tgindex
አንድነት በተውሂድ ብቻ ነው

አንድነት በተውሂድ ብቻ ነው

Статистика

ዛሬ ቀን ሀይማኖታችሁን ሞላሁላቺሁ በናንተምላይ ፀጋየን ዋልኩላቺሁ ከሀይማኖትም እስልምናን ወደድኩላቺሁ(ሱረቱልማኢዳሕ:3) የዚህ ቻናል አላማ ሙሥሊሙን ኡማ ሀቅማቺ በቻለው ኢሥላምን ለማስገንዘብና ሙሥሊሙ አላማው ዱኒያ እሚቀር ስራ ሳይሆን አሄራ እሚሻገርን ስራ እንዲሰራ ሰበብ ለመሆንነው። ቻናላቺንን ይቀላቀሉ ሼርያድርጉ👉https://t.me/toyba99 ለሀሣብና አሥተያየት👇 👉 @Toyba55

Последний пост
24 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
34
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 071
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
128
34 постов
Вовлечённость
12,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 34
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
62
1/48двое суток
71
1/72трое суток
76

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 24 июл.54из KhalidNasirAbuumer

    https://t.me/KhalidNasirAbuumer

  • 20 июл.86из mukamil12

    ብዙዎችን ለመቀየር ብዙዎች መሆን የለብህም፥ በዋጋ ከሁሉም የምታንሰው ትንሿ ጨው በዋጋ በሚበልጧት መኃል ገብታ ለሁሉም ለውጥ እና ጣዕምን እንደምትሰጥ ሁሉ በገባንበት ሁሉ የለውጥ እና የጣዕም ምክንያት ኢንሻሏህ እንሆናለህ፡፡ ከአንድ እስራ ሐሞት ይልቅ ጠብታ ማር ብዙ ንቦችን ትስባለች፥ ከጉልበት ብልሃት ከድፍረት ዕውቀት ይበልጣል። ✍ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም https://t.me/Wahidcom

  • አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ አዋጅ አዋጅ 📍        48 ሰዓት የቀረው ምዝገባ የተከበራቹ ወንድሞች፣እህቶች በማእከላችን የሚሰጠው የቁርኣን ቂራት 3ዙር ምዝገባ ሊያልቅ በመሆኑ ፈጥናቹ እንድትመዘገቡ የመጨረሻ ሰዓታት ለይ እንገኛለን ሆነም ቀደም ሲል ካስመረቅናቸው የቃዒዳ ትምህርት በአጭር ጊዜ እቅድ አውጡቶ ተማሪዎች በሚመጥን መልኩ በTelegram,IMO,WhatsApp, zomm እያስቀራ በ1 ወር ጊዜ የቃዒዳን ት/ት  አስጨርሶ አስመርቋል አልሃምዱሊላህ። በማእከላችን ከሚሰጡ ዋና ዋና ትምህርቶች 1 ቃዒዳ 2 ቁርኣን በነዘር(እያዩ መቅራት)   3 ሂፍዝ በሽምደዳ 4 ተርቢያ በመጨረሻ የቁርኣን ትውልድን መፈጠር አላማ ይዘን  ዓመታችን አስቆጥረናል።Allhmdullialh አድራሻ ስ.ቁ 093787673 Telegram username @AbuUmerfoislam24434 በማናገር ፈጥነው ይመዘገቡ!          የማዕከሉ ዳይሪክተር Khalid Nasir                 KHALID QUR'AN HD

  • 13 июл.812из islamic_post17

    ማንም ሰው አላህ የጻፈለትን ሪዝቅ ሙሉ በሙሉ ሳይጨርስ አይሞትም፣ አንተ ሰበቡን አድርግ እንጂ ሰጪው አላህ መሆኑን አትዘንጋ። ጉዳይህን በሙሉ ለእሱ ስጥ፤ እሱ ልመናህን ሰሚ፣ ፍላጎትህንም አዋቂ ነውና። ​ልብህን ከጭንቀት አሳርፋት፤ ወፎችን የሚያበላው ጌታ አንተንም አይጥልህም🙌🤍 ➝ @islamic_post17

