tgindex
አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

አጫጭር ጠቃሚ ፅሁፎች

Статистика
@so_funyанглийский

✍No Matter what language you speak. ☞This channel will make reader . ➡️Some time i have to post ads to Grow the channel. ➡️If you have Some Gifs or Videos or FEED BACK then Feel Free to Share With 👉some Funny pic ,Videos & GIFs.

Последний пост
16 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 164
−4 за 2 дн.
Сутки
−2
−0,17%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 400
20 постов
Вовлечённость
206,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ፈረንሳይ -ከሴኔጋል ግምት ፈረንሳይ =0 ሴኔጋል =1 😁

  • ለምሽታችን:- አእምሮን ከልክ በላይ መጨነቅ (Overthinking) እንዴት ማቆም ይቻላል? 🧠🛡️ "ከመጠን በላይ መጨነቅ ችግርን አይፈታም፤ ይልቁንም የዛሬን ሰላም በመስረቅ የሌለ ችግርን በአእምሯችን ውስጥ ይፈጥራል።" ብዙዎቻችን በአንድ ነገር ላይ ከመጠን በላይ በማሰብና ተመሳሳይ ሀሳቦችን በአእምሯችን ውስጥ ደጋግመን በማብሰል እንሰቃያለን። ይህ "Overthinking" የምንለው ልማድ አእምሯችንን ያደክማል፣ የውስጥ ሰላማችንን ይነጥቃል እንዲሁም ውሳኔ እንዳንወስን ያግደናል። ታዲያ ይህንን ጎጂ የአእምሮ እሥራት እንዴት መስበር እንችላለን? እነዚህን በተግባር እንሞክራቸው፦ 🚪 . ሀሳቡን ማስተዋል እንጂ አብሮ አለመጓዝ (Awareness)፦ ጭንቀት ሲጀምርዎት መጀመሪያ ቆም ይበሉና "አሁን አእምሮዬ ከመጠን በላይ እያሰበ ነው" ብለው ራስዎን ይታዘቡ። ሀሳቡን እንደ እንግዳ አድርገው ይዩት እንጂ ወደ ውስጥ ገብተው አብረውት አይጨነቁ። ሀሳብ መጣ ማለት የግድ እውነት ነው ማለት አይደለም። 🎯 . በችግሩ ላይ ሳይሆን በመፍትሔው ላይ ማተኮር፦ ከመጠን በላይ የሚጨነቁ ሰዎች ሁሌም የሚያስቡት "ይህ ነገር ቢበላሽስ? እንዲህ ቢሆንስ?" በሚሉ ፍርሃቶች ላይ ነው። አስተሳሰብዎን ወዲያውኑ ይቀይሩና "አሁን ባለው ሁኔታ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ? መፍትሔው ምንድነው?" ወደሚለው ተግባራዊ እርምጃ ይሻገሩ። ⏳ . ለጭንቀት የሰዓት ገደብ መስጠት (The 15-Minute Rule)፦ ጭንቀትን ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ማቆም ከባድ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በቀን ውስጥ 15 ደቂቃ ብቻ "የማሰብያ ሰዓት" ይስጡ። በዚያ ሰዓት ያሰቡትን በወረቀት ላይ ይፃፉ። ያ ሰዓት ሲያበቃ ግን ወዲያውኑ ወደ ሌላ ሥራ በመግባት አእምሮዎን በሌላ ነገር ይጠምዱት። 🌱 . ወደ "አሁን" ቅጽበት መመለስ (Mindfulness)፦ ከመጠን በላይ መጨነቅ ወይ ስለ ትናንት ጸጸት ነው ወይም ስለ ነገ ፍርሃት ነው። ሁለቱም በእጃችን የሉም። አእምሮዎ ሲበተን ትኩረትዎን ወደ አሁኑ ሰዓት ይመልሱ። በጥልቀት ይተንፍሱ፣ በዙሪያዎ ያሉትን ተፈጥሮዎች ይመልከቱ፣ ሻይ ይጠጡ። ዛሬ ላይ መኖር ትልቁ መድኃኒት ነው። ❌ . ፍጹም ለመሆን አለመጨነቅ (Done is better than Perfect)፦ ብዙውን ጊዜ ከመጠን በላይ የምናስበው ሁሉንም ነገር መቶ በመቶ ፍጹም አድርጎ ለመሥራት ስንጨነቅ ነው። ስህተት መሥራት የሰው ልጅ ተፈጥሮ መሆኑን ይቀበሉ። ፍጹም የሆነ ውሳኔ ለመወሰን ከመጠበቅ፣ ያመኑበትን ውሳኔ ወስነው በተግባር መንቀሳቀስ ጭንቀትን ይገድላል። 💡 ለማጠቃለል፦ አእምሮዎ የእርስዎ አገልጋይ እንጂ የእርስዎ ገዥ መሆን የለበትም። ሀሳቦች እንዲያሥሩዎት አይፍቀዱ። ዛሬን በሰላም ለመኖር አእምሮዎን ነፃ ያውጡ! መልካም ምሽት ቤተሰብ❤❤❤

