- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 20:51
- Постов за неделю
- 12
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Образование
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 103
- 1/48двое суток
- 118
- 1/72трое суток
- 127
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
መጀመሪያ ተክፊረል ዑሙም እና ሙዐየን ለዩ ይህ ዑሙም ነው ነገርግን ሸይኽ ፈውዛን ሀፊዞሁላህ ሙዐየንም ቢሆን ይከፍራል እንደሚሉ አውቃለሁ እንዲሁም ሙዐየንን ማክፈር ኺላፍ የለበትም ይላሉ በተቃራኒው እነ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን:ሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚ እና ሌሎችም ኺላፍይ ነው ብለዋል። ሁላችንም ሰለፎችን እንከተላለን ባዮች ነን የሰለፎች ጎዳና ይዳኘን እሳቸውም ቢሆን ኺላፍ የለበትም ብለው ሌሎችን ኺላፍ አለ ያሉትን አላስገደዱም እንደእኔ ኺላፍ የለበትም ብላችሁ ተናገሩ አላሉም በተናጠል ማክፈርን ተግባራዊ ያላደረጉ ከመሆናቸው ጋር......ኺላፍ የለም በማለት ከሰለፎች ፈውዛንን ማን ቀደማቸው??? ይህን አይነት ጥቅል የሆነ ንግግር አምጥታችሁ ለአንድ ግለሰብ ማስረጃ አታድርጉ ኡሱሉል ፊቅህ ተማሩ ምናልባት ለመቅራት እስከ ዛሬ ካልታደላችሁ ከዚህ በኃላ ተማሩ..... ነገሩ <የለለው መስጠት አይችልም>። በመጨረሻም እስከዛሬም ወደፊትም ኢንሻአላህ የአህባሽም ይሁን ሽርክ የሚሰራ ሰው ጠበቆች አይደለንም ሽርክን ከነ ተፋሲሎቹ: ተውሂድ እና ሱናን እናስተምራለን እንኳን እናንተን በጭፍን ተከትለን ልናከፍር ይቅርና ፈውዛንንም ይሁን ሌሎች በዚህ ዘመን ያሉትንም ይሁን የጥንቶቹን ዑለማዎች በመረጃ(በደሊል) ነው የምንከተለው ። በድብቅ ጀመዐ ሰብስቦ መጮህ አይደለም ጎበዝ ከሆናችሁ በአካልም ይሁን በLivestream ሸይኻችሁን ምናለ ቀርቦ ስርአት ያለው ውይይት እንዲያደረግ ብታመቻቹ የተንሻፈፈ(መስመር የለቀቀ) አካሀዱን ቀጥታ ከሰማይ እንደመጣ ወህይ አለረእስ ወልአይን ከምትቀበሉት አላህ ሀቅን በሀቅነቱ ያሳየን የምንከተለው ያድርገን ባጢልን በባጢልነቱ ያሳየን የምንርቀው ያድርገን አላህ ሆይ እኔንም ሙስሊም ወንድም እህቶቼንም የሰለፎችን መንገድ አጥብቀን የምንይዝ አድርገን። Share አድርጉት https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu
без подписи
በዚህ ዘመን በሀገራችን ማክፈር ላይ የወደቁት ሙስጠፋ እና ሙሪዶቹ በሸይኽ ኢብኑ ባዝ እና በሸይኽ ሳሊሀል ፈውዛን ተንጠልጥለው የ አብደላህ አልጀርቡዕን አቋም ያራምዳሉ።የሚገርመው ሙስጠፋ ጀርቡዕን የሚያወድስበትን ድምፅ ከዚህ በፊት ሰምታችዋል ነገርግን ጀርቡዕ ሸይኽ አልባኒን አና ሌሎች የሱና ዑለማዎችን በኢርጃእ ይወርፋል ይህ ማለት ጀርቡዕን ማወደስ በተዘዋዋሪ አልባኒን ሙርጂአ ማለት ነው። በዛ ላይ አላህን አትፈሩም አላባኒ ተውበት አድርገዋል ትላላችሁ ድምፃቸውን ስሙ ትላላችሁ በዚህ ልክ ቂል አትሁኑ አናንተ እንደምትሉት ተውበት አደረጉ እንበል ለምንድነው አሁን ጀርቡዕ እሳቸውን ሙርጂአ የሚላቸው ???ይህንን ጥያቄ መልሱልን የሚገርመው ጀርቡዕ እነ አልባኒን በኢርጃእ ሲሳድብ ነገርግን ሙስሊሞችን የሚያከፍረውን ሰይድ ቁጥብን:እናም ዩሱፍ አልቀርዳዊን ............ አያከፍርም ይህ ድምፅ ላይ ሸይኽ አብዱሰላም ሰይድ ቁጥብን ታከፍራለህ ሲሉት እንደተቆጣ ይናገራሉ። Share አድርጉት https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu
— مقطع (الجربوع القطبي)
ሱረቱል ከህፍ🤍 ቃሪእ: ዐብደላህ መጥሩድ🎙 @quran_post18❤️🩹
مَن يَهْدِ اللَّهُ فَهُوَ الْمُهْتَدِ ۖ وَمَن يُضْلِلْ فَلَن تَجِدَ لَهُ وَلِيًّا مُّرْشِدًا سورة الكهف.. 🎙 ሱረቱ አል- ካህፍ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا (ሱረቱ አል- አሕዛብ - 56) አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ ሱረቱል ካፍ ✅ ከጁመዓ ቀን ሱናዎች ↩️ سنن_يوم_الجمعة ➊ الغسل ➋ الطيب ➌ السواك ➍ لبس الجميل ➎ قراءة سورة الكهف ➏ التبكير لصلاة الجمعة ➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ 🔹ገላን መታጠብ 🔹ሽቶ መቀባት 🔹ሲዋክ መጠቀም 🔹ጥሩ ልብስ መልበስ 🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት 🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ 🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት ﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!} ~ ቀደም ባለው ዘመን መውሊድን ደጋፊዎቹ ጭምር ቢድዐ መሆኑን ያምኑ ነበር። ክርክራቸው ቢድዐ ሐሰና (መልካም ቢድዐ) ነው የሚል ነበር። ዛሬስ?አይናቸውን በጨው አጥበው እነ አቡበክርንና እነ ዑመርን ሳይቀር መውሊድ አክባሪዎች እያደረጓቸው ነው። አንዳንዶቹማ ነብዩን ﷺ ሳይቀር መውሊድ አክባሪ ለማድረግ ሲንደፋደፉ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጣቸውም። ነብዩ ﷺ “በኔ ላይ ሆነ ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ!” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] እልህ በሳቸው ላይ እስከሚዋሽ ያደረሰው ሰው ወዮለት! ለማንኛውም ቀደም ያሉት የመውሊድ #ደጋፊዎች ይሄ ድግስ ከነባሩና ከጥንቱ ኢስላም ውስጥ የማይታወቅ መጤ ፈሊጥ እንደሆነ አስረግጠው መስክረዋል። ንግግራቸውን እጠቅሳለሁ፡- 1. አቡ ሻመህ (665 ሂ.)፡- “በዘመናችን ከተፈጠሩ ከዚህ አይነት ነገሮች ያማረ ከሆነው የላቀው አላህ ይጠግናትና በኢርቢል ከተማ በያመቱ ከነብዩ ﷺ የልደት ቀን ጋር በሚገጥመው ቀን ይፈፀሙ የነበሩ ሶደቃዎች፣ በጎ ነገሮች፣ ጌጦችንና ደስታን ማንፀባረቅ ነው።” [አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢደዕ ወልሐዋዲሥ፡ 95] 2. አት-ተዝመንቲይ (682 ሂ.)፡- “የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” [አስ-ሲረቱ አሽ-ሻሚያህ፡ 1/441] 3. አቡ ዙርዐህ አል-ዒራቂይ (826 ሂ.)፡- “ይህንን ነገር ምግብ በማብላት መልኩ እንኳን ከሰለፎች አናውቀውም።” [ተሽኒፉል ኣዛን፡ 136] 4. ኢብኑ ሐጀር (852 ሂ.)፡- “የመውሊድ ድርጊት መሰረቱ ቢድዐ ነው። ከሶስቱም ክፍለ-ዘመናት መልካም ቀደምቶች አልተላለፈም።” [አልሓዊ ሊልፈታዊ፡ 1/188] 5. አስ-ሰኻዊይ (902 ሂ.)፡- “የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።” [ሱቡሉል ሁዳ ወረሻድ፡ 1/439] 6. አስ-ሲዩጢይ (911 ሂ.)፡- “የመጀመሪያው ይህን ስራ የፈጠረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዞፈር ነው።” [አል-ሓዊ፡ 1/189] (መጤ እንደሆነ መናገራቸውን ለመውሰድ ያክል እንጂ ንግግሩን ያጣቀስኩት መውሊድ የተጀመረው በሺዐዎች እንደሆነ በማስረጃ አሳልፌያለሁ።) 