#የmom
Статистикаኑ እናንብብ #ተከታታይ ልቦለዶችን #ግጥም #አስተማሪ ፅሁፎችን #የህይወት እይታዎች #አሰገራሚ የመፅሃፍ ሀሳቦች ከእናንተው ወደ እናአንተው እናደርሳለን እንዲጨመር እንድናስተካክል ምትፈለገትን ሀሳቦች ፃፉልኝ ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት ይፃፍልን👇 @Yemom_bot @BM846 @yemomdan
- Последний пост
- 2 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 25
- 1/48двое суток
- 28
- 1/72трое суток
- 30
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኛ ሀገር ሴቶች እስኪ ደህና ነገርም ኮርጁ😎😎
ከአበቦች ጠረን ፥ ቀለም ቀማሚ ከገላሽ ምትሐት ፥ ውበት ለቃሚ እኔን የሚያስንቅ ፥ ምርጥ ገጣሚ ! ያገኘሽ እንደሁ ... ፀጉርሽን አይቶ ፥ ቅኔ ዘራፊ ሳቅሽ ሲነካው ፥ ውበት ለፋፊ እንደኔ ያለ ፥ ጎበዝ ጸሐፊ ! ያገኘሽ እንደሁ ... በድሮ አድናቆት ሳያሰለችሽ አዲስ ቃል ፈጥሮ የሚያቆነጅሽ ካለ ? ይመችሽ ! ወደ እሱ ብትሄጅ ፥ ወይ ብንለያይ ? በእርግጥ ያ አይደለም ፥ ትልቁ ጉዳይ ! ብቻ ልንገርሽ ! እሱም አይለካሽ ፥ እኔም አልሆንሽ ግጥም ብቻ ነው ፥ የሚመጥንሽ ። 📌 የሶሪያው ባለቅኔ ኒዛር ቃባኒን ግጥም ሀብታሙ እንደተረጎመው Habtamu Hadera
ወደ አዲስ አበባ ከመጣሁ ገና አንድ ሳምንቴ ነው። የጉዞ ድካሜን ለማራገፍና ራሴን ለማዝናናት የተሻለ ቦታ እየፈለግሁ ኢንተርኔት ላይ ማሰስ ጀመርኩ። ብዙ ሰዎች የፈለጉበትን ቦታ ስመለከት፣ “ሰሚት ፍየል ቤት” የሚል ቦታ አገኘሁ። ወዲያው ራይድ ጠራሁ። ከ20 ደቂቃ በኋላ ፍየል ቤት ደረስን። ለራይዱ 360 ብር፣ ከነቲፑ 400 ብር ከፍዬ ወረድኩ። እዚያው ሆኜ አሁንም ጎግል ማፕ ከፍቼ ፍለጋዬን ስቀጥል፣ ብዙ የማሳጅና የሞሮኮ ቤቶችን አሳየኝ። ከነሱ ውስጥ “ናኒ ሪላክስ ማሳጅ እና ሞሮኮ” የሚለውን መረጥኩና ማፑን ተከትዬ በሩ ላይ ደረስኩ። ወደ ውስጥ ስገባ… አንዲት ሴት ከካሸር ባንኮኒው ጋር ቆማለች፤ በቁጥር ብዙ የሆኑ ሴቶች ደግሞ ሶፋው ላይ ተደርድረዋል። ወዲያው አንዷ ቀረብ አለችና፣ “ምን ፓኬጅ ትፈልጋለህ?” አለችኝ። እኔም የብዙ ጊዜ ድካም ስለነበረብኝና ለሞሮኮ የሚሆን ጊዜ ስለሌለኝ፣ “አሪፍ ማሳጅ እፈልጋለሁ” አልኳት። ሌላ ሀገር እንደለመድኩት፣ እድሜዋ በ40ዎቹ የምትሆን ቆንጆ ሴት የማሳጅ ሜኑ ይዛ መጥታ፣ “Dear customer, do you need oil massage, Thai massage, or deep massage?” ብላ በጨዋነት እንድትጠይቀኝ ነበር የጠበቅኩት። የሆነው ግን ሌላ ነው! 😂 አንድ ሮዝ ቢኪኒና ጡት ማስያዣ ያደረገች፣ በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለች እንቦቃቅላ መጣች። ገና ምንም ሳትጠይቀኝ፣ “ልብስህን አውልቅ!” አለችኝ። አወለቅኩ። ቀጠል አድርጋ፣ “ፓንትህንም አውልቅ” ስትለኝ፣ “ኧረ እኔ አፍራለሁ!” አልኳት። እሷም፣ “ፎጣ አለ፣ አታስብ፤ አውልቅ” ብላ ፎጣ ሰጠችኝ። እኔም ማፈሬን ትቼ ወገቤን በፎጣ ጠቅልዬ አወለቅኩ። “እሺ፣ አሁን ምርጫዬን ትጠይቀኛለች” ብዬ ስጠብቅ፣ የወይራ ዘይት ጀርባዬ ላይ አፈሰሰችና ለ3 ደቂቃ ብቻ አሸችኝ። ከዚያም፣ “ኤክስትራ ትፈልጋለህ?” ስትለኝ፣ “ኤክስትራ ማስቲካ” መስሎኝ 50 ብር አውጥቼ ሰጠኋትና፣ “አዎ፣ ስጪኝ!” አልኳት። 😂 እሷም “ኤክስትራ” ማለት ሌላ ነገር እንደሆነ አስረዳችኝና… “አሁንስ ትፈልጋለህ?” እያለች ቢኪኒዋን አወለቀች። እኔም ባስረዳችበት መንገድ ተመስጬ፣ “ስንት ነው ይሄ ነገር?” አልኳት። እሷም፣ “ሁለት ሺህ (2,000) ብር” አለችኝ። እኔም፣ “እሺ፣ ይሁን” ብዬ ልሳሳት ስል… “ቸሬ! ተነስ… ተነስ!” የሚል ድምፅ ሰማሁ። ደንግጬ ብንን ብዬ ስነቃ… አቡሽ አጠገቤ ቆሞ፣ “ቁርስ ደርሷል፤ ወደ ሳሎን ና!” እያለኝ ነው። 😂😂 ለካ ይሄ ሁሉ ደስታ በህልሜ ነበር! ያሳዝናል! 🤣🤣🤣 ከጠጡ አይንዱ ከነዱ አይጠጡ ማለት እሄ አይደል
እያንዳንዱ የዝናብ ጠብታ መሬት ላይ ሲወድቅ፣ ያለፉ ዓመታት ድምፃቸውን ያሰሙኛል። የልጅነቴ ሩጫ፣ በዝናብ የተሞላ ሳቅ፣ የጭቃ ጨዋታዎች እና ያለ ምንም ጭንቀት የኖርኳቸው ቀኖች እንደገና በልቤ ይነሳሉ። ያኔ ክረምት ብርድ አልነበረም፤ ደስታ ነበር። ዝናብ ማለት ቤት ውስጥ መደበቅ ሳይሆን ከጓደኞቼ ጋር መሮጥ፣ መሳቅ እና አለምን በትንሽ ዓይኖቻችን እንደ ትልቅ ተአምር ማየት ነበር። ዛሬ ግን ክረምት ሲመጣ የምፈልገው የዝናብ ጃንጥላ አይደለም፤ የዚያን ጊዜ ንጹህ ልብ ነው። ያለ ፍርሃት የምትስቅ፣ ያለ ጭንቀት የምትጠብቅ፣ በትንሽ ነገሮች ታላቅ ደስታ የምታገኝ የልጅነቴን ልብ ናፍቃለሁ። አንዳንድ ዝናቦች መሬትን ብቻ አያርሱም... የተሸፈኑ ትዝታዎችንም ያበቅላሉ። እና አንዳንድ ጊዜ፣ ከመስኮት ውጭ የሚዘንበውን ዝናብ ስመለከት፣ የምሰማው የሰማዩን ማጉረምረም አይደለም...የልጅነቴ ሳቅ ነው። ©️ የሶሪት ማስታወሻ