  • https://aaaonline.info/pjFkbB

  • የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1635518748044544&inviterId=1191684771456103&language=am&time=Sept-03-2024-Dec-02-2024

  • 1. አልበርት አንስታይን፡- አንስታይን ከ1879-1955 የኖረ ታላቅ የሳይንስ ሊቅ ነበር። በተለይ ሁለት ግኝቶቹ የሳይንስ እይታችንን በእጅጉ የቀየሩ ሲሆን አንስታይን ምድራችን ካፈራቻቸው የሳይንስ ሊቆች ውስጥም ሆነ ወደፊት ከሚወለዱት ውስጥ ተወዳዳሪ አይገኝለትም የሚባል ብርቅዬ ሳይንቲስት ነው። አንስታይን በልጅነቱ ዳይስሌክሊስ (ሲያነቡ ወደ ግራ የሚያነቡ) የነበረ ሲሆን በትምህርቱ ደካማ በመሆኑ አስተማሪዎቹ ደደብ አድርገው ይገምቱት ነበር። በ15 ዓመቱ ትምህርቱን አቁሞ ከዓመት በኋላ ዙሪክ የሚገኝ አንድ ፖሊ ቴክኒክ ለመግባት አመልክቶ የመግቢያ ፈተናውን ወድቋል። ይህ ሰው ግን በፊዚክስ ንድፈ ሃሳብ ዓለምን በመቀየሩ የኖቬል ሽልማት ለመሸለም የበቃ ድንቅ ሳይንቲስት ነው። 2. ቶማስ ኤዲሰን፡ ይህ ታላቅ ፈላስፋ ትምህርት ቤት የሄደው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር። ምክንያቱም በስምንት ዓመቱ አስተማሪው "ደደብ" ብሎ ስለሰደበው እናቱ ከትምህርት ቤት አውጥታ ቤት ውስጥ አስተማረችው። በዘጠኝ ዓመቱ ይሞክራቸው የነበሩት ነገሮች ከእናቱ አቅም በላይ ሆኖ ተገኝቷል። ቶማስ ኤድሰን በህይወት ዘመኑ አንድ ሺህ አዳዲስ ግኝቶችን የፈለሰፈ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የኤሌክትሪክ ብርሃን እና ሸክላ ማዘፈኛ ሲኖሩበት ያሻሻላቸው ነገሮች ደግሞ ፊልም ማሳያ፣ ቴሌፎን ይገኙበታል። 3. ሰር ዊንስተን ቸርችል፡ ይህ ሰው ታላቅ እንግሊዛዊ ፖለቲከኛ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ሰዓሊ ሲሆን እንግሊዝን በአንደኛ እና ሁለተኛ የዓለም ጦርነት በተለያየ የመንግስት ስልጣን ደረጃ የመራ ታላቅ የፖለቲካ ሰው ነው። (በአገራችን መዲና አዲስአበባ ጎዳና በስሙ ተሰይሞለታል) ቸርችል ይህቺ ምድር ካፈራቻቸው ድንቅ የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ቢሆንም በትምህቱ ደካማ ስለነበር ሮያል የውትድርና ኮሌጅ ለመግባት ከአንዴም ሁለት ግዜ ተፈትኖ በመውደቁ መግባት አልቻለም ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ቸርችል በአመራር እና በንግግር ችሎታው ለሃገሩ ትልቅ ሚና ተጫውቶ ያለፈ መሪ ነው። 4. ሪቻርድ ብራንሰን፡ የVirgin Group መስራች የሆነው ብራንሰን የዲስሌክሲያ (dyslexia) ችግር የነበረበትና ደካማ የአካዳሚክ ብቃት ነበረው። በ 16 ዓመቱ ትምህርቱን ያቋረጠ ነገር ግን ዓለም አቀፍ የሆነ የንግድ ኢምፓየር መገንባት የቻለ ስኬታማ ሰው መሆን ችሏል። 5. አይዛክ ኒውተን፡- ኒውተን በልጅነቱ ቸልተኛ እና ሰነፍ ተማሪ እንደሆነ ይቆጠር ነበር። በመጨረሻም ሰዋሰው ወደሚያስተምር ትምህርት  ቤት ተላከ። እዚያም እውነተኛ እምቅ ችሎታውን ማሳየት ጀመረ፤ በኋላም ደካማ ውጤቶች ስለነበሩት ከትሪንቲ ኮሌጅ ሆነ ከካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ሲመረቅ የክብር ወይም የማዕረግ ተመራቂ አልነበረም። ነገር ግን በታሪክ ከታወቁት ታላላቅ የሳይንስ ፈጣሪዎች አንዱ በመሆን የዘመኑ ሳይንስ በእርሱ ስራዎች ላይ ለመመርኮዝ በቅተዋል። 