tgindex
የአባ ሚዲያ

የአባ ሚዲያ

Статистика

የአባ ሚዲያ YeAba Media የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መረጃ እና ትምህርቶችን ያገኛሉ ይህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የምንማማርበት Channel ነው !  ወደ ቻናላችን በመቀላቀል 👇 ➲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መፅሐፍትን ስንክሳር ትምህርቶች ➲ መዝሙራትን በግጥና ኪነ-ጥበብ ➲ ጥያቄዎችን በሐይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁ መርምሩ በተጨማሪም የኮምፒውተር Programmin

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
172
−1 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
52
18 постов
Вовлечённость
30,2%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
10
1/48двое суток
11
1/72трое суток
12

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #mezmur ከክፉ ቀን መውጫ በይ ተመላለሺ ጓዳዬን ጎብኚልኝ፣ እኔ ምን አውቃለሁ ምን እንደጎደለኝ፣ የተወደደውን አምሃ ስጦታ ፣ ተቀበዪ እናቴ የኔንም ሰላምታ። ከክፉ ቀን መውጫ ከሞት የሚያድን ነው፣ አማላጅነትሽ ለሚተማመነው፣ አላፈርኩም እኔ ስምሽን ጠርቼ፣ አዝኜ ብወጣ መጣሁ ተደስቼ። . ልቤ ሰማይ ይሁን ለልጅሽ ዙፋ፣ አንቺን እንዳከብር በቀሪው ዘመን፣ ይሁንልሽ ቤቴ የልደቱ ስፍራ፣ ማረፊያ እንዲሆንሽ ከወለድሽው ጋራ። ❴አዝ❵ በይ ተመላለሺ ጓዳዬን ጎብኚልኝ፣ እኔ ምን አውቃለሁ ምን እንደጎደለኝ፣ የተወደደውን አምሃ ስጦታ ፣ ተቀበዪ እናቴ የኔንም ሰላምታ። ❴አዝ❵ ታናሿ ደመና ከባህር የወጣሽ፣ በወለድሽው ዝናብ ዓለምን ያረጠብሽ፣ አስጨናቂዎችሽ ከጫማሽ ወደቁ፣ አማላጅነትሽን በእምነት ስላወቁ። ❴አዝ❵ ለጨለመው ልቤ ሁኚልኝ መብራቴ፣ የመስቀሉ ፍቅር እንዳይጠፋ ፊቴ፣ ላስብ አንቺን ብቻ ሆኜ በፀጥታ፣ አይቻለሁ እና ፍቅርሽ ሲያበረታ። ቀሲስ አሸናፊ ገብረ ማርያም

  • ✞✞✞ ✝💒✝ 💚💛❤️ 💠💠💠 ✞✞✞ ቅዱስ ገብርኤል ዘተዋህዶ ቴሌግራም ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ ዓምላክ ዓሜን  🙏🙏🙏 ††† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት ቅዱስ አልዓዛር እና ለቅዱሳን ቤተሰቡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† ቅዱስ አልዓዛር ካህን ††† ††† ይህ ቅዱስ #የብሉይ_ኪዳን_ሰማዕታትተብለው ከሚታወቁት ዋነኛው ነው:: የነበረበት ዘመንም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲሆን " #ዓመተ_መቃብያን/ #ዘመነ_ካህናት" ይባላል:: በወቅቱ ሰሎሜ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ ይኖር የነበረው ቅዱስ አልዓዛር በኢየሩሳሌም ተወዳጅ ነበር:: ሐረገ ትውልዱ ከአሮን ወገን ነውና በክህነቱ ተግቶ ያገለግል ነበር:: በዚያ ላይ ሊቀ ካህንነትን በመመረጡ ሕዝቡን ይሠራ: ያስተምር: ያስተዳድር ነበር:: ቅዱስ አልዓዛር ከተባረከች ሚስቱ ሰሎሜ 7 ወንዶች ልጆችን አፍርቷል:: እነርሱንም በሥርዓት አሳድጐ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጐ ነበር:: በዚያው ዘመን በኢየሩሳሌም አካባቢ የሚኖሩ 3 እኩያን (ክፉ) ካህናት ነበሩ:: እነዚሁም ሕዝቡን ከማስቸገር: ፈጣሪን ከማሳዘን ቦዝነው አያውቁም ነበር:: የክፋታቸው መጨረሻ ግን የገዛ ሃገራቸውን ማጥፋት ሆነ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- 3ቱም ተመካክረው የአልዓዛርን የሊቀ ካህንነት ቦታ ሊቀሙ ወስነው ወደ እርሱ ሔዱና እንዲህ አሉት:: "ሹመት በተርታ: ሥጋ በገበታ" ሲሆን ያምራልና እኛ በተራችን በወንበሩ ላይ እንቀመጥ::" እርሱ ግን "ሕዝቡን ጠይቃችሁ ተሾሙ" አላቸው:: እነርሱም ሕዝቡን ጠርተው "ሹመት ይገባናል" ቢሏቸው ሕዝቡ መልሶ "አልዓዛርን የሾመው እግዚአብሔር ነውና እናንተም ከፈጣሪ ጠይቃችሁ ተሾሙ" አሏቸው:: በዚህ ጊዜ 3ቱ እኩያን ተቆጡ:: ምክንያቱም እግዚአብሔር እንደ ማይሰጣቸው ያውቃሉና:: ወዲያው ግን 3ቱም ከአካባቢው ጠፉ:: ከኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ጨካኙ የግሪክ ንጉሥ አንጥያኮስ ሔዱ:: አንጥያኮስ ማለት "ቀኝ ዐይናችሁን ገብሩልኝ" የሚል ንጉሥ ነው:: እርሱን " #ኢየሩሳሌም ባለቤት የላትምና ሒደህ ውረራት" አሉት:: "አጥሩ ጥብቅ ነው:: በምን እገባለሁ?" ቢላቸው "እኛ በመላ እናስገባሃለን" አሉት:: እርሱም 240,000 ሠራዊት አስከትቶ ወረደ:: እነርሱ ቀድመው ወደ ኢየሩሳሌም ገብተው ያስወሩ ጀመር:: "እናንተ ሹመት ብትነሱንም እኛ ግን አንጥያኮስን ያህል ንጉሥ በእሥራኤል አምላክ አሳምነን መጣን" እያሉ ይሰብኩ ገቡ:: ቅዱስ አልዓዛር "አትስሟቸው:: በዚያም ላይ አሕዛብ የተቀደሰውን ምድር መርገጥ የለባቸውም" ብሎ ነበር:: ነገር ግን አንዳንድ ችኩሎች አይጠፉምና ፈጥነው የከተማዋን በር ከፈቱት:: ሠራዊቱን ደብቆ ትንሽ ራሱን የቆመ የመሰለው አንጥያኮስ በምክንያት: በክፋትና በመላ ሁሉን ሠራዊቱን አስገባ:: የሚገርመው በጊዜው የከተማዋ ሕዝብ 12 እልፍ (120,000) ሲሆን ንጉሡ ያስገባው ሠራዊት ግን 24 እልፍ (240,000) ሆኖ ተገኘ:: ወዲያው አንጥያኮስ ሕዝቡን ሰበሰበና አልዓዛርን ለብቻው ጠርቶ ተናገረው:: "አንተ አምላክህን እንደምትወድ ሰምቻለሁ:: አንተ የበጉን መስዋዕት በልተህ: #ለስዕለ_ኪሩብ ሰግደህ: ሕዝቡን ግን እሪያ (አሳማ) እንዲበላና ለጸፀሐይ እንዲሰግድ አድርግልኝ" አለው:: ቅዱስ አልዓዛር መለሰለት:- "እግዚአብሔር የሾመኝኮ በጐ ሃይማኖትን ላስተምር እንጂ ለክፋት አይደለም:: ለሕዝቤ የክፋት አብነት ፈጽሞ አልሆንም" አለው:: ያን ጊዜ ንጉሡ በቅዱሱ ላይ ተቆጣ:: "የምልህን ካላደረግህ ብዙ ግፍ ይደርስብሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የፈለግኸውን አድርግ" አለው:: በዚያን ጊዜ ንጉሡ የቅዱሱን ሚስትና 7 ልጆች እንዲያመጡለት አዘዘ:: ቅዱሱ እያየ ከፊቱ ላይ 7ቱንም ልጆቹን በሰይፍ አስመታቸውና 7ቱም ወደቁ:: ለአንድ አባት ይህ የመጨረሻው መራራ ፈተና ነው:: #አልዓዛር ግን ምን አንጀቱ በኀዘን ቢቃጠልም ከልጆቹ ለእግዚአብሔር አድልቷልና ቻለው ታገሠው:: በዚህ ለውጥ እንዳልመጣ ያየው ንጉሡ ሌላ ፍርድ ተናገረ:: ቅዱሱንና ሚስቱን ( #ሰሎሜን) በፈትል ጠቅልለው በሠም ነከሯቸው:: (ጧፍ እንደሚሠራበት መንገድ ማለት ነው:: ) አሁንም ግን ከአምልኮታቸው ፈቀቅ ባለማለታቸው ትልቅ ብረት ምጣድ ተጥዶ: 2ቱም ከነነፍሳቸው እንዲቃጠሉ ተደረገ:: ቀጥሎም ሕዝቡን እንዲፈጁ አዋጅ ወጣ:: በከተማዋ ከነበረው ሕዝብ 40,000 ያህሉ ተገደሉ:: 40,000 ያህሉ ሲማረኩ 40,000 ያህሉን ደግሞ #ይሁዳ የሚባል አርበኛ በር ሰብሮ ይዟቸው ሸሸ:: "እንሾማለን: እንሸለማለን" ብለው ሕዝባቸውን ያስፈጁ እነዚያ ካህናትም #እግዚአብሔር ፈርዶባቸው እነርሱም ተገደሉ:: ቅዱሱ የአልዓዛር ቤተሰብ ግን የክብርን አክሊል አግኝተዋል:: ††† #የእሥራኤል_አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር እንዲህ ካለው መከራ በኪነ ጥበቡ ይሰውረን:: ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን:: ††† ነሐሴ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (ሰማዕት) 2.ቅድስት ሰሎሜ ሰማዕት (ሚስቱ) 3."7ቱ" ቅዱሳን ሰማዕታት (ልጆቹ) 4.ቅዱስ አሞን ሰማዕት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ብሶይ (ቢሾይ) 4.አቡነ ኪሮስ 5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ††† "አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ:: የቅድስናህንም #መቅደስ አረከሱ:: #ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት:: የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ:: የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት:: ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ:: የሚቀብራቸውም አጡ::" ††† (መዝ. 78:1) ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር 🙏🙏🙏    👇👇👇 🌹🌹🌹 ይህ ገፅ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ  በስልክዎ ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ወዳጆችዎን ወደዚህ ገፅ በመጋበዝ በረከት ይቀበሉ ።🙏🙏🙏 👇👇👇

