tgindex
Werabe university muslim students union

Werabe university muslim students union

Статистика
@wrumsuОбразованиеанглийский

This is the official telegram channel of wrumsu. Email: wrumsu12@gmail.com twitter: http://twitter.com/wrumsu Telegram: @wrumsu

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14:02
Постов за неделю
1
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 438
−8 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,21%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 291
29 постов
Вовлечённость
89,8%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
368
1/48двое суток
421
1/72трое суток
454

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የ خلاصة نور اليقين ኪታብ record ምትፈልጉ ወንድሞች @Al_amin_022 እህቶች @R3Y1NN ላይ ማግኘት ትችላላችሁ

  • 9 авг.846134

    ﷽ ⭐ ትላንት ከተማርነው መካከል⭐ 👉ነብዩ ﷺ ለ ሁለተኛ ጊዜ ወደ ሻም ያደረጉት ጉዞ እድሚያቸው ሃያ አምስት ሲሞላ ለንግድ ወደ ሻም ሂደዋል እመቤት ኸዲጃ ሃብታም እና ምትከበር ሴት ነበረች በገንዘብ ሰው ቀጥራ ታሰራ ነበር እና ነብዩን ﷺ እውነተኝነት አደራ ጠባቂነት እና ጥሩ ስነ ምግባራቸው ስትሰማ እሳቸውን መረጠች እና ተስማምተው መይሰራ ከሚባለው አገልጋይዋ ጋር ለሳቸው ለመነገድ ወደ ሻም ተጓዙ እና ሁለት ወር ቆይተው በጣም ብዙ ትርፍ አትርፈው ተመለሱ. 👉ነብዩ ﷺ እመቤት ኸዲጃ ስለ ማግባታቸው ከ ሻም ከተመለሱ ቡሃላ ኸዲጃ በ ገንዘቧ ላይ ልዩ በረካ ባየችሰዓት እና የነብዩን ﷺ ባህሪ ከ አገልጋይዋ መይሰራ በነገራት ጊዜ ምንም እንኳን የ መካ ሹማምንት ጠይቀዋት እምቢ ብትልም ነብዩን ﷺ ግን እራሳቸው ጠይቀው አገባቻቸው. 👉እመቤት ኸዲጃም ከሳቸው በፊት አቢ ሃለህ ሚባል ሰው አግብታ ነበር. በትዳር ሃያ አምስት ዓመት አሳልፈዋል እሳቸው በሕይወት እያሉ ሌላ ሴት አላገቡም ነበር 👉ከ ኸዲጃ ቡሃላ ያገቧቸው ባለቤቶቻቸው 2..ሰውዳ ቢንት ዘምአ 3.አኢሻ ቢንት አቢበክር 4..ሃፍሳ ቢንት ዑመር  5.ዘይነብ ቢንት ኹዘይመህ 6.ረምላ ቢንት አቢ ሱፍያን 7.ጁወይሪያ ቢንት ሃሪሳ 8.መይሙና ቢንት ሃሪሳ 9.ሰፍያ ቢንት ሁየይ 10.ዘይነብ ቢንት ጀህሽ 11.ኡሙ ሰለማ   👉የወለዷቸው ልጆች ቃሲም. አብዱላህ. ዘይነብ. ኡሙ ኩልሱም. ፋጢማ. ሩቅያ(ከኸዲጃ) እና ኢብራህም(የ ማሪየቱል ቂብጥያ ልጅ ነዉ)ናቸው 👉ነብዩ  በሃጀረል አስወድ ምክንያት በቁረይሽ መሃከል ስለመፍረዳቸው ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እድሜያቸው ሰላሳአምስት ላይ እያሉ ነብይነት የካዕባ ሕንፃ በጎርፍ በመፍረሱ ምክንያት የቁረይሽ ጎሳዎች መልሰው ገነቡት ነገር ግን የተቀደሰውን ሐጀረል አስወድን ቦታው ላይ የመመለስ ሰዓት ሲደርስ የትኛው ጎሳ ይህንን ትልቅ ክብር ያግኝ በሚል በጎሳዎቹ መካከል ከፍተኛ አለመግባባትና ጭቅጭቅ ተፈጠረ ​በመጨረሻም በካዕባ በር መጀመሪያ የሚገባው ሰው ይፍረደን ብለው ተስማሙ በበሩ የመጀመሪያ ሆኖ የገቡት ነብዩ ﷺ ነበሩ እርሳቸውንም ሲያዩት ሁሉም በደስታ ታማኙ (አል-አሚን) መጣ  በእርሱ ፍርድ እንስማማለን  አሉ ​ነብዩም ﷺ የሚከተለውን ብልህና ፍትሐዊ መፍትሔ ሰጡ ​አንድ ኩታ(ጋቢ)እንዲመጣ አዘዙ ​ሐጀረል አስወድን በገዛ እጃቸው አንስተው ጨርቁ መሃል አደረጉት ​የእያንዳንዱ ጎሳ መሪዎች የጨርቁን ጫፍ እንዲይዙና በአንድነት ወደ ላይ እንዲያነሱት አደረጉ ​ድንጋዩ ወደ ተፈለገበት ቦታ ከተቃረበ በኋላ ነብዩ ﷺ በገዛ እጃቸው አንስተው ቦታው ላይ አስቀመጡት ​በዚህ  ፍርድ ምክንያት ሁሉም ተደሰቱ.       ❤️صلي الله عليه وسلم❤️

  • السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ዛሬ የአላህ ፍቃድ ከሆነ ዘወትር ቅዳሜ እና እሁድ በonline ከ መግሪብ ሰላት ቡሃላ (1:20) ሚቀራው የነብዩ ﷺ ታሪክ ኪታብ (خلاصة نور اليقين) ቂርዐታችን ዛሬም ይቀጥላል ኢንሻ አላህ .

  • 2 авг.1 168156

    ⭐ዛሬ ከተማርነው ትምህርት መካከል ⭐ ⭐የእናታቸው አሚና መሞት ነቢዩ (ﷺ) የ6 ዓመት ልጅ እያሉ እናታቸው አሚና ከመዲና(የ አባታቸውን ቀብር ለማየት ሂደው)ከ ጉዟቸው ወደ መካ ሲመለሱ በአብዋእ በተባለ ስፍራ አረፉ. ከዚያ በኋላ ከ አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ እና ሞግዚታቸው ኡሙ አይመን ጋር በመሆን ወደ መካ በመመለስ ከ አያታቸው ጋር አደጉ. ⭐የአያታቸው አብዱልሙጥጠሊብ መሞት 👉 እናታቸው ካረፉ በኋላ አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ የልጅ ልጃቸውን ከ ልጆቻቻው አስበልጠው በመውደድ በመንከባከብ እና ፍቅር በመስጠት እጅግ የተለየ ቦታ ሰጡዋቸው። 👉 ነቢዩ ﷺ የ8 ዓመት ልጅ እያሉ አያታቸው አብዱልሙጠሊብ አረፉ ይህም ለነቢዩ ﷺ ሌላኛው የሀዘን ምዕራፍ ነበር አያታቸው ከመሞታቸው በፊት ልጃቸውን አቡ-ጧሊብን ነቢዩን ﷺ እንዲንከባከብ በውክልና አስረከቡት. ይህ የታሪክ ክፍል የነቢዩን ﷺ የልጅነት ፈተናዎች አላህ ለሚወደው ነገር እያዘጋጀውን እንደነበር ያሳያል. أَلَمۡ يَجِدۡكَ يَتِيمٗا فَـَٔاوَىٰ የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል) 👉ፍየል ስለ መጠበቃቸው እና የመጀመሪያ ወደ ሻም ጉዞ ነብዩ ﷺበልጅነታቸው ለመካ ሰዎች ፍየልን ይጠብቁ እንደነበር እና በዚያ በሚያገኙት ገንዘብ አጎታቸውን በ ኢኮኖሚ ያግዙ ነበር. ከዛም እንድሜያቸው 9 ወይም 12 ሲሆን ለ መጀመሪያ ጊዜ ወደ ሻም ለንግድ እየተጓዙ እያለ. ቡስራ ሚባል አካባቢ ሲደርሱ በሂራ ሚባል መነኩሴ(ቄስ) ነብዩን አይቷቸው የ ወደፊት ነብይ መሆናቸውን ለ አጎታቸው ነግሯቸው እሳቸውን ካገኝዋቸው ሊገሏቸው ሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ እና ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ነግሯቸዋል.

