ትምህርተ ወንጌል
Статистикаየሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ለተለያዩ አስተያየቶች ጥቆማዎች በውስጥ መስመር ያናግሩን @Buralike
- Последний пост
- 3 янв. 2025 г.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
መቅረት ክልክል ነው
አንደምን ቆያቹ የእግዚያብሔር ቤተሰቦች ያገለገለ ክራር መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች ካላቹ ከስር ባለው ሊንክ እናግሩኝ 👉👉@Buralike👈👈
👉ጥያቄ መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነብዩ ሙሴን ለምን ያህል ጊዜ አናግሮታል
አምላካችን እግዚብአሔር እኛን የፈጠረን ስሙን ለመቀደስ፣ ክብሩን ለመውረስ በመሆኑ በትሕትና ለእርሱ ተገዝተን መኖር አለብን፡፡ ለሌሎች መዳንም ምክያት እንድንሆን በሕይወት ውስጥ የሚገጥሙንን ሰዎች በየዋህነትና በትሕትና መቀበል እንዲሁም አብሮ በፍቅር መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ይከተሉት ለነበሩት ደቀ መዛሙርቱ መኖርና ማገልገል ያለባቸው በትሕትና መንፈስ መሆን እንዳለበት እንዲህ ሲል ይገልጻል፤ ‹‹ነገር ግን ከእናንተ የሚበልጠው አገልጋይ ይሁናችሁ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፡፡ ራሱንም ዝቅ የሚያደረግ ሁሉ ይከብራልና፡፡ (ማቴ. ፳፫፥፲፩-፲፪) አምላካችን ያዘዘን እንዲህ ሁኖ ሳለ በዚህ ጊዜ ከፈጣሪያቸው የራቁ ብዙኃን ሰዎች ግን የዋህነትም ሆነ ትሕትና በውስጣቸው ባለመኖሩ ትዕቢት በላያቸው ሰልጥኖባቸዋል፤ ልባቸውም በክፋት ደንድኗል፡፡ ይህም በድፍረት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲተላለፉና ኃጢአት አብዝተው እንዲሠሩ ስለሚያደርጋቸው ከእውነተኛ መንገድ የራቁ ከመሆናቸውም በላይ ለሌሎችም ጥፋት መንሥኤ ይሆናሉ፡፡ በፍቅርና በመተሳሰብ መኖር ሲገባ፤ ጥያቄም ሆነ እርዳታ ሲጠየቁ በትሕትና ከመመለስ ይልቅ ክፋትና ጥላቻ በተሞላበት አንደበት ምላሽ ይሰጣሉ፤ በአብዛኛው ጊዜም በጎ ሥራንም ለመፈጸም ፍቃደኛ አይደሉም፡፡ ሰዎች የዋህነት ወይንም ትሕትና ሲጎላቸው ከፍቅር ይልቅ መጥፎነት ያስባሉ፡፡ በቤተሰባዊም ሆነ በማኅበራዊ ግንኙነታቸው መከባበር እንዳይኖር፣ መናናቅ እንዲፈጠርና ክፋት እንዲስፋፋ ይጥራሉ፡፡ በዚህም ፍቅርና ሰላም አጥተው ዘወትር በስጋትና በጥላቻ ስሜት ይኖራሉ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ በምድራዊ ጉልበቱ ተመክቶ የኋላኛውን ዓለም ሳያስብ ቢኖርና ለኃጢአቱ ስርየት ሳያገኝ ቢሞት ዘለዓለማዊ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በልባቸው የዋሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመንፈስ ትሑታን የሆኑትንም ያድናቸዋል›› ብሎ በመዝሙሩ እንደነገረን በምድር የሚገጥሙንን መከራና ፈተና ለማለፍ እንዲሁም ድኅነተ ነፍስን ለማግኘት በንስሓ ወደ ፈጣሪ ተመልሰን የዋህነትን ልንለብስ ትሑትም ልንሆን ይገባናል፡፡ (መዝ.፴፫፥፲፰)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞✞✞ 🙏" ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት "🙏 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ የተሰበሰብነው በስምህ ነውና ወደኛ ተመልከት በመካከላችንም ተገኝልን ። መንፈሳችንን በጸጋህ ሙላልን በምንማማርባቸውና በምንነጋገርባቸው ነገሮች መወሰን የሚገባንን አሳየን በነገር ሁሉ አንተን ደስ የሚያሰኝ አንተ የምትመራን ቤተክርስቲያንንም የሚያከብር አድርግልን ። የውሳኔያችን መሪ አንተ ብቻ ሁን ። ፍሬያማ እንዲሆኑ የምታደርግም አንተ ብቻ ነህና ድንቁርናችንን ፣ ግብዝነታችንንና የዓለምን ሥርዓት ለመከተል መጣራችን ስሕተት እንዳይጥለን ጠብቀን ። ከአባቶቻችን ጋር ሆነህ በጉባኤያቸው ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ለማጽናትና የክህደትን አረም በሚነቅሉ ወቅት እንደተገኘህና ሁለንተናቸውን እንደረዳህ እኛንም እንዲሁ ርዳን ። የተሰበሰብነው በስምህ ስለሆነ ሐሳባችንን ሁሉ በዚህ ዓለም ሐሳብ ሳይባክን ከአንተ ሳይለይና በፍቅርህ ለተመሠረተው እውነተኛነት እንድንጣጣር አድርገን ። በስምህ በተሰበሰብነው አንዳችንም የተለወጠና ክፋትን የሚያስብ ልቦና ይዘን በዚህ ጉባኤ እንዳንቀርብ አድርገን ። ክብርህን ለመመስከር በተቀበልናት በዚች ኃላፊነት ሁሉ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ብለን በትሕትና እንድንመላለስም አድርገን ። ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ማኅበራችንና ጉባኤያችንን ባርኪልን ። የማኅበራችንን እቅድ ፣ አማናዊ ሕይወት የሚያሰጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለሁሉ ለማዳረስ የምናደርገውን ጥረት ሁሉ አንቺ አስፈጽሚን ። በማናቸውም ምክንያት መሰባሰባችንንና አንድነታችንን እንዳንተው መጽናናትን ስጪን ። ጉባኤ ሐዋርያትን የባረከ አምላክ የኛንም የደካሞቹን መሰባሰብ ይባርክ ። በሁላችን እናት በእመቤታችን ድንግል ማርያም ስም ለዘላለሙ አሜን ። አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር : ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ : ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች ፡ እንዲሁም በምድር ትሁን ። የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ ፡ በደላችንንም ይቅር በለን ፤ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል ። አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ፡ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ :መንግሥት ያንተ ናትና ፡ ኃይል ክብር ምስጋናም ፡ ለዘላለሙ አሜን ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ፤ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ፡ሰላም እንልሻለን:በሀሳብሽ ድንግል ነሽ : በሥጋሽም ድንግል ነሽ ። የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ : ሰላምታ ላንቺ : ይገባል ። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና : የማኅፀንሽም ፍሬ ፡ የተባረከ ነው ። ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ ፡ ልዑል እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ፡ ከተወደደው ልጅሽ ፡ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ፡ ይቅርታንና ምሕረትን ለምኝልን ፡ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘላለሙ አሜን ። 🤲
🔴ከቅዳሴ ማርያም ➤ለመለኮት እንደ ፀሐይና እንደ ጨረቃ ክበብ እንደ ሰውም መጠን ያለው አይደለም ድንቅ ነው እንጂ። የሰው ኅሊና የመላዕክትም አእምሮ በማይደርስበት በአርያም የሚኖር ነው እንጂ ። ➤ለመለኮት ወርድና ቁመት ላይና ታች ቀኝና ግራ ያለው አይደለም በሁሉ የመላ ነው እንጂ ። ➤ለመለኮት የሚዘረጋበት የሚሰበሰብበት ያለው አይደለም ግዛቱ ባገር ሁሉ ነው እንጂ ። ➤ለመለኮት በላይ ጠፈር በታችም መሠረት ያለው አይደለም ጠፈሩ እርሱ መሠረቱም እርሱ ነው እንጂ ። ➤ለመለኮት ከምድር ከውስጥዋ የሆነውን ያነሳ ዘንድ ማጎንበስ ራስንም ዝቅ ማድረግ ያለበት አይደለም ለጴጥሮስ እንዳሳየው ሁሉ በእጁ የተያዘ ነው እንጂ ። ➤ለመለኮት በሚታይ ገንዘብ በሚወሰንም ገንዘብ ደረትና ፊት የኋላም ጀርባ ያለው አይደለም በነደ እሳት የተሸፈነ ነው እንጂ ። ነደ እሳት ግን እርሱ ነው ። መለኮትስ ንጹህና ጽሩይ ብሩህም ነው ። ➤የላከ አብን በህላዌ አባት እንደሆነ እናምናለን የተላከ ወልድንም በህላዌ ወልድ እንደሆነ እናምናለን ማኅየዊ መንፈስ ቅዱስንም በህላዌ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እናምናለን ሦስቱ ስም አንዱ እግዚአብሔር ነው ። ➤አብርሃም ከይስሐቅ እንደሚበልጥ ይስሐቅም ከያዕቆብ እንደሚበልጥ አይደለም ለመለኮት እንዲህ አይደለም ። አብ ከልጁ አይበልጥም ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም መንፈስ ቅዱስም ከወልድ አያንስም ወልድም ከአባቱ አያንስም ። ➤አብርሃም በፍጥረት ሥርዓት ይስሐቅን እንደሚያዘው ይስሐቅም ያዕቆብን እንደሚያዘው አይደለም ። መለኮት እንዲህ አይደለም አባት በመሆን አብ ልጁን አያዝዘውም ወልድም ልጅ በመሆን አይበልጥም መንፈስ ቅዱስም ትክክል ነው ። ➤መለኮት ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ነው ። አንድ አምላክ አንዲት መንግሥት አንዲት ሥልጣን አንዲት አገዛዝ ነው ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
✝✝ጥያቄ? ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መዳኒታን ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግልና እንደምትወልድ ያበሰራት ቅዱስ መልአክ ማን ነው ?
без подписи
◽️ ተክለሃይማኖት ፃድቅ◽️ ተክለሃይማኖት ፃድቅ ስምህ ያድናል ከመውደቅ ተክለሃይማኖት ፃድቅ ስምህ ያድናል ከመድቀቅ ቅኔ ልቀኝልህ ልዘምር በደስታ አይቻለሁ ባንተ ችግሬ ሲፈታ/2/ ስጋዬ ታሞብኝ ተጨንቃ በህይወቴ በስምህ ታመንኩኝ ተክለ አብ አባቴ ከቤቴ ሳልወጣ ገዳምክን ሳስበው መከራው አልፎልኝ በአይኔ አይቻለሁ ኢትዮጵያዊው ፃድቅ ተክለሃይማኖት ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት አዝ==== ስፍገመገም ልወድቅ በዝቶ ፈተናዬ ደገፍከኝ አባቴ መተህ መመኪያዬ ተስፋዬ ተሟጦ አይኔ እንባ ሞልቶ ፀበልህ ሲነካኝ አገኘሁኝ ድህነት ኢትዮጵያዊው ፃድቅ ተክለሃይማኖት ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት አዝ==== በተስፋ ሞልተኸኝ ስመጣ ከደጅህ የበዛው ህመሜ ሸፈንከው በፅድቅህ ሞኝ ነው ይሉኛል ሳያውቁ አባቴ መሰከርኩ ልጅህ በርትቶ ጉልበቴ ኢትዮጵያዊው ፃድቅ ተክለሃይማኖት ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት አዝ==== ከችግር ከሀዘን ያመነህ ይወጣል አይኑ ተከፍቶለት አብርቶ ይታያል በሰው እጅ የመጣ ነበር ይሆን እና ድኖ ይመለሳል በፅድቅህ ገናና ኢትዮጵያዊው ፃድቅ ተክለሃይማኖት ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት አዝ==== የደብረ አስቦቱ የኢቲሳው አባት መሰከረች በእውነት ፅላልሽ በእውነት ክንፍን የተሸለምክ የምህረት አባት ዳቢሎስ አፈረ ስትታይ በዳሞት ኢትዮጵያዊው ፃድቅ ተክለሃይማኖት ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት https://t.me/yemsganasehat