(አስቴር አወቀ is weird) so my friend recommend me to listen አስቴር አወቀs #በደሳሳ_ጎጆ and he said በደንብ ስማት ሰማዋትም:- (በደሳሳ ጎጆ ሃረግ በወረሰው ይመጣል ቱባ ልጅ በቅባት የራሰው) ቱባ ምንድነው? ዝምብለህ imagine ደሳሳ ጎጆ and ሃረግ የወረሰው። በቅባት የራሰው?👀👀 (ጎፈሬው ከፊቱ ይላል ቀና ደፋ እንዳልተኛ አረገኝ እንዳላንቀላፋ) አሁንም ኢማጅን ደፋ ቀና የሚል ጎፈሬ ያውም እንዳትተኛ የሚያረግ😂😂 (አመለኛው ቤቴ ፍቅር ነው ማገሩ ሰተት ብለህ ግባ ይጨነቅ መንደሩ) This tells the whole story እኮ bro😂 ደሳሳ ጎጆ was her እሙሙ። ሃረግ ወርሶታል? (maybe ግጥሙን የፃፈው ሰው አልተላጨውም ኗራል🙌) ሲጀመር በቅባት የራሰው ልጅ ከፊቷ ደፋ ቀና እያለ እንቅልፍ ከየት ይመጣል? ከዚህ በላይ አላብራራም ልመሰጥበት🙌
ደወለች። አነሳሁት። አውቃታለሁ... ስልኳንም መዝግቤዋለሁ። ነገር ግን ትውውቃችን እምብዛም ነው። አስታውሳለሁ፤ ካሁን በፊት አንድ ጊዜ ደውላልኛለች። የሰው ስልክ ልትጠይቀኝ። ያኔ ነው ስልኳን ያወቅሁት። ለምን እንደሆነ አላውቅም መዘገብኩት። ከተደወለ ግን ወራት አልፎት ነበር። እና ... ዛሬም የደወለች በስራ ምክንያት ነው። ምሽት ሁለት ሰአት! በእርግጥ በዚ ሰአት መደወል አልነበረባትም። ማለቴ ሥራው ያን ያህል አጣዳፊ ስላልነበር ማደር ይችል ነበር። ግን ደወለች... አነሳሁት። የሥራ ወሬ ያወራን ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ነው። ሰላሳ ደቂቃ ሙሉ ወፍ ዘራሽ ወግ አውግተን ማለት ነው! ሰው ይህን ያህል ወገኛ ይሆናል? ይህስ የወግ ነበር... የሥራ ወጉን ለሁለት ደቂቃ ያህል አወጋንና... ሌላ ወግ ጀመርን። ለተከታታይ ሰዓታት አወራን። እኩል ሌሊት አልፎ ሰአቱ ሰባት ሰአት ሊደፍን ሲል ደከመን፤ ተኛን። እንደዚህ እያልኩ እያሰብኩ ተኛሁ... ደግማ ስትደውል ስንት ሰአት እናወራ ይሆን 🤔
የጠላነው ስሜት! እንደ ሄራክሉጦስ እሳቤ ሁሉም ነገር በእንቅስቃሴ ውስጥ ነው! የእርሱም ብቻ ሳይሆን Everything is in motion የሚለው ሀረግ አባባል ብቻ ሳይሆን «የህልውና መሰረት\foundation of physics» ነው። ድንጋዮች፣ ምድር ሰማይ ዛፎች ግዑዛን ሳይቀሩ ሁሉም የሁለንተና አካላት በእንቅስቃሴ ውስጥ ናቸው። ታድያ የሰው ልጅም ቢሆን እንደ ዝርያ በርካታ ያለፈባቸው phases አሉ። ትላንት አውሬ እና ታዳኞቻችንን ከማራሯጣችን አንስቶ ዛሬ ያለን የኑሮ ደረጃ እስክንደርስ ብዙ ያሳለፍናቸው መንገዶች እና ውጣ ውረዶች አሉን! እንደ ዝግመተ-ለውጥ ሳይንቲስቶች ከሆነ አሁን አሁን «ውጫዊ ጫና ስለቀነሰ አካላዊ ለውጣችን የበለጠ እያዘገመ» እንዲሄድ አድርጎታል። ነገር ግን አካላዊ ለውጣችን ቢዘግምም የኑረት ዘያችን ከምን ግዜውም በላይ በፍጥነት እየተቀየረ ነው። ቀን በቀን ታሪክ የሚመስሉ ነገሮች እንሰማለን። ዐስር ዓመታት እልፍ እስኪመስሉን ድረስ ኑረታችንን ቀይረውታል። ገና በሀያዎቹ መባቻ እድሜያችን ድሮ እኮ... በማለት እንድናወራ ተገደናል። አሁን ቴሌግራም 2008፣ ፌስቡክ 1996፣ ዩቲውብ ሚያዝያ 1997፣ ጉግል 1990፣ GPT 2015 ዓመት ላይ ነው የጀመሩት። በኢትዮጵያ ካላንደር ነው ያልኩት! የድሮውን ፌስቡክ እኮ.... ዩቲውብ እኮ...ጉግል እኮ... window explorer, firefox ምናምን በቅጡ ተደምመን ሳናጣጥማቸው ድሮ እኮ ለማለት በቅተናል። ገና ወጣቶች ሳለን ድሮ... ከማኅበራዊ ሚድያ በፊት እያልን እንደታሪክ እናወራዋለን። እነዚ የሚታዩን ለውጦች ሲሆኑ በዘመናት በሕቡዕ ቀስ በቀስ ድራሹ እየጠፋ ያለው አንዱ «ስሜትን የምንቀበልበት» መንገድ ነው። አብርኆት ገንፍሎ ሲነሳ አንዱ ጠላት ያደረገው ነገር ቢኖር «ስሜት» ነው። መንጋን በስሜት [ከተፈጥሮ ጋር ተናቦ] መምራት የለመደ ማኅበረሰብ ሀገርን «በስሜት ሳይሆን በስሌት» መምራት ጀምሯል። ከስሜት ተነቅለን ወጥተን ወደ ምክንያታዊ ጎዳና የመምራቱን ጉዞ ተያይዘነዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ በስሜት ተፈጥሯችንን ሆነን የኖርንባቸውን እነኚያን ዘመናት የጨለማ ዘመን፣ የድንጋይ ዘመን፣ የመዳብ ዘመን፣ የዋሻው ዘመን ምናምን ብለን ሰይመናቸዋል። የምንጠቀምባቸውን ዕቃዎች እያሰብን ማለት ነው! ይሄ አብርኆታዊ ሂደት ከስሜቶቻችን ሙሉ በሙሉ አስወጥቶን ወደ ማሽን ዘመንነት እየዶለን ይገኛል። we are on the process! የእናት የለጅ ፍቅር፣ የጓደኝነት መተሳሰቦች፣ የባልና የሚስት ፍቅር፣ ማኅበረሰባዊ ተግባቦት፣ አዘኔታዎች፣ ቀስ በቀስ ለመደብዘዝ እየታገሉ ያሉ ውጫዊ ጫና ክፉኛ እያረፈባቸው እና እየተፈተኑ ያሉ ነገሮች ናቸው። አንዲት ሰለጠነች ከምትባል ሀገር የመጣች ወዳጄ ስለዚሁ ጉዳይ ስናወራ እንዲህ አለችኝ:- « እዛ እኮ የሰዎች ፈገግታ፣ ትህትና፣ ንግግር fake ነው! በውስጥህ ታላቅ ሀዘን ኖሮብህ ከላይ ፈገግ ትልላታለህ ። ሲስተሙ ይሄንን ቅብ ማንነት እንድትላበስ ግድ ይልሀል፣ ደንበኞች ሲመጡ ፈገግ ማለት ግዴታህ ስለሆነ ቢከፋህም፣ ደስም ባይልህ ፈገግ ትላለህ፣ ተሸንፌያለሁ ስትል የሚቀበልህ ንቀት ስለሆነ በርህን ዘግተህ ታለቅሳለህ፣ ከውጪ ስደግሞ ድራማህን ትቀጥላለህ» ይህንን የምለው ስሜቶች አሁን ላይ ጠፍተዋል በሚል ስሜት ሳይሆን ስሜታችንን የምናስወጣበት መንገድ suppress እየተደረገ ነው እያልኩ ነው!