- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 30
- 1/48двое суток
- 34
- 1/72трое суток
- 37
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ወዳጁ ነኝ ስትል ወዳጁ እንዳይሰማህ !
👉 ሰይደል አሪፊን ከመዋኢዛቸው(ምክራቸው ) መካከል ፦ ለአላህ ብለው የተዘያየሩ ወንድማማቾች በሊቃዕቸው ብዙ በረካ አላቸው ይላሉ ከነሱም ውስጥ 👉 ወንጀላቸው ይታበስላቸዋል 👉 የተበታተነው ርዝቃቸው ይሰበሰብላቸዋል 👉 አላህ ጀነትን ይወፍቃቸዋል 👉 አሏህ ውዴታውን ይሰጣቸዋል 👉 🤲 አሏሁመም ረሓም ሰይደል አሪፊን ‼
የረቢእ ድምቀት # 18 ሙስሊሞችን ማሰቃየት ✍የነብዩ የዳእዋ እንቅስቃሴ ይፋ በመሆኑ የተቆጡ ሙሽሪኮች ሙስሊሞችን ማሰቃየት ጀመሩ በዋናነት ስቃይ የበረታው በያሲር ቤተሶች ላይ ነበር ★የቤቱ አውራ ያሲር የአማር አባት በጣም አሰቃዩት አንገቱንም አንቀው ገደሉት ★እናት ሱመያ ሁለት እጆቹአና ሁለት እግሮቹአ መሬት ላይ ወጥረውት እርጉዝ ሆና በጩቤ አሰቃይተው ገደሉአት የመጀመሪያዋ የሙስሊም ሸሂድ ሆና ተመዘገበች ★ልጅ አማር ስቃይ ሲበረታበት ጣዎቶቻቸውን አወድሶ ነብዩንም ተሳድቦ ከስቃይ አመለጠ ወደ ነብዩ እያለቀሰ መጣና የሆነውን ነገራቸው አሳቸው ልብህን እንዴት ታገኘዋለህ አማር ሆይ አሉት የተረጋጋች ናት አላቸው አሁንም ድጋሚ ይዘው ካሰቃዩህ እኔን ስደበኝ አብሽር አሉት አሏህ ተግባሩን አመስግኖ አንቀጽ አወረደለት "ልቡ በኢማን ሞልቶ በምላሱ ቢክድ ተገዶ ከሆነ ችግር የለውም የሚል አንቀጽ አወረደ" ስቃይ ከበረታባቸው ውስጥ ★ሀበሻዊው ቢላል ኸባብ አቡ አሚር ከሴቶች ዚኒራህ ለቢባህ ይገኙበታል ጹሁፉ እንዳይረዝም ታሪካቸው ይዘለል ✍ Istbrek Sundus
⚠️خرج رسول الله ﷺ في بعض مغازيه، فلما انصرف جاءت جارية سوداء فقالت: ነቢዩ ﷺ በአንድ ዘመቻቸው ወጡ። ከዘመቻውም ሲመለሱ፣ አንዲት "ጃሪየቱ ሰውዳእ" ወጣት ሴት መጥታ እንዲህ አለች፦ ⚠️ يا رسول الله، إني كنت نذرتُ إن ردَّك اللهُ صالحًا أن أضربَ بين يديك بالدفِّ وأتغنّى. የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አላህ እርስዎን በሰላም ከመለሰልኝ፣ በፊትዎ #ዱቤ(ዳፍ) እንዲመታ እና እንዲዘፍን ብዬ ተስሌ ነበር። ⚠️ فقال لها رسول الله ﷺ: إن كنتِ نذرتِ فاضربي، وإلا فلا. فجعلت تضرب…» የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሏት፦ ስለት ተስለሽ ከሆነ #ቃልሽን ሙይ ማለትም ዱቤውን ምቺ ፤ ካልሆነ ግን አታድርጊው። ከዚያም #ዱፉን መምታት ጀመረች… ⚠️لو كان ضربُ الدفِّ حرامًا، لما أقرَّ النبيُّ ﷺ النذرَ به، ولا أذن لها أن تضربه؛ لأن النبيَّ ﷺ لا يُقرُّ على الحرام ولا يأمر به. ولذلك يُفهم من هذا الحديث أن ضربَ الدفِّ ليس حرامًا. #ዱቤ (ዱፍ) መምታት ሐራም ቢሆን ኖሮ፣ ነቢዩ ﷺ ይህንን ስለት አያፀድቁም ነበር፣ እንድትመታውም አይፈቅዱላትም ነበር፤ ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ #በሐራም ነገር ላይ አያፀድቁም፣ ወደ #ሐራምም አያዙም። ስለዚህ ከዚህ ሐዲስ የምንረዳው #ዱቤ መምታት በራሱ ሐራም አለመሆኑን ነው። ⚠️نفهم أن النذر لا يختص بالرجال دون النساء، ولا بالنساء دون الرجال، وإنما يكون النذر في الأمور التي تكون عبادةً مشروعة. #ስለት የሚባለው ለወንዶች ብቻ ወይም ለሴቶች ብቻ #የተወሰነ እንዳልሆነ እንረዳለን ። #ስለት የሚሆነው ሸሪዓ የተፈቀደና የኢባዳ አይነት በሆነ ነገር ላይ ነው። ⚠️فمثلًا: لو قال رجل: لله عليَّ، إن قضى الله حاجتي أن أصلي ركعتين؛ فهذا نذرٌ في عبادة، ويصح من الرجل كما يصح من المرأة. ለምሳሌ፦ አንድ ሰው፦ አላህ ሆይ! ሐጃዬን ካሳካህልኝ፣ ሁለት ረከዓ ሶላት እሰግዳለሁ ቢል፣ ይህ በኢባዳ ላይ የተደረገ ስለት ነው። ይህም ለወንድም እንደሚበቃው ሁሉ ለሴት ለሴትም ይበቃል። ⚠️وكذلك الدفُّ؛ فإذا ثبت جوازه بالنذر، فلا يصح أن يُقال: إنه خاص بالنساء فقط دون الرجال، بل الأصل أن الحكم لا يختص بأحد الجنسين إلا بدليل. እንዲዚሁም #ዱቤ መምታት ለውንድም ለሴትም ይበቃል ፤ በስለት ምክንያት መፈቀዱ ከተረጋገጠ፣ ለሴቶች ብቻ ነው፣ ለወንዶች አይፈቀድም ማለት ከማስረጃ ውጭ ነው። ⚠️أما قول بعض من انحرف عن الدين: «إن ضرب الدف لا يجوز إلا للنساء»، فهذا القول لا دليل عليه، ومخالف لما يُفهم من الحديث. ስለዚህ ዱቤ መምታት ለሴቶች ብቻ ነው የሚፈቀ የሚሉ አንዳንድ #ከዲን ያፈነገጡ ሰዎች አባባል ማስረጃ የሌለው ነው እንደዚሁም ከሀዲሡ አረዳድ በተቃራኒ ናቸው ። ሰይፉሏህ የነቢ ወዳጅ
ዲሪቷም አደራች ሸረሪቱም💛 በሰፈር 27 የመካ ከሀዲያን (ቁራይሾች) ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለመግደል በቤታቸው ዙሪያ ከበው ያደሩበት ምሽት ነበር። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አላህ በሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት ከአቡበከር (ረ.ዐ) ጋር ለመሰደድ ሲነሱ፣ ጠላቶቻቸውን ለማታለልና የሰዎችን አደራ ለመመለስ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብን በ አልጋቸው ላይ እንዲተኙ አድርገዋል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና አቡበከር (ረ.ዐ) ከመካ ከወጡ በኋላ በቀጥታ ወደ መዲና አልሄዱም። ጠላቶቻቸውን ለማስቀየስ በመካ አቅራቢያ በሚገኘው የሳውር ዋሻ (Cave of Thawr) ውስጥ ለሦስት ቀናት ተሸሽገዋል። የቁራይሽ መሪዎች ዋሻው በር ላይ እስኪደርሱ ድረስ ተከታትለዋቸው ነበር። ነገር ግን አላህ ተአምር አድርጎ በዋሻው በር ላይ ሸረሪት ድር እንድታደራ እና ርግብ እንቁላል እንድትጥል በማድረጉ ጠላቶች "እዚህ ውስጥ ሰው የለም" ብለው ተመልሰዋል። አቡበከር ጠላቶች ዋሻው በር ላይ መቆማቸውን አይተው ሲፈሩ፣ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "አቡበከር ሆይ! ሦስተኛቸው አላህ የሆነን ሁለት ሰዎችን ምን ይመስልሃል? አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና" በማለት ያረጋጉበት ታሪካዊ ንግግር የተከሰተው በዚህ ወቅት ነው። የሰፈር 27ቱ የሂጅራ ጉዞ ዝም ብሎ የተደረገ ሳይሆን እጅግ የረቀቀ ስትራቴጂ የነበረው ነበር፡ የአስማእ ቢንት አቡበከር ሚና፦ የአቡበከር ልጅ አስማእ ነፍሰጡር ሆና ሳለ በምሽት በድብቅ ወደ ዋሻው ምግብ ታደርስላቸው ነበር። የምግብ እቃውን የምታስርበት ስላጣች የወገብ ቀበቶዋን ለክፍላ የሰጠችበትና "ባለ ሁለት ቀበቶዋ" (ዛት-አን-ኒጣቃይን) የሚል ክብር ያገኘችው በዚህ ታሪክ ነው። የአብዱላህ ኢብኑ አቡበከር ሚና፦ የመካን ከሀዲያን ወሬና እቅድ በቀን አድምጦ ማታ ማታ ወደ ዋሻው እየመጣ መረጃ ያደርስ ነበር።አሚር ኢብኑ ፉሀይራህ፦ የነሱን የእግር ኮራ እጮች ለማጥፋት የበግ መንጋዎችን እየነዳ ይከተላቸው ነበር
ደሀወች ጋር ለመቀመጥ ሞክር የነሱ ህልም አንተን መተናነስ ያስለምዱሀል የነሱ ትልቁ ህልማቸው አንተ እንደምትኖረው መኖር ነው!!
ሰላዋት የሚያበዛ ሰው 3 ጥቅም ያገኛል : 1, ቀጥታ ወደ አላህ ያደርስሀል 2, ሸኽ ወይም ሙረቢ ጋ ያገጣጥምሀል( አላህን እንድትፈራ ያደርግሀል) 3, ከረሡለላህ ﷺ ጋር ትስስርህ ይጠነክርና በመናምህ ረሱልን ﷺ እንድታይ ያደርገሀል እኛ የተገባን ባንሆንም አላህ ዛሬ ለይል ምናያቸው ያድርገን። ከሸህ አዲል اللهم صل وسلم على الذات المحمدية والآل واغفر لنا ما يكون وماقد كان.☺️
✨አዲስ መንዙማ ጌታዬ እንዴት ነሁ መሀመድ አሚን(የሚያምረዉ)||የመዉሊድ መንዙማ አጀብ አጀብ ቢስሚላሂ ብዬ ጀመርኩኝ ባንተ ስም መቼም አንተን ይዤ ባዶ አልመለስም ድካ አልፎ ወንጀሌ ስራየ ቢደብስም የቀኙ መዝገቤ ከግራየ ቢያንስም ይሞላል ባንተ ስም ዙል ፈድሊል አዚሙ እኔስ ይገርመኛል አለመግደርደሬ ሁሉ እንደሞላልኝ ስደለቅ ማደሬ ጦይባ ከአንቱ ዘንዳ ባለመሀደሬ ጭር አለብኝ እሳ የሩሄ መንደሬ ምንድን ነው ነገሬ በዝቷል ናፍቆትሁ ጌታዬ እንዴት ነሁ ምነው ባየንሁ🥺
ከመድሆቻችን#1 የከውኑ ሞገስ የኛው ፈንታ ረሱል አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ሲወሱ እርሳቸውን በውብ ቃላት በውብ ዜማ በነፍስ እንጉርጉሮ እያስታወሰ እንዴት ነሁ የሚላቸው ወዳጅ ሳይነሳ አይቀርም በነብዩ መሃባ እጅግ የተሞሸሩት የመድሁ ባለሞአል sheikh ሙሀመድ አወል ሀምዛ ቀደምቶቹ ናቸው አላህ እኛንም በመድኃቸው የምናጌጥ ነቢን አወድሰው ከማይጠግቡት ሙሂቦች ውስጥ አኛንም ያድርገን አላሁመ ሰሊ አላ ሰይዲና ሙሀመድ 💚💚💚 Khemis mubarak💜
🥀 መገን ነቢ🥀 🥀 የአለሙ ሹም የመዲናው ጌታ ወዳንቱ የሸሸ አያፍር አይረታ በጨነቀው ጊዜ ያገኛል እርጋታ ፈጥነው ይደርሳሉ ኡመት ሲንገላታ ናቸው አስታራቂ ከአሏህ አቃራቢ 🥀 ያረሱለላሂ የኡመቱ ኒዕማ ባንቱ ላይ ይገኛል ተቅዋና ከራማ ላንቱ የገባ ሰው የለውም ነዳማ ድንጋጤ የለበት ነገ በቂያማ አብሽር ይሉታል ሙስጠፋ ያ ነቢ 🥀 በሻሻው መልካሙ የአሩሰ ጠይባ በስሙ የኖረ አዛብም አይገባ የሙሀባውም ሰው የለውም ገለባ ባንቱ ስም የኖረ አስራር እየጠባ ቢጣጣር ቢጣጣር አይደርሰው ጋላቢ
▪️▪️ ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ለምን መጻፍ አልቻሉም ወይም አልጻፉም? አስደናቂውና ጥልቁ ሚስጥር ሲገለጥ! 🗝️ ከአላህ አዋቂ (ዓሪፍ ቢላህ) ከሆኑት ከሸይኽ አሊ ደደ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ዕንቁ ንግግሮች ውስጥ የተቀነጨበ አስደማሚ ትንታኔ፤ [ነቢዩ (ﷺ) የማይፅፉበት ጥበብና ሚስጥር] ሸይኹ "የጥበብ ማህተሞች" በተሰኘው መጽሐፋቸው 77ኛው ጥያቄ ላይ እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ፡- *"ነቢዩ (ﷺ) አለመጻፋቸው፣ መጻፍ ከነቢይነት ፍፁማዊ ባህሪያት አንዱ ሆኖ ሳለ፣ እርሳቸውም የዚህ ሁሉ ዕውቀት ምንጭ፣ ማዕከልና መሰረት ሆነው ሳለ፤ እንዲሁም በታሪካዊ ዘገባዎች (አኽባር) ላይ እንደተወሳው ስለ ተለያዩ የፅሁፍ አይነቶችና ስለተጻፉ ገጾች ውስጥ ስላለው ነገር የሚያውቁና የሚናገሩ ሆነው ሳለ፤ ለምን አልጻፉም? ከዚህ በስተጀርባ ያለው ጥበብ ምንድን ነው?"