tgindex
ጽዮን ፍሬ ዘሰንዳፋ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር እና መዝሙር ማጥኛ

ጽዮን ፍሬ ዘሰንዳፋ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር እና መዝሙር ማጥኛ

Статистика

ይህ ቻናል የተከፈተው በሰንዳፋ እና በኬ ከተማ እንዲሁም በዙሪያዋ ያሉ ኦርቶዶክሶችን ለማቀራሪብና ፤ወጣቶችን ለማንቃት፤መዝሙሮችን ለማስጠናት የተከፈተ ቻናል ነው ።

Последний пост
14 мар.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
209
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
138
22 постов
Вовлечённость
66,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 мар.127из tsionfer

    ‹‹ እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል አምላካችንም ዝም አይልም በፊቱ እሳት ይነዳል፡፡ ›› መዝ 49፡3 ~~~~~~~~~~~~~~~~~~ የአብይ ፆም 5ኛ ሳምት ደብረ ዘይት ~~~~~~~~~~~~~~~~~ ደብረ ዘይት ማለት ደብረ ዘይት ጌታችን ያረገበትና ስለ ዓለም ፍጻሜ ምልክቶች ያስተማረበት በወይራ የተከበበ ተራራ ነው ደብረ ዘይት ተብሎ በተራራው ስም ይጠራ እንጂ የጌታችን በዓለ ምጽአቱን የምናስበበት በዓል ነው ደብረ ዘይት ከጌታችን ከ18ቱ በዓላት አንዱ ነው በደበረ ዘይት ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን አስተምሯቸዋል 1የምጽዓቱን ምልክቶች 2 የምጻቱን ምሳሌዎች 3 የአመጣጡን ሁኔታዎች 1የምጽአቱ ምልክቶች የሐሰተኞች ነቢያት በክርስቶስ ስም መነሳት ልዩ ልዩ የጦር ዓይነት መሰራት የጦርና የጦር ወሬ መብዛት የርሀብ መከሰት የቸነፈር ብዛት (አዳዲስ ህመሞች መምጣት) ሕዝብ በሕዝብ ላይ መነሳት መንግሥት በመንግሥት ላይ መነሳት ብዙ ሰዎች ሃይማኖታቸውን መካድ የአመጻ መብዛት ከሰው ልብ ውስጥ የፍቅር መቀዝቀዝ ቅዱስ ወንጌል በዓለም መሰበክ ርኩሱ በቅዱሱ ስፍራ መቆም ደጋግ ሰዎች ለመከራ ተላልፈው መሰጠት መገረፍ መሞት እነዚህና የመሳሰሉት የምጽአቱ ምልክቶች ናቸው 2 የምጽአቱ መቅረብ ምሳሌ የበለስ መለምለም በለስ በክረምት አትለመልምም በበጋ ነው የምትለመልመው የበለስ መለምለም የክረምቱን ማለፍ የበጋውን መምጣት ወይም የመከሩን መድረስ ታስረዳለች የበለስ መለምለም የመከር መድረስ ምልክት እንደሆነ የምጥ ጣር መጀመሪያም ምጽአት እንደ ቀረበ ያስረዳል 3 የአመጣጡ ሁኔታዎች 1 እንደ መብረቅ መብረቅ በዝናም ጊዜ ሳይታሰብ እነደሚመጣ ሁሉ ክርስቶስም እንዲሁ ባልታሰበበት ሰአት ይመጣል 2 እንደ ሌባ ሌባ በሌሊት ባለቤቱ ባላሰበበት ባልጠበቀበት ሰአት ይመጣል የቤት ባለቤት ሌበው መቸ እንደሚመጣ ቢያወወቅ ተዘጋጂቶ ይጠብቅ ነበር ክርስቶስም መቸ እንደሚመጣ አይታወቅም ተዘጋጅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል 3 እንደ ኖህዘመን የጥፋት ውሃ የጥፋቱ ውሃ በኖህ ዘመን ለነበሩ ሰዎች ባላሰቡት ባልጠበቁት ሰዓት መጥቶ አጥፍቶቸውዋል ክርስቶስም ባልታሰበበት ሰአት መጥቶ ይህን ዓለም ያሳልፈዋል + የምጻቱ ፍጻሜ የፀሐይ መጨለም የጨረቃ ደም መሆን የከዋክብት መርገፍ (ማለፍ) ያንግዜ የሰው ልጅ ምልክቱ በሰማይ ይታያል ሰማይና ምድር ያልፋሉ ሙታን ይነሳሉ አውሬ የበላው ውሃ የወሰደው በጦር የሞተው በምንም ዓይነት ሞት የሞቱት ሁሉ ይነሳል ሴቶች እንደሄዋን 15 ዓመት ሁነው ወንዶቹ እንደ አዳም የ30 ዓመት ሁነው እንደ ዓይን ጥቅሻ እንደ ከንፈር ንክሻ ፈጥነው ይነሳሉ ምድር አደራዋን ትሰጣለች በነፋሳት እንደኳስ ትጠቀለላለች ከነበረችብት ወዳልነበረችበት ይወስዳታል የነፍስ ስራዋ ይገለጻል ኀጥአን በገራው ጻድቃን በቀኙ ይቆማሉ ስድስቱ ቃላተ ወንጌል ለመስክርነት በጥያቄ ይቀርባሉ ለጻድቃን ይፈርድላቸዋል የአባቴ ቡሩካን ወደእኔ ኑ ይላቸዋል ከጸሐይ ሰባት እንጅ አብርተው አምላካቸውን መስለው ወደ መንግሥተ ሰማያት ይሄሉ;; በኀጥአን ይፈረድባቸዋል ይፈርድባቸዋል እናንተ ርጉማን ሂዱ ይላቸዋል ከቁራ ሰባት እጅ ጠቁረው አለቃቸው ዲያብሎስን መስለው ወደ ገሃነም ይሄዳሉ ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን #ፅዮን ፍሬ 💚💛❤️✝💚💛❤️ 💚 @tsionfer 💚 💛 @tsionfer 💛 ❤️ @tsionfer ❤️ 💚💛❤️✝💚💛❤️