  • ዛሬ በነበረው የ online ቂርዓት ላይ ለነበረው መቆራረጥ ታላቅ አፍወታን እንጠይቃለን.

  • 1 авг.1 135911

    ﷽ ⭐ነብያችን ﷺ ማናቸው? እሳቸው ለዓለማት እዝነት ተደርገው የተላኩት የመጨረሻው የአላህ ነብይ የነብያት ዲን የሆነውን እስልምና ይዘው የመጡ የመልእክተኞች አውራ ናቸው የዘር ሐረጋቸው ቁረይሽይ ሲሆኑ ከነቢዩላህ ኢስማዒል ዓለይሒሰላም ይዛመዳሉ. 👉 የዘር ሐረጋቸው እና የአባታቸው መሞት 🎯 ነቢዩና ሙሐመድ (ﷺ)  ቢን ዓብዱላህ - ቢን ዓብዱል ሙጥጠሊብ ( ስማቸው ሸይባ)- ቢን ሐሺም (የእሳቸው ስም ዓምር) - ቢን ዐብዲልመናፍ - ቢን ቁሰይ - ቢን ኪላብ - ቢን ሙራህ - ቢን ከዕብ - ቢን ሉአይ - ቢን ጋሊብ - ቢን ፊህር - ቢን ማሊክ - ቢን ነድር - ቢን ኪናናህ - ቢን ኹዘይማህ - ቢን ሙድሪካህ - ቢን ኢልያስ - ቢን ሙደር - ቢን ኒዛር - ቢን መዓድ-  ቢን ዓድናን። ከ እናታቸው አሚነህ ጋር በ አምስተኛው አያታቸው (ኪላብ) ጋር ይዛመዳሉ 🎯 አባታቸው ዐብዲላህ ነቢዩ ﷺ ከመወለዳቸው በፊት (አመዛኙ) በንግድ ጉዞ ላይ እያሉ መዲና ውስጥ አርፈዋል 👉ውልደታቸው 🎯 ውልደት የተወለዱት ጊዜ በዓመተ ፊል (የዝሆን ዓመት) በመካ ከተማ ነው የተወለዱበት እለት ሰኞ ለመሆኑም ሰሒህ ሀዲስ መጥቶበታል ቀኑ ምን ቀን ነበር የሚለው ላይ ልዩነቶች አሉ ረቢዓል አወል 3ተኛ 8ተኛ 10ኛ 12ተኛ ተብሏል ግን በእርግጠኝነት አይታወቅም. 👉የጥቢ እናቶቻቸው 🎯 የነቢያችን(ﷺ) የጥቢ እናቶች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው :- እናታቸው አሚና ቢንት ወህብ ሱወይበቱል አስለሚያህ እና ሃሊመቱ ሰዓድያህ አጥብተዋቸዋል .

  • 1 авг.1 02451

    አላህ ካለ ዛሬ ከ መግሪብ ሰላት ቡሃላ የ online ቂርዓታችን ሚቀጥል ይሆናል ኢንሻ አላህ

  • 26 июл.1 701131

    አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ በ online ምንቀራው ቂርዓት ዛሬም ይቀጥላል ትላንትና የቀራነው አብዛኛው ተማሪ ስላላዳመጠ ከ መጀመሪያ ጀምረን እንቀራለን ኢንሻ አላህ.

  • 25 июл.1 769419

    Share خلاصة نور اليقين الجزء الأول.pdf

  • 25 июл.1 6511

    አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ خلاصة نور اليقين ኪታብ ቂርአት ዛሬ ነዉ ምንጀምረው እና የ ኪታቡ hard copy የሌላችሁ በዚህ ተጠቀሙ