7. አዝ-ዘርቃኒይ (1112 ሂ.)፡- “መውሊድን መፈፀም ቢድዐ ነው።” [ሸርሑል መዋሂብ፡ 1/264] ይስተዋል። እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ እንደሆነ ግን ባንድ ድምፅ እየመሰከሩ ነው። (وَشَهِدَ شَاهِدࣱ مِّنۡ أَهۡلِهَاۤ) እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ መሆኑን በግልፅ ይናገራሉ። የድሮዎቹ መውሊድ አክባሪዎች ከነ ክፍተታቸው የሆነ ያክል ኢንሷፍ ነበራቸው፣ ሚዛናዊነት። ቢያንስ መጤ ቢድዐ መሆኑን እንዲህ እቅጩን ይናገራሉ። የዛሬዎቹስ? አይኔን ግንባር ያድርገው ካሉ አይመለሱም። ብቻ አንባቢ አንድ ቁም ነገር ይውሰድ። መውሊድ በደጋፊም በነቃፊም ኢጅማዕ (የጋራ ስምምነት) መጤ ፈሊጥ ነው፣ ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ የማይታወቅ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የተጠነሰሰ ቢድዐ!! በየመንደሩ ከዚህ የተለየ እያስተጋቡ ለሚበጠብጡ አካላት ይሄ አስደንጋጭ መብረቅ ነው! “ነባሩ እስልምና” እያሉ ልባችንን ለሚያደርቁ ሁሉ አንድ መልእክት ይድረሳቸው። ነባሩ ኢስላም ማለት የነብዩ ﷺ፣ የሶሐቦች፣ የታቢዒዮች፣ የአትባዑ ታቢዒን ኢስላም ነው። የአኢማዎቹ፣ የነ ቡኻሪ፣ የነ ሙስሊም፣… ኢስላም። ከዚህ ውጭ ያለ እምነት በኢስላም ስም ቢጠራም፣ "ነባሩ" እያሉ ቢያሽሞነሙኑትም ነባር ሳይሆን ፎርጂድ ነው። ስለዚህ መውሊድና ነባሩ እስልምና ፈፅሞ አይተዋወቁም። ስለሆነም መውሊድን የሚቃወመው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ወዝጋባ ሱፍዮች እንደሚሉት የሃያና የሰላሳ አመት እድሜ ያለው ወይም በ “ወሃ.ብዮች” የተጀመረ አዲስ ፈሊጥ ሳይሆን ስሩ ከነብዩ ﷺ ዘንድ የሚዘልቅ ከሱፍ .ዮቹ የተንሻፈፈ አረዳድ የቀደመ ጥንታዊ ነው ማለት ነው። ማምታቻ! - መውሊድ ራሳቸው በሚያከብሯቸው የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ መሆኑ ሲነገር ጊዜ እንደ ሐሰን ታጁ ያሉ የዚህ ቢድዐ ደጋፊዎች ሌላ ማምታቻ አምጥተዋል። ይኼውም ቢድዐ የሆነው በኦፊሴል ማክበሩ እንጂ ቀድሞም ነበር የሚል። ይሄ የለየለት ማምታታት ነው። 1ኛ፦ በቁርኣንም በሐዲሥም የመውሊድ በዓል ፈፅሞ አልተወሳም። ቢወሳ ኖሮ ቀደምቶች በተፍሲራቸውና በሐዲሥ ድርሳኖቻቸው ይገልፁት ነበርና። 2ኛ፦ ከሰለፎች ውስጥ አንድ እንኳ ኦፊሴል ባልሆነ መልኩ እንኳ ያከብሩ እንደነበር መረጃ የለም። 3ኛ፦ በቁርኣንና በሐዲሥ የሚገኝ፣ በሰለፎች የተፈፀመ ቢሆን ኖሮ ከላይ የዘረዘርኳቸው የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ ነው ብለው አይደመድሙም ነበር። አንዳቸውም በኦፊሴል ከመከበሩ በፊት በግል ወይም በማህበረሰብ ደረጃ ይከበር ነበር አላሉም። = የቴሌግራም ቻናል ፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
በዚህ እረፍት እንዲህ አይነት ውስጥ የሚነኩ በዲናችን ለመፅናት መሰረት የሆኑ ነገሮችን በማድመጥ እና ቂርአት በመቅራት ጊዜያችንን እናሳልፍ።
🎙«የሂዳያ ወጎች» ክፍል 1 🎥አድስ የፖድካስት ፕሮግራም 1- ቢላል ኢብኑ ረባሕ (7:18) 2- ሙስዓብ ኢብኑ ዑመይር (28:01) 3- የያሲር ቤተሰቦች (42:40) 4- ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ (59:00) 5- ኸባብ ኢብኑል አረት (1:25:18) 6- ኡሙ ሐቢባ ረምላ (1:57:06) √ የመዝጊያ ንግግር (2:17:19) የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1