* 🖋️ ምላሹ፡- እውነተኛው አምላክ አላህ (ሱ.ወ) አሳማኝና መቋጫ በሆነው ውብ ቃሉ ላይ እንዲህ በማለት አስገንዝቦናል፡- ﴿وَلَا تَخُطُّهُ بِيَمِينِكَ إِذًا لَّارْتَابَ الْمُبْطِلُونَ﴾ [አል-ዐንከቡት፡ 48] *"በቀኝ እጅህም አትጽፈውም፤ ያኔ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር።"* ምክንያቱም እርሳቸው ጽፈው ቢሆን ኖሮ "ይህንን ቁርኣን የቀድሞ ሰዎችን መጽሐፍት አንብበውና ገልብጠው ያመጡት ነው" በሚል መሠረተ-ቢስ ውንጀላ በተነሳ ነበር። 🖤 ከዚህም የጠለቀው ሌላው ሚስጥር... ኢማም አል-ኒሳቡሪ (ረ.ዐ) አንድ አስገራሚ ሚስጥር ያጋራሉ፡- "እርሳቸው (ﷺ) ያልጻፉትና ያላሰሉት (ያልቆጠሩት)፣ ቢጽፉ ወይም ትንሿ ጣታቸውን ቢያጥፉ የብዕራቸውና የጣታቸው ጥላ በአላህ (ሱ.ወ) ስም እና ዝክር ላይ ያርፍ ስለነበር ነው። ይህ ስለሆነም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አላቸው፡- *"ሀቢቢ (ወዳጄ) ሆይ! አንተ ብዕርህ ከስሜ በላይ እንዲሆን፣ እንዲሁም የብዕርህ ጥላ በስሜ ላይ እንዲያርፍ ስላልፈለግክና ስላላሰብክ፤ እኔም አንተን ለማክበርና ከፍ ለማድረግ ስል ሰዎች ድምፃቸውን ከአንተ ድምፅ በላይ እንዳያደርጉ አዘዝኩ። በዚህ ታላቅ አደብህ (ስነ-ምግባርህ) ምክንያት ጥላህ መሬት ላይ እንዲያርፍ አልፈቅድም።"* አላህን በብዛት የሚያወሳ፣ አላህ (ሱ.ወ) በከፍተኛው መላእክት ስብስብና በፍጡራን ሁሉ ዘንድ ከፍ ያደርገዋል። ይህንን የአላህን ፀጋ በተውፊቅ ያገኘ ሰው ልብ ይበለው! ቃዲ ዒያድ 'አሽ-ሺፋ' በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡- *"የእርሳቸው (ﷺ) ጥላ መሬት ላይ ያልነበረው (ያላረፈው)፣ ያ ጥንታዊው ጥላ በእግር እንዳይረገጥ ከመጠበቅ አንፃር ነው። እርሳቸው ንፁህ ብርሃን (ኑር) ናቸው ተብሏል፤ ብርሃን ደግሞ ጥላ የለውም። ይህም እርሳቸው በሰው ልጅ ቅርፅ የተገለጠ ብርሃን ሲሆኑ፣ ይህንኑ ጥላ-አልባ የሆነውን አጽናፈ-ዓለማዊ ህልውና የተላበሱ መሆናቸውን ያመለክታል። በሌላ በኩልም መላእክት በሰው ተመስለው ሲመጡ ጥላ እንደሌላቸው ሁሉ እርሳቸውም እንደዚያው ናቸው ተብሏል።"