  • 10 июл.92из mahircomp123

    የሥላሴ ውዝግብ🙂! ® t.me/mahircomp123

  • ተማሪ ስንሆን ዱኒያ እና ዱኒያ አካባቢ ያሉ ነገራትች ትልቁ ፍላጎታችን ሊሆን አይገባም። እራሴን እንድፈትሽ ካደረጉኝ ከኢማሙ ሻፊዒይ ረሂመሁ'ሏህ ንግግሮች መሀል ለእናንተም ላጋራችሁ። "አንድ ሰው አሉ ትልቅ የሚባል የእውቀት ደረጃ ላይ አይደርስም ለመማር ብሎ ከቤት እየጠፋ እናት አባቱን ያስቸገረ ፣ገንዘቡን ሙሉ ያጠፋ፣የሚማረውን ነገር ፊት ለፊቱ ያደረገ፣ሱቅ ይሰራ የነበረ  ሱቁን የዘጋ፣ልቦናውን(ውስጡን)ረሀብ ያቃጠለው፣ከመቸገሩ የተነሳ ፀጉሩ ተባይ የኸለቀበት፣ ቤተሰቦቹ የናፈቁት ሆኖ ቤተሰቦቸ ናፈቁኝ ጠፋሁ የማውቀው ሰው አጣሁ የሚለው ነገር ያስጨነቀው ቢሆንጂ"! አይገርምም እኛ ግን ሌት ከቀን tik tok ላይ ተጥደን እንውል እናድርና ቁርአን ከበደኝ ስንል አናፍርም https://t.me/KhalidNasirAbuumer

  • 7 июл.1091из Ramus134

    ያየህብኝን አታሳይብኝ እኔ እና አንተ  የምናውቀውን  አትንገርብኝ እያየኸኝ ነው የወንጀል ሸክም አደካክሞኛል የተውከኝ እለት ያበቃልኛል ቆሽሿል ብለህ አልገፋኸኝም ከንፁህ ደጅህ ሰተርከኝ አይደል በዛው ማርልኝ በነካው እጅህ🤲 https://t.me/Ramus134