✅ክረምቱን እንጠቀምበት! ➖➖➖➖➖➖➖➖ ..ክረምቱን ነፃ የሆናችሁ ተማሪዎችና መምህራን በምትችሉት አቅም ጊዜያችሁን ስለዲናችሁ በመማር አሳልፉት፡፡ ..የሚያስተምራችሁ ካጣችሁ በድምፅ የተለቀቁ ትምህርቶችን በማዳመጥ፣ ቁርኣን በመሐፈዝ፣ መፃህፍትን በማንበብ እራሳችንን እንለውጥ፡፡ ..ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያሳውቀዋል፡፡” ባይሆን የወላጆችን ሐቅ በማይጋፋ መልኩ መሆኑ እየተስተዋለ፡፡ ..ማስተማር የምትችሉ ደግሞ ያላችሁን በማካፈል ላይ ተጠመዱ፡፡ ..ቁርኣን በደንብ የያዘ እሱን ያስተምር ዛሬ ዛሬ ነብዩ ﷺ “ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው” ማለታቸውን ብዙዎቻችን ትኩረት ነፍገነዋል፡፡ ..አጫጭር የተውሒድ ኪታቦችን የቀራ ሰው ያንኑ ያካፍል ደዕዋ ማድረግ የሚችል በተለይም በገጠር አካባቢ አቅሙ በሚችለው ሰዎችን ያስተምር፡፡ ..ወላጆች ልጆቻችሁ ክረምቱን ባግባቡ እንዲጠቀሙ አግዙ የክረምት ትምህርት የሚሰጡ መድረሳዎች ካሉ ልጆቻችሁ፣ ታናናሽ ወንድምና እህቶቻችሁ እዚያ እንዲከታተሉ አድርጓቸው፡፡ ..አስተማሪዎች አመቱን ሙሉ እንደ ልብ የማታገኙት ሙስሊም እንዳለ አስባችሁ የተሻለ ጥረት ለማድረግ ተንቀሳቀሱ፡፡ነብዩ ﷺ “ወደ መልካም የሚያመላክት እንደሚተገብረው ሰው ነው” ማለታቸው ይታወስ፡፡ አላህ ሁላችንንም ያግዘን፡፡ ✍በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሃፊዘሁሏህ
✅ክረምቱን እንጠቀምበት! ➖➖➖➖➖➖➖➖ ..ክረምቱን ነፃ የሆናችሁ ተማሪዎችና መምህራን በምትችሉት አቅም ጊዜያችሁን ስለዲናችሁ በመማር አሳልፉት፡፡ ..የሚያስተምራችሁ ካጣችሁ በድምፅ የተለቀቁ ትምህርቶችን በማዳመጥ፣ ቁርኣን በመሐፈዝ፣ መፃህፍትን በማንበብ እራሳችንን እንለውጥ፡፡ ..ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያሳውቀዋል፡፡” ባይሆን የወላጆችን ሐቅ በማይጋፋ መልኩ መሆኑ እየተስተዋለ፡፡ ..ማስተማር የምትችሉ ደግሞ ያላችሁን በማካፈል ላይ ተጠመዱ፡፡ ..ቁርኣን በደንብ የያዘ እሱን ያስተምር ዛሬ ዛሬ ነብዩ ﷺ “ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው” ማለታቸውን ብዙዎቻችን ትኩረት ነፍገነዋል፡፡ ..አጫጭር የተውሒድ ኪታቦችን የቀራ ሰው ያንኑ ያካፍል ደዕዋ ማድረግ የሚችል በተለይም በገጠር አካባቢ አቅሙ በሚችለው ሰዎችን ያስተምር፡፡ ..ወላጆች ልጆቻችሁ ክረምቱን ባግባቡ እንዲጠቀሙ አግዙ የክረምት ትምህርት የሚሰጡ መድረሳዎች ካሉ ልጆቻችሁ፣ ታናናሽ ወንድምና እህቶቻችሁ እዚያ እንዲከታተሉ አድርጓቸው፡፡ ..አስተማሪዎች አመቱን ሙሉ እንደ ልብ የማታገኙት ሙስሊም እንዳለ አስባችሁ የተሻለ ጥረት ለማድረግ ተንቀሳቀሱ፡፡ነብዩ ﷺ “ወደ መልካም የሚያመላክት እንደሚተገብረው ሰው ነው” ማለታቸው ይታወስ፡፡ አላህ ሁላችንንም ያግዘን፡፡ ✍በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሃፊዘሁሏህ
без подписи
🔖 ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸዉ እንዲህ ይላሉ፦ يَقُول ابْن القَيّم "رحمه الله " إذا مَنع الله عَنك شَيئاً تُريده و تُحبه ، فتَح لَك بِحكمته ورَحمته أبوَاباً أخرَى هِي أنفَع لَك ! فَلا تَحزن و لا تَيأس وَكًن مُوقِناً لحكمَة الله وَ عَدله وَ رحمَتِه. «አላህ ከምትፈልገው እና ከምትወደው ነገር ቢከለክልህ በጥበቡ እና በእዝነቱ ሌሎች የሚጠቅሙህን በሮች ይከፍትልሃል! ስለዚህ አትዘን ወይም ተስፋ አትቁረጥ የአላህን ጥበብ፣ ፍትሀዊነት እና እዝነት እርግጠኛ ሁን።