- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 3
- 1/48двое суток
- 3
- 1/72трое суток
- 3
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ይህን ያህላል የምንወድህ ዕድሜ ተጎምዶ ከራስ ገላ ላይ ላንተ ቢለገስ እንደኩላሊት እልፍ ማለዳ እልፍ ሺህ ለሊት ቆጥረህ ለክተህ የማትደርስበት ደምረህ ሰፍረህ የማትጨርሰው ይህን ያህላል የሚወድህ ሰው ፍቅርን ውበትን የምንገልፅበት ምንቆዝምበት ምንተክዝበት ምንፅናናበት ትንፋሽ አድለህ ብትሰወርም ካይናችን ጎድለህ፤ ባታወጋንም ባንጠይቅህም ረግቶ ቢንሳፈፍ ዝምታ ውስጥህ እኛ ግን አንተን እንደመዝሙር ነው የምናደምጥህ። እንኳን በተራ ባልቀና ጆሮ የምትታፈር በሊቅ ባዋቂ ልክህን ያህል ሰርተሃል በቂ። ዜማ ቢነጥፍ ከጉሮሮህ ላይ እንደትናንቱ ድምፅህ ባይሰላም ዝም ብለህ ክረም ቆየን በሰላም ከፍቶህ እንዳናይ በስህተት እንኳ እንዳይደብርህ ይህን ያህል ነው የምናከብርህ። ✍️ ገጣሚ አስታወሰኝ ረጋሳ
የፒያሳ ድምጾች Echoes of piassa
በሙዚቃ ቅንብር (Arrangement)፣ ፕሮዳክሽን (Production)፣ ሚክሲንግ (Mixing) እና ማስተሪንግ (Mastering) የሚሰራ ባለሙያ ነው። ከዚህ ሙያዎች እያንዳንዳቸው ምን እንደሚያካትቱ እነሆ፦ 1. የሙዚቃ ቅንብር (Music Arrangement) ይህ የዘፈን መሰረታዊ ሀሳብን ወደ ሙሉ ሙዚቃ የመቀየር ሂደት ነው። በዚህ ሂደት፦ * የትኞቹ መሳሪያዎች (ፒያኖ፣ ጊታር፣ ድራም፣ ባስ ወዘተ) እንደሚጠቀሙ ይመረጣል። * የዘፈኑ መግቢያ (Intro)፣ ኮረስ (Chorus)፣ ቨርስ (Verse) እና መጨረሻ (Outro) ይደራጃሉ። * ሙዚቃው የሚያስነሳው ስሜት እንዲጠናከር ይሰራል። 2. ሙዚቃ ፕሮዳክሽን (Music Production) ይህ ከመጀመሪያ ሀሳብ እስከ የመጨረሻ ዘፈን ድረስ ያለውን ሂደት ያካትታል። * ከዘፋኙ ጋር የዘፈኑን አቅጣጫ መወሰን። * የመቅረጫ ክፍለ ጊዜዎችን ማስተዳደር። * የድምፅ ጥራትን ማረጋገጥ። * ለገበያ የሚቀርብ ጥራት ያለው ዘፈን ማዘጋጀት። 3. ሚክሲንግ (Mixing) ሚክሲንግ ማለት ሁሉንም የተቀረጹ ድምፆች በተመጣጣኝ ሁኔታ ማዋሃድ ነው። * የዘፋኙ ድምፅ ግልጽ እንዲሰማ ማድረግ። * የሙዚቃ መሳሪያዎች እርስ በርስ እንዳይጋጩ ማስተካከል። * ኢኮ (Reverb)፣ ዲሌይ (Delay) እና ሌሎች የድምፅ ተፅዕኖዎችን መጠቀም። 4. ማስተሪንግ (Mastering) ይህ የመጨረሻው የድምፅ ማሻሻያ ሂደት ነው። * የድምፅ መጠን (Loudness) ማመጣጠን። * በስልክ፣ በመኪና፣ በስፒከር ወይም በጆሮ ማዳመጫ ላይ ተመሳሳይ ጥራት እንዲሰማ ማድረግ። * ዘፈኑን ለSpotify፣ Apple Music፣ YouTube እና ሌሎች መድረኮች ዝግጁ ማድረግ። በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዘርፍ ያለው ሚና የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሮች ብዙ ጊዜ ከጀርባ የሚሰሩ ቢሆንም፣ የዘፈን ጥራትን እና የመጨረሻ ውጤቱን በእጅጉ ይወስናሉ። የዘፋኙ ሀሳብ በሙያዊ መልኩ ተቀናብሮ ለአድማጭ እንዲደርስ ያደርጋሉ።
አንዳንድ ቦታዎች ዝም ብለው ቦታ ብቻ አይደሉም። የታሪክ የትዝታ የሰውነት መልክ እና ማህደር ናቸው። ፒያሳ እንደዚያ ከነበሩ ቦታዎች አንዱ ነበር። «የፒያሳ ድምጾች (Echoes of Piassa)» የተሰኘ የዲጂታል ስነጥበብ አውደ ርእይ የድሮዋን ፒያሳ መልክ በምስላዊ ትረካ ሊያስጎበኛችሁ ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል ፈንድቃ ባህል ማእከል ላይ ከትሟል። ኤግዚቢሽኑ ተከፍቷል። እስከ ነሐሴ 18 ይቆያል። የልጅነት የጉርምስና እና የጉልምስና ታሪካችሁ ከፒያሳ ጋር በትዝታ እና ናፍቆት የተቆራኘ፤ ወይም በራሳችሁ መንገድ የቀደመ መልካችንን ከአሁኑጋ ማመሳከር ለወደዳችሁ ጊዜ አብጁና ጎብኘት አድርጉ። ጊዜው አጭር ነው ነገ ዛሬ ስትሉ ሳታውቁት እልም ይላል። በነገራችን ላይ ቋሚ ነገር ባናቆይ ኤግዚቢሽኑን የመሰለ መንፈስ ያለው ቋሚ ኤግዚቢሽን ቢኖር ሁሌም እመኛለሁ። #የፒያሳድምፆች
የክረምት ሥነ ጽሑፍ ስልጠና !
