tgindex
°°ቪኪ ድርሰቶች°°

°°ቪኪ ድርሰቶች°°

Статистика

ምርጥ ምርጥ ታሪክ ያላቸውን ድርሰቶች ይቀርባሉ።እናንተም ተቀላቀሉን እና አዳዲስ ታሪኮችን ያንብቡ፤ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛዎ በማጋራት ትብብር አድርጉልን🙏🙏

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
335
+3 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
228
20 постов
Вовлечённость
68,1%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 23
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
86
1/48двое суток
98
1/72трое суток
106

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ክፍል አስራ ሶስት ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ እህቷ ግን አሁንም በቁጣ እየተንፈረፈረች ነበር። እኔ ደግሞ ጠረጴዛው ላይ የተተወውን ፖስታ እያየሁ ነበር። ምክንያቱም ያ ፖስታ... የሁላችንንም ሕይወት የሚቀይር ሚስጥር የያዘ መስሎ ተሰምቶኛል...      በዚህ  ሁኔታ እያለን ሳለ ስልኬ ጠራ አብዱ ነበር ዝምም አልኩና ጥሪው እስኪያልቅ ጠብቄው ስልኬን ልዘጋው ስል 25 ያልተሳ ጥሪ አየሁ በአላህ አስደነገጠኝ በብዛት የደወሉት የሱፍ...እና...አብዱ ሲሆኑ ሁለቴ ደሞ እናቴ ደውላለች      ምን ተፈጥሮ ይሆን ብዬ ሽንት ቤት እንደሚሄድ ሰው ጓሮ ሄጄ ከቤቱ ጀርባ በቅድሚያ ለአብዱ ደወልኩ     ወድያው ስልኩ ከመጥራቱ አነሳልኝ አብዱ...አንተ አዉዙ ቢላህ ምን ሆነህ ነው ሞተህ ነበር? እኔ...እየቀለድኩ አው አላህ ወስዶ መለሰኝ አብዱ...አንተ አቀልድ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ እኮ ልለጥፍ ነበር እኔ...ኸረ መስጊድ ላይ የተለጠፈው ይበቃል አብዱ...አሁን የት ሆነህ ነው እኔ...የሆነ ቦታ ነግርሀለሁ ብዬህ የለ...ምን ያንገበግብሀል አብዱ...እየቀለድኩ አይደለም የመስጊዱ ኢማም ሼህ ሙኸዲን በጣም እየፈለጉህ ነው እኔ...እንዴ ለምን? አብዱ...አላውቅም ምን ሰርተህ እንደሄድክ አላህ ይወቀው ለብዙ ሰው ተናግረዋል አንተን ያየ ሰው እንዲጠቁማቸው እኔ...እንዴ ይህን ያህል አብዱ...አው ነገሮች እየከፉ ነው መተህ በስርዓቱ አናግራቸው እኔ...በተደናገጠ በቀላው  አይኔ ቀና ስል በመኝታቤቱ መስታወት በኩል የአብሱ እህት ስታየኝ አየኋት ና    ...እሺ በቃ እደውልሀለሁ አሁን መሄድ አለብኝ አብዱ....ቻው....ቻው! ብዬ ፈጥኜ ዘጋሁት እና...      መታጠብያው ጋ ሄጄ አውቄ እንደታጠበ ሰው እጆቼን ውሀ አስነክቼ እያራገፍኩ ገባሁ... በሩ መለስ አርጌ ገባሁና ተቀመጥኩ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ማንም አልተናገረም። የቤቱ ፀጥታ ከቀድሞው በላይ ከባድ ሆኖ ተሰማኝ። አብሱ ዓይኗን ከፖስታው ላይ እስካሁን  ማንሳት  አልቻለችም። እህቷ ግን አሁንም በንዴት እየተንፈረፈረች ነበር አንድም በኔ ነው መሰል እንዴት እንደምታየኝ። እህቷ..."ይሄን እንኳን እንዳታነቢው!" አለች ፖስታውን እያመለከተች። "እንዴት ያልታወቀች ሰው መጥታ የፈለገችውን ተናግራ ትሄዳለች?" አብሱ ግን... ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ፖስታውን ወደ እጇ አነሳችው። "እኔ ማወቅ እፈልጋለሁ..." አለች በቀስታ። "ምኑን?" አለች እህቷ። "እውነቱን።" እህቷ በንዴት እየተነሳች። "እውነት? ከሀያ ዓመት በኋላ የመጣ እውነት ምን ይጠቅመናል?" አብሱ ምንም ሳትል እጆችዋ አየተንቀጠቀጡ ፖስታውን ከፈተችው። በውስጡ ያለውን ወረቀት እያወጣች ሳለ አንድ ትንሽ ፎቶግራፍ ከወረቀቱ መሀል ወድቆ መሬት ላይ ተንሸራተተ። እኔ አንስቼ ተመለከትኩት። በፎቶው ላይ አንድ ወጣት ወንድ እና አንዲት ወጣት ሴት ቆመው ነበር። ወንዱን ወዲያው አወቅሁት። የአብሱ አባት ነበር። ነገር ግን ከጎኑ ያለችው ሴት... ዛሬ መጥታ የሄደችው እሷ ነበረች። አብሱ ፎቶውን እንዳየች ትንፋሿ እየተዋጠ። ከዚያም ወረቀቱን ከፈተች። በላዩ ላይ የተፃፈውን የመጀመሪያ መስመር እንዳነበበች ዓይኖቿ ተከፈቱ። "ለልጆቼ..." ብላ በቀስታ አነበበች። ያ ደብዳቤ... የሟቹ አባቷ የመጨረሻ መልእክት ነበር። ይሄ ፖስት 15❤️ ካገኘ....  🤗 .........ይቀጥላል.........             @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • አንዳንድ ፍቅር... አንዳንድ ፍቅር አለ    ላለመጥፋት እየታገለ፤   የመውደድ ልኬት         የፍቅር ስሌት፤ ሳይኖራቸው      የተፋቀሩ — ስንት አሉ... ፍቅር እየተሰጣጡ፣ ነፍስ እየተለዋወጡ፤ ለዘላለም       የሚኖሩ። ስንት አሉ.....      @Rufaylen13 💫            ✍️ ህላዌ💕