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ (( مَن تَركَ ثَلاثَ جُمَعٍ تَهاونًا بِها ، طَبعَ اللهُ على قَلبِه )) "ሶስት ጁሙዐዎችን በቸልተኝነት (ሳይሰግድ) ያሳለፈ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።" [አልአልባኒይ ሐሰኑን ሶሒሕ ብለውታል።] = የቴሌግራም ቻናል :- t.me/IbnuMunewor
✍ [ سنن يوم الجمعة ] قال فضيلة الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين - رحمه الله تعالى - : ➊ قراءة سورة الكهف . ➋ الإغتسال . ➌ السواك . ➍ الطيب . ➎ التبكير إليها، أن يبكر حين تطلع الشمس . ➏ أن يلبس الإنسان أحسن ثيابه التي عنده سواء كان جديداً أم غسيلاً . ➐ يتحرى الدعاء لأن في الجمعة ساعة لا يوافقها عبد مسلم يسأل الله شيئاً وهو قائم يصلي إلا أعطاه إياه . ➑ أن يكثر من الصلاة على النبي ﷺ . ( لقاء الباب المفتوح، 105). = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu
ዳዕዋ ላይ ስትሰማራ አቃቂር ይፈለግልሃል ! ያለ ብቻ ሳይሆን የሌለም ይለጠፍብሃል ! 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ ~ t.me/Darutewhide
ወላጆችህን ከቻልክ አቅምህ በሚፈቅደው አስደስታቸው። ካልሆነልህ ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የመከፋታቸው፣ የመጨነቃቸው፣ የመተከዛቸው ሰበብ አትሁን። "አይዟችሁ"፣ "ከጎናችሁ ነኝ" ማለት ቢቀር "አትስጉ፣ ደህና ነኝ" ማለት ልናሳጣቸው አይገባም። ሰርቶ ማገዝ፣ ከጎን መቆም ካቃተ፣ ፊትን ከመከስከስ፣ የሻከረ ቃል ከመናገር መቆጠብ ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል :- t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor
وفي الحديث يقول ﷺ: أخوف ما أخاف عليكم الشرك الأصغر فسئل عنه فقال: الرياء أخوف ما يخاف على الصالحين الشرك الأصغر؛ لأن الشرك الأكبر قد يعرفونه ولا يخفى عليهم، لكن الشرك الأصغر قد يُبتلى به الصالحون وهو الرياء في القراءة أو صلاة أو صوم أو حج أو غير هذا، فلهذا خافه النبي ﷺ عليهم فيجب الحذر منه! الشيخ: عبدالرزاق البدر حفظه اللّٰه
ረሱል 🕋 እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لَا يَتَمَنَّيَنَّ أَحَدُكُمُ الْمَوْتَ مِنْ ضُرٍّ أَصَابَهُ، فَإِنْ كَانَ لَا بُدَّ فَاعِلًا فَلْيَقُلِ : اللَّهُمَّ أَحْيِنِي مَا كَانَتِ الْحَيَاةُ خَيْرًا لِي، وَتَوَفَّنِي إِذَا كَانَتِ الْوَفَاةُ خَيْرًا لِي﴾ “ማናችሁም በገጠመው ጉዳት የተነሳ ሞትን እንዳይመኝ። ማድረጉ የማይቀር ከሆነ እንዲህ ይበል፦ አላህ ሆይ! ህይወት ለኔ መልካም እስከሆነች ድረስ አቆየኝ። ሞት ለኔ የተሻለ ከሆነ ደግሞ ውሰደኝ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5671