18ኛው ዓመታዊ የመጻሕፍት ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በይፋ ተከፈተ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የሚያዘጋጀው 18ኛው ዓመታዊ የመጻሕፍት ዓውደ ርዕይ በስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ በድምቀት ተከፍቷል። ከዛሬ ሰኔ 1 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ይቆያል ይምጡና ይታደሙ፤ መጻሕፍቶችን ይሸምቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ
18ኛው የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 🗓️ ከ ሰኔ 1 - 7 2018ዓ.ም 📍 AAU Main Campus, 6Kilo አይቀርም👌
በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደረገ፡፡ ወዲያውኑም የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ እየገፋ በመምጣቱ ያለመንግሥት ፈቃድ እንዲህ ዓይነት ጽሑፎችን እንዳያትምና እንዳያሰራጭ ዋስ ጠርቶ ከእስር ተፈታ፡፡ ጦርነቱ በተፋፋመበት ወቅትም ተስፋ ሕዝቡ ለነፃነቱ እንዲታገል የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን እያሳተሙ ከማሰራጨት አልቦዘነም ነበር፡፡ ለአብነት ያህል የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ባለው መሳሪያ ጠላትን እንዲከላከልና እጁን አጣጥፎ እንዳይቀመጥ የሚያሳስብና ‹‹የኢትዮጵያ ፋና›› የሚል ርዕስ ያለው ጽሑፍ እያሳተመ ያሰራጭ ነበር፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ተስፋ ታሰረ፡፡ በመኖሪያ ቤቱ የነበሩትን ጽሑፎች ቀደም ብሎ በመደበቁ በፋሺስቶች ዘንድ እንደወንጀለኛ የሚያስቆጥረው ነገር ስላልተገኘበት ከእስር ተፈታ፡፡ ከእስር ከተፈታ በኋላም ጽሑፎችን በማተምና በማሰራጨት አርበኞችን የማነቃቃት ስራውን ቀጠለበት፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት (1928 ዓ.ም - 1933 ዓ.ም) ብዙዎች በዱር በገደል ሆነው ወራሪውን ኃይል ፋታ ነስተው ታላቅ የአርበኝነት ተጋድሎ ባደረጉበት ወቅት ፣ ተስፋ ገብረሥላሴ የተለያዩ ወረቀቶችን እያባዛ የአገር ፍቅር ስሜትን የሚኮረኩር ፤ የአርበኞችን ጀግንነትም የሚገልጹ ጽሑፎችን በከተማ ይበትን ነበር፡፡ ተስፋ በመልዕክቶቹ አርበኛው እንዳይበተንና ኅብረቱን አጠንክሮ እንዲፋለም ከማሳሰብ ባሻገር የአርበኞች ማኅበር እንዲቋቋም ሃሳብ ካቀረቡ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡ በዚህ ምክረ ሃሳብ መሰረትም የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር በ 1931 ዓ.ም ሊቋቋም ችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፋሺስት ኢጣሊያ አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይፈፅም የነበረውን ግፍና በደል በወቅቱ ለንደን ይገኙ ለነበሩት ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ደብዳቤ በመላክ ያሳውቁ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ተስፋ በድጋሜ በፋሺስት ወታደሮች ታሰረ፡፡ ማተሚያ ቤቱም ተወረሰበት፡፡ በእስር ቤቱ ውስጥም እስረኞች በረሀብና በውሃ ጥም መጎዳታቸውን ተመለከተ፡፡ የእስር ቤቱን ኃላፊ አስጠርቶ ‹‹… አርባ ማር ትሬዛ ብር ስላለኝ ይፈቀድልኝና ዳቦ ገዝቼ ላብላቸው…›› ብሎ ጠየቀ፡፡ የእስር ቤቱ ኃላፊም በተስፋ አነጋገር ስሜቱ በመነካቱ ብዙ ዳቦ ፣ ሻይና ውሃ መጥቶ ለእስረኞች እንዲታደላቸው በማድረጉ እስረኛውን ሁሉ በረሀብና በውሃ ጥም ከማለቅ ታደገው፡፡ ከወራሪው የፋሺስት ኢጣሊያ ኃይል መባረር በኋላ ተስፋ ሰላማዊ ኑሮ ለመምራት ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡ ማተሚያ ቤቱንም