tgindex
👆🏻የዲኔ ጉዳይ ያገባኛል👆🏾

👆🏻የዲኔ ጉዳይ ያገባኛል👆🏾

Статистика

በዚህ ቻናል ♦️#ተውሒድና_ሱና በሰለፎች አረዳድ ብቻ ከተለያዩ የሰለፊያ መሻይኾችና ኡስታዞች ትምህርት ይቀርባል። ♦ እንዲሁም ሙስሊሙን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን እናጋራለን ተቀላቀሉ ولقد بعثنا في كل أمة رسولاً عن اعبد الله واجتنبوا الطاغوت https://t.me/yedine_guday ሀሳብ እስተያየቶን በ👇ያድርሱን @Yedinegudaybot

Последний пост
20 июл.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
644
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
93
26 постов
Вовлечённость
14,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 26
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
33
1/48двое суток
37
1/72трое суток
40

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በተገለልን ግዜ አመፆችን መዳፈር ... መስጂዶች ውስጥ ከቁርአን ፣ ኪታብ ጋር እየሆንን ስንገለል ወንጀሎችን የምናተራምስ ከሆነ በርግጥም እየረከስን ነው ! ኧረ አሏህን እንፍራ ! ከደርስ የተቆረጠ ምክር ሙሐመድሲራጅ ሙ ኑር https://t.me/MerkezulimamiAhmed

  • የእውነተኛ ተውበት ማሳያ... የተቡክ ዘመቻ አልፎ ነቢዩ (ﷺ) ወደ መዲና ተመለሱ፡፡ ሙናፊቆች እየመጡ ሀሰተኛ ምክንያት እየደረደሩ ማሉ፤ ነቢዩም (ﷺ) ውጫዊ ሰበባቸውን ተቀብለው ይቅር አሏቸው፡፡ ተራው የካዕብ ኢብኑ ማሊክ ደረሰ፡፡ ካዕብ እንደ ሙናፊቆቹ ውሸት መደርደር፣ ማምለጫ መፈለግ ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን እርሱ ለአላህና ለረሱሉ (ﷺ) እውነተኛ መሆንን መረጠ፡፡ ወደ ነቢዩ (ﷺ) ቀረብ አለና፡ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንም ዓይነት ሰበብ የለኝም፤ ከዚህ በፊት እንደ አሁኑ ተመችቶኝ አያውቅም» በማለት እውነቱን ተናገረ፡፡ ነቢዩም (ﷺ)»ይህ ሰውማ እውነቱን ተናግሯል» አሉ፡፡ ነገር ግን እውነተኛነቱ ወዲያውኑ ምቾትን አላመጣለትም፤ ይልቁኑ ትልቅ ፈተናን እንጂ፡፡ አላህ ፍርዱን እስኪያወርድ ድረስ ነቢዩ (ﷺ) ማንም ሰው ከካዕብና ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር እንዳያወራ ከረረ ያለ እገዳጣሉ፡፡ ያቺ ሰፊዋ መዲና በካዕብ ላይ ጠበበችበት፡፡ ምድር መረጋጋጫ አጣችለት፡፡ ሰላምታ የሚመልስለት፣ ቀና ብሎ የሚያየው ሰው ጠፋ፡፡ ለአምሳ ቀናት ሙሉ በፀፀት እሳት እየነደደ፣ ሌትና ቀን እምባውን እየዘራ ወደ ጌታው አለቀሰ፡፡ በዚህ መሃል የሻም ንጉስ የችግሩን ጊዜ ተጠቅሞ በደብዳቤ ሊያታልለውና ሊያሸፍተው ቢሞክርም፣ ካዕብ ግን ደብዳቤውን እሳት ውስጥ በመክተት ለአላህና ለረሱል ያለውን ታማኝነት አረጋገጠ፡፡ በሃምሳኛው ቀን ንጋት ላይ፣ የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው አላህ እውነተኛነታቸውን አውቆ፣ ከሰማያት በላይ ተውበታቸውን መቀበሉን የሚገልጽ አንቀጽ አወረደ፡ የመዲና ተራሮች በደስታ ድምፅ አስተጋቡ! «ያ ካዕብ ሆይ! የምስራች!» የሚል ጩኸት መዲናን አናወጣት፡፡ ካዕብ በደስታ ብዛት ወዲያውኑ ለአላህ ሱጁድ ወረደ፡፡ ወደ መስጂድ ሲሮጥ ሰሐቦች በደስታ ከበውት እንኳን ደስ አለህ ይሉት ጀመር፡፡ ነቢዩም (ﷺ) ፊታቸው እንደ ጨረቃ በደስታ እያበራ፡ «እናቱ ከወለደችህ ጀምሮ ካለፉት ቀናት ሁሉ በበለጠ በላጭ በሆነው ቀን የምስራች!»አሉት፡፡ ካዕብም በደስታ እያለቀሰ፡ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህ ያዳነኝ በእውነተኛነቴ ነው፤ ከእንግዲህም በህይወቴ እውነትን እንጂ አልናገርም» አለ፡፡ አላህ የከዕብ አይነት ተውበት ይወፍቀን! t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