6. ቻርለስ ዳርዊን፡ በዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሃሳብ የሚታወቀው ዳርዊን እንደ መካከለኛ ተማሪ ይቆጠር ነበር። ከትምህርቱ ይልቅ ከቤት ውጭ እንቅስቃሴዎችን እና ናሙናዎችን መሰብሰብን ይመርጥ ነበር። ወጣቱ ዳርዊን በትምህርቱ በመድከሙ አባቱ "አንተ ከአደን እና ውሻ በስተቀር የምትወደው ነገር የለም፤ ስለዚህ ለራስህም ሆነ ለቤተሰብ ውርደት እንዳትሆን" ብሎ ከትምህርት ቤት አስወጣው። የህክምና ትምህርት ሞከረ አስጠላው። የሃይማኖት ትምህርትም ሞክሮ ነበር አልሆነለትም። ብዙውን ግዜውን ግን ከስፖርተኞች ጋር ነበር የሚያጠፋው። ይህ ሰው ግን በመጨረሻ አጠቃላይ የስነ-ህይወት ሳይንስን ለመቀየር ችሏል። 7. ፓብሎ ፒካሶ፡- ታዋቂው አርቲስት ለመደበኛ ትምህርት አነስተኛ ፍላጎት የነበረው ሲሆን ብዙ ጊዜ እንደ ደካማ ተማሪ ይቆጠር ነበር። የጥበብ ተሰጥኦው ግን የማይካድ ነበር እናም በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከፍተኛ ተደማጭነት ካላቸው አርቲስቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል። 8. ስቲቭ ጆብስ፡ የአፕል ካምፓኒ መስራች የሆነው ጆብስ፣ በአመፀኛ ተፈጥሮው እና በመደበኛ ትምህርት ላይ ፍላጎት በማጣት ይታወቅ ነበር። ነገር ግን የእሱ የፈጠራ ራዕይ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪውን ለውጦታል። 9. ቢል ጌትስ፡- የማይክሮሶፍት መስራች የሆነው ጌትስ ጎበዝ ግን ብዙ ጊዜ ስልቹ የሚባል ተማሪ ነበር። ለሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ያለውን ፍቅር ለማሳካት ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አቋርጧል፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉት ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ እንዲፈጠር አድርጓል። 10. ማርክ ትዌይን፡- የ"The Adventures of Tom Sawyer" and "Adventures of Huckleberry Finn" ፀሃፊ የሆነው ይህ ታዋቂ ደራሲ እንደ ሰነፍ ተማሪ ይቆጠር ነበር። ብልህነቱ እና የመተረክ ችሎታው ግን ከአሜሪካ ታላላቅ ጸሐፊዎች አንዱ አድርጎታል። 11. ቤንጃሚን ፍራንክሊን ይህ ሰው የሂሳብ ትምህርት አይሆነውም ነበር። እናም አባቱ ከትምህርት ቤት አስወጥቶ ሻማና ጧፍ ሲያሰራው አደገ። ነገር ግን ይህ ሰው አሜሪካ ካፈራቻቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ በመሆን ታዋቂ ፖለቲከኛ፣ ሳይንቲስት፣ ጸሐፊ እና የፔንሲልቫኒያ ፕሬዚዳንትና የአሜሪካ መስራች አባት ለመባል የበቃ ሰው ነው። 12. ሴናተር ኤድዋርድ ኤም ኬኔዲ ይህ የማሳቹሴትስ ሴናተር በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ሁሉ ተወዳድሯል። ግን ፈተናውን ጓደኛው ሲፈተንለት ተይዞ ከሚማርበት ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተባርሮ ነበር። ------------------------------ እነዚህ ታሪኮች ያቀረብነው መደበኛ ትምህርት እንደማያስፈልግ ሳይሆን በቀደምት የትምህርት ህይወታችን ውጤታማ መሆን አለመቻላችን የግድ የወደፊትን ስኬት የሚወስን አለመሆኑን ለማሳየት ብቻ ነው። እነዚህን ግለሰቦች ወደ ታላቅነት የመራቸው ልዩ ባህሪያቸው እና ጽናታቸው ነው። ------------------------------ ከእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ከእናንተ ወይም ከልጆቻችሁ/ከእህት-ወንድሞቻችሁ ጋር የሚመሳሰለው የትኛው ነው?