በአዲስ መልኩ በማጠናከር ‹‹ሀ ሁ… እውቀት ይስፋ …ድንቁርና ይጥፋ… ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ.. ›› ብለው ጽሑፎችን ማሳተም እና ማሰራጨት ቀጠሉ፡፡ በዚህ ስራቸውም ትምህርትን በመላ ኢትዮጵያ ለማዳረስና መሃይምነትን ለማጥፋት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክተዋል፡፡ ዘመናዊ የሕትመት መሳሪያዎችን ከውጭ በማስመጣት ስራቸውን አስፋፉ፡፡ ‹‹ሀ ሁ››ን ፣ ‹‹አቡጊዳ››ንና ‹‹መልዕክተ ዮሐንስ››ን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ 300 በላይ መፅሐፍትን ማዘጋጀትና ማሳተም ችለዋል፡፡ የፊደል ገበታን ቀርፀው መሃይምነትን ለማጥፋት ካበረከቱት አስተዋፅኦ በተጨማሪ በአርበኝነት ትግላቸው ላደረጉት ተጋድሎ የቀኝ አዝማችነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ለስራ እጅግ የተለየ ክብር ነበራቸው፡፡ 97ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ሲያከብሩ‹‹ … ሆዴ እህል በልቶ ቢጠግብም እጄን ስራ ይርበዋል …›› በማለት ለስራ ያላቸውን ጉጉትና አክብሮት ገልፀው ነበር፡፡ እድሜያቸው ገፍቶ እንኳ በድርጅታቸው ዋና መስሪያ ቤት እየተገኙ የስራውን ሂደት ይቆጣጠሩና እርሳቸውም ኃላፊነታቸውን ይወጡ ነበር፡፡ ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ከእፅዋት የቀለም ዱቄት ቀምመውና በጥብጠው ፣ ከመቃ እንጨት ብዕር ቀርጸው በወረቀት ላይ ፊደል በመፃፍ በካርቶን ላይ እየለጠፉ በማቅረብ ሚሊዮኖችን ከመሃይምነት ያወጡና የእውቀትን ብርሃን የፈነጠቁ ታላቅ የአገር ባለውለታ ናቸው፡፡ ‹‹ያነበበ እውቀትን ጠገበ ፣ ድንቁርናን ክዶ ወደ እውቀት ተሳበ ፣ የጥበብን ገጿን ለማየት ቀረበ›› የሚለው ግጥም ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴን የሚመለከት ይመስላል፡፡ ቀኛዝማች ተስፋ የስራቸውን አስፈላጊነትና የትምህርትን ጥቅም ሲያስረዱ ‹‹ማንኛውም ሰው እናት አገሩ ባስገኘችለት፤ ሊቃውንት አባቶች አዘጋጅተው ባቆዩለት ፊደል ተምሮ ማንበብና መፃፍ ተቀዳሚ ተግባሩ ይሆናል፡፡ መምህራንም የፊደላትን ስነ ባሕርይ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም በየጊዜው የሚነሳው ብሔራዊ ትውልድ ራሱን ክዶ ሌላውን ሆኖ እንዳይገኝ ወይም ‹መነሻውን አያውቅ መድረሻውን ይናፍቅ› ከመሰኘት ነፃ ያደርገዋል›› ብለው ነበር፡፡ ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ በስራቸው ላይ ከጎናቸው ሆነው ሲያበረታቷቸውና ሲደግፏቸው ከኖሩት ወይዘሮ አለሚቱ ንጉሤ ጋር ጋብቻ መስርተው 13 ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በሕይወት እስከ ነበሩበት ጊዜ ድረስ 42 የልጅ ልጆችንም ዐይተዋል፡፡ ‹‹ሀ ሁ … እውቀት ይስፋ… ድንቁርና ይጥፋ … ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ...›› ብለው በማወጅ ድንቁርናን ለማፋት በመላ ኢትዮጵያ የፊደል ሰራዊትን ሲያዘምቱ የኖሩት አርበኛው ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ግንቦት 26 ቀን 1992 ዓ.ም አርፈው ስርዓተ ቀብራቸው በማግሥቱ ግንቦት 27 ቀን 1992 ዓ.ም በቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ “እውቀት ይስፋ ፣ ድንቁርና ይጥፋ ይህ ነው ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ።"
