tgindex
Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

Статистика

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 149
+35 за 5 дн.
Сутки
+39
+1,85%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
74
22 постов
Вовлечённость
3,4%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
16
1/48двое суток
18
1/72трое суток
19

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.19из sink1112

    "የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ቤት እግሩን ማራቅ ሲጀምር፣ ፍቅርም ከእርሱ ፈቀቅ ትላለች፤ ያን ጊዜ ከሚያየውና ከሚዳስሰው ሁሉ ጋር መጋጨት ይጀምራል። ግጭቱም ከሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ከተፈጥሮ፣ ከአካባቢው፣ ከማኅበረሰቡና ከራሱ የሕሊና ሙግት ጋር እንጂ። ​ፍቅር በሌለበት ምድር ባዶነት ትነግሣለች፤ ፍቅር በሌለበት ልብ የውስጥ ሰላም አይገኝም። ፍቅር ከራቀ ደግሞ ሁሉ ነገር ድቅድቅ ጨለማ ይለብሳል። ​ስለሆነም የሰው ልጅ ሆይ! ሙሉ ፍቅርን ታገኝ ዘንድ ሁልጊዜም እግሮችህ ወደ አምላክህ ቤት ይፋጠኑ። ያኔ ለሕሊናህ ፍጹም ሰላምና ፍቅር ታገኛለህ፤ ያን ጊዜ ባዶነትህ ይሞላል፣ ጨለማህም በብርሃን ይተካል።"

  • без подписи

  • без подписи

  • ብሎ : ሲከተሉትም አይቶ:- "ምን ትፈልጋላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም:- "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" አሉት:: ትርጉዋሜው "መምሕር ሆይ!"ማለት ነው:: "መጥታችሁ እዩ" አላቸው:: መጥተው የሚኖርበትን አዩ:: በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ:: አሥር ሰዓት ያህል ነበረ:: ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን #ዼጥሮስ ወንድም #እንድርያስ ነበረ:: +"+ (ዮሐ. 1:47) =>+"+ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ:: በኀዘን ወይም በግድ አይደለም:: "በተነ:: ለምስኪኖች ሰጠ:: ጽድቁ ለዘለዓለም ይኖራል" ተብሎ እንደ ተጻፈ:: +"+ (2ቆሮ. 9:7) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

  • ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኩዋን ለሐዋርያው "ቅዱስ እንድርያስ" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳቸሁ ✞✞✞ =>መሐሪ #እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ በዛ : ሰውነታችሁ ከፋ ሳይል በአባታዊ ርሕራሔው ጠብቆ ይሔው ወርኀ ሐምሌን በሰላም አስፈጸመን:: አይመስለንም እንጂ በእነዚህ 30 ቀናት ሚሊየኖች አንቀላፍተዋል:: ሚሊየኖች በደዌ ዳኝነት ተይዘዋል:: በርካቶቹም ከሃይማኖታቸው ወጥተዋል:: +ታዲያ እኛ ይህ ሁሉ ያልደረሰብን በጐ ስለሆንን አይደለም:: ይልቁኑ ቸርነቱ በእኛ ላይ ስለበዛ ብቻ ነው እንጂ:: አሁንም በሰላም ከአዲሱ ዘመን እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል:: =>በዚህች ዕለት ደግሞ እነዚህን ቅዱሳን እናከብራለን:- +*" ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ "*+ =>ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው #በቤተ_ሳይዳ አካባቢ ሲሆን የሊቀ ሐዋርያት #ቅዱስ_ዼጥሮስ ትንሽ ወንድም ነው:: አባቱም #ዮና ይባላል:: ገና ከልጅነቱ ጀምሮ አሣ ማጥመድን ከትልቅ ወንድሙ ተምሯል:: እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ ኦሪትን ተምሮ የመጥምቁ #ቅዱስ_ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኗል:: +ከእርሱም እያገለገለ ለ6 ወራት ተምሯል:: በወቅቱ ከወንጌላዊው (ወልደ ዘብዴዎስ) #ዮሐንስ ጋር ቅርብ ባልንጀራም ነበር:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ያን ድንቅ #ምሥጢረ_ሥላሴ ከተመለከቱትም አንዱ ነው:: +ጌታ ከጾም (ከገዳመ ቆረንቶስ) በተመለሰ ጊዜ እንድርያስ #መንፈስ_ቅዱስ አነሳስቶት ተከትሎታል:: መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያዐትት ኃጢአተ ዓለም - የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ" ማለቱን ሰምቶ ቅዱስ እንድርያስ ጌታን ተከተለ:: +በዚህም የመጀመሪያው የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመባል በቃ:: (ዮሐ. 1:47) ሊቁ #ማር_ገላውዴዎስም እመቤታችንን ሲያመሰግናት "ለሐዋርያ #እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ:: ለመጀመሪያው ሐዋርያ ለእንድርያስ ሃይማኖቱ ማርያም አንቺ ነሽ::" ብሏል:: (#መልክዐ_ስዕል) +ቅዱሱ ሐዋርያ ስሉጥ (ፈጣን) አገልጋይ እንደ ነበርም ወንጌል ይነግረናል:: (ዮሐ. 6:5) ለ3 ዓመታት ከ3 ወት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ : በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ : ምን ሃገረ ስብከቱ #ልዳ ብትሆን ብዙ አሕጉረ ዓለምን ሰብኩዋል:: +ይህች ቀን ሐዋርያው ከጌታ ጋር በመርከብ ውስጥ የተነጋገረባትና ቅዱስ ማትያስን ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ያዳነባት ናት:: ቅዱስ እንድርያስ 30 ቀናት የሚፈጅ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ ከአርድእቱ ጋር ወደ ወደብ ቢሔድም መርከበኞች ሁሉ አናሳፍርም በማለታቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣት መርከበኛ መስሎ ሐዋርያውንና አርድእቱን የሠላሳውን ቀን መንገድ በሰዓታት ልዩነት እንዲጨርሱ አድርጉዋል:: +ቅዱስ እንድርያስም ፍጡር (እንዲሁ ሰው) መስሎት ለጌታችን ስለ ጌታችን ሰብኮለታል:: መርቆታልም:: መርከበኛው ጌታችን መሆኑን ሲያውቅም ደንግጦ አልቅሷል:: "ሶበ አእመረ ኪያሁ ወጠየቀ አምሳሎ:: ዘተናገርኩ በድፍረት ምስሌከ ኩሎ:: ሥረይ ሊተ ጌጋይየ ወኅድግ ይቤሎ::" እንዲል:: +"ማረኝ?" ብሎታል:: ጌታችንም "አይዞህ እኔ ካንተ ጋር ነኝ" ብሎታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ ለወንጌል አገልግሎት ተግቶ ያረፈው ታሕሳስ 4 ቀን ነው:: +*" ቅዱስ ዻውሎስ መናኒ "*+ =>ይህ ቅዱስ መላ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ሲሆን የተባረከች ሚስት እና 2 ቡሩካን ልጆች የነበሩት አባት ነው:: #ቅዱስ_ዻውሎስ የነዳያን አባት : እጅግ ባለ ጸጋ : ቤተሰቡን የቀደሰና ባለ ሞገስ ሰውም ነው:: +ታዲያ ምጽዋት ወዳጅ ነውና ሲመጸውት : ሲመጸውት ሃብቱ አለቀ:: አሁንም መመጽወቱን አላቆመምና ቤቱ : ንብረቱ አልቆ ከነ ቤተሰቡ ነዳያን ሆኑ:: እርሱ ግን ያለ ምጽዋት ማደር አይችልምና አንድ ሃሳብ መጣለት:: ሚስቱንና ልጆቹን መሸጥ እንዳለበት ወሰነ:: +እነርሱ እንደ መሪያቸው ፍጹማን ናቸውና በደስታ ሃሳቡን ተቀበሉት:: መጀመሪያ ትልቁ ልጅ ተሸጠ:: ገንዘቡ ግን አሁንም በምጽዋት አለቀ:: ቀጥሎ ትንሹ ልጅ ተሸጠ:: አሁንም በምጽዋት አለቀ:: 3ኛ ደግ ሚስት ተሸጠችና እርሱም ተመጸወተ:: +በመጨረሻ ቅዱስ ዻውሎስ ራሱንም ሽጦ መጸወተና ይህ ድንቅ ሥራ ተጠናቀቀ:: ( ነገሩ ግራ እንዳያጋባን "ተሸጡ" ስንል ለአሕዛብ ወይም ለሌላ ሰው አይደለም:: 4ቱም የተሸጡት ለገዳማት ሲሆን ገዥዎቹ አበ ምኔቶቹ ናቸው:: ) ቅዱስ ዻውሎስ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መትቶ ምጽዋትንም : ገዳማዊ ሕይወትንም አትርፏል:: +በሁዋላ ወደ ተሸጠበት ገዳም ገብቶ እንዲህ ብሎ ጮኸ:- "ጌታ ሆይ! የሰጠኸኝን ሁሉ ላንተ መልሼ ይሔው መጥቻለሁ::" ጌታም ከሰማይ መለሰለት:- "ወዳጄ ሆይ! ባንተ ደስ ብሎኛል:: ተቀብዬሃለሁ" አለው:: 4ቱም #ቅዱሳን በንጹሕ ተጋድሎ ኑረው በዚህች ቀን ዐርፈው የማታልፈውን ርስት ወርሰዋል:: +*" ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት "*+ =>ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር #ሚካኤል : #ገብርኤል : #ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው:: +በ3ቱ ሰማያት ካሉት 9ኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (#የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው። መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው። #ለኖኅ መርከብርን ሲሠራ ያገዘው ፥ ከጥፋት ውሃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው:: +በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: #ቅዱስ_ሱርያል በሌላ ስሙ "#እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው:: +*" ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም "*+ =>እነዚህ ወጣቶች በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሲሆን ከተወለዱባት #ገሊላ ወደ ግብጽ (#ገዳመ_አስቄጥስ) በምናኔ መጥተዋል:: ለ20 ዓመታትም በክህነት አገልግሎትና በተጋድሎ ኑረዋል:: +አንድ ቀን መናፍቃን (አርዮሳውያን) በወታደር ተከበው መጥተው በገዳሙ እንቀድሳለን አሉ:: የራሳቸውን መስዋዕት መንበሩ ላይም አኖሩ:: ከዛ ያሉ አበው አዘኑ:: ወጣቶቹ መርቆሬዎስና ኤፍሬም ግን ለአምላካቸው ቀኑ:: +ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መናፍቃኑን "በክርስቶስ አምላክነት የማያምን በዚህ መቅደስ ውስጥ አይሰዋም" ብለው በድፍረት የመናፍቃንን መስዋዕት ወደ ውጪ በተኑት:: በዚያች ሰዓት መናፍቃኑ 2ቱን ቅዱሳን ወደ መሬት ጥለው ደበደቧቸው:: ረገጧቸው:: የቅዱሳኑ አጥንቶችም ተሰባበሩ:: በመጨረሻ በስቃዩ ብዛት 2ቱም በአንድነት ዐረፉ:: =>የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ ተረፈ ዘመኑን የንስሃ : የፍቅርና የአንድነት ያድርግልን:: ከወዳጆቹም በረከትን ያድለን:: =>ሐምሌ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ዻውሎስ መናኒ (ከቤተሰቡ ጋር) 3.ቅዱስ ሱርያል (እሥራልዩ) ሊቀ መላእክት 4.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ኤፍሬም (ሰማዕታት) 5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት (ፍልሠቱ) 6.እናታችን ማርያም ክብራ ኢትዮዽያዊት (የዐፄ ናዖድ ሚስት)=>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ) 2.አባ ሣሉሲ ክቡር 3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት 4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት =>+"+ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ጌታ ኢየሱስን ተከተሉት:: ጌታ ኢየሱስም ዘወር

  • “​በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሰራለሁ።’’          ✍️ዘፍጥረት 39፥9

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ††† ✝✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን ሴት : ሕዝቅኤል ነቢይ እና ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝✝ ቅዱስ ሴት ነቢይ †††✝✝ ††† አባታችን ሴት የመጀመሪያዎቹ ፍጥረቶች የአዳምና ሔዋን የተባረከ ልጅ ነው:: ቀደምተ ፍጥረት አዳም እና ሔዋን በዕጸ በለስ ምክንያት ከገነት ከተባረሩ በኋላ በመጀመሪያ ቃየን እና አቤልን ከነ መንትያዎቻቸው ወልደው ነበር:: ነገር ግን የልጅ ደስታቸው ቀጣይ ሊሆን አልቻለም:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ቃየን ሲሆን ወንድሙን አቤልን በጾታዊ ፍላጐት ምክንያት በመግደሉ ነበር:: የአቤል ሞት ለአባታችን አዳም መራር ዜና ነበር:: ወላጅ እንኳን ደጉን ይቅርና ክፉ ልጁም እንዲለየው አይፈልግምና:: ቅዱስ አዳም ቅዱስ አቤልን