  • без подписи

  • 7 нояб. 2024 г.2 57522из Higehateta

    ☑️ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ብድር ሰጠች😁 በአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው። የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው። በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል። የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው። Via:Ayuzehabesha መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን:: መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::👇👇 Join here⬇️ http://t.me/Higehateta http://t.me/Higehateta

  • 1. መቆጣጠር የማትችለውን ነገር ተቀበል! ሁልጊዜ የሚደርስብንን ነገር መቆጣጠር ባንችልም ምላሽ የምንሰጥበትን መንገድ ግን መቆጣጠር እንችላለን። 2. ስኬት የራዕይ ውጤት ነው! ሁሉንም ጊዜህን እና ጉልበትህን ስኬታማ ለመሆን ከማዋል ይልቅ እሴት ለመፍጠር፣ ከራስህ በላይ ትልቅ ለሆነ ነገር አውለው። ይህን ስታደርግ ስኬት በራሱ ጊዜ ፈልጎህ ይመጣል። 3. በመከራ/ስቃይ ውስጥ ትርጉም አለ! መከራ/ስቃይ የህይወት ክፍል የሆነና የማይቀር ነው። ስለዚህ በህይወት ውስጥ ትርጉም ካለ በመከራ ውስጥም ትርጉም አለ። "ያለ መከራ/ስቃይ የሰው ህይወት ሙሉ አይደለም" 4. መከራ/ስቃይ ለዘላለም አይቆይም! መከራ/ስቃይ የማይቀር ቢሆንም - ቋሚ ግን አይደለም። የነጻነት ጊዜ ይመጣል፣ መከራ የሚቆምበት ጊዜ ይመጣል። ያ ጊዜ የሚመጣው ከስቃይህ ጀርባ ያለውን ትርጉም ስታገኘው ወይም ስትፈጥረው ነው። 5. አቅምን ሙሉ በሙሉ መገንዘብ ከራስ አልፎ ለሌሎች የመኖር ውጤት ነው። ሰው ራሱን ለአላማው ሙሉ በሙሉ መስጠት አለበት። ይህን ሲያደርግ ከሚያስበው በላይ ሰው ይሆናል፣ የበለጠ ሰው በሆነ መጠን ራሱን በተግባር እያሳየ እና አቅሙን እየተጠቀመ ይመጣል። 6. ዓላማ በሕይወት እንድንኖር ያደርገናል! ተስፋ የቆረጡ፣ የመኖር ዓላማቸውን (Purpose) ያልፈጠሩ፣ በህይወት የመቆየት እድላቸው አነስተኛ ነው። ነገር ግን አንድ የሚያበረክቱት ነገር እንዳለ የሚያውቁ ሰዎች ማንኛውንም መከራ/ስቃይ ተሻግረው በህይወት የመኖር እድላቸው ሰፊ ነው። 7. ሰው አላማውን ይፈጥራል! "የሰው ልጅ የህይወቱ ትርጉም ምን እንደሆነ ሌሎችን መጠየቅ የለበትም፣ ይልቅ ሲጠየቅ መመለስ ያለበት እሱ መሆኑን ማወቅ አለበት። ሕይወት ትጠይቃለች፣ ትሞግታለች፣ እናም ጥያቄውን መመለስ፣ ተግዳሮትን አልፎ መነሳት እና ለህይወታችን ትርጉም መስጠት የእኛ ድርሻ ነው። 8. በፍቅር የተነቃቃህ ሁን! በሄድክበት ቦታ ሁሉ ፍቅር ለማሳየት ጥረት አድርግ። የአለም ጨለማ ብርሃንህን እንዲያደበዝዝ አትፍቀድ። የሌሎች ክፋት ክፉ እንዲያደርግህ አትፍቀድ። ————————————————— አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏 ——————————————

  • без подписи

  • ማነው የወደቀው ? ****💡💡💡 ስለ ዘመናዊው የኢትዮጵያ ትምህርት ብዙዎች ብዙ ብለዋል ፤ ብዙ ፅፈዋል ። ከእነዚህም መካከል  ፕ/ር ኧረነስት ዎርክ አንዱ ናቸው በጥናታቸውም  " ... ነፃይቱ ኢትዮዽያ ውስጥ ያለው የትምህርት ስርዓት ቅኝ ከተያዙት የአፍሪካ አገሮች የማይለይ በመሆኑ በጣም አደገኛ እንደሆነ ይገልፃሉ። " ይህም  የሚሼል ፉ ኮ አባባል " ... የቅኝ ግዛት የመጨረሻው ደረጃው ትምህርትና ተቋማትን መቆጣጠር ነው  :: " የሚለው ሀሳብ ይበልጥ ያጠናክረዋል :: የዎርክ የጥናት ሪፖርት በ1924 ዓ.ም በቀረበበት   ወቅት   " የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት የምዕራቡን  አለም መምሰል የለበትም ፤   መሆን ያለበት "የኢትዮጵያ " ነው የሚል ነበር ::   ሌላኛዋ አሜሪካዊቷ የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የነበረችው ዶ/ር ኤዲት ሎርድም 1954 ዓ.ም በፅሁፏ ላይ  ስለ ኢትዮጲያ የትምህርት ቤቶች ካሪኩለም ታዝበው  “ ... ካሪኩለም ማዘጋጀት ያለብን የተማሩ ኢትዮጵያውያንን በተማሩ እንግሊዛውያን ፣ ፈረንሳውያን ወይም አሜሪካዊያን ሞዴል ለመቅረፅ ነዉ? ወይስ ሊፈቱ የሚገባቸው የዚህች አገር ችግሮች ምንድን ናቸው? የሕዝቡ ፍላጎትስ ምንድን ነው ? ብለን ጠይቀን ነው? የአሁኑ የትምህርት ፕሮግራም እንዴት ነው እነዚህን ችግሮች የሚፈታው ? እንዴትስ ነው የሕዝቡን ፍላጎት የሚያሟላው ? “ ብለዉ  ነበር :: የኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት መሰረታዊ ችግሮች በዚህ ጥናት ውስጥ በግልፅ ተቀምጠዋል። ትምህርት ዝግ ሆኖ ሀገር በቀል ይሁን የሚባል ጉዳይ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ነገር ግን የማህበረሰቡን  እሳቤ ኋላ ቀር ብሎ የውጭውን ከእነ ምናምኑ መጫን ትልቅ ስህተት ነው ። ብራዚላዊው የትምህርት ፈላስፋ ፖሎ ፌሬሬ አባባል ከሆነ ትምህርት ችግር ፈቺ የሚሆነው  ከሽምደዳ  (Banking (deposite) system ) ወጥቶ ለማህበረሰብ ችግር መፍትሄ ፈላጊ ሆኖ ሲቀርብ ነው ይህም( problem posing  and  problem Solving system) ይሉታል :: ሊቁ ፕ/ር ማዕምር  የኢትዮጵያ ትምህርት የራስ እውቀት ነፃነት (ሉዓላዊነት)  የለውም  ይላሉ :: ይህም በፅንሰ ሃሳብም ፣ በስነ ዘዴውም እንዲሁም  በማስተማሪያ ቋንቋው ምዕራባዊ በመሆኑ  ደመነፍሳዊ  (zombie concept) ነው ይላሉ ። ይህም ትምህርቱ የራሱን ፍኖት መፈንጠቅ እንዳይችል አድርጎታል፤ ምሁራዊ አድር ባይነት እና የተበላሽ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ እንድንዘፈቅ አድርጎናል ይላሉ።  