- Последний пост
- 6 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 16
- 1/48двое суток
- 18
- 1/72трое суток
- 19
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ቱርክ በሙሉ አቅሟ ወደ ቁርአን ወደ ኢስላማዊ እሴት እየተመለሠች ነው። 460 ሺህ የቁርአን ተማሪዎች ምረቃ ፕሬዚደንቱ ረጀብ ጠይብ ኦርዶሃን በተገኙበት ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- ╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
Kuuxa waynaanu kee cisidik yalli Nee kak dacrisaaya 🤲🤲🤲
ሰላት የልብ እረፍት፣ የነፍስ ብርሃን እና ወደ አላህ የሚያቀርብ ታላቅ አምልኮ ነው። አላህ ሰላታችንን ይቀበል፣ በዲኑ ያፅናን፣ ጀነቱንም ይወፍቀን። አሚን። 🤲🏽🕌
Fitna mango cubusunaam meqe Qunxaaneyti 🤲🤲🤲
"Diini sinni sehdayti bedu sinni lacih masala!" #Yimabla@shifa35
የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) ሙእሚንን በብዙ ባህሪዎች ገልፀዉታል፡፡ በብዙዎቹ ንግግሮቻቸው ዉስጥም የመልካም ሥነምግባርን አስፈላጊነት ጠቁመዋል፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡- * “ሙእሚን ለራሱ የሚወደዉን ነገር ለወንድሙ ይወዳል፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል፡፡) * “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳዉን ያክብር፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል፡፡) * “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል፡፡) * “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል።) * “ ከምእመናን መካከል የተሟላ የኢማን ባለቤቶች በሥነምግባር ይበልጥ ምርጥ የሆኑት ናቸው፡፡” * “አንድ ሙእሚን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ሆኖ ካገኛችሁት ቅረቡት፤ እሱ ጥበብን ያስተምራልና፡፡” (ኢብኑ ማጀህ ዘግበዉታል፡፡) * “መልካም ሥራው ያስደሰተው፤ መጥፎው ያስከፋው ሰው እሱ ሙእሚን ነው፡፡” (አሕመድ፣ ጦበራኒ፣ አል-ሓኪም ዘግበዉታል፡፡) * “አንድ ሙእሚን ወንድሙን በሚያስቸግር እይታ እሱን ማየት የለበትም፡፡” (ኢብኑል ሙባረክ ዘግበዉታል፡፡) * “ሙስሊም ሙስሊምን ማስደንገጥ የለበትም፡፡” (ጦበራኒ ዘግበዉታል፡፡) ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- ╰┈@ustaz_yasin_nuru_offcial
#ጣፋጭ #ሀዲስ አንብበው ለሌሎችም ማካፈል አይዘንጉ!! ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች አየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ አቡበክርን "ያ አባ በከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት። አቡበክርም "3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.ከአንተ ጋር መቀመጥ፣ 2.አንተን ማየት፣ 3.