ቀብሮ: ፈጽሞ አለቀሰ:: ልቅሶውም እንዲሁ የወርና የሁለት ወር አልነበረም:: አራት ኢዮቤልዩ (ሃያ ስምንት ዓመታት) ነበር እንጂ:: ይህንን ሐዘንና ልቅሶ የተመለከተ እግዚአብሔር ደግሞ ደግ ፍሬን በሔዋን ማኅጸን ውስጥ አሳደረ:: ይሕ ሕፃን በተወለደ ጊዜ "ሴት" ብለው ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "የአቤል ምትክ" እንደ ማለት ነው:: ሴት ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በብዙ ነገሩ አዳምን የሚመስል ነበረ:: ደም ግባቱ: ቅንነቱ: ታዛዥነቱ: ደግነቱ ሁሉ ልዩ ነበር:: በዚህም አዳምና ሔዋን ተጸናንተዋል:: ትልቁ ነገር ደግሞ ዓለም የሚድንባት እመቤት ድንግል ማርያም ከስልሳ በላይ የአዳም ልጆች ተመርጣ ለቅዱስ ሴት መሰጠቷ ነው:: ይሕንን ምሥጢርና የሴትን ማንነት ያስተዋለው ሊቁ አባ ሕርያቆስ እመ ብርሃንን እንዲህ ሲልም አመስግኗታል:: "ሒሩቱ ለሴት - የሴት ደግነቱ: በጐነቱ: ቅንነቱ አንቺ ነሽ" (ቅዳሴ ማርያም) አባታችን ሴት በሚገባው ትዳር ተወስኖ ቅዱስ ሔኖስንና ሌሎች ብዙ ልጆችን ወልዷል:: አባታችን አዳም ባረፈ ጊዜ የዚህን ዓለም እረኝነት (በደብር ቅዱስ ላሉት) ተረክቧል:: አዳምም ልጆቹንና ወርቅ እጣን ከርቤውን አስረክቦታል:: ሴት እንባው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አስቀድሞ አዳምን: አስከትሎም ሔዋንን ገንዞ በክብር ቀብሯቸዋል:: ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ከሥጋቸው ጋራ በቤተ መዛግብት (በተቀደሰው ዋሻ) ውስጥ አኑሮታል:: የአገልግሎት ዘመኑ በተፈጸመ ጊዜ ደጉ ሴት ኃላፊነቱን ለልጁ ሔኖስ ሰጥቶ በዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመቱ ዐርፏል:: እርሱም ከወላጆቹ አዳምና ሔዋን ጋር ተቀላቅሏል:: ††† ✝✝ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ✝✝ ††† ††† ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤል የነበረው ቅ/ል/ክርስቶስ በ500 ዓመት አካባቢ ሲሆን የጼዋዌ (ምርኮ) አባልም ነበር:: እሥራኤልና ይሁዳ ወደ ባቢሎን በምርኮ ሲወርዱ አብሮ ወርዷል:: ቅዱሱ ከአራቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ሐረገ ትንቢቱም በአርባ ስምንት ምዕራፎች የተዋቀረ ነው:: በዘመኑ ሁሉ ቅድስናን ያዘወተረው ቅዱሱ ከደግነቱ የተነሳ በጸጋማይ (ግራ) ጐኑ ተኝቶ ቢጸልይ ስድስት መቶ ሙታንን አስነስቷል:: ወገኖቹ እሥራኤልንም ያለ መታከት አስተምሯል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት ታላቁን ራዕይ እንዳየ ታስተምራለች:: ነቢዩ በፈለገ ኮቦር ካያቸው ምሥጢራት እነዚህን ያነሷል:- 1.እግዚአብሔርን በዘባነ ኪሩብ ተቀምጦ ሲሠለስና ሲቀደስ አይቶታል:: የኪሩቤልንም ገጸ መልክእ በጉልህ ተመልክቷል:: (ሕዝ. 1:1) 2.በመጨረሻው ቀን ትንሣኤ ሙታን : ትንሣኤ ዘጉባኤ እንደሚደረግም ተመልክቷል:: (ሕዝ. 31:1) 3.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ኆኅት ኅትምት/ኆኅተ ምሥራቅ (የምሥራቅ ደጅ) ሁና አይቷታል:: ይሕ የምሥራቅ ደጅ (በር) ለዘላለም እንደታተመ ይኖራል:: የኃያላን ጌታ ሳይከፍት ገብቶ: ሳይከፍት ወጥቷልና:: (ሕዝ. 44:1) በመጨረሻ ሕይወቱ እሥራኤል ለክፋት አይቦዝኑምና ነቢዩን አሰቃይተው ገድለውታል:: †††✝✝ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ✝✝††† ††† አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስ እና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ : በገሊላ አካባቢ አድጐ : ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕፃን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው:: ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለአሥራ አምስት ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኳን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላእክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው:: በዚህ ቀንም ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል:: ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ለሰባ ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም : በመጽሐፍም ደክሟል:: ሦስት መልዕክታት : ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት : እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጓቸዋል:: ዳግመኛ ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት:: ††† እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:- ¤ወንጌላዊ ¤ሐዋርያ ¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም ¤አቡቀለምሲስ(ምሥጢራትን ያየ) ¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት) ¤ወልደ ነጐድጓድ ¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር ¤ፍቁረ እግዚእ ¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ) ¤ቁጹረ ገጽ ¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ) ¤ንስር ሠራሪ ¤ልዑለ ስብከት ¤ምድራዊው መልዐክ ¤ዓምደ ብርሐን ¤ሐዋርያ ትንቢት ¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን ¤ኮከበ ከዋክብት ††† በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: የሴት ደግነቱ : የሕዝቅኤልም በረከቱ ይደርብን:: ††† ሐምሌ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሴት ነቢይ (ወልደ አዳም) 2.ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ 3.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ቅዳሴ ቤቱ) 4.ቅዱስ አሞን ሰማዕት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት 2.አቡነ መብዐ ጽዮን ጻድቅ 3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ 5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮጵያ) 6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት 7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት ††† ". . . "እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም" ይላል ጌታ እግዚአብሔር:: "የእሥራኤል ቤት ሆይ! ተመለሱ:: ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ:: ስለ ምንስ ትሞታላችሁ?" በላቸው::" ††† (ሕዝ. ፴፫፥፲፩) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ✝✝††† እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዘዮሐንስ እና ለሰማዕቱ አባ ኖብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ††† ††† ኢትዮጵያዊው ጻድቅ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሸዋ (መርሃ ቤቴ) ነው:: ወላጆቻቸው ዘካርያስ እና ሶፍያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ : እመ ብርሃንን የሚወዱና ለነዳያን የሚራሩ ነበሩ:: ደጉ ዘካርያስ መስፍን ሲሆን እርሱ በሌለበት የሸዋ ገዢ ሊያገባት በመሞከሩ ቅዱስ ገብርኤል ቀስፎታል:: ሕዝቡ ገዢነቱን ለዘካርያስ ሰጥተውታል:: ከቆይታ በኋላም ድንግል ማርያም የተባረከ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን "ዮሐንስ" አሉት:: በሒደት ግን ዘዮሐንስ (የዮሐንስ) ተብሏል:: ቅዱሱ ዘዮሐንስ እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ በእናቱ እቅፍ ቆይቶ ወደ ትምሕርት ገብቷል:: ጸጋ እግዚአብሔር ጠርቶታልና በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አደን ይወድ ነበርና ሊያድን ሲወጣ 'ብርሕት ደመና' ድንገት ነጥቃ ከኢትዮጵያ (ሽዋ) ወደ ኢየሩሳሌም (ጐልጐታ) አደረሰችው:: ደስ ብሎት ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ደመናዋ ወደ ሃገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከሰማይ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ወርደው ባረኩትና "ክፍልህ ከእኛ ጋር እንዲሆን መንን" አሉት:: ዘዮሐንስ ወላጆቹንና ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ (ዲቁና ነበረውና) ሃያ አምስት ዓመት ሞላው:: ያን ጊዜ ወላጆቹ "እንዳርህ" ቢሉት "የለም! አይሆንም" አላቸው:: አርጅተው ነበርና ስለእነርሱ ዕረፍት ጸለየ:: ፈጣሪም ሰምቶታልና ሁለቱም በክብር ተከታትለው ዐረፉ:: ሕዝቡ በወላጆቹ ፈንታ "እንሹምሕ" ቢሉት "እንቢ" ብሎ ወርቁን : ብሩን : ርስቱን : ቤቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገባ:: ጊዜው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባረፉ በሃምሳ ዓመት አካባቢ ሲሆን አባ ሕዝቅያስ አበ ምኔት ነበሩ:: (ከዚህ በኋላ አንቱ እያልን እንቀጥል) አባ ዘዮሐንስ ለሰባት ዓመታት ገዳሙን ረድተው መነኮሱ:: እንደ ልማዱ ደመና ነጥቆ ወስዷቸው ከኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳት ቅስና ተቀብለዋልና በደብረ ሊባኖስ ለሃያ አምስት ዓመታት አገለገሉ:: ቤተ መቅደሱን በመዓልት ሰባት ጊዜ በሌሊት ሰባት ጊዜ ያጥኑ : እልፍ እልፍ ይሰግዱ : ተግተው ይጸልዩ : ይታዘዙም ነበር:: ከዚያም በፈጣሪ ትዕዛዝ በትግራይና በሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ወንጌልን ሰብከዋል:: እድሜአቸው ሰባ በሆነ ጊዜ ወደ ጌታ መቃብር (ጐልጐታ) ሔደው ተሳልመው በእርሱ (በጌታ) ትዕዛዝ ወደ ደራ (ጣና ዳር) ተመለሱ:: በአካባቢውም ገብርኤልና መስቀል ክብራ የሚባሉ ደጋግ ባለ ትዳሮች ነበሩና በእንግድነት ከቤታቸው አደሩ:: ቤቱ በቅጽበት በበረከት ሞላ:: እነርሱም የጻድቁን አምላክ አመሰገኑ:: ቀጥሎም በመስቀል ክብራ መሪነት ጻድቁ ዘዮሐንስ ወደ ክብራን ገብርኤል ደሴት ገቡ:: (በነገራችን ላይ ደሴቱ ክብራን የተባለ መስቀል ክብራ በምትሰኘው ደግ ሴት ስም ነው:: እርሷና ባሏ ገብርኤል የተቀደሱ ሰዎች ነበሩና::) ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ ወደ ደሴቶቹ (ክብራንና እንጦንስ ኢየሱስ) እንደ ገቡ ደሴቶቹ በግማሹ የስውራን ቤት : እኩሉ ደግሞ የጣዖት (ዘንዶ) አምላኪዎች መኖሪያ ነበር:: ጻድቁ ክብራን ገብርኤልንና እንጦንስ ኢየሱስን የመሠረቱት በ1315 ዓ/ም አካባቢ በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን ነው:: በአካባቢው ዘንዶ ይመለክ ነበርና ያንን በጸሎታቸው አጥፍተው ሕዝቡን አጥምቀዋል:: በዚያም ገዳሙን የወንድና የሴት ብለው ከፈሉ:: የወንዶች ክብራን ሲሆን ሴት አይገባበትም:: አበ ምኔቱም ራሳቸው ጻድቁ ነበሩ:: የሴቶች እንጦንስ ኢየሱስ ከካህናት በቀር ወንድ አይገባበትም:: እመ ምኔቷም እናታችን ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ሆነች:: ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ በክብራን ለሰላሳ አምስት ዓመታት ተጋድለዋል:: ለጸሎት ከመቆማቸው ብዛት እግራቸው አብጦ : ቆሳስሎ ነበር:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ይገለጽላቸው : ያነጋግራቸውም ነበር:: እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ሠርተው: ለወንጌል እንደሚገባ ኑረው: በተወለዱ በመቶ አምስት ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ጌታችንም በስማቸው ለተማጸነና ገዳማቸውን ለሳመ የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 13 ቀን ይከበራል:: ገዳማቸው (ክብራን ገብርኤልና እንጦንስ ኢየሱስ) ድንቅ ነውና እንድታዩት ተጋብዛቹሃል:: ††† ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት ††† ††† በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል:: ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል:: በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣዕመ ስብከቱም ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል:: ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች:: ††† ቸር ጌታ መድኃኔ ዓለም በጻድቁና በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ††† ሐምሌ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮጵያዊ) 2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት 3.መቶ ዘጠና ሺህ ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማኅበር) 4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ 5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮጵያዊ) 6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት 7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ) 3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ) ††† "ስለዚህ እኔ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ስለሚሆን በጌታ በኢየሱስ ስለማመንና ለቅዱሳን ሁሉ ስለሚሆን መውደድ ሰምቼ ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም::" ††† (ኤፌ. ፩፥፲፭) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

  • без подписи

  • без подписи

  • ††† እንኳን ለእናታችን ቅድስት መሪና ሰማዕት እና ቅዱስ ለንጊኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ታላቋ ቅድስት መሪና ሰማዕት (SAINT MARINA THE GREAT) ††† ††† እናታችን ቅድስት መሪና ስም አጠራራቸው ከከበረ : ተጋድሏቸው ካማረ ታላላቅ ሴት ሰማዕታት አንዷ ናት:: ተወልዳ ያደገችው ከዋናው ዘመነ ሰማዕታት በፊት በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ነው:: አባቷ ዳኬዎስ የሚባል ጣዖት አምላኪ ቢሆንም እናቷ ግን ክርስቲያን ነበረች:: ነገር ግን እናቷ ገና በ5 ዓመቷ ሞተችባትና ለሞግዚት ተሰጠች:: የእግዚአብሔር ጥበብ ሆኖ ሞግዚቷ ደግ ክርስቲያን ነበረችና ለ10 ዓመታት ሃይማኖተ ክርስቶስን እና ምግባረ ጽድቅን አስተማረቻት:: ዕድሜዋ 15 ዓመት ሲሆን አባቷ ዳኬዎስ አረፈ:: በዘመኑ ዳኬዎስ የሚሉት (ቅዱስ መርቆሬዎስን የገደለው) ክፉ ንጉሥ ነበርና ክርስቲያኖችን አሳደዳቸው:: ይህን ዜና ቅድስት መሪና ስትሰማ ደስ አላት:: እጅግ ባማረ ንጽሕና እንደ ኖረች ሁሉ በክርስቶስ ስም ደሟን ለማፍሰስ አስባ ወደ ንጉሡ መኮንን ሔደች:: ††† አበው እንዳስተማሩን ከሴቶች ሰማዕታት በውበትና ደም ግባት እንደ ቅዱሳት:- *መሪና *አርሴማ እና *ጣጡስ የሚያክል የለም:: ዐይንን ማፍዘዝ የሚችል ውበት ነበራቸው:: መኮንኑ መልኩዋን ዐይቶ ሰውነቱ ተናወጠ:: "ጣዖት አምልኪና የእኔ ሚስት ሁኚ" አላት:: እርሷ ግን መኮንኑን ከነ ጣዖቱ አቃለለችው:: "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ" አለችው:: መኮንኑ ካነጋገሯ የተነሳ ተቆጥቶ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ:: መሬት ላይ ጥለው በብረት ዘንግ ቢመቷት አካሏ እየተቆረጠ ብዙ ደም ፈሰሰ:: ወስደውም ጨለማ ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ አድኗት: አጽንቷትም ዐረገ:: በማግስቱ በመጋዝ አካሏን ቆራርጠው ጣሉ:: ዳግመኛ ሊቀ መላእክት አዳናት:: ወደ ጨለማ ክፍል ወስደው ሲጥሏት ትልቅ ዘንዶ መጣባት:: እጆቿ ተዘርግተው እጸለየች ዋጣት:: እርሷ ግን ጸሎቷን ቀጠለች:: ከደቂቃዎች በሁዋላ ግን ዘንዶው ለ2 ተሰነጠቀና እጆቿ እንደተዘረጉ ወጣች:: በሌላ ቀን ግን ሰይጣን ፊት ለፊት መጥቶ ታገላት:: ከሰማይ ነጭ ርግብና መስቀል ወርዶላታልና አልቻላትም:: ከእግሯ በታች ጥላ ደጋግማ ረገጠችው:: ሰይጣንም በሐፍረት እየጮኸ ሔደ:: "ለሰይጣን ኬደቶ ከመ አሣዕን በእግር" እንዲል:: (እንዲህ ነበሩ የቀደመው ዘመን እናቶቻችን) መኮንኑ ከክርስትና ያስወጣት ዘንድ በትልቅ ጋን ውሃ አስፈልቶ "በዚያ ላይ ቀቅሏት" አለ:: ድንገት ግን ከሰማይ ነጭ ርግብ ወርዳ: ውሃውን አቀዝቅዛ: 3 ጊዜ በውሃው አጠመቀቻት:: (እስከዚህ ሰዓት ድረስ አልጠመቀችም ነበርና) ርግቧ የብርሃን ልብስ አልብሳ: አክሊለ ክብር ደፋችላት:: መኮንኑ ተስፋ ስለ ቆረጠ "አንገቷን በሰይፍ ምቱ" አለ:: በዚያች ሰዓት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ "ብጽዕት መሪና ብጽዐን ይገባሻል" አላት:: "ስምሽ በሚጠራበት: መታሰቢያሽ በሚደረግበት ሁሉ በዚያ ረድኤት: በረከት ይበዛል:: አንቺን ያከበረውን አከብረዋለሁ:: ከርስትሺም አስገባዋለሁ" ብሏት ጌታችን ዐረገ:: ወታደሮቹ አንገቷን በሰየፉ ጊዜ ታላቅ መነዋወጽ ሆነ:: ድውያን ተፈወሱ: ዕውሮች አዩ: አንካሶች ረቱ: የማይሰሙትም ሰሙ:: ቅዱሳን መላእክትም ከሰማያት ወርደው የቅድስት መሪናን ነፍስ በዝማሬ አሳረጉ:: ††† ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት ††† ††† ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22) ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ "አሞኛል" ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ:: በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ:: ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች:: ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል:: "ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ:: በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ:: ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት:: ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት : ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ:: በመጨረሻም በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽድቅ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: በዚህች ዕለትም አይሁድ አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል:: ††† እግዚአብሔር በቸር ጥሪው ሁላችንም ወደ ቀናው የጽድቅ ጐዳና ይጥራን:: ከሰማዕታቱም ረድኤት በረከት ይክፈለን:: ††† ሐምሌ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት መሪና እናታችን (ታላቋ ሰማዕት) 2.ቅዱስ ለንጊኖስ ሐራ (ሐዋርያና ሰማዕት) 3.ቅዱስ አብጥልማዎስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት 2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት 3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል) 4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ 5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ 6.አባ ሳሙኤል 7.አባ ስምዖን 8.አባ ገብርኤል ††† "ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል : ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ : እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል::" ††† (ዮሐ. 19:33) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи