- Последний пост
- 19 нояб. 2024 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
💫💫ክብር 💫💫 ክፍል 2 📖📖ሮሜ 8፥29-30 ⚱ክብር ካቦድ ወይንም ክብደት ከሚለው ቃል ጋር የተገናኘ ነው። ⚱ልክ አንድ ሰው ክብደት ለመጨመርና ጡንቻ ለማውጣት ስፓርት እንደሚሰራ ፤ በመንፈሳዊ ህይወት ላይ መስራት የእግዚአብሔርን ክብር ይጨምራል። ⚱አለም የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጡ ሰዎችን ትፈልጋለች። ⚱እግዚአብሔር አለም ከመፈጠሩ በፊት እኛ የእርሱ ክብር ገላጮች እንድንሆን ወስኗል። ⚱እየሱስ ከብሯል ፤ እናንተም እንደዚሁ። ⚱በእግዚአብሔር ክብር ተሞልታችኋል! ✨አብራችሁን ሁኑ ፤ ተባረኩ✨ @surafelma
💫💫ክብር 💫💫 ክፍል-1 📖📖2ተኛ ቆሮንጦስ 4 ⚱️ሰው ከእግዚአብሔር ክብር ውጪ ሙሉ አይደለም:: ⚱️ሰው መጀመሪያ ሲፈጠር በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ነው የተፈጠረው:: ⚱️የሰው ዘር ሀጥያትን ሲያደርግ ከእግዚአብሔር ጋር ነው የተለያየው:: 🔴ነገር ግን እየሱስ ወደ ክብሩ እንድንገባ በደሙ ዋጅቶናል! ⚱️ክብር ማለት የተገለጠ የእግዚአብሔር ህልውና ማለት ነው:: ⚱️የእግዚአብሔር መገኘት በሁሉም ቦታ ቢገኝም; የተገለጠ የእግዚአብሔር ህልውና ግን በሁሉም ስፍራ ላይ አይገኝም! ✨ተባረኩ✨ @surafelma
የፃድቅ ፀሎት ያእቆብ 5:14-16 ⚡️⚡️ፀሎት ሀይል አለው:: 🍎🍇ፀሎት እንደ እግዚአብሄር ቃል ሲሆን ፍሬው ታላቅ ነው:: 1 ነገሥት 8:35 ⚡️⚡️መፅሐፍቅዱስ እንደሚል ልክ እንደ ኤልያስ እኛም ሰዎች ነን:: 🙅🏻♀️🙅🏻♂️በሰማይ ያሰርነው በምድር የታሰረ ይሆናል! ⛈⛈እንደሀይማኖተኛ ሳይሆን በህይወታችሁ የእግዚአብሔርን ክብር ከሰማይ ለማውረድ ፀልዩ:: 1 ዮሐንስ 5:15 😇ፀሎት እርግጠኛንት የተሞላ ፀሎት እንጂ በጥርጣሬ አይሁን ኢሳያስ 40:30 🙋🏻♀️🙋🏻♂️በሁሉም አባታችሁን አመስግኑ!!! 🔥የፃድቅ ሰው ፀሎት በስራዋ ሀይልን ታደርጋለች!!!🔥🔥🔥 🔥🔥በመንፈስ ሳትደክሙ እለት እለት በመገኘቱ ውስጥ ተመላለሱ🚶🏽♂️🚶🏽♀️ Join now @surafelma @surafelma
የኢየሱስ ስም 📖የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፦ 📖2 ቆሮንጦስ 10፥3 📖ኤፌሶን 2፥5-7 🌎በዚህ ዓለም ውስጥ እንኖራለን ግን ከዚህ ዓለም አይደለንም። 🤺🤺ሰለዚህ ዓለም እንደሚዋጋው አንዋጋም።🤺🤺 🔥🔥የኢየሱስ ስም ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስም ነው። 🔥🔥ከሀይላትና ከስልጣናት በላይ ነው። 👑👑ኢየሱስ በአብ ቀኝ ሲቀመጥ እናንተም ተቀምጣችኋል።👑👑 🕺🏻ከዚህም የተነሣ በድፍረት ከዚህ ዓለም አይደለሁም ማለት እንችላለን።🕺🏻እኔ ሰዎች የሚሉኝን አይደለሁም።🕺🏻 ኢየሱስ እንዳደርግ የሚፈልገኝን ማድረግ እችላለሁ።🕺🏻እኔ ሁኔታዬ የሚለኝን አይደለሁም። @surafelma @surafelma join
Tebarekubet
ዉጤት ዛሬ 6:00 ላይ ይፋ ይሆናል! ልክ እንደወጣ ዉጤታቹን የምታዩበት websites እነዚህ ናቸው :: 1. eaes.et 2. eaes.gov.et 3. eaes.edu.et 4. result.neaea.gov.et 4. t.me/EAESbot እኛም ቀድመን አልሰራ የሚላችሁ ከሆነ እገዛ የምናደርግላችሁ ይሆናል ።
“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
ወንጌል ለኃጢአተኛው ሰው የኃጢአት ሥርየትና ጽድቅን ያቀረበው በአንድ መንገድ ነው! እርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን! ከአንዱ መንገድ ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ የኃጢአት ሥርየትና ጽድቅ የሚገኝበት መንገድ የሚጠቁም እርሱ "ልዩ ወንጌል" ነው! ወንድም ብንያም @surafelma @surafelma
. | አለ | ዘማሪ ደረጀ ማሴቦ 🕝-6:26 min || 💾12.0MB ◈𝖓𝖊𝖜 𝖆𝖒𝖆𝖟𝖎𝖓𝖌 𝖌𝖔𝖘𝖕𝖊𝖑 𝖘𝖔𝖓𝖌◈ 💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 ▷@surafelma ◁ ▷@surafelma ◁ △Join us△
#ምሕረት "የእግዚአብሔር ምሕረት ነፃ ነው፤ ቢሆንም ግን እጅግ ውድ ነው። ስጦታው በዋጋ የሚገዛ አይደለም" (ፍራንሲስ ቻን፤ ሁሉን አስጣይ ፍቅር) ፀሐፊው፣ ስለ ምሕረት 3 መሰረታዊ ነገሮች ጠቆመን፦ • ምሕረት እጅግ በጣም ውድ መሆኑን፣ • በዋጋ ልንገዛው እንደማንችል እና • ነፃ ስጦታ እንደሆነ። ይህን ውድ ምሕረት በነፃ አግኝተናል! እኛ ጋር ነፃ የሆኑ ሁሉ፣ ኢየሱስ ከፍሎባቸዋል! ሐዋርያው “አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥” ይላል። (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥13) አማኞች ሁልጊዜም፣ ማን እንደነበርን እና ምን እንደተደረገልን ማስታወስ ይኖርብናል! እንደ ሐዋርያው ሁላችንም የተተወልን ወይም ምሕረት ያገኘንበት ነገር አለ። የበደል ዶሴ ያልተዘጋለት፣ ዕዳ ያልተወራረደለት፣ መተላለፉ ያልተተወለት ... ማን አለ? የተቀበልነውን ምሕረት በማሰብ በምስጋና ቀናችንን እንጀምር! ✍️messager kaleb https://t.me/healingjesus11 https://t.me/healingjesus11 https://t.me/healingjesus11 https://t.me/healingjesus11
“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
part 2 #እግዚአብሔር_ያስቀመጠን_ቦታ_መገኘት ሀጢያት #ሀጢያት ማለት ትክክለኛ ፍቺው መንገድ መሳት ማለት ነው። መቼም ዱባይ የሚሄድ ሰው የ America ትኬት አይቆርጥም ለምን 🌁ገነት መሄድ የፈለገ ሰው መቁረጥ ያለበት ትኬት ፅድቅ ነው። የሀጢያት ትኬት ቢኖረው ግን ገነት አይደለም በሩን አያይም 😎man ስለዚህ እግዚአብሔር ያስቀመጠን ቦታ መገኘት ማለት እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር መተው (መለየት) ማለት ነው። 😒bro እግዚአብሔር ካስቀመጠህ ቦታ ፈቀቅ የምትለው ሀጢያት ስሰራ ብቻ ነው። ከሀጢአት በመራቅ በእግዚአብሔር ሀሳብ እንመላለስ 📱አሁኑኑ group ወይም ለምትወዱት ሰው ሼር ያርጉ መልካም ቀን Join and share @surafelma @surafelma
#እግዚአብሔር_ያስቀመጠን_ቦታ_መገኘት part 1 📌 እግዚአብሔር ሁሉንም ክርስቲያን ያስቀመጠበት ቦታ አለው እና ሰዎች እንድ አንድ ጊዜ የሰው ልጅ ይስትና እግዚአብሔር ካስቀመጠው ቦታ ይሸሻል ። 📌እናም እግዚአብሔር ያዝንብናል ከዛ ወይ እናስተካክላለን ውይም የመሞቻችን ቀን ደርሶ ሳንመለስ ቀን ይጨልምብናል 📌 በዚ ምድር ላይ በጣም ፈተናም ከሚበዛበት ነገር መሀል እግዚአብሔር ባስቀመጠን ቦታ መገኘት ነው #part2 ይቀጥላል @surafelma @surafelma
Surafel...h pinned «💎 መንፈስ ቅዱስ 💎 👑መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው❕ ሐዋ 5:3-4, ማት 28:19 🌈 በመንፈስ ቅዱስ ሰማያት ውበትን አገኙ እዬብ 26:13 👍🏼መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ካለ የእግዝአብሄር ልጆች ነን። ሮሜ 8:9 💡በኛ ውስጥ ያለው ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ ነው 1ኛቆሮ 3፡17, 6:19, ሮሜ 8:9,11 ቆላ 1:27። 🔋መንፈስ ቅዱስ ስለእየሱስ እንድንመሰክር ሀይል ያስታጥቀናል ሐዋ1:8, ሐዋ 4:31, ሐዋ…»
💎 መንፈስ ቅዱስ 💎 👑መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው❕ ሐዋ 5:3-4, ማት 28:19 🌈 በመንፈስ ቅዱስ ሰማያት ውበትን አገኙ እዬብ 26:13 👍🏼መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ካለ የእግዝአብሄር ልጆች ነን። ሮሜ 8:9 💡በኛ ውስጥ ያለው ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ ነው 1ኛቆሮ 3፡17, 6:19, ሮሜ 8:9,11 ቆላ 1:27። 🔋መንፈስ ቅዱስ ስለእየሱስ እንድንመሰክር ሀይል ያስታጥቀናል ሐዋ1:8, ሐዋ 4:31, ሐዋ 10:38. 🙏መንፈስ ቅዱስ ድካማችንን ያግዛል ለኛ ይማልዳል። ሮሜ 8:26 ⭐️መንፈስ ቅዱስ ስብእና አለው⭐️ 🙂መንፈስ ቅዱስ ስሜት አለው ሐዋ 5:3-4, ኤፌ 4:30, ኢሳ 63:10። ➡️መንፈስ ቅዱስ ይመራል አቅጣጫ ያሳያል። ሐዋ 13:2፣ ሐዋ16:6 ፣ሉቃ 4:1. 🎁መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሄር የተሰጠን ስጦታ ነው። ሐዋ1:4, ሐዋ 2፡33. 📜መንፈስ ቅዱስ ምርጥ አስተማሪ ነው። ዩሀ 14:26፣ነህ 9፡20 💪መንፈስቅዱስ የውስጥ ሰውነታችንን ያጠነክራል ኤፌ3፡16 💞መንፈስ ቅዱስ ወዳጅና አፅናኝ ነው። ዩሐ 14:17, ዩሐ 16:7 😇መንፈስ ቅዱስ እውነተኛ የደስታ ምንጭ ነው።ሮሜ 14:17, ፊሊ 4:4. ✝ክርስቶስን ምንመስለው በመንፈስ ቅዱስ ነው።2ቆሮ 3:18 🚫ያለመንፈስ ቅዱስ ክርስትና ባዶ ነው‼️ ሮሜ 8:14,15,16 @surafelma @surafelma
“እንደ ዛሬው ቀን በሥርዓቱ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ልባችሁ ፍጹም ይሁን።” — 1ኛ ነገሥት 8፥61 @surafelma
ድህረ ዘመናዊነት ክፍል2 (postmodernism chapter 2) እንግዲህ እነዚህን ካየን አሁን ወደሌላኛው ምዕራፍ እንሻገር። "አንድ ሀይማኖት የለም" በድህረ ዘመናዊነት አስተሳሰብ ሁሉም ሀይማኖት እውነት አይደሉም የሚል ነበር። በዚህም ምክንያት አንዳንድ ሀገራት ላይ ወንጌል መስበክ አደገኛ መሆኑን እስከመግለፅ ድረስ የተስፋፋ መሆኑን ምስክር ነው። ቻርለስ ዳርዊን (የዳርዊንዝም እንቅስቃሴ አባት) የሚወዳት ሴት ልጁ በሞት ከመነጠቋ በፊት ዳርዊን እጅግ በጣም አክራሪ አማኝ ነበር። ሴት ልጁ ከዚህ አለም በሞት ስትለይ "እግዚአብሔር የለም" ብሎ አዲስ እንቅስቃሴ አስጀመረ። እርሱም "እግዚአብሔር ልጄን ስለገደለብኝ፤ እግዚአብሔር ፈፅሞ የለም" ብሎ በምሬት ይናገር ነበር። የሚገርመው ነገር ግን ይህ ሰው ሳያውቀው እግዚአብሔር መኖሩን በአቋራጭ ይናገር ነበር። ምክንያቱም የእግዚአብሔር የመኖር ህልውና ምድሪቱን ስለሸፈነ ማንም ቢሆን ቢወድም ባይወድም ስለ እግዚአብሔር ህልውና ይናገራል!!!!! ስለዚህ "አንድ ሀይማኖት ብቻ የለም።" የሚለው ፍልስፍና መቻቻል የሚል ቃል አመጣ። ይህም መቻቻል የሚለው ቃል ደግሞ "የሀይማኖት ጉባዔ" የሚል ድርጅት እንዲቋቋም አደረገ። የአሜሪካ የሀይማኖት ጉባዔ ውስጥ የኃይማኖት አባቶች ሲባሰቡ ሙስሊሙም ይሁን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ፣ ፕሮቴስታንቱ ይሁን 7ኛ ቀን አንድቬንቲስት አምላክን ፈጣሪ ብለው የሚጠሩት። ይህንን ካላሉ እርምጃ ይወሰድባቸኋል። አስተውሉ፤ "መቻቻል" የሚለው ቃል የወንጌል አማኝ ቃል (የወንጌል) አይደለም። እኛ የተጠራነው "አንቺ በኃይማኖትሽ እኔ በኃይማኖቴ" ተባብሎ መቻቻል ሳይሆን ወንጌልን ለሁሉ አድርሰን ከጨለማ ወደ ብርሀን፣ ከሞት ወደ ህይወት፣ ከሙታን ወደ ትንሳኤ ወደ የሚያሸጋግር ወደ ጌታ እንዲቀርቡ ነው። ... ይቀጥላል... ስለዚህ ፅሁፍ አስተያየት ካላችሁ በ @surafelma መግለፅ ትችላላችሁ 💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 @surafelma @surafelma
ድህረ ዘመናዊነት ክፍል 1 ድህረ ዘመናዊነት የሚል ፍልስፍና የተጀመረው እ.ኤ.አ በ1970 ዓ.ም ላይ በቻርለስ ዳርዊን እና ቢንግ ባንግ ፈላስፋዎች ተጀመረ። በ1930 እ.ኤ.አ የተነሳ ሲሆን የተጠናከረው ግን በ1970ዎቹ (እ.ኤ.አ) ዓ.ም ላይ ነበር። ከዛም በፊት ግን ዘመናዊነት የሚል በ1868ዎቹ እና በ70ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ የነበረ ፍልስፍና በድህረ ዘመናዊነት ተሸንፎ ወደቀ። ይህም ፍልስፍና "ሁሉም ነገር ተመርምሮ እውነት አለመሆኑን ወይም መሆኑን መለየት አለብን" የሚል መሪ ቃል ነበረው። ነገር ግን በዳርዊን እና በሌሎች ፈላስፋዎች አማካኝነት ድህረ ዘመናዊነት እንዲህ የሚል መሪ ቃል ነበረው፤ እርሱም "እውነት አንፃራዊ ናት" የሚል ነበር። "እውነት አንፃራዊ ናት" የሚለው ቃል እኔ ከአንድ ሰው ጋር ስከራከር የእርሱን መቀበል አልፈልግም ወይም "አንተ ልትዳኘኝ አትችልም። የእኔ እውነት ነው። በእኔ ጫማ ላይ ሆነ ካለየህ በስተቀር ልትከራከረኝ አትችልም" እንደማለት ነው። ይህም ለወንጌል እንቅፋት ነው። ይህም ፍልስፍና እግዚአብሔር የለም ብለው ለሚያምኑ እጅግ በጣም ዋስትና የሆነ ቃል ነው። በጀርመን ሀገር ውስጥ ኢየሱስ ያድናል ተብሎ ድምፅ አውጥቶ አይሰበክም። የአለበለዚያ ለእስር እንዳረጋለን። በዚያ ሀገር የመስበኪያ ዘዴ ባነር ላይ ኢየሱስ ያድናል ብሎ ለጥፎ መቆም ነው። በህንድ ሀገር ውስጥ 186 ያህል አማልክት ያመልካሉ። በዚህም መሀል አንድ ሚስዮነር ኢየሱስ ያድናል ብሎ ቢሰብክ ህንድ ሀገር ውስጥ ያለው ሰው ወንጌል ሰምቶ ቢቀበል፤ 186 አማልክቱን ሳያስወግድ ኢየሱስን 187ኛ አምላክ አድርጎ ያመልከዋል። ይህም ቅይጥ አምልኮ ይባላል። ይህም የሚያሳየው ድህረ ዘመናዊነት እንዴት እንደተስፋፋ የሚያሳይ ነው። ይህም በድህረ ዘመናዊነት አስተሳሰብ ትክክል ነው። እውነት አንፃራዊ ናት የሚለው የድህረ ዘመናዊነት ፍልስፍና ለወንጌል አያዋጣም።... ...ይቀጥላል ስለዚህ ፅሁፍ አስተያየት ካላችሁ @surafelma መግለፅ ትችላላችሁ። 💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 @surafelma @surafelma