ታህሣሥ 24 ቀን 1895 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ፣ ቡልጋ ውስጥ አክርሚት በተባለ ስፍራ በመምህር ገብረሥላሴ ቢልልኝ እና ወ/ሮ ሥዕለአብ ወ/ሚካኤል ቤት ይችን ዓለም የተቀላቀለው ልጅ ‹‹ተስፋ›› የሚል ስም ተሰጠው፡፡ 4 ዓመት ሲሞላውም ከአባቱ እግር ስር ተቀምጦ ፊደል መቁጠር ጀመረ፡፡ የሕፃኑ ተስፋ ወላጆች አራሽ ገበሬዎችና ከብት አርቢዎች ስለነበሩ፣ ተስፋ እያደገ ሲሄድ ከትምህርቱ ይልቅ ወደ ከብት ጥበቃው እንዲያተኩር ተደረገ፡፡ ተስፋ ከትምህርት ይልቅ ከብት ጥበቃ ላይ እንዲያተኩር መደረጉ ያልተዋጠላቸው የተስፋ አያት መሪጌታ ቢልልኝ ተስፋን እንዲያስተምሩላቸው መምህር ገ/አብ ለተባሉ የቤተክህነት ሊቅ ወስደው ሰጧቸው፡፡ መምህር ገብረአብም ሕፃኑን በደስታ ተቀብለው ንባብን ፣ ዳዊትን ፣ ውዳሴ ማርያምን ፣ መልክዓ ማርያምን ፣ መልክዓ ኢየሱስንና ሰዓታት ዘሌሊትን አስተምረው በድቁና አስመረቁት፡፡ ተስፋ ድቁናውን ከተቀበለ በኋላም በአክርሚት ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ማገልገል ጀመረ፡፡ የተስፋ አባት መምህር ገብረሥላሴ ከቅስና ሙያቸውና ከግብርና ስራቸው በተጨማሪ በትርፍ ጊዜያቸው ከእፅዋት ቀለም እያነጠሩ ለፀሎትና ለአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚሰጡ መጻሕፍትን በብራና ይፅፉና ያዘጋጁ ነበር፡፡ በጊዜው ግብር የሚከፈለው አዲስ አበባ ነበር፡፡ ግብር መክፈያ ወቅቱ ሲደርስና ነጋዴዎቹ እንደ ሚመጡ ሲያውቅ ፣ ነጋዴዎቹን ከኋላ ከኋላ እየተከተለ ፣ እነርሱ ሳያዩት ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ፡፡ ነጋዴዎቹ ብዙ ርቀት ከተጓዙ በኋላ ተስፋን አዩት፡፡ ወደኋላ እንዳይመልሱት ብቻውን ሊሆን ነው፡፡ ስለሆነም ይዘውት አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ለ 5 ቀናት ያህል ከነጋዴዎቹ ጋር በእግሩ ተጉዞ አዲስ አበባ ደረሰ፡፡ በወቅቱ ቤተመንግስት ውስጥ ሥራ ወደነበራቸው ወደ ታላቅ ወንድሙ ብርሃኔ ገ/ሥላሴ ዘንድ ቀረበ፡፡ ታላቅ ወንድሙ ሲያዩት ፣ ‹‹እንዴት መጣህ? ለመሆኑስ እናትና አባታችን ሰምተዋል?›› ብለው በጥያቄ ሲያፋጥጡት ተስፋ ‹‹አልተናገርኩም›› ይላል። ‹‹በል አሁን ገብተህ እረፍና አብረውህ ከመጡት ሰዎች ጋር ትመለሳለህ›› ብለው አስገቡት። ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ትውልድ ስፍራው ሲመለስ ልቡም ዓይኑም ወደ ኋላ ዕየተመለከተ ፣ ‹‹እዚህማ ተመልሼ እመጣለሁ ፤ እስኪ የሚከለክለኝን አያለሁ›› እያለ እየዛተ ነበር፡፡ እንዳሰበውም አልቀረም በ 1909 ዓ.ም ተመልሶ ወደ አዲስ አበባ ሄደ፡፡ ታላቅ ወንድሙም ‹‹በል እንግዲህ ልብህ አላረፈም፤ መልሼም አልሰድህም፡፡ አንድ ክፍል ቤት አለችኝ ፤ እዚያች እረፍና የምትፈልገውን ትሰራለህ›› አሉት፡፡ ከተማውን ከተለማመደ በኋላም ተስፋ ራሱን ለመቻል ሲል ሱቅ በደረቴ ሆኖ ስራ ጀመረ፡፡ መርፌ ቁልፍ፣ ምላጭ ፣ መፋቂያና የመሳሰሉትን እያዞረ ይሸጥ ነበር፡፡ ከዚያም ታላቅ ወንድሙን ብድር ጠየቀ፡፡ የ75 ሳንቲም ብድር፡፡ በዚያች 75 ሳንቲም በወቅቱ ታዋቂ የነበረ ሽቶ ይሸጥ ነበር፡፡ ይህ ሽቶ ከፈረንሳይ በጅቡቲ በኩል አድርጎ ነበር የሚመጣው። ሽቶውን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስመጡ ነጋዴዎችም ነበሩ። ተስፋ ሽቶውን በ 75 ሳንቲም ገዝቶ ‹‹እሪ በከንቱ›› ወደሚባለው ሰፈር በመሄድ በሰፈሩ ላሉ ሴቶች በትርፍ ይሸጣል፡፡ ከዚህ ሽያጭ በሚያገኘው ገንዘብ መጽሐፍ ገዝቶ ይሸጥ ነበር፡፡ አዲስ አበባ በገባ በዓመቱ ፣ በወርሃ በየካቲት 1910 ዓ.ም ዘመን ተሻጋሪ የኢትዮጵያውያን ባለውለታ የሚያደርገውን ተግባር አከናወነ፡፡ የፊደል ገበታን አዘጋጀ፡፡ የተስፋ አባት መምህር ገብረሥላሴ ከእፅዋት ቀለም እያነጠሩ ለፀሎት እና ለአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚሰጡ መጻሕፍትን በብራና ይፅፉና ያዘጋጁ ስለ ነበር ተስፋም የአባቱን ፈለግ ተከትሎ የፍየል ቆዳ በእንጨት ላይ በመወጠር እየፋቀ ፣ ቀለሙን ከልዩ ልዩ እፅዋት እያነጠረና ፊደላትን በመቃ ብዕር እየፃፈ በማራባት ወገኑን የሚጠቅም ስራ ያከናውን ጀመር፡፡ በዚያ ጊዜ ግዕዝም ሆነ አማርኛ ማንበብና መፃፍ ፣ በቤተ ክህነትና በቤተመንግስት የተገደበ እንጂ ሰፊው ህዝብ ዘንድ አልተዳረሰም ነበር፡፡ ስለዚህ ለሰዎች መፅሐፍ ቅዱስ በግዕዝም በአማርኛም ካነበበላቸው በኋላ ፣ ‹‹በሉ ግዙ፤ ይጠቅማችኋል›› ሲላቸው ፣ ‹‹አንተን አብረን ካልገዛን ማን ያነብልናል? ልጆቻችን አያውቁም ፤ እኛም አናነብም›› ይሉት ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ‹‹እንዲህ ሰርቼ ፣ እንዲህ ቢማሩ ፣ በኋላ የተለያዩ መፅሀፎችን እያዘጋጀሁ እሸጣለሁ ፤ እኔም እጠቀማለሁ…›› ብሎ ሩቅ በማሰብ መጻሕፍትን ማዘጋጀት የጀመረው፡፡ በ 1921 ዓ.