⛪️📚🙏 1, እመጓ 2, ዝጎራ 3, መርበብት 4, ዴርቶጋዳ 5, ዮራቶራድ 6, ዣንቶዣራ 7,መጽሐፈ ሄኖክ 8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ 9, ፍኖተ አእምሮ 9, አዳም እና ጥበቡ 10, ዝክረ መስቀል 11, ሰይፈ ሥላሴ 12, ፍትሐ ነገስት 13, መጽሐፈ መነኮሳት 14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና 16, ህግጋተ ወንጌል 17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን 18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል 19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ 20, ግድለ ተክለሃይማኖት 21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ 22, የወጣቶች ህይወት 23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት 24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት 25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ 📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖 ✝ ይቀላቀሉን ✝
ክፍል 8 በተደጋጋሚ በሮሜ መልዕክት ላይ የተጠቀሱ ቃላት ትርጉም የቀጠለ...👆👇👆👇 መዳን ድኅነት (Salvation) ይህ ቃል በሐዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ይገኛል። ይህ ቃል የግሪኩ ሶዞ (sozo) የሚለው ግሥ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን በሦስቱም ግሥ ማለትም በኃላፊ በአሁንና በመጻኢ (በወደፊት) ግሥ ጥቅም ላይ የዋለ ነው። መዳን በእምነት የሚደረግ ጥምቀት ዳግመኛ በመወለድና የኃጢአት ይቅርታን በማግኘት ከክርስቶስ ከሞቱና ከትንሣኤው ጋር በመሳተፍ ክርስቶስን በመልበስ ይጀምራል። ከዚያም የክርስቶስ አካል ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ በመታተም የክርስቶስን ሥጋና ደም በመመገብ ከዚያም ይህን ጸጋ ለመጠበቅና በፍቅር በሚሰራ እምነት በተግባር ለመኖር በተጋድሎ ያልፋል። ስንጠመቅ በእምነት ድነናል። ሆኖም ሶዞ (sozo) መዳን የሚለው የግሪክ ቃል በሐዲስ ኪዳን በጥቅም ላይ የዋለው በኃላፊ ግሶች ብቻ ሳይሆን በአሁንና በወደፊት ግሶችም ላይም ነው። እንዲያውም በሐዲስ ኪዳን ሶዞ(sozo) የሚለው ቃል በተደጋጋሚና ከፍ ባለ ቁጥር ጥቅም ላይ የዋለው ባለፈ ግሥ ላይ ሳይሆን በወደፊት ግሥ ላይ ነው። ስለዚህ መዳን ያለፈ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአሁንም የወደፊትም ጉዳይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ መዳን ያለፈ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአሁን ጉዳይ መሆኑን ሲገልጽ "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን (በመዳን ላይ ላለን) (who are being saved) ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። " 1ኛ ቆሮ.1:18 "ወንድሞች ሆይ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን (by which also ye are being saved) ወንጌል አሳስባችኋለሁ::" 1ኛ ቆሮ.15:1-2:: መዳን በወደፊት ግሥ ሲገለጽ ደግሞ "ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቁጣው እንድናለን። (we shall be saved from wrath) ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን (we shall be saved by his life)::" ሮሜ.5:9-10:: -"...ኢየሱስን ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ... (Jesus who deliver us from the wrath to come...)" 1ኛ ተሰ.1:10 እዚህ ላይ የእኛ ተስፋ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ በሚመጣበት ጊዜ መዳን መሆኑን በግልጽ እናያለን። "በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን (Salvation) ፈጽሙ" ፊል. 2:12 (መድሎተ ጽድቅ ቅጽ.2 : 406-408) ጸጋ (Grace) ጸጋ ነጻ ስጦታ ያለ ዋጋ የሚሰጥ ማለት ነው። መዳናችን በእግዚአብሔር ጸጋ የተሰጠ ነው። ያድነን ዘንድ አስቀድሞ የወደደና የፈቀደ ይህን አባታዊ ፈቃዱን ለመፈጸምም ሰው የሆነና እስከ መስቀል ሞት ድረስ መከራ የተቀበለ ወደ መቃብር ወርዶ በዚያም ሞትንና ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ድል አድርጎ መዳናችንን የፈጸመው እርሱ ነው። መዳናችን ጸጋ ነው የሚባለው ይህ የተሰጠንና የተደረገልን ሁሉ ከእርሱ የተገኘ (የተሰጠ) እንጂ እኛ የተገባን ሆነን ከመገኘታችን የተነሳ ያገኘነው ባለመሆኑ ነው። ከዚያም የሰጠንን የመዳን ጸጋ ገንዘብ እናድርገውና እንጠቀምበት ዘንድ ውስጣችንን ወደርሱ የሚጠራውና የሚቀሰቅሰው ወደርሱ እንድንሄድ የሚጠራንና በየመንገዱ የሚያግዘን ይህን ሁሉ የሚያደርገው እርሱ እግዚአብሔር ነው። (መድሎተ ጽድቅ ቅጽ. 2 ገጽ.242) መዳን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። መዳንን ጸጋ ያሰኘው ያድነን ዘንድ እግዚአብሔር አብ ልጁን እስኪልክልንና ለሞት እስኪሰጥልን ድረስ እግዚአብሔር ወልድም የኛን ባሕሪይ ባሕሪይው እስኪያደርግልንና መከራ ሞትን ያውም የመስቀል ሞትን እስኪቀበለልልን ድረስ የሚያደርሰው የእኛ የሆነ አንዳችም ነገር ሳይኖር እንዲሁ ያደረገልን በመሆኑ ነው። "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።" ዮሐ.3:16 እንዲል። ይህ ሁሉ ይደረግልን ዘንድ ከእኛ የሆነ ምንም