  • без подписи

  • 11 авг.1186из poem_Hiwe

    ያልታመመው ሞተ🙂‍↕️

  • 11 авг.12691из poem_Hiwe

    ክፍል አስራ ሶስት ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ እህቷ ግን አሁንም በቁጣ እየተንፈረፈረች ነበር። እኔ ደግሞ ጠረጴዛው ላይ የተተወውን ፖስታ እያየሁ ነበር። ምክንያቱም ያ ፖስታ... የሁላችንንም ሕይወት የሚቀይር ሚስጥር የያዘ መስሎ ተሰምቶኛል...      በዚህ  ሁኔታ እያለን ሳለ ስልኬ ጠራ አብዱ ነበር ዝምም አልኩና ጥሪው እስኪያልቅ ጠብቄው ስልኬን ልዘጋው ስል 25 ያልተሳ ጥሪ አየሁ በአላህ አስደነገጠኝ በብዛት የደወሉት የሱፍ...እና...አብዱ ሲሆኑ ሁለቴ ደሞ እናቴ ደውላለች      ምን ተፈጥሮ ይሆን ብዬ ሽንት ቤት እንደሚሄድ ሰው ጓሮ ሄጄ ከቤቱ ጀርባ በቅድሚያ ለአብዱ ደወልኩ     ወድያው ስልኩ ከመጥራቱ አነሳልኝ አብዱ...አንተ አዉዙ ቢላህ ምን ሆነህ ነው ሞተህ ነበር? እኔ...እየቀለድኩ አው አላህ ወስዶ መለሰኝ አብዱ...አንተ አቀልድ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ እኮ ልለጥፍ ነበር እኔ...ኸረ መስጊድ ላይ የተለጠፈው ይበቃል አብዱ...አሁን የት ሆነህ ነው እኔ...የሆነ ቦታ ነግርሀለሁ ብዬህ የለ...ምን ያንገበግብሀል አብዱ...እየቀለድኩ አይደለም የመስጊዱ ኢማም ሼህ ሙኸዲን በጣም እየፈለጉህ ነው እኔ...እንዴ ለምን? አብዱ...አላውቅም ምን ሰርተህ እንደሄድክ አላህ ይወቀው ለብዙ ሰው ተናግረዋል አንተን ያየ ሰው እንዲጠቁማቸው እኔ...እንዴ ይህን ያህል አብዱ...አው ነገሮች እየከፉ ነው መተህ በስርዓቱ አናግራቸው እኔ...በተደናገጠ በቀላው  አይኔ ቀና ስል በመኝታቤቱ መስታወት በኩል የአብሱ እህት ስታየኝ አየኋት ና    ...እሺ በቃ እደውልሀለሁ አሁን መሄድ አለብኝ አብዱ....ቻው....ቻው! ብዬ ፈጥኜ ዘጋሁት እና...      መታጠብያው ጋ ሄጄ አውቄ እንደታጠበ ሰው እጆቼን ውሀ አስነክቼ እያራገፍኩ ገባሁ... በሩ መለስ አርጌ ገባሁና ተቀመጥኩ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ማንም አልተናገረም። የቤቱ ፀጥታ ከቀድሞው በላይ ከባድ ሆኖ ተሰማኝ። አብሱ ዓይኗን ከፖስታው ላይ እስካሁን  ማንሳት  አልቻለችም። እህቷ ግን አሁንም በንዴት እየተንፈረፈረች ነበር አንድም በኔ ነው መሰል እንዴት እንደምታየኝ። እህቷ..."ይሄን እንኳን እንዳታነቢው!" አለች ፖስታውን እያመለከተች። "እንዴት ያልታወቀች ሰው መጥታ የፈለገችውን ተናግራ ትሄዳለች?" አብሱ ግን... ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ፖስታውን ወደ እጇ አነሳችው። "እኔ ማወቅ እፈልጋለሁ..." አለች በቀስታ። "ምኑን?" አለች እህቷ። "እውነቱን።" እህቷ በንዴት እየተነሳች። "እውነት? ከሀያ ዓመት በኋላ የመጣ እውነት ምን ይጠቅመናል?" አብሱ ምንም ሳትል እጆችዋ አየተንቀጠቀጡ ፖስታውን ከፈተችው። በውስጡ ያለውን ወረቀት እያወጣች ሳለ አንድ ትንሽ ፎቶግራፍ ከወረቀቱ መሀል ወድቆ መሬት ላይ ተንሸራተተ። እኔ አንስቼ ተመለከትኩት። በፎቶው ላይ አንድ ወጣት ወንድ እና አንዲት ወጣት ሴት ቆመው ነበር። ወንዱን ወዲያው አወቅሁት። የአብሱ አባት ነበር። ነገር ግን ከጎኑ ያለችው ሴት... ዛሬ መጥታ የሄደችው እሷ ነበረች። አብሱ ፎቶውን እንዳየች ትንፋሿ እየተዋጠ። ከዚያም ወረቀቱን ከፈተች። በላዩ ላይ የተፃፈውን የመጀመሪያ መስመር እንዳነበበች ዓይኖቿ ተከፈቱ። "ለልጆቼ..." ብላ በቀስታ አነበበች። ያ ደብዳቤ... የሟቹ አባቷ የመጨረሻ መልእክት ነበር። ይሄ ፖስት 15❤️ ካገኘ....  🤗 .........ይቀጥላል.........             @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • 7 авг.194112из poem_Hiwe

    ክፍል አስራ ሁለት ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ "ምን?!" ብለን በአንድ ድምፅ ጮህን። አብሱ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳች። "ታዲያ ማን ነሽ?" ሴትየዋ እንባዋን እየጠረገች... "እኔ.....እ          ከብዙ ዓመታት በፊት የአባታችሁ ''ሚስት'' ነበርኩ።   የሴትየዋ ቃል ከተሰማ በኋላ ለጥቂት ሰከንዶች ማንም አልተናገረም። አብሱ በድንጋጤ ቆማ... "ይሄ እንዴት ይሆናል?" አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ። "እናቴ ብቻ ናት የአባቴ ሚስት ብዬ የማውቀው።" ሴትየዋ ለመነጋገር እራስዋን እያዘጋጀች "እናታችሁን ከማግባቱ በፊት ... እኔና አባታችሁ ለአጭር ጊዜ ተጋብተን ነበር። ከዚያ ግን ተለያየን።" እህቷ... ወዲያው ጠየቀቻት... "ታዲያ ለምን እስከ ዛሬ ዝም አልሽ?" ሴትየዋ አንገቷን ደፋች። "ምክንያቱም ይህህ  ደብዳቤ ።" ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረ። አብሱም በጥሞና ታዳምጣት ነበር። "ምን ማለትሽ ነው?" አለች ያቺ አረፍተ ነገር እንደ መብረቅ በቤቱ ውስጥ ወደቀ። አብሱ በድንጋጤ ከቆመችበት ወደ ኋላ አፈገፈገች። "ምን አልሽ?" አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ። ሴትየዋ እንባዋን እየጠረገች ዝም ብላ... "እውነት ነው... ከብዙ ዓመታት በፊት እኔና አባታችሁ—" "ዝም በይ!" እህቷ በንዴት ጮኸችባት። "አንድ ደቂቃ ! ቀብር ላይ መጥተሽ የአባታችን እህት ነኝ አልሽ፤ አሁን ደግሞ ሚስቱ ነበርኩ ትያለሽ! ቀጥሎ ምን ልትይ ነው?" ሴትየዋ... ለመናገር ሞከረች። ..."እባክሽ አዳምጪኝ..." እህቷ..."አላዳምጥሽም!" አለች በቁጣ። አብሱም... በሀዘንና በድንጋጤ መካከል ተወጥራ... "እንዴት እናምንሻለን?" አለች። "እስከ ዛሬ የት ነበርሽ? አባቴ ሲታመም? ሲቸገር? እኛ ስናድግ?" ሴትየዋ አንገቷን ደፋች። "እኔም ስቃይ ነበረብኝ..." እህቷ.."እኛስ?"   አለች እህቷ በቁጣ      እየተንቀጠቀጠች። "እኛ ስንቸገር የት ነበርሽ? አሁን ደግሞ ከሞተ በኋላ...  ?" ክፍሉ በውጥረት ተሞላ። እኔ... ጣልቃ ልግባ አልፈለኩም፤ ነገር ግን ሁኔታው እየከፋ ነበር። ሴትየዋ... እንባዋን አፈሰሰች። "እውነቱን ለመናገር መጥቻለሁ ብቻ..." "አይ!" በንዴት በሩን አመለከተች። "እኛ አሁን እውነትም ሆነ ውሸት መስማት አንፈልግም። ከቤታችን ውጪ!" "እባክሽ—" "ከቤታችን ውጪ አልኩሽ!" አለች በጩኸት። አብሱ... ምንም ባትናገርም ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው ነበር። ሴትየዋ... አብሱን ተመለከተች። "ልጄ..." ብላ ስትናገር አብሱ ወዲያው ፊቷን አዞረች። ያኔ ሴትየዋ ምንም ሳትናገር ፖስታውን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች። "አንድ ቀን እውነቱን ማወቅ ከፈለጋችሁ... በውስጡ ሁሉም ነገር ተጽፎበታል።" ብላ በዝግታ ወደ በሩ አመራች። እህቷ በቁጣ ቆማ እያየቻት ነበር። ሴትየዋ ደጃፉ ላይ ደርሳ ለመጨረሻ ጊዜ ዞር ብላ አብሱን ተመለከተች። "ይቅርታ..." ብቻ አለቻት ። ከዚያም ወጥታ ሄደች። በሩ እንደተዘጋ ክፍሉ በከባድ ፀጥታ ተዋጠ። አብሱ ዝም ብላ ፖስታውን ትመለከት ነበር እህቷ ግን አሁንም በቁጣ እየተንፈረፈረች ነበር። እኔ ደግሞ ጠረጴዛው ላይ የተተወውን ፖስታ እያየሁ ነበር። ምክንያቱም ያ ፖስታ... የሁላችንንም ሕይወት የሚቀይር ሚስጥር የያዘ መስሎ ተሰምቶኛል...          .........ይቀጥላል.........            @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • 6 авг.1777из poem_Hiwe