  • የሚሆነውን ሁሉ ይልቁንም የጌታችንን የመወለዱን ነገር በምሳሌ እያደረገ ነገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸውና በአብርሃምና በይስሐቅ ሣራም በተቀበረችበት መቃብር ወስደው እንዲቀብሩት ከነገራቸው በኋላ በ137 ዕድሜው እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ በሰላም ዐረፈ፡፡ የግብፅ ሰዎችም 70 ቀን አለቀሱለት፡፡ ዮሴፍም አባቱን ባዘዘው ቦታ በእነ አብርሃም መቃብር ከቀበረው በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሰ፡፡ የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ‹‹ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፣ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል›› ብለው ፈርተው ወደ ዮሴፍ መልዕክት ልከው ‹‹አባትህ ገና ሳይሞት ‹ዮሴፍን እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፣ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና፤ አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል› ብሎሃል›› ብለው ላኩለት፡፡ ወንድሞቹም መጥው በፊቱም ሰግደው ‹‹እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን፣ በአባቶችህ አምላክ ባሮችህን ኃጢአታችንን ይቅር በለን›› አሉት፡፡ ዮሴፍም እንዲህ ሲሉት አለቀሰ፡፡ እርሱም ‹‹ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ ስለሆነ አይዟችሁ አትፍሩ›› እያለ እንዳይፈሩ አጽናናቸው፤ደስም አሰኛቸው፡፡ ዮሴፍም በግብፅ ተቀምጦ 110 ዓመት ኖረ፡፡ የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ካየ በኋላ ወንድሞቹን ጠርቶ ‹‹እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፣ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል፡፡ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ብሎ አማላቸው፡፡ ዮሴፍም በ110 ዕድሜው በሰላም ዐረፈ፡፡ በሽቱ አሽተው በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት፡፡ ዮሴፍም ‹‹እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ማለቱ አንድም ከግብፅ ምድር እንደሚወጡና የአባቶቻቸውን ርስት ከነዓንን እንደሚወርሱ ሲነግራቸው ነው፡፡ ፍጻሜው ግን ግብፅ የመቃብር ከነዓን የትንሣኤ ምሳሌ ናቸው፡፡ አንድም ግብፅ የገሃነም ከነዓን የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ያዕቆብም እንዲሁ ብሏልና ዮሴፍም እንዲህ ያለ ስለምን ነው ቢሉ አባቶቻችን እንዲህ ማለታቸው መውጣታችንን ቢያውቁ ነው ብለው እንዲነቁ፣ እንዲተጉ፣ አንድም ለማጸየፍ ነው፣ ‹‹አባቶቻችን አጥንታችን እንኳን ከዚህ አይቅር›› ብለዋል ብለው እንውጣ እንዲሉ ነው፡፡ † ነሐሴ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር 4.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 5.አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ) 6.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ) 7.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት † ወርኀዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ 7

  • https://youtu.be/dLAEsRQdUVQ?si=LVLvezbNiixxqy84 ፀጋን የተመላሽ ሆይ

  • ነሐሴ ፪ /2/ በዚች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር ቅድስት አትናስያ አረፈች። የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ባለጸጎች ነበሩ እነርሱም በሞቱ ጊዜ እንግዶችን እና የገዳም አባቶችን ሁሉ ትቀበላቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ክፉ ሰዎች ወደ ኃጢአት መለሷትና ኃጢአት መስራት ጀመረች። ስለዚህም ነገር የገዳም አባቶች ሰምተው ዮሐንስ ሐጺርን በንስሐ እንዲመልሳት ላኩት። እርሱም ወደርሷ በገባ ጊዜ በዝሙት ልትጥለው አልጋዋ ላይ ሆና ጠበቀችው። እርሱም እንዲህ እያለ ይዘምር ነበር በሞት ጥላ ውስጥ ብሔድም እንኳ ክፉን አልፈራውም አንተ ከእኔ ጋራ ነህና። ከእርሷ ጋራም በአስቀመጠችው ጊዜ ራሱን ዘንበል አድርጎ አለቀሰ መነው ብትለው እግዚአብሔርን እንዳሳዘነችው ነገራት። በመጨረሻም ቃሉንም ሰምታ ደነገጠችና ተንቀጠቀጠች ምን ይሻለኛል አለችው ንስሐ ግቢ አላት እርሷም እግዚአብሔር ይቀበለኛልን አለችው እርሱም አዎን አላት እርሷም ወደምትሔድበት ከአንተ ጋራ ውሰደኝ አለችው እርሱም ነዪ ተከተይኝ አላቴና ተከተለችው። በመሸ ጊዜም እርሷን አስተኝቶ እርሱ ግን በጸሎት ይተጋ ነበር። ሌሊትም በጸሎት ላይ ሳለ የብርሃን ምሰሶ አየ መላዕክትም የአንዲትን ነፍስ ሲያሳርጉ አየ። በነጋም ጊዜ ወደ አትናስያ ሲደርስ ሞታ አገኛት። ስለ ርሷም ያስረዳው ዘንድ እየሰገደ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም ገና ቤቷን ትታ ስትወጣ ይቅር እንዳላት ነገረው። ከዚህም በኋላ ሒዶ ለአረጋውያን የሆነውን ሁሉ ነገራቸው እነርሱም እርሱ እንዳያት ማየታቸውን ነገሩት የኃጢአተኛን ወደ ንስሐ መመለሱን እንጂ ሞቱን የማይሻ እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤

  • "ድንግል ሆይ ከተወዳጅ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ ወደ እኔ ነይ፤ እኛን ትባርኪ ዘንድ!" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ) ​በቅዱስ ወንጌል ታሪክ ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽመው ሲለያዩ አንመለከትም። 👉​በቤተልሔም፡ እረኞችና ሰብአ ሰገል ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት (ማቴ 2፥11)። 👉​በስደት፡ መልአኩ ቅዱስ ዮሴፍን "ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ሽሽ" አለው (ማቴ 2፥13)። 👉​በቃና ዘገሊላ፡ ተአምራት ሲደረግ እናትና ልጅ በአንድነት ነበሩ (ዮሐ 2፥1)። 👉​በቀራንዮ፡ በእግረ መስቀሉ ሥር አደራ ተሰጥታናለች (ዮሐ 19፥26)። ​ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ምስጋናው "ከተወደድው ልጅሽ ጋር ወደ እኔ ነይ" ብሎ የተማፀነው ይህንን የወንጌል እውነት በመረዳት ነው። ጌታችን ከእናቱ ጋር እንዳለ ሁሉ፣ በህይወታችንም በረከቱና ሰላሙ እንዲበዛ የእመቤታችን ምልጃና እናታዊ ፍቅር አይለየን። ​ፆሙ የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት ያድርግልን! ​እንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!