ነገር የሌለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ይህን ሁሉ ያደረገልን "ጠላቶቹ ሳለን" ሮሜ.5:10 መሆኑ ጸጋውን እጅግ የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል። መዳናችንን እንዲህ ባለ ድንቅ ቸርነቱ ከፈጸመ በኋላም ይህን ሁሉ ያደረገልንን እርሱን በማመንና የመዳን ጸጋውን የምናገኝባቸውን መንገዶች በቤተክርስቲያን በኩል በማዘጋጀት እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ የሚነሱ ሰዎች ሁሉ ይድኑ ዘንድ መዳንን በነጻ ሰጠን። አምነን እንድን ዘንድ ተጠምቀን ልጅነትን የኃጢአት ይቅርታን በሞቱ መሳተፍንና በትንሳኤው ለመሳተፍ ባለ ተስፋ መሆንን ቅዱስ ስጋውን በልተን ክቡር ደሙን ጠጥተን የዘላለም ሕይወትን እናገኝ ዘንድ ይህን ሁሉ የሰጠንና ያደረገልን በፍጹም አባታዊ ቸርነቱ ብቻ ነው። ስለዚህም መዳን ጸጋ ነው ሰው አንዳችም ዋጋ ያልከፈለበት ነጻ ሥጦታ ነው። በጸጋው መዳን ማለት ይህን ሁሉ በነጻ የተሰጠንን አምኖ በመቀበል መዳን ማለት ነው። በጥምቀት የምናገኘው ልጅነትና ሌላው ጸጋ ሁሉ ነጻ ሥጦታ ነው። በምስጢረ ቁርባን የምናገኘው ሥጦታ ሁሉ ነጻ ስጦታ ጸጋ ነው። ልጅነቱ ጸጋ ነው። ሥርየተ ኃጢአቱ ጸጋ ነው። ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ጸጋ ነው። ንስሐ ገብቶ ይቅርታን ማግኘት መቻል ጸጋ ነው። ጾሙ ጸሎቱ ተዘክሮው ቅዱስ ቃሉ... ይህ ሁሉ ጸጋ ነው። የእርሱ የአባትነቱ ነጻ ሥጦታ ነው። መዳናችን በእርሱ የተፈጸመና የተሰጠ ነጻ ሥጦታ በመሆኑ ጸጋ ይባላል። የምንድነው በዚህ ጸጋ ሆኖ በተሰጠን የመዳን መንገድ በመሄድና በመኖር ነው። እያንዳንዱ ሰው ይህን የተሰጠውን የመዳን ጸጋ ለመጠቀም የራሱ ሱታፌ ወይም ድርሻ ደግሞ አለው። "በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ" ፊል. 2፥12 እንዲል። ዳግመኛም "አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደግሞ በከንቱ እንዳትቀበሉ እንለምናለን።" 2ኛ ቆሮ.6:1 በማለት የእግዚአብሔር ጸጋ ቢሰጠንም አብረን መስራተሰ ወይም የሰው ድርሻም እንደሚያስፈልግ ያስተምረናል። ይቀጥላል...
ክፍል 7 በተደጋጋሚ በሮሜ መልዕክት ላይ የተጠቀሱ ቃላት ትርጉም መጽደቅ ጻድቅነት (righteousness) "ጻድቅነት፣ መጽደቅ- righteousness የሚለው ቃል ሥርወ ትርጉሙ "የተስተካከለ ግንኙት" ማለት ነው። የመጀመርያዋ ቤተ ክርስቲያን ገጥሟት የነበረው ዋኔ ጉዳይ፣ አንድ ሰው የአይሁድን የኦሪት ሕግጋትና ሥርዓቶች (ግዝረት፣ መሥዋተ ኦሪት...) ሳይፈጽም ከእግዚአብሔር ጋር የተስተካከለ ግንኙነት ሊኖረው ይችላል ወይስ አይችሉም? የሚለው ነበር። ይህም ማለት አሕዛብ ግዝረትን እና ሌሎች በኦሪት የታዘዙትን ነገሮች ሳይፈጽሙ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመናቸው ብቻ ከእግዚአብሔር ጋር የተስተካከለ ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ነበር። ቢጽ ሐሳውያን (Judaizers) ይባሉ የነበሩት ወገኖች "አይችሉም" ብለው በአሉታ መለሱ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ "ይችላሉ" ብሎ በአወንታ መለሰ። ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜና በገላትያ መልዕክቱና በገላትያ መልዕክቱ ላይ በዋናነት የጻፈው በዚህ ጉዳይ ዐውድ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ ላይ ስለ መጽደቅ የጻፈው "ከክርስቲያናዊ መልካም ሥራ ነጻ ስለመውጣት ነው" የሚለው የፕሮቴስታንቶች አተረጓጎምና አረዳድ እነርሱ ራሳቸው የፈጠሩት አረዳድ እንጂ አንዳችም የቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ መሰረት የለውም። ጉዳዩ በክርስቶስ በማመን ከሚገኝ ከኦሪት የግዝረትና የመንጻት ሥርዓቶች ነጻ የመሆን ጉዳይ እንጂ በእምነት መልካም ሥራ ከመሥራት ነጻ መውጣት የሚል አይደለም። (መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2. ገጽ. 404) ስለዚህም መጽደቅ በክርስቶስ ምህረት ይቅርታን እንዳገኘን የሚገልጽ ቃል ነው። መጽደቅ ቅጽበታዊና በአንዴ የሚፈጸም በኃጢአት እንኳ ቢኖር ለዘላለማዊ ድህነት ዋስትና የሚሰጥ የተሳሳተ ትርጉም የለውም። መጽደቅ ሲባል ክፍ ኃጠአተኛ የነበረው ጻድቅ እውነተኛ የሚሆንበት ሕጋዊ ብያኔም አይደለም። ይልቅ መጽደቅ በክርስቶስ ለሚያምንና ለሚከተል ሕያውና ሂደታዊ የሆነ dynamic የሆነ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር የተስተካከለ ግንኙነት መኖር ነው። ቀድሞ በኃጢአት ምክንያት የተፈጠረው የጥል ግድግዳ ፈርሷል። ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን የጥል (ያልተስተካከለ) ግንኙነት በመስቀሉ በፈጸመው እርቅ ተስተካክሏል። ይህ ነው መጽደቅ። በመስቀሉ ያገኘነውን የተስተካከለ ግንኙነት በሕይወት የምንኖረው ነው። ስለዚህ ይህ ደግሞ ቅጽበታዊ ተግባር አይደለም። መቀደስ (sanctification) አንድን አካል ወይም ቁስ ለእግዚአብሔር ስራ አገልግሎት መለየት ነው። ቅድስናም የመቀደስ ውጤት ሲሆን ለእግዚአብሔር ተለይቶ መሰጠት ነው። ይህም በፍጻሜው ከኃጢአት መንጻትማ ከዓለምና ከቁሳዊ ነገሮች መለየት ነው። ይህ ደሞ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ የሚፈጽመው ሂደታዊ ነው። መቀደስ በትህርምታዊ ተጋድሎ የሚፈጸም ነው። በኦርቶዶክሳዊው ትምህርት መጽደቅም ሆነ መቀደስ የተነጣጠሉ ሳይሆን የመዳን እግዚአብሔርን የመምሰል አካል ናቸው። ይቀጥላል...
+ አልፋና ኦሜጋ ክርስቶስ + መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ‘አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ’ አለ:: A እና Ω የግሪክ የመጀመሪያና የመጨረሻ ፊደላት ናቸው፡፡ ጌታችን መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ ሲል ከዓለም መፈጠር በፊት የነበርሁ ዓለምንም አሳልፌ ለዘላለም የምኖር እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ ወደ ጥልቁ መለኮታዊ ዘላለማዊነት ሳንገባ ያለንባትን የምድርን ታሪክ ይዘን ብቻ እንዲሁ ካየነው ክርስቶስ መጀመሪያም መጨረሻም ነው፡፡ ‘እግዚአብሔር ‘በመጀመሪያ’ ሰማይና ምድርን ፈጠረ’ ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር አብ ‘መጀመሪያ’ በተባለው በልጁ በክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ፈጥሮአል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ የሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ይህችን ምድር በግርማው መጥቶ የሚያሳልፋትም እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ ለምድርም መጀመሪያዋና መጨረሻዋ ክርስቶስ ነው፡፡ መቼም እኛም ከምድር ተፈጥረናልና ይህ ነገር እኛንም ሳይመለከተን አይቀርም፡፡ ነቢዩ ከእናቴ ሆድ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ እንዳለ በእናታችን ማሕፀን የሳለንና በኋላም ለእኛ ምጽዓት በሆነችው የሞታችን ዕለት ነፍሳችንን ወደ እርሱ የሚወስዳት መጀመሪያችንና መጨረሻችን እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ግን ለሁሉ የማይቀር ነው፡፡ ወዳጄ ክርስቶስን አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያና መጨረሻ መሆኑን ታምናለህ፡፡ በአንተ ሕይወት ውስጥ ግን ክርስቶስ እውነት መጀመሪያና መጨረሻ ነው? ለአንዳንዶች ክርስቶስ መጀመሪያቸው ነበር፡፡ ዴማስ ለክርስቶስ አልፋ ብሎ ዘምሮለት ነበር፡፡ ከጳውሎስ ጋር ሆኖ ለፊልሞና ሰላምታ ሲልክም ነበረ፡፡ በኋላ ግን ዓይኑ በተሰሎንቄ ውበት ተማረከ፡፡ የአሁኑን ዓለም ወደደና ከሐዋርያት ጋር ማገልገሉን ተወ፡፡ ክርስቶስ ለእርሱ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልሆነም፡፡ ‘ሰውን ፍጻሜውን ሳታይ አታመስግነው’ የሚለውን ቃል ዘንግተን ያመሰገንናቸው እንደ ሰማልያል አብርተው ጀምረው እንደ ሰይጣን ጨልመው የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ‘የዛሬን አያድርገውና እንዲህ እንዲህ ነበርሁ’ ብለው የሚተርኩ መነሻዬ ቤተ ክርስቲያን ነበረ የሚሉ መዳረሻቸው ሌላ የሆኑ በመንፈስ ጀምረው በሥጋ የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ክርስቶስ ግን መነሻም መድረሻም እኔ ነኝ ይላል፡፡ ክርስቶስ የማጣት ጊዜ አምላክህ የማግኘት ጊዜ ትዝታህ አይደለም፡፡ በማግኘትህ ውስጥም እግሩን አትልቀቀው፡፡ በደጅ ጥናትህ ጊዜ ጌታዬ ካልከው ስትሾምም አትርሳው፡፡ ቀንህን ስትጀምር ስሙን ጠርተህ ከጀመርህ ወደ ሥራህ ቦታም ስትሔድ ቤትህ አስቀምጠኸው አትውጣ፡፡ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነውና በእርሱ የጀመርከውን ቀንህን ከእርሱ ጋር ጨርሰው፡፡ ሰው በሥራ ቦታው በንግዱ ብዙ ወንጀል የሚሠራው ፈጣሪውን ሥራ ማስጀመሪያ ብቻ ሲያደርገው ነው፡፡ እግዚአብሔር መፍጠር የጀመረባትን የሳምንቱን መጀመሪያ እሑድ ዕለትን አሐዱ ብለን በቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር እንጀምራለን፡፡ በማግሥቱ ወደ ሥራና ማኅበራዊ ሕይወታችን ስንገባ ግን ክርስትናችን ይጠፋል፡፡ ሳምንቱን አልፋ ብለን የጀመርንበት አምላክ ኦሜጋ ሆኖ አብሮን እንዳይሰነብት እናደርገዋለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ማደሪያው እንጂ መቃብሩ አይደለችም፡፡ እርሱ በቤተ ክርስቲያን በረድኤት ቢገለጥም በሁሉ ቦታም የሞላ አምላክ ነው፡፡ ክርስቶስን የምናስበው እሑድ ብቻ ከሆነና በሌሎቹ ቀናት በምንውልበት ሥፍራ የማናስበው ከሆነ ፤ ‘’ሥራ ሌላ ክርስትና ሌላ’’ ብለን የምንገድበው ከሆነ ትንሣኤውን ሳይሰሙ እሑድ ዕለት በመቃብሩ ሽቱ ሊቀቡ እንደሔዱት ቅዱሳት ሴቶች በእኛ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ገና አልተነሣም ማለት ነው፡፡ ‘ከቤተ ክርስቲያን ስትወጣ ክርስቶስን ከረሳኸው ክርስቶስ ለአንተ አልተነሣም ማለት ነው’ ይላል ቅዱስ አምብሮስ፡፡ ሐዋርያት ጌታ በምድር ሲመላለስ በነበረ ጊዜ ሁሉን ትተው የተከተሉት መጀመሪያቸው እርሱ ነበር፡፡ ዐርብ ዕለት ግን ከመካከላቸው ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ ኮበለለ፡፡ እነርሱም መከራ ፈርተው ተበተኑ፡፡ ዮሐንስ ብቻ የወደደውን እስከ መጨረሻው ወድዶ ተከተለው፡፡ እርግጥ ነው የቀሩት ወንድሞቹም ከትንሣኤው ወዲያ በንስሓ ተመልሰው መጀመሪያቸውን ክርስቶስ መጨረሻቸው አደረጉት፡፡ ክርስቶስን ከማንም በላይ መጀመሪያዋም መጨረሻዋም ያደረገችው አልፋና ኦሜጋ የተጻፈባት ድንግል ማርያም ነበረች፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለዓለም ሊሠጥ ሲፈቅድ ዓለምን ወክላ የተቀበለችው ድንግል አልፋ ክርስቶስ በማሕፀንዋ ተጽፎባት በቤተልሔም ግርግም በእቅፍዋ ነበረ፡፡ ከመስቀሉ ሥርም ቆማ ቃሉን ትሰማ ነበር፡፡ ያለ ምጥ የወለደችው ድንግል አርብ ዕለት በልጅዋ ሥቃይ ተሰቃይታ ስታምጥ ምጥ ካለ ልጅ መኖሩ አይቀርምና ‘እነሆ ልጅሽ’ ብሎ ዮሐንስን ሠጣት፡፡ በእርስዋ ሕይወት ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ ነበረ፡፡ ወዳጆች ሆይ ዛሬ የእግዚአብሔር ልጆች ነን ፤ ነገ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ አልክድህም ብለን እንዳንዝት ሦስቴ እንዳንክደው እንፈራለን፡፡ መጀመሪያችን የሆነው አምላክ መጨረሻችን እንዲሆን ግን ‘እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን’ እያልን ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጸልያለን፡፡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥቅምት 14 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አላውቀውም ብሎ ሦስት ጊዜ የካደው ሐዋርያ ስም ማን ይባላል ?
ክፍል 6 የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች 👉 ሮም አሁን የኢጣልያ ዋና ከተማ ናት። በቀድሞው ዘመን ግን የታወቁት ዓለማት ሁሉ ርዕሰ ከተማ ነበረች። ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ ምዕራቡንና ምስራቁን ዓለም የሚገዙ ነገሥታት የሚነግሱ በዚያች ከተማ ነበር። ስለዚህ የዓለም ከተማ ትባል ነበረች። የሮም ግዛት ሰፊ በመሆኑ በየቅኝ አገር የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ወደ ሮሞ እየገቡ ስለሚኖሩ የሕዝቡ ብዛት መጠን አልነበረውም። መደበኛ ቋንቋው ግን ግሪከኛ ነበር። በዚህም ምክንያት ኤሊኖሮማይስ (የግሪክና የሮም) አገዛዝ እየተባለ ይነገር ነበር። የንጉሠ ነገሥት ከተማ በመሆኗ የልዩ ልዩ ሃይማኖት ሰዎችም ይገኙበት ነበር። ከ ክርስቶስ ልደት በፊት 61 ዓመት አስቀድሞ ፓምፔ የተባለው ሮማዊ የሶርያ ገዢ በደማስቆ በኩል አልፎ ከአይሁድ ጋር በመዋጋት ኢየሩሳሌምን ከያዘ በኋላ አይሁድን ማርኮ ወደ ሮሜ ስለወሰዳቸው ከሮማ ነዋሪዎች መካከል ብዙ አይሁድ ይገኙ ነበር። 👉 ቅዱስ ጳውሎስ በ 52 ዓ.ም ከአቴና ወጥቶ ወደ ቆሮንቶስ በሄደ ጊዜ በቀላውዴዎስ ቄሳር አዋጅ ከሮሜ ተሰደው የመጡ አቂላንና ሚስቱ ጵርስቅላን አገኘ። ከነርሱም ጋር አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል ቆየ። አቂላና ጵርስቅላ በሮሜ ስለሚገኙ ክርስቲያኖች ለቅዱስ ጳውሎስ ነገሩት። እነዚህ በሮም ያሉ ክርስቲያኖች በበዓለ ሃምሳ በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ያመኑና ሐዋ. 2:10 በልዩ ልዩ ምክንያት ወደ ሮሜ በገቡ ክርስቲያኖች የተሰበኩ ናቸው። የሮሜ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ከሁለት ወገን የተገኙ ነበሩ። ከአይሁድና ከአረማውያን (አሕዛብ):: ሁለቱም በክርስትና የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች መሆናቸውን ረስተው በጥንቱ ልማዳቸው የተነሳ ክርክር ፈጠሩ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ክርስቲያኖች መልዕክቲቱን ሊጽፍ የተነሳው በዚህ ምክንያት ነበር። 👉 ቅዱስ ጳውሎስ ከሮሜ ክርስቲያኖች መካከል የሚያውቃቸው ሰዎች ስላልነበሩ አቂላና ጵርስቅላ ከከተማዋ ክርስቲያኖች የአንዳንዱን ስም ሰጡት። እርሱም መልዕክቲቱን አዘጋጅቶ የአንክራኦስ ዐቃቢት በነበረችው በፌቤን እጅ በ 54 ዓ.ም አከባቢ ላከላቸው። ሮሜ.16:1::
ክፍል 5 ሁለተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞ ሁለተኛው ጉዞ የተከናወነው በ 50 ዓ.ም ገደማ ነው። በመጀመርያው ጉዞ ማርቆስ አብሮ ተጉዞ ነበር። ነገር ግን ጵንፍልያ ከተማ ሲደርስ እናቱ ስለናፈቀችው መመለስ በመፈለጉ በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞት መጣ። ስለዚህም በሁለተኛው ጉዞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስን ይዞ ወደ ኪልቅያ ሶርያ ሲጓዝ በርናባስ ደግሞ ማርቆስን አስከትሎ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። በዚህም ጉዞው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ግሪክ ደርሷል። የተጓዘባቸውና ያስተማረባቸው ከተሞችም:- ድርብያ ልስጥራ ፍርግያ ገላትያ ሚስያ ጢሮአዳ ሳሞትራቄ ናፑሊ ፊልጵስዩስ ተሰሎንቄ በርያ አቴና ቆሮንቶስ አንክራኦስ ኤፌሶን ቂሳርያ ኢየሩሳሌም እና አንጾኪያ ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁን ጢሞቴዎስን የጠራው በዚህ ጉዞው በልስጥራ ነው። ሦስተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞ ይህ ጉዞ የተከናወነው በ 54 ዓ.ም ገደማ ሲሆን በዚህ ጉዞው ሉቃስን ጢሞቴዎስን ቲቶን አስከትሎ በኋላ ጊዜው መነሻው ከሆነች ከአንጾኪያ ይነሳል። ከዚያም ተነስቶ ገላትያን ፍርግያን እያስተማረ ወደ ኤፌሶን ወረደ። በኤፌሶንም ሁለት ዓመት ተቀምጦ ከቆየ በኋላ በጢሮአዳ አድርጎ ወደ መቄዶንያ ሄደ። በዚያም በ 2ኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ጊዜ ያቋቋማቸውን አብያተ ክርስቲያናት እየጎበኘ እያስተማረም ቆየ። አልኮሪቆን የተባለውንም አገር ለመጎብኘት የቻለው በዚህን ጊዜ ነው። (ሮሜ. 16:9) ማለት ከዚያ ሲነሳ በአልኮሪቆን አድርጎ ወደ ቆሮንቶስ ወርዷልና። በቆሮንቶስም 3 ወራት ሲያስተምር ከቆየ በኋላ ወደ ሶርያ ለመመለስ ተገደደ። ምክንያቱም አይሁድ አጽንተው ይጠሉት ነበርና። እንደገናም ከቆሮንቶስ ወደ መቄዶንያ ሄደ። በጢሮአዳ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። ሐዋ. 20:13:: በዚህ በመጨረሻው ሐዋርያዊ ጉዞ ለ 4 ዓመታት ያህል ሲዘዋወር ቆይቷል።
ክፍል 4 የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ 👉 አንድ ገበሬ መሬቱ ለዘሩ ዘሩም ለመሬቱ ተስማሚ መሆኑን አውቆ እንዲዘራ ጳውሎስም ትምህርቱ ለሕዝቡ ሕዝቡ ለትምሕርቱ ተስማሚ የሚሆንበትን ቦታና ጊዜ የትምህርቱንም ዓይነት እየመረጠ ይሰጣቸው ነበር። የሚሰብክባቸው ቦታዎች በዚያን ጊዜ በዓለም የታወቁና ብዙ ሕዝብ የሚገኝባቸው አህጉር (ከተማዎች) ነበሩ። ለምሳሌ አንጾኪያ፣ ኤፌሶን፣ ተሰሎንቄ፣ ቆሮንቶስ፣ አቴና፣ ሮምና የመሳሰሉት ነበሩ። ደግሞም የሚያስተምረው በተለያየ ሰው በተሰበሰበት ቦታ በምኩራብ፣ በአደባባይ በገበያ፣ በቲያትር ቦታ ነበር። በየደረሰበትም ሀገር በመጀመርያ የሚገባው የሚያስተምረው በአይሁድ መካከል ነበር። ስለዚህም ከነርሱ ውስጥ ክርስቲያን ያደረጋቸው ብዙዎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ከአሕዛብም ውስጥ ያሳመናቸው እጅግ በጣም ብዙ ነበሩ። በዚህም ምክንያት የአሕዛብ መምህር ይባላል። ጳውሎስ ባመነ ጊዜ ክርስቲያኖች የሚገኙት በኢየሩሳሌምና በአከባቢዋ ብቻ ነበር። ነገር ግን ጳውሎስ በትጋት ከማስተማሩ የተነሳ በእርሱ ጊዜ ከኢየሩሳሌም አንስቶ እስከ እስጳንያ ያሉት አገሮች ክርስትናን ተቀብለው ቤተ ክርስቲያን አቋቁመው ተገኝተዋል። እየደረሰ በቃል ካስተማራቸው ይልቅ በኋላ በመልዕክት መልክ ያስተላለፋቸውና ያሳመናቸው እጅግ ብዙዎች ናቸው። ይህንንም ሁሉ ሲሰራ ይህንንም ሁሉ ሀገር ሲዞር ከቶ አንድ ቀን አስቸግሮ ከሰውም ገንዘብ ወስዶ አያውቅም።በእጁ እየሰራ ራሱንም ሰውንም ይረዳ ነበር እንጂ። (1ኛ ቆሮ. 4:12፤ 9:5? ፤2ኛ ቆሮ.11:7 ፣ሐዋ ሥራ. 20:34፣ 1ኛ ተሰ. 2:9:: እንዲህ የወንጌል አገልግሎት በትጋት ከፈጸመ በኋላ "መልካሙን ገድል ተጋድያለኹ፥ ሩጫውን ጨርሻለኹ፥ሃይማኖትን ጠብቄያለኹ::" 2ኛ ጢሞ.4:7 በማለት ጽፏል። ቅዱስ ጳውሎስ የክርስቶስ ወንጌልን ለማስተማር ሦስት የሐዋርያዊ ጉዞዎች በማድረግ የክርስትና እምነት በመካከለኛው ምስራቅና በአውሮፓ እስከ ስፔን ድረስ አስተምሯል። የመጀመርያው የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞ 👉 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ (ሐዋ. 13:1-13) በአሕዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ጋር ወጡ። በዚህ ጉዞዋቸው በጠቅላላው ወደ 2000 ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል። ይህም ጉዞ የተከናወነው በ 46 ዓ.ም አከባቢ ነው። የተሸፈኑትም ሀገሮች ሲሊንውቂያ፣ ቆጵሮስ፣ ስልማና ጳፋ ጰርጌን ገላትያ ጵስድያ ኢቆንዮን ሊቃኦንያ ልስጥራ ደርቤን ጵንፍልያ አታልያ እና አንጾኪያ ናቸው። (ሐዋ 14) ቅዱስ ጳውሎስ በጉዞው አንጾኪያ እንደደረሰ ከአይሁድና ከአረማውያን ወገን ክርስቲያን የሆኑት ወገኖች ተጣልተው አገኘ ምክንያቱም አይሁድ አረማውያንን በክርስቶስ ብታምኑ ብትጠመቁ ም ካልተገረዛችሁ ምን ይረባችኋል? እያሉ ያደክሟቸው ነበርና። ጳውሎስ ይህን ሁከት ለማረጋጋት ሲል ሐዋርያት ወዳሉበት ወደ ኢየሩሳሌም ወረደና ሁኔታውን አስረዳ። ሐዋርያትም ተሰብስበው የመጀመርያውን ሲኖዶስ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ 50ኛው ዓመት አድርገው ነበር። በዚህም ጊዜ ብዙ ከተወያዩ በኋላ የመጨረሻ ውሳኔ አድርገው የተስማሙበት የሚከተለው ነበር። (ሐዋ. 15:1-30 ይመልከቱ) 💦 ከአህዛብ ወገን ክርስትናን የተቀበሉ ወንድሞች ከአይሁድ ወገን ክርስትናን ከተቀበሉት ጋር ሁሉም እኩል (ትክክል) መሆናቸውን። 💦 ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዳይበሉ ሳይታረድ ደሙ ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ እንዳይበሉ ደምም እንዳይበሉና ከዝሙት እንዲርቁ ከነዚህ በቀር ሌላ ከባድ ሸክም እንዳይጭኑባቸው። 💦 ግዝረትም በብሉይ ሕግ ውስጥ ኃይል ቢኖረውም በሐዲስ ሕግ ቦታ እንደሌለው አሕዛብም የአይሁድና የፈሪሳውያንን ልማድ ለመጠበቅ እንደማይገደዱ ወሰኑ። ይቀጥላል...👆👇👆👇