  • 5 июл.103из MizanTvOfficial

    የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ③①⑧③]👌 #ቁርኣን

  • 27 июн.15021из mukamil12

    ከሦስት ነገራቶች በፊት መሻይኮች እግር ሥር ቁጭ ብለህ ዲንህን ተማር። 📌አንደኛ ከትዳር በፊት! ትዳር ለሰው ልጅ ተወዳጅና አስፈላጊ ነገር መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም! አብዛኛውም ሰው ለወደፊት ትዳር ይዛለሁ ብሎ የተቻለውን ያህል ሐብት ለማጠራቀም ይጣጣራል! በተመሳሳይ መልኩም ሰው ወደ ትዳር ከመግባቱ በፊት መሻይክ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ዲኑን ካልተማረ ወደ ትዳር ከገባ በኋላ እማራለሁ የሚለው ዘበት ነው! በተለይም እንደ እኛ በደሃ ሐገር ውስጥ በኑሮ ውድነት ቀውስ ውስጥ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ለሚኖር ሰው ከትዳር ቦኋላ ቁጭ ብየ እማራለሁ የሚለው የማይገኝ የሕልም እንጀራ ነው። ስለሆነም አደራህን ከትዳር በፊት ዲንህን አጥብቀህ ተማር ቦኋላ እንዳይቆጨህ። 📌ሁለተኛ ስደት ከመውጣትህ በፊት! ምንም እንኳን አብዛኛው ሰው ዲኑን ያወቀው ስደት ከወጣ በኋላ ቢሆንም ስደት ላይ በ online  የሚቀሰመው ዲናዊ ትምህርት በአካል ከመሻይኽ ስር ቁጭ ብሎ ከሚማረው ትምህርት የሰማይና የምድርን ያህል ልዩነት አለው። በአካል መሻይኽ እግር ሥር ቁጭ ብሎ መማር ትልቅ ተጽዕኖ ያለውና እውቀትን ሥነ ምግባርን መተናነስን በአንድ ላይ ሰብስበን የምንማርበት ብቸኛ ቦታ ነው። ስለሆነም ወደ ስደት ከመውጣትህ በፊት ወይም ወደ ስደት ለመሄድ ከመድረስህ በፊት መሻይኽ እግር ሥር ቁጭ ብለህ ዲንህን አጥብቀህ ተማር። 📌ሦስተኛ ንጽጽር ከመጀመርህ በፊት! በተለይም በዚህ ጊዜ  ሶሻል ሚዲያ በሰፊው በተንሰራፋበት ዘመን የኩፍርና የጥመት አንጃዎች ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም እስልምናን የማጠልሸት ሥራ በተንሰራፋበት ዘመን ንጽጽር መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ለሁላችንም ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው! ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሳናስበው በቂ ዲናዊ ትምህርት ሳንማር እቭን መሰረታዊ እውቀት እንኳን ሳይኖረን  ወደ ንጽጽሩ እንገባና ከዛም ወደ ኋላ ተመልሰን እንደ አዲስ መማሩ ዳገት ይሆንብናል። ስለሆነም ወደ ንጽጽሩ ከመግባታችን በፊት ቁርአንን አሳምሮ ከማንበብ ጀምሮ ኡሱሎችን ተፍሲሮችን ዒልመል ሐዲሶችን ሉጋዎችን ሐዲሶችን መሻይክ እግር ሥር ቁጭ ብለን መማር ይኖርብናል። ንጽጽር ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና ማንም እየተነሳ የሚሰራው ሥራ አይደለም! በእናንተ ቋንቋ ሳወራችሁ ንጽጽር ማለት በአንድ ሜዳ ላይ በአንድ ጊዜ ተከላካይም አጥቂም ሆኖ እንደመጫወት ነው! ለአንድ ተጫዋች በአንድ ሜዳ ላይ በአንድ ጊዜ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ምሳሌውን ከእኔ በላይ አብዛኞቻችሁ በደንብ ትረዱታላችሁ። ስለሆነም ወደ ንጽጽር ከመግባታችሁ በፊት መሻይኽ እግር ሥር ቁጭ ብላችሁ በመማር ላይ አደራችሁን። ✍ ሁሌም ወደ አላህ ከጃዩ ወንድማችሁ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/mukamil12

  • إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّاتُ الْفِرْدَوْسِ نُزُلًا እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ የፊርደውስ ገነቶች ለእነሱ መስፈሪያ ናቸው፡፡ خَالِدِينَ فِيهَا لَا يَبْغُونَ عَنْهَا حِوَلًا በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ከእርሷ መዛወርን የማይፈልጉ ሲኾኑ፤ (መስፈሪያቸው ነው)፡፡ قُل لَّوْ كَانَ الْبَحْرُ مِدَادًا لِّكَلِمَاتِ رَبِّي لَنَفِدَ الْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَاتُ رَبِّي وَلَوْ جِئْنَا بِمِثْلِهِ مَدَدًا «ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት (መጻፊያ) ቀለሞችን በሆነ ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳን የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ባለቀ ነበር» በላቸው፡፡(ሱረቱል ካህፍ ቁ107-109) ❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️ 🩵 ከማያልቀው የአላህ ውብ ቃላቶች የምናነብበት በመልካም ስራ የምንሽቀዳደምበት ከመጥፎ የምንርቅበት በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚

  • 25 июн.95из MuradTadesse

    انه الموت يا عباد الله💔

  • የዘንድሮ (የ1448 ዓ.ሂ) የዓሹራ ጾም ከነገ ወዲያ ሃሙስ ሰኔ 18 ነው። ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን መጾም ተወዳጅ በመሆኑ ነገ ረቡዕ ሙሐረም 9ን፣ ወይም ከኋላው ጁሙዓን መጾም ይቻላል። ይበልጥ የሚወደደው ከፊት 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን መጾም ሲሆን፣ ሁለት ቀን መጾም የማይችል ሰው ዋናውን የ10ኛውን ቀን ብቻ መጾምም ይቻላል። የዓሹራን ጾም መጾም ያለፈ የአንድ አመት ወንጀልን እንደሚያስምር ነቢዩ صلى اللہ عليہ وسلم ተናግረዋል። ዛዱል መዓድ https://telegram.me/ahmedadem