  • 24 июл.1 59136

    ✨የክረምት የኢልም ጉዞ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ ✨ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ​ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ እንዴት ናችሁ? ​ክረምት ሲመጣ ብዙ ጊዜ ጊዜያችንን እንዴት እንደምናሳልፍ ግራ ይገባናል። አንዳንዴም ጊዜያችን በከንቱ ያልፋል። በዚህ ጊዜ ግን አብረን እንድንጠቀምበት እና የነቢዩን ﷺ ሕይወት በቅርበት እያየን ኢማናችንን የምናድስበት የonline የደርስ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።🎉 ​በዚህ ክረምት «ዅላሰቱ ኑሪል የቂን» የተሰኘውን የሲራ ኪታብ አብረን እንቀራለን። አላማችን የነቢዩን ﷺ ታሪክ እየቀራን ከሕይወታቸው ትምህርት መውሰድ፣ ጊዜያችንን በኸይር የምናሳልፍበት መንገድ መፍጠር እና በጀማዓ ሆነን በዲን ላይ መበርታት ነው። ​ለዒልም ስንል የምናሳልፈው ጊዜ የቂያማ ቀን ትልቅ ስንቃችን ነውና፣ ሁላችሁም በዚህ የኸይር ስራ ላይ እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛለን።🎁 ✅ ደርሱ ሐምሌ 18 ይጀመራል! ​ፕሮግራማችን ​📖የኪታቡ ስም ፦ ዅላሰቱ ኑሪል የቂን ( خلاصة نور اليقين في سيرة سيد المرسلين) 📆​ቀናት፦ ቅዳሜ እና እሁድ ⏰​ሰዓት፦ ከመግሪብ (ከ1:10) እስከ ኢሻ ሶላት 📍​ቦታ፦ [https://t.me/wrumsu_discussion] ​📝 ምዝገባ ​የዚህ ፕሮግራም አካል ለመሆን እና አብረን ለመማር፣ መመዝገብ የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ/Username አሳውቁን። ​👉 ለመመዝገብ  ለሴቶች፦ [@R3Y1NN]                             ለወንዶች:-@Al_amin_022 ​አላህ የምንማረው እውቀት በተግባር የምንኖርበት ያድርግልን። ​የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ የዳዕዋ እና ኢርሻድ እስትራክቸር

  • 23 июл.1 25674

    السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ✨የዱንያም ይሁን የአኺራ ስኬታችን መሠረት የሆነውን የዲን እውቀት ለመቅሰም፣ ሐያእ፣ አዳብ እና መልካም ስነ-ምግባር የተላበሰች የሙስሊም ሴት ስብዕናን ለመገንባት ሁልጊዜም መትጋት ተቀዳሚ ሃላፊነታችን ነው። ​ ✨​በዚሁ መሠረት፤ መጪው ቅዳሜ በኦንላይን ከሚጀመረው «ኹላሰቱ ኑሪል የቂን » ኪታብ በተጨማሪ፤ ከእሱ ቀደም ብሎ በየሳምንቱ ጁምአ ማታ የሚቀራ በሴቶች ሕይወት ውስጥ አንገብጋቢነትና አስፈላጊነት ያለውን «አዳበል ሙስሊማት» ኪታብ አብረን ለመቅራት በአላህ ፈቃድ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። ✨ስለዚህ ዉድ እህቶቻችን ከዚህ የዒልም ማዕድ እንድትቋደሱ በክብር ተጋብዛቿል። ​💡 ማሳሰቢያ፦ የተከበረው ኪታብ በውጭ ገበያ ለማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ፣ እህቶቻችን ፒዲኤፉን (PDF) አውርዳችሁ በፕሪንት (Hard Copy) መልክ አዘጋጅታችሁ ብትይዙት ደርሱን በንባብ ለመከታተልና ማስታወሻ ለመያዝ እጅግ ምቹና የተሻለ ይሆናል! ​📌 የደርሱ ዝርዝር መግለጫ፡ ​ ​📖​የሚቀራው ኪታብ፦ አዳበል ሙስሊማት (آداب المسلمة) 📆​​ቀን፦ በየሳምንቱ ጁምአ ማታ ⏰​ሰዓት፦ ከመግሪብ ሶላት በኋላ ከ1፡10 እስከ ዒሻ ​📍ቦታ ​፦ WRU MUSLIM FEMALE STUDENTS      TELEGRAM GROUP NB:ወደ ግሩፑ ለመግባት ተወካይ እህቶችን ማናገር ትችላላችሁ @R3Y1NN ​ ​አላህ ቀልባችንን ለዕውቀት ክፍት ያድርግልን፤ የሚጠቅመውን አውቀን በሱ ከሚሠሩት ንጹህ ባሮቹም ያድርገን!🤲 የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ የዳዕዋና ኢርሻድ እስትራክቸር