  • 8 мар.126из tsionfer

    ✍️...መፃጉ!! በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓጨድውያንን መፈወሱን ዕራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው «ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም» አለው:: «ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ» ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ «የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ» እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ «በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና «በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡ ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በዕለቱ በቅዳሴ ላይ የሚነበቡትም ምንባቦች የሚከተሉት ናቸው፡ 1ኛ. የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላትያ ሰዎች 5:1(26 2ኛ. የሐዋርያው የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት 5፡14-20 3ኛ. የሐዋርያት ሥራ 3፡1-12 እንዲሁም የዕለቱ ምስባክ ደግሞ በመዝሙር 4ዐቁጥር 3 ላይ የሚገኘው እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፡፡ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ፡፡ የሚለው ይሆናል፡፡የዕለቱ የወንጌል ንባብም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ከቁጥር 1 እስከ 25 ድረስ ያለው ነው፡፡ ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! #ፅዮን ፍሬ 💚💛❤️✝💚💛❤️ 💚 @tsionfer 💚 💛 @tsionfer 💛 ❤️ @tsionfer ❤️ 💚💛❤️✝💚💛❤️

  • 18 янв.166из tsionfer

    "እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!" 💚💛❤️ ከተራ ምን ማለት ነው❓ ✒️ በየዓመቱ የጥምቀት በዓል በድመቀት ይከበራል ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሀይማኖታዊ ገለፃ ከተራ 'ከበበ' ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ነው ፍቺው ውሀ መከተር 'መገደብ' ማለት ነው። የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሀ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል። የምንጮች ውሀ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውሀው እንዳይሄድ ይገደባል ከተራ በዓል በየዓመቱ በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ይውላል። የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ምዕመናን ሲወርድ ሲዋረድ ይዘው በመጡት ሀይማኔታዊና ባህላዊ እሴት መሰረት በጥምቀትን በዓል ዋዜማ ወንዝ ምንጭ ውሀው ይገደባል ይከተራል። ውሀው የሚከተረው በማግስቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው። ይህ በጥምቀት ዋዜማ የሚደረገው ውሀውን መከተርና መገደብ ስርአትም "ከተራ" የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ https://t.me/tsionfer

  • "በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ"መዝ ፱፥፲፩ 🌹 @tsionfer 🌹

  • ለውሃ አልመጣም፤ ወደ እኔ መጣ። He didn't come for the water, He came for me አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ልትቀዳ በመጣች ጊዜ ኢየሱስ “ውሃ አጠጭኝ?” አላት። ሳምራዊቷ ሴት “አንተ አይሁዳዊ ነህ፤ እኔ ደግሞ ሳምራዊት ሴት ነኝ። እንዴት መጠጥ ትለምነኛለህ?” አለችው። ኢየሱስም “የእግዚአብሔርን ስጦታና መጠጥ የሚለምንሽ ማን እንደሆነ ብታውቂ ኖሮ ትለምኚው ነበር፣ የሕይወትንም ውሃ ይሰጥሽ ነበር” አላት። (ዮሐንስ 4:7-10) ኢየሱስም “ይህንን ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ዳግመኛ ይጠማል፤ እኔ የምሰጠውን ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም። (ዮሐንስ 4:13-14) When a Samaritan woman came to draw water, Jesus said to her, “Will you give me a drink?” (His disciples had gone into the town to buy food.) The Samaritan woman said to him,“You are a Jew and I am a Samaritan woman. How can you ask me for a drink?”Jesus answered her, “If you knew the gift of God and who it is that asks you for a drink, you would have asked Him and He would have given you living water.” Jesus answered,“Everyone who drinks this water will be thirsty again, but whoever drinks the water I give them will never thirst. Indeed, the water I give them will become in them a spring of water welling up to eternal life.”  @tsionfer

  • ✨✨✨✨እንኳን አደረሳችሁ ✨✨✨✨ ‹‹ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ›› ቅዱስ ያሬድ በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕትና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት 29 ተጸንሶ ታኅሣሥ 29 (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ5,500 ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ…

  • ✨✨✨✨እንኳን አደረሳችሁ ✨✨✨✨ ‹‹ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ›› ቅዱስ ያሬድ በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕትና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት 29 ተጸንሶ ታኅሣሥ 29 (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ5,500 ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ መልአኩ መጥቶ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹እነሆ! ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ›› አላቸው፡፡ ሉቃ2፡10-12፡፡ ከመለአኩም ጋራ ሠራዊተ መላእክት መጥተው ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው /ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ/›› አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‹‹እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ፣ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ›› ተባባሉና ፈጥነው መጡ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ፡፡ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፤ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር አደነቁ፤ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡ ሉቃ 2፡13-19፡፡ ...

  • አገልግሎት ከእግዚአብሔር ጋር የመኖርን ጣዕም ከቀመሱ ቡሃላ ሌሎችም ቀምሰው እንዲወዱት መጥራት ማቅረብ ነው 🌹 @tsionfer 🌹         ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  • በብዙ መከራ እና ፈተና ዉስጥ ሆኖ እግዚአብሔር ያዉቃል ማለት ከብዙ መከራ እና ፈተና ይሰዉራል። ታሞ ነበር ዳነ አጥቶ ነበር አገኘ፣፣ አዝኖ ነበር ሳቀ እግዚአብሔርን ተማምኖ ነበር ድንቅ አደረገለት ለመባል ያብቃችሁ  በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!           🌹        @tsionfer          🌹         ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  • The heart itself is only a small vessel, yet dragons are there, and lions, there are poisonous beasts, and all the treasures of evil, there are rough and uneven roads, there are precipes; but there too is God and the angels, life is there, and the Kingdom, there too is light, and there the apostles and heavenly cities, and treasures of grace. All things lie within that little space. St. Macarius of Egypt ልብ ራሱ ትንሽ ዕቃ ብቻ ነው፣ ነገር ግን ዘንዶዎች እዚያ አሉ፣ አንበሶችም አሉ፣ መርዛማ አራዊት አሉ፣ የክፋትም ሀብት ሁሉ፣ ሻካራና ወጣ ገባ መንገዶች አሉ፣ ገደልም አለ፤ ነገር ግን እግዚአብሔርና መላእክትም እዚያ አሉ፣ ሕይወትም እዚያ አለ፣ መንግሥትም እዚያ አለ፣ ብርሃንም እዚያ አለ፣ ሐዋርያትና ሰማያዊ ከተሞች፣ የጸጋም ሀብትም እዚያ አለ። ሁሉም ነገር በዚያ ትንሽ ቦታ ውስጥ ይገኛል። የግብፅ ቅዱስ መቃርዮስ          🌹     @tsionfer         🌹      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  • ደግመህ ሀጢአት ብትሰራም ደግመህ ንስሐ ግባ! ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሄር በምሕረቱ ባለፀጋ ነው @tsionfer

  • 31 дек.110из tsionfer

    ታህሳስ ❷❷ ብስራተ ገብርኤል °°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ይህ ቀን እመቤታችን ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ ታላቁን የብስራት ዜና ቅዱስ ገብርኤል የነገረበት ቀን ነው። ብስራተ ገብርኤል መጋቢት ❷❾ ቀን አይደለምን ቢሉ ? አዎ መጋቢት 29 ቀን በእለተ እሁድ ከጠዋቱ በ 3 ሰአት ላይ ነው። ታዲያ ለምን በዛሬው ቀን እናከብረዋለን ለሚሉ መጋቢት ወር ምን ግዜም የጌታችን መድኃኒታችን የ ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቁ አብይ ፆም ነው። በዚህ የፆም ወቅት ደግሞ የሀዘን የለቅሶ የእንባ ወቅት ነው የጌታችን ህማም መከራ እያሰብን የምንከርምባት ወር ናት በመሆኑም ደስታ ፌስታ በዚህ ወቅት የለም ታቦት አይወጣም በአጠቃላይ የንግስ በዓላቶ የተከለከሉ ናቸው። አከባበሩንም ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን እና አባቶቻችን በዚህ መልኩ አስቀምጠውታል። የመጋቢት 29 ቀን ስቅለቱ በጥቅምት 27 እንዲከበር የመጋበት 5 እረፍቱ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በጥቅምት 5 ቀን እንዲከበር የመጋቢት 10 የመስቀል በዓል በመስከረም 17 ቀን እንዲከበር አድርጋለች። እንዲሁም ታለቁ አባት ደቅስዮስ መጋቢት 29 ቀን የሚከበረውን ብስራተ ገብርኤል ወደ ታህሳስ 22 ቀን ዞሮ እንዲከበር አድርጓል ። መልዐኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በ እግዚአብሔር ፊት ፀጋን አግኝተሻልና አትፍሪ ። እንሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ ሉቃ 1 : 30-31 እንኳን አደረሳችሁ !!! አደረሰን የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ ፍቅሯ ይደርብን ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ @tsionfer @tsionfer @tsionfer

  • እግዚአብሔር አስበው"። ጠላቶቹንም ድል አድርጎ በሰላም ተመለሰ መልአኩም ዳግመኛ ተገልጦለት "ለምን ፈጣሪህን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ረሳህ" አለው።ጦርነቱም ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ ቅዱስ መርቆሬዎስም ለበዓል ማክበር አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ ሰዎችም ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳልመጣና ዕጣንን በማሳረግም እንዳልተባባረ አስረዱት። + ከዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጣው በመዘግየቱም አድንቅ "ለአማልክት ዕጣን ለማድረግ ከእኔ ጋር ያልወጣህ የእኔን ፍቅር እንዴት ተውህ" አለው። በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው "እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም"። ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፋት ዘንድ አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉበት። + በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት ፈርቶ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠርያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘው ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ። የማይጠፋ ሰማያዊ አክሊልንም ተቀዳጅቶ ወደ ዘላለም ሕይወት ከገባ በኋላ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነፁለት እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን በውስጣቸው ገለጠ። + ከተአምራቱም አንዲቱ ዑልያኖስ በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ካደ በዚያንም ወራት ቅዱስ ባስልዮስ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ነበረ ተአምራቱ በተጻፈበት መጽሐፍ እንደተጻፈ ምእመናን በጽኑዕ ሥቃይ ዑልያኖስ ባሠቃየ ጊዜ መክሮ አስተምሮ ከስሕተቱ ይመልሰው ዘንድ ቅዱስ ባስልዮስ ወደርሱ መጣ። + ዑልያኖስም ቅዱስ ባስልዮስን በአየው ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ሰደበ ቅዱስ ባስልዮስንም አሠረው በዚያ በእስር ቤትም የቅዱስ መርቆሬዎስን ሥዕል አይቶ በፊቱ ቅዱስ ባስልዮስ ጸለየ ሥዕሉም ከቦታው ታጣ። ያን ጊዜ ወደ ዑልያኖሰሰ ሒዷልና በጦርም ወግቶ ገደለውና ወዲያውኑ ወደቦታው ተመለሰ ከጦሩም አንደበት ደም ይንጠፈጠፍ ነበር። ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን እንደገደለው አውቆ እንዲህ ብሎ ተናገረ "የክርስቶስ ምስክር ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?" ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ሥዕሉ ራሱን ዘንበለሰ አደረገ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔር አመሰገነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ገድለ መርቆሬዎስና የኅዳር25 ስንክሳር። @tsionfer @tsionfer @tsionfer

  • +++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።       + ኅዳር25 ቀን + እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ለቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስላሞች ወገን ከነበረ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተአምር አድርጎ ከመለሰው ከቅዱስ ዮሐንስ፣ ከአቃርዎስና ከሮማኖስ ከመታሰቢያቸወ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                  +++ + ቅዱስ መርቆሬዎስ፦ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው። በሁለተኛ ትርጓሜ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው። ይህም ቅዱስ አስሊጥ ከምትባል አገር ነው እርሷም የአባቱና የአያቱ አገር ናት እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው። + የአባቱና የአያቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ነበር በአንዲት ዕለትም እንደልማዳቸው ለማደን ወጡ ከገጸ ከለባት ወገንም ሁለት ወንዶች ተገናኙአቸውና የቅዱስ መርቆሬዎስን አያት ስዲሮስ በሉት። ሁለተኛም አባቱን አሮስን ሊበሉት ፈለጉ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ከለከላቸው "ከእርሱ የሚወጣ መልካም ፍሬ ስለ አለ አትንኩት" አላቸው። + ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ዙሪያቸውን በእሳት ከበባቸው በተቸገሩ ጊዜም ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ አባት አሮስ መጥተው ሰገዱለት በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደ በጎች የዋሆች ሆኑ አብረውትም ወደ መንደር ገቡ። + ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለው ጠሩት የውሻ መልክ ያላቸው በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት የሚኖሩ ሆኑ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ የቅዱስ መርቆሬዎስ ወላጆች አስቀድሞ አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትንም ጸጋ በተቀበሩ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ኖኅ ብለው ሰየሙት እናቱንም ታቦት አሏት ፒሉፓዴርንም መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት። የውሻ መልክ ያላቸው ግን የእግዚአብሔር መልአክ በተገለጸላቸው ጊዜ እንደ ነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ። + ንጉሡም የኖኅንና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀረባቸው በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር በንጉሡ ፊት የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው የንጉሡ ያቀረባቸውን ሁሉንም አራዊት አጠፏቸው። ንጉሡም ይህን በአየ ጊዜ እጅግ ፈራ የአራዊትንም ተፈጥሮአቸውን ያርቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ለመነው። እርሱም በለመነ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ። + ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ንጉሡ ወስዶ ገዥና የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው የውሻ አርያ ያላቸውም ይታዘዙለት ነበር ከእርሳቸውም የተነሣ ሁሉም ይፈሩ ነበር። ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የሾመውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ከሀዲ ንጉሥ ተነሣ ንጉሡም ከጦር አባት ወደ ጦርነት ላከው። ከሀዲው ንጉሥ ግን እነዚያን የውሻ አርያ ያላቸውን አባብለውና ሸንግለው ወደርሱ የመጧቸው ዘንድ ወታደሮችን ላከ በአመጧቸውም ጊዜ ሃይማኖታቸውን ይለውጡ ዘንድ አብዝቶ ሸነገላቸው ባልሰሙትም ጊዜ ሊአሠቃያቸው ጀመረ አንዱ አምልጦ ሸሽቶ ወደ ጌታው ሔደ ሁለተኛውም በሰማዕትነት ሞተ። + ከጦር ሜዳ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት በመለሰ ጊዜ ሚስቱንና ልጁን ፈለጋቸው ግን አላገኛቸውም ንጉሡ የሱ ወገኖች ድል እንደሆኑ በሰማ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መኰንኑ የሞተ መስሎት ነበርና የቅዱስ መርቆሬዎስን እናት ወስዶ ሊአገባት ፈለገ ከንጉሥ ወታደሮችም አንዱ ንጉሡ ያሰበውን በጽሞና ነገራት። እርሷም ይህንኑ ወታደር ከአገር ውስጥ በሥውር ያወጣት ዘንድ ለመነችውና ከልጇ ከብፁዕ መርቆሬዎስ ጋር ወጥታ ወደ ሌላ አገር ሔደች። ንጉሡም ከእርሱ የሆነውን የመኰንኑም የመርቆሬዎስን አባት ሚስቱን ለማግባት ማሰቡን እንዳይነግሩት አዘዘ የውሻ መልክኮች ያላቸው ከእርሱ ጋር እንዳሉ የተቆጣም እንደሆነ እንደሚአመጣቸውና አገሮችን ያጠፋሉ ብሎ ይጠራጠራልና ስለዚህ እጅግ ይፈራዋል። + ከዚህም በኋላ ደግሞ በንጉሡ ላይ ጦርነት ተነሣ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት ወደ ጦርነት ወጣ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ይዘው ማረኩት ወደ ሮሜውም ንጉሥ አቀረቡት ንጉሡም ክርስቲያን ነበርና የተማረከው መኰንን ክርስቲያን መሆኑን በአወቀ ጊዜ አልገደለውም በክብር አኖረው እንጂ እጅግም ወደደውና ከጥቂት ቀኖች በኋላ በመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ላይ ገዥ አድርጎ ሾመው። + ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ሚስቱና ልጁ መርቆሬዎስ ወዳሉበት አገር ደረሰ ሚስቱም በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ በአየችው ጊዜ ባሏ እንደሆነ አወቀችው እርሱ ግን አላወቃትም በአንዲትም ዕለት እርሱና ጭፍሮቹ ከእንግዳ ማረፊያ ቤት በወጡ ጊዜ ልጅዋን መርቆሬዎስን ወስዳ ያማሩ ልብሶችን አልብሳ ሒዶ ከመኰንኑ ፈረስ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘችው እርሱም አባቱ ነው በተቀመጠም ጊዜም ጭፍሮች ይዘው ወደ መኰንኑ ፊት አቀረቡት መኰንኑም ልጁ እንደሆነ አላወቀምና በእርሱ ላይ ተቆጣ። + የመርቆሬዎስ እናት መጥታ "ጌታዬ ሆይ እኛ መጻተኞች ነን አንተም መጻተኛ እንደሆንክ በአወቅሁ ጊዜ ልጅህ ሁኖ ልጄ ከአንተ ጋር እንዲሆን አሰብኩ" አለችው። እርሱም ጠየቃት እንዴት እንደተሰደደችም መረመራት እርሷም ሚስቱ እንደሆች ነገረችው በዚያንም ጊዜ አወቃት ልጁን መርቆሬዎስንም አወቀው አጅግም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔር አመሰገኑት ያንንም የእንግዳ ማረፊያ ቤት ቤተ ክርስቲያን አደረጉት እግዚአብሔርም እያመሰገኑ በአንድነት ኖሩ። + ከዚህም በኋላ አባቱና እናቱ በሞቱ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዶ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው ቅዱስ መርቆሬዎስም መኰንንነትን በተሾመ ጊዜ ያ ገጸ ከልቡ ከርሱ ጋር ነበር ወደ ጦርነትም አብሮት የሚወጣ ሆነ። ለመዋጋትም በሚሻ ጊዜ የቀድሞ የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ነበር ማንም ሊቋቋመው የሚችል የለም። ለቅዱስ መርቆሬዎስም ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠው ዜናውም በሁሉ ቦታ ተሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችም ከፍ ከፍ አለ። + እንዲህም ሆነ ያን ጊዜ በዚያን ወራት በሮሜ አገር ጣዖትን የሚያመልክ ዳኬዎስ የሚባል ንጉሥ አለ። ጠላቶቹም የበርበር ሰዎች ተነሡበት እርሱም ከእርሳቸው ጋር ሊዋጋ ሠራዊቱን ሰብስቦ ወጣ እነርሱ ግን እንደ ባሕር አሸዋ ብዙ ነበሩ ብዛታቸውንም በአየ ጊዜ ደንግጦ እጅግ ፈራ ቅዱስ መርቆሬዎስም "እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ በእጃችንም አሳልፎ ሊሰጣቸው አለውና አትፍራ" አለው። + ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ የእግዚአብሔርን መልአክ በውጊያው ውስጥ አየው የተሳለ ሰይፍም በእጁ ውስጥ አለ ያቺንም ሰይፍ ሰጠውና እንዲህ አለው "ጠላቶችህን ድል በአደረግህ ጊዜ ፈጣሪህ