አንተ ባዘዝካቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ። ° ዑመርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?" "በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ 1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣ 2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣ 3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ። ° ዑስማንን ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን? በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.ሰዎችን ማብላት፣ 2.ሰላምታን ማብዛት፣ 3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣ ° አልይን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?" "በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.እንግዳን ማክበር፣ 2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣ 3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣ ° አባ ዘርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?" "በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :- 1.እርሃብን እወዳለሁ፣ 2.በሽታን እወዳለሁ፣ 3.ሞትን እወዳለሁ፣ ነብዩም "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?" አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣ በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣ ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ። ° ነብዩ ሰለላሁ አለየሂ ወሰለም🥰 " እኔም በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.ሽቶን እወዳለሁ፣ 2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣ 3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣ በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት። 1.መልዕክትን ማድረስ፣ 2. አማናን አደራን መጠበቅ፣ 3.ሚስኪኖችን መውደድ፣ ጅብሪል ተመልሶ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ ረሱልና ሱሃቦቻቸው ከመቀመጫቸው ሳይነሱ ተመልሶ ወደ መሬት ዱብ አለ አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:- "አላህም ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም እንዲህ ብሏል:- በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣ 2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣ 3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ። አላህ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ሱሃቦች የወደዱትን ያስወድደን! ° ይህን ጣፋጭ ሐዲስ በማንበባችሁ ከፍ ያለ አጅር ታገኛላችሁ -ኢንሻ አሏህ። ሼር በማድረግ ለሌሎች ብታካፍሉ ግን እነሱ ባነበቡት ልክ ለናንተም ሀሰናት ይፃፍላችኋል! ኢንሻ አሏህ!! አላህ አንብበው ከመጠቀሙት ያድርገን! ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- ╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