✡መኖር ወይስ መሞት✡ ✔️ የነፍስ ጥያቄ ነው መኖር ወይስ መሞት? በትንሽ እንቅብ ላይ እደምትበራሳት፡ ዙሪያዋ ጨልሞ ግን ማህልዋ መብራት፡ እጂጉን የምትገርም የሂወት ተስፋ ናት፡ ደግሞ ሌላ ሳስብ ሁለተኛውን ፊት፡ በመኖር ተስፋ ላይ በመቆም ስታክት፡ ሞት ትዝ ይለኛል ሁለተኛው መስኮት፡ ገና ምን ሰርቸ ምኑንስ አይቸ፡ ከተስፋየ ርቄ ልኑር ተለይቸ፡ በፍፁም አይሆንም በርግጥ እኔ አቃለሁ፡ ሞት ቢሆን ጥቅሜ ነው ከሱ ጋር ስላለሁ፡ ግና ግና ቢሆንም የምኖርለትስ ገና ብዙ ስራ፡ ታዲያ ለማን ይሰጥ ምንም ሳያበራ፡ የቆመው እንቅቤ ይኑር ያለስራ፡ ታዲያማ በጨለማው አለም፡ ሂወት ብትከብድም፡ ፈትና ፈትና ብታሰለቸንም፡ እሱ ያየልንን ሳንይዝማ አኖድቅሞ፡ ምጥ ይበዛል እጂ መወለዱ አይቀርም፡፡ አንዳንዴ የምናየው ሌላ የተባለው ሌላ ይሆናል ግን ያባቴ ልጆች እመኑኝ በነገራችን በሂወታችን ሁሉ ላይ አግዛቤር አዋቂ ነው አሜን✝ ✍ በበፂ #Markengeta #join and #share @surafelma @surafelma
ዐሥርቱ ቆነጃጅት በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25፥1-12 ድረስ ስናነብ ዐሥሩም ሚዜዎች ሆነው በሙሽራው ግብዣ ለመገኘት የመጡ ነበሩ። ነገር ግን ሙሽራው በመዝግየቱ እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ስለነበር እንቅልፍ ወሰዳቸው ይለናል። በድንገት፤ እነርሱ ባላሰቡበት ሰዓትና ወቅት ሙሽራው መጣ። "ሙሸራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት" የሚል መልዕክተኛ በየጎዳናዎቹ እየጮኸ ስለነበር ዐሥርቱ ቆነጃጅት ከእንቅልፍ ቀሰቀሳቸው። ከአሥርቱ ቆነጃጅት መካከል አምስቱ ብልሆች ሲሆኑ አምስቶቹ ደግሞ ሰነፎች ነበሩ። ብልሆቹም ለመብራታቸው ዘይት ይዘው ስለነበር መብራታቸው ሳይጠፋ ሙሽራው ለመቀበል አልተቸገሩም ነበር። እነዛም ሰነፎቹ ዘይት እንዲሰጣቸው ለመኗቸው። ብልሆቹ ግን "ያለን ዘይት ለእኛም ሆነ ለእናንተ አይበቃም፤ ስለዚህ ገበያ ገዝታችሁ ኑ" አሏቸው። እነርሱም ዘይት ገዝተው እስኪመጡ ድረስ ሙሽራው አዳራሽ ገባ። በሩም ተዘጋ። ሰነፎቹም በሩ ተዘግቶ ሲያዩ ማንኳኳት ጀመሩ። ሙሽራው ግን "ከቶ አላቃችሁም" አላቸው። ጌታ ኢየሱስ የሚመጣበት ጊዜ አይታወቅም። ስለዚህ ነቅተን እንጠብቅ። አለበለዚያ እንደ ብልሆቹ ከሙሽራው ጋር በክብር እንገባለን ወይም እንደ ሰነፎቹ ተዋርደን ለቅሶ እና ጥርስ ማፏጨት ወደ ሆነበት ወደ ጥልቅ እንገባለን። ከሁለቱ መካከል አንዱን ምረጡ ሕይወት ወይስ ሞት 💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚💯𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 💯𝙟𝙤𝙞𝙣💯𝙟𝙤𝙞𝙣💯𝙟𝙤𝙞𝙣 @surafelma @surafelma