በን/ላ/ክ/ከ የወረዳ 07 ሙስሊም ወጣቶች ጀመዓ
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 21
- 1/48двое суток
- 24
- 1/72трое суток
- 25
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ፀጥተኛው መስዋዕትነት፡ ሌሎችን ለማስደሰት ስትል በዝምታ መቅለጥ ስኳር ራስን ለሌሎች ስለመሰዋት ጥልቅ የሆነ ትምህርት ታስተምረናለች፤ ጠዐሟን በሙሉ ለሻዩ ሰጥታ በዝምታ ትጠፋለች፤ በዚህም መልካሙ አሻራ እና ጣፋጩ ቃና በቋሚነት ይኖራል፤ሰዎችም ስኳሯን ረስተው ሻይዋን ያመሰግናሉ ፤ያደንቃሉ ፤ስኳራ ግን በዝምታ ተሰውራለች። ሁሉም በጎ ሥራ የሰዎችን ጭብጨባ አይፈልግም። ባለታላላቅ አእምሮዎችና ቅን ልቦች ምስጋናን ወይም ሙገሳን ሳይጠብቁ በሌሎች ሕይወት ውስጥ አዎንታዊ አሻራቸውን ማሳረፍን ይመርጣሉ።እስኪ እራሳችንን ብቻ አንውደድ፤ለሌሎችም መኖር እንልመድ፤በሀዲስ ውስጥ "የሰው መልካሙ ሰዎችን የጠቀመ ነው" ይላል። በጎ ሥራን ሥራ፣ መልካም አሻራንም አሳርፍ፤ የተከበረው ሥራህ ራሱ ስለ አንተ ይናገር።
📢 ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ ኢማም አሻፋዒይ መድረስ በክረምት ከጠዋት 3 ሰአት እሰከ 6 ሰአት ከመስከርም ወር ጀምሮ ከዐስር እስከ መግሪብ ለሚማሩ ተማሪዎች ቁርኣን እና መሰረታዊ የዲን እውቀትን ማስተማር የሚችል ብቁ ኡስታዝን መቅጠር ይፈልጋል። 📌 ዝርዝር መረጃዎች የስራ መደብ፦ ኡስታዝ ተፈላጊ መስፈርት፦ መሰረታዊ የዲን እውቀት ያለው እና ማስተማር የሚችል ጾታ፦ ወንድ ብዛት፦ 1 (አንድ) የስራ ሰዓት፦ በክረምት ከጠዋት 3 ሰአት እሰከ 6 ሰአት ከመስከረም ወር ጀምሮ ከዐስር እስከ መግሪብ ደሞዝ፦ በመድረሳው ስኬል መሰረት (በስምምነት) 📍አድራሻ ከጎተራ ዝቅ ብሎ ቡና ቦርድ ጀረባ ሰኔ ዘጠኝ አንደኝ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ 📞 እንዴት ማመልከት ይቻላል? አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች በመደወል መመዝገብ እና ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። 📱 09 44 74 88 63 📱 09 12 60 57 71 ማስታወቂያውን ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ።
🕌 || የጁሙዓ ኹጥባ 🏷 በደል! ከትልቅ እስከ ትንሹ 🗓 || ጁሙዓ ዐ1/12/2018 ▸ አማርኛውን ለማድመጥ -> 2:46 ---------------------------------- ▸ በኡስታዝ ዐብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ ---------------------------------- ▸ @assualihin ▸ @menhajadama
без подписи
የጁምዐ ኹጥባ አማርኛው 6:13 ላይ ይጀምራል
ኢንሻአላህ የጁምዐ ኹጥባ በኡስታዝ ዐብዱልዋሲዕ ሸኽ ነስሮ ይሆናል።
https://www.facebook.com/share/1Bz6Fy33Si/
"ሴኩላሪዝም አልጠራልንም። ሴኩላሪዝም Atheism (ሀይማኖት የለሽነት) የሚመስላቸው አሉ። አንድ ተማሪ አልሐምዱሊላህ ሲል ሴኩላሪዝም የተጣሰ የሚመስላቸው አሉ። በምሳ ሰዓት አንድ ተማሪ ሶላት ልስገድ ሲል ልምን አትሰግድም ይባላል። ምን አገባው? ይህ እኮ ሰብዓዊ መብቴ ነው።" - አልዩ ሰዒድ (በፌደራል መጅሊስ የትምህርት ክፍል ዳይሬክተር) ከበር አውልቀነው የምንገባው ሀይማኖት የለንም። ሴኩላሪዝም የትምህርት ስርዓቱን ከሐይማኖት ተፅዕኖ ነፃ ያወጣል እንጅ፤ በሴኩላሪዝም ስም እኛ ከሀይማኖት ነፃ እንድንሆን አንገደድም። ለሁላችንም የሚሆን ቻለንጅ፦ መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZSXwfPJ2n/ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት አድርጉ። ይህ ለጥያቄ አለን ትውልድ ቀላሉ ሀላፊነት ነው። ወደ ተግባር ! ! ! @aaumsu
የ'ነባርና መጤ' የታሪክ ስህተት‼ =================== «እምነቶቹ እንግዶች ናቸው፤ እኛ ግን የአገሩ ባለቤቶች ነን!» → አሕመዲን ጀበል || ✍️ በኢትዮጵያ የፖለቲካና የማህበራዊ መስተጋብር መድረክ ላይ አልፎ አልፎ የሚስተጋባ፣ የሀገሪቱን ታሪክ ካለማወቅ ወይም እውነታውን ሆን ብሎ ከመካድ የሚመነጭ አንድ በጣም አስገራሚ ትረካ አለ። እርሱም፦ "ክርስቲያኑ ነባርና የአገሪቱ ብቸኛ ባለቤት፣ ሙስሊሙ ደግሞ በጊዜ ሂደት የገባ መጤ ነው" የሚለው አደገኛና የተሳሳተ ድምዳሜ ነው። 🔗 ይህንን የታሪክ መዛባት፣ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ካስቀመጣቸው እውነታዎች እና ከሎጂካዊ የታሪክ ትንተና አንፃር እንደ አንድ ሙስሊም በሚከተለው ሚዛናዊና ጠንካራ መረጃ መሞገት እንችላለን። 1⃣ መሠረታዊው እውነት፦ ሀገር ከእምነቶች በፊት ነበረች! 🎀 ማንኛውም የታሪክ ተማሪ ሊገነዘበው የሚገባው ቀዳሚ እውነት ቢኖር፦ እምነቶች ከመምጣታቸው በፊት በዚች ምድር ላይ ሀገርና ህዝብ ነበሩ። ኢትዮጵያዊያን ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ እምነቶችን በእንግድነት ተቀብለዋል። የአይሁድ እምነት፣ ክርስትና፣ እስልምና፣ ካቶሊክ፣ እንዲሁም ፕሮቴስታንት ሁሉም ከመካከለኛው ምስራቅና ከአውሮፓ የመጡ "እንግዶች" ናቸው። እምነቶቹን ያመጡት መምህራን መጤዎች ነበሩ፤ እምነቶቹን ተቀብለው የኖሩት ግን እዚሁ ምድር ላይ የነበሩ ነባር ኢትዮጵያውያን ናቸው። 2⃣ የክርስትና "መጤ" ሰባኪያን ታሪክ: 🎀 ክርስትና ወደ አገራችን የገባው በነባር ኢትዮጵያውያን ጥረት ሳይሆን ከመካከለኛው ምስራቅ በመጡ ስደተኞችና መምህራን አማካኝነት ነው፦ ☑ ፍሪምናጦስ (አባ ሰላማ/ከሳቴ ብርሃን)፦ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ330 E.C. በስደት ወደ አክሱም የመጣ የሶሪያ ተወላጅ ወጣት ነበር። እምነቱን የሰበከውና የአክሱሙን ንጉሥ ኢዛናን ያጠመቀው እርሱ ነው። ☑ ዘጠኙ ቅዱሳን፦ በአምስተኛው ክፍለ ዘመን (በ451 E.C. ከተደረገው የቻልኬዶን ጉባዔ በኋላ) ከሮማ ግዛትና ከመካከለኛው ምስራቅ በሃይማኖታዊ ስደት ተሰደው ወደ አክሱም የመጡ የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ። እነ አባ አፍጼ፣ አባ ገሪማ፣ አባ ሊቃኖስና አባ ዘሚካኤል አረጋዊ ለአጠቃላዩ የሰሜን ህዝብ ክርስትናን የሰበኩ "መጤ" ስደተኞች ነበሩ [6]. (ምንጭ፦ AAU, Institute of Ethiopian Studies, Dictionary of Ethiopian Biography, 1975, Pp. 209-210) [6]. ⬇️እነዚህ ታላላቅ የክርስትና መምህራን ወደ አገራቸው ስለመመለሳቸው ምንም ዓይነት የታሪክ መረጃ የለም። እዚሁ ምድር ላይ ቀርተው ከህዝቡ ጋር ተዋህደዋል። 3⃣ የእስልምና "እንግዶች" እና የታሪክ ምጸት (The Paradox): 🎀 እስልምና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ክርስትና ወደ አክሱም በገባ በ285 ዓመታት ልዩነት ውስጥ (በ615 E.C.) በነቢያዊው ሂጅራ አማካኝነት ነው። ከመካ የመጡት የነቢያችን ﷺ ሶሐቦች በሰሜን ኢትዮጵያ በስደት እንዲቀመጡ ተፈቀደላቸው። እዚህ ላይ ነው ትልቁና ወሳኙ የታሪክ እውነት የሚመጣው፦ ☑ ወደ አክሱም የመጡት እነዚያ የነቢያችን ሰሐቦች በሀገሪቱ የኖሩት ለ15 ዓመታት ብቻ ነው። ረሱል ﷺ በመዲና የእስልምናን መንግስት ሲመሰርቱ፣ ሁሉም ሰሐቦች ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በዚሁ በሞት ተለይተው በትግራይ (ነጃሺ) ከተቀበሩት ጥቂት ሰሐቦች ውጪ፣ አንዱም የውጭ አገር ስደተኛ እዚህ ሀገር ውስጥ አልቀረም [1, 2]。 ✒️ ይህ ምን ማለት ነው? ሰሐቦቹ ሄደዋል፤ እስልምናን ተቀብለው ያስቀጠሉት ግን 100% ነባር የነበሩ፣ ከዚያ በፊት ክርስትናን ወይም የአይሁድ እምነትን ይከተሉ የነበሩ ነባር ኢትዮጵያውያን ናቸው። ታላቁ የታሪክ ምጸት (Paradox) እዚህ ላይ ነው፦ የእስልምናን እምነት ያመጡት መምህራን (ሰሐቦች) ሙሉ በሙሉ ወደ አገራቸው ተመልሰው፣ እምነቱ የቀጠለው በነባር ኢትዮጵያውያን ደም ሆኖ ሳለ [1, 2]፤ በሌላ በኩል ግን እምነቱን ያመጡት የውጭ አገር መምህራን (ዘጠኙ ቅዱሳንና ፍሪምናጦስ) ሳይመለሱ እዚሁ ምድር ላይ ቀርተው እያለ [6]፣ ዛሬ ላይ ቆሞ ሙስሊሙን "መጤ" ክርስቲያኑን "ነባር" አድርጎ ለመሳል መሞከር ፍፁም የታሪክ ድንቁርና ነው። 4⃣ የጋራ አገራችንን በጋራ እኩልነት እንገንባ! 🎀 እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፣ አባቶቻችን በ615 G.C. የመካ ስደተኞችን (ሶሐቦችን) በነፃነት ተቀብለው ጥገኝነት በመስጠታቸው እንደምንኮራው ሁሉ፤ የአይሁድ እምነት ተከታዮችንና የክርስቲያን ስደተኞችን (ነገስታቱና ህዝቡ) በእንግድነት ተቀብለው እምነታቸውን እንዲሰብኩ በመፍቀዳቸውም እንኮራለን። ይህ የጋራ አገራዊ ክብራችንና እንግዳ ተቀባይነታችን ማሳያ እሴታችን ነው። ስለዚህ፦ ☑ ማንም በዚህ ምድር ላይ "የበለጠ ነባር" ወይም "ባለቤት" የለም። ☑ማንም በዚህ ምድር ላይ "የበታች መጤ" ወይም "እንግዳ" የለም። ሀገራችን የሁላችንም ናት! ዛሬም ይህችን ሀገር በጋራ መገንባት የምንችለው የጎንዮሽ ንትርክንና ኋላ ቀር የ"ነባርና መጤ" የድንቁርና ጨዋታዎችን ትተን፣ እኩልነት የሰፈነባት፣ ሁላችንንም በምትመስልና በእኩልነት በምትወክል መንገድ በጋራ መገንባት ስንችል ብቻ ነው። ያሻቸውን የስም ማጥፋት ዘመቻ (አክራሪ፣ አይ ኤስ፣ ወሃቢያ) ቢለጥፉብን፣ እውነቱ ግን አይለወጥም፤ እኛ አገራችንን እኩል ለማድረግ ከመታገል ወደ ኋላ አንልም! ቸር እንሰንብት! || t.me/MuradTadesse
🕌 || የጁሙዓ ኹጥባ 🏷 መልካም ስነ ምግባር በኢስላም 🗓 || ጁሙዓ 26/10/2018 ▸ አማርኛውን ለማድመጥ -> 4:21 ---------------------------------- ▸ በኡስታዝ ዐብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ ---------------------------------- ▸ @assualihin ▸ @menhajadama
⏳ ብዙዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ታላቅ ብስራት... የጥበብ እና የእውቀት ማዕድ ተዘርግቷል! ሁላችሁም ስትጠይቁን የነበረው የታላቁ ዓሊም ዶ/ር ሼኽ ሙሐመድ ሀሚዲን የቁርኣን ተፍሲር ፕሮግራም በቅርብ ቀን በደዕዋ ቲቪ የዩቲዩብ ቻናላል ወደ እናንተ በተከታታይ ሊደርስ ነው! መንፈስን ለሚያድሰው እና እውቀትን ለሚያሰፋው ለዚህ ልዩ ፕሮግራም ራስዎን ያዘጋጁ። ቆይታችሁን በዳዕዋ ቲቪ (Daewa TV) የዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ያድርጉ። 📢 ይህን ኸይር ስራ አሁኑኑ ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያዳርሱ! ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ይጠብቁን! #DaewaTV #Tafsir #DrSheikhMuhammedHamidin #ComingSoon #EthiopianMuslims °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook 📱Youtube 📱Telegram ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ
የሰዓታት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል ••• የዘመናዊውን ዓለም ግስጋሴ ከምናስበው በላይ ፈጣን ነው። ዛሬ ላይ ሰዎች የሚያደርጉት ትግል የመሬት ወይም የሀብት ትግል ብቻ አይደለም። ሰፊው ትግል የሰው ልጆች አዕምሮ የሚመራበትን መንገድ ወደ መቆጣጠር ዞሯል። ምን እናስብ?! ምንን እንደ እውነት እንቀበል?! ለምን ዋጋ እንስጥ?! ••• የሚሉትን ሁሉ የሚወስኑልን አካላት በዝተዋል። የዘመኑ የኃይል ማጠንጠኛም ይኼው ነው። የሰዎችን አስተሳሰብ መቆጣጠር!!! ስለዚህ እኛ እንደ ሙስሊም ፤ ብሎም እንደ ተማሪ የአዕምሮ ሚዛናችንን ከመበረዝ መጠበቅና እውነትን በጥልቀት የተረዳ ማንነትን መገንባት ይጠበቅብናል። ያ ሳይሆን ከቀረ የዘመናዊው ቅኝ ግዛት ሰለባዎች መሆናችን አይቀሬ ነው። ጀመዓችንም የዚህን ጉዳይ አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዛሬ ከምሽቱ 03:00 ጀምሮ "critical thinking" በሚል ርዕስ በዚሁ በቻናላችን በኩል በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ስልጠና አዘጋጅቶላችኋል። ይህንን ስልጠና እንደ መንደርደሪያነት በመውሰድ በመጪዎቹ ሳምንታት ደግሞ እንደነ ፌሚኒዝም ባሉ የተለያዩ መጤ አስተሳሰቦች ላይ ስልጠናዎችን የምናዘጋጅ ይሆናል። ስልጠናውን የሚሰጥልንም ተወዳጁ የሀሩን ሚዲያ ጋዜጠኛና ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ቦታዎች የካበተ ልምድ ያለው የሚዲያ ባለሙያ ወንድም አብዱረሒም አሚን ነው። በዚህ አስተዋይ ማንነትን ለመገንባት በሚደረግ ስልጠና ላይ ተሳታፊ በመሆን፤ ዘመኑን የሚመጥን በቂ የአዕምሮ ስንቅን ይያዙ! @AAU6kilojemea
2) ከእውነታው በታች የመቆጠር፦ አንዳንድ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከአኗኗር ዘይቤያቸው፥ ከአሰፋፈራቸውና ከሚኖሩበት መልከዓምድር የተነሳ አልያም ሆነ ተብለው ሳይቆጠሩ ተዘለው፥ ቆጣሪዎች በሚሰሩት ሸፍጥ ወይንም ስለቆጠራው ዓላማና ጥቅም ካለመረዳት ቆጠራውን በስጋት በማየት ራሳቸው ያነሰ መረጃ በመስጠታቸው የተነሳ ከእውነታው በታች ሊቆጠሩ ይችላሉ። 3) ከእውነታው የበለጠ መቆጠር፦ በተቃራኒው አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለሕዝብና ቤት ቆጠራ ጥቅም በመረዳታቸው ከፍ ያለ ቤተሰብ ሲያስመዘግቡ አልያም ቆጣሪዎቹ የሚፈልጉትን የሕብረተሰብ ክፍል መረጃ ከፍ አድርገው በመሙላታቸው የተነሳ ከእውነታቸው ከፍ ባለደረጃ ሊቆጠሩ ይችላሉ። 4) የቆጠራ ዉጤት መረጃን በአግባቡ ካለመጠበቅ የሚመጣ የዉጤት መዛባት፦ ቆጠራው ተጠናቆ ካበቃ በኋላ ማንኛውም የቆጠራውን ዉጤት ማግኘት የቻለ አካል ሆነ ብሎ ዉጤቶቹን በማዛባት በቆጠራው ከተገኘው የተለየ ዉጤት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል። 5)ከእምነትና ግንዛቤ ማጣት የሚፈጠር የዉጤት መዛባት፦ ሕዝቡ የቆጣሪውን አካል ማንነትና አሰራር ላይ እምነት ከማጣት አልያም ስለቆጠራው በቂ ግንዛቤ ካለመያዝ የተነሳ ተገቢው መልኩ ባለመቆጠር የዉጤት መዛባት ሊፈጠር ይችላል። 6) ቴክኖኖጂያዊ ጉዳዮች፦ ለቆጠራው በተግባር ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂ ለጥቃትና ለማጭበርበር የተጋለጠ በመሆኑ የተነሳ በቆጠራው ላይ ልዩ ፍላጎት ያላቸው አካላት በቴክኖሎጂው ላይ ያለውን ከፍተት በመጠቀም የቆጠራውን ዉጤትን ሊያዛቡ ይችላሉ። 7) የቋንቋ እና የባህል ክፍተት የሚፈጥረው የዉጤት መዛባት፦ ለቆጠራ የሚሰማሩ አካላት የሚቆጥሩትን ሕብዝ ቋንቋ እና ባህል አለማወቃው በቆጠራቸው ትክክለኛ መረጃ መሰብሰብ እንዳይችሉ በማድረግ አጠቃላይ ቆጠራው ትክክለኛ ዉጤት እንዳይኖረው ሊያደርግ ይችላል። 8) የሪሶርስ ወይም የበጀት እጥረት የሚፈጥረው የዉጤት መዛባት፦ ለየሕዝብና ቤት ቆጠራ ባለስልጣን ወይም ለተወሰኑ አከባቢዎች ቆጠራ ከአከባቢው የቆዳ ስፋት፥የሕዝብ አሰፋፈር፥ የአየር ሁኔታ፥ መልከዓ ምድርና የቆጠራ ጊዜ ጋር የማይመጣጠን ወይም በቂ በጀት፥ሀብትና የሰው ኋይል አለመመደብ በቆጠራው ዉጤት ላይ ተጽዕኖ ያሳርፋል። 9) የቆጠራው ወቅትና መርሃግብር ችግር፦- የሕዝብና ቤት ቆጠራ ጊዜ ህብረተሰቡ ጠቃሚ ወይም ወሳኝ አድርጎ ከሚያያቸው ሌሎች ሁነቶች፥በዓላት፥የጾም ጊዜ፥ የምርት አጨዳ፥ ወይም ሌላ መሰል ጊዜ ጋር በተመሳሳይ ወቅት በሚሆንበት ሁኔታ ሁሉም የህብተሰብ ክፍል ለቆጠራው ቅድሚያ ባለመስጠት በሚፈጠር ክፍተት የተነሳ ትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ሊደረግ ይችላል። 10) የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት፦ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች የሕዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤትን ለእነርሱ ፍላጎት አላማ ማሳኪያ እንዲሆን በመሻት የቆጠራው ዉጤት እንዲዛባ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህም በቆጠራው ዉጤት ከፍ ብሎ ወይም አንሶ እንዲታይ የሚፈልጉትን የህብረተሰብ ክፍል ዉጤትን ሊያሳድጉ ወይም ሊያሳንሱ የሚችሉ የቆጠራ ስልቶችን በመጠቀም፥ከበቂ በላይ ወይም በታች ቆጣሪዎችን በመመደብና መሰል ተግባራትን በመፈጸም አልያም ከቆጠራው መጠናቀቅ በኋላ ዉጤቱን በሚፈልጉት መልኩ በመቀየር ዉጤቱን ሊያዛቡ ይችላሉ። እና ምን ይደረግ? ✅✅✅✅✅ 1) ትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ እንዲደረግ መንግስት ለሃይማኖት ተቋማት፥ ለጎሳ መሪዎች፥ተሰሚነት ላለቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ትኩረት በመስጠት በጀት በመመደብ የሕብረሰቡ ንቃተ ሕሊና እንዲያድግ መሥራት ይገባዋል። 2) ለአርብቶ አደር አከባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፥በቂ የሰው ኋይልና በጀት በመመደብ ትክክለኛ ቆጠራ ሊደረግ ይገባል። 3) ሰፊ የቆዳ ስፋት ላላቸው ክልሎች፥ዞኖችና ወረዳዎች ከስፋታቸው ጋር የሚመጣጠን የሰው ኋይልና በጀት ሊመደብ ይገባል። 4) በሕዝብና ቤት ቆጠራ ላይ ሁሉም ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ቆጣሪዎች እንዲሳፉ የማድረግ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ለየአከባቢዎቹ የአከባቢውን ቋንቋ፥ባህልና ስነ-ልቦና የሚያውቁ ቆጣሪዎች ሊመደቡ ይገባል። 5) ቆጠራው የሚቆጠረው አከባቢ ሕዝብ ትክክለኛ መረጃ ስለመመዝገቡ ማጣራት እንዲችል የቆጠራው መረጃ መመዝገብ ያለበት ተቆጣሪው ሕዝብ በሚናገረው ቋንቋ ሊሆን ይገባል። 6) ከቆጠራው እቅድ፥ዝግጅትና ሂደት ጭምር በፌደራል፥በክልል፥ዞንና ወረዳ፥ከተማ በሕዝብና ቤት ቆጠራ መሥሪያ ቤት ከተለያየ ኋይማኖት ተከታዮች ወኪሎች እንዲሳተፉ ማድረግ። 7) የህዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት ከቆጠራ በፊት የህብረተሰቡን ንቃተ ሕሊናን ማሳደግ በሚችል መልኩ ስለቆጠራው አስፈላጊነት በሁሉም መልኩ ተገቢ ትምህርት መስጠት ይገባል። 8) ከቆጠራው ጊዜ ቆጣሪዎች ትክክለኛ መረጃ መቀበል ስለመቻላቸው ማረጋገጥ የሚቻልበት፥ ቅሬታም የሚቀርቡበት ስርዓት ማዘጋጀትና መረጃዎቹ ዳግም በቅሬታና ለአጥኚዎች ክፍት ሊሆን የሚችልበትን ስርዓት መዘርጋት። 🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒 እስከዛሬ ለማሰናከል በመንገዳችን ላይ የተለያዩ አጀንዳዎችን እየወረወሩ ከመስመር ለማውጣት ብዙ ደክመዋል።ዛሬም አጀንዳዎችችንና ምድባችን አንለቅም።ጉዞው ይቀጥላል። ለማንኛውም የኔን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ ፈጥናችሁ አድርጉ። ሊንኩ ከታች በአስተያየት መስጫው ላይ ተቀምጧል።👇 💢💢💢💢💢💢💢💢💢 ከኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተወሰደ
"ሿሿ" የተሠራው የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ብዛት 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ ዝም ብሎ በወረቀት ላይ የሚሰፈር የቁጥር ጉዳይ አይደለም፤ የህልውና፣ የፍትህ እና እኩል የመታየት ጥያቄ ነው። ማኅበረሰቡ የ1999 ዓ.ል. (እ.ኤ.አ የ2007ቱን) ቆጠራ በሙሉ ልቡ ያልተቀበለበት በርካታ ምክንያቶች አሉት። "ሙስሊሞች ብዙ የሚመስሉት ሂጃብ ስለሚያደርጉ ነው" 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 የ1999 የሕዝብ ቆጠራ ዉጤት የሕዝበ ሙስሊሙ ቁጥርን ሆነ ተብሎ የማሳነስ ሸፍጥ ሥራ የተሠራበት ነው።አንዳንዶቹ ያፈጠጡና ያገጡ ነበሩ። ለምሳሌ በወቅቱ በሕዝበ ሙስሊሙ ልሂቃን፣ሚዲያዊችና ጥቂት ሙስሊም ባለ ስልጣናት ዘንድ ተቃውሞና ትችት አስተናግደው ነበር። የቆጠራው ሪፖርት በሁሉም ስፍራ የሙስሊሙን ቁጥር ዝቅ አድርጎ ቢያቀርብም በተለይ ደግሞ የሙስሊሞች ቁጠር በኦሮሚያ ክልል 47. 5%(አርባ ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ)፣ ቤኒሻንጉል ክልል 45.4%(አርባ አምስት ነጥብ አራት በመቶ)፣አዲስ አበባ ከተማ 16. 2%(አስራ ስድስት ነጥብ ሁለት በመቶ) ፣አማራ ክልል 17.2%(አስራ ሰባት ነጥብ ሁለት በመቶ) ፣ ደቡብ ክልል(ሳይከፋፈል) 14. 1%(አስራ አራት ነጥብ አንድ በመቶ) ፣ትግራይ ክልል 4%( አራት በመቶ) እንደሆነ ተደርጎ መቅረቡ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮ ነበር። ለተናሳው የሕዝበ ሙስሊም ተቃውሞ የያኔዋ የስታስቲክስ ባለስልጣን አመራር ሙስሊሞች ከቆጠራው ሪፖርት ይልቅ መሬት ላይ ብዙ መስለው የሚታዩት ሂጃብ ስለሚያደርጉ ነው የሚል አስቂኝ ምላሽ ሰጥተውም ነበር። 1999ኙ የሕዝብና ቤት ቆጠራ በክልል ደረጃ ብቻ ሳይሆን ሙስሊም የሚበዛባቸውን ዞኖች፣ከተሞችና ወረዳዎችን ጭምር የሙስሊሞችን ቁጥር አሳንሶ በማቅረብ በመጨረሻም በኢትዮጵያ የሙስሊሞች ከሀገሪቱ ሕዝቦች መካከል 33. 8%(ሰላሳ ሦስት ነጥብ ስምንት በመቶ) አድርጎ አቅርቧል። የቆጠራ ውጤቱ መዘዝ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ቆጠራው የማኅበረሰቡን ትክክለኛ ገጽታና ስፋት ከማሳየት ይልቅ፣ በፖለቲካ ፍላጎት ተጠምዝዞ የሙስሊሙን ቁጥር ሆን ተብሎ ከእውነታው አሳንሶ ለማሳየት የተሰራ ስህተት እንደነበር በጽኑ ያምናል። ይህ ደግሞ በሀገር፣ በክልልና በወረዳ አስተዳደሮች ውስጥ ልናገኝ የሚገባንን ተሳትፎ እና ፍትሃዊ ውክልና ነፍጎናል። የዚህ የተዛባ ቆጠራ አደጋ አንዴ ተከስቶ የሚያበቃ አልነበረም። የቆጠራ ውጤት ቢያንስ ለአስር ዓመታት የሀገርን ሀብትና በጀት ለመከፋፈል የሚያገለግል በመሆኑ፣ በሙስሊሙ አብላጫ አካባቢዎች ሊሰሩ የሚገባቸው መንገዶች፣ ልጆቻችን የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች፣ እና እናቶቻችን የሚታከሙባቸው የጤና ተቋማት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እንዲታለፉ አድርጓል። ከምንም በላይ ደግሞ፣ አምልኳችንን የምንፈፅምበት መስጊድ እና የምናርፍበት የመቃብር ቦታ ለማግኘት ስንጠይቅ "በአካባቢው ያላችሁ ቁጥር አነስተኛ ነው" በሚል ሰበብ ማኅበረሰቡ በገዛ ሀገሩ መብቱን እንዲገፋና የባህልና የቋንቋ ተጽዕኖ እንዲደርስበት ትልቅ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው የቆጠራው ሂደት ግልጽነት ስለጎደለው ነው። የማኅበረሰቡን ቋንቋና ባህል የማያውቁ ቆጣሪዎችን በማሰማራት፣ መረጃዎችን በመደበቅ፣ እንዲሁም ሰፊ መልክዓ ምድር ላይ የሚኖረውን አርብቶ አደር ሙስሊም በበቂ ሁኔታ በጀትና የሰው ሀይል ሳይመደብለት ከቆጠራ ውጭ እንዲሆን ተደርጓል። ዛሬ ላይ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄ ግልጽና ቀጥተኛ ነው፤ አሁን የምንፈልገው ሌላውን የሚጎዳ ሳይሆን ሁላችንም በሀገራችን እኩል የምንታይበት፣ የሃይማኖት አባቶችና የማኅበረሰብ መሪዎች በታዛቢነት የሚሳተፉበት፣ ከማንኛውም የፖለቲካ ጫና ነፃ የሆነ፣ እና እውነተኛ ገጽታችንን የሚያሳይ ፍትሃዊ ቆጠራ እንዲካሄድልን ነው። እኛ እኩል መቆጠር የምንፈልገው ሀገራችንን በእኩልነት ለመገንባት ነው። ትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ማካሄድ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ነው። የሚከተሉትን ነጥቦችን በማየት የአጀንዳውን አስፈላጊነትን መረዳት ይቻላል።እነርሱም፦ 1) የሕዝብ ብዛትን ይወስናል፦ በትክክል ያልተቆጠረ የሕብረተሰብ ክፍል ከእውነታቸው ጋር በሚቃረን መልኩ የሕዝቡ ብዛት አንሶ ወይንም በዝቶ ሊገለጽ ይችላል፤ ይህም የትኛው ህዝብ ብዙሃን የትኛው ህዝብ አናሳ ተብሎ እንደሚበየን ይወስናል። 2) ተገቢ ያልሆነ ዉክልና፦ የሕዝብ ቁጥር መዛባት አንድ የሕብረተሰብ ክፍል በመንግስት ተቋማት፥በየደረጃው ባሉ የክልል፥የዞን፥የወረዳና የከተማ ምክርቤቶች በተመራጭ ዉክልናው መጠን ላይ ከተገቢው በታች የመወከል አልያም ከተገቢው በላይ የመወከል ሁኔታን ሊፈጠር ይችላል። 3) የሕዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት በመሆኑ መንግስት ምን ዓይነት ፖሊሲ መከተል እንዳለበት በመወሰን አንድን የሕብረተሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ ሌላውን ተጎጂ ያደርጋል። 4) ቆጠራው ለ10 እና ከዚያ በላይ ዓመታት የሚደረግ በመሆኑ አንድ ጊዜ የሚደረግ ቆጠራ የሕብረተሰቡን የሕዝብ እድገት መጠን ለመተንበይ አገልግሎት ላይ የሚዉል በመሆኑ በቆጠራውና በቀጣይ በሚኖረው ትንበያ መሠረት የበጀት ክፍፍል፥ የጤና፥የትምህርትና ሌሎች ወሳኝ ተቋማት ግንባታ አስፈላጊነት፥አዲስ ወረዳ ወይም ቀበሌ ይዋቀር የሚለውን ጉዳይ ለመወሰን የሕዝብ ቁጥር ከግምት የሚገባ በመሆኑ የቆጠራው መዛባት ጉዳቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ሳይሆን ዓመታትን የሚሻገር ነው። 5) የቆጠራ ዉጤት ክህዝብ ብዛት ባሻገር ስለ የገቢ ምንጭና ድህነት፥ እድሜ፥የትምህርት ደረጃ፥ የሥራ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን የሚያካትት በመሆኑ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ልዩ ተጠቃሚ አልያም ተጎጂ የማድረግ እድሉ ከፍተኛ ነው። 6) የህዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት ላይ ተንተርሰው ከሚታቀዱት ነገሮች መካከል የመንገድ ግንባታ፥ የትራንስፖርት ስምሪት፥የቤቶች ግንባታ፥የከተማ ፈጠራ፥የከተማ ደረጃ ምደባ፥የኤልክትሪክና የስልክ መስመር ዝርጋታ ወዘተ ይጠቀሳሉ። የተሳሳተ ቆጠራ ዉጤት ላይ በመንተራስ ለአንድ አከባቢ ሕዝብ ዝቅተኛ መሠረተ ልማቶች ለሌላው ደግሞ ከፍያለ መሠረተ ልማት እንዲታቀድና እንዲሰራ ያደርጋል። 7) ለሃይማኖት ተቋማት የቦታ አሰጣጥ ላይ የወጡ መመሪያዎች የሃይማኖቱ ተከታዮች የቦታ ጥያቄ በቀረበበት አከባቢ ምን ያክል ብዛት ያላቸው የሃይማኖት ተከታዮች አሉ? የሚለውን በዋነ መስፈርት የሚጠቀም በመሆኑ የአንድ ሃይማኖት ተከታይ ወደኖች ለእምነት ተቋማት የሚሰጣቸውን የመሬት አቅርቦት መጠን ይወስናል። 8) የሕዝብ ቆጠራ ዉጤት መዛባት የአንድን ዞን፥ወረዳ ወይም ከተማ አብዛኛው ሕዝብ የየትኛው ቋንቋ ተናጋሪ እንደሆነ ለማወቅና የትኛው ቀንቋ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ለመሰን የሕዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት አገልግሎት ላይ የሚዉል በመሆኑ በቆጠራው አንሶ የተቆጠረው የሕብረተሰብ ክፍል ሲጎዳ ቁጥሩ ከፍ ብሎ በቆጠራው የታየውን የሕብረተሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ ያደርጋል። የተሳሳተ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ምክንያቶች 🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒 1) ያልተሟና ትክክለኛ ያልሆነ የመረጃ አሰባሰብ፦ ቆጠራው በአቆጣጠር ስልት ችግር፥ ብቃት የሌላቸው ቆጣሪዎች፥እና ሌሎች ምክንያቶች ትክክለኛና ሙሉ መረጃ ባለመሰባሰብ የቆጠራ ዉጤት ሊዛባ ይችላል።
ነገ ኢንሻአላህ ጀርመን አደባባይ የመን ኮሚኒቲ መስጂድ የጁምኣ ኹጥባ አለን
без подписи
без подписи
እነኝህ ከኢስላም ጠልነት የመነጩ ጭቆናና መድሎዎችን ሕዝበ ሙስሊሙ እያስተናገደ የዘለቀው ስለመብት እንጂ ከጥላቻ በመነሳት በተለያዩ መልኩ በደል የሚፈጽሙትን የሚቀጣ ህግ የለም።በተደጋጋሚ ወደ ፍርድ ቤት ያመሩ ጉዳዮች ብይናቸው "መብታችሁ ነው።ይህን ማድረግ አይችሉም" በሚል ላይ የሚወሰን ነው።ብይኑ ሆነ ብሎ ከጥላቻ የተነሳ ያን ሁሉ በደልና ጭቆና ያደረሱ አካላትን በዝምታ ይልፋል። ምክንያቱም የኢስላም ጠልነትን የሚከለክል ህግ ባለመኖሩ ኢስላምና ሙስሊም ጠሎቹ በድርጊታቸው የመቀጠል እድል አገኙ። በመሆኑም በሀገራዊ ምክክር ላይ የኢስላምና ሙስሊም ጠልነት ጉዳይ በሚገባ ተነስቶ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል። መፍትሄው ምንድነው? 📶📶📶📶📶📶📶 መፍትሄውን ተግባራዊ ለማድረግ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሲቪክ ማህበራትና በዲጂታል ሚዲያ ተደራጅቶ መብቱን በንቃትና በህጋዊ መንገድ ማስከበር ይኖርበታል። የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣትም በትምህርት ስርአቱና በታሪክ መጽሀፍት ውስጥ የተዛቡ ውክላናዎችን የሚያስተካክሉ ስልታዊ ይዘቶችን ማካተት ወሳኝ እርምጃ ነው። በስተመጨረሻም፣ ይህንን ስር የሰደደ ጥላቻ በህግ መዋጋት የዜጎችን እኩልነት በማረጋገጥ የፍትሃዊነት ሜዳውን ሙሉ በሙሉ ያስተካክላል። 1) ኢስላም ጠልነት በኢትዮጵያ ዉስጥ ከጥንት ጀምሮ በአስተሳሰብ፥በአሰራር፥ በፖሊሲ፥ በታሪክ ትርክት፥በኢማጅኔሽን፥ በአሰራር፥ወዘተ በሚገለጽ በኢትዮጵያ ዉስጥ እንደነበር በግልጽ መተማመን ላይ እንዲደረስ ማድረግ። 2) ኢስላም ጠልነት በሙስሊሞች ዘርፈ ብዙ ችግሮችንና የመብት ጥሰቶችን፥መገለሎችንና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ብዙ ጉዳት እየፈጠረ መሆኑን በተጨባጭ ማስረጃ መተማመን ላይ መድረስ። 3) የየትኛውም የመንግስት መዋቅር፣ ሕዝባዊ እና ማህበሰባዊ ተቋማት አሰራር፥ፖሊሲዎችና ባለድርሻዎች ከሙስሊም ጠልነት ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕግና ስርዓት በመዘርጋት ከኢስላም ጥላቻ የጸዳ ሕዝብና መንግስት መኖሩን ማረጋገጥ። 4) ሙስሊሙ በትምህርት፣በሥራ በቅጥር ፣ግልጋሎትን በሚያገኝበት ወቅትና ባጠቃላይ በአደባባይ ህይወቱ መድልዎ እንዳያጋጥመው ማድረግ፡፡ ሃይማኖት ተኮር የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል ጥሰቱን በሚፈጽሙት አካላት ላይ ቅጣት የሚያሳልፍና ለመብቱ ጥበቃ ለማድረግ የሙስሊም ጠልነት ልዩ ድጋጌ ማስወጣት። 5) ሙስሊሙ አናሳ ሆኖ በሚኖርበትና በየትኛውም አካባቢ ባለው የግል ሕይወት ከትንኮሳ፣ ከዘለፋና ከጥቃት የተጠበቀ እንዲሆን ማስቻል። 6) ሙስሊሙ በታሪክ ድርሳናት፣ በኪነ-ጥበብ ስፍራዎች፣ በኦፊሴላዊ ንግግሮች (ወዘተ) (misrepresent) አለመሆኑን ማረጋገጥ። 7) እንደሀገርና ሕዝብ ሙስሊም-ጠል ዘይቤያዊና ባህላዊ አባባሎችን መዋጋት። 8) ሙስሊም-ጠልነትን በህገ-መንግስት እውቅና እዲሰጠው ማድረግ። 9) ሙስሊሞችን ከሃይማኖት ዝንባሌያቸው በመነሳት “ጨዋ”፣ “ነባር”፣ “ ጥሩ’’ ወይንም “አክራሪ”፣ “ፀንፈኛ” ወዘተ በማለት ፈርጆ የማሸማቀቅን አካሄድ ማስቀረት። 10) የእስልምና ጥላቻ ክልከላን በሕግ ማስቆም ማለት የጨዋታ ሜዳውን ወደ አጥቂዎቹ ማዞር እንደሆነ ማሳመን ያስፈልጋል። ።።።።።።።።።። አህመዲን ጀበል #ኢስላም_ጠልነት #ሙስሊም_ጠልነት #ኢትዮጵያ #መዋቅራዊ_መድልዎ #የመብት_ጥሰት #እኩልነት #የታሪክ_ትርክት #ተቋማዊ_መድልዎ #የጥላቻ_ንግግር #የሀገራዊ_ምክክር #የመስጂዶች_ጥቃት #የፍትህ_ስርዓት #ሂጃብ #ሃይማኖታዊ_እኩልነት #ማህበራዊ_ፍትህ #ፀረ_ኢስላም_ጠልነት #የዜጎች_መብት #የአመለካከት_ለውጥ #ከጥላቻ_የጸዳ_ማህበረሰብ #ህጋዊ_ከለላ #ኢስላሞፎቢያ #ማህበራዊ_መከፋፈል #የተዛባ_ውክልና #የሃይማኖት_ነጻነት #ስልታዊ_ጫና #የስራ_ዕድል_መድልዎ #የሀገር_ሰላም #የሲቪክ_ማህበራት #ዲጂታል_ሚዲያ #የታሪክ_እውነት #ሙስሊሞች #ኢስላም #ሀገራዊ_ምክክር #የሙስሊሞች_ጥያቄዎች #ኢትዮጵያዊነት #የጋራ_መፍትሄ #ፍትህና_እኩልነት #የኢትዮጵያ_ሙስሊሞች #ብሄራዊ_ውይይት #መብትና_ግዴታ #የሃይማኖት_እኩልነት #MariBiyyoolessaa #GaaffiiMuslimootaa #MariifiNagaa #EenyummaaFiMirga #HaqaaFiWalqixxummaa #MuslimootaItoophiyaa #FurmaataWaliinii #SagaleeMuslimootaa #Tokkummaa. #NationalDialogueEthiopia #EthiopianMuslims #NationalConsensus #ሀገራዊምክክር #ReligiousEquality
።።።።።። ይነበብ።።። ኢስላም-ጠልነትን እውቅና ሰጥቶ መዋጋት ⛔⛔⛔⛔⛔⛔⛔⛔⛔⛔⛔⛔ ኢስላም(ሙስሊም) -ጠልነት በሀገራችን በታሪክ ትርክት፣ በመንግስት መዋቅራትና በህብረተሰባዊ ጉድኝቶች ውስጥ በተደጋጋሚ እራሱን እየገለፀ በህዝባችን ላይ ሁለንተናዊ የሆነ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል። የኢስላም ጠልነት በሀገራችን መኖሩ ግልጽ ቢሆንም ጉዳዬ ነው በማለት በትኩረት ላልተመለከተ ሰው የማህበራዊ ሚዲያ ዘመን ላይ በመሆናች ላስተዋለ ሰው ዘወትር ራሱን በገሃድ እየገለጸ የምናየው እውነታ ነው።ሌላው ቢቀር በዚህ ጽሁፍና በሌሎች በዚህ ገጽ በሚለጠፉ ጽሁፎች ላይ ኢስላምንና ሙስሊሞችን አስመልክቶ የሚሰጡ ጥቂት የጥላቻ አስተያዮችን መመልከት ብቻ በቂ ነው። ይህንን የጥላቻ አዝማሚያ ገጦ እየታየ እንደሌለ በዝምታ ማለፍ ማህበራዊ መከፋፈልን ከማስፋቱም በላይ የተተኪውን ትውልድ የእኩልነት ተስፋ ሙሉ በሙሉ ያጨልማል። ችግሩን በግልጽ አውጥቶ መወያየትና መጋፈጥ ተራ የፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን፣ የሀገሪቱን ሰላምና መዋቅራዊ አንድነት ለመጠበቅ የሚደረግ የህልውና ጉዳይ ነው። ስለዚህ በጥላቻ ላይ የተገነቡ ትረካዎችን በምክንያታዊና በእውቀት ላይ በተመሰረቱ ስራዎች ማፍረስ የሁላችንም ቀዳሚ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል። የሙስሊም ጠልነት 8ቱ መገለጫዎች ⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕ የኢስላም ጠልነት ስልታዊ መገለጫዎች ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሀገሩ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የባህል ተጠቃሚነቱ ላይ እኩል ድርሻ እንዳይኖረው ለማድረግ የሚቀረጹ ረቂቅ መሰናክሎች ናቸው። ማህበረሰቡን ከታሪካዊ አበርክቶው ነጥሎ እንደ ስጋት ብቻ መፈረጅ፣ ተቋማዊ መድልዎ በህጋዊ መንገድ እንዲቀጥል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። በመሆኑም እነዚህን ሰባት መርዛማ መገለጫዎች በትክክለኛ መረጃና በንቃት መለየት ለትግሉ መነሻ መሰረት ነው። 1) ሙስሊሞችን መጤ አድርጎ በማየት፣ በጥላቻ እና በንቀት፣ መብትን በመጣስ፣ በማግለልና በመድልዎ የሚገልጽ ነው። ለምሳሌ ለአንድ ሙስሊም ዜጋ ሙስሊም በመሆኑ ብቻ በታሪክና በማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ እንደ "መጤ" ወይም የውጭ ሀገር ሰው አድርጎ መመልከት። 2) ሙስሊሞችንና የኢስላምን ጉዳይ ሁልጊዜ እንደ ብሔራዊ ደህንነት ስጋት አድርጎ መቁጠር። ለምሳሌ፦ የሙስሊሙን የመብት ጥያቀፀዎችን ወይም ሐይማኖታዊ ስብሰባዎችን ያለምንም በቂ ምክንያትና ማስረጃ ሁልጊዜ እንደ "የሀገር ደህንነት ስጋት" ፈርጆ በጥርጣሬ መከታተል። 