በጎሳ በምንኖርበት ወቅት የአንዱ ስሜት ለአንዱ እንደ አንቴና እያገለገለ ከጥቃት፣ ከአውሬ ሲጠብቀን የነበረው የስሜት መናበባችን አሁን ላይ እምብዛም ነው። እንደሀገር :-ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ያደጉትን ልጆች ጨምሮ መንግስት ሳይቀር ለማኅበረሰቡ\ለሌላው ስሜት መጠንቀቅ ቅንጦት አድርገውታል። መንግስትም የማኅበረሰቡ ችግርን በማኅበራዊ ሳይንቲስቶች(sociologist) ከማስጠናትና መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ትኩረቱ fountain ላይ ነው። bcz የማህበረሰቡ ስሜት is not የዘመኑ priority! በብዙው ሀገር! ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ያደጉ ልጆች አዘኔታ ለሌላው ስሜት መጠንቀቃቸው ከሌሎቹ ትውልዶች አንጻር የወረደ ነው። ለሌላው ማሰብ(empathy) በሂደት የሚዳብር ተፈጥሮአዊ የጋራ ኑረት መሰረት ነው። ይሄ በአካላዊ ግንኙነት ውስጥ፣ ህመምን ከቦታው ሆኖ ማየት፣ የአይን ንክኪ፣ አስፍቶ ማሰብ የሚፈልግ ጥበብ ነው። ብዙ ሰዎች ይሄንን አልታደሉትም። ስሜቶች የኑረት ማገሮች ናቸው። ህይወት ያለው ሁሉ ስሜት አለው። አሁን ላይ ስሜቶቻችንን በጥበብ ማስወጣት\መግራት (emotional intelligence era) ላይ ነን። ስሜቶችን አለማውጣት ከባድ ቁስለትና የመኖርን ጣዕም የሚያዛባ እንቅፋት ነው። ሀዘንም፣ ደስታም እየኖርን እያለን መሆኑን የሚያሳዩን የተፈጥሮ ስጦታዎቻችን ናቸው። ዘመኑን ዋጁ እንዲል ቅዱስ ቃሉ ዘመኑን መስለን ስሜቶቻችንን ሳንጫን ስሜቶቻችንን እናጣጥማቸው። የጠላነው ስሜት ጠላታችን ሳይሆን የኑረታችን ማገር ነው።
ፈረስህን ወደ ውሃው ልትወስዳት ትችላለህ፤ ግን እንድትጠጣ ማድረግ አትችልም። ይህ ስለ ፈረስ ብቻ አይደለም፤ ስለ ሰው ልጅ ነው። ስለ ነፃ ምርጫ፣ ስለ ፈቃድ ነው። ሰዎችን መምከር እንችላለን። መንገድ ማሳየት እንችላለን። እውነትን ማስረዳትም እንችላለን። ነገር ግን እውነቱን እንዲቀበሉ ልናስገድዳቸው አንችልም። ለውጥ ከውጭ የሚገፋ ኃይል አይደለም፤ ከውስጥ የሚበቅል ፍላጎት ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎችን ለማዳን እንደክማለን። እጃችንን እንዘረጋለን፣ ቃላችንን እንሰጣለን፣ ጊዜያችንንም እንሠዋለን። ነገር ግን እጅን መያዝ የሚቻለው ሌላኛው እጁን ሲዘረጋ ብቻ ነው። የተዘጋ ልብ በግድ አይከፈትም። የሁሉም ሰው ኃላፊነት እኛ ላይ አይደለም። መንገድን ማሳየት የእኛ ድርሻ ነው፤ መራመድ ግን የእነርሱ ውሳኔ ነው። ብርሃንን ማብራት እንችላለን፤ ዓይናቸውን እንዲከፍቱ ግን ልናስገድዳቸው አንችልም። ሁሉንም ሰው መቀየር የሚቻል አይደለም። ሁሉንም ሰው ማሳመንም አይቻልም። የሰው ልብ የሚለወጠው ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው። ምናልባት የሕይወት ትልቁ ጥበብ ሰዎችን በኃይል መቀየር ሳይሆን፣ ለመለወጥ ሲወስኑ ከጎናቸው መቆም ነው። ምክንያቱም ውሃው ሁሌም እዚያው አለ፤ መጠጣት ግን የጠማው ሰው ውሳኔ ነው። ©️የሶሪት ማስታወሻ
"ካብ ለካብ" ++++++ (በአንድ የፈረንጅ ቲክቶክ ቪዲዮ መነሻነት የተጻፈ ቀላል ታሪክ) ------------ አልጋው ላይ ተኝቶ አጫጭር ቪዲዮዎችን እያፈራረቀ ሲመለከት ስልኩ ጠራ። የደዋይዋን ስም ሲያይ ፈገግ አለና በሁለተኛው ጥሪ አነሳው። «ሄይ የኔ ፍቅር። እንዴት ዋልክልኝ? የት ነህ?» አለችው። «ሄይ ማሬ... ቤቴ ነኝ» ብሎ መለሰላት። «ቤትህ ምን እያደረግክ?» «ምን አደርጋለሁ?…ዝም ብዬ ስልኬ ላይ ያው በቲክቶክ እየዛግኩ» «ውይ…ደብሮሃል እንዴ የእኔ ፍቅር?» «አይ ብዙ አልደበረኝም…» «ኦኬ…እኔማ የደወልኩልህ ዓለም ሲኒማ ቴአትር ልንገባ እንደሆነ ልነግርህ ነው.. ከዛ በኋላ ደሞ እራት እንበላለን ብለናል፣ ስለዚህ ዛሬ አልመጣም። አርብ ስለሆነ ፈታ ልበል ብዬ እኮ ነው» «ኦ... እሺ። ኢንጆይልኝ» ‹‹ኢንጆይልኝ ስትለኝ እንዴት ደስ እንደሚለኝ ታውቃለህ አይደል?›› ‹‹ለዛ እኮ ነው ሁሌ የምልሽ›› ‹‹ሃሃ…የራስህ ብራንድ እኮ ናት…አማእንግሊዝኛ…የእኔ ፍቅር›› ‹‹እንዲህ ካበረታታሽኝማ ሳልሰረቅ የአይምሮ ምናምን ሄጄ አስመዘግባታለሁ በቃ…›› «አይ አንተ…! ኤኒዌይ ከእራት በኋላ ደግሞ የሆነ ላውንጅ እንሂድ ማለታቸው የማይቀር ነው… ስለዚህ ስልክ ባላነሳ እንዳታስብ..ጫጫታው አያሰማም›› ‹‹አላስብም›› ‹‹ደሞ ቤቴ ድረስ የሚያደርሰኝ ሰው ስላለ ምንም ብለህ እንዳትጨነቅ » «ኦኬ ጉድ… ግን ማን ነው እቤት የሚያደርስሽ?» «ቤቲ» «ቤቲ... ?የቷ ቤቲ?» «ቤቲ ናታ! ቤስት ፍሬንዴ?» «ማ…?›› ‹‹ምን ሆነሃል? ቤቲ ጠፍታህ ነው›› ‹‹ አይ…... እ…ኖ…አልጠፋችኝም…ሶ …ቤቲ ታደርስሻለች…አ?» «አር ዩ ኦኬ የእኔ ፍቅር?›› «አይ አም ፋይን…ያልጠበቅኩት…እሷ…ማለቴ እሷስ አብራችሁ አታመሽም ወይስ...?» «ታመሻለች ግን እሷ መጠጥ አትጠጣም ስለዚህ ችግር የለውም። አትጨነቅ አልኩህ እኮ» «እ..አይ… አልተጨነቅኩም... እና አሁን ከ..