በመሆኑም ሃገርና ማህበረሰብን ከማልማትና ከማሳደግ ይልቅ የውድቀት ምንጭ ነው ይላሉ።  እንደ አብሪ ኮከቡ ገ/ህይወት ባይከዳኝ አባባል " ... አንድ ህዝብ አርነት ሊኖረው የሚችለው በሁሉም ነገር ራሱን ሲችል ነው ። አርነት የሌለው ህዝብ ውሎ አድሮ የሌሎች ተገዥ ይሆናል። የፖለቲካ ነፃነት ብቻውን ምንም ነው ።  እንደ ዶ/ር ይርጋ ገላው ምልከታ ደግሞ  የትምህርት  ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ ከውጪ የተቀዳ በመሆኑ ሃገር በቀል ቅኝ ግዛትን (native colonization) እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ይላሉ ። ይህም ማህበረሰቡ በገዛ ሃገር ባይተዋር ፣ እሴት አልባ ፣ ትርጉም አልባ አድርጎታል ይላሉ። ይህም የተማሩ የተባሉ ሽሚዝ ለባሾች (ቢሮክራት) ህዝቡን በተበላሽና በጭቆና ቀንበር ውስጥ እንዲዘፈቅ አድርገውታል። የክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ የትምህርቱን ስርዓት አምርረው በተቹበት " የልም ዣት " በተሰኘው ብሉይ ረጅም የልቦለድ መጽሐፋቸው መግቢያ  ላይ  “ትምርት ለሰው ሁለተኛ ፈጣሪው” ነው ይላሉ :: አክለውም “ ...እቤቴ እንግዳ ቢመጣ ተቀብዬ ማስተናገድ አለብኝ እንጂ እንዴት ቤቱን ትቼለት እወጣለሁ ይላሉ (ቃል በቃል አይደለም የተወሰደው ) ከውጪ በመጣውና በሀገር በቀሉ ትምህርት መካከል የሆነው ይህ ነው። ለማሳያ በዚሁ መፅሀፋቸው ውስጥ ባሉት ሁለት ወካይ ገጸ ባህርያት አማካይነት ማለትም በተዋበችና በልጇ በተከስተ መካከል  የተፈጠረውን የእሴት ልዩነት ፣ የስነ ልቦና መፈርቃት ወዘተ ... ጥሩ ማሳያ ነው ። በስንት ጥረትና ልፋት  ያስተማረችው  እናቱን ፤ አንድ ቀን ምሳ ቋጥራለት ስትሄድ በጓደኛው ምንህ ናት ተብሎ ሲጠየቅ" ገረዳችን ናት " ብሎ  ሲያፍርባት ታዝበናል።  ቆይቶ ቆይቶ  ባህር ማዶ ሲሻገር ሊሰናበታት እንኳን አይፈቅድም ። እንዳልተፈጠረች ጥሏት  ይጠፋል። ከዚህ የተሻለ ማሳያ ምን አለ? ትምህርቱ የፈጠራቸው ተከስታውያንን ፕ/ር ማዕምር  " የስርዓታዊ ና መዋቅራዊ ድህነት አዋላጆች (Midwifery of the systematic living poverty) ። ዛሬስ ? በቂ የትምህርት ፍልስፍና ፣ ስነ - ዘዴ ፣ መፅሀፍ ፣ ት/ቤት፣ ወዘተ የሉንም ።  እነዚህ ነገሮች በአግባቡ ባልተሰሩበት ሁኔት  የተወሰደው እርምጃ ልክነት አጠያያቂ ነው። ትምህርት ላይ የሚፈረገውን ሸፍጥ እዚህ አልዘበዝ ብም። ነገር ግን  ትምህርት የፖለቲካ መሳሪያ መሆን የለበትም ።Alas! © Teshale Kebede Bedriya