без подписи
ኢላሂ… ሰዎች ኃጢአት ሲሠሩ በሰዎች ፊት እንዳይጋለጡ ይፈራሉ፤ እኔን ግን በፊትህ ቆሜ እንዳልዋረድ እምፈራ አድርገኝ። ሰዎች ዱንያ ከስፋቷ ጋር ተጣባ ስታስጨንቃቸው ከጭንቀት የሚያወጣቸውን መፍትኄ ይሻሉ፤ እኔን ግን ልቤ ዕረፍትና መጽናናት የሚያገኘው በአንተ ዚክር ብቻ አድርግልኝ። ጌታዬ ሆይ፣ ልቤ በኃጢአት እንዳይረካ፣ በገፍላ ውስጥ እንዳይረጋ፣ በሚያልፍ የዱንያ ሕይወትም እንዳይታበይ ጠብቅልኝ። ደስታዬን ባንተ አድርግልኝ፣ ፍርሃቴን ካንተ፣ ተስፋዬንም ባንተ አድርግ። ኢላሂ… ፊቶች በሚለዋወጡበት ቀን ፊቴን በኃጢአት አታጥቁረው፤ ሚዛን በሚሰየምበት ቀን በመልካም ሥራዬ ሳይሆን በቸርነትህና በይቅርታህ ሚዛኔን አክብድልኝ፤ ባሮችህም በሲራጥ ላይ በሚያልፉበት ጊዜ እግሮቼን በምሕረትህ አጽናልኝ። እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ፤ አንተ ግን ኃያሉ ጌታ ነህ። እኔ ድሀ ነኝ፤ አንተ ግን ከሁሉ የበለጠ ሀብታም ነህ። እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ አንተ ግን እጅግ ይቅር ባይና አዛኝ ነህ። አሚን💚 ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- ╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
ቀብር ውስጥ ያለው ሰውዬ በጣም የሚመኘው ነገር ምንድነው ብላችሁ ታስባላችሁ ' ብለው እኮ ጠየቁ ተከታዮቻቸውን 😔 ~ ' በጣም የሚመኘው ነገር ሁለት ረከዓ መስገድ ነው ብለን እናስባለን ' አሏቸው ። ~ ' እሺ እሱ አልቻለም እናንተ ስገዱ ' አሉን😔 ~ ይሄ ሰውዬ አልቻለም እድል የለውም አይደል እንዴ ? ~ እናንተ እኮ እድል አላችሁ 🥹 ጊዜው ከማለፉ በፊት… በቃ እናንተ ተጠቀሙበት ¡¡ ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- ╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
📌ከሸይጧን ጋር ቃለምልልስ . ሥም ፡ ሸይጧን እንባላለን በዋናው፣ ኢብሊስም ሥማችን ነው፤ ሌሎች አባ ሙራ ይሉናል፤ በተለያየ ቋንቋ የተለያየ ሥም ይሠጡናል፡፡ አድራሻ ፡ ከሰማዩ ዓለም ከተባረርን ቆይተናል፤ ምድር ላይ ከነዝርያችን ተበትነናል፣ ዓለምን ከጫ እስከ ጫፍ ሞልተናል፡፡ ፓሰፖርት ቪዛ አያስፈልገንም፤ አንታይም አንጨበጥም፤ በፈለግነው ቅርፅ እንቀርባለን፤ ደም ዉስጥ ጭምር እንዘዋወራለን፡፡ ዕድሜ ፡ ለምነን በሰፊው ተሠጥቶናል፤ ተማፅነን የጠየቅነውን ተችረናል፤ አላህ ብቻ ይወቀው ቁጥሩን፤ ብቻ እስከ ዓለም ፍፃሜ አለን፡፡ ሥራ ፡ ምን ጥያቄ አለው የታወቀ ነው፤ አናፍርበትም ሥራችን ነው፤ ዓለም በፅድቅ ጎዳና እንዳትጓዝ ማተራመስ፤ በሠላም እኖራለሁ የሚልን ሕዝብ ማመስ፤ ከመንገዳችን የራቀውን አድኖ መመለስ፤ በወንጀል ኃጢኣት ነፍሱን ማደስ፣ ወደተዘጋጀልን የጀሀነም እሣት አብረን መፍሰስ፡፡ የሥራ ልምድና የብቃት ማረጋገጫ ፡- ተጨባጭ ሥራችንን ማየት ይቻላል፤ ጥረታችን በአብዛኛው ተሳክቶልናል፤ የዓለምን ሕዝብ 2/3ኛውን አክፍረናል፤ የሙስሊሞችን አንድነት ላያንሠራራ ንደናል፤ ወጣቶችን እግር በግር ተከታትለን አፍንድተናል፡፡ ደመወዝ : ቁርጣችን ቀድሞውኑ ተነግሮናል፤ ከጠዋቱ በእሣት ተበስረናል፤ ስለበሰበስን ዝናብ አንፈራም፤ ወደ ተውባው በር ፈፅሞ አንመጣም፤ ከጀነት እሣትን መርጠናል፤ በሰዎች ክፋትና ራስ ወዳድነት ተደስተናል፤ ከክፍያ ሁሉ ይህ ብቻ ይበቃናል፤ ምነው በንግግርህ እኛ እኛ ማለት ታበዛለህሳ? ድሮም ይኸው ነበር እኮ ትልቁ ሙሲባችን፤ ከእዝነቱ ለመባረር ምክንያታችን፤ ከንፁህ እሣት ተፈጥረን፤ ከጭቃ ለተፈጠረው ስገድ ተባልን፤ አምርረን ተቃወምን እንቢ አልን፤ በዚያው ተባረን ቀረን። የትምህርት ሁኔታ አልተማረም እንዳትለኝ ተምሬያለሁ፤ አያውቅም እንዳትለኝ አውቃለሁ፤ እያወቅኩ አጠፋለሁ፣ እያየሁም አበላሻለሁ። ዓላማህ ፡ በያዝነው መንገድ እዘልቃለን፤ በሥራችን እንበረታለን፤ ብዙ ተከታዮችን እናፈራለን፤ ወጣቱ እንዳይሾልክብን በሱስ መያዝ፤ ሽማግሌውን በረጅም ምኞት ማደንዘዝ፤ ዘፈን : እሱ እኮ ነው የምድር ላይ ድምፃችን፤ እኛን ወክለሎ መናገሪያችን፤ በዕድሜ ለገፋው ጥሩ ትዝታ፤ ለወጣቱ የልብ ትርታ፤ ሙሰልሰልስ? ታዳጊውን እንቀርፅበታለን፤ ኮረዳዋን እናስለቅስበታለን፤ ጎረምሳውን ሥራ እናስፈታበታለን፤ ግብረገብነትን እናጠፋበታለን፡፡ ስለ ኸልዋ ፡ የተነፋፈቁ ወዳጆችን እናገናኝበታለን፤ በምን ችግር አለው ሥም እናቀራርባለን፤ ሦስተኛ ወገን ሆነን እናደራድራለን፤ ሻይ ቡና እናስብላለን፤ ከኋላ ሆነን እንገፋለን፤ ሲወድቁ ጥለን እንጠፋለን፡፡ ኢኽቲላጥ ፣ ንፁህ እና ጠሃራውን ቀላቅለን፤ አሳስቀን አጨዋውተን አሳስበን፤ አቀራርበን አጠባብሰን፤ ቀዩን መስመር እንንዳለን፤ ከዚያ የለንበትም እንላለን፡፡ ፍቅር ፡ ይህን ጉዳይ እንዴት ላስረዳህ፤ ላታውቅ ነገር ላይገባህ፤ መተዳደሪያችን እሱ ነው፤ በሱ ሥም እንምላለን፤ እናት አባት እናስክዳለን፤ ዲነኛውን እናፈዛለን፤ እናከንፋለን ጨርቅ እናስጥላለን፤ እስከማጋደል ሁሉ እንደርሳለን፤ የሚመችህ የሰው ልጅ ባህሪ: ተናዳጅ ሰው ፈረሣችን ነው እንጋልበዋለን፤ ቀናተኛ ከልብ ያምነናል እንቅልፍ እናሳጠዋለን፤ ተጠራጣሪ ይሠማናል እናቃጥለዋለን፤ ሓሲድ ያዳምጠናል በቁሙ እንገድለዋለን፡፡ የዓላማህ ተባባሪዎች ፡ የቱን ጠርቼ የቱን ልተው፤ የቱን ጠቅሼ የቱን ልለፈው፤ ለጥቅም ያደሩ ሆዳም ዑለሞች፤ በሁለት ፊት የሚኖሩ አስመሳይ ሙናፊቆች፤ በፈጣሪያቸው እምነት ያጡ ከሀዲያን ካፊሮች፡፡ ሰዎችን በምንና እንዴት ታጠምዳለህ? ወጣቱን በፆታዊ ፍቅር ጎልማሳውን በገንዘብ በብር ሽማግሌውን በምኞት በማስከር . ከሸይጣን ቃለምልልስ ክፍል- 2 ስለ ነቢያችን ምን ትላለህ? ህብረተሰቡን የለወጡብኝ፤ ጣዖት አምላኪን ያነቁብኝ፤ ተውሒድ አንግበው ያሸሹብኝ፤ ተስፋ ማይቆርጡ እማይደክሙ፤ ተልዕኳቸውን በአግባቡ የፈፀሙ፡፡ ስለ አቡበክር ፡ እንደስሙ ሁሉ ታማኝ ነበር፤ በዲኑ ጉዳይ እማይበገር፤ የካብኩትን ጦር የናደብኝ፤ ሴራዬን ሁሉ ያወቀብኝ፤ በፅኑ አቋሙ የፈተነኝ። ስለ ዑመር ፡ ብርቱ ሰው ነበር ጠንካራ፤ አላህን እንጂ የማይፈራ ሞገስ ያደለው ቀብራራ ፤ ላስመሳይ ከሀዲ የማይራራ፤ እርሱ ባለበት ዝር አንልም፤ በሄደበት መንገድ አናልፍም፡፡ ሶላሐዲን አልአዩቢ፡ የዲን ጠባቂ ክንደ ብርቱ፤ የካፊር ጠላት እጀ ብረቱ፤ ዘብ የቆመ ለእምነቱ፤ የሰበሰብነውን ያተነነ፤ ጭፍሮቻችንን የበተነ፡፡ ስለ እነ ፊርዐውን እና አቡጀህል ምን ትላለህ? ፊርዐውን፡ የቅርብ ዘመድ ነው አጋራችን፤ ዋናው ሚንስትር ተባባሪያችን፤ ጌታ ነኝ ብለህ ጎርር አልነው፤ ያልነው አለ አጃጃልነው፤ እስከ ባህሩ ተከተልነው፤ በመጨረሻም አስበላነው፤ ውሃ ሲወስደው ጠፋን ጥለነው። አቡ ጀህል ፡ የኛ ጀለስ ነው እንደ ሥሙ፣ እሱና ዕውቀት አይስማሙ፤ ከአቋሙ የማመለስ ጅል፤ ዝንፍ ውልፍት ፍንክች የማይል፤ በድር ዘመተ እየፎከረ፤ አልተመለሰም በዚያው ቀረ፡፡ ለዓላማህ መሳካት ለነማን መልዕክት ታስተላልፋለህ? ለጥቅመኛ ዓሊሞች እና እልም ላሉ ጃሂሎች ለጥቅመኛ ዓሊሞች ፡ በጥቅማችሁ የመጣን እንዳትለቁ፤ ወንበራችሁን አታስደፍሩ አታስነኩ፤ አዋቂዎችን ወዲያ ግፉ፤ አላርፍ ላለው ሥም ለጥፉ፤ ለጃሂሎች ፡ ታውቃላችሁ ተኮፈሱ አትማሩ፤ ለምታደንቁት አጥብቃችሁ ተከራከሩ፤ ከርሱ በላይ አዋቂ የለም በሉ፤ በማያስቆጣው ሁሉ ተቆጡ፤ በአቋማችሁ ፅኑ አትለወጡ፡፡ ምን ትጠላለህ? አዛን እና ኣየት አል-ኩርሲ ስለ አዛን ፡ እኛን ለማባረር የተላከ ሚሳይል፤ እሱ ሲወጣ ችሎ መቆም አይሆንልን፤ ፈሣችንን እንኳን መቆጠጣር አንችል፡፡ አየት አልኩርሲ ፡ እኛ ነን ትሩፋቷን ለአቡ ሁረይራ የነገርነው፣ እሷን የሚያዘወትርን ፈፅሞ አንቀርበው። ሌላ እውነታ ንገረኝ ፡ ጠሃራ የሌለው ሰው ነው ማረፊያችን፤ ደጋሚ መተታም ባዕድ አምላኪ ነው ደንበኛችን፤ ነጀሳና ቆሻሻ ቦታ ነው መገኛችን፤ መላእክት ናቸው ጠላቶቻችን፤ እነርሱ የሚወዱትን እንጠላለን፤ እነርሱ የሚጠሉትን እንወዳለን ፤ ቁርኣን ከሚቀራበት ቤት አንገባም፤ ዚክር የሚያደርግን ሰው አንቀርብም ፡፡ ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- ╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
⭐የቁርአን ቱሩፋቶች ⭐ 2⃣ ቁርአን የልቦች ብርሃን፣ የነፍስ ስንቅ! 📖✨✨ በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው። ቁርአን ለአንዳንዶች መጽሐፍ ብቻ ሊመስላቸው ይችላል፤ ለምእመናን ግን የሕይወት ካርታ፣ የጨለማ ብርሃን እና የጌታቸው ንግግር ነው። እስኪ ቆም ብለን የዚህን ታላቅ ቃል ጥቂት ትሩፋቶች (በረካዎች) እንመልከት፡- 1. የልብ መረጋጋት እና ሰላም (Peace of Heart) 🌿💎 በዚህ በረበሸው ዓለም ውስጥ ለልባችን ብቸኛው መድኃኒት የጌታችን ቃል ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- > "... أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ" > "...ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ።" (ሱረቱ አል-ረዕድ፡ 28) ቁርአን በተቀራበት ቤት ውስጥ ሰላም ይሰፍናል፣ ጭንቀትና መከፋት ቦታ አይኖራቸውም። 🕌 💡 የእለቱ መልዕክቴ፡- ውድ እህት/ወንድሜ! ቁርአን እንዲቀራልህ አትጠብቅ፤ አንተ እራስህ ቅራው። ልብህ በዱንያ ስራ ደርቆ ከሆነ በቁርአን አርጥበው። ዛሬውኑ ቢያንስ 10 አንቀጾችን በመቅራት ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት አድስ። 🤝📖 ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- ╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
ቀድመን ደርሰናል የጎደለውን አሰውቀናል እንኳን ለ1447ኛው ዓ.ሂ ታላቁ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ኢድ ሙባረክ፤ Iid Mubaarak! 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Baga ayyaana Iid al-adha bara 1447tiin nuun gahe! 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
"የአረፋ ቀን ጾም ያለፈውንና የሚመጣውን የሁለት አመት ወንጀል ያስምራል።" ረሱልﷺ