    አላወቁም...እንጂ...😞💔

  • ውዶቼ ፍቅር ወይንስ እምነትን እያነበባቹ ነው?💖 ለሀሳብ... አስተያየት...      @Rufaylen13 💫             ✍️ ህላዌ💕

  • 5 авг.234101из poem_Hiwe

    ክፍል አስራ አንድ ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ የውጭው በር በሀይል ተንኳኳ። የበሩ ድምፅ በቤቱ ውስጥ የነበረውን ፀጥታ ሰብሮ አለፈ። እኔ፣ አብሱ እና እህቷ በአንድ ጊዜ ወደ በሩ ዞር ብለን ተመለከትን። እህቷ ቀስ ብላ ተነሳች። "በዚህ ሰዓት ማን ይሆን?" ብላ እያጉረመረመች ወደ በሩ ሄደች። በሩን እንደከፈተች ግን በድንጋጤ ወደ ኋላ አፈገፈገች። "እንዴት መጣሽ አለቻት?!"  በመደነቅ። እኔም ተነስቼ ወደ ደጃፉ ተመለከትኩ። የቆመችው ሴት በቀብሩ ቀን የተመለከትናት ሰው ነበረች። ራሷን "የአባታችሁ እህት ነኝ" ብላ ያስተዋወቀችው ሴት ናት።     (.... ስለሷ ባለፎ አልነገርኳቹም አይደል አብሱ ልክ ከሀኪም ቤት እነደገባች ከአክስትየዋ ጋ ከብዙ ሰአት ጭቅጭቅ በኋላ ባይስማሙም አብሱ የአባቷ ቀብር ከተፈፀመ በኋላ ሶስት ቀን ቆይታ ተጣልተው ከቤት ወጣች እንደውም የሆነ ስልክ ተደውሎላት በምክንያት ከሄደች በኋላጨዛሬ ድጋሚ ስትመጣ ነው...) ያው የተጣሉበትን ጉዳይ በግልፅ ባላቅም ከዚህ ጊዜ በኋላ  ለምን ሲሞት ጠብቀሽ መጣሽ በሚል ነው... ...አብሱ እንዳየቻት ፊቷ ተቀየረ። አብሱ..."አሁንስ ምን ፈልገሽ መጣሽ?" አለቻት በቁጣ የተሞላ ድምፅ። አክስትየዋ ግን የአብሱን ቁጣ እንዳልሰማ ዝም እቤቱ ውስጥ ሰተት ብላ ሶፋው ላይ ተቀመጠች። ዓይኖቿ ቀይ ሆነው ይታዩ ነበር። አክስትየው..."ይቅርታ... መምጣት አልፈለኩም ነበር። ግን የግድ መምጣት ነበረብኝ።" አለች በተሰበረ ድምፅ። እህቷ እጆቿን አጣጥፋ፣    ..."ምን ማለት ነው?" ብላ ጠየቀቻት። አክስትየዋ...ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ አሮጌ ፖስታ አወጣችና። "ይህን ከመሞቱ በፊት አባታችሁ ተሰጥቶኝ ነበር።" አለች። አብሱ ፖስታውን እያየች ቀረች። አብሱ..."ከአባቴ?" አክስት..."አዎ።" አብሱ..."ለምን እስከ አሁን ደበቅሽው?" አክስት... ትንፋሽ አወጣች። "ምክንያቱም የነገረኝ ጊዜው ሲደርስ ብቻ እንድሰጣችሁ ነበር።" ክፍሉ በድንገት ፀጥ አለ። አብሱ በሚንቀጠቀጡ እጆች ፖስታውን ከፈተችው... ውስጡ የታጠፈ ወረቀት እና አሮጌ ፎቶግራፍ ነበር። ፎቶውን እንዳየች ዓይኖቿ ተከፈቱ። "ይሄ... አባዬ ነው!" አለች በድንጋጤ። እህቷም ፎቶውን ተመለከተች። ነገር ግን ከአባታቸው አጠገብ የቆሙትን ሁለት ልጆች አላወቀቻቸውም። "እነዚህ እነማን ናቸው?" አለች በፍጥነት። ሴትየዋ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለች። ከዚያም የሚከብዳትን ነገር ልታወጣ እንደምትሞክር አወኩ። "እውነቱን ለመናገር ከባድ ነው..." አለች። "ግን ከእንግዲህ መደበቅ አልችልም።" እኔም ሆንኩ አብሱና እህቷ በጥሞና እየተመለከትናት ነበር። "እኔ የአባታችሁ እህት አይደለሁም..." አለች ቀስ ብላ። የተናገረችው ቃል እንደ መብረቅ በቤቱ ውስጥ ወደቀ። "ምን?!" ብለን በአንድ ድምፅ ጮህን። አብሱ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳች። "ታዲያ ማን ነሽ?" አክስትየዋ እንባዋን እየጠረገች... "እኔ.....እ .........ይቀጥላል......... @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • 5 авг.1975из poem_Hiwe