ም ማተሚያ ቤት በማቋቋም ‹‹እውቀት ይስፋ ፤ ድንቁር እና ይጥፋ ፤ ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ›› የሚለውን ኃይለ ቃል አርዕስት በመስጠት ፊደልን ፣ ፊደለ ሐዋርያንና አቡጊዳን በሦስት ረድፎች እያዘጋጀ በማሳተም በመላ ኢትዮጵያ ማሰራጨት ጀመረ፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ከፊደላት ጋር ተዋወቁ፡፡ የእውቀት ብርሃንን በመላ አገሪቱ የማዳረስ ዓላማ በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ምክንያት ሊሰናከል በተቃረበበት ጊዜ ተስፋ ራሱ ባዘጋጀው የፊደል ገበታ ተጠቅሞ አርበኝነቱን ጀመረ፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን የመውረሯ ጉዳይ እርግጠኛ እየሆነ በመጣበት ወቅት እንዲህ በማለት ጽፎ ለሕዝቡ አሰራጨ፡፡ ‹‹ከባሕር እየወጣ መጣልን አሳው ፣ በሰይፍ እየመተርን ባረር እቆላን ፈጥነን እንብላው ፣ ጥንት አባቶቻችን ምግባቸው ይህ ነው ፣ ምነው ያሁን ልጆች ዝምታው ምንድን ነው ፣ የባሕሩ አሳ ወጥቶ ከጎሬው ፣ አጥማጁ አንቆ እንጂ ስጋውን ይብላው፡፡›› ተስፋ ይህን መሰል ወኔ ቀስቃሽ ጽሑፎችን እያዘጋጁ በማተምና በማባዛት በመላ ኢትዮጵያ በማሰራጨት ሕዝቡ አገሩን ከወራሪው ኃይል ለመከላከል እንዲነሳ አድርገዋል፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን መውረር በጀመረችበት ወቅት አንዳንድ የኢትዮጵያን ባለስልጣናትን በገንዘብ እየደለለች የስለላና የማስከዳት ስራ ስትጀምር ተስፋ የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ፎቶ የጽሑፉ አርማ በማድረግ የዓድዋ ጀግኖች የፈፀሙትን አኩሪ ተግባር መድገም እንጂ ለገንዘብና ለስልጣን ብሎ አገርን ለጠላት አሳልፎ መስጠት እጅግ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን ለመግለፅ: ‹‹የተረገመ ነው አገሩን የከዳ ፣ ክብሩን ነፃነቱን ሀበሻን የጎዳ፡፡ ከኢትዮጵያ (ከሀበሻ) ጠላት ጉቦ የበላችሁ ፣ የት ነው የምትበሉት አገር ሳይኖራችሁ፡፡ ያልታመኑ ሌቦች ከሹመት ተሸረው ፣ አገሪቱን ይምሩ ታማኞች ተመርጠው›› በማለት ስለሁኔታው ሃሳባቸውን በግጥም አቅርበው ነበር፡፡ ተስፋ እነዚህንና መሰል ጽሑፎችን እያተመ በብዛት ሲያሰራጭ አገር በመክዳት የተጠረጠሩት ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆኑ ወረራውን የሚቃወሙትና የከዳተኞቹን ድርጊት የሚያወግዙት ሹማምንት ጭምር ያጉረመርሙ ጀመር፡፡ በጊዜው ይታተሙ የነበሩ ጽሑፎች ሁሉ በጽሕፈት ሚኒስቴር ሳይመረመሩና ፈቃድ ሳይሰጣቸው ማሰራጨት የተከለከለ ስለነበር ተስፋ ተይዞ እንዲቀርብና በየክፍላተ አገሩ አሳትሞ ያሰራጫቸው ጽሑፎችም እንዲሰበሰቡ ታዘዘ፡፡ ተስፋም ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ፊት ቀርቦ ‹‹በመላ ኢትዮጵያ ያሰራጨኸውን ስብከት የት ነው ያሳተምከው?›› ተብሎ ተጠየቀ፡፡ እርሱም ‹‹በሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስ ግቢ ውስጥ ባለው ማተሚያ ቤት ነው›› ብሎ መለሰ፡፡ በዚህም ምክንያት ሊቀ ጳጳሱ ‹‹ስለምን በብፁዕነትዎ ግቢ ውስጥ ወንጀል ተሰራ?›› ተብለው ሲጠየቁ ‹‹አገራችሁን አትካዱ ፤ ከጠላት ጉቦ አትቀበሉ› ብሎ መስበኩ ወንጀልነቱ ምንድን ነው?…›› ብለው መልስ ሰጡ፡፡ ጉዳዩ እንዲጣራ ተወስኖ ተስፋ
без подписи