ክፍል 3 የቀጠለ...👆👇👆👇 👉 ይህን የሚያውቀው ሐናንያ በቅድሚያ ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር ጀምሮ ነበር። እግዚአብሔር አያውቀው ይመስል ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ማስረዳት ጀመረ። በመጨረሻ ግን "ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና" በማለት እግዚአብሔር ሐናንያን ላከው። ሐዋ. 9:13-15። 💦 ጳውሎስም በተጠመቀ ጊዜ አይኑ በራለት፣ ምስጢር ተገለጸለት። መንፈስ ቅዱስም አደረበትና ላዲሱ ሃይማኖት ቀናተኛ ሆኖ ልዋል ላድር ሳይል ዕለቱን ማስተማር ጀመረ። ክርስቶስ ተጠምቆ ልዋል ላድር ሳይል ዕለቱን ገዳም እንደገባ ሳውልም ከተጠመቀ በኋላ ጥቂት ቀን በደማስቆ ቆይቶ ወደ አረቢያ ምድረ በዳ ሂድ ሦስት ዓመት ተቀምጦ ሱባኤውን ፈጸመ። ገላ.1:17። እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ። በዚያም በነበሩ በአይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ። ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት። በጣም ተናደው ለመግደልም ብዙ ሙከራ አደረጉ። ስለዚህም በሌሊትም በቀንም የደማስቆን በር ይጠብቁ ነበር። ክርስቲያኖች ግን ይህን በሰሙ ጊዜ በቤቱ መስኮት አውጥተው በቅርጫት አድርገው አሹልከው ሰደዱት። ሐዋ.9:24-25፤ 2ኛ ቆሮ. 11:33። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ወረደ ከዚያም ወርዶ ሐዋርያትን (ለማግኘት) ይፈልግ ጀመር። ሐዋርያት ግን ቀድሞ የክርስቲያን ጠላት መሆኑን በማወቃቸው ይሸሹት ነበር። ሐናንያና በርናባስን አግኝተው በክርስቶስ ማመኑን እስኪረዱለት ድረስ። ሐዋ.9:26-27:: በኢየሩሳሌም ጥቂት ወራት ከተቀመጠ በኋላ ወደ ሀገሩ ወደ ጠርጤስ ሄደ። ከዚያም ገንዘቡን አሰናድቶ ወደ አንጾኪያ ሄደ ። 👉 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከልዩ ልዩ ሀገሮች ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን በመያዝ ሦስተኛውን ጉዞ አጠናቆ ኢየሩሳሌም ገባ። ነገር ግን ኢየሩሳሌም የገባበት ጊዜ የፋሲካ በዓል ስለነበር ከልዩ ልዩ ሀገሮች የተሰበሰቡ አይሁድ በከተማዋ ነበሩ። እነዚህ በዝርወት የሚኖሩ አይሁድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን በየሀገራቸው በትምህርቱ የተነሳ ሲቃወሙት የነበሩ ናቸው። እኚህ አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን በኢየሩሳሌም ሲያዩት ታላቅ ተቃውሞ አነሱበት። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ተቃውሟቸውን ለመግታት እንደ አይሁድ ህግ በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዓት መፈጸም ጀመረ። ነገር ግን ከኤፌሶን የተከተለውን ጥሮፊሞስን ወደ መቅደስ ያስገባው ስለመሰላቸው ተቃውሟቸው በረታ። ሐዋ. 22:29:: ከተማውንም አወኩት። ይህ ነበር ቅዱስ ጳውሎስን በ58 ዓ.ም ለሮም እስር የዳረገው። ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ታስሮ ሮም ገባ።በዚያም በቁም እስር ሆኖ ለሁለት ዓመታት ያህል ወንጌልን ሰበከ። የሁለቱን ዓመት የቁም እሥር እንደጨረሰ ወደ ኔሮን ፍርድ ቤት ቀረበ። ይህም በ60ዎቹ ዓ.ም ነው። በፍርድ ቤቱ በተደረገው ምርመራ የሮሜን ህግ የሚቃወም ምንም ወንጀል ስላልተገኘበት በነጻ ተለቀቀ። ከዚህ በኋላ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አራተኛውንና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያልመዘገበውን ጉዞውን ያደረገው። ይህ ጉዞው በመታሰሩ አዝነው ተክዘው የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት የጀመራቸውን ሥራዎች ፍጻሜ ለማየት የተደረገ ጉዞ ነው። በዚህም ጉዞው ኢየሩሳሌምን ኤፌሶንን ሎዶቅያን መቄዶንያን ቀርጤስን ጢሮአዳን ድልማጥያን እልዋሪቆን፣ ኒቆጵልዮን ብረንዲስን ጎብኝቷል። በዚህ የመጨረሻው የስብከት ጉዞው ለአራት ዓመታት ያህል ቆይቷል። 👉 በመጨረሻም በ 64 ዓ.ም ኔሮን በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመጹ ነገሩን ሁሉ ክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሳ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ መሠየፍ መታረድ እጣ ፋንታው ሆነ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ 65 ዓ.ም ተይዞ ወደ ወኅኒ ገባ። ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮማ ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሠይፎ በ 67 ዓ.ም ሐምሌ አምስት ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ። በረከቱ ይደርብን!
ከሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ የትኛውን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