  • 17 июн.132из Sle_qelbachn1

    ▪ ኢማም ኢብኑ አል-ቀይም «ወንድሙን በወንጀሉ ያነወረ ሰው፣ ያንኑ ወንጀል ሳይሰራው አይሞትም» ይላሉ። እውነት ነው፤ የሰውን ስህተት እየፈለጉ ማሸማቀቅም ሆነ መሳለቅ የደግ ሰዎች ተግባር አይደለም። ትርፉ ውርደት እንጂ ክብር አይሆንም። ነገ እኛ ላይ ላለመድረሱ ምን ዋስትና አለን? አላህ በሰዎች ነውር ከመጠመድ ጠብቆ በራሳችን ጥፋት ላይ የምንተኩር ያድርገን! 📺 t.me/Sle_qelbachn1

  • 5 июн.1941из Wahidcom

    “ደጃል” دَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም “ሐሳዌ” ማለት ነው፥ ቀደምት ሠለፎች ይህንን አሰር ለእኛ አስተላልፈውልናል። "አሰር" أَثَر የሚለው ቃል "አሰረ" أَثَرَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ትውፊት" "ቅብብሎሽ" "ቅሪት" ማለት ነው፥ "ሠለፍ" سَلَف የሚለው ቃል "ሠለፈ" سَلَفَ ማለትም "ቀደመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀደምት" ማለት ነው፦ 9፥100 ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ "የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች" እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አሏህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ "የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! እነዚህም "ሰሓቢይ" صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው፥ "የተከተሏቸው" የተባሉት ሁለተኛው ትውልድ "ታቢዒይ" تَابِعِيّ እና ሦስተኛው ትውልድ "ታቢዑ አት-ታቢዒን" تَابِع التَابِعِين ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ ሠለፍዩን ናቸው፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72 ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”*። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم ዐሊሞች ከተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" ሐዲስ እና ከሠለፎችን አሰር በደሊል ሲያንቆራጥጡት ረሻድ ኸሊፋህ፦ "የሙሐመድ"ﷺ" ሐዲስ ሆነ የሠለፎችን አሰር የሚባለውን ነገር አልቀበልም፥ ቁርኣን በቁርኣን ብቻ ይፈሠራል" ብሎ አረፈው። የእርሱ ፈለግ የሚከተሉ ዛሬ ላይ በመላው ዓለም ሲኖሩ አሥራ አራት ትውልድ በቅብብሎሽ የመጣውን የቁርኣን አረዳድ ሙሉ ለሙሉ አይቀበሉም። ቁርኣኒይ የሚባሉት ሙናፊቁን "ቁርኣን በቁርኣን እንጂ አይብራራም፥ ቁርኣንን የሚያብራራ መጽሐፍ ሆነ ሰው የለም" ብለው የተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" ንግግር ሆነ የሠለፎችን አረዳድ አይቀበሉም፥ የሚያጅበው ግን እራሳቸው በራሳቸው መንገድ ቁርኣን ፈሣሪዎች እና የተፍሢር መጽሐፍ ማዘጋጀታቸው ነው። ይህ አባባላቸው የሰፈር ጉልቤዎች ትዝ አሉኝ፥ የሰፈር ጉልቤዎች "እቃውን ማንም ማውረድ አይችልም" ይለሉና እራሳቸው በወሰኑት ሒሣብ ያወርዳሉ። በተመሳሳይ ቁርኣኒይ የሚባሉት ሙፍሠዲን "ቁርኣን የተብራራ ነው፥ ማንም ማብራራት አይገባውም" ይሉክና እራሳቸው አብራሪ ሆነው ታገኛቸዋለህ። ቁርኣኒያዎች አቋማቸው "ተውራት ለሙሣ አልተወረደም፥ ለማን እንደወረደ ቁርኣን አይገልጽም። እስራኤል ያዕቆብ አይደለም፥ ያዕቆብ ማን እንደሆነ ቁርኣን አይገልጽም" ይላሉ፥ ከዚያ የሐዲስ እና የሠለፎችን ተፍሢር ስታስቀምጥ አይቀበሉም። እነዚህ ሰዎች በመላው ዓለም ላይ ኢኽቲላጥን አስፋፊዎች ናቸው፥ "ኢኽቲላጥ" اِخْتِلَاط ማለት "መደባለቅ" ማለት ሲሆን ወንድ እና ሴትን በትምህርት፣ በጉባኤ፣ በአምልኮ ቦታ ደባልቀው የሚያስተምሩ እና ትውልድን የሚያበላሹ ናችው። ይህ ፈሣድ አገራችን ላይ እንደ ሰደድ እሳት በድብቅ እየተስፋፋ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ጭንብሉን ገልጦ በግልጽ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እየተስፋፋ ይገኛል፥ ይህንን ጉዳይ ስናስጠነቅቅ ትውልዱን በፈሣድ እንዳይበከል እና የእሳት እራት እንዳይሆን እንጂ የሰዎችን ግላዊ ስብዕና ለመንካት በፍጹም እና በጭራሽ አይደለም። አውቀው ይሁን ሳያውቁ የቁርኣንያን እሳቤ የሚያራምዱትን አምላካችን አሏህ ሂዳያውን ይወፍቃቸው! እኛንም ከቁርኣኒያህ ፈሣድ እና ኒፋቅ ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም

  • مَّن ذَا الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ أَضْعَافًا كَثِيرَةً ۚ وَاللَّهُ يَقْبِضُ وَيَبْسُطُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች አድርጎ የሚያነባብርለት ማነው? አላህም ይጨብጣል፤ ይዘረጋልም፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡(ሱረቱል በቀራ 245) የዛሬ የጁምዓ መልዕክቴ ለአላህ መልካም የሆነን ብድር የምታበድሩበትን ምርጥ ሰደቃ ልጠቁማችሁ ነው ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት በርካታ የውሀ ጉድጓዶችን ያስቆፈረ፣ አቅም የሌላቸው ወንድም እህቶችን በነፃ ቂርዓት የሚያስቀራ፣ የማህበራዊ ኃላፊነት ዘመቻዎችን የሚያስተባብር፣ በርካታ ወጣቶች የቁርዓን፣ የሰለዋትና የስቲግፋር ዊርድ እንዲኖራቸው ያስቻለ ተቋም ነው። ተቋሙ ለሚሰራቸው ስራዎች ማስኬጃ የሚሆን የአመት በጀት በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ይህን ምርጥ የሰደቃ ዕድል መጠቀም የምትፈልጉ @yeneatik  ላይ አናግሩን ስለ ኢፋዳ በደንብ እናስረዳቹሀለን ለሀጃዎቻችሁ ነይቱ እና ጁምዓችሁን በሰደቃ አስውቡት ❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️ ለአላህ መልካም የሆነን ብድር የምናበድርበት፣ በሩቋ ሀገር ያሉትም  ያሉበትን ጭንቅ የሚረሱበት ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በሰደቃ፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚 https://t.me/+4NTWuwaPFz83ZWI0