ግንቦት 26 ቀን 1992 ዓ.ም ከ 26 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የፊደል ገበታ አባት አርበኛው ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ያረፉበት ዕለት ነበር። ‹‹ሀ ሁ…እውቀት ይስፋ…ድንቁርና ይጥፋ…ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ…›› ተስፋ ገብረ-ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋ..... ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ፊደል ያላት አገር ናት፡፡ ይህም ከበርካታ የዓለም አገራት ተለይታ እንድትታይ ከሚያደርጓት መገለጫዎቿ መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ፊደል በመላ አገሪቱ ተስፋፍቶ አገራዊ መገለጫነቱ ይዳብርና ብዙዎችም ማንበብና መፃፍ ችለው ከመሃይምነት ያመልጡ ዘንድ የአንድ ኢትዮጵያዊ ጠቢብ ርዕይና ጥረት ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህ አርቆ አሳቢ ጠቢብ ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ይባላሉ፡፡
"የኔ ዜማ" ምሽት! አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት! እባክዎ ሸር በማድረግ ተባበሩን! 55ኛው የባህል ማዕከል የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ግንቦት 05፥2018 ዓ.ም ይካሄዳል። በዕለቱም አንዱ ኮከብ፤ ተወዳጁ ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ የክብር እንግዳችን ሆኖ በመካከላችን በመገኘት ሙያዊ ልምዱን ያካፍለናል። እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ለእናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ተሰናድቶ ይጠብቃችኃል። #ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው። 🖊️ ከአዘጋጆች
без подписи
ጋሽ ስብሃት (ነፍስ ይማር) "ወደሽ ነው! ሁልሽም ልደቴን ታከብሪያታለሽ!" እያሉ ወዳጆቻቸውን ፈገግ ያሰኙ ነበር። ምነዋ ቢሉ አይረሴው የአርበኞች ቀን በሚከበርበት ዕለት ነውና የተወለዱት። ይኸው እናስታውሳቸዋለን። በነገራችን ላይ የቅርብ ወዳጃቸው ደራሲ አለማየሁ ገላጋይም በሚያዝያ ወር ነው የተወለደው። ሚያዝያ 5 ቀን 1960 ዓ/ም። ምናለ 22 ቀን ቢታገስ¡? አይ አሌክስ¡ እንኳን ተወለዳችሁ። አተረፍንባችሁ። 🖊️ ጸሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ ደራሲ ጋሽ ስብሐት ለአብ ገብረ እግዚአብሔር ሚያዝያ 27 1928 በአርበኞች ቀን ተወልደው : የካቲት 12 2004 በሰማዕታት ቀን አረፉ። እኛም ሟች ነን ከመሞታችን በፊት ግን ሟች አምላክ እንሁን፤ሞትን እንቅደመው
ቴአትርን ወደድኩት ዛሬ የኮከብ ሰው ቴአትር በዓለም ሲኒማ ሲከፈት እኔ ተመልካች ነበርኩ። ከወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ብንለማመደውም ሁሉም ሰው ዘንድ የነበረው ጥልቅ ስሜት ስራውን አግዝፎት የራሴን ቴአትር እምመለከት አልመሰለኝም ነበር። ግራ እስኪገባኝ ድረስ ከተመልካቹ ጋር አብሬ ነበርኩ ስስቅ፣ ሳለቅስ፣ ስናደድና ሳጨበጭብ ወዘተ ነበር። ፍቄ፣ መስኪ፣ አማንና እንዳለ ከልቤ ወደድኳችሁ። ትወና በዚህ ልክና ችሎታ ሲሰራ ደስ ይላል። እንዴት ሰው በዚህ መጠን ሌሎች ሰዎችን መሆን ይችላል? እጅግ በጣም ከባድ ነው። ይህ ዓይነቱ ረቂቅ አቀራረብ ለተመልካቹ ትልቅ ተቁዋቁሞ ይሰጠዋል። አዲስ ነገር እንዲያጣጥም መንገድ ይከፍትለታል። ቴአትር ከተለመደው የሳሎን መቸት እንዲወጣና ተመልካቹም የቴአትርን ልዩ ዓለም በምናቡ እንዲገነባ ያስችለዋል። በስመዓብ ልጆቼ እንዴት ታምሩ ነበር። ፍቄ፣ መስኪ፣ አማንና እንዳለ ብርሃኑ በጣም ወደድኳችሁ። ትወናን ዋኛችሁበት። ኖራችሁበት። ኧረ ከዚህም በላይ ከአጥናፍ አጥናፍ አስተጋቡበት። ቁዋንቁዋችሁ ቴአትር ብቻ ይሁን። የመምህራችንን ጋሽ ዓለሙ ገብረአብ ባለቤት ወሮ አስቴር ዕድሜሽን ያርዝመው። አዱና ጃምቢም ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ታላቁዋ ተዋናይት ሙሉዓለም ታደሰ ስለመጣሽ ደስ ብሎናል።አጋፋሪ ሽመልስ በቀለ ወርቅ ነበርክ። የመድረክ ባለሙያዎቹ፣ አስተባባሪዎች፣ ገፅ ቅብና አልባሳት፣ መብራትና ድምጽ ባለሙያዎች፣ ቁሳቁስ ባለሙያዎች እንዲሁም ዓለም ሲኒማ ለሀገራችንም ጭምር ኬር ይሁን ብያለሁ። 🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭 ከ ኮከቡ ሰው ቴያትር አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በቴያትሩ መክፈቻ ላይ የተሰማው