3) ሙስሊሞች አናሳ በሆኑበት አካባቢ ጥቃት፣ ስድብ፣ ንቀትና የተሳሳተ ውክልና (በታሪክ፣ በአርት ወዘተ) ማድረስ። ለምሳሌ፦ በፊልሞች፣ በቲያትር፣ድራማ ወይም በታሪክ መጽሐፍት ላይ የሙስሊም ገጸ-ባህሪያትን ሁልጊዜ ያልተማሩ፣ ኋላ ቀር ወይም አገልጋይ አድርጎ መሳል። በቀላሉ የኢትዮጽያ ፊልምና ድራማ የሙስሊም ገጸ ባህሪ ድርሻ "ሸምሱ ሱቅ" እድርጎ በተመልካች አዕምሮ ላይ መሳል። 4) ሙስሊም ጠልነትን መሠረት አድርጎ እውቀትን ወደ ሀገር ማስገባት። ለምሳሌ፦ የእስልምናን ታሪክ በጦርነትና በትርምስ ብቻ አዛብተው የሚያሳዩ ምዕራባውያን ወይም የውጭ ሀገር የትምህርት መጽሐፍትን በቀጥታ በስራ ላይ ማዋል።ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለን በኬነዲ ቤተ መጽሐፍት ስለኢስላም አሉታዊና በጥላቻ የተሞሉ መፅሀፍት ብቻ መሙላቱን ታዝበን ነበር።በጊዜው ካነሳናቸው ጥያቄዎች አንዱ በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው አቀረብን። በመጨረሻም የነዚያ መጽሀፍት ተቃራኒ የሆኑ መጽሐፍትን ገዝተን ወደ ቤተመጽሐፍቱ እንዲገቡ አደረግን። በሙስሊሞች ታሪክና ወቅታዊ ጉዳይ ላይም በጥላቻ የተሞላውን የሀጋይ ኤርሊችን መጽሐፍ ብቻ ተቃራኒ እይታዎችን በመተው ወደ ሀገር ማስገባትና መጠቀምም የዚሁ አካል ነው። 5) ሙስሊሞችን "ጥሩ ሙስሊም እና "መጥፎ ሙስሊሞች"፣ "ነባርና መጤ" የሚለው ክፍፍል ራሱ የኢስላሞፎቢያ(የኢስላም ጠልነት) አካል ነው። ለምሳሌ፦ ሕጋዊ መብቱንና እኩልነቱን የጠየቀን ሙስሊም "አክራሪ/መጥፎ"፣ መብቱ ተገፎ ዝም ያለውን ደግሞ "ጥሩ ሙስሊም" በማለት መፈረጅ። 6) አድሏዊ አባባሎች፦ "ኢስላም ሀገሩ መካ፣ አሞራ ሀገሩ ዋርካ" እና መሰል አባባሎች ከጥንተ እስከ አሁን ዘመን ሙስሊም ባልሆነው ከፊል ሕዝብ ዘንድ በስፋት መጠቀም። ለምሳሌ፦ በማህበረሰቡ ውስጥ "ኢስላም ሀገሩ መካ፣ አሞራ ሀገሩ ዋርካ" የሚሉና ሙስሊሙን ከሀገሩ ታሪክና ባለቤትነት የሚያገሉ አባባሎችን በዕለት ተዕለት ንግግር መጠቀም።ይህ የኢስላም ጠልነት በ21 ክፍለ ዘመን ጭምር ቀጥሎ ሙስሊሙን አረብ አደርጎ በማየት ወደ አረብ ሀገር ሂዱ።ቁርኣን ለአረቡም ሆነ ለመላ ሙስሊም ያዘዘውን ኢስላማዊ አለባበስን ጭምር የአረቦች ብሎ መፈረጅን ያጠቃልላል። 7) የሙስሊም ጥናቶች ሙስሊሞችን አቅም በሚገድብ መልኩ የተቀረጹ መሆናቸው (ሙስሊሞች የሚጠኑት አመጋገባቸው እንጂ ታሪካቸው አለመሆኑ)። ለምሳሌ፦ አካዳሚያዊ ምርምሮች የሙስሊሙን ታላቅ ሀገራዊና ፖለቲካዊ አበርክቶ ትተው፣ ስለ አመጋገባቸው ወይም ስለ አለባበስ ባህላቸው ብቻ በትናንሽ ርዕሶች ላይ ማተኮራቸው። የበዓል የሚዲያ ዝግጅቶች ብዙ ጊዜ ስለ ሙስሊሞች የሀገር አስተዋጽኦ ሳይሆን ስለምግብ አሰራራቸው፣ በአርትም የሆነ አከባቢን በጅግነት ያወድስና ሙስሊም ጋር ሲደርስ ስለታሪኩ ሳይሆን ስለሀብቱ(ቡና፣ማር፣ወዘተ) ተብሎ ይገለፃል። 8) መስጂዶችና ኢማሞች ኢላማ መደረግ ፦ የኢስላም ጠልነት በሀገራችን ስር ሰዶ መገኘት አይነተኛ መገለጫው ሊታፈሩና ሊከበሩ የሚገባቸው መስጂዶችና የመስጂድ ኢማሞች ጥቃቶች ናቸው። ለዚህ አይነተኛ ማሳያው ባለፉት ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ መስጂዶች መቃጠል፣ዛሬም ድረስ የቀጠለው የኢማሞች ግድያዎች ናቸው። የኢስላም ጠልነቱ ጫፍ መድረሱን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሞጣ ላይ ተቀርጾ እንዳየነው መስጂድ አቃጥለው ከበው በደስታ ሲጨፍሩ መታየቱ ነው። በከተሞችም ቢሆን ሙስሊሞች መስጂድ ለመሥራት ቦታ ለማግኘት እየከፈሉ ያሉት ዋጋ ቀላል አይደለም። በህጋዊ መንገድ መንግስት ፈቅዶ እንኳ " በሰፈራችን እንዴት መስጂድ ይሰራል?" የሚሉ አካላት ፈተና ራሱ ሌላኛው የከተማ የኢስላም ጠልነት ማሳያዎች ናቸው። የሚገርመው የፍትህ ስርዓቱ ራሱ በኢስላም ጠልነት ሰለባ መሆኑ ማሳያ የነዚያ ከኢስላም ጠልነት የመነጩ የመስጂዶች ቃጠሎና ጥቃቶች፣ የኢማሞች እና የምዕመናን ግድያ፣ የኢስላምና የነቢዩ ሙሐመድ(ሰዐወ) በአደባባይ መሰደብ አንዱም እንኳ የህግ አካል ተከታትሎ ለሕግ ሳያቀርብ መቅረቱ ነው።ይህም የሀገሪቱን ፖሊስና ሌሎች የፍትህ አካላት በእጅጉ እንድንታዘብ አድርጎናል። የጸረኢስላም ጠልነት አዋጅ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ሙስሊም ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚደርስባቸው ስልታዊ ጫና እና እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉ ትላልቅ ተቋማት ውስጥ ጭምር ዛሬ ድረስ ሙስሊም ሴቶች በማንነታቸውና በሂጃባቸው ምክንያት የሥራ ዕድል መከልከላቸው የመዋቅራዊ መድልዎ ግልጽ ማሳያ ነው። ተቋማቱ ሙስሊሙን ማህበረሰብ እንደ ደንበኛና አገልግሎት ተቀባይ በደስታ እየተቀበሉ፣ እንደ ሠራተኛ ግን በየትኛውም የሥራ መደብ ማንነቱን ገፍተው ለማግለል ራሳቸው የጻፏቸውን መመሪያዎች እንደ ሰበብ ይጠቀማሉ። ይህ ዓይነቱ ድርብ ስታንዳርድ ኢስላም ጠልነት የወለደው እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?