  • መጪዉ ዘመን ለሀገሬ የምመኝላት መልካም የሆነ የጎላ #የተግባር ዘመን እንዲሆንላት ነው ። ... የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለጸው #በተግባሩ እንጂ #በንግግሩ አይደለም ። የተግባር መሰረቱ ደግሞ #ጽኑ_ፍላጎት ነው ! ችግሮችን ከመቅረፍ ችግሮቹን የሚያላዝኑ ና ልማታዊ እንቅፋቶችን ከሚፈጥሩ ሀሳቦች የምንወጣበት፣ መጪው ዘመን ጠቃሚውን የምናስቀጥልበት፣ ችግሮቻችንን ለይተን የምንቀርፍበት ፣ የመነጣጠልና የመለያየት እሳቤዎችን የምንገራበት ፣ ገናና ና ልእለ ኃያል የሆነች አገራችንን አጥብቀን የምንፈጥርበት ና የምናስቀጥልበት ፣ የአገር ፍቅር መሰረት ያለው ና ለአገር ፍቅር ተግባራዊ የሆኑ እሳቤዎችን ና ተግባሮችን የምናለማበት ና የምናስቀጥልበት ፣ አገር የሚገነባ፣ የሚያለማ፣ የሚያበለፅግ፣ ከራሱ በፊት ለአገሩ ክብር ዘብ የቆመ ዜጋ የምንቀርፅበት፣ ፍፁም #ሰላማዊ ና #የተረጋጋ ቤተሰብ፤ማህበረሰብ ፤ዜጋ፣ሀገር ፣ አገር ና አህጉር የምንፈጥርበት ፣ እርሃብ ፣ ጠኔ ፣መከራ፣እንግልት ፣አምጪ የሆነውን #ጦርነት የምናስቀርበት፣ ከንቱ ና እርባነቢስ ከሆነ ፀብ ፣ ንትርክ፣ ሙግት ና ክርክር ከንቱነት የምንረዳበት ፣ ባልተጋገረ ና ባልዳበረ ዳቦ ተጠቃሚነት ወይም ባል ተገነባ ሀብት እኩል የሀብት ና የልማት ተጠቃሚነት ከሚል እሳቤ ወጥተን ትልቁ ና የደረጀውን ለሁላችንም የሚበቃ ፣ የሚመጥን ና የሚገባ ልማትን አጥብቀን የምንገነባበት ፣ ለመልካም እሳቤ ና ተግባር ዘብ የምንቆምበት ፣ ለአገሩ ልማት ተቆርቋሪ አሳቢ ቀማሪ ና ጦማሪ (ፀኃፊ) የምንፈጥርበት፣ በሀሳብ ና በብዕር የሚያምን ትውልድ የምንገነባበት ፣ መዋጋት ካለብን ዋነኛ ጠላታችን ድህነት ነው! (የቀድሞው ክቡር ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ) የሚያባላን ቃታ የሚያማዝዘን ችግር ውስጥ የሚከተን መልካሙን ከክፉ ለይተን እንዳናቅ ና እንዳንለይ የሚያደርገን ድህነታችን ነው ።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ተሸካሚ በሌለበት ሸክም የለም...!! ፨፨፨ << አንድ ነገር የሚታየው በሌላ አካል ለመታየት ስለሚችል ሳይሆን ነገር ግን ሌላ አካል ስላየው ነገሩ ሊታይ ቻለ፤ ወይም አንድ ነገር ተመሪ የሚሆነው መሪ ስላለው እንጂ ነገሩ ተመሪ ስለሆነ አይደለም። አንድ ነገር ሸክም የሆነው ተሸካሚ ስላለው እንጂ ነገሩ በራሱ ሸክም ሆኖ አይደለም። ይኽ ማለት አንድ ውጤት በራሱ ልቆ የወጣበት አካል ውጤቱ የራሱ ሳይሆን ምክንያት ስላለው ነው። ውጤት የሆነ ነገር በራሱ ውጤት አያመጣምና። ቅድስናም እንዲሁ ቅዱስ የሚሆነው አማልክት ስለሚወዱት እንጂ በራሱ ቅዱስ ስለሆነ አይደለም። >> / ሶቅራጥስ /