ከቤ …ከቤቲ ጋር አብራችሁ ናችሁ?» «አዎ…ተገናኝተናል የሆነ ነገር ልግዛ ብላ ሱቅ ገብታ ነው። አሁን እራሱ መኪናዋ ውስጥ ሆኜ ነው የማወራህ» «ተይ እንጂ?» «አዎ…ምነው የገረመህ መሰልክ?» «አይ ምን ይገርመኛል…? ምንም አልገረመኝም አረ» «ሃሳብህ የተሰረቀ ይመስላል። ዩ አር ኦኬ አይደል?» «ኖ ኖ... ደህና ነኝ።» ለአፍታ ጸጥታ ሰፈነ። «ኦኬ ስለዚህ በቃ ፈታ ብዬ አመሻለሁ…ነገ ጠዋት ስበር ወዳንተ እመጣለሁ… ስራ አጎሳቆለኝ እኮ ሰሞኑን… እስቲ ዛሬ ይለፍልኝ።» «ተፍታቺ የእኔ ቆንጆ... ኢንጆይልኝ» «ታንኪው ናሆምዬ። እወድሃለሁ።» «እኔም እወድሻለሁ።» ናሆም ስልኩን ዘግቶ ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠና አጠገቡ ወደተኛችው ሴት ዞረ። ሁለት ትራሶች አነባብራ ቀና ብላ ታየዋለች። «..ሰላም ናት…ካንቺ ጋር ነኝ ነው የምትለኝ » አላት ፊቱን ቋጥሮ። ሴቲቱ በሳቅ ፈነዳችና፣ «ሃሃሃ... አለ መኮንን» አለች፡፡ «ምን ያስቅሻል?» ቆጣ ብሎ ጠየቃት፡፡ «ምንም።» «ሲሪየስሊ ዋት ኢዝ ሶ ፈኒ?» ሳቋን በእጇ አግታ ታስቀር ይመስል አፏ ላይ አድርጋ፣ «አይ…እንደው ዋሸሽኝ ብለህ እንኳን ልትናገራት እንደማትችል ሳስብ ነገሩ አስቆኝ ነው…›› አለችው ከሳቋ እየታገለች፡፡ ‹‹እና ታዲያ እሱ ምኑ ነው የሚያስቀው?›› አላት አሁንም እንደተኮሳተረ፡፡ «...የሚያስቀውማ አንተም እየዋሸሃት መሆኑ ነዋ…እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ አለች አያቴ » ‹‹ኤጭ…እባብ ካብ ምናምን.. እስቲ ዛሬ እንኳን ይሄን ያሮጊት ተረትሽን ተወት አድርጊ…›› ብሎ በብስጭት ተስፈንጥሮ ካልጋው ተነሳ፡፡ ---- በዚህችው ቅጽበት በሌላኛው የከተማው ጫፍ ደግሞ እንዲህ ሆነ፡፡ ሰላም ስትነጋገርበት የቆየች ስልኳን ስልቻ የሚያህል ቦርሳዋ ውስጥ ጨመረችና የመኪናውን መሪ በጣቶቹ ወደ ሚቆረቁረው ወንድ ዞረች። «ጉድ ኒውስ ሃንድሰም» አለችውና ወደኋላ ደገፍ ብላ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ተሳካልሽ አይደል?›› አላት ሳቅ ብሎ እያያት፡፡ «ድሮስ ! ዛሬ የፈለግንበት ቦታ የፈለግነውን ያህል ማምሸት ከፈለግንም ማደር እንችላለን።» ሳቁ ደመቀ። ሰከንዶች እንዳለፉ ፊቷን ጨፍገግ አድርጋ፣ «ግን ቤቲስ?» ስትል ጠየቀችው። «ስለእሷ አታስቢ…ትንሽ ቆይቼ እደውልላታለሁ፣» አላት ዘና ብሎ፡፡ ግን አሁንም ፊቷ አለመፈታቱን ሲያይ ቁኝ እጁን ወደተጋለጡ ጭኖችዋ ሰደደና፣ «አታስቢ አልኩሽ እኮ…ዋናው ያንቺ ነበር..እኔማ ከናሆም ጋር አመሻለሁ እላታለሁ አለቀ!›› ብሎ ጨመረ፡፡ ህይወት እምሻው
መንገድ ላይ የጀበና ቡና የምትሸጥ ሴት ማፍቀርኮ ችግር የለውም። ችግሩ ፉክክርህ ከግንበኛ፣ ከተራ አስከባሪ፣ ከአናፂ ምናምን ጋር ነው። የማስተርስ ዲግሪ ሰርቼ...ስምንት አመት ሙሉ የባንክ ስራን ቀጥቅጨ...ያሰብኩትን ሁሉ ጨብጬ...የአልማዝ ልብ ግን ከመንገድ ወያላዎች ለይቶ አያዬኝም። «የሴት ልጅን ልብ የሚያሸንፈው ያልተጫወተ ነው» የሚለው የእማዬ ምክር እዚህ ላይ አይሰራም። በኑሮ ሰባት እጥፍ የምበልጣቸውን ሰዎች በምላስም በልጨ መገኘት አለብኝ። ችግሩ መሰሎቼ ስላልሆኑ ያ ባለጌ ሽመልስ እንደ ኮሜዲያን የሚታይበት ዳስ ውስጥ የኔ ቀልድ እጅ እጅ ይላቸዋል። አንዳንዶቹማ እያወራሁ በፈጠጣው አቋርጠውኝ ሁላ ሌላ ወሬ ይጀምራሉ። ሽመልስ ማውራት ሲጀምር ግን አልሚ ራሱ ቡና መቅዳቷን ቆም ታደርጋለች (ስትስቅ እንዳያስደፋት መሆኑ ነው። ገና ሲጀምር እንደሚያስቃት እርግጠኛ ነች።) እኔ በበኩሌ ከሚያሰቀው ነገሩ ብልግናው ስለሚበዛብኝ ሁሌ እንደተሸማቀኩ ነው። «አባቴ 'ሽመልስ' ያለኝ ከበቶቼን የሚጠብቅ እረኛ ተወለደልኝ ብሎ ነው። እኔ ደግሞ የህይወቴ ጥሪ ከዚህም በላይ ነው ብዬ ጠፍቼ መጣሁ። እረኝነት እጣፈንታዬ እንደሆነ የገባኝ ግን እዚህም መጥቼ መኪና ሳግድ ነው!» «ታዲያ የትኛው ተሻለህ...የከተማው ወይስ የገጠሩ እረኝነት?» ይለዋል አንዱ ሰው መስሎት። «ተመልሼ መግቢያ የለኝም እንጂ የገጠሩ ይሻለኝ ነበር። እዛኮ ቢያንስ ሲደብረኝ አህያ እበ*ለሁ!» ብሎ በሰላሳ አመት የሰበሰብነውን ቀልብ ይገፈዋል። የፈለገው እንስሳ ጋር ሴክስ ማድረግ ይችላል...እሱ የኔ ጉዳይ አይደለም። ችግሩ ምንም የመጀናጀኛ አየር እየሰጠኝ አይደለም። እሱ ባለበት አይደለም መጀንጀን ወሬ መጨረስ ራሱ አልቻልኩም። «ባለፈው መኪናዬ ስታክ አድርጋብኝ...» ብዬ ስጀምር «አይይ!... አሁን እዚህ ማን ስለመኪና ያውቃል ብለህ ነው?» ብሎ ያናጥበኛል። «የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ።» ብዬ ረጅም ሳክስ ስጀምር «ቡና በስኳር እየጠጣህ የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ ብትለኝ አላምንህም» ብሎ ባጭሩ ይቀጨኛል። አሁን አሁን ገና ከሩቅ ሳዬው እንደ ስፔን ኮርማ ተንደርድሬ ልወጋው ሁሉ ያምረኛል። ወዲያው ከሀሳቤ ብንን ስል ፍቅር የት ድረስ እንዳወረደኝ አስብና እገረማለሁ። እንዲህ አብሮ መዋል ሳያናንቀን በፊት በፊት ሽመልስ ይመቸኝ ነበር። መኪናዬን ይዤ ስመጣ ቆንጆ የፓርኪንግ ስፓት እንዳገኝ ይረዳኛል። የሆነ ቀን ከመኪናዬ ሳልወርድ «እስኪ ቡና እዘዝልኝ» አልኩት። አንዲት ቀይ ልጅ የጀበና ቡና ይዛ መጣች። ከቡናዋ ጋር ምን እንዳቀመሰችኝ አላውቅም ከዛ ቡኃላ ልክ አይደለሁም። ፈገግ ስትል ብቅ የሚለው የተነቀሰ ድዷ አብስትራክት ስዕል ይመስል በየ ደቂቃው የአንገቴን አቅጣጫ እየቀየርኩ አየዋለሁ። ፓንቷ ውስጥ ሻጥ አድርጋው የምትሔደው ሺቲ በተንቀሳቀሰች ቁጥር በዳሌዋ ሲያስገለምጠን ይውላል። ስትስቅ ድዷ...