  • ለአላህ ብየ እወድሃለሁ። ታላቁ ባለውለታችን ውዱና የተከበርከው የተውሒዱ አርበኛ የሱናው ሰባኪ ኡስታዛችን ኡስታዝ ሳዳት ከማል። አላህ ይጠብቅህ። ረዥም እድሜ ከዓፊያና ከመልካም ስራ ጋር አላህ ይወፍቅህ። = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

  • ሓዲስን አለመቀበል፣ ቁርኣንን አለመቀበል ነው https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

  • «አህሉል አሠር» የሞባይል አፕልኬሽን ይህ መተግበሪያ የተለያዩ ኢስላማዊ ደርሶችን በደረጃና በስርዓት ለመማር እጅግ አመቺ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ጠቃሚ ይዘቶች በአንድ ላይ አካቶ ይዟል፦ ዘርፈ-ብዙ የኪታብ ደርሶች፦ የዐቂዳ፣ የመንሀጅ፣ የሲራ፣ የአደብ፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ፣ የነሕው እና የሶርፍ ትምህርቶች። እያንዳንዱ የድምፅ ቅጂ (ኦዲዮ) ከኪታቡ ሶፍት ኮፒ (PDF) ጋር አብሮ የተያያዘ ነው። አፑን ለአጠቃቀም ልዩ እና ምቹ የሚያደርጉት ባህሪያት፦   • ደርሶችን ከጀማሪ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ በቅደም-ተከተል የሚያስተምር።   • ትምህርቱን ሲጨርሱ ራሶን የሚፈሹበት ፈተናዎች ያሉት።   • በትምህርቱ መሃል አስፈላጊ ነጥቦችን በቀላሉ መፃፍ የሚያስችል ጥሩ ማስታወሻ መያዣ ያለው።   • የደርሶች ማውጫ በየዘርፉ በጥራት የተከፋፈለበት።   • የፈለጉትን ደርስ በቀላሉ መልሰው ለማግኘት ምልክት ማድረግ የሚያስችል።   • ከቅጅዎቹ መካከል የመረጡትን ለሌሎች ማጋራት (Share) የሚያስችል አማራጭ።   • አፑን ለአጠቃቀም አመቺ የሚያደርጉት ማስተካከያዎች ያሉት።   • ደርሱን አቋርጠው በሌላ ጊዜ ማዳመጥ ቢፈልጉ በትክክል ካቆሙበት ሰከንድ የሚጀምር። የአፕሊኬሽን አዘጋጅ፦ HUDASOFT https://t.me/hudasoft ይህ ስራችን የላቀው አላህን ፊት ብቻ ተፈልጎበት የተሰራ (የጠራ) ይሆን ዘንድ፤ በዚህ ስራ ላይ ለተባበሩትም ሆነ ይህንን ስራ ለሚያሰራጩት በሙሉ አላህ መልካም ስራችንን እንዲቀበለን እንማፀነዋለን። አፑን አሁኑኑ አውርደው ይጠቀሙበት፦ 🔗 የማውረጃ ሊንክ (Google Play Store)፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahlulaser.hs.app

  • Social Media አጠቃቀም https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

  • ዛሬ ሰኔ 21 የሺ ደበሌ ሁዘይፍ መሰጅድ የተደረገ ሙሀደራ ርዕስ:ሱናን አጥብቆ መከተል በተለይ በሰሞኑ ቁርአንዮች ነን እያሉ ነገር ግን ከቁርአን ጋ የተራራቁ ሰለመሆናቸው የተዳሰሰበት ወሳኝ ደዕዋ በኡስታዝ ኢብኑ ምነወር አላህ ይጠብቀው ።

  • قل لمن الأرض و من فيها إن كنتم تعلمون

  • የሙስሊሞች ቁጥር በጣም ጥቂት በሆኑበት አካባቢ የምትኖሩ ሙስሊሞች በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጥንቃቄ ካላደረጋችሁ በሌሎች ባህልና እምነት የመወዋጥ፣ ኢማንን የማጣት ከፍተኛ አደጋ አለ። ይሄ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። ከሚኖርበት አካባቢ ተፅእኖ ነፃ የመሆን እድሉ እጅግ የመነመነ ነው። የተፅእኖው መጠንና አይነት ከሰው ሰው ቢለያይም የራስን ማንነት ጥሎ በሚኖሩበት ማህበረሰብ ባህልና እምነት ውስጥ የመቅለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው። በዚህ የተነሳ በምዕራቡ ዓለም ከሚኖሩ ሙስሊሞች ውስጥ እምነታቸውን የሚያጡት ቀላል አይደሉም። አንዳንዱ ቀጥታ ራሱ፣ ሌላው በልጁ፣ በልጅ ልጁ ላይ ውጤቱ ይታያል። እምነቱ ብቻ ሳይሆን መጠሪያ ስሙ ሳይቀር ጉራማይሌ ይሆናል። ካርሎስ ዑመር፣ አይዛክ ሙሐመድ አይነት ስም የሚያጋጥመው የዚህ በሰፊው ማህበረሰብ የመውዋጥ ውጤት ነው። መፍትሄውስ? 1- ምዕራቡን ዓለም ቋሚ መኖሪያ አድርጎ መያዝ አይገባም። መቼም እንደ ሙስሊም ከኢስላም የበለጠ ውድ ሃብት እንደሌለን የሚዝዘነጋ አይደለም። ዱንያዊ ምቾትን ብቻ ማየት አይገባም። ኢማን ከሌለው ድሎት ኢማን ያለበት መከራ ይሻላል፣ በኣኺራ ለሚያምን ሰው። 2- በራስም ላይ በልጆችም ላይ አጥብቆ መስራት ያስፈልጋል። ማለትም ዲንን መማርም፣ ማስተማርም ከየትኛውም ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው። 3- ኢስላምን መተግበር ሌላኛው የኢማን ጋሻ ነው። ሶላትን ሳያዛንፉ መስገድ፣ ረመዷንን መፆም፣ ሐጅ ማድረግ፣ ዘካ መስጠት፣ ዘካተል ፊጥር፣ ኡዱሒያ፣ አለባበስን ማስተካከል፣ ሶደቃ መስጠት፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ቤተሰብን መዘየርና መደገፍ፣ ደዕዋ ማዳመጥ፣ ... እጅግ ወሳኝ ነገሮች ናቸው። ሰው ከኢስላም የሚወጣው ከመጨረሻው ቃል በፊት በሂደት ተሸራርፎ ነው። ኢስላምን በየዘርፉ የሚተገብር ሰው ድንገት ተነስቶ በአንድ ቅፅበት አይወጣም። ከመጨረሻው ዉሳኔ በፊት ተሸርፎ ተሸርፎ አልቋል። በዒባዳው ጣዕም አጥቶ ቀድሞ ርቋል። ስለዚህ እነዚህን የሸይ^ ጣን በሮች ለመዝጋት ቀድሞ ከአላህ ጋር ያለንን ትስስር ማጠናከርና መጠበቅ ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • ✍የዘንድሮ ዓሹራ ጾም የፊታችን ሀሙስ ሰኔ18 ነው የሚውለው። ቀኑን መፆም የ አንድ ዓመት ያለፈ ወንጀልን ያስምራል። ከፊት 9ነኛውን ቀንም መጾም ተወዳጅ ነው፤ ይህ ደግሞ ነገ ረቡዕ ሰኔ 17 ነው።

  • በዒልም ጎዳና ላይ ለሚሰንፉ ልቦች መርፌ የሆነው የሸይኽ ዐብዱልከሪም አል-ኹደይር ድንቅ ሙሓደራ! ደጋግሜ አዳምጠዋለሁ!! እናንተም አዳምጡት። t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

  • ወንድም አቡ ሱፍያ – በ አንድ ቀን ፆን የ 365 ቀን ወንጀል ይማራል..