  • 2 июн.14911из Ramus134

    ​ የ"ቁርአንዮች" (የሐዲስ ከሐዲያን) ክህደት እና ፍንትው ያለ ምላሽ! ​አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ የተከበራችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች። ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ላይ "ቁርአን ብቻ ይበቃል፣ ሐዲስም ሆነ ተፍሲር አያስፈልግም" የሚሉ አዳዲስ ሙግቶች ሲንጸባረቁ እያየን ነው። እነዚህ ወገኖች ራሳቸውን "ቁርአንዮች" ብለው ቢጠሩም፣ በተግባር ግን የቁርአንን አንቀጾች በቀጥታ የሚክዱ ናቸው። ​ዛሬ እነዚህን ሁለት ዋና ዋና ብዥታዎች (ሹብሃዎች) በቁርአን፣ በሐዲስ እና በሎጂክ እንበትናቸዋለን። ​1፦ "ቁርአን በራሱ የተብራራ ስለሆነ የነቢዩ ማብራሪያ (ሐዲስ) አያስፈልግም" ​ ቁርአን በራሱ የተብራራ ነው የሚለው ቃል እውነት ቢሆንም፣ አላህ (ሱ.ወ) ግን ቁርአንን ለሰዎች እንዲያብራራ የመረጠውና ስልጣን የሰጠው ታላቁን ነቢይ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ነው። ቁርአን እንዲህ ይላል፦ ​وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ "ለሰዎችም ወደ እነሱ የተወረደውን ታብራራላቸው ዘንድ አንተንም ማስታወሻውን (ቁርአንን) አወረድን፤ ያስተነትኑም ዘንድ።" (ሱረቱ አን-ነሕል 16:44) ​ ቁርአን ያለ ነቢዩ ማብራሪያ በራሱ ብቻ ለሁሉም ሰው ግልጽ ከሆነ፣ አላህ ለምን ነቢዩን "ለሰዎች ታብራራላቸው ዘንድ" ብሎ ሰገየው? ይህ አንቀጽ የነቢዩ ማብራሪያ (ሐዲስ) የግድ እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ ትልቅ ማስረጃ ነው። ​ብዥታ 2፦ "እኛ የምንከተለው ቁርአንን ብቻ ነው፤ ሐዲስን አንቀበልም" "ቁርአንን ብቻ እንከተላለን" የሚሉ ሰዎች የቁርአንን ግማሽ አንቀጽ አምነው ግማሹን የካዱ ናቸው። ምክንያቱም ቁርአን በነቢዩ የመጣውን ሁሉ እንድንቀበል በግልጽ ያዛል፦ ​وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ "መልእክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም ነገር) ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ተከልከሉ፤ አላህንም ፍሩ።" (ሱረቱ አል-ሐሽር 59:7) ​በሌላ አንቀጽ ላይ ደግሞ ነቢዩን አለመታዘዝ ክህደት (ኩፍር) እንደሆነ አላህ ይነግረናል፦ ​قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ "አላህንና መልእክተኛውን ታዘዙ በላቸው፤ እምቢ ቢሉም አላህ ከሐዲዎችን አይወድም።" (ሱረቱ ዓሊ-ዒምራን 3:32) ​3. የ"ቁርአንዮችን" ጀርባ የሚሰብር ሎጂካዊ ሞገት ​እነዚህን ሰዎች ማንም ተራ ሙስሊም ሊያፋጥጣቸው የሚችልባቸው 3 ቀላል ጥያቄዎች አሉ፦ ​የሰላት ቁጥርና ረከዐ፦ ቁርአን ላይ "ስገዱ" የሚል ትእዛዝ አለ። ነገር ግን ሱብሒ 2 ረከዐ፣ ዙህር 4 ረከዐ፣ መግሪብ 3 ረከዐ መሆኑን በቁርአን ውስጥ የትኛው ምዕራፍና ጥቅስ ላይ ነው ያለው? የለም! ይህንን ዝርዝር ሕግ ያገኘነው ከነቢዩ ሐዲስ ብቻ ነው። ሐዲስን ካልተቀበልክ እንዴት ነው የምትሰግደው? ​የዘካት መጠን፦ ቁርአን "ዘካን ስጡ" ይላል። ነገር ግን ከወርቅ 2.5% (ሁለት ነጥብ አምስት በመቶ) መውጣት እንዳለበት ቁርአን ላይ የት አለ? የለም! ይህንንም ያስተማረን ሐዲስ ነው። ​የሐጅ ስነ-ስርዓት፦ ካዕባን 7 ጊዜ መዞር (ጠዋፍ) እንዳለብን ቁርአን ላይ አልተጠቀሰም። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው "ስነ-ስርዓታችሁን ከእኔ ያዙ" ያሉት። (ሶሒሕ ሙስሊም፡ 1297)። ​4. የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የትንቢት ተአምር ​የሚገርመው ነገር፣ ከ1400 ዓመታት በፊት ታላቁ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) እንደነዚህ አይነት ሰዎች እንደሚመጡ በትክክል ተንብየው ነበር፦ ​لَا أُلْفِيَنَّ أَحَدَكُمْ مُتَّكِئًا عَلَى أَرِيكَتِهِ يَأْتِيهِ الْأَمْرُ مِنْ أَمْرِي مِمَّا أَمَرْتُ بِهِ أَوْ نَهَيْتُ عَنْهُ فَيَقُولُ: لَا نَدْرِي، مَا وَجَدْنَا فِي كِتَابِ اللَّهِ اتَّبَعْنَاهُ "ከእናንተ አንዳችሁ ሶፋው (አልጋው) ላይ ተደግፎ፣ እኔ ካዘዝኩት ወይም ከከለከልኩት ነገር ትእዛዝ ሲመጣው፡- 'እኛ ይህንን አናውቅም፤ በአላህ መጽሐፍ (በቁርአን) ውስጥ ያገኘነውን ብቻ ነው የምንከተለው' ሲል እንዳላገኘው (ተጠንቀቁ)!" (ሱነን አቢ ዳውድ፡ 4605፣ ቲርሚዚ፡ 2663፣ ሸይኽ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)። ​ሱብሐን አላህ! ዛሬ ቲክቶክና ቴሌግራም ላይ ተቀምጠው "ቁርአን ብቻ" የሚሉት ሰዎች ልክ ነቢዩ እንዳሉት ሶፋቸው ላይ ተደግፈው ዲኑን ለመናድ እየሞከሩ ነው። ​"ቁርአንዮች" ነን የሚሉ አካላት ቁርአንንም ሆነ ሐዲስን የማይከተሉ፣ ይልቁንም የራሳቸውን ስሜት (ነፍስያ) አምላክ አድርገው የያዙ ናቸው። ሐዲስ ከሌለ ቁርአንን በተግባር መተርጎም አይቻልም። ዲናችን የተሟላው በቁርአን መሪነትና በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስተማሪነት (በሐዲስ) ብቻ ነው። ​ይህንን ሹብሃ ሰባሪ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ የዲንዎን ጥራት ይጠብቁ! https://t.me/Ramus134 https://t.me/Ramus134 በወንድም ረመዳን ✍️