* 🌌 በዚህም ምክንያት፣ አንዳንድ የጥበብ ሰዎች (ዓሪፎች) የተቀደሱ መናፍስት (አርዋህ አል-ቁድሲያ) ወደ አካልነት ሲቀየሩ ምን እንደሚመስሉ ተገንዝበዋል። በተቃራኒው ደግሞ እርኩስ መናፍስት አካልን ሲላበሱ፣ ከሌሎች አለማዊ ጥላዎች ይልቅ የእነርሱ ጥላ እና ጨለማ መሬት ላይ እጅግ ይከብዳል/ይጠቁራል። ይህንን ልብ በለው፣ በውስጡ ጥልቅ የሆኑ መንፈሳዊ (ዒርፋናዊ) ምልከታዎችን ይዟልና! አንዳንዶች፣ "እርሳቸው ያልጻፉት በመጻፍ ተጠምደው ከማፈዝ (በልብ ከማስታወስ) እንዳይዘናጉ፣ እንዲሁም ዕይታቸው እንደ ቀደምት ሰዎች (ሰለፊያዊ) እንዳይሆን ነው" ይላሉ። ሸይኽ አሊ ደደ ግን እንዲህ ይላሉ፡- *"በዚህ ላይ የጠለቀ ምልከታ አለኝ፤ እርሳቸው ሳይጽፉ ይህን ሁሉ ተግባራዊ ማድረጋቸው በራሱ የሚያንፀባርቅ ተዓምር፣ ግልፅ የሆነ ድንቅ ምልክት፣ እንዲሁም ልዩ ምርጫና የበላይነት ነው። ታላቁ ብዕር (አል-ቀለም አል-አዕላ) የሚያገለግለው፣ እና የተጠበቀው ሰሌዳ (አል-ለውሕ አል-መሕፉዝ) መጽሐፉና መመልከቻው የሆነ ሰው፣ ምስሎችን በመሳልና ዕውቀቶችን በአካላዊ መሳሪያዎች ለመግለጽ አይገደድም። ምክንያቱም ጽሑፍ/መስመር በአካላዊ መሳሪያ የሚወጣ የአዕምሮ ጥበብና የተፈጥሮ ጉልበት ውጤት ነውና።"* 📜 የኡማው (የህዝባቸው) ሚስጥር በዚህ ውስጥ ሌላ አስደናቂ ምልክት አለ። የእርሳቸው (ﷺ) ኡማ ከሌሎች ህዝቦች መካከል 'መንፈሳውያን' (ሩሓኒዮች) ናቸው። አላህ (ሱ.ወ) በኢንጂል (ወንጌል) ላይ እንዲህ ሲል ገልጿቸዋል፡- *"የሙሐመድ ህዝቦች፣ ኢንጂላቸው (መፅሐፋቸው) በደረታቸው ውስጥ ነው።"* ምንም እንኳን የጽሑፍ መስመሮች ባይኖሩ ኖሮ እንኳን፣ ጥንካሬያቸው ፍጹም በመሆኑና ዝግጁነታቸው የጎላ በመሆኑ የእርሳቸውን (ﷺ) ህግጋት በልባቸው ያጠኑ ነበር። እርሳቸው መፃፍን መተዋቸው የሙሐመዳዊ ማዕሱምነት (ከስህተት የመጠበቅ) ሚስጥሮችን ይዟል። እርሳቸው 'ኡሚይ' (ያልተማሩ/ያልጻፉ) ነቢይ ናቸው። 'አል-ኡም' ማለት ደግሞ መሰረት (አስል) ማለት ነው፤ የእርሳቸውም ዘንድ የመጽሐፉ መሰረት (ኡሙል ኪታብ) ይገኛል። 🗝️ ማጠቃለያ፦ *"ከብርሃናት ጨረር ጥቂቱን አብራራሁልህ፤ ከሚስጥራትም ምልክቶች አሳየሁህ። ይህንን ሚስጥር በመግለጽ ረገድ አላህን ፍራ፤ አላህ ፀጋውን አብዝቶ የሚለግስ ጠባቂ ነው።"* ▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️ ከ ጀዋሂሩል ቢሃር ኪታብ
🌙🌙ቂሷ አውሊያኡ ሷሊህ🌙🌙 ♈️♈️«እቺን ለሊት እንግዳቹ ነኝ ያረሱለሏህ ﷺ»♈️♈️ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 አል-ሓፊዝ አዝ'ዘሀቢ'ይ ስለ ዓቢዱና ዛሂዱ አቢል ኸይር አል-አቅጧእ (374 አ.ሂ) የህይወት ታሪኽ ሲናገሩ በራሳቸው አፍ ይቺን ቂሷ ይጠቅሳሉ : «..