  • 21 июл.1 497125

    ✨የክረምት የኢልም ጉዞ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ ✨ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ​ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ እንዴት ናችሁ? ​ክረምት ሲመጣ ብዙ ጊዜ ጊዜያችንን እንዴት እንደምናሳልፍ ግራ ይገባናል። አንዳንዴም ጊዜያችን በከንቱ ያልፋል። በዚህ ጊዜ ግን አብረን እንድንጠቀምበት እና የነቢዩን ﷺ ሕይወት በቅርበት እያየን ኢማናችንን የምናድስበት የonline የደርስ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።🎉 ​በዚህ ክረምት «ዅላሰቱ ኑሪል የቂን» የተሰኘውን የሲራ ኪታብ አብረን እንቀራለን። አላማችን የነቢዩን ﷺ ታሪክ እየቀራን ከሕይወታቸው ትምህርት መውሰድ፣ ጊዜያችንን በኸይር የምናሳልፍበት መንገድ መፍጠር እና በጀማዓ ሆነን በዲን ላይ መበርታት ነው። ​ለዒልም ስንል የምናሳልፈው ጊዜ የቂያማ ቀን ትልቅ ስንቃችን ነውና፣ ሁላችሁም በዚህ የኸይር ስራ ላይ እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛለን።🎁 ✅ ደርሱ ሐምሌ 18 ይጀመራል! ​ፕሮግራማችን ​📖የኪታቡ ስም ፦ ዅላሰቱ ኑሪል የቂን ( خلاصة نور اليقين في سيرة سيد المرسلين) 📆​ቀናት፦ ቅዳሜ እና እሁድ ⏰​ሰዓት፦ ከመግሪብ (ከ1:10) እስከ ኢሻ ሶላት 📍​ቦታ፦ [https://t.me/wrumsu_discussion] ​📝 ምዝገባ ​የዚህ ፕሮግራም አካል ለመሆን እና አብረን ለመማር፣ መመዝገብ የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ/Username አሳውቁን። ​👉 ለመመዝገብ ለሴቶች፦ [@R3Y1NN] ለወንዶች:-@Al_amin_022 ​አላህ የምንማረው እውቀት በተግባር የምንኖርበት ያድርግልን። ​የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ የዳዕዋ እና ኢርሻድ እስትራክቸር