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ስለአባቱ፦ "አባቴና እናቴ የተገናኙበትን ጊዜ በትክክል ባላውቀውም መስሪያ ቤታቸው አንድ ላይ መሆኑን አውቅ ነበር፡፡ እርሱ የመድረክ መሪ እርሷ ደግሞ የመድረክ ተወዛዋዥ ነበረች፡፡ የተጋቡት በ1967 ዓ.ም ነው እናቴ ጥላዬ አራጌ የ17 ዓመት ወጣት ነበረች፡፡ እርሱ ደግሞ ወደ 20ዎቹ መጨረሻ ነበር ሲሉ አውቃለሁ፡፡ በተጋቡ በአንድ አመታቸው እኔ ተወለድኩኝ፡፡ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ብዙ አመት አብረው አልኖሩም፡፡ የተለያዩበትን ቀን በትክክል ባላውቀውም ለ6ኛ የልደት ቀኔ እለት ግን እናቴ አልነበረችም፡፡በ1974 መሆኑ ነው፡፡ አባቴ ከዚያ በኋላ ለራሱ አልኖረም፡፡ እናትም አባትም ሆኖ አሳደገኝ፡፡ የኖረው ለእኔ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት ቤት አስተምሮኛል፡፡ በዘመናዊ አስተዳደግና በጥሩ ስነምግባር አሳድጐኛል። አባቴ ሙዚቀኛ እንድሆን ፈጽሞ አይፈልግም፡፡ አስቦትም አያውቅም፡፡ ምክንያቱም በእነርሱ ዘመን በኪነጥበቡ አካባቢ የነበሩ ሰዎችን በኑሮ ውጤታማ አለመሆንን በማየት ይመስለኛል፡፡ በተጨማሪም ልክ የምስራ ሳይሆን የማጠፋ ስለሚመስለው የኔን ሙዚቀኝነት አልወደደውም ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን የስራ ውጤቴን የእኔንም ስነስርዓት ሲያየው ሞያዬን እየተቀበለው መጥቶ ነበር፡፡ ግን መጨረሻውን ሳያየው ቀረ የምወደው አባቴ በ1993 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡" ምንጭ ፦ ከተወዳጅ ሚዲያና ኮምኒኬሽን የተመዘዘ
ቴዲ አፍሮ አልበም ሆነ ነጠላ ዜማ በለቀቀ ጊዜ ሁሉ የሆነ መነሻሸጥ ውስጥ፣ የሆነ መፅናናት ውስጥ፣ የሆነ ፍካት ውስጥ ይከተናል!!! ቴዲ ሁሌም ለምንሰጠው ፍቅር እና ክብር የሚመጥን ኢትዮጵያዊ ነው። ነገ የሚለቀቀውን “ኢቶሪካ” አልበሙን በጉጉት የምንጠብቀው ሙዚቃ ለመስማት ብቻ አይደለም። ለመፅናናት፣ ለመነሸጥ፣ ድባባችንን ለማፍካትም ነው። And we need it badly! ኧረ ሐሙስ መቼ ነው!?🙌🏽 ከ ዳዊት ተስፋዬ Dejaf Tv
ዝምተኛው ቴዲ አፍሮ ! (በዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ) #Ethiopia | ቦታው መኖርያ ቤቱ ነው። ፊት ለፊቴ ተቀምጧል። አጠገቡ ባለቤቱ ክብርት አርቲስት አምለሰት ተቀምጣለች። ራት ቀርቧል። ጥያቄ ጠየኩት... " ቴዲ ላንተ የተለየ ቅዱስ ስፍራ የት ነው? " አስቦ መለሰልኝ... " ኢትዬጵያ ! " ብሎ ዝም አለ። ያልገባው መሰለኝ። ደግሜ ጠየኩት... " ማለቴ ከቅዱስ ስፍራዎች ላንተ የተለየው ቦታ የት ነው? " አሁንም እንደተረጋጋ መለሰልኝ " ኢትዬጵያ ! " አለና አንገቱን ደፋ አደረገ። ለመጨረሻ ጊዜ ሞከርኩኝ... እያስረዳሁት " ከአክሱም፣ ከላሊበላ፣ ከግሸን ከመሳሰሉት አንተ ልዩ ቅዱስ ቦታ የምትለው የትኛውን ነው? " ቴዲ ፈገግ ብሎ አየኝና " ሁሉንም ቅዱስ ስፍራዎች አከብራለሁ! ለእኔ ቅዱስ ቦታ ኢትዮጵያ ናት ! " አለኝ። የክብር ዶክተር ቴዎድሮስ ካሳሁን እኔ ቀርቤ እንዳየሁት እጅግ በጣም መልካም ሰው ነው። 1. ቴዲ ለየትኛውም ብሔር ጥላቻ ወይም ንቀት የለበትም። የተለየ የብሔር ፍቅርም የለውም። ለእርሱ ሁሉም ኢትዬጵያውያን እኩል የተወደዱ፣ የተከበሩ ናቸው። 2. ቴዲ አፍሮ የሚተማመነው በችሎታው፣ በዝናው ወይም በገንዘቡ አይደለም። በሰራዊት ጌታ በልዑል እግዚአብሔር ግን እጅጉን ይተማመናል። " የሚጠብቀኝ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነው" ብሎኛል። 