    ምረጪ🥰☹️

  • 2 авг.283112из poem_Hiwe

    ክፍል አስር ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነገር ግን እሷን ለመውቀስ አልቻልኩም። ምክንያቱም እሷ የልቤን ሚስጥር አታውቅም ነበር።     እህቷ ከኔ ተለይታ ከሄደች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ በሆስፒታሉ አደባባይ ውስጥ እየተዘዋወርኩ ቆየሁ። አዕምሮዬ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን እያሰበ ነበር። "እብሱ ወንድሜ ነው ያለችኝ..." ያቺ አንዲት አረፍተ ነገር አሁንም በጆሮዬ ውስጥ እያስተጋባች ነበር። አብሱ ለእኔ ያላትን ስሜት ባላውቅም፣ ቢያንስ እኔ ያለኝን ስሜት ለእሷ እንኳን እንዳልገለጽኩላት ሳስብ ራሴን ወቀስኩ። ቀስ ብዬ አብሱ ወደ ተኛችበት ክፍል ገባሁ... ተኝታለች   አልጋው ጫፍ ካለው ወንበር ላይ ተቀምጬ አይን አይኗን መመልከት ጀመርኩ እንዴት ግን እንደምታምር አላህ አዳልቶባታል... በተቀመጥኩበት ስለሷ ሳስብ ስልኬ ጠራ አብዱ ነው ድምፁን አጥፍቼ ስለነበር ስልኬ አልቀሰቀሳትም ቀስ ብዬ ስልኩን ይዤ ወጣሁ ከበሩ ራቅ ብዬ ከአንድ ጥግ ቆሜ አነሳና... አብዱ...አሰላም አለይኩም እንዴት ነህ ግን...በናፍቆት ድምፅ እኔ...ደህና ነኝ አልሃምዱሊላህ አብዱ...ባለፎ የሮጥክበት ጉዳይ ከምን ደረሰ... አንተማ በአላህ ብዙ ነገር ደብቀኸኛል እኔ...አንድም ጥያቄውን ለማለፍ...አንድም የኔን እንዲመልስ ብዬ...መስጊድ ምን ተባለ ሌላ ነገር ስለኔ... ምንም አልነገሩህም አብዱ...ሁኔታዬ ገብቶታል... እሱን እኮ ነው ምልህ ምን ላይ ነህ ኡስታዝ አሊን አናግርያቸው...አላህን የሚያስቆጣ ተግባር እንደፈፀምክ ነገረኝ እኔ...ምን ስለምን...ሰለ አብሱ መሆን አለበት.(በውስጤ) አብዱ...ምንነቱን እንኳ አልነገረኝም ጓደኛህ አይደል እየዋሸህለት ነው አሉኝ እስኪ ንገረኝ... እኔ...ስመጣ ሁሉን ነግርሀለሁ... ከጀርባዬ በቅርብ ርቀት ስጠራ ዞርኩ ሀኪሙ ነበር... እኔ...አብዱ በቃ ሲመቸኝ እደውላለሁ አብዱ...ኢብሮ እንዳዘጋው መች ጨረስን እየተቆጣ ኢብራሂም በአላህ ንገረኝ... ....ዘጋሁበት.... በፍጥነት ወደ ሀኪሙ ሄድኩ... ከሰዓታት በኋላ ዶክተሩ አብሱ ከሆስፒታል መውጣት እንደምትችል ነገረኝ    በሆስፒታሉ ያሉብንን ብር ከፋፍለን ወጣን...ድጋሚ ቀጠሮ ሰጡን አብሱንም ምግብ ፈሳሽ በደንብ መውሰድ እንዳለባት መከራት... ከአብሱ ጋ አብረን ወደ መኪናው አመራን። መንገዱን በሙሉ አብሱ ዝም ብላ ነበር። ከአልፎ አልፎ የምትጠርገው እንባ ብቻ የውስጧን ስቃይ ይገልጥ ነበር። አብሱ ከሆስፒታል ከወጣች በኋላ ቀጣዮቹ ቀናት እንደ ህልም አለፉ። የአባቷ ቀብር፣ የሀዘን ተጋሪዎች መምጣትና መሄድ፣ የቤቱ ጭንቀት... ሁሉም ነገር ተደበላልቆ ነበር። ...እኔም ከእነሱ ጎን ለመሆን የምችለውን ሁሉ አደርግ ነበር።ነገር ግን ከቀብሩ በላይ የሚያስጨንቀኝ አንድ ነገር ነበር። "የአብሱ እህት" ከሆስፒታሉ ጀምሮ የምታየኝ አይኗ የተለየ ነው።ልቤ ውስጥ የደበቅኩትን ሁሉ እንደምታውቅ ይሰማኛል። አንዳንድ ጊዜ አብሱን ስመለከት እሷ ወደ እኔ እያየች ትይዘኝ ነበር።ያኔ ደግሞ ልቤ በፍጥነት ይመታል። "ዛሬ ነገረቻት ይሆን?" "ወይስ ገና አልነገረቻትም?" የሚለው ሀሳብ አልተወኝም እያሰቃየኝ ነው። ከቀብሩ ማግስት በኋላ ቤታቸው የሚመጡት ሰዎች እየተቀነሱ መጡ። የሆነ ቀን ግን አብሱ፣ እህቷ እና እኔ ብቻችንን በሳሎኑ ተቀምጠን ሳለን የውጭው በር በሀይል ተንኳኳ።             .........ይቀጥላል......... @Rufaylen13                   ✍️ ህላዌ💕

  • 1 авг.276101из poem_Hiwe

    ክፍል ዘጠኝ                ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ         እህትየዋ ደሞ በፍጥነት ከኔ ፊት ቀደም ብላ ወደ ክፍሉ ገባች....    እህትየዋ ከኔ ቀደም ብላ ገብታ አብሱን ተጠምጥማ አቅፋት ከሳመቻት በኋላ አጠገቧ ተቀመጠች አሁንም አይኖቼ በተደናገጠ መንፈስ በጭንቅላቴ ከአሁን አሁን ነገረቻት ብዬ ልቤ በአፌ ሊወጣ ደረሰ.. ከአብሱዬ አልጋ አጠገብ ቆሜ እኔም እንደእህትየው ላቅፋት ልስማት ፈልጌ ነበር ግን እንደምንም እራሴን ቆጠብኩት እኔ...እንዴት ነሽ ምን እየተሰማሽ ነው አልኳት(እህትየው እንዴት እንደምታፈጥብኝ) አብሱ... ደህና ነኝ አስጨነኳቹ አይደል?  እህቷ...ኸረ አላስጨነቅሽንም ብላ ወሬ ልቀጥል ስትል...አባ.. አብሱ...አባዬን ብቻውን ተውኩት አይደል (ማልቀስ ጀመረች) እህቷ...ተነሳችና እያቀፈቻት ተይ እንደዚህ አትበይ መጠንከር አለብን ያላንቺ ማን አለኝ? አብሱ...እሺ...ስለ ቀብሩ ምን አረግሽ ነይ ወደ ቤት እንሂድ... እኔ...በነሱ ወሬ ጣልቃ ላለመግባት ዝም ብዬ ዝም ብዬ እንሂድ ሰትል ግን... አይ አሁን አንቺ አትሄጂም! አብሱ...እሄዳለሁ እንጂ አባዬን እኮ ብቻውን አስቀረሁት(እያለቀሰች) እህቷ...የራሷንም የእህቷንም እንባ እየጠረገች ደሞ አባዬ ብቻውን አይደለም አብሱ...  እንባዋን እየዋጠች እና ከማን ጋ ነው? እህቷ...አንዲት የአባዬ እህት ነኝ ባይ ለመቅበር መታለች አብሱ....የአባዬ እህትእ?        አባዬ እህት የለኝም ነበር አይደል እንዴ ያለን ደሞ ማናት? እስከዛሬ ያልጠየቀቹ ለመቅበር የምትመጣው... ኮስተር ብላ እህቷ...እሱን በደንብ እንጠይቃታለን አብረን እኔም ብዙ ላለመጨቃጨቅ ብዙም ጥያቄ አልጠየኳትም አብሱ...ወደኔ  እያየች እና አሁን አልወጣም መች ልወጣ ነው? እኔ...ወደ ከሰአት በኋላ ትወጫለሽ ጭንቀት አታብዢ አሁን እህቷ...ደሞ ጓደኛሽን እስከዛሬ መች አስተዋወቅሽኝ አብሱ...ጥቂት ፈገግ ለማለት እየሞከረች ውይ አቤኒን ነው እሱ ወንድሜ ማለት ነው እህቷ...በግልምጫ እየተመለከተችኝ...እ ደሞ ማን አልሽኝ ስሙን እኔ... የምናገው ቃል ጠፍቶብኝ ድንግጥ ብዬ አፌ ተሳስሯል አብሱ...አቤኒ(አቤኔዘር) እሱ እንደ ወንድሜ የማየው ነው ....እኔ እዛ ቆሜ አንድም እህትየው ከአሁን አሁን ጉዴን ተናገረችኝ እያልኩ አንድም ደሞ አብሱ እሱ ወንድሜ ነው ያለቹ አባባል ባለሁበት ፍዝዝ ድርቅ አርጎኝ በቆምኩበት... አብሱ...አቤኒ ተዋወቃት እንጂ አላወካትም...ያቺ የምሳሳላት  ታናሽ እህቴ እኮ ናት። ...  ስትለኝ ነቃ ብዬ... እኔ...አይ አወኳት በመልክም በጣም ነው የምትመሳሰሉት(ሁለቱንም በአይኔ እያስተያየሁዋቸው እህቷ...አንተም የአብሱ ጓደኛ ወንድም መሆንህን አወኩኝ... እኔ... ይህን ቃል ባላወጣ ይሻለኝ ነበር ግን አንገቴን ወደ መሬት እያቀረቀርኩ በደከመ ድምፅ... አው...አልኳት ነርሷ መታ አሁን ውጡ አለችን... እህቷ...አብሱን እየተመለከተቻት በቃ አሁን እኛ እንውጣ አንቺ እረፍት አርጊ ብላ እኔም ተሰናብቻት አብረን ከክፍሉ ወጣን...አብሱ እየወጣን እያለ እህቷን ወደ ኋላ እንድዞር ጠራቻት... እና እህትየው ተመለሰች እኔ ወጥቼ ከበሩ አጠገብ ቆምኩኝ.... ምን እንደተባባሉ አላውቅም እህትየው ከጥቂት ቆይታ በኋላ ወጣች....ሄደች ለመውጣት እኔም እንደምንም አስቆምኳት እንድታወራኝ ብዬ እኔ...ምን አልሻት ነገርሻት እንዴ? እህቷ...ኮስተር ብላ አልነገርኳትም ግን እነግራታለሁ! እኔ... ልቤ በፍጥነት እየመታ ነበር። "ምን ማለትሽ ነው? ምን ልትነግሪያት ነው?" አልኳት በተጨነቀ ድምፅ። እህቷ.. ለጥቂት ሰከንዶች ፊቴን ትኩር ብላ አየችኝ ና "ኢብራሂም... እህቴን በጣም እንደምትወዳት አውቃለሁ።" እኔ...ይህን ቃል እንደሰማሁ ደሜ በአንድ ጊዜ ወደ ፊቴ ተምዘገዘ። "እኔ... ምን እያልሽ ነው?" ብዬ ለመካድ ሞከርኩ። እህቷ..."አትድከም። ከዓይንህ ይነበባል። ከድሮ ጀምሮ ስለ አንተ አውቃለሁ" እኔ...አንገቴን ወደ ታች ደፍቼ ዝም አልኩ። እህቷ..."ግን..." አለች ድምፇን በመቀነስ፣ "አሁን የምታስብበት ጊዜ አይደለም። እሷ አባቷን አጥታለች። በጣም ተጎድታለች።" እኔ..."አውቃለሁ..." አልኩኝ በቀስታ። እህቷ..."ስለዚህ የምነግራት ነገር ካለ አሁን አይደለም። ግን አንተም ከልብህ የምትፈልጋት ከሆነ እስክትረጋጋ ጠብቅ።" ...ይህን ብላ ከኔ ዞራ ሄደች። እኔ ግን በሆስፒታሉ ኮሪደር መሀል እንደ ሰው ሳልሆን እነደ ሀውልት ቆሜ ቀረሁ። እህቷ ያወቀችው ነገር አንድ ብቻ አይደለም ...ለአመታት የሸሸግኩት ጉዴን ነው.... እህቷ ከኔ ተለይታ ከሄደች ከቆይታ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ መስኮት ተጠግቼ ቆምኩ። አሁንም የአብሱ ድምፅ በጆሮዬ ውስጥ ይደጋገም ነበር። "እሱ ወንድሜ ማለት ነው..." ያቺ አንዲት አረፍተ ነገር ከብዙ ዓመታት ጀምሮ በልቤ የገነባሁትን ተስፋ በአንድ ጊዜ ያፈረሰች መሰለኝ። ነገር ግን እሷን ለመውቀስ አልቻልኩም። ምክንያቱም እሷ የልቤን ሚስጥር አታውቅም ነበር። .........ይቀጥላል.........                 @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • SkillMoney Complete tasks and manage your rewards. https://t.me/SkillMoney01_bot/earn?startapp=ref_C2373B01

  • Online ስራ ነው።ገና ስትገቡ 100 ብር ይሰጣል።ቻናሉን ስትቀላቀሉ ደግሞ 200 ብር!እስኪ ሞክሩት።

  • 30 июл.29571из poem_Hiwe

    ክፍል ስምንት                ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ...ልቤ በደረቴ ውስጥ እንደሚፈነዳ እየመታ ነበር።... ዓይኖቼ ያዩትን ለማመን አልፈለጉም፤ እግሮቼም ከቦታቸው ተቸንክረው ቀሩ። ያን ቅጽበት ጊዜው የቆመ መሰለኝ፤ የሰዎቹ ጩኸት ከጆሮዬ ራቀ፣ የምሰማውም የልቤን ድብደባ ብቻ ሆነ...      ...የኔ... ንግስት በመሬቱ ላይ ተዘርራለች...   ከገባሁበት ሰመመን ሳልወጣ አላውቀውም ሰዎቹን እንዴት እንደተረማመድኳቸው ገፍትሬያቸው በሁለቱ እጆቼ አንገቷን ደግፍያት ነርስ...ነርስ ብዬ ተጣራሁ ወድያውኑ የድንገተኛ በሩን በእግሬ ገፍትሬው አልጋው ላይ አስተኛህዋት ሀኪሞቹ መተረማመስ ጀመሩ..ዶክተሩ መቶ ግሉኮስ እየሰካላት ነው....አንዷ በኔ ጩኸት የተደናገጠቹ  ነርስ  እኔን ለማረጋጋት እየሞከረች እባክህ ከክፍሉ ውጣ ትድናለች ደህና ናት አታስብ እያለች የግዴን ወጣሁ...      አብሱ እስክትነቃ በሆዴ ለአላህ ዱአ ካደረኩ በኋላ ተነስቼ ሲጨንቀኝ በሩ ላይ ቆሜ ወደ ግራ ወደ ቀኝ መመላለስ ጀመርኩኝ...     የአባትየው አስክሬን ወደ ቤት እንደተሸኘ አወኩ ብዙም ሰው የለም ግን የተወሰኑ ሴቶች ብቻ ከኔ ጋ አብረው እያለቀሱ አብሱን ሲጠብቁ እኔ አለሁ ችግር የለም ምንም አይፈጠርም አዲስ ነገር ካለም እደውልላችኋለሁ ብዬ ወደ ቤት እንዲሄዱ በስንት ልምምጥ ሸኘሁዋቸው...   (...ማዘኔን ስላዩት የሆነ የሩቅ ዘመድ መስያቸው እንዴት አርገው እንዳፅናኑኝ ምስኪኖች ናቸው...)     ከትንሽ ቆይታ በኋላ...በሩ ላይ ቆሜ ነርሶቹን እየተጠባበቅኩ ባለሁበት የአብሱ እህት እያለከለከች በተቆራረጠ ትንፋሽ ከጀርባዬ መጣች ስዞር የማላውቃት እያስመሰልኩ  በጥያቄ  አይን ስመለከታት( ያው በ አብሱ ስልክ ፎቶዋቸውን አይቼ ነው ያወቅኳት) የኔን ቃል ሳትጠብቅ እህቷ...በተደናገጠ ስሜት እንዴ ኢብራሂም  አለችኝ... ግርር ተሰኝታ እኔ... አይኖቼ በአንዴ ወደ ቀይ ተለወጡ በሆነ ነገር እንደተመታሁ ደንግጬ...ዝምም አልኳት እህቷ...ሁኔታዬን በአግራሞት እየተመለከተች ልትናገር የነበረውን መለሰቹ ...እንዲህ ሁለታችንም ተፋጠን በቆምንበት... ከአብሱ ክፍል ነርሷ በፍጥነት ወታ የአብሳላት ቤተሰቦች አለች   ሁለታችን ወደሷ ለመጠጋት እየሞከርን አቤት አለን አለን አልናት ....ቶሎ በሉ ከሁለታችሁ ውስጥ ማነው A+ ደሙ የሆነው እኔ እኔ አለሁ ነርስ ሁለታችንም እሷ እየመራችን ደም የሚሰጥበት ክፍል ገባን ከዛን እህትየው አልሰማ አለች እኔ ነኝ የምሰጠው እኔ ለእህቴ አላንስም ብላ ነርሷ ላይ ስታምፅ አልሰማ ስትለኝ ነርሷ በመጨረሻም የእህትየውን ደም ሁኔታ ስትለካት የሷም እንደወረደ መስጠት እንደማትችል ነገረቻት     ... ገላገለችኝ ኡፍ!  የኔ ደም ተወሰደ ና ትንሽ ተቀምጬ ተነሳሁ ከክፍሉ ወተን አብሱ ካለችበት ክፍል በሩ ላይ......ምንም አልተነጋገርንም በጎሪጥ እየተያየን እኔና እህቷ መጠባበቅ ጀመርን...    እህትየው ያፈጠጡብኝን አይኖቿን ወደ መሬት ቀልበስ እያረገች.. እህቷ...ከአብሱ ጋ የት ነው የምትተዋቁት አለች? እኔ...መጀመሪያ አንቺ እኔን የት ነው የምታውቂኝ? እህቷ...የኔን ጥያቄ መልስልኝ መቼም መስጊድ አይደለም(በአሽሙር እየተናገችኝ) በሀሳቤ  (እንዴት እንዲህ አወቀችኝ እኔ ሳላውቃት አሁን አብሱ ጉዴን ልሰማ ነው አበቃልኝ በቃ) እህቷ...ፀጥታ ሳበዛባት እ ንገረኛ የት ነው የምታውቃት(ኮስተር ብላ) እኔ...የምናገራት ሲቸግግረኝ የሆነ ቦታ የሆነ ቦታ ነው የምንተዋወቀው ቆይቷል ...ሁለታችን እንዲህ ክርክር በጀመርንበት ከአብሱ ክፍል ነርሷ ወታ የምስራች አበሰረችን ... እንኳን ደስስ አላችሁ አብሳላት ነቅታለች ...   እህትየው ቀደም ብላ እህቷ... ወደ ውስጥ መግባት እንችላለን አለች ነርሷ....አዎ ትችላላችሁ ብዙም እንዳቆዪ ግን እንዳናስጨናንቃት ጥብቅ ማስጠንቀቅያ ሰታን ሄደች...          እኔ ግን በበሩ ላይ ቆሜ ቀረሁ። እግሮቼ ወደ ክፍሉ ሊወስዱኝ ሲፈልጉ፣ ልቤ ግን ወደ ኋላ ይጎትተኝ ነበር። አብሱ ስትነቃ መጀመሪያ የምትጠይቀው ሰው ማንን ይሆን? እኔን ስታይ ምን ትላለች? ከዚያ በላይ ደግሞ... እህቷ ስለ እኔ ምን ታውቃለች? የነበረው ፍርሃት ከደቂቃ ወደ ደቂቃ እየጨመረ ነበር... እህትየዋ ደሞ በፍጥነት ከኔ ፊት ቀደም ብላ ወደ ክፍሉ ገባች....            ይቀጥላል... ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ ፃፉልኝ🤗                       @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • አንድ መፅሐፍ ውስጥ ገብታችሁ የመኖር እድል ቢሰጣችሁ የትኛው መፅሐፍ ውስጥ ትኖራላችሁ?

  • 28 июл.3228из poem_Hiwe

    без подписи

  • 27 июл.29173из poem_Hiwe

    ክፍል ሰባት                ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ አብሱ ናት...አጠገቤ ሁኖ እንዳነሳው ሲያፈጥብኝ...አነሳሁት... ግን የሚሰማኝ የ እንባዋ ድምፅ ነው... ሮጬ እንዴት አንዳለፍኩት ባላውቅም በሩን ከፍቼ በተደናገጠ ድምፄ...በእርብትብት አንደበቴ አብሱ...አብሱዬ ባክሽ አውሪኝ              አ..አብሱ እሷ...እንባዋ ድምጿን እያቆራረጠ እባክህ ቶሎ ናልኝ  ባክህ እኔ...ምንድነው.. ምን ተፈጠረ  አባባ ምን ሆኑ? እሷ...አባዬዬዬ....አረፈ.. እኔ...እ   እሺ...የት ነሽ እሷ...ሆስፒታል      ትንሽ በቻልኩት አቅም አረጋግቻት...ወደሷ ለመሄድ በፍጥነት ወደ አብዱ ተመለስኩ በሩን ስከፍተው ቅድም ያየሁት አይኑ ቀልቶ ፊቱ ተኮሳትሮ አብዱ...አንተ ያ አላህ! ደሞ ማንን ነው      ያወራኸው  እኔ...ቆፍጠን ባለ አታውቃትም አብዱ...አዎ አንተንም አላውቅህም ምንህ ናት አንደዚህ የሆንክላት እኔ..ቃል ጠፍቶብኝ የምመልሰውን ሳስብ የምዋሸውን አብዱ...ለካስ ከእኔ የደበቅከው ብዙ ነገር አለ ተሳስቻለሁ ወላሂ እኔ...አሁን ጊዜው አይደለም መሄድ አለብኝ አብዱ...ደሞ የት ነው ምትሄደው? መስጊድ ሂድ እንጂ እኔ... ከሄድኩበት ስመለስ የባሰ እያስቆጣሁት ነው ግን መልስ የለኝም  ለሚጠይቀኝ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ብዬ በሩን ከፍቼ  ወጣሁ...  ሮጥኩኝ አብዱ...በድምፁ ሊመልሰኝ ኢብሮ... ኢብራሂም እያለ ይጣራል እሱንም ድምፁንም ባልሰማ ወደ ቤቴ መልሼ ከነፍኩኝ      የቤቴን በር ከፍቼ ያው ለዝነጣም ብዬ ከገዛሁት ውስጥ አብሱ ከኔ ላይ የለመደቹንም ልብሶች ጥቁር መርጬ ከለበስኩ በኋላ ሁለት ቅያሪ ልብስ በመያዣ እቃ ይቼ ወጣሁ...    መንገድ ጀምሬ መኪና ከመያዜ በፊት የተወሰነ ብር እናቴ ካስቀመጠችልኝ ገንዘብ ላይ አውጥቼ መኪና እየያዝኩ እያለ ስልኬ ጠራ አብዱ ነው...አንስቼ እኔ... በአላህ በቃ እንዳሳዘንኩህ አውቃለሁ ግን ተወኝ ስመጣ አወራሀለሁ አብዱ..እሺ...ግን  አንተኮ  ወንድሜ ነህ የሆነ ነገር ብትሆንብኝስ? እኔ... ምንም አልሆንም ስለኔ አትጨነቅ     ... ስልኩን ዘጋሁት። የአብዱ ቃል በልቤ እያስተጋባ ነበር፤ “ወንድሜ ነህ...” ያለኝ ድምፅ አልረሳውም። ግን በዚህ ሰዓት አብሱ ብቻ ናት በአይኔ የምትታየው። መኪናው እየገሰገሰ ነው፤ እኔ ግን ወደ ምን እንደምሄድ እንጂ ሄጄ አብሱን እንዴት እንደማፅናናት አላውቅም...    ... በሀኪም ቤቱ በር ላይ የተወሰኑ ሰዎች ወትሮ ከሚለብሱት የተለመደ ልብሳቸው ላይ አንድ አራት ሴቶች ጥቁር ሻርኘ ትከሻቸው ላይ ጣል አርገው ወገባቸውን እየደለቁ ባላቸው ድምፅ ያለቅሳሉ ይጮኻሉ... በርቀቱ እነሱ መሀል አብሱ እንደሌለች በአይኔ ካጣራሁ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ ውስጠኛው ክፍል ገባሁ ማንንም ሳልጠይቅ የሰው ግርግር ወደ በዛበት አንድ የሆነ ቦታ ግን    ...  ዞር ስል በመታጠፍያ ቦታ የሚያለቅሱ የሚጮሁ ሰዎች ክብ ሰርተው ይተረማመሳሉ ይሯሯጣሉ እግሬ እየፈራም እየተባበሸም ምንድነው ሰው.. የሆነው ብዬ በሰው ላይ ተደራርበቤ መሀል እየሆነ ያለው ብዬ በአይኔ ሳማትር.....ያየሁት ነገር ለመናገር  ለማመን ይከብዳል ግን... ...ልቤ በደረቴ ውስጥ እንደሚፈነዳ እየመታ ነበር።... ዓይኖቼ ያዩትን ለማመን አልፈለጉም፤ እግሮቼም ከቦታቸው ተቸንክረው ቀሩ። ያን ቅጽበት ጊዜው የቆመ መሰለኝ፤ የሰዎቹ ጩኸት ከጆሮዬ ራቀ፣ የምሰማውም የልቤን ድብደባ ብቻ ሆነ...      ...የኔ... ንግስት በመሬቱ ላይ ተዘርራለች...            ይቀጥላል... ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ ፃፉልኝ🤗                       @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • 25 июл.358113из poem_Hiwe