  • 30 июн.2 7761512

    🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 FROM ACADEMIC STRUCTURE 💫 የምስራች ለወራቤ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ💫 السلم عليكم ورحمة الله وبركاته ✅ ተጀመረ ተጀመረ✅ 📚✨የክረምት ንባብ /Reading challenge📚 🗣የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሆይ! አላህ ሱብሀነ ወተዐላ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል:- اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ “አንብብ በዛ በፈጠረህ ጌታህ ስም…” (ሱረቱል ዓለቅ) እናማ እናንተስ ይህን የክረምት ዕረፍት ትርጉም ባለው መልኩ ማሳለፍ ይፈልጋሉ? ዕረፍቱን እንዲሁ በከንቱ አያሳልፉት! እውቀትዎን የሚያሳድጉበት፣ መንፈስዎን የሚያድሱበት እና ከጓደኞችዎ ጋር የሚወዳደሩበት ታላቁ የክረምት ንባብ ቻሌንጅ ተጀምሯል! 🧠💡 በእስልምና ታሪክ፣ በግል ብቃት ማሳደጊያ (Personal Development) ወይንም በሌሎች አለም አቀፍ የፅሁፍ ስራዎች ዲንን ተኮር የሆኑ በእስልምና ዙሪያ ማንበብ ለምትፈልጉ ሁሉ ይህ የክረምት ንባብ ቻሌንጅ የእናንተ ነው! 🌟 ለምን መሳተፍ አለብዎት? በዚህ challenge በመሳተፍ:- ➨የክረምቱን መዝናኛ ጊዜ ለቀጣይ የትምህርትና የህይወት ጉዞዎ መሰረት ወደሚጥል እውቀት ይቀይሩት። ➨ ከሌሎች የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በመገናኘት ሃሳብና እውቀት ይለዋወጡ። ➨የአካዳሚክ እውቀትዎን ከውስጥ ማንነት እና ከመንፈሳዊ ጥንካሬ ጋር አጣምረው ያሳድጉ። 📅 ንባቡ እንዴት ይሰራል? የመጽሐፍ ዝርዝር ፦ አዲሱ ንባብ ከመጀመሩ በፊት የሚያነቧቸውን መጻሕፍት እናንተን ውድ የጀመአችን ተማሪዎች የሚመጥኑ መፅሀፎች ተመርጠው ይለቀቃሉ። ✅ደረጃዎን ያሳውቁ፦ በየሳምንቱ 3-5 ቀናት 5-7 ገጽ ይለቅቃል 👉በአሸናፊነት ያጠናቁ:- በሳምንቱ መጨረሻ ለሚለቀቀው ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ በቅድሚያ የመለሱ 3 ተማሪዎች የሞባይል ካርድ ይሸለማሉ።በተደጋጋሚ ላሸነፈ እንዲሁም ልዩ ተሳትፎ ላደረገ አንድ ተማሪ እረፍት አልቆ ግቢ ከገባን ቡኋላ ልዩ ሽልማት ይኖረዋል። 🗣ማስታወሻ፦በሳምንቱ ካነበቡት ገፆች መሀከል አሪፍ የሚሉትን አንቀፅ በጥቅስ መልኩ የላኩ ተማሪዎች አሪፍ የሚባለው ተመርጦ የሳምንቱ ምርጥ ጥቅስ በመባል ይመረጣል። ታዲያ ይህን አጓጊ እና አስተማሪ መድረክ ለመሳተፍ አልጓጉምን?። ይህን ቻሌንጅ በመሳተፍ ጀመአችንን በእውቀት ወደ አንድ እርምጃ ከፍ እናድርግ 🚀 የንባብ ቻሌንጁን ለመቀላቀል ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ፦ 💬 https://t.me/wrumsqaa 💫💫 join በማለት ይህን ክረምት የማይረሳ እና የእውቀት ዘመን እናድርገው።

  • 29 июн.1 68121

    * “የሱንና ሐቅ በኛ ላይ”፣ እንዲሁም ሱንናን ለሚያስተባብሉ ሰዎች የተሰጠ ምላሽ * ትላንት እሁድ ሰኔ 22/2018 በሑዘይፋህ መስጂድ የቀረበ = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • 28 июн.884103из EHEMSU

    ታላቁ የቲክቶክ መድረክ ነገ ሰኞ ከምሽቱ 3:00 ላይ ነው! ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ታሪካዊ ዳራ፤ ሕጋዊ መሠረት እና አሁናዊ ሁኔታ ከመፍትሔ ጋር በጥልቀት ይዳሰሳል። የድምፃችን ይሰማው ታጋይ ሙባረክ አደም፤ ጠበቃው ሙስጠፋ ሺፋ፤ የንፅፅር መምህሩ የሕያ ኢብኑ ኑሕ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፀሐፊው ሁሴን ዩሱፍ በመድረኩ ላይ ሀሳቦቻቸውን ያንፀባርቃል። ፨ ፖስተሩን በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ፤ ፕሮፋይልም እናድርግ ፨ የዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች በቻናሎቻችሁ ላይ አጋሩ ፨ የሀይስኩል ጀመዓዎች መልዕክቱን አድርሱ ፨ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያላችሁ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕናዎች፤ ኡስታዞች እና ዳዒዎች መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ ሁሉም ተጋባዥ ነው። አጀንዳው የሁሉም ነውና ሁሉም ይገኝ። ተማሪ፣ የተማሪ ወላጅ፣ መምህር፣ የመንግስት ሰራተኛ ወዘተ ... ማንም እንዳይቀር። 🗓 ቀን፡ ሰኞ፣ ሰኔ 22 (Monday, 29 June) ⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት እውቀትን መፈለግ መብት ነው፤ እምነትንም በክብር መተግበር እንዲሁ! የቲክቶክ ገፃችንን Follow በማድረግ ዝግጅቱን ይጠብቁ፦ https://www.tiktok.com/@aaumsu ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! @EHEMSU