  • ✞✞✞ ✝💒✝ 💚💛❤️ 💠💠💠 ✞✞✞e ቅዱስ ገብርኤል ዘተዋህዶ ቴሌግራም ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ ዓምላክ ዓሜን  🙏🙏🙏 †††እንኳን ለቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ : ቅዱስ ዋርስኖፋ እና አባ ዮሐንስ ዘጐንድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† ††† ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ ††† ††† ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ3 ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል:: እንደ ዮሐንስ ወንጌላዊ ያሉት በ20ዎቹ ውስጥ : ቅዱስ ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ30ና በ40ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን እነ ቅዱስ ዼጥሮስ ደግሞ በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ:: ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም : ከጐልማሶችም : ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው:: ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) ስምዖን እና ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል:: ቅዱሱ ጌታችን ተከትሎ : ከ12ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ : 3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ተምሮ : በዕርገቱ ተባርኮ : በበዓለ ሃምሳም 71 ልሳናትን ተቀብሎ : ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል:: ቅዱስ ታዴዎስ እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም ሐምሌ 2 ቀን ዐርፏል:: ቅዱሱ ሐዋርያ ያረፈው ሶርያ ውስጥ ሲሆን ከ250 ዓመታት በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ ታንጾለት በዚህች ቀን ወደ ቁስጥንጥንያ ፈልሷል:: ይህንን ያደረገው ደግሞ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነው:: ከሐዋርያው ዘንድም ብዙ ተአምራት ተደርገዋል:: ††† ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት ††† ††† ቅዱሱ በትውልድ ግብፃዊ ሲሆን ገና ከልጅነቱ ጣዕመ ክርስትና የገባው ነበር:: መጻሕፍትን በማንበብ: ክርስትናንም በመለማመድ ስላደገ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት የመወደድ ሞገስ ነበረው:: በእድሜው እየጐለመሰ ሲሔድ በተጋድሎውም እየበረታ ሔደ:: በወቅቱ እርሱ የነበረባት ሃገር ዻዻስ በማረፉ ሊቃውንቱና ሕዝቡ ተሰብስበው አምላክን ጠየቁ:: እንደሚገባም መከሩ:: በደንብ አስተውለዋልና እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው ሁሉም ቅዱስ ዋርስኖፋን መረጡ:: ዛሬን አያድርገውና በአባቶቻችን ዘመን ሕዝቡም ሆነ ሊቃውንቱ መሪ መምረጥን ያውቁ ነበር:: ተመራጮቹ ደግሞ እንኩዋን እንደ ዘመናችን "ሹሙኝ : ምረጡኝ" ሊሉ በአካባቢውም አይገኙም ነበር:: ቅዱስ ዋርስኖፋ ለዽዽስና እንደ መረጡት ሲያውቅ "ጐየ" እንዲል መጽሐፍ: ጨርቄን ማቄን ሳይል በሌሊት ጠፍቶ በርሃ ገባ:: (እንዲህ ነበሩ አበው) በገባበት በርሃ ውስጥ በዓት ሠርቶ በጾም: በጸሎትና በስግደት በርትቶ ዓመታትን አሳለፈ:: እርሱ በበርሃ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ጀምሮ ብዙ ክርስቲያኖች አልቀው ነበር:: እርሱ ግን ከዓለም ርቁዋልና ይህንን አላወቀም ነበር:: አንድ ቀን መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ "አንተ በስሙ ደማቸውን ለሚያፈሱ አክሊላት እየታደለ : ሰማያዊ ርስትም እየተካፈለ ነውኮ! አልሰማህም?" አለው:: ቅዱስ ዋርስኖፋም "ለካም እንዲህ ያለ ክብር አምልጦኛል" ብሎ: በርሃውን ትቶ ወደ ከተማ ወጣ:: መልአኩ እንዳለውም ክርስቲያኖች ሲሰቃዩ ደረሰ:: ቅዱሱም ሳያመነታ ስመ ክርስቶስን ሰብኮ: ብዙ ተሰቃይቶ በዚህች ቀን አክሊለ ሰማዕትን በአክሊለ ጻድቃን ላይ ደርቧል:: ††† እጨጌ አባ ዮሐንስ ዘጐንድ ††† ††† ጻድቁ ተወልደው ያደጉት በኢየሩሳሌም ሲሆን ነገዳቸውም እሥራኤላዊ ነው:: ነገር ግን ተጋድሏቸውን የፈጸሙት በሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ ነው:: እጨጌ አባ ዮሐንስ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ ባለ ረዥም እድሜ ጻድቅ መሆናቸው ይነገራል:: አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያረፉት በ562 ዓመታቸው ሲሆን እጨጌ አባ ዮሐንስ ደግሞ በ500 ዓመታቸው ነው:: የሚገርመው ጻድቁ የታላላቁ ጻድቃን ገብረ መንፈስ ቅዱስ : ተክለ ሃይማኖት: ሳሙኤል: ዜና ማርቆስ እና ሌሎችም ባልንጀራ ነበሩ:: በዛ ዘመን ዘረኝነት በቅዱሳኑ ዘንድ አልነበረምና ነጭ ሆነ ጥቁር : ከየትም ይምጣ የሰው ልጅ መሆኑ ብቻ በቂ ነበር:: እጨጌ አባ ዮሐንስ በሃገራችን 5 በዓቶች የነበሯቸው ሲሆን በአንድ በዓት የሚኖሩት ለ50 ዓመት ነበር:: በዚህም በኢየሩሳሌም ለ50 ዓመት : በኢትዮዽያ ደግሞ ለ450 ዓመታት ኑረዋል:: ከበዓቶቻቸው አንዱ ደብረ ሊባኖስ ሲሆን በገዳሙ ለ50 ዓመታት አበ ምኔት(እጨጌ) ሆነው አገልግለዋል:: "እጨጌ" የሚባሉትም በዚህ ምክንያት ነው:: ጻድቁ የመጨረሻ ዘመናቸውን ያሳለፉት በጐንድ (ጉንድ) ተክለ ሃይማኖት ገዳም ነው:: ገዳሙ የሚገኘው በሰሜን ጐንደር ዞን : በለሳ ወረዳ ውስጥ ሲሆን የመሠረቱትም ራሳቸው ናቸው:: ነገር ግን በራሳቸው እንዲጠራ አልፈለጉምና ገዳሙ የሚጠራው በወዳጃቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም ነው:: ጐንድ እኛ ኃጥአን ሳይገባን ያየነው ገዳም ነው:: ዛሬም ድረስ ድንቅ የሆኑ አበው የሚኖሩበት : ተአምራትም የማይቋረጥበት : ፈዋሽ ጠበል ያለው ደግ ገዳም ነው:: ጻድቁ እጨጌ አባ ዮሐንስ ግን አስታዋሽ አጥተው እየተዘነጉ ካሉ ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ምንም ዛሬ አጽማቸው ፈልሶ ወደ ደቡብ ኢትዮዽያ አካባቢ ቢሔድም እርሳቸው በ500 ዓመታቸው ያረፉት በዚህ ገዳም ውስጥ ነው:: ††† እግዚአብሔር ከሐዋርያው : ከሰማዕቱና ከጻድቁ ክብርን : በረከትን ያሳትፈን:: ††† ሐምሌ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት 3.እጨጌ አባ ዮሐንስ (ዘጐንድ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት 2.ቅድስት አርሴማ ድንግል 3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ 5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት 6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት) ††† "ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል::" ††† (1ዼጥ. 5:3) ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር 🙏🙏🙏    👇👇👇 🌹🌹🌹 ይህ ገፅ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ኦርቶዶክሳውያን ወዳጆችዎን ወደዚህ @YeAbaMedia መማማርያ በመጋበዝ በረከት ይቀበሉ ።🙏🙏🙏 👇👇👇          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

  • ሐምሌ 26 የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ የዕረፍቱ በዓል ነው። በአረፈም ጊዜ ጌታችን  ወደርሱ መጥቶ እጆቹን  በላዩ ጫነ ለሥጋውም  መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን  ሰጠው በአባቱ  በያዕቆብም መቃብር አኖሩት። አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅን ማሳደግ የሚያውቅ አምላኩን አባት ሆኖ ያሳደገ ኢየሱስ ክርስቶስ አባቴ ብሎ የጠራው ሲያርፍም ክርስቶስ በእጆቹ የገ ነ ዘው አባቴ ብሎ ያለቀሰለት ቅዱስ አባት ነው። ሐምሌ 26 የዕረፍት በዓሉ ሲሆን በዚ ዕለት መላእክት ለታማኝነቱ የክብር አክሊል አቀዳጅተውታል ። አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ በዓላት ሁለት ሲሆን ግንቦት 24 በስደት ወደ ግብፅ ሀገር የገባበት እንዲሁም ሐምሌ 26 ዕረፍቱ የሚታሰብበት ነው። የአባታችን የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ምልጃና ጸሎቱ  አትለየን።🙏

  • ከእስክንድርያ እንዲያሳድዷቸው አዘዘ። ንጉሡም ይህን አባት እጅግ ወደደው አከበረውም እንደወደደም አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን ይሠራ ዘንድ ፈቀደለት። እርሱም በምስር ሰሜን አልዋህ በሚባል አገር አብያተ ክርስቲያን ሠራ በሹመቱም ዘመን ሌሎች ብዙዎችን ሠራ። ካደረጋቸው ተአምራቶቹ ሌላው ይህ ነው ሚናስ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ ሙቶ ከተገነዘ በኋላ በዚህ አባት ጸሎት ተነሣ። የመነሣቱ ምክንያትም እንዲህ ነበር ይህ አባት ስምዖን በመላው አብያተ ክርስቲያናት ንብረት ንዋየ ቅድሳትና አልባሳት ላይ መጋቢ አድርጎ ይጠብቅ ዘንድ ቄሱን ሾመው። ሁልጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በቤትህ ውስጥ አታኑር እያለ ያዝዘው ነበር። ከዚህም በኋላ ድንገተኛ ደዌ አገኘውና አንደበቱና ጒረሮው ተጣጋ። ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምቶ እጅግ አዘነ ስለ አቢያተ ክርስቲያናትም ንብረት ያንን ቄስ ከሞት ያድነው ዘንድ በዚያች ሌሊት እግዚአብሔርን እየለመነ መላዋን ሌሊት ለጸሎት ተጋ። መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ያ ቄስ ለመሞት እንደተቃረበ ይህ አባት ሰምዖን ሰማ ስለ አቢያተ ክርስቲያናት ነብረት ይጠይቃት ዘንድ አዝዞ ወደ ቄሱ ሚስት ረዳቱን ላከ። ወደ ቄሱ ቤትም በቀረበ ጊዜ ሰዎች እያለቀሱለት ጩኸታቸውን ሰማ በገባ ጊዜም ሙቶ ልብሰ ተክህኖ መጐናጸፊያ ሲያለብሱት በዐልጋ ላይም ሲያስተኙት ብዙዎችም በዙሪያው ሲያለቅሱ አገኛቸው ያም ረዳቱ የቄሱን በድን ሊሳለም ዘንበል አለ። ያን ጊዜም ያ የሞተው ቄስ ተነሥቶ አቀፈውና የክቡር አባ ስምዖን ፈጣሪ እግዚአብሔር ሕያው ነው አለው። ረዳቱም በርታ አትፍራ አለው። ቄሱም በጌታው በአባ ስምዖን ጸሎት አዎ በእውነት ጸናሁ እግዚአብሔር ሕይወትን ሰጥቶ ከሞት አስነሥቶኛልና አለ። ያን ጊዜም ያ ረዳት ስለ መሞቱ ደንግጠው የነበሩትን ካህናት እነሆ ቄሱ ከሞት ተነሥቷል ብሎ ጠራቸው። ካህናቱና ሕዝቡም ወደርሱ በቀረቡ ጊዜ ቄሱ እንዲህ አላቸው እኔ ሙቼ እንደነበረ ዕወቁ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት አቆሙኝ ከአባት ሐዋርያ ማርቆስ እስከ አባ ይስሐቅ ያሉትን ሁሉንም የጳጳሳት አለቆች ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት ቁመው አየኋቸው እኔንም ከወንድማችን ከሊቀ ጳጳሳት ስምዖን የአብያተ ክርስቲያናትን ንብረት ለምን ሸሸግህ ብለው ገሠጹኝ። ያን ጊዜም ጌታ ክርስቶስ ይቺን ነፍስ በውጭ ወዳለ ጨለማ ውሰዱአት ብሎ አዘዘ። ሊወስዱኝም በጐተቱኝ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ዙፋን ፊት የጳጳሳት አለቆች ሰገዱ እንዲህ እያሉም ማለዱ ይህን ሰው አንድ ጊዜ ማረው ንብረታቸውን ስለሚጠብቅላቸው አብያተ ክርስቲያናት ብሎ ወንድማችን ስምዖን ስለ እርሱ እነሆ ቁሞ ይጸልያልና። ጌታችንም ልመናቸውን ተቀብሎ ነፍሴን ወደ ሥጋዬ መለሰ እንዲህም አለኝ እነሆ ስለ ምርጦቼና ስለ ወንድማቸው ስለ ሊቀ ጳጳሳት ስምዖን ማርኩህ አንተም የአብያተ ክርስቲያናትንም ንብረት ግለጥለት። አለዚያ ግን ወደዚህ እመልስሃለሁ የእነዚህንም ልመናቸውን ስለአንተ ሁለተኛ አልቀበልም። በዚያ የነበሩም ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ኀዘናቸውም ወደ ደስታ ተለወጠ ይህም ቄስ ይህን ተአምር ለሁሉ እየተናገረ ብዙ ዘመናት ኖረ። ይህም አባት ስምዖን በበዐቱ ውስጥ በገድል የተጸመደ ሁኖ ኖረ መንጋዎቹንም ያስተምራቸው፣ ይገሥጻቸውና በቀናች ሃይማኖትም ያጸናቸው ነበር። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ። † ሐምሌ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮጵያዊ) 2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት 3.መቶ ዘጠና ሺህ ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማኅበር) 4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ 5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮጵያዊ) 6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት 7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ † ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ) 3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ) ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በርከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)

  • ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ከእሳት እንዲጨምሩአቸውና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ደማቸው እስኪፈስ ድረስ እንዲገርፉአቸው አዘዘ። ዳግመኛም ስለታምና ረጃጅም በሆኑ ችንካሮች ሥጋቸውን ቸንክረው ከታች እሳትን አነደዱባቸው ጌታችንም መልአኩን ልኮ ከእሳቱ አዳናቸው። እንደገናም በታላቅ ዛፍ ላይ ዘቅዝቀው ይሰቅሏቸው ዘንድ አዘዘ። ከአፍንጫቸውና ከአፋቸው ብዙ ደም ወረደ ጌታችን ፈጣሪያችንም ከመላእክቱ ጋራ ወርዶ አዳናቸው መኰንኑም በፊቱ በቆሙ ጊዜ ከጽናታቸው የተነሣ እጅግ አደነቀ። ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ፈርማ ላካቸው መኰንኑም ለአማልክት ዕጣን አጢሱ አላቸው እምቢ በአሉትም ጊዜ ከኮምጣጤና ከሙጫ ጋራ ጨው ደባልቆ አፍልቶ በአፋቸውና በአፍንጫቸው ጨመረ እነርሱም ይህን ሁሉ ሥቃይ ታገሡ። ከዚህም በኋላ በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከታች እሳትን አነደዱባቸው የእጆቻቸውንና የእግሮቻቸውንም ጥፍሮች አወለቁ በብረት በትሮችም አጽንተው መቷቸው። በዚያን ጊዜም የመኰንኑ ሚስት ሞተች እርሱም ደንግጦ ይቅር እንዲሉት ሚስቱንም እንዲአስነሡለት ቅዱሳኑን ለመናቸው። እነርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመኑት ያን ጊዜም ተነሣች መኰንኑም ከሕዝቡ ሁሉ ጋራ በጌታችን አመነ ቅዱሳኑንም ወደ ሀገራቸው ይሔዱ ዘንድ ለቀቃቸው። ወደ ሀገራቸው ወደ ገምኑዲም በደረሱ ጊዜ የቀረ ገንዘባቸውን ለድኆችና ለችግረኞች ሰጡ የቅዱስ አንያኖስንም ሥጋ ስሙ ሰረባሞን ለሚባል አንድ ጻድቅ ሰው አደራ አስጠበቁት እንደቀድሞውም በፊቱ መብራትን እንዲአበራ አዘዙት። ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ሔደው በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። መኰንኑም እንዲገርፉአቸውና እንዲጐትቱአቸው አዘዘ ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ ደንቆሮና ዲዳ የሆነች ሴትም መጥታ ከቅዱሳኑ ደም ወስዳ አፏንና ጆሮዎቿን ልቧንም ቀባች ወዲያውኑም ድና ተናገረች ሰማችም። መኰንኑ ግን አሠራቸው ከዚህም በኋላ እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው። የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በዚያም ከገምኑዲ አገር ሰረባሞንና ሌሎች ሰዎችም ነበሩ በበፍታና በከበሩ ልብሶች ገነዙአቸው መዓዛው ጣፋጭ በሆነ ሽቱም ቀቡአቸው ወደ አገራቸው ወደ ገምኑዲም ወሰዱአቸው። ከገምኑዲም ከተማ ውጭ በደረሱ ጊዜ ሥጋቸው የተጫነበትን ሠረገላ የሚስቡ እንስሶች ቆሙ። ሥጋችን በውስጡ ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር የመረጠው ቦታ ይህ ነው የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ በዚያም አኖሩአቸው። ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው ሥጋቸውንም ከቅዱስ አንያኖስ ሥጋ ጋር በውስጥዋ አኖሩ በገምኑዲ አገርም ድንቆችንና ተአምራቶችን እያሳዩ እስከ ዛሬ ድረስ አሉ። ለእኒህ ቅዱሳንም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውንም እንደችሎታው ለሚያደርግ ኃጢአቱ ይሠረይለታል ሥቃይንም ከቶ አያይም ብሎ መከራ በሚቀበሉበት ጊዜ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። #ቅዱስ_አባ_በላኒ በዚህችም ቀን ከግብጽ ደቡብ አካ በሚባል አውራጃ ባራ በምትባል መንደር ይኖር የነበረ ቅዱስ ሰማዕት አባ በላኒ አረፈ። ይህም ቅዱስ ቄስ ነበር። የምእመናንን መከራቸውን የሰማዕታትንም መገደላቸውን በሰማ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጥቶ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመኰንኑ ፊት ታመነ መኰንኑም ጽኑ የሆነ ሥቃይን ብዙ ቀን አሠቃየው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀዳጀ። #አባ_ቢማ_ሰማዕት በዚህችም ዕለት ከላይኛው ግብጽ ከብህንሳ ከተማ አባ ቢማ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ሰው ባለጸጋና በጎ የሚሠራ ድኆችንም የሚወድ በሀገርም ላይ የተሾመ ነበር። በአንዲት ዕለትም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በራእይ ፊቱ ከፀሐይ ብርሃን እጅግ እየበራ አየው እንዲህም አለው ሰላም ለአንተ ይሁን ወደ መኰንኑም ሒደህ በስሜ ታመን። እኔ የክብር አክሊልን አዘጋጅቼልሃለሁና። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ተነሥቶ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ። ከዚህም በኋላ ጸሎት አድርጎ ከቤቱ ወጣ ሉቅያኖስ ወደሚባል መኰንንም ሒዶ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም በአየው ጊዜ ሹም እንደሆነ አውቆ ከእርሱ ንዋየ ቅድሳትን ፈለገ ዳግመኛም ለአማልክት እንዲሠዋ ፈለገ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ስለ ንዋየ ቅድሳት ከእኔ ልትሻ አይገባህም የረከሱ አማልክትንም ስለማምለክ ትእዛዝህን አልሰማም እኔ ሰማይንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁና። መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ ተቆጥቶ ምላሱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም እንደ ቀድሞው ምላሱን መለሰለት። ከዚህ በኋላ በማበራያ ውስጥ አበራዩት በብረት ዐልጋ ላይም ቸንክረው በበታቹ እሳትን አነደዱ እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጉዳትም አስነሣው። ከዚህ በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገልጾለት አጽናናው ከዚህም በኋላ በወህኒ ቤት ጨመሩት በዚያም ተአምራትን አደረገ። ጋኔን ያደረባት የአቅፋሃስ ሀገር ሰው የዮልያኖስ እኅት ነበረች ቅዱስ ቢማም ያንን ጋኔን ከእርሷ ላይ አወጣውና አሳደደው ዜናውም በሀገሩ ውስጥ በተሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብዙዎች አመኑ። መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃየው በመንኰራኵርም የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች አወለቁ በእሳት በአጋሉት በብረት ሰንሰለትም አሥረው ጐተቱት። በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥም ጣሉት ከዚህም ጌታችን አዳነው። ከዚህም በኋላ በአንገቱ ታላቅ ደንጊያ አንጠልጥለው በባሕር ውስጥ ጣሉት አሁንም ጌታችን አዳነው። ሁለተኛም ከእሳት ጨመሩት። ከዚህም ጌታችን አዳነው በእሳቱም መካከል እየጸለየ ቆመ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያም ያሠቃዩት ጀመሩ ዘቅዝቀውም ሰቀሉት ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ ጨምረዉ በላዩ እሳትን አነደዱበት ጌታችንም ተገለጠለትና ከእሳቱ አዳነው። ከዚህም በኋላ ጌታችን ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉን ለሚጽፍ በስሙም ምጽዋት ለሚያደርግ ሁሉ የዘለላም ሕይወትን ያድለው ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጠው። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንደ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማይ ተቀበለ። የአቅፋሃስ ከተማ ሹም የሆነ የዮልዮስ ባሮችም ሥጋውን አንሥተው ወደ ሀገሩ ወሰዱት እስከ ስደቱ ዘመን ፍጻሜ ድረስም በመልካም ቦታ አኖሩት። ከዚህም በኋላ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያንንና ገዳምን ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ በሽተኞችም ሁሉ ይፈወሱ ነበርና። † ሐምሌ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ኪሮስ ጻድቅ (አረጋዊና ገዳማዊ) 2.አባ ብሶይ ጻድቅ (ኮከበ ገዳም) 3.አባ ሚሳኤል ነዳይ (ጻድቅ) 4.አባ ቢማ ሰማዕት 5.አባ በላኒ ሰማዕት 6.ቅዱሳን አቤሮንና አቶም (ሰማዕታት) † ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 4.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ)

  • #ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ https://youtu.be/T2kITq7AIZc?si=OKqq9tyTJ6Yy-B1C