አንድ ግዜ ወደ ረሱላችን ﷺ ከተማ መዲና በጣም ተርቤ ገባው ፤ አምስት ቀን ሙሉ የምቀምሰው ነገር አጥቼ ቆየው ። ወደ ቀብራቸው ሄድኩና ነብያችንም ﷺ አቡበክርም ዑመርም ላይ ሰላምታ አቀረብኩ ። ከዛም እቺን ለሊት እንግዳቹ ነኝ ያረሱለሏህ አልኩ። ከሚንበሩ ኋላ ጋደም አልኩ ፤ በህልሜ ሰይዳችንን ﷺ አቡበክር በቀኛቸው በኩል ዑመር በግራቸው በኩል ዐሊይ ደግሞ ፊት ለፊታቸው ሆነው አየኋቸው። ከዛም ሰዪዲ ዐሊይ ነቅነቅ አደረጉኝና ፡ "ተነስ የአላህ መልክተኛ ﷺ መጥተዋል" አሉኝ። ቆምኩና ሄጄ የተከበረው ግምባራቸውን ሳምኳቸው ። እሳቸውም የገብስ ዳቦ ሰጡኝ ። ግማሹን እንደበላው ነቃሁ ። ስነቃ ግን እጄ ላይ የቀረው ግማሽ ነበር ..» 📗 ታሪኹል ኢስላም : 7/920 አሏሁመሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ሰይዱና ወመውላና ወሸፊኡና ሙሀመዱን ወአላ አሊሂ ወሷሂቢሂ ወሙሂቢሂ
የኸዲጃ እና የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ለሰለም) ፍቅር ናሙና !! በውዷ ኸድጃ(ረዲየላሁ ዐንሃ) እና በአሽረፈል ኸልቅ መሀል የነበረውን ሙሀባ ለመረዳት ቀርቶ ለመክተብ እንኳ እጅግ ሩቅ ነው። ባይሆን ለበረካው አንድ አጋጣሚ ጨምረን ለፍቅር ዱስቱር ብለን እንዝጋ። ••• ወቅቱ ከብዙ የትግል እና የመከራ ጊዜ በኋላ የድል ብስራት የመጣበት ነው። ረሡልﷺ ለበርካታ ዓመታት ፋታ በማይሰጥ የዱንያ እና የአኼራ ጭንቀት ውስጥ በማሣለፋቸው ኸድጃም(ረዲየላሁ ዐንሃ) የተዘነጉ ይመስላል። ••• መካ የሚከፈትበት ቀን ደረሰ። ረሡልﷺ ከ አስር ሺህ በላይ ሠራዊት ይዘው ያለ ምንም ጦርነት በድል አድራጊነት መካ ገቡ። ከባልደረቦቻቸው ጋር በግፍ ከወጡበት የትውልድ ሀገራቸው በታላቅ ናፍቆት ሲደርሱ ሁሉም ወደናፈቀው ለመሄድ ፈልጎ ነበር። ረሡልﷺ ግን አንድ አስገራሚ ተግባር ፈፀሙ። ••• ጠቅላላ ሠራዊቱን በመያዝ ወደ ኸድጃ(ረዲየላሁ ዐንሃ) ቀብር ሄድ። ከቀብራቸው አጠገብ በመቆም የተወሰነ ጊዜ አሳለፉ። ዚያራቸውን እንደጨረሱ የተወሠኑ ሠሀባዎች የሚያርፉበት ቦታ የቱጋ ቢሆንላቸው አንደሚሻል ጠየቋቸው። ረሡልምﷺ ይህንን ተናገሩ "ከኸድጃ ቀብር ፊት ለፊት ቤቴን ገንቡልኝ። ስወጣ ስገባ ልመለከታት እሻለሁ።" ሙሀባ መጀን❤️❤️❤️❤️❤️أَلْفُ أَلْفِ مليون صَلَاةٍ، وَأَلْفُ ألف ألف ألف ألف ألف أَلْفِ سَلَامٍ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ وَآلِهِ
አሰላም አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ✋ ቢስሚላህ አልሀምዱሊላህ አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ💚 የዐለሙ ዐይነታ የተሰኘውን ቻናላችን የከፈትንበት ዋነኛ ዐላማ በአላህ ፍቃድ ረሱልን ለማወቅ ለማስተዋወቅ የርሳቸውን ውዴታ ለመያዝ ለማስያዝ ብለን ነው:: ታድያ በዚህ ቻናል ቂሳዎችን,ሰለዋቶችን,መድሆችን,ግጥሞችን,ዲናዊ ምክሮችንና የሰሀባና የነብያት ታሪኮችን ያገኙበታል:: አኛም ወደዚህ ቻናል ወደጆቻችሁን እንድትጋብዙልንና ላልደረሳቸው ሰዎች እንድታጋሩልን እንፈልጋለን:: ኑ በንፁህ ልብ ወደ ንፀህ ፍቅር እንሂድ!!!! ኑ ረሱላችንን በጋራ እንውደድ🥰 @yalemuayneta5