የሐጅ (የእስልምና አምስተኛው ማዕዘን) ዋና ዋና አስተማሪ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦ 1. ፍጹም አንድነትና እኩልነትእኩልነት ማሳያ፦ ሁሉም ወንድ ሐጃጆች ተመሳሳይ ነጭ ልብስ (ኢሕራም) ይለብሳሉ።ዘርና ቀለም የሌለው፦ በሀብት፣ በስልጣን፣ በዘርና በቋንቋ መካከል ያለውን ልዩነት ያጠፋል።አንድ አምላክ፦ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአንድ ቦታ ተሰብስበው አንድ አምላክን ብቻ ያመልካሉ። 2. ትዕግሥትና ራስን መግዛትፈተናዎችን መቋቋም፦ በከፍተኛ ሙቀት፣ መጨናነቅና ድካም ውስጥ በትዕግሥት ማለፍን ያስተምራል።ክልክል ነገሮች፦ በኢሕራም ወቅት መናደድ፣ መጨቃጨቅ፣ ስድብና ስሜታዊነት በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው። 3. የመጨረሻው ዓለም (አኺራ) ማስታወሻየትንሳኤ ቀን ምስል፦ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በነጭ ልብስ ዓረፋ ሜዳ ላይ ሲቆሙ የመጨረሻውን የፍርድ ቀን ያስታውሳል።ዱንያን መተው፦ የቅንጦት ልብሶችንና ቁሳቁሶችን ትቶ መሄድ የሰው ልጅ ወደ ቀብር የሚወስደውን ከፈን ያሳያል። 4. ታሪካዊና መንፈሳዊ ትስስር የነቢያት ፈለግ፦ የነቢዩ ኢብራሂም ፣ የባለቤታቸው ሀጀር እና የልጃቸው ኢስማዒልን ታላቅ መስዋዕትነት ያስታውሳል።የሰይጣን ፈተና፦ በጀመራት (ድንጋይ መወርወር) ስነ-ስርዓት አማካኝነት ሰይጣንንና ክፉ ምኞትን የመታገል ምልክት ነው። 5. ሙሉ በሙሉ ለአላህ እጅ መስጠትለጥሪው ምላሽ መስጠት፦ "ለበይከ አሏሁመ ለበይክ" (ጌታዬ ሆይ ለጥሪህ ታዛዥ ሆኜ መጥቻለሁ) በማለት ፍጹም ታዛዥነት ይገለጻል።ወንጀል መማር፦ በትክክልና በቅንነት የተፈጸመ ሐጅ ሰውን ልጅ ከወንጀል አጥቦ እንደ አዲስ እንደተወለደ ሕፃን ያደርገዋል።
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ዛሬ ጀምረዋል 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضِيَ الله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". صحيح الجامع ، رقم 1133 ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:‐ «በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች በበለጠ ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል:‐ 1. ጾም፦ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም) 2. ዚክሮችን ማብዛት፦ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል። عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 7/224 وصحّح إسناده أحمد شاكر ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፤ «ከነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል። ከተክቢር አደራረግ መካከል፤ الله أكبر ، الله أكبر لا إله إلا الله ، والله أكبر ولله الحمد “አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች መካከል ነው። ሰዎችን ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈልጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት የተሳሳተ አፈፃፀም ነው።