  • 26 мая167из Yahyanuhe

    ነገ የዓለም ሙስሊሞች የዒድ አል-አድሃ በዓልን በአንድነት ያከብራሉ። ይህ በዓል ግን ከበዓልነቱና ከመሥዋዕቱ ሥርዓት በላይ፣ እጅግ ጥልቅ የሆነ የፍቅር፣ የፈተና እና የታዛዥነት ታሪክ ያለው ነው። ​ነቢዩ ኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) ልጃቸውን እንዲሠዉ ታዘዙ። አልተከራከሩም፣ አልተግደረደሩም፤ ኢምንት አላመነቱም፣ ፈቃዳቸውን ለአላህ ትዕዛዝ አስገዙ። ነቢዩ ኢስማኤልም (ዐለይሂ ሰላም) ለአባታቸው "አባቴ ሆይ፣ የታዘዝከውን ፈጽም" በማለት በታላቅ የሞራል ልዕልና ታዛዥነታቸውን አሳዩ። ​ይህ በዓል የሚያከብረው ይህንን ያለማወላወል በአላህ ላይ ያለ እምነት እና ታማኝነት ነው። ​አላህ የሚፈልገው የደም መሥዋዕቱን አይደለም፤ ፈጽሞም ይህንን አይፈልግም። አላህ የሚፈልገው ሰዎች "አምኛለሁ" ሲሉ ምን ያህል በቃላቸው እንደሚጸኑ ነው። እውነተኛ እምነት ማለት ልብን ከዓለማዊ ፍቅር ሁሉ አላቅቆ፣ ለአላህ ብቻ ማስገዛት ነው። በርግጥ ኢብራሒምና ልጃቸው ​እንደተጠየቁትም ፈጸሙ፣ በርግጥም እነርሱ በቃላቸው የሚኖሩ እውነተኞች ነበሩ። ​በዚህ የተቀደሰ ቀን አላህ ዱዓችንን፣ ጾማችንን፣ መሥዋዕታችንን እና ልመናችንን ይቀበለን። በእምነታችን ቃል ላይ የምንጸናበትን አቅምም ይስጠን። 🐏​ መልካም የዒድ በዓል ለርስዎና ለቤተሰብዎ! ​تَقَبَّلَ ٱللَّهُ مِنَّا وَمِنكُم (አላህ ከእኛም ከእናንተም ይቀበለን!) ⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻ https://t.me/Yahyanuhe