    ክፍል ስድስት                ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ እኔም ሳልነሳ ከአይኔ እስክትጠፋ በአይኔ ሸኘሁዋት...           አብሱዬ ጥላኝ ስትሄድ ከፋኝ ማልቀስም መጮህም አማረኝ ከዛን አብሱዬ የምታለቅስባት ማርያም ጋ ሂጄ ማርያምዬ እኔስ እኔስ አልታይሽም ወይ?? የምታናግረኝ ይመስል ጮህኩባት የምናገረው ስለጠፋብኝ አቀርቅሬ አጎንብሼ እስኪደክመኝ  አለቀስኩኝ በእውነቱ ስለ አባትዋ ሳይሆን ስለ ራሴ ነው ያለቀስኩት አልቅሼ አልቅሼ ሲቀለኝ አይኗን ቀና ብዬ ማየት አሳፍሮኝ ቀጥ ብዬ ከቤተክርስቲያኑ ወጣሁ...        እቤት ስደርስ ሰአቱ ሄዶ 3:00 አልፎ ነበር...እራት መብላት ደብሮኝ እንቅልፍ ከወሰደኝ ብዬ ጋደም አልኩኝ ግን ሊወስደኝ አልቻለም በአይኔ ላይ ትመላለሳለች መላ አካላቴን ተቆጣጥራዋለች...       እንቅፍ እንቢ ሲለኝ ትንሽ ከጭንቀቴ ለመውጣት በለሊቱ 6:00 ተነስቼ ፊልም ማየት ጀመርኩ እንደውም የባሰ ተነቃቃሁ አብሱዬ መልዕክት ከላከች ብዬ ስልኬን ባየው ምንም አላከችልኝም       ወደ 7.. ከምናምን 8 ሊሆን ሲል እንቅልፍ በተቀመጥኩበት ወሰደኝ 10 ሰዐት አካባቢ ደግሞ ብቻ የሆነ ቅዠት አይቼ ባነንኩኝ ተነስቼ ሰላት ሰገድኩኝ...የማነጋ የለም ሳልተኛ ጨለማ ለብርሃን እጁን ሰጠ                 ጠዋት ወደ 3:00 አብዱ ደወለለልኝ እኔ... ገና ሄሎ ከማለቴ እሱ..."ሱብሃናላህ!  አንተ ዛሬ መስጊድ በር ላይ ያየሁት ነገር ልቤን አስደነገጠኝ! እኔ...ሁሌ ስለሚቀልድ ቀልድ መስሎኝ እያፌዝኩ ደሞ ምን አየህ? እሱ..."ፎቶህ ተለጥፎ፣ 'ይህ ሰው እንዳይገባ' ተብሎ አየሁ! ዋላሂ ምን ፈጽመህ ነው?!" እኔ..."አስታግፊሩላህ! ምን አልከኝ?! ፎቶዬ መስጊድ በር ላይ?!" እሱ..."አዎ ዋላሂ! እኔም ሳየው ደነገጥኩ!" እኔ..."እኔ ምንም አላጠፋሁም! ምናልባት ሌላ ሰው ነው የተመሳሰለብህ?" እሱ...እየቀለደ "አይ ወንድሜ፣ ጢምህም ጭምር በግልጽ ይታወቅ የለ እንዴ እኔ..."ያ ከሆነ ጉዴ ነው! አሁኑኑ ወደ መስጊዱ እየመጣሁ ነው በቃ መጣሁ!" እሱ..."አትቸኩል... መጀመሪያ አንድ ነገር ልጠይቅህ..." እኔ..."ምንድነው? ልቤ ሊፈነዳ ነው!" (በሀሳቤ) ትላንት ከአብሱዬ ጋ ቤተክርስቲያን ታየሁ እንዴ በሀሳቤ ያለው ጥፋት ይህ ብቻ ነው የማስታውሰው ግን ምን ብዬ ነግረዋለሁ ዝምም ልበል እሱ...ወንድሜ ቀልድ ትተን አንድ ነገር ንገረኝ...  የደበቅከኝ ነገር ካለ አሁን ንገረኝ። ያጠፋኸው ምንድነው? በአላህ፣ እውነቱን ንገረኝ!" እኔ..."ዋላሂ ልቤን አስፈራራኸው!  እኔ የማውቀው ጥፋት ቢኖር ኖሮ አሁኑኑ እነግርህ ነበር።" እሱ..."አይ ወንድሜ፣ በአላህ አትደብቀኝ... ሰው እንዲሁ በመስጊድ በር ላይ ፎቶው አይለጠፍም!" እኔ...ቆይ እስኪ... ላስታውስ አንድ ጊዜ የጓደኛዬን ጫማ ተሳስቼ ለብሼ ወጥቼ ነበር... ግን በኋላ መልሼለታለሁ! እሱ... "ይሄ አይደለም! ሌላ ነገር አለ!" እኔ..."ዋላሂ ከዚያ በላይ የማስታውሰው ነገር የለም! እኔ አሁን ራሴን እየጠረጠርኩ ነው! እሱ...ና በቃ እራስህ ጉዳዩን አጣራ እኔ...እሺ መጣሁ  በቃ... ዘጋሁበት ከቤቴ ወጣሁ አሁን ሄጄ ቤተክርስቲያን ስትገባ አየንህ ቢሉኝ ምንድነው የምላቸው ለሀጂ..     በደመነፍስ  እየተራመድኩ መጀመሪያ አብዱ ቤት ሄድኩ ባንኳኳ ባንኳኳ የሚከፍትልኝ የለም ከበሩ ስወጣ ከጀርባዬ ኢብሮ ኢብሮ እያለኝ ከሩቅ እንድቆም በእጁ ምልክት ይሰጠኛል ስዞር አብዱ ነው አጠገቤ መቶ ሰላም ከተባባልን በኋላ ስለ ሁኔታው ሊነግረኝ እሱ...አንተ ምን አርገህ ነው ግን በአላህ ብሎ ወሬ ልንጀምር ስል ስልኬ ጠራ...     አብሱ ናት...አጠገቤ ሁኖ እንዳነሳው ሲያፈጥብኝ...አነሳሁት... ግን የሚሰማኝ የ እንባዋ ድምፅ ነው...            ይቀጥላል... ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ ፃፉልኝ🤗                       @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕

  • 20 июл.387154из poem_Hiwe

    ክፍል አምስት                ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ     አርብ ነጋ....አብሱዬን ላገኛት ነው ማለት ነው....        በጠዋቱ ፏ ብያለሁ ሻወር ወስጄ ወጣሁ ስራ ቦታ የመስራት ሞራል ላይ ባልሆንም አብሱዬ እስክደዉልልኝ ድረስ ብዬ ሄድኩኝ ስሄድ የሱፍ ብቻውን በር ላይ በትንሽዬ ዱካ ተቀምጦ የሰዉን ትርምስ ይታዘባል ልክ እንዳየኝ አግራሞት በሚመስል መልኩ ተመልክቶኝ እሱ...አሰላሙ ዐለይኩም? እኔ...ወዐለይኩሙ ሰላም፣ አልሃምዱሊላህ! አንተስ? እሱ...(የኔንም ጥያቄ ባልሰማ አልፎት)         ደሞ የት ልትሄድ ነው? እኔ...የት እሄዳለሁ ዛሬ በቃ እንዲህ መልበስ አሰኘኝ እሱ...ሳቅ እያለ... ተወው በኋላ አብረን እናያለን (ድንገት መተህ ድንገት ሁሌም ትጠፋ የለ) እኔ...እሺ ተወው   (የሆነ ወንበር ላይ ተቀምጬ)ስልኬን መጎርጎር ጀመርኩ ከአሁን አሁን ደወለችልኝ እያልኩ ይኸው 8:00 ሞላኝ እንደውም አንዳንዴ መንጎራደድ ጀምሬያለሁ ስልኬን እያየሁ...     በተቀመጥኩበት 9:20 ላይ ጠራ... አብሱዬ ናት እኔ...በተደናገጠ በተደሰተ ድምፄ ወለም አርጎኝ የኔ ንግስት.. ብዬ ጠራኋት እሷ...በአንዴ ሰምታኝ አትቀልድብኝ እባክህ አቤኒ እንዴት ነህ ግን.. እኔ...ደህና ነኝ አለሁ መጣቹ አይደል? አንቺስ እንዴት ነሽ..አባባስ? (ጥያቄዎች አበዛሁባት) እሷ...ቆይ ሁሉንም ወደ በኋላ አወራሀለሁ ቤተክርስቲያን ና እኔ...እሺ እመጣለሁ በተለመደው ስዓት እሷ...መልስም ሳሰጠኝ ዘግታዋለች ግን ድምጿ ልክ አይደለም...አባትየው ምን ሆኖ ይሆን?  የሱፍን ሄጃለሁ ብዬው ወደ ቤቴ ስከንፍ ሄድኩኝ ያው እንደሁልጊዜው ልለብስ ነው ግን ከለሩን ቀይሬዋለሁ...    11:00 ሆኖ ከቤተክርስቲያን ወጪ አጥር አቅራብያ ቆምያለሁ አብሱን ስዞር በግራዬ በኩል ስትመጣ አየሁዋት     አጠገቤ ከመድረሷ ምን እንደሆንኩ ባላውቅም ልትጨብጠኝ እጇን ስዘረጋልኝ እኔ ግን ሄጄ እናቱን እንዳገኘ ህፃን ተጠመጠምኩባት በቃ ባለቃት ደስስ ይለኝ ነበር እንዳስጨነኳት ያወኩት ልቀቀኝ በሚል ምልክት ድምጿን እክህህህህ... ስትለኝ ነው በእፍረት ይቅርታ ብዬ ለቀቅኳት...     ቤተክርስቲያን አንደገባን እሷ ለፈጣሪ ሰላምታ ስሰጥ ስለማልችልበት አንገቴን ጎንበስ ቀና አድርጌ ገባሁ እና ለብዙ ሰዐት ከማርያም ፊት ቆማ እያለቀሰች ታወራለች  ምን እያላቻት ይሆን? ማርያም ስሟን ያወኩት ከአብሱዬ ነው ከአፏ አጠፋም..   እኔ ከበሩ አጠገብ ቆሜ እየተመለከትኳት ነው ሳስብ ስለኔ ምናለ ብትነግርልኝ ምናለ እያልኩ ሳሰላስል አብሱዬ አጠገቤ ካለው ድንጋይ መታ ተቀመጠች...    ከዛን ትንሽ ቀልቧ ወደኔ መለስ ሲል አወራችኝ... እሷ...እንዴት ነህ ግን? ተመችቶሀል እኔ...እኔማ አለሁ እንዳለሁ..አንቺ እንዴት ነሽ... እሷ...እንዲህ እንደምታየኝ ይኸው ብላ አይኖቿ እንባ አቀረሩ እኔ...እንባዋን ለላማየት እየታገልኩ አባትሽ እንዴት ናቸው ተሻላቸው? ቤት መተዋላ እሷ...አው ቤት መቷል ግንን ብላ ያፈነቹ እንባዋ ዱብ ዱብ አለ እኔ...እሺ አታልቅሺ እባክሽ ንገሪኝ እኔ ምን ላርግልሽ...ብዬ አባበልኳት አቀፍኳት ግን አላቆመችም ... ባቀፍኳት አንድ እጄ የራሴን እንባ በፀጥታ እጠርጋለሁ ስትረጋጋ እራሷ ከእቅፌ ወጣች እኔም እንባዬን ዋጥ አይኔንም እንደበፊቱ አድርጌ በእርጋታ እኔ...እሺ አባባ ምን ተባሉ ህክምናው እ...ዳግም እንዳታለቅስ አየተሳቀቅኩ እሷ...ተስፋ የለውም መዳን አይችልም አሉን እኔ... እንዴት? ለምን? እሷ...በቃ ሊድን አይችልም ብለው መለሱን የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሷል አባዬን ላጣው ነው...ምን ላርግ በተሰበረ ድምፅ እኔ...እሺ እኔ ምን ላርግልሽ እባክሽ አንድ ነገር በይኝ...ብር ነው? እሷ...አይ አይደለም ብር አልተቸገርኩም እኔ... እና ምን ምንድነው?   እንዲህ እያወራኋት...ስልኳ ጠራ እህቷ ናት አውርታ...ስጨርስ መሄድ አለብኝ ብላ ብድግ አለች እኔ...ምን ተፈጠረ? አብረን እንሂድ? እሷ..አይ እህቴ እየጠበቀችኝ ነው መሄድ አለብኝ እኔ...ልሸኝሽ እሺ..ብዬ ልነሳ ስሞክር አይ አንተ ተቀመጥ ብላ ትከሻዬን መለስ አረገች እኔ...እሺ ቆይ መች ነገርሽኝ ንገሪኛ ምን ላርግልሽ? በምን ላግዝሽ? እሷ...አይኖቿ እንባ እንዳቀረሩ በቃ ፀልይልኝ ብላ ተሰናብታኝ ማርያም ደሞ ስማት እየተዋከበች ከግቢ ወጣች..... እኔም ሳልነሳ ከአይኔ እስክትጠፋ በአይኔ ሸኘሁዋት...            ይቀጥላል... ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ ፃፉልኝ🤗                       @Rufaylen13 💫                        ✍️ ህላዌ💕