቀች ታናሽ ዘር ውስጥ በሕልም መልክ ተቀምጦ ነበር።ታላቁ ንስር በአንድ እንቁላል ውስጥ አንድ ቀን የመብረር ተስፋ ይዞ ''አድፍጦ'' ይጠብቅ ነበር።ስለዚህ በመረጋጋት ትኩረት እግዚአብሔር በሰጠ አላማ ላይ ይሁን🙏 ፍቃዳቹ ከሆነ join&share ማድረግ አትርሱ🙏 http://t.me/blssing1
ያዕቆብ 4 (James) 6፤ ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፡— እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፡ ይላል።
без подписи
ለህይወቴ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ እንዴት አውቃለሁ? ለህይወትህ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምታውቀው በዚህ መንገድ ነው፦ የእግዚአብሔርን ቃል አንብብና አጥና፣ ታዘዘውም:: —ጀስቲን ፒተርስ
без подписи
VALENTINE'S DAY #ወጣት_ሆይ_ንቃ ሼር በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ❗ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም። የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ??? ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው። የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው። ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት። ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው) ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም። እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው። ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል። ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር። በዚህ የሃጥያት ቀን በትንሹ ይህ ይሆናል 1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗ 2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗ 3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው። Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው። እንግዲህ ምርጫው ያንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን??? " ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። " (ትንቢተ ሆሴዕ 4 👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 #እወዳችኋለሁ❤❤ 👉 inbox me @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
ኢየሱስ ባሉ ከድካም ትወጣላችሁ ። ምሳሌ 18 (Proverbs) 10፤ የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።
ዛሬ እግዚአብሔርን ይህንን ጥቅስ እንድታነቡ እፈልጋል ትንቢተ ኢሳ 60፥22 የዛሬው ቀን ምንም ቢመስል፣ እምነታችሁን አጠንክሩ። እግዚአብሔር ታሪካችሁን ሊለውጥና ሐዘናችሁን ወደ ደስታ ይቀይረዋል ። የእርሱ ጊዜ መቼም አይዘገይም፤ ሁልጊዜም ፍጹም ነው። መጸለይን ቀጥሉ፣ ተስፋ አትቁረጡ። ተአምራት በየቀኑ ይፈጸማሉ፤ ስለዚህ ማመንን በፍጹም አታቁሙ። እግዚአብሔር በሕይወታችሁ ውስጥ ነገሮችን በጣም በፍጥነት ሊለውጥ ይችላል። አሁንም በእግዚአብሔር የምትታመኑ ከሆነ፣ “አሜን” በሉ