  • 21 мая165из islamic_post17

    ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِنَّ لِلَّهِ مَلَائِكَةً سَيَّاحِينَ فِي الْأَرْضِ يُبَلِّغُونِي مِنْ أُمَّتِيَ السَّلَام﴾ “የህዝቦቼን ሰላምታ ለእኔ የሚያደርሱ በምድር ተንቀሳቃሽ የአላህ መላኢካዎች አሉ።” (📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 6853) አስቡት እገሌ የእገሌ ልጅ በርሶ ላይ ሰለዋት አዉርዷል ብሎ ሲነግራቸዉ🥰 اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد🤍 Share ➕ 💻@islamic_post17✅️

  • 18 мая170из IbnulQeyyimMedresa

    📢 ታላቅ የምሥራች! የ 5 ወር ከግማሽ የዒልም ድግስ 📢 ለብዙ ጊዜ በጉጉት ስንጠብቃቸው የነበሩ ድንቅ 4 ኪታቦችን በአንድ ላይ የምንማርበት ልዩ የዒልም ማዕድ ተዘጋጅቷል ! 📚 የምንንማማራቸው ድንቅ ኪታቦች ዝርዝር፦ #1 «አዳእ ወደዋእ» (በሽታውና መድኃኒቱ)፦ ሙኽተሰር ሳይሆን ዋናውን ኪታብ ሙሉውን እናስተምራለን ። በወንጀል ለደከመች ነፍስ፣ ወደ አላህ መቃረብን ለናፈቀች ቀልብ እና ከወንጀል አዙሪት ለመውጣት ለምትታገል ነፍስያ ሁሉ ፍፁም መፍትሔ የሰነቀ ድንቅ ኪታብ! #2 «ሒራሰቱል ፈዲለህ» :- ኢስላማዊ እሴቶችን፣ የሴቶችን ሒጃብና ክብር እንዲሁም ማህበረሰባዊ ስነ-ምግባርን ከምዕራባውያን ባህል ወረራ እንዴት መጠበቅ እንዳለብን የሚያስተምር ኪታብ። #3 «መውኢዘቱ ኒሳእ»  :- በተለይ ለሙስሊም እህቶች የተዘጋጀ፣ በዱንያም በአኺራም ስኬታማ የሚሆኑበትንና ትዳራቸውን እንዲሁም ቤተሰባቸውን በዲን የሚያንፁበትን መንገድ የሚጠቁም ወሳኝ መካሪ ኪታብ። #4 «ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ» :- አላህ በማንኛውም ሰዓትና ቦታ እንደሚመለከተን (ሙራቀባህን) በማስታወስ፣ ልባችንን ለአላህ ፍርሃትና ለጥንቃቄ የሚያዘጋጅ ድንቅ የልብ ማለስለሻ አጠር ያለ ኪታብ ነው ። 📅 ቀናት፦ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:30 ጀምሮ 🛑 ምዝገባ ላይ ነን! እድሉ እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ይመዝገቡ። 🔗 ለመመዝገብ እና መስፈርቶቾን ለማወቅ ፦ @KitabAstemari 📲 የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ibnulQeyyimMedresa

  • 17 мая150из halalfkr

    ∞ጨረቃ ታይታለች∞ ¤ ወርሃ ዙልሒጃ ገብቷል። የ10ቱ የዙልሒጃ ቀናት ጾም ነገ (ሰኞ) ግንቦት10 ቀን 2018 ዓ.ል ጀምሮ 1 ብሎ ይጀምራል።

አንድነት በተውሂድ ብቻ ነው — tgindex