ስትራመድ ዳሌዋ! እህህ ሁኗል የኔ ኑሮ! ታዲያ እኔ እሷን...እሷ ደግሞ ሽመልስን እንደምትወድ ለመረዳት ብዙ አልፈጀብኝም። በብልግና ቀልዱ መሳቅ ብቻ አይደለም...ጭራሽ «ብልግናቸውን የማይደብቁ ሰዎች ጨዋ ነው የሚመስሉኝ» ብላ ልትደግፈው ትሞክራለች። ፍቅር የሚባለው የበሽታ አይነት ሲይዝ መጀመሪያ የሚያጠቃው መለኪያ ሚዛንህን ሳይሆን አይቀርም። ለኔ አልማዝን አለም ላይ የትም መገኘት የማትችል እንቁ አድርጎ ያሳዬኛል። ለሷ ደግሞ ሽመልስን አርብ ሮብ የሚፆም ጨዋ አድርጎ ያሳያታል። ቢሆንም...ቢሆንም! እሷን የመጥበስ እድሌ ተንጠፍጥፎ እንዳላለቀ ይሰማኛል። አንድ ጧት እንደመጣሁ አምስት መቶ ብር የሻይ ሰጠሁትና ራቅ ወዳለ ሰፈር ላኩት። አልሚን ብቻዋን አገኘኋት። «የሆነ ቆንጆ ሬስቶራንት አለ። ዛሬ የሚመችሽ ከሆነ ራት ልጋብዝሽ!» አልኳት...ስለማመድ የዋልኩት ይሔ መሆኑን ለራሴም ማመን እያቃተኝ። «ውይ ደስ ይለኝ ነበር። ግን ዛሬ አክሴቴ ከገጠር ትመጣብኛለች። ወይ ሌላ ቀን እናድርገው?» «ኧረ ችግር የለውም። ያን ያህል አንገብጋቢ ነገር አስመሰልሺውኮ!» ከረባቴን አላላሁትና መልሼ አጠበኩት። ተነስቼ ወጣሁ። ደሜ ፈልቷል። ውስጤ አላመናትም። ሽመልስ እንደመጣ «ዛሬ የት ነህ? ከስራ ስወጣ ለምን አንድ ሁለት እንልም?» አልኩት። «ውይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ግን ዝናቡን እንደምመጣ ቃል ገብቼለታለሁ!» አለ የሰጠሁትን ብር አገላብጦ እያዬ! አያውቅም ብሎ ስም እየፈጠረ እንደሆነ ገብቶኛል። «ዝናቡ ዝናቡ?» «ዝናቡ ይሔ ባለፈው 'ቶሎ ባይነሳ አፉ ላይ ያለው የጠጅ ሽታ ሊያሰክረኝ ነበር' ብለህ የቀለድክበት» እውነት ለመናገር ሊያስመልሰኝ ነው የነበረው። «አስታወስኩት! ታዲያ ለምን እኔ እናንተ ጋር አልመጣም?» «ኧረ አይሆንህም!» «ግዴለም! ይልቅ ቆንጆ ጠጅ ቤት ውሰዱኝ!» ሳይመልስልኝ ጥዬው ገባሁ። ከስራ እንደወጣሁ ባኮረፈ ፊት ይዞኝ መሔድ ጀመረ። ጠጅ ቤት ከገባን ቡኃላ ከሁሉም ተነጥለን የራሳችንን ወሬ ለመጀመር ሁለት ብርሌ ነው የፈጀብን። ያለ ሰበብ እንዳልመጣሁ ገብቶታል። «አልሚን ትወዳታለሀ?» አለኝ ሌሎች እንዳይሰሙን እየተጠነቀቀ! በጥያቄው አልተገረምኩም። «ፍቅር የሰው ልክ አያውቅም ወዳጄ። ያንንም ያንንም ሲጨብጥበት በቆየበት እጁ ነው የሚጨብጥህ! መጨበጡን እንጂ ማንን እንደጨበጠ አያውቅም። እውር ነው። የሚመመራን ግን እሱ ነው። የምለው ገብቶሀላ?» «ይሔ ቢገባኝ የመኪና እረኛ ሁኜ እቀር ነበር ብለህ ነው?» «ልልህ የፈለኩት ፍቅር ደረጃ የማይለያይ ደጋሽ ነው። የመኪናውን ባለቤት ከመኪናው እረኛ ጋር ጠጅ ያስጠጣል!» ፈገግ አለ። «ተውልኝ ልትለኝ እንደመጣህ ገብቶኛል። እኔም ልልህ ነበር።» «እና ለምን አላልከኝም?» «ትርፉ ድካም ነው። እሷ የምትወደው አንተን!...ለምን ጊዜዬን አባክናለሁ?!» ከስካሬ ነቃ አልኩ። «እኔን እንዳጫዋች ነው የምታዬኝ። አንተ ስትመጣ ግን ያለባህሪዋ ቆጠብ ትላለች። እንድትወዳት ለማድረግ ትጥራለች። እኔ ምንም አይነት ሰው ብሆን ለሷ አይን አልሞላም።» እንባ አቀረረ። ይሔን ንግግር እኔ ቀድሜው ባለማለቴ ደስ አለኝ። «ይገባኛል ስሜትህ» አልኩት ውስጤ እየተፍነከነከ። ፊቴን ያዘንኩ ላስመስል ሞከርኩ ግን አልቻልኩም። የሚታየኝ የአልሚ ቀሚስ ውስጥ ገብቼ አሸሸ ገዳሜ ስል ነው። ወዲያው ጥግ ላይ የነበረው ዝናቡ እየተንገዳገደ ተነስቶ ወደኛ መጣ። «አንድ ሁለት መቶ ብር አላችሁ አንዴ?» አለን «ለምንህ?» «አሁን አይደል እንዴ ትዝ የሚለኝ? ለካስ ያቺን ቅንዝራም አልማዝን ቀጥሬያታለሁ! ህእ!» ሁለታችንም ደንዝዘን ቀረን። ደመናውን ሳናዬው ዝናቡ ከዬት መጣ? ሰማይ ሳያስገመግም መብረቁ እንዴት መታን? ብሩን ተቀብሎን ሲወጣ ባለማመን እናየዋለን። በሩ ላይ ሲደርስ ዞር ብሎ «ጠጅ እስቀምጡልኝ! ጠቅ ጠቅ አድርጊያት እመለሳለሁ» አለንና በሁለቱም አይኑ ጠቀሰን። በህመም ስሜት አይናችንን ጨፈንን። "የሴት ልጅን ልብ የሚያሸንፈው ያልተጫወተ ነው!" ፨፨፨ ሚካኤል አዝመራው
#የmom pinned «እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ እንዴት ከባድ ጊዚአችሁ አለፈ ? እንዴት የተሰበረ ልባችሁን ጠገናችሁ? የአፈሰ እጃችሁ ባዶ ሆኖ ስታገኙት ..... ድንጋጤ እንዴት አደረጋችሁ ? . . እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ ስትታመሙ ስታጡ ቤት ስትውሉ መረሳት እንዴት ሳይሰብራችሁ ቀረ ? .... ያልፍልኛል ብላችሁ የሄዳችሁበት…»