  • 28 июн.5073из aaumsu

    ታላቁ የቲክቶክ መድረክ ደረሰ _ ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ! ! ! ስለኒቃብ መጠየቅ በምርቃት ቀን እስከ ማሳሰር ከመድረሱ በፊት ጀምሮ ስላለው የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት ታሪካዊ ዳራ በሰፊው ይዳሰሳል። ሕገ- መንግስቱን ጥሰው ስለሚጥሱት መብት ሕጋዊ ቦታ በሰፊው ይተነተናል። ከእኛ ስለሚጠበቀው ነገርም በደንቡን ውይይት ይደረጋል። ሙባረክ አደም፦ በድምፃችን ይሰማ የመብት ትግል እንቅስቃሴ ፈርቀዳጅ ታጋይ፤ አክቲቪስት፤ ቲክቶከር፤ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕና፤ የሂባ ፋውንዴሽን መስራች ነው። ፕሮግራማችንን በመድረክ መሪነት የሚያስተናብርልን ይሆናል። ሙስጠፋ ሺፋ፦በድምፃችን ይሰማ የመብት ትግል እንቅስቃሴ ወቅት ለታሰሩት ጠበቃ ሆኖ አገልግሏል፤ አሁንም በጥብቃና ሙያው አንቱታን ካተረፉ ባለሙያዎች መካከል ነው። ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ሕጋዊ መሠረት ያብራራልናል። የሕያ ኢብኑ ኑሕ፦የንፅፅር ትምህርት መምህር፤ የሒዳያ ኢስላማዊ ማህበር መስራች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕና ነው። ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት ታሪካዊ ዳራ ያብራራልናል። ሁሴን ዩሱፍ፦የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፀሐፊ ሲሆን ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውን በዝርዝር ያስቀምጣል። መቅረት አይታሰብም። ጀመዓዎች በቻናሎቻችሁ ላይ አሰራጩት። ሁሉም ለሁሉም ያድርስ። በአንድነት በአንድ መድረክ ተሰባስበን ስለመብቶቻችን እውቀትን እንጨብጥ። 🗓 ቀን፡ ሰኞ፣ ሰኔ 22 (Monday, 29 June) ⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት እውቀትን መፈለግ መብት ነው፤ እምነትንም በክብር መተግበር እንዲሁ! የቲክቶክ ገፃችንን Follow በማድረግ ዝግጅቱን ይጠብቁ፦ https://www.tiktok.com/@aaumsu ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! @aaumsu

  • 28 июн.1 170456

    🏆 الله أكبر 🏆 ልክ እንደ አምናው ሁሉ የጊቢያችን ዋንጫ በሙስሊም ተመራቂ እጅ ገብቷል! 🎓🥇 ወንድማችን ጃፈር ሙሀመድ ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነርሲንግ ዲፓርትመንት 3.98 CGPA በማምጣት የወራቤ ዩንቨርስቲ የዋንጫ ተሸላሚ እና የማዕረግ ተመራቂ በመሆን አጠናቋል:: "وَمَن جَدَّ وَجَدَ" “የጣረ ያገኛል” እንኳን ደስ አለህ!!! 🏆 ألف مبروك 🏆 ✨