  • 3 дек.131из tsionfer

    መርቆርዮስ መርቆርዮስ /2/ የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ ባስልዮስ ጎርጎርዮስ ሰምሯል ልመናቸሁ ስዕሉ ዘለለ ታማራት አያችሁ እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆርዮስ /አዝ ===== ኡልያኖስ ተገድሏል አይማኖት ይስፋፋል ብሎ መሰከረ መርቆርዮስ ሀያል ገፀ ከለባቱ ባህርይ ቀየሩ እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ /አዝ ===== ትካዜ አዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ መርቆርዮስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ /አዝ ===== ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዮስ ወደደ ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ በጋለ ሹል ብረት መርቆርዮስ ተወጋ ስሙ ተሰየመ ከሰማዕታት ጋራ /አዝ===== አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር መፍቀሬ አብካለ ያፕሎፓዴር ቄሳርያ እስርቤት መርቆርዮስ ታሰረ ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ ዘማሪ ዲ/ን ታዲዎስ ግርማ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮ ✥        💚 @tsionfer  💚  ✥   ✥        💛 @tsionfer 💛      ✥ ✥        ❤️ @tsionfer❤️      ✥ ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╯    ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  • #የናቁሽ_ሁሉ የናቁሽ ሁሉ ወደእግሮችሽ ጫማ ይሰግዳሉ የካዱሽ ሁሉ ይፀፀታሉ እኛ ግን አንቺን እናከብራለን}2 እናታችነን ፅዮን አንልሻለን} እናቴ እመቤቴ እኔም እልሻለው ጌታዬ ባደራ የሰጠኝ አንቺን ነው ከእግረ መስቀሉ ስር አንቺን አጊኝቻለው ትውልድ ነኝና ብፅዕት እልሻለው በድል ነሺዎች ዘንድ በፃድቃን ሰማዕታት በቅዱሳኑ ና በትጉሃን መላዕክት የሰለጠነ ነው ስምሽ በእግዚአብሔር ዘንድ በፍጥረታት ሁሉ እጅግ የሚወደድ እናቴ ማርያም ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ ያልሽኝን እንዳልፈፅም የሚከለክለኝ ብሏልና ልጅሽ በቤተ ዶኪማስ ለምኝልን ድንግል እንባችን ይታበስ የጌድዮን ፀምር ዳግማዊቷ ሰማይ ሕይወትን ያስገኘሽ ወላዲተ ፀሐይ የሕወትን መና ያገኘነው እኛ ካንቺ ተወልዶ ነው የአለሙ እረኛ ዘማሪት መብራት ድርብሣ (አብ-ሳላት) @tsionfer @tsionfer @tsionfer

  • 29 нояб.151из tsionfer

    ​​እንኳን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ "ጽዮን ማርያም" "ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል:: እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች:: ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን:: ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም:: ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው:: "ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19) #በመጨረሻም_ኅዳር_21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:- 1. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19) 2. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1) 3. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል:: "ሰላም ለኪ ማርያም እምነ:: ዘሰመይናኪ ጸወነ:: ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ:: ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ:: ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21) 4. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1) 5. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል:: 6. በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል:: 7. በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል:: 8. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው:: " አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን " "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና:: ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና:: #እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው:: 1. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት:: "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም) 2. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: ¤ "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ¤ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) 3. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና:: 4. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና:: @tsionfer @tsionfer @tsionfer

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

ጽዮን ፍሬ ዘሰንዳፋ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር እና መዝሙር ማጥኛ — tgindex