ልብ የሚነካ የነብዩ(ሠዐወ) ገጠመኝ👇 ነብዩ (ሰዐወ) ጠዋፍ እያደረጉ ሳለ አንድ ዓእራብይ /የአረብ ገጠሬ/ …‘ያ ከሪም!’ /ቸሩ ፈጣሪ ሆይ እንደማለት/… እያለ ሲጣራ ሰሙት። እርሳቸውም ከኋላው ሆነው …’ያ ከሪም!’… አሉ። ዓእራብዩም አቅጣጫ በመቀየር …’ያ ከሪም!’… እያለ መጣራቱን ቀጠለ ነብዩም (ሰዐወ) ከኋላው ተከትለው …’ያ ከሪም!’… አሉ። ዓእራብዩም ፊቱን ወደ እርሳቸው በማዞር:- “አንተ ባለግርማ እና በሻሻ ፊት ሆይ!… ዓእራብይ ስለሆንኩ ነው የምታሾፍብኝ?… በአላህ እምላለሁ! የፊትህ ሞገስ እና በሻሻነት ባልነበረ ወዳጄ ሙሐመድ (ሰዐወ) ዘንድ ወስጄ እከስህ ነበር!” አላቸው። ነብዩም (ሰዐወ) ፈገግ ብለው:- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ነብይህን አታውቀውም ማለት ነው?” አሉት ዓእራብዩም “አዎን!” ሲል መለሰላቸው። “ለመሆኑ በእርሱ ላይ ያለህ እምነት ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት ዓእራብዩም:- “በነብይነቱ አመንኩኝ! አይቼው ግን አላውቅም፣ ረሱልነቱን ተቀበልኩኝ! አግኝቼው ግን አላውቅም።” ሲል መለሰላቸው። ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ ዓእራብይ ሆይ! የዱንያው ነብይህ እና የአሄራ አማላጅህ እኔ መሆኔን እወቅ!” አሉት። ዓእራብዩም የነብዩን(ሰዐወ) እጅ በፍጥነት መሳም ያዘ ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ህዝቦች ንጉሶቻቸውን እንደሚያደርጓቸው አታድርገኝ፤ አላህ (ሱወ) ኩራተኛ እና አጉራዘለል አድርጎ አላከኝም፤ ይልቁንም አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርጎ በእውነት ልኮኛል።” አሉት በዚህን ጊዜ .. ጅብሪል ወደ ነብዩ መጣና:- “ሙሐመድ ሆይ አላህ (ሱወ) ሰላምታን ያቀርብልሀል! በክብር እና ልቅናም ከሌሎች አስበልጦሀል፤ ለዚህ ለዓእራብይ:- የአላህ ቸርነት እና ቻይነት እንዳያዘናጋው!፣ ነገ በትንሹም ይሁን በትልቁ፣ በልምጩም ይሁን በቅሉ እንደሚተሳሰበው ንገረው”… አላቸው። ዓእራብዩም:- “አንቱ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ሆይ! ጌታዬ ይተሳሰበኛል ማለት ነው?” ብሎ ጠየቃቸው “አዎን ከፈለገ ይተሳሰብሀል!” አሉት “እንግዲያውስ በአሸናፊነቱ እና በልቅናው ይሁንብኝ! የሚተሳሰበኝ ከሆነ እኔም እተሳሰበዋለሁ!” አለ። ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ጌታህን በምን ትተሳሰበዋለህ?” አሉት። “ጌታዬ በወንጀሌ ከተሳሰበኝ እኔ በምሕረቱ እተሳሰበዋለሁ፣ በጥፋቴ ከተሳሰበኝ እኔ በይቅር ባይነቱ እተሳሰበዋለሁ፣ በስስታምነቴ ከተሳሰበኝ እኔ በቸርነቱ እተሳሰበዋለሁ!”… አለ። ~~ ነብዩ (ሰዐወ) ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ አለቀሱ። ጅብሪል ወደ ነብዩ ወርዶ:- “ሙሐመድ ሆይ! አላህ ሰላምታን ያቀርብልሀል። ለቅሶህንም ቀንስ! የአርሽ ተሸካሚ መላኢካዎችን ተስቢህ ከማድረግ አዘግይታቸዋለችና ይልሃል። ለዓእራብዩ ወንድምህ ደግሞ:- እንዳይተሳሰበን ንገረው! እኛም አንተሳሰበውም! እርሱ የጀነት ጎረቤትህ ነው!።”… አላቸው። አላህ በታላቋ ጀነተል ፊርደውስ ውስጥ የነብዩን (ሰዐወ) ጉርብትና ከሚያገኙት እንዲያደርገን እንለምነዋለን። ያ አላህ ይህንን መልእክት አንብበው ለሚያስተላልፉ ሁሉ ከነቤተሰቦቻቸው ምሕረትህን ለግስ መመንዳትንም አትንፈጋቸው …ያ ከሪም!።
መይሰራ የተባለ ሰሐቢይ ረ•ዐ እንዲህ ይላል • የመውሊድ ወጎች 'ያ ረሱለላህ ﷺ መቼ ነው ነብይ የሆኑት?' አልኳቸው እሳቸውም "አላህ ምድርና ሰማይን ሰባት አድርጎ በፈጠረ ግዜ ዐርሽን ፈጠረና በዐርሽ ግርጌ ላይ 'ሙሐመዱን ረሱሉላሂ ኻተሙል አንቢያእ' (ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛና የነብያት መደምደሚያ ነው) ብሎ ፃፈበት። አደምና ሐዋ የኖሩበትን ጀነትም ፈጠረና በበሮች፣ በጉልላቶች በቅጠሎችና በድንኳኖች ላይ ስሜን ፃፈ። አደም የዚያን ግዜ በሩሕና በጀሰድ መሀል ነበር። አላህ ሕያው ካደረገው ቡኃላ ዐርሽን ሲያይ ስሜን ተመለከተ። አላህም 'የልጆችህ ሁሉ አለቃ' ነው ብሎ ነገረው። ሸይጣንም ባሳሳታቸው ግዜ ንስሓ ገቡ። በኔ ስምም ሸፈዓ ጠየቁ። (አማለዱ)" ሓፊዝ አቡል ሑሰይን ኢብን በሽራን እንደዘገበው (469/1)
ረቢዕ ታላቁ የደስታችን ወር ሊገባ ቀናት ቀርተውታል💛 አላህ በሰላም በአፊያ ለዚህ ወር ያድርሰን🤲 አሚን❤️
በቅርብ ቀን ለረቢዑ የተዘጋጀ ምርጥ መድህ በማዲህ ነስረዲንና ሙባረክ
መለኛ ነኝ ያለ በመላው ደከመ በመላህ ውጣ ሲል ጀሊልም ሐከመ እውቀት አለኝ ያለ በእውቀቱ ደከመ በእውቀትህ ውጣ ሲል ጀሊልም ሐከመ ቀልቡ ደረቀና ሴት ወንዱ ጠመመ ምነው ሶብር አሳጠን ቀልባችን ታመመ የኪብሪያ ጥምጣም ሁሉም ጠመጠመ ሙራድና ሙራድ አልተገጣጠመ ሰው ዟሂር ነው እንጂ ውስጡን አልሰለመ የሁሉ መሄጃ መንገዱ ጨለመ ነጋዴ ነኝ ያለ ብቻውን ዋለለ ንግድ በያይነቱ ለኔ ይሁን አለ ገበሬ ነኝ ያለ ብቻውን ዋለለ እርሻ በያይነቱ ለኔ ይሁን አለ እኔ እኔ በማለት ሙላውም ታገለ የመኽሉቅን ስራ ኻሊቅ አስተዋለ የሂስድን ዘበኛ ጌታችን አዘዘው በጎሚ ሴት ወንዱን እርስበርሱ አያያዘው ጌታችን አየና የኸልቁን ክፋቱን ፈውጀን ፈውጅ አድርጎ ሰደደው አፋቱ
https://t.me/tilku_sew/9338