  • ማስታዎሻ! ~ በአንድ ቀን ፆም ብቻ የ365 ቀናት ወንጀላችንን ማሳበስ! ➥ የዐሹራ ፆም መቼ ነው? ➥ እንዴትስ እንፁመው? ➥ በላጩ የአፃፃም መንገድ የቱ ነው? ➥ ለመሆኑ የመፆማችን ምክኒያት ምንድን ነው? 🖱ወንድም አቡ ሱፍያን t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

  • 📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ! ✅ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ጥሪውን ያቀርባል። 📚 የፕሮግራሙ ልዩ እንግዳ፦ ታላቁ የ-የመን ሙሓዲስ ፈደይለቱ ሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ (ሀፊዘሁላህ) —(በየመን የሚገኘውና በርካታ ተማሪዎችን ያፈራው የታዋቂው የመዕበር መርከዝ አስተማሪ) ◈እንድሁም ትልቁ አባታችን ፈደይለቱ ሸይኽ ሙሳ አል-ቀጧን (ሀፊዘሁላህ) ይገኛሉ። 🎙️ በፕሮግራሙ ላይ የሚታደሙ መሻይኾች እና ኡስታዞች፦ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን   ከደሴ ▪️ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ         ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ    ከደሴ ▪️ ሸይኽ ይማም ሰዒድ        ከደሴ ▪️ ሸይኽ አሕመድ አወቀ       ከደሴ ▪️ ሸይኽ በድሩ ዩሱፍ           ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን     ከቢስቲማ ▪️ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ        ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን       ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሐሰን አሊ ቃዲ          ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሁሰይን አቡ ሶላሑዲን ከደሴ ▪️ ሸይኽ አወል አሕመድ መነዮ  ከመረሳ ▪️ ሸይኽ አወል አህመድ          ከከሚሴ ▪️ሸይኽ ዒሳ አደም                 ከደሴ 🔸 ዶክተር /ኡ ሁሴን አሊ         ከከላላ 🔸 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር       ከአ.አበባ 🔸 ዶክተር/ኡ ሰዒድ ሙሳ         ከአ.አበባ 🔸 ኡስታዝ ኸድር አሕመድ     ከከሚሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሒዛም          ከአዳማ 🔸 ኡስታዝ  ዐብደሽኩር          ከአሶሳ 🔸ኡስታዝ ዐብዱሰላም ሐሰን   ከአዳማ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን   ከሀርቡ 🔸 ኡስታዝ አቡ አዩብ      ከኮቦልቻ 🔸 ኡስታዝ ሙርሰል        ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሻኪር      ከኮንቦልቻ 🔸 ኡስታዝ አቡ ረያን        ከመርሳ 🔸ኡስታዝ መሀመድ አያሌው ከወልዲያ 🔸ኡስታዝ አቡ ዓብዱ ረዛቅ ጅረሳ ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ    ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ ዐብዱልመሊክ ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሐሳን        ከኮቦልቻ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሃኒፋ         ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ መ/ሲራጁ       ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ ዐሊይ ሰይድ     ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አንሷር መሀመድ ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ         ከደሴ 🔸ኡስታዝ ጀውሀር  ክፍሌ    ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዐብዲረሕማን ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡል መዓሊ      ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሹራ            ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ማሂ            ከኮንቦልቻ 🔸 ወንድም አቡ ሂበቲላህ       ከደሴ 👥 የአንሷር መስጅድ ኢማምና ጀመዓዎቹ ባጠቃላይ... 👤እንዲሁም ሌሎች ከተለያየ ሀገር  በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው መሻይኾችና ኡስታዞችም በቦታው ይገኛሉ! 📆 የፕሮግራሙ ቀናት፦ የመጀመሪያ ቀን፦ ሰኔ 6/2018 (ከፊታችን ቅዳሜ ጧት 3:00) ጀምሮ ለ 4 ተከታታይ ቀናት ይቆያል። 🏘 ማሳሰቢያ፦ ለታዳሚዎች በቂ የምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል።—የሌሊት ብርድ ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ መልካም ነው።— 🤩በእነዚህ የቴሌ ግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ ይመዝገቡ፦ 📝ኡስታዝ አቡ ሻኪራ አህመድኑር @Abuhureirehonline    0923467646 📝 ኡስታዝ አቡ ዐዩብ   092 588 7118 @Attewhid11 📝 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን @Abu_Hibetillah_Al_aseriy 0942819970 💙የቦታው አቅጣጫ ካስቸገራችሁ በነዚህ የእንግዳ ተቀባይ ወንድሞች ስልክ ቁጥሮች ላይ ይደውሉ፡ 📞 ወንድም አንዋር 0916582567 📞 ወንድም አቡ አማር 0913803997 📞 ወንድም ሰኢድ 0935568513

  • ያ ጀማዓህ! ምርጫው እስከሚያልፍ ድረስ አላስፈላጊ ስብስብ ውስጥ አትገኙ፣ ማታ ማታም አታምሹ፣ ስትንቀሳቀሱ መታወቂያም ያዙ። ሰው በሞተበት ሁኔታ ነው የሚቀሰቀሰው። ሐጅ ላይ የሞተም ተልቢያ (ለበይከልሏሁምመ ለበይክ) እያለ ይቀሰቀሳል። ኳስ አፍቃሪው ወንድሜ ሆይ! ሞት አማክሮ አይመጣም። አስበኸዋል! የውመል ቂያማ ከDSTV ውስጥ ተቀስቅሰህ ወደ አላህ ስትሄድ? ኢሄንን ኳስ የሚባል ጣጙት እንራቅ አሏህ ይጠብቀን ኻቲማችን እንዳይበላሽ

  • አልሐምዱ ሊላህ! አዲስ ቀን፣ አዲስ ተስፋ ለሰጠን ጌታ ምስጋና ይግባው። የዛሬውን ቀናችንን ከስህተታቸው ታርመውና ተስተካክለው ሕይወታቸውን ከሚያድሱት መልካም ባሮቹ ያድርገን። ጌታዬ ሆይ! ለሌላ አዲስ ቀን ስላበቃኸኝ፣ ራሴን እንድፈትሽና እንድስተካከል ተጨማሪ ዕድል ስለሰጠኸኝ አልሐምዱ ሊላህ። ​ዛሬም ሙሉ እምነቴን በአንተ ላይ ጥዬ ተነሳሁ፤ አንተን የያዘ ምን ይጎድልበታል? ማረፊያዬም፣ ዋስትናዬም አንተ ብቻ ነህ። t.me/Sle_qelbachn1

  • خير كلمة يقولها المسلم يوم العيد تقبل الله منا ومنكم #عيد_الأضحى #عيد_الأضحى_المبارك

  • السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🎉🎊🎊عيد مبارك 🎊🎊🎉 كل عام و أنتم بخير تقبل الله منا و منكم صالح الأعمال አላህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን። እንኳን አደረሰን ።

  • 🔅 የተወሰኑ የኡድሑያ ሕግጋት ▪️ አስተራረድ ✔️ ቢላዋውን አንገቱ ላይ ከመጫኑ በፊት የግድ "ቢስሚላህ" ማለት አለበት። ሱናውን ሙሉ ለማድረግ ግን የሚከተለውን ይላል፡- "ቢስሚላሂ ወላሁ አክበር" (በአላህ ስም፣ አላህ ታላቅ ነው) "አላሁማ ሀዛ ሚንከ ወለከ"፣ (ትርጉም፦ አላህ ሆይ! ይህ ካንተ የተገኘ (ጸጋ) ነው፣ ላንተም የተደረገ ነው። ✔️በውክልና ከሆነ ደግሞ "ቢስሚላሂ ወላሁ አክበር" (በአላህ ስም፣ አላህ ታላቅ ነው) "አላሁማ ሀዛ ሚንከ ወለከ፣ አላሁማ ተቀበል ሚን [የወካይ ስም]" (ትርጉም፦ አላህ ሆይ! ይህ ካንተ የተገኘ (ጸጋ) ነው፣ ላንተም የተደረገ ነው፤ አላህ ሆይ! ከእገሌ [የወካይ ስም] ተቀበለው):: ▪️ የኡድሒያ ስጋ አከፋፈል ✔️ ኡድሒያ ካረዱ በኋላ ስጋውን ሙሉ በሙሉ መብላትም፣ ሁሉንም ሰደቃ ወይም ስጦታ መስጠትም ይቻላል። ነገር ግን ሶስት ቦታ አካፍሎ መብላት፣ ለአቅመ-ደካማ ሰደቃ መስጠትና ለወዳጅ ዘመድ ስጦታ ማበርከቱ ይወደዳል። ምንም እንኳ በቂና ግልጽ መረጃ ባይኖረውም በርካታ ሊቃውንት ትንሽም ቢሆን ለአቅመ ደካማ መስጠት ግዴታ ነው ስለሚሉ ሰደቃ መስጠቱ ባይቀር ይመረጣል። ✔️ በዛ ያለ ቤተሰብ ያለበትና ስጋ የሚያንሰው አባወራ ማካፈሉን ትቶ ሙሉውን ለቤተሰቡ ማድረጉ እንደሚሻል ኢብራሂም አል-ሐለቢይ የሚባሉት የፊቅህ ሊቅ ገልጸዋል። ▪️ የኡድሒያን ቆዳ መሸጥ ይቻላልን? ኡድሒያ የሚታረደው ወደ አላህ ለመቃረብ ነው! ስጋውን ለሶስት ከፍሎ፥ አንድ ሶስተኛውን ለቤት፣ አንድ ሶስተኛውን በስጦታ መልኩ ለዘመድ፣ ለጎረቤትና ለጓደኛ፤ አንድ ሶስተኛውን ሳይበስል ለአቅመ-ደካሞች መስጠቱ የጠበቀ ሱና ነው። ✔️ የኡድሒያውን ቆዳም ይሁን ሌላ ነገር ሽጦ ገንዘቡን መጠቀም ወይም በገንዘቡ ፋንታ ለሰራተኛ መስጠት አይቻልም! ቆዳውን ሳይሸጡ ለራስ መጠቀም ወይም ለአቅመ ደካማ በነጻ-ሰደቃ- መስጠት ግን ይቻላል። ዛዱል መዓድ https://telegram.me/ahmedadem

  • ንግዳቸው ትርፋማ የሆነላቸው አባት! ~ ~ ~ ሸይኽ ሙሀመድ ኢብን ሳዐድ አሽ'ወይዒር ይባላሉ!። በዘመናችን ፊቅህ ክንፏን ዝቅ ያደረገችለት እውቁ የመዲናው ፈቂህ "ሸይኽ ዐብድሰላም አሽ'ወይዒር" ወላጅ አባት ናቸው። እኚህ ወላጅ አባት ለታላቁ ኢማም ኢብን ባዝ ረሂመሁሏህ እጅግ የቅርብ አማካሪ ወዳጅና ፀሀፊ የነበሩ  ሰው ናቸው።  ሸይኽ ኢብን ባዝ (ረ.ሂ) ለ30 አመታት "ኑሩን ዓለ ደርብ" በተሰኘው በካሴት ይተላለፍ በነበረው የፈታዋ ፕሮግራም ላይ የተሰጡትን ከ11,300 በላይ የድምፅ ትምህርቶችና ፈታዋዎች ወደ ፅሁፍ በመቀየር (مجموع فتاوى ومقالات متنوعة) በሚል ርዕስ በ30 ሙጀለድ አዘጋጅተው በቀላሉ ለኡማው እንዲደርስ የአንበሳውን ድርሻ የተወጡ ጀግና ሰው ናቸው ከዛም በተጨማሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተበታተኑ የሸይኽ ኢብን ባዝን ጽሁፎችና መጣጥፎችን በማደራጀትና ለኪታቦቹም ማውጫና ርዕስ በማዘጋጀት በአጠቃላይ ከሰዎች እይታ በስተጀርባ ለሸይኽ ኢብን ባዝ ዳዕዋ ሰፊውን እጅ ወስደው የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ቁልፍ ሰው ነበሩ። አላህ ይዘንላቸውና ከዚህም ስራቸው ጎን ለጎን የአላህም ተውፊቅ ታክሎበት ለልጃቸው ሸይኽ ዐብድሰላም አሽ'ወይዒር እዚህ መድረስ ትልቁን የአባትነት ትግልና አስተዋፅኦ አበርክተዋል። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

👆🏻የዲኔ ጉዳይ ያገባኛል👆🏾 — tgindex