  • 28 июн.1 13956

    የዲን ተማሪ ባህሪ(ሲፋት) ይደመጥ በሚገባ ቋንቋ በተለይም ክረምት ላይ መድረሳ የምንገባ✋✋

  • 27 июн.1 891262

    🌙 ከወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዋና አሚር ✍️ አብዱልሀኪም ሙሰማ ለ2018 ዓ.ል ተመራቂ ተማሪዎች የተላለፈ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት 📜 በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ። ክቡራን ተመራቂ ተማሪዎች:- በዚህ ታላቅ እና ደማቅ ቀን ላይ በወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ስም እና በራሴ ስም ለሁላችሁም ከልብ የመነጨ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። ዛሬ የተመረቃችሁት የትምህርት ደረጃ ብቻ አይደለም፤ የስነምግባር፣ የትዕግስት፣ የእምነት እና የትግል ውጤት ነው። በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አላህን ታግሳችሁ፣ በዱዓ ተጠናክራችሁ እና በጥረታችሁ ዛሬ ወደዚህ ክብር ደርሳችኋል። አልሐምዱሊላህ! ውድ ተመራቂዎች፤ እስልምና ለሰው ልጅ የሕይወት ስርዓት ነው። ከመስጂድ ውስጥ የሚቀር ሀይማኖት ብቻ ሳይሆን ማህበረሰብን፣ ፍትሕን፣ እውቀትን፣ አመራርን እና ሰብዓዊነትን የሚመራ ሙሉ ስርዓት ነው። ዛሬ ዓለም በብዙ ችግሮች ውስጥ እየተዘፈቀች ነው፤ ፍትሕ ጠፍቷል፣ ሙስና በዝቷል፣ ወጣቶች ተስፋ እያጡ ነው። ይህን ሁሉ የሚያስተካክለው ግን ከእውቀት ጋር የተጣመረ ኢማን ነው። እናንተ ዛሬ የተመረቃችሁ ወጣቶች የኡማው ተስፋ ናችሁ። እስልምናን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የምታሳዩ ትውልድ መሆን አለባችሁ። የሙስሊም ወጣት ሲማር ለራሱ ስራ ብቻ አይዘጋጅም፤ ለዑማው ጥቅም፣ ለፍትሕ እና ለአላህ ደስታ ይዘጋጃል። ዛሬ የሙስሊሙ ዓለም ከብዙ አቅጣጫ ጫና ውስጥ ነው። በብዙ ቦታዎች ሙስሊሞች ፍትሕ እየተነፈጉ ነው፣ ወጣቶች ከዲናቸው ለማራቅ ብዙ ፈተናዎች እየተፈጠሩ ነው። ነገር ግን የተማረ፣ ዲኑን የጠበቀ እና ለእውነት የቆመ ወጣት ማንኛውንም ፈተና ማሸነፍ ይችላል። እኛ ሙስሊሞች ከምንም በፊት የምናስቀድመው ዲናችንን ነው። ከዘር በፊት እስልምናችንን ነው። ከግል ጥቅም በፊት የኡማውን ጥቅም ነው። እስልምና የፍትሕ ዲን ነው፤ ማንንም መበደል አያስተምርም፣ ማንንም መጥላት አያዝዝም። ነገር ግን በእውነት ላይ መቆምን፣ ለሐቅ መናገርን እና ፍትሕን መጠበቅን ያስተምራል። ዉድ ተመራቂዎች፤ ዛሬ የምትወጡት ወደ ቀላል ዓለም አይደለም። ግን አላህን የፈራ ሰው መንገዱ አይጠፋዉም። እውቀታችሁን ከተቅዋ ጋር አጣምሩ፣ ስኬታችሁን ከስነምግባር ጋር አስተሳስሩ፣ የተማራችሁትንም ለኡማው እና ለሀገራችሁ ጥቅም አውሉ። ነቢዩ ﷺ “ከሰዎች ሁሉ በላጩ ለሰዎች የሚጠቅም ነው” ብለዋል። ስለዚህ እውቀታችሁ ለማህበረሰብ ብርሃን ይሁን፣ ተግባራችሁ የእስልምና ውበት ይሁን። በመጨረሻ፤ ይህን ቀን እንድትደርሱ ዱዓ ላደረጉላችሁ ወላጆቻችሁ፣ በእውቀት ላሳደጉአችሁ መምህራን እና ከጎናችሁ ለነበሩ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል። አላህ እውቀታችሁን የሚጠቅም ያድርግላችሁ፣ ዲናችሁን ያጽናላችሁ፣ ለኡማው ክብር እና ለሀገራችሁ በረከት ያድርጋችሁ። እንኳን ደስ አላችሁ! አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ። ✍️አብዱልሀኪም ሙሰማ የወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዋና አሚር

Werabe university muslim students union — tgindex