  • #ሰኔ_26 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን የከበረ #የመላእክት_አለቃ_የቅዱስ_ገብርኤል በዓሉ ነው እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው፣ የታላቁ ነቢይና መስፍን የነዌ ልጅ #የቅዱስ_ኢያሱ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ገብርኤል ሰኔ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ የገብርኤል በዓሉ ነው እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው። በውስጧም ከቤተ ክርስቲያንዋ የጣራ ዕንጨት ብዙ ተአምር ይገለጽ ነበር ጽጋብ በሚሆንባት በዚያች ዓመት ውኃ ይንጠፈጠፋል ረሀብ ከሆነ ግን ላብ እንኳ አይታይም ነበር። የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ተአምራቶቹ ብዙዎች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ኢያሱ_ነቢይ_ወመስፍን በዚህችም ቀን የታላቁ ነቢይና መስፍን የነቢያት አለቃ የሙሴ ደቀ መዝሙር የነዌ ልጅ የኢያሱ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ከታናሽነቱ ጀምሮ ለሙሴ አንገቱን ዝቅ አድርጎ የሚታዘዝ ፍጹም ትሑት ሆነ ስለዚህም በሙሴ ላይ ያደረ መንፈስ ቅዱስ አደረበት። ነቢዩ ሙሴም ከአረፈ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የእስራኤልን ሕዝብ ተረከባችው። እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው ከሙሴ ጋራ እንደኖርሁ ከአንተም ጋራ እኖራለሁ ጽና በርታ ለባለሟሌ ሙሴ ያዘዝሁትን ሕጌን ጠብቅ ከእርሱም ፈቀቅ አትበል ሕጉንም ትጠብቀውና በሱም ትጸና ዘንድ በውስጡም የተጻፈውን ታደርገው ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንደበትህ ማንበብን አያቋርጥ። የኢያሱም ልቡ ጸና ሰላዮችንም ወደ ኢያሪኮ ላከ ሀገሪቱንም አይተው ሲመለሱ የኢያሪኮ ሰዎች አዩአቸው ሰላዮችም እንደሆኑ አውቀው ተከተሏቸው። እነርሱም ረዓብ በሚሏት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሸሸጉ እርሷም ሠወረቻቸው እነርሱም በሚመጡ ጊዜ ከቤተሰቦቿና ከዘመዶቿ ጋራ እንደሚያድኗት ቃል ገቡላት። በደኅናም ሸኘቻቸው። ከዚህም በኋላ ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ አሻገረ ካህናቱ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ተሸክመው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ቆመው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እስከሚሻገሩ ድረስ የወንዙን ውኃ እግዚአብሔር እንደ ግድግዳ አቁሞት ነበርና። ከዚህም በኋላ ደግሞ በግንብ የተከበበች ኢያሪኮን ሰባት ቀን ዞራት ከእርሱም ጋራ የልዑል ታቦተ ሕጉ ነበረች ቅጽሮቿንም አፈረሰ በውስጧም የሚኖሩ አሕዛብን ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር ገደለ ሁሉንም አጠፋቸው። አሕዛብ ሁሉ የእስራኤልን ልጆች ፈሩአቸው ከመፍራታቸውም ጽናት የተነሣ የገባዖን ሰዎች ተንኰል አደረጉ ስንቃቸውን ሰንቀውና አዘጋጅተው መጡ አሮጌ አቁማዶቻቸውን ያረጁና የተቀደዱ የተጠቀሙም የወይን ረዋቶችን በትክሻቸው ተሸከሙ። ጫማቸውም ያረጀና የተተበተበ ነበር ልብሳቸውም በላያቸው ያረጀ ነበር። ለስንቅም የያዙት እንጀራ የደረቀና የሻገተ ነበረ። ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ወደ ገልገላ መጥተው እኛ ከሩቅ አገር መጥተናል አሁንም ለእኛ ማሉልን አሏቸው። የእስራኤልም ልጆች ኤዎያውያንን ከእናንተ ጋራ እንዴት መሐላን እንማማላለን አሁንም በአቅራቢያችን ትኖሩ እንደሆነ ተጠንቀቁ አሏቸው። ኢያሱንም እኛ ከሩቅ አገር የመጣን ባሮችህ ነን አሉት እርሱም ከወዴት ናችሁ ከወዴትስ አገር መጣችሁ አላቸው። እነርሱም እኛ ባሮችህ በፈጣሪህ በእግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ አገር መጣን በግብጻውያን ያደረገውን ሁሉ በዮርዳኖስ ማዶ በሚኖሩ በሁለቱ በአሞሬዎን ነገሥታትም ያደረገውን ሁሉ ሰምተን መጥተናል አሉት። የአገራችን ሰዎች ሁሉና አለቆቻችን ለመንገድ ስንቅ ያዙ ትቀበሏቸውም ዘንድ ሒዱ እኛ ባሮቻችሁ ነን አሁንም ለእኛ ማሉልን በሉአቸው አሉን። እነሆ ወደእናንተ እንመጣ ዘንድ ከቤታችን በወጣንበት ቀን ይህ እንጀራችን ትኩስ ነበር አሁን ግን ሻግቷል ደርቋልም ይህም የወይን ረዋት አዲስ ሳለ መላንበት አሁን ግን ተራቁቷል አርጅቶም ተቀድዷል መንገዳችን እጅግ የራቀ ነውና ይህም ልብሳችን ይህም ጫማችን አርጅቷል አሏቸው። መኳንንቱም ስንቃቸውን ተቀብለው አዩ የእግዚአብሔርንም ቃል አልጠየቁም ኢያሱም ከነሱ ጋራ ሰላምን አደረገ ሊያድናቸውም ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ የሕዝቡም አለቆች ማሉላቸው። ከሦስት ቀን በኋላም እስራኤል ከቅርብ እንደሆኑ ሰሙ። ኢያሱም በቅርብ እንደሆኑ በሰማ ጊዜ በሽንገላ ለምን ወደእኛ መጣችሁ አሁንም ለእግዚአብሔር ቤትና ለእኛ ባሮች ትሆናላችሁ አላቸው። የአሞሬዎን ነገሥታትም የገባዖን ሰዎች ሔደው ለእስራኤልና ለኢያሱ እንደ ተገዙ በሰሙ ጊዜ እነዚህ አምስቱ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬብሮን ንጉሥ፣ የኢያሪሞት ንጉሥ፣ የለኪሶ ንጉሥ፣ የአዶላም ንጉሥ ተሰብስበው ዘመቱ መጥተውም ገባዖንን ከበቡአት ሊዋጉም ጀመሩ። የገባዖን ሰዎችም በገልገላ ውስጥ ወደ እስራኤል ሰፈር ወደ ኢያሱ ልከው ባሮችህን ለመርዳት እጅህ አትስነፍ ከተራሮች ላይ የሚኖሩ የአሞሬዎን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ወደ እኛ መጥተህ ርዳን ፈጥነህ አድነንም አሉ። ኢያሱም ከገልገላ ወጣ ሰልፈኞችም የሆኑ ሕዝብ ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው በእጅህ እጥላቸዋለሁና በፊታችሁም አንድ ስንኳ የሚቀር የለምና አትፍሯቸው አለው ኢያሱም ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት በሌሊት ደረሰባቸው። እግዚአብሔርም ከእስራኤል ፊት የተነሣ አስደነገጣቸው ኢያሱም ብርቱ ጥፋትን አጠፋቸው ከእነርሱም ወደ ቢቶሮን ቍልቍለት በሸሹትም እግዚአብሔር የበረድ ድንጋይ ከሰማይ አውርዶ ጨረሳቸው። የእስራኤል ልጆች በጦራቸው ከገደሏቸው በደንጊያ በረዶ የሞቱ በዙ። ያንጊዜም እግዚአብሔር አሞሬዎንን በእስራኤል ልጆት እጅ አሳልፎ በሰጣቸው ጊዜ ኢያሱ ፀሐይ በገባዖን ጨረቃም በኤሎም ቈላ ትቁም ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ ፀሐይና ጨረቃም ቆሙ። ጠላቶችንም ሁሉንም አጠፋቸው ከእነርሱም የቀረ የለም። ከዚህም በኋላ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ርስትን አካፈላቸው ያለ ዕውቀት በስሕተት ሰው የገደለ በውስጡ ይማጠን ዘንድ ስባት መማጸኛ ከተሞችን እግዚአብሔር እንደ አዘዘው ሠራ። ዕድሜውም መቶ ሃያ በሆነው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሰበሰባቸው የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ በአምልኮተ እግዚአብሔርም እንዲጸኑ ትእዛዞቹንም እንዳይተላለፉ አዘዛቸው። እንዲህም አላቸው እርሱ ፈጣሪያችን ቀናተኛ ነውና ጣዖት ብታመልኩ ያጠፋችኋል ሕጉን ብትጠብቁ ግን የበረከት ልጆች ትሆናላችሁ። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ያዕቆብ ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች በገዛው ናብሎስ በሚባል ቦታም ተቀበረ ሠላሳ ቀኖችም ያህል ታላቅ ልቅሶ አለቀሱለት። † ሰኔ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን 2.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ቅዳሴ ቤቱ) † ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ 3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)

  • https://vt.tiktok.com/ZSQ2PsUoq/

  • видео или голосовое, без подписи

  • Channel name was changed to «የአባ ሚዲያ»

  • Channel photo updated

  • በአረፈም ጊዜም በመርከብ ጭነው ወደ ቆጵሮስ ከተማ አደረሱት። ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ መጡ ከሳቸውም ጋር ወንጌሎች መስቀሎች መብራቶችና ማዕጠንቶችም ይዘው ነበር የሐዋርያት ጉባኤ ከታላቂቱ ቤተ ክርስቲያን እስኪያደርሱት በዝማሬና በማኅሌት በሚገቡት ጸሎቶች ሁሉ እያመሰገኑ ሥጋውን ተሸከሙ። ካህናቱም መቃብሩን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ሊያዘጋጁ ወደዱ። ቀድሞ ስለ ክፉ ሥራቸው ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አውግዞአቸው የነበሩ ሁለት ዲያቆናት ተቃወሟቸው። ስለዚህም አርባ ቀን ተቀመጠ ነገር ግን ሽታው እንደ ሙታኖች ሽታ አልተለወጠም እንደ አንቀላፋ ሰው ሆነ እንጂ። ከዚህም በኋላ አንድ ደግ ዲያቆን ወደ ቅዱሱ ሥጋ ቀርቦ አባቴ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ አንተ ባለሟልነት እንዳለህ እኔ አውቃለሁ። ብትፈቅድስ ክፉዎች ተቃዋሚዎችን ልታሸንፋቸው ትችላለህ አለ። የቅዱስ ኤጲፉንዮስንም እጅ ይዞ ምድሩን መታባት በዚያንም ጊዜ ሁለቱ ዲያቆናት በግምባራቸው ተደፉ። ለመሞትም ደረሱ ወደ ቤታቸውም ወስደዋቸው ሞቱ። ቅዱስ ኤጲፋንዮስንም ካህናቱ በሚጣፍጡ ሽቱዎች ገነዙት። በከበሩ ልብሶችም ጠቅልለው ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥ ጨምረው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ቀድሞ በሕይወቱ ሳለ እንደሚሠራው ከሥጋው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። =>ግንቦት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት (ገዳማዊት) 2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት) 3.አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ 4.አባ ጌርሎስ (ጻድቅና ሰማዕት) 5."45" ሰማዕታት (የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት) 6.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት =>ወርኀዊ በዓላት 1.አማኑኤል ቸር አምላካችን 2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ) 3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት) ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)

  • ☦️ቅዱስ_ዮሴፍ☦️ ☦️ወር በገባ በ 26 እመቤታችን በስደቷ ወቅት እንኳን ያልተለያት የእመቤታችን ጠባቂ የአባታችን አረጋዊ ዮሴፍን ወርሐዊ መታሰቢያቸው ፡፡ በዕብራይስጥ ቋንቋ ድኅነት ለሚባለው ለስምህ አጠራር ሰላምታ ይገባል ☞መከራንና ጭንቅን የታገሠ የድንግል ሕፃን አምላክ በሥራው ከፍ ከፍ ያደረገው ለስምህ አጠራር ሰላምታ ይገባል፡፡ ሕፃኑንና እናቱን በመያዝ ወደ ግብጽ ምድር በወረድህ ጊዜ እንባ ማኅተሙ ለሆነለት ፊትህ ሰላምታ ይገባል፡፡ የክብራን አለቃቸው የሆንክ ከክቡራን ሁሉ የምትቀድም ዮሴፍ ሆይ በግብጽ ምድር ደማቸው ለፈሰሰና ለተዋጁ መጀመሪያቸውና መሪያቸው አንተ ነህ፡ ☞መልኩ የከፋ የመከራ ፊት ስደትን በአንድነት ለሚያዩ ዐይኖችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ☞በድንግል እቅፍ የተቀመጠውን የሰማያዊ አምላክ ቃል ዘወትር ለሚሰሙ ጆሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ከድካም የተነሣ የመነጨውን የድንግል ፊት ደም ግባት ወዝ በላያቸው ለተሣሉባቸው ጉንጮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ በበረሀ የምትኖር የግብጽ ምድር አንበሳ ዮሴፍ ሆይ የአብ አካላዊ ቃል ወልድን በአፋ ይሰሙ ዘንድ ከአባቶች ዕድልን ያገኘ እንደ አንተ ያለ ማን ነው፡፡ ☞ዮሴፍ ሆይ ከስደት ቅርጫፍ የተገኘ የልቡና ኅዘን አበባን ባለ መረጋጋት ለአሸተቱ አፍንጫዎችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ልጆችህን የተውህ የግብጽ ምድር ባሕታዊ ዮሴፍ ሆይ ከማርያም ከልጇ ጋር እውነትን እየተነጋገሩ ፈጽመው ዝም ለማይሉ ከንፈሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ አረጋዊ ዮሴፋ ሆይ በዚች ምድር ደግ ሰው አልቋልና ፈጽመህ አድነን፡፡ ☞ሰሎሜ በምታዝለው በልጇና በድንግል ፊት በሥርዐት ሊሚናገር አፍህ ሰላምታ ይገባል፡፡ዮሴፍ ሆይ ከቸርነትህና ከሃይማኖት የተነሣ ድህነት እንድታመጣለኝ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው አምላክ የተቀበለውን የአማላጅነትህ ፀጋህን አገኝ ዘንድ ዕድሜ ይሰጠን፡፡ ፍጻሜ የሌለብህ የአብ ልጅ ፈመን የሆንክ ዮሴፍ ሰሎሜን የምታዝለው የድንግል ልጅ አምላክ በመጀመሪያ ለመሣመው አፈህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ☞ዓለምን የሚቃጥል የሚያስፈራ የእሳት ነበልባል ጌታ በመጠኑ ለዳሰሱ እጆችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ኑሮህ ገዳም የሆነ የናዝሬቱ ባሕታዊ ዮሴፍ ሆይ በሥጋና በደም በኩል እኅትህ ከሆነች ሰሎሜ ጋር ከወልድና ከእናቱ ዘንድ ስለ ኢትያጵያና ሕዝቦቿ ለምንልን፡፡(መልክአ ዮሴፍ)       😇"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" ምሳ📖📖 🌟፥🌟🌟                      ☦️☦️☦️

  • 🌿✨ የኢትዮጵያ የብርሃን ሰረገላ፦ ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ✨🌿 ​"ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢነዳ በነፍሱ ከተጎዳ ምን ይጠቅመዋል?" (ማቴ. 16÷26) 📖 በእምነትና በትሩፋት የጸኑት የአባታችን የአቡነ ሀብተማርያም ዜና ገድል ለነፍስ ምግብ ለሥጋ መድኃኒት ነው! 💖 ​🕊️ ትውልድና ቅዱስ አጀማመር ​በ1486 ዓ.ም በንጉሥ እስክንድር ዘመን፣ በራውእይ ምድር ከባለጸጋው ፍሬ ብሩክ እና ከደግዋ ዮስቴና ተወለዱ። 🤱✨ እናታቸው ዓለምን ንቃ በበረሃ በምትጋደልበት ወቅት፣ አንድ ባሕታዊ ባያት ጊዜ፦ "ከአንቺ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም፣ ዜና ገድሉ እስከ ዓለም ዳርቻ የሚደርስ፣ ነፍሳትን ከሲኦል የሚያወጣ ታላቅ ልጅ ትወልጃለሽ" በማለት ትንቢት ነገራት። 🌟🔗 ​አባታችን ግንቦት 26 ቀን ተወልደው በ40 ቀናቸው ሀብተማርያም ተብለው ተሰየሙ። 💒 ሕፃን ሳሉ በቤተክርስቲያን "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" የሚለውን ጸሎት ሰምተው በልባቸው በማሰር፣ እንደ ፈጣን ፈረስ 🐎 እየሮጡ ይሰግዱ ነበር። ​🛡️ የጽናትና የተአምራት ሕይወት ​አባታችን በግ ጠባቂ ሳሉ የታዩባቸው ድንቅ ተአምራት የእግዚአብሔርን ክብር ገልጠዋል፦ • ​የእሸቱ ተአምር፦ 🌾 ሰርቀው እሸት ሊያበሏቸው የሞከሩ እረኞችን "ከየት እንደመጣ አላውቅምና አልበላም" በማለት እምቢ አሉ። በላያቸው ላይ የሚመጣውን መቅሠፍት አስቀድመው በማወቅም ወደ ቤታቸው በመግባት ከጥፋት ውኃ ተረፉ። 🌧️🚫 • ​እንደ ሳሙኤል መጠራታቸው፦ 🗣️ ጌታችን በሌሊት ሦስት ጊዜ "ሀብተማርያም" ብሎ ጠራቸው። አባታችንም "ጌታዬ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር" በማለት በምስጢር ከፈጣሪ ጋር መነጋገር ጀመሩ። 🤝✨ • ​የበትሩ ተአምር፦ 🦯 በጉልበት በትራቸውን የቀማቸውን እረኛ፣ በጸሎታቸው ኃይል በአየር ላይ ሰቅለውታል። በኋላም በእመቤታችን ስም ሲለምኑት ይቅር ብለው አውርደውታል። 🏇🔥 ​📜 ለአቡነ ሀብተማርያም የተሰጠ ድንቅ ቃልኪዳን ​ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሃድ ተገልጦ ለአባታችን እንዲህ የሚል ታላቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው፦ ✍️💎 👉• ​የብርሃን ሰረገላ፦ 🏎️✨ የማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል ባነበቡ ጊዜ ወደ ፈለጉበት ቦታ የሚያደርሳቸው የብርሃን ሰረገላ ተሰጣቸው። 👉• ​የእሳት ሰረገላ፦ 🔥 ሰማያዊቷን ኢየሩሳሌም ለመሳለምና ሥጋ ወደሙን ለመቀበል የሉቃስንና የዮሐንስን ወንጌል ሲያነቡ የሚጭናቸው የእሳት ሰረገላ ተሰጣቸው። 👉• ​ለምሕረት፦ 🤝 በሕይወት ሳሉ ልብሳቸውን የሰጠ፣ ምግብ ያበላ፣ ውኃ የቀዳ ወይም ስማቸውን ጠርቶ የዘከረ ሁሉ መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርስ ቃል ተገባላቸው። 👉• ​ከመከራ ለማዳን፦ 🛡️ ሰውን ከቸነፈር፣ ከእሳት፣ ከመብረቅና ከረሃብ እንዲያድኑ እንደ ሐዋርያት ሥልጣን ተሰጣቸው። ​✍️ የድልና የክብር ስንኝ ​በራውእይ ምድር የበቀልህ ጽጌ፣ 🌹✨ የማርያም ሀብት ነህ የመንፈስ በረከት የጸጋዬ አጥቢያ። ☀️ እንደ ሳሙኤል በሌሊት ተጠርተህ፣ 🗣️🌙 ከፈጣሪህ ጋር በሚስጥር ተዋህደህ። 🤝🔗 ​በብርሃን ሰረገላ ሰማይ የምትበር፣ 🏎️💨 የገዳማት አባት የሚስጥር መዝገብ የጽድቅ መከመር። 💒 በትርህ ስትነሳ ጠላት ይንቀጠቀጣል፣ 🦯💥 ጸሎትህ ሲደርስ ነፍስ ከሲኦል ይወጣል። ⛓️🔓 ​የወንጌል አርበኛ የጽናት ተምሳሌት፣ 📖🛡️ ለሀገራችን ሁን የእምነት መሠረት።