🌙 የዓመቱ ምርጥ አስር ቀናት መባቻ፦ የዙልሒጃህ መጀመሪያ 🌙 ታላቅ ብስራት ለሙስሊሙ ኡማ! ዛሬ የዙልሒጃህ ወር አንደኛ ቀን ነው። አላህ በምድር ላይ ካሉ ቀናት ሁሉ በበለጠ የከበሩትን የአጅር በሮች በሰፊው የተከፈቱባቸውንና መልካም ስራዎች በእጥፍ የሚታሰቡባቸውን ታላላቅ አስር ቀናት እንድንደርስ አድርጎናል። ብዙዎቻችን የረመዳንን የመጨረሻ አስር ቀናት በጉጉት እንጠብቃለን ነገር ግን ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ ዙልሒጃህ የመጀመሪያ አስር ቀናት የሰጡንን ምስክርነት ልብ ልንለው ይገባል። _ እነዚህ ቀናት አላህ ዘንድ ያላቸው ክብር አላህ በቁርአኑ ታላቅነታቸውን ሲገልጽ በእነዚህ ቀናት ምሏል። በሱረቱል ፈጅር መጀመሪያ ላይ እንዲህ ይላል፦ وَالْفَجْرِ ۞ وَلَيَالٍ عَشْرٍ "በጎህ እምላለሁ። በአስርቱም ሌሊቶች (በዙልሒጃህ የመጀመሪያ አስር ቀናት) እምላለሁ። (ሱረቱል ፈጅር 1-2) የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "በእነዚህ አስር ቀናት ውስጥ እንደሚሰራው መልካም ስራ አላህ ዘንድ ይበልጥ የተወደደ ስራ ያለበት አንድም ቀን የላችሁም።" > ሶሃባዎችም፦ "ያ ረሱለላህ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን አይበልጥም?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፦ "አዎ፣ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን አይበልጥም ከአንድ ሰው በስተቀር... እርሱም በነፍሱና በገንዘቡ ወጥቶ ከዚያ ምንም ሳይዝ (ሸሂድ ሆኖ) የቀረ ሰው ብቻ ነው" አሉ። (ቡኻሪ) 🔖 በእነዚህ ቀናት ልንሰራቸው የሚገቡ ታላላቅ ኢባዳዎች እህቶቼና ወንድሞቼ! እነዚህ ቀናት ዝም ብለው የሚያልፉ የዱንያ ቀናት አይደሉም። እድሜያችን አጭር ናት አላህ እድሉን ሰጥቶን ዛሬ ላይ ስላደረሰን በቁጭትና በንቃት ልንጠቀምባቸው ይገባል። 1. ጾም (በተለይ የአረፋ ቀን)፦ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘጠነኛው ቀን (የአረፋ ቀን) ድረስ መጾም እጅግ የተወደደ ነው። በተለይ በአረፋ ቀን መጾም ያለፈውን የአንድ ዓመት እና የመጪውን የአንድ ዓመት ወንጀል ያስምራል። 2. ዚክርን ማብዛት፦ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በእነዚህ ቀናት ተህሊል (ላ ኢላሃ ኢልለላህ) ተክቢር (አላሁ አክበር) እና ተህሚድ (አልሐምዱ ሊላህ) ማብዛትን አዘውናል። 3. ሶላትን በወቅቱ እና በጃማዓ መስገድ፦ ፈርድ ሶላቶችን ጠብቆ መስገድና ሱናዎችን ማብዛት። 4. ቁርአን መቅራትና ሰደቃ መስጠት፦ በየቀኑ የምንችለውን ያህል ቁርአን መቅራት እንዲሁም የተቸገሩትን መርዳት። ዱንያ በስራና በጭንቀት ልታታልለን ትችላለች። ነገር ግን ዛሬ የጀመሩት አስር ቀናት የነፍሳችን ማደሻ ወቅቶች ናቸው። ምናልባት በሚቀጥለው ዓመት በእነዚህ ቀናት መሬት ላይ መሆናችንን ማንም አያውቅም። ስለዚህ ስልካችንን የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችንን እና የዱንያ ወሬዎቻችንን ለጥቂት ቀናት ቀነስ አድርገን ራሳችንን ለአላህ ታዛዥነት እናስገዛ። አላህ እነዚህን ቀናት በአግባቡ ተጠቅመው ከሚምራቸውና ጀነትን ከሚወርሱት ሳሊህ ባሮቹ ያድርገን። 📝 ራማስ አል ሀናኒ ╭┈──── •🔖• ╰┈➢ @Ramas_Alhanani
የአለህ በሮች ትንሽ ብትሆን እስቲ እንተበበር ሀቂቃ በመሥጂዳችን በየ አመቱ ከ300 በላይ ሰዎች ኡዱሂያ ከሌላ ቦታ ይመጠለቸው ነበር ዘንድሮ እነሱም የለንም አትጠብቁን ብለውናል የለን እድል ከሰው ሰብስበንም ቢሆን ቀኑን እንዲደሰቱ ማድረግ ነው, ከለከቹ በውስጥ መስመር ደረሰኙን ኮሜንት ላይ ለኩልን