3. ቴዲ ክርስቶስን ይወዳል። በሳሎኑ ግድግዳ ላይ የተሰቀለው የአለም መድሃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በትልቁ ተስሏል። ቴዲ ያንን ስዕል እያየ ይተርከዋል፣ ይገልጠዋል... የጌታ እናትም የልብ ወዳጁ ናት! 4. ቴዲ አፍሮ መዝሙር ያዳምጣል። የሚወዳቸውን ሁለት የድሮ መዝሙሮች ከፍቶ አሰምቶኛል። በራሱ ሐይማኖት ባይደራደርም ለሁሉም ሐይማኖቶች ክብር አለው። በራሱ ሐይማኖት ያሉትን የገዳም አባቶች ያከብራቸዋል፣ ይሰማቸዋል። 5. ቴዲ ሲናገር ቁጥብ ነው። ቃላት አያባክንም። በሚገባ አስቦ ነው የሚናገረው። ቃላቶቹን ያሻቸዋል፣ ያሽሞነሙናቸዋል! አጣፍጦ፣ አሳምሮ፣ ቀምሮ ያወጣቸዋል። ቴዲ ሲያወራ መስማት እንደ ሙዚቃው ነው። 6. ቴዲ አፍሮ ለትዳሩ ታማኝ ነው። አምለሰትን በስስት አይን ያያታል። እርሷም ሳራ አብርሃምን ' ጌታዬ ' ብላ እንዳከበረችው ባልዋን በፍቅርና በክብር ትንከባከበዋበች። ባልና ሚስቱን በቤታቸው ማየት፣ በፍቅር ሲያወሩ መስማት እጅግ ደስ ያሰኛል። 7. ቴዲ ያለውን ዝና የሚያውቀው አይመስልም። ወይም ትኩረት አይሰጠውም። ስለሱ ለማውራት ስሞክር ወሬውን ፈጥኖ ይቀይረዋል። መሞገስን ይሸሻል! በጣም ትሁት ነው! ዝምተኛነቱ ኩሩ ሊያስመስለው ይችላል። ግን ቴዲ ኩሩ አይደለም! ሰውን በሁለት እጁ የሚጨብጥ፣ ጎንበስ ብሎ እጅ የሚነሳ ጨዋ ሰው ነው። 8. ለቴዲ ሙዚቃ ህይወቱ ነው! በጣም ከፍተኛ የሙዚቃ ክህሎት Musical Intelligence እንዳለው ይታወቃል። ኑሮው ከቤቱ ወደ ስቱዲዬ፣ ከስቱዲዬ ወደ ቤቱ ነው። የሙዚቃ ስራዎቹ የሚወደዱት በስጦታው ላይ ትጋት ተጨምሮባቸው ነው። ቴዲ የሙዚቃ Genius ይመስለኛል ! 9. ቴዲ አፍሮ መጻህፍትን ያነባል። ለማንበብ ጊዜ አለው። ታሪክ ይወዳል። ታሪክን በጥልቀት ይመረምራል፣ ይፈትሻል፣ ያሰላስላል። ቴዲ ጥሩ አሰላሳይ (Thinker) ነው። 10. ከቴዲ ጋ ባሳለፍኳቸው ሰዓታት የትኛውንም የፖለቲካ ሰው አንስቶ አላወደሰም፣ አልተቃወመም። ፖለቲካዊ አስተያየቶችን ሲሰጥ አልሰማሁትም። 11. ቴዲ አፍሮ ቀርበው ሲያዩት በሚዲያ ከሚታየው በላይ ልዩ ሞገስ፣ ውበትና ክብርን የተላበሰ ሰው ነው። ጃኬት በቲሸርትና በጂንስ ለብሶ ዘውድ የጫነ፣ ካባ የደረበ ፣ በትረ መንግስት የጨበጠ ንጉስ ይመስላል። 12. ቴዲ ሐሙስ ከሚወጡት ስራዎቹ ሀገራዊ የሆኑትን ሁለቱን ከፍቶ አሰምቶኛል። እጅግ በጣም አስደናቂ ናቸው። ለሀገርና ለህዝብ ያለውን ፍቅር የሚያንፀባርቁ ታሪካዊ ስራዎች ናቸው። የክብር ዶክተር ቴዎድሮስ ካሳሁን ስራውን እንዲሰራ እንፍቀድለት። ቴዲን መጥላት ይቻል ይሆናል። በቴዲ መጠላት ግን አይቻልም። ንፁህ በሆነው ልቡ ውስጥ ጥላቻ የለም። " ፍቅር ያሸንፋል " ሲል በፍቅር ተሞልቶ ነው። ማንንም የመጉዳት አቅም የለውም። ወንድማችንን ያለ ልዩነት እንቀበለው። ሊወደድ፣ ሊደነቅ፣ ሊከበር የሚገባው ስጦታችን ነው! ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ
የጥበብ ዋርካ የዋርካ ጥላ የጥላ ግዙፍ የግዙፍ ረቂቅ የረቂቅ ልሂቅ የልሂቅ ቁጥብ የቁጥብ ለጋስ የለጋስ ማማ ከማማም ዳሽን የዳሽን ሰንደቅ የሰንደቅ ምጡቅ ከምጡቅም ሩቅ የሩቅ ድብቅ የድብቅ ቃል ሰንዱቅ ከሰንዱቅም ውድ ከውድም ውድ አርድ የውድ አርድ ትውልድ የትውልድ ግርማ ከግርማም ንዑድ የንዑድ ትሁት የትሁት አርማ የፍቅር ዜማ ቴዲ አፍሮ!! ተናፍቀህ ነበር መልካሙ ሁሉ ይግጠምህ!!! 🖊️ ያሬድ ሹመቴ
እነሆ እዚህ ደርሰናል። እንደ ፈጣሪ ፈቃድ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ በ 8:00 ሰዓት በአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ይከፈታል። በእኔ በኩል ቀረ የምለው ነገር የለም። እንደ ሌሎቹ ስራዎቼ በከፍተኛ ጥንቃቄ በጣም ጥሩ አድርገን እንደሰራነው እናምናለን። ኑ ተመልከቱት። በሰላም ያገናኘን! ከ አዘጋጁ - ዶ/ር ተሻለ አሰፋ እሁድ መጋቢት 20 በ 8:00 ሰዓት 🎭 በአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