  • ༄𝕫𝕚𝕡ራ: ♡ ማነው ማርያምን ተው አትጥራት የሚለኝ ♡ ማነው ማርያምን ተው አትጥራት የሚለኝ ስሟን ሳወድሳት የሚከለክለኝ የእርሱን ነፃ ፈቃድ እየተጠቀመ የእኔን ነፃ ፈቃድ ለምን ተቃወመ የአንቺን ወዳጅነት አጥብቄ ስለያዝኩ በፀረ ማርያሞች ብሆን የተወገዝኩ መቼም ቅር አይለኝ ደስተኛ ነኝ እኔ የእናትና ልጁ ወዳጅ በመሆኔ ተዋት ሲሉኝማ ብሶብኛል ጭራሽ እያልኳት በሀዘኔ ነሽ በጭንቄ ደራሽ በሚጠሏት መሀል ስሟን እየጠራሁ የጠላቴን ጭንቀት ሀዘን አበዛለሁ ከፅንሰት ጀምሮ እስከ እርገቱ ድረስ ያልተለያዩትን ሊለይ ክፉ መንፈስ እንቅልፉን በማጣት ሌተቀን ቢዞርም ሲያምረው ይቅር እንጂ ማርያማን አልተውም ይከፋዋል ብዬ ወዳጅና ዘመድ አልል ወደ ኋላ ማርያምን አልተውም በውስጣቸው ያለው የእመቤቴ ጠላት ስሟን ሰምቶ ይቃጠል በጩኸት ስጠራት ፅዮንን ክበቧት እናታችን በሉ የተባለው ትንቢት እንዲፈፀም ቃሉ ቀራንዮ ላይ ሰጠን ምስጋና ለእግዚአብሔር ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እያላት እንዲኖር በችንካር በጅራፍ በደም የታጠበ በከባድ ስቃይ ውስጥ ስለኛ አሰበ የሚወዳት እናቱን ለሚወደን ሰቷል ታድያ ፍቅር ሌላ በምን ይገለጣል  ጠራው ደጋግሜ ሱስ ሆኖብኝ ስሟ ስለራቀ በእርሷ የሔዋን መርገሟ ያልፍ ይሆናል እንጂ የምለው አይበዛ የልጇ ቤዛነት ነብሴን ስለገዛ ማርያም ማርያም ይላል ቢመረመር ደሜ አርጋልኝ እንዲፃፍ በህይወት መዝገብ ስሜ ጠላት እስከሚያጣ ስሟን ማይሰማበት አወድሳታለው በቀንም በሌሊት መምህር ምሕረታብ ተስፋ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ @maedot_ze_orthodox ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ ♡ ማርያም ድንግል ♡ ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል ይእቲኬ ቤተ ምስአል ዘአስተዐፀቡ ታቀልል ለኩሉ ፍጥረት ትተነብል በአክናፈ መላእክት ትትኬለል ይእቲ ተአቢ እም ኪሩቤል ወትፈደፋድ እም ሱራፊል ትርጉም፡- ማርያም ድንግል መመኪያቸው የደናግል እርሷም እኮ የምልጃ ቤት ናት የሚያሰጨንቀውን የምታቃልል ለፍጥረት ሁሉ ትማልዳለች በመላእክት ክንፎችም ትጋረዳለች እርሷ ትበልጣለች ከኪሩቤል ደግሞ ትልቃለችለች ከሱራፌል መዝሙር በማህበረ ቅዱሳን ዘማርያን ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ @Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ ♡ የወርቅ መቅጃ ነሽ ♡ አንቺ የወርቅ መቅጃ ነሽ እኔ የተጠማሁ ነኝ ልጅሽ የሕይወት ውሃ ከጥሜ የሚያረካኝ እኔ ተሻጋሪ ነኝ ማርያም ሆነሽኝ ድልድይ ልጅሽ አሻጋሪዬ ነው ከርስቴ የሚያስገባኝ እኔ እርቃኔን ነኝ ከጸጋው ርቄ በክፉ ግብር በኃጥያት ወድቄ ማርያም አንቺ ነሽ የሸማኔ እቃ 'ልጅሽ ልብስ ነው ለሁሉ የሚበቃ/2/ አንቺ መርከቤ እኔም ነጋዴ ልጅሽ ዕንቁዬ ትርፌ ዘመዴ ለእኔ ለደሃ መከማቻዬ 'የከበረ ጌጥ ልጅሽ ቤዛዬ/2/ እኔ ተጓዥ አንቺ መቅዘፍያ ልጅሽ ወደብ ነው የሕይወት ማረፍያ አንቺ ፊደል ነሽ እኔ ተማሪ 'ልጅሽ ወንጌል ነው ቸር አስተማሪ/2/ ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ @Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ ♡ ስምሽን ስጠራው ♡ ስምሽን ስጠራው ድንግል ስምሽን ስጠራው ማርያም ላንደበቴ ማር ነው ለልቤ ሰላም ስምሽን ስጠራው ማርያም ትውልድ ነኝና ልጅሽ የፈጠረኝ ድንግል እመቤቴ ላንቺ ምስጋና አለኝ በፈቃደ እግዚአብሔር በአባቶቼ ፀጋ ሰዓሊ ለነ እላለው ሲመሽም ሲነጋ በጠየቅሽው ጊዜ ወይኑን እንዲመላ አክብሮሻልና በቃና ገሊላ የሰላም እናት ሆይ ሰላም ልበልሽ ዘመኔ ይፈፀም ሳመሰግንሽ በሰላምታ ድምፅሽ መንፈስ ተመልቼ አደግድጌ ልቁም እጆቼን ዘርግቼ በአብይ ቃል ጮሄ ልመስክር በብርቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናቱ ከሰማይ ሲገኝ ነው አንችን ማወደስ ሲገለጥ ሲፈቀድ ከመንፈስ ቅዱስ ማርያም ህይወቴ ነሽ ምክንያት ለመዳኔ ብዙ ነው ምስጢሩ አንችን ማመስገኔ ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ ♡ ማርያም ማርያም ብዬ ♡ ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወለደኝ/2/ ገና በማህፀን በእናቴ የምጥ ቀን ደጋግሜ ሰማሁ ሲጠሩት ስምሽን በሰከንዳት እድሜ የማውቃት አንዲት ቃል ልቤላይ ያለው ስም ማርያም ማርያም ይላል ማርያም...ማርያም አዝ= = = = = ሔዋን ምጧ ቀሎ ልጆቿን ታቀፈች በአመላጅነትሽ እናቴም ታመነች በተወለድኩባት በመጀመሪያው ቀን ስምሽን እየሰማሁ ወጣሁ ከማህፀን ማርያም...ማርያም አዝ= = = = = ከቃልኪዳን ስም ጋር አደኩኝ አብሬ ምልጃሽ ሳይለየኝ አለሁ እስከዛሬ የሕይወቴን ፈደል ካንቺ ላይ ቆጠርኩኝ በልጅሽ አምኜ ዳግም ተወለድኩኝ ማርያም...ማርያም አዝ= = = = = የክፉ ቀን ስንቄ ያዘልኩሽ በልቤ የሕይወቴ ምግብ እንጀራ መሶቤ እንደትላንትናው ዛሬም እጠራሻለሁ የመስቅል ስር ክብሬን እንዴት እረሳለሁ የመስቅል ስር ክብሬን እንዴት እተዋለሁ ማርያም...ማርያም ❤️❤️❤️ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

የአባ ሚዲያ — tgindex