tgindex
TMA (Traffic Management Authority)

TMA (Traffic Management Authority)

Статистика

Work With Us / 'ከኛ ጋር ይስሩ'

Последний пост
19:06
Последнее чтение
07:09
Постов за неделю
29
Всего постов
63
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
6 699
0 за 3 дн.
Сутки
+6
+0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 485
40 постов
Вовлечённость
22,2%
к подписчикам
Постов в день
4,1
всего 63
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 271
1/48двое суток
1 456
1/72трое суток
1 570

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 19:066404

    видео или голосовое, без подписи

  • 19:056632

    ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ የመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት ተዋህደው አዲስ አበባን ምቹ የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል አድርገዋታል፡፡ የአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ፣ በ2018 ዓ.ም በርካታ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችንና ስብሰባዎችን በደመቀ ሁኔታ አስተናግዳለች። ከተማዋ ከተለያዩ የዓለም ማዕዘናት የመጡ መሪዎችን፣ ዲፕሎማቶችን፣ የቢዝነስ ሰዎችንና ባለሙያዎችን በክብር ተቀብላ፣ በብቃት በማስተናገድ በሰላም ሸኝታለች። ይህ ስኬት ከተማዋ ያላትን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ከማሳየቱም በላይ፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበቻቸውን ፈጣን የእድገትና የመዘመን ጉዞ ለዓለም ያበሰረ አጋጣሚ ሆኗል። አዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ለነበሩት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች አዲስ ፊትና ድምቀት ይዛ እንድትቀርብ ካደረጓት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል በከተማዋ የተተገበረው መጠነ-ሰፊ የኮሪደር ልማት ግንባታ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ሰፋፊና ንፁህ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መስመሮች፣ ዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና ውብ የአረንጓዴ ስፍራዎች የከተማዋን ገፅታ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል። ይህ የመሰረተ ልማት መዘመን በኮንፈረንሱ ወቅት የመጡ እንግዶች በከተማዋ ውስጥ ያለምንም እንግልትና በከፍተኛ ደህንነት እንዲንቀሳቀሱ ከመርዳቱም በላይ፣ ለአዲስ አበባ ዘመናዊና ማራኪ ውበትን አላብሷታል። የትራፊክ ፍሰቱን በማቃለልና የእይታ ውበትን በመጨመር ረገድ የኮሪደር ልማቱ ለኮንፈረንስ ቱሪዝሙ ትልቅ አጋዥ ሆኗል። ከተማዋ በቅርብ ጊዜያት የገነባቻቸው ድንቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶችና ዘመናዊ ፓርኮች ለስብሰባ የመጡ እንግዶች የትርፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ተመራጭ ስፍራዎች ሆነዋል። እንደ አንድነት ፓርክ፣ እንጦጦ ፓርክ፣ የወዳጅነት ፓርክ እና ሌሎች አዳዲስ የወንዝ ዳርቻ መዝናኛዎች እንግዶችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። እነዚህ ስፍራዎች ከተማዋ ከመደበኛ የስብሰባ አዳራሾች ባለፈ፣ እንግዶች የሚዝናኑባቸው፣ ተፈጥሮን የሚያደንቁባቸውና የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በአንድ ቦታ የሚያዩባቸው የቱሪዝም ማዕከላት ሆነው አገልግለዋል። ይህም የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ከባህላዊና ከተፈጥሮ ቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር የከተማዋን የቱሪዝም ገቢና ዝና ከፍ አድርጎታል። ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ታዋቂ የሆቴል ብራንዶች በአዲስ አበባ መበራከታቸው ከተማዋ በ2018 ዓ.ም ላስመዘገበችው ስኬት ሌላኛው ምሰሶ ነው። ሆቴሎቹ እንግዶችን በከፍተኛ የደህንነት፣ የፅዳትና የቅልጥፍና ደረጃ ከማስተናገዳቸውም በላይ፣ የኢትዮጵያውያንን ባህላዊ የእንግዳ ተቀባይነት ጨዋነት ከዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር አዋህደው አቅርበዋል። የስብሰባ አዳራሾች ዝግጁነት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችና የሰለጠነ የሰው ኃይል መኖር ሆቴሎቹ ለኮንፈረንሶቹ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አስችሏቸዋል። ከተማዋ በአንድ ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ እንግዶችን በምቾት የማሳደርና የማስተናገድ ሙሉ ብቃት እንዳላት በተግባር የታየበት ሆኗል። በአጠቃላይ አዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ያስተናገደቻቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ከተማዋ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያላትን የማይተካ ሚና ዳግም ያረጋገጡ ነበሩ። ከተማዋ እንግዶቿን ተቀብላ፣ በከፍተኛ ፍቅር አስተናግዳ፣ በሰላም በመሸኘት ያሳየችው ብቃት የሚደነቅ ነው። ይህ ስኬት ከተማዋ የገነባቻቸው ዘመናዊ የኮሪደር መሰረተ ልማቶች፣ ማራኪ የወንዝ ዳርቻዎችና የቱሪዝም ፓርኮች እንዲሁም የላቀ የሆቴሎች ዝግጁነት ጥምር ውጤት ነው። አዲስ አበባ አሁን ላይ ስብሰባዎች የሚካሄዱባት ከተማ ብቻ ሳትሆን፣ የመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት የተዋሃዱባት፣ አስተማማኝና ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል መሆኗን ለዓለም አስመስክራለች። ይህ ተሞክሮ ወደፊትም ከተማዋ ይበልጥ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እንድትስብና እንድታስተናግድ በር የሚከፍት ነው።

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 19:026361

    በከተማዋ የፍጆታ አቅርቦትን በማሳደግና ሕገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል- አቶ ጃንጥራር አባይ በከተማዋ የተጀመረው የገበያ ማረጋጋት እና የሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር ሥራዎች የፍጆታ አቅርቦትን በማሳደግና የኑሮ ውድነትን ትርጉም ባለው መንገድ በመከላከል ረገድ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አስታወቁ። የአዲስ አበባ የገበያ ማረጋጋት፣ ሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የ”አዲስ አበባ ታምርት” ግብረ-ኃይል ባለፉት ሁለት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል፡፡ ግብረ-ኃይሉ በከተማዋ የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ከሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሶስት ወራት ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፣ ባለፉት 60 ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት መድረክ ገምግሟል። በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በከተማዋ የፍጆታ አቅርቦትን ማሳደግ እና ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መከላከል በመቻሉ ገበያውን ማረጋጋት እና የኑሮ ውድነትን ትርጉም ባለው መንገድ መከላከል ተችሏል ብለዋል። ባለፉት ሁለት ወራት ሕጋዊ የንግድ ሥርዓትን በማስፈን ረገድ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል። ምክትል ከንቲባው አያይዘውም የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት በኩል የነዋሪውን እርካታ ማሳደግ ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው፣ አሁንም ገበያውን በዘላቂነት ለማረጋጋት ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ በዚህም በየደረጃው የሚገኙ የግብረ-ኃይሉ አባላት በጥብቅ ዲሲፕሊን ተቀናጅተው ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። የግብረ-ኃይሉ ምክትል ሰብሳቢ እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከአቅርቦት አንፃር አመርቂ ውጤት የተመዘገበ መሆኑን ገልጸው፣ ክፍተት በሚታይባቸው መስኮች ላይ በቅንጅት ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል። የግብረ-ኃይሉ ጸሐፊ እና የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመከላከል የግብይት ሂደቱን ፍትሃዊነት በማረጋገጥ ረገድ የተሠራው ሥራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። AMN

  • 14 авг.1 43469

    📌

  • 14 авг.1 5481110

    #እንወቅ:_

  • 14 авг.1 18512

    የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ሳምንታዊ ኦንላይን ቲቪ ስርጭት (ኦንላይን ቲቪ ዜና ነሃሴ/8 2018)

  • 14 авг.1 2391

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 2501

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 2491

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 12721

    በተያዘው በጀት ዓመት የመንገድ ደህንነት ማሻሻያ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ **************** (ት/ማ/ባ ነሀሴ 8/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥና የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ምቹ ለማድረግ በርካታ የምህንድስና ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በበጀት ዓመት ካለፈው በጀት ዓመት በተሻለ ሁኔታ እግረኞችን ከትራፊክ ግጭት ለመታደግ የሚያስችል በእግረኛ መንገዶች፣ ህዘብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች፣ በተርሚናሎች፣ ለአደጋ ስጋር በሆኑባቸው ቦታዎች በቁጥር 250 ቦላርዶች ይተክላሉ፡፡ 200 ኪሎሜትር የመንገድ ቀለም ቅብ፣ 720 ምልክትና ማመላከቻ ተከላ እና 48 የትራፊክ መብራቶች ጥገናና የማሻሻያ ስራዎች ይከናወናሉ፡፡ እንዲሁም ግጭት የሚበዛባቸው መንገዶችን በመለየት 100 የፕላስቲክና የአስፓልት የፍጥነት መቀነሻ ጉብታዎች፤ በትምህርት ቤቶች አካባቢም የመንገድ ደህንነት ማሻሻያ ስራዎችን (School zone improvement) በ15 ቦታዎች ይገነባሉ፡፡ የከተማዋ መንገድ ተጠቃሚ የትራንስፖርት አማራጮች እንዲኖሩት ለሞተር አልባ ትራንስፖርት (Non-Motorized Transport) እንቅስቃሴዎች የሚመቹ 6 ቦታዎች ላይ መሰረተ ልማቶች አንዲሟሉ ይደረጋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባለፈው በጀት ዓመት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባከናወነው ያላሰለሰ የመንገድ ደህንነት ስራዎች በከተማዋ እየደረሱ ያሉ አደጋዎች የመቀነስ አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት በትራፊክ አደጋ የደርሰ ሞት ከ2017 ጋር ሰነጻጸር በቁጥር 29 ቀንሷል፡፡

  • 14 авг.1 7728

    ❗️

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

TMA (Traffic Management Authority) — tgindex