tgindex
የማ/መ/ወ/ቅ/ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ካቴድራል አክሊለ ምክሕነ ሰ/ት/ቤት ገጽ

የማ/መ/ወ/ቅ/ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ካቴድራል አክሊለ ምክሕነ ሰ/ት/ቤት ገጽ

Статистика

ይህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአ/አ/ሀ/ስ/የማ/መ/ወ/ቅ/ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ካቴድራል የአክሊለ ምክሕነ ሰ/ት/ቤት የቴሌግራም ገጽ ነው።

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
265
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
212
20 постов
Вовлечённость
80,0%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
111
1/48двое суток
127
1/72трое суток
137

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የምሕረት አዋጅ ሊታወጅ 15 ዓመታት ሲቀሩት፣ በአምላክ ቅዱስ ፈቃድ መካኒቱ ሀና በብሥራተ መልአክ በ5485 ዓ.ዓ ነሐሴ 7 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጸነሰች። ያች ድንግል የተጸነሰችባት ሰዓትና ዕለት ምንኛ የተባረከችና የተቀደሰች ናት! ​የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከትና አማላጅነት አይለየን፤ አሜን!"

  • видео или голосовое, без подписи

  • ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለእግዝትነ ማርያም በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች። የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄምና ሃና ይባላሉ። እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፡- ኢያቄም:- "አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ፤ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች። እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ ሃናም አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ (ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፤ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም "7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ" አየሁ አላት፤ ሃናም እኔም አየሁ አለችው ምን አየሽ ቢላት "ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ" አለች። ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡ እነሱም እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡፡ ምልጃዋ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን፡፡

  • አስቸኳይ መልእክት 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 የደብረ ታቦር ድራማ የሚሰሩ አባላት 🔔🔔🔔🔔🔔🔔 1.ተመስገን ዘውዴ 2. ሰለሞን በቀለ 3.ብሩክ ደጀኔ 4. መላኩ አሻግሬ 5.ጌትነት አለሙ 6.ጸጋዘአብ ከበደ 7. ሲሳይ አበራ 8 ተካልኝ አበራ 9. ሚኪያስ ሚደቅሳ 10.ሮዛ ሹምበዛ 11. ፍቅርተ ብስራት 12. ሀብታሙ ተሰማ 13. ስንታየሁ ዘርዶ 14. ፀጋነህ ከበደ      ስማችሁ ከላይ የተጠቀሰ አባላት በተደጋጋሚ ጥሪ መገኘት አልቻላችሁም ያሉን ቀናት ጥቂት ስለሆኑ  ዛሬ ረቡዕ ምሽት 12:00 ጀምሮ እንድትገኙ እናሳስባለን

  • видео или голосовое, без подписи

  • የፍልሰታ ጾም አስተባባሪዎች ስም ዝርዝር

  • የማ/መ/ወ/ቅ/ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ካቴድራል አክሊለ ምክሕነ ሰ/ት/ቤት ገጽ pinned «🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 ሰላም ተወዳጆች እንደምን ናችሁ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ በዚህ የጾም ወቅት በወጣላችሁ ስም መሰረት በቤተ መቅደስም (ልብሰ ስብሀት በመልበስ) ሆነ በአዳራሽ በሚደረጉ መርሀ ግብራት ላይ በመገኘት እንድታስተባብሩ እያሳሰብን ህፃናቱ ረቡዕ እና አርብ ቤተመቅደስ የተቀሩትን ቀናት በአዳራሽ የሚሆኑ ይሆናል በዚህም መሠረት በ4,5,7,11,12 እና በ14 አዳራሽ እንድትገኙ የተቀሩትን…»

  • 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 ሰላም ተወዳጆች እንደምን ናችሁ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ በዚህ የጾም ወቅት በወጣላችሁ ስም መሰረት በቤተ መቅደስም (ልብሰ ስብሀት በመልበስ) ሆነ በአዳራሽ በሚደረጉ መርሀ ግብራት ላይ በመገኘት እንድታስተባብሩ እያሳሰብን ህፃናቱ ረቡዕ እና አርብ ቤተመቅደስ የተቀሩትን ቀናት በአዳራሽ የሚሆኑ ይሆናል በዚህም መሠረት በ4,5,7,11,12 እና በ14 አዳራሽ እንድትገኙ የተቀሩትን ቀናት በቤተመቅደሱ በመገኘት እንድታስተባብሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን የተባረከና የተቀደሰ ጾም ያድርግልን"

  • 6 авг.161из AAsundayschool

    “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

  • 6 авг.150из AAsundayschool

    видео или голосовое, без подписи

  • የሀዘን ማስታወቂያ የሰ/ት/ት ቤታችን ወጣት አባል የሆነው ኪሩቤል ሰለሞን የባለቤቱ(የሚስቱ) አባት ከዚህ አለም ድካም ስላረፉ ነገ በቀን 30/11/2018 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 በመልዕልተ አድባራት ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት ልብሰ ስብሀት በመልበስ እንድናስቀብር እና ሀዘንተኞቹን እንድናፅናና እናሳስባለን ። አክሊለ ምክሕነ ሰ/ት/ቤት እግዚአብሔር አምላክ የአባታችንን ነብስ እንዲምርልንና ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናትን ይሰጥልን ዘንድ ትመኛለች ።

  • Check out አክሊለ ምክሕነ ሰ/ት/ቤት ዘወይብላ's video! #TikTok https://vm.tiktok.com/ZS4ASwNYk/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

  • видео или голосовое, без подписи

  • 2 авг.225из hassukyb

    видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 2 авг.218из hassukyb

    видео или голосовое, без подписи

የማ/መ/ወ/ቅ/ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ካቴድራል አክሊለ ምክሕነ ሰ/ት/ቤት ገጽ — tgindex