የማትገመቱ ሁኑ 🤪 የሳመኝን ሰው እንኳን ስሙን መልኩ እንኳን የሚታወሰኝ ከናይት ክለቡ እልፍ የሚሽከረከር መብራት ቀለማት ጋር ተበውዞ ነው።…… የዘጠኝ ዓመት ፍቅረኛዬን ከንፈር ያስከዳኝን አሳሳሙን ግን…… ፍቅረኛዬን አልኩ እንዴ? ኸረ ከሁለት ሳምንት በኋላ የማገባው እጮኛዬ ነው። ማለቴ ነበር ማታ ያ ከይሲ እስከሳመኝ ደቂቃ ድረስ…… በቃ ተበላሁ።…… እጮኛዬን እፈልግሃለሁ ብዬ ቀጠርኩት።…… ፍትልክ ብሎ ከእጅ እንደወደቀ እቃ ያመለጠኝ "አላገባህም! " የሚለው ቃል ነው። በቃ ዱብ ነው ነው ከአፌ የወደቀው…… ዝም አለ። አፉ ብቻ አይደለም ገፁም ዝም አለ። ተናደደ? ጠላኝ? ክፋቴ ከቃል በላይ ሆኖበት ነው? በቃ ዝም አለ…… ቀበጣጠርኩ "ማለቴ መጋባት ያለብን አይመስለኝም።… በአንተ ምክንያትኮ አይደለም…… አንተማ ዕንቁ ነህኮ…… እኔጋ ነው ችግሩ…… " ከኑሮ ከከበደ ዝምታ በኋላ "ምክንያትሽን ማወቅ እፈልጋለሁ! " ብሎ የዝምታውን ጭነት ለእኔው አቀበለኝ። ጭጭ…… ፀጥ…… ልጉም…… ዲዳ ምንድነው የምለው? አንተ ስመኸኝ እንደማታውቀው የሆነ የማላውቀው ሳስበው ሸበላ የሚሆን ሰው ሲስመኝ እኔና አንተ መጋባት እንደሌለብን እንደመገለጥ ፈነጠቀልኝ ነው የምለው? እጮኛዬ እጮኛዬ ከመሆኑ በፊት የረዥም ዓመት ቦይፍሬንዴ ነበረ።… ቦይፍሬንዴ ከመሆኑ በፊት የሰፈር ጓደኛዬ ነበር። ጓደኛዬ ከመሆኑ በፊት እቃእቃ በተጫወትን ቁጥር በፀብ የምንጨርስ የእቃቃ ባሌ ነበር።…… ቤተሰብ… ጓደኞቻችን… የሚያውቀን ሁሉ ፍፁም የሆንን ጥንዶች መሆናችንን ነው የሚነግረን።…… እውነት ነው። አንዲት ሴት ባል ይሁነኝ ብላ ልታልም የምትችለው መስፈርት ሁሉ አለው።…… ማታ እንደሳመኝ ልጅ የቆምኩበትን የሚያስረሳ መሳም ብቻ የለውም። የሳመኝ ሰው ከአሜሪካ ከመጣች ጓደኛዬጋ ክለብ ሄደን ነው። ሞቅ ባለኝ አሳቻ ሰዓት እንጨፍር አለኝ። እየጨፈርን ነበር…… የሆነ እንደመለስለስም እንደመጠንከርም…… እንደማቀፍም እንደመሳብም… እንደፍቅርም እንደጥላቻም… እንደብዙ ነገር የሆነ አያያዝ ወገቤን ይዞ ሳበኝ…… ሳመኝ ልበለው…… አይደለም…… በከንፈሩ የሆነ ዓለም ፈጠረ… ኖሬበት የማላውቅ ዓለም…… በቃ ይኸው ነው።…… ወደ ናይት ክለቡ ዓለም ስመለስ ተቆናጠርኩ። ተሳደብኩ።…… ተመነጫጭሬ ጥዬው ወደቦታዬ ተመለስኩ…… ወደ ራሴ ሳልመለስ ቀረሁ እንጂ…… "ካንቺ ስለመጣ ደስ ብሎኛል። ለሰርጉ ጓግተሽ ስለነበር ልብሽን እንዳልሰብረው ብዬ እንጂ። እኔና አንቺ ጓደኝነት እንጂ የፍቅር አይነት ቅመም በመሃከላችን እንደሌለ ካወቅኩ ቆይቻለሁ።" አላለም። አምልጦት ከአፉ ወድቆ ነው የሚሆነው ብዬ አሰብኩ። ይሄ ሁሉ ቃልማ አይወድቅበትም። ማለት? ማንን ስመህ ነው? " እየቀናሁ ባልሆነ…… ✍️(ሜሪ ፈለቀ)
እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ እንዴት ከባድ ጊዚአችሁ አለፈ ? እንዴት የተሰበረ ልባችሁን ጠገናችሁ? የአፈሰ እጃችሁ ባዶ ሆኖ ስታገኙት ..... ድንጋጤ እንዴት አደረጋችሁ ? . . እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ ስትታመሙ ስታጡ ቤት ስትውሉ መረሳት እንዴት ሳይሰብራችሁ ቀረ ? .... ያልፍልኛል ብላችሁ የሄዳችሁበት መንገድ አባጣው ጎርባጣው አተርፍ ባይ አጉዳይ ሲደርጋችሁ ምን አላችሁ?? . . እናንተ የበረታችሁ ድንገተኛ ሃዘን ጎጃቹ ሲገባ፣ ያተርፋል ያላችሁት ሲያከስር ፣ መከዳት ልባችሁን ሲያርደው ......እንዴት ጨለማው ነጋላችሁ? ተስፋችሁ የተሟጠጠ ማድጋችሁ የጎደለ ኪሳቹ የተራቆተ እለት ........ ጭንቀት እንዴት ድል ሆነላችሁ . . እናንተ የበረታቹችሁ ሆይ መውለድ እምቢ ሲላችሁ ፣ ልጃችሁ ሲታመም፣ ጤናችሁ ሲጓደል .....ተስፋ የለም ስትባሉ ልባቹ እንዴት ተስፋ አየ ??? . . መፅሃፍ ቅዱስ የበረቱ ሰዎችን የአንበሳን አፍ ከዘጉ ፣ከሰይፍ ስለት ካመለጡ፣ የእሳትን ሃይል ካጠፉ፣ የባእድ ጭፍሮችን ካባረሩ ፣በጦርነት ሃይለኛ ከሆኑ ሰዎች እኩል ከድካማቸው የበረቱትን ያወሳል ከድካም መበርታት ቀላል አይደለም ! ቅዱስ ዳዊት ልጁ አቤሰሎም ሲያሳድደው የሚያስጨንቁኝ እንዴት በዙ! ብዙዎች በእኔ ላይ ተነሡ። ብሏል ትግስተኛው እዮብ መከራ ሲሸከም ድካሙ ሲበረታበት ስለ ምን ከማህፀን አልሞትሁም ብሏል . . የሰው ልጅ ሃያል ነው ከድካሙ ይበረታል አይነጋም ያለው ይነጋል . . እናንተ የበረታችሁ ሆይ እናንተ ግን እንዴት እንዴት በረታቹ ??? © Adhanom Mitiku
የውስጥ ቁስልን በዲጂታል ሜካፕ ለመሸፈን መሞከር የቱሪዝም ስኬት ሳይሆን የታማኝነት ክስረት ነው:: ኢትዮጵያ ዛሬ የሚያስፈልጋት ለዓለም 'ውብ መታየት' ሳይሆን ለዜጎቿ የሚጠግቡባትና የሚረጋጉባት 'ውብ ሀገር' መሆን ነው። ልጆችህ ተርበው ኑ ቤቴ ሙሉ ነው ጎብኙ እደሩ አይባልም:: የራበው እንግዳህንም ገንጥሎ ከመብላት አይመለስማ! እሱ ደግሞ የቤትህን ክብር ያወርደዋል በግብዣህ ልክ ዮአኪን በቀለ ❤️🤝✍
61 ገደማ የሚሆኑ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ የተባሉ ግለሰቦችን ሃገራችን ኢትዮጵያ ሆዬ አዱኛ ጥላ ለድግስ ጠርታቸዋለች ከተለያዩ አፍሪካ ሃገራት:: ድግሱ ስሙ Africa Social Media Influencers Summit ይባላል:: እዚህ ድግስ ላይ የተጠሩ የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች በአጠቃላይ 321 ሚሊዮን ተከታዮች አሏቸው:: ይህ 321 ሚሊዮን የተባለው ቁጥር በዲጂታል ዓለም ያለውን ግዙፍ የሰው ኃይልና የተጽዕኖ አቅም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይህንን ቁጥር በሥነ-ሕዝብ እና በዓለም አቀፍ ስታቲስቲክስ ሚዛን አስልተን ስናስቀምጠው የሚከተለውን አስገራሚ እውነታ እናገኛለን:: ከሀገራት የሕዝብ ብዛት አንጻር 321 ሚሊዮን ሕዝብ ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ከምትገኘው ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ (USA) የሕዝብ ብዛት ጋር ተቀራራቢ ነው (የአሜሪካ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ወደ 340 ሚሊዮን ገደማ ነው)። ይህ ማለት እነዚህ ኢንፍሉዌንሰሮች በአንድ ላይ የሚደርሱበት የሰው ቁጥር ከአፍሪካ ግዙፍ ሀገራት የሆኑትን የናይጄሪያን እና የኢትዮጵያን የሕዝብ ብዛት በአንድ ላይ ቢደመሩ እንኳን ይበልጣል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራትን የሕዝብ ብዛት በሦስት እጥፍ ገደማ (2.6 እጥፍ) ይበልጣል ማለት ነው:: በአጭሩ ባሻዬ እነዚህ ተከታዮች በአንድ ክልል ቢሰበሰቡ ኖሮ ከቻይና እና ከሕንድ በመቀጠል በዓለም ላይ 3ኛው ግዙፍ ሀገር መሆን የሚችል Digital Nation ይፈጥሩ ነበር። ዝማዴ እስካሁን ያወራነው ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉ 30 የሚሆኑ አፍሪካ ሃገራት ስለተወጣጡ ማህበሳዊ ሚዲያ እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ነው:: ከእነዚህ ባሻገር ከእኛም ወገን 150 ሚልየን አጠቃላይ ተከታይ ያላቸው 120 ቲክቶከሮች ተጠርተዋል:: ምታዋ እንግዲህ ድምሩን 471 ሚልየን አጠቃላይ ተከታይ ያላቸው 180 የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የተገኙበት ነው ማለት ነው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን ያዘጋጀው ድግስ:: እርግጥ ነው በዲጂታል ማርኬቲንግ ሳይንስ ውስጥ ተደራራቢ ተከታይ Overlap Audience የሚባል መርህ አለ። ለምሳሌ እኔ አቤል ብርሃኑ የወይኗ ልጅንም ፣ አዶናይ የምትሉትንም እኩል ብከተል የሁለቱ አጠቃላይ ፎሎወር ውስጥ እኔ Overlap Audience እባላለሁ:: በዚህ ሂደት ብዙ ሰዎች ከአንድ በላይ የሆኑ ኢንፍሉዌንሰሮችን ሊከተሉ ይችላሉ። ይህንን ተደራራቢነት በግምት 40% ያህሉን ብንቀስ እንኳን ተደራሽነቱ ወደ 280 ሚሊዮን ይደርሳል። ይህ ቁጥር ደግሞ ከመላው የሰሜን አሜሪካ (USA, Canada, Mexico) ሕዝብ ግማሽ ያህሉን ይሸፍናል። ወይም ደግሞ የናይጄሪያን እና የኢትዮጵያን ጠቅላላ ሕዝብ በአንድ ላይ ደምረን እንደመድረስ ማለት ነው። በአጭሩ እነዚህ 180 ሰዎች በአንድ ድምፅ “ኢትዮጵያን ጎብኙ” ብለው ኮንቴትንት ቢሰሩ በዓለም ላይ ካሉ 30 ሰዎች መካከል አንዱ ይህንን ጥሪ ይሰማል ማለት ነው። ይህ ተራ ማስታወቂያ ሳይሆን Digital Conquest ነው። የዚህ ሰሚት ዋነኛ ግብ “Visit Ethiopia” የተሰኘውን የቱሪዝም ዘመቻ ማሳለጥ ነው። መንግስት በዚህ ዓመት በትሪልየን አይደል በጀት የመደበው? ከዛ ላይ ቱሪዝም ዘርፉ ካለው ገቢ ላይ ለቪዚት ኢትዮጵያ የተወሰነውን መደበ እንበል:: ያው የተመደበው በጀት ባይነግሩንም:: የሆነው ሆኖ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የአንድ ሀገር ገጽታ የሚገነባው በባህላዊ መገናኛ ብዙኃን (CNN, BBC) ብቻ ሳይሆን በSoft Power ወይም ለስላሳ ተጽዕኖ ነው። ኢንፍሉዌንሰሮች የዚህ ኃይል ግንባር ቀደም ተዋናዮች ናቸው። ኢትዮጵያ በጦርነት በድርቅና በውስጥ ግጭት ስሟ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲጎድፍ ቆይቷል። ይህንን አሉታዊ ትርክት ለመቀየርና “ኢትዮጵያ ለጎብኚዎች ክፍትና ሰላማዊ ናት” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የዲጂታል ዘመቻው አስፈላጊነት በንድፈ-ሐሳብ ደረጃ አጠያያቂ አይደለም። ወደ ዋናው አንገብበጋቢ ተቃውሟችን ለማለፍ እውር ሰጋር ፈረስ የሚል ስም እንዳያስለጥፍብን ተቃውሟችንን በማስረጃ እስደግፈን ማለፍ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው ማስረጃ አቅርበን እንለፍ ተከተሉኛ! ኳስ የምታዩ በተለይ የአርሴናል ደጋፊ የሆናችሁ ይሄንን በደንብ ታስተውላላችሁ:: አፍሪካዊቷ ሃገር Rwanda የአርሴናል ማልያ እጀታ ላይ "Visit Rwanda" ብላ ለማፃፍ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥታለች:: ታላቅ ተቃውሞ ገጥሟት ነበር። ሆኖም ግን ከጥቂት ዓመታት በኋላ የሩዋንዷ የቱሪስት ፍሰቷ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ የወጣው ወጪ ትርፋማ ኢንቨስትመንት (ROI) መሆኑ ተረጋግጧል። ይሄን ነገር ከእኛ ሃገር ጋር የሚለየው ሰፊው ክፍተት እዚህ ጋር ነው:: የተቃውሟችንም ሎጂክ ምሰሶም ይሄ ነው:: ሩዋንዳ ያንን ያህል ወጪ ለቱሪስት ስህበት ፎጭጭሸ ያደረገችው የውስጥ ሰላሟን አረጋግጣ:: መሰረተ ልማቷን አሟልታና የቱሪስት አገልግሎቷን አሳልጣ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ምርትና አምራች ኃይሉ ገበሬ ገና በውስጥ ችግሮች እየታመሰ Marketing ላይ ማተኮር "ጋሪውን ከፈረሱ ፊት ማስቀደም" ስለሆነብን ነው:: በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ የኑሮ ውድነት:: በዋጋ ግሽበት እና በአንዳንድ አካባቢዎች በረሃብ እየተፈተነ ባለበት ወቅት:: ለኢንፍሉዌንሰሮች መስተንግዶ የሚወጣው በጀት ሥነ-ምግባራዊ ጥያቄ ያስነሳል:: ለምን በሉኛ! የሰሚቱ በጀት ከቱሪዝም ገቢ ላይ የተመደበ መሆኑ በራሱ በኢኮኖሚክስ መርህ Re-investment ሊባል ይችላል። ማለትም ከዘርፉ የተገኘን ገቢ ዘርፉን ለማሳደግ መጠቀም። በሳይንሳዊው የሀብት አጠቃቀም ስሌት ለአንድ ኢንፍሉዌንሰር ለሚከፈል የአምስት ኮከብ ሆቴል ወጪ ፣ ስንት የተራቡ ወገኖችን መመገብ ይቻል ነበር? የሚለው ጥያቄ የሞራል ልዕልና አለው። በአንድ ሀገር ውስጥ መረጋጋት ሳይኖርና ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት ባቃታቸው ሁኔታ የሚደረግ የገጽታ ግንባታ፣ እንደ ውጫዊ ቅብ (Lipstick on a pig) ሊቆጠር ይችላል። የሰሚቱ አዘጋጆች እንደሚሉት “ሀገር መለወጥ ካለባት ማስታወቂያውም መሰራት አለበት” የሚለው መከራከሪያ ጠንካራ ቢሆንም የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ግን “የውስጥ ቁስልን በሜካፕ መሸፈን” የሚመስል ተግባር ውስጥ እንድንገባ አድርጎናል። ቱሪስቱ ቢመጣ እንኳን በጸጥታ ችግር ምክንያት ተንቀሳቅሶ መጎብኘት ካልቻለ ኢንፍሉዌንሰሮቹ የሰሩት ማስታወቂያ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሆኖ ስለሚገኝ በረጅም ጊዜ የሀገሪቱን ታማኝነት ይጎዳዋል። መንግስት በችግር ላይ ላለው ህዝብ ቅድሚያ ሳይሰጥ ለውጭ እንግዶች የሚያደርገው ድግስ በህዝብና በመንግስት መካከል ያለውን መተማመን ያላላል። የአፍሪካ ኢንፍሉዌንሰሮች ሰሚት በራሱ መጥፎ ሀሳብ አይደለም እንዲያውም ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ዲጂታል ምህዳር ትልቅ ፋይዳ አለው። ነገር ግን ጊዜው ህዝብ በረሃብና በኑሮ ውድነት በሚማቅቅበት ወቅት መሆኑ የቅድሚያ ተዋረድ ስህተት (Strategic Misalignment) እንዳለ ያሳያል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት “ውብ መታየት” ብቻ ሳይሆን “ውብ መሆን” ጭምር ነው። የውስጥ ሰላምና የዜጎች የሆድ ጥያቄ ሳይመለስ የሚደረግ ማንኛውም ትልቅ ድግስ፣ የቱሪዝም እድገት ሳይሆን “የገጽታ ግንባታ ጭንብል” ሆኖ ሊቀር ይችላል። ስለዚህ፣ መንግስት እንዲህ ያሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ሲያቅድ፣ ከውጫዊው ብልጭልጭ ይልቅ የውስጣዊውን ህመም ሚዛን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
ዶስቶይቭስኪ Note The Underground ላይ እንዲህ ይላል፦‹‹ለመተኛት ብቻ የምትጠቀማት ያቺ ክፍልህ ከሆነ ግዜ በኋላ መላው ዓለምህ ሆኗ ትቀራለች!›› አጋጥሟችሁ ያውቃል? አንድ ቀን አንድ ሰውን እናጣለን፤ ከዛ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ይበላሻል!። በአስፓልቱ አደባባይ መስቀለኛ ጋር የተሰቀሉ ሁለት የመብራት ፖሎች አሉ። አንዱ ያበራል ሌላኛው ግን ጠፍቷል። እና በሚበራው አንፖል ዙርያ የሚያንዣብቡ የእሳት እራቶች አሉ። የጠፋውን ግና ልብ የሚለው አልነበረም። የእሳት እራት እንዲህ ነች ወደ አንፖል የምትጠጋው ብርሃን ለመስረቅ ብቻ ነው። አንዳንዴ ባላድግ ነገሮች እና ሰዎችን ባለምድ የሚል ምኞት ነበረኝ። ለተከታታይ አራት አመታት ማታ ከመተኛቴ በፊት ለፈጠረኝ አምላክ እንዲህ እያልኩ እጸልያለሁ፦እውቀቴና እድገቴን ወስደህ የድሮ ደስታዬን መልስልኝ። ያሳለፍነው ጣፋጭ የልጅነት ግዜያት ተቀልብሰው የምንቆያት አንድ ቀን በአፍ የመረረች የልብ ህመም ትሆናለች። ያኔ ምንም የማናስብበት ግዜያት በፍጥነት አልቀው ተመሳሳይ አሰልቺ ቀኖችን እንደጋግማለን። እነዛ የዝናብ ላይ ሩጫዎች፣ የባህል ዋዜማ ጉጉቶች፣ የንጹህ ፈገግታ ድምሮች፣ እውነተኛ ወዳጅነት፣ ልብስ የሌለበት ልባዊ ፍቅር በጠቅላላ በመዳፍ ላይ እንዳለች እፍኝ ተበትኖ ተሰውሯል። እንደ እፉዬ ገላ በገዛ እድሜያችን ስሌት እፍ እፍ ተብለን ከልጅነታችን ተገፍተናል። የድሮው ከረሜላ እንዳለ ነው፤ ነገር ግን ምላሳችን ስር ያለው የከረሜላ ጥፍጥና ዛሬ ላይ የለም። በቀላሉ አንደሰትም በከባዱም ደስታ ጠፍቷል። በትልቁም በትንሹም እርካታ የለሽ ደባሪ ሰው ሆነናል። አምነን የማንቀበለው እንዲህ ያለው እውነት ያማል!። አሁን ይሄን ስጽፍ ለሊት ሆኗል። ምንአልባት ይህን ጽሁፍ ጥቂቶች ነው የሚያነቡት። ታውቃላችሁ ሁሌም ለሊት በዚህ ሰዓት እኔነቴን እንደዚህ እለዋለሁ፦ሁሉም ነገር ይቀየራል፤ አዎ ትቀየርና ተስፋ የሚያደርጉብህን ሁሉ ታኮራለህ ብዬ ቃል ገብቼልህ ነበር። ነገር ግን ምንም ለውጥ የለም!። ከትናንት የከፋ ነው የገጠመኝ፤ እራሴን እራሱ ማትረፍ አልቻኩም!። «ወፍ ጭጭ እስኪል ቆሜ ነው ሌቱን ማነጋው!» 🎶 ሞገስ ዘአምድ
ድሬዳዋ ለአንድ የስራ ጉዳይ ሄጄ እየተመለስኩ ሳለ ፕሌን ውስጥ ከጎኔ ከተቀመጠጭ ቆንጅዬ እንስት ጋር ለመተዋወቅ ያህል ጨዋታ ጀመርኩ እኔ 👉 ሰላም ቆንጂት እሷ 👉 ሰላም ወዳጄ እኔ 👉 ከድሬ ወደ ሸገር በሰላም ነው? እሷ 👉 አዎ በሰላም ነው አንድ ሴቶችን ብቻ የሚመለከት የውይይት መድረክ ላይ ተሳትፌ እየተመለስኩ ነው እንጂ የሸገር ሰው ነኝ። እኔ 👉 ምን ነበር መድረኩና ውይይቱ? እሷ 👉 የወንዶች በሀሪ እና አጠቃላይ ከሴት ጋር ባላቸው ግንኙነት ያላቸው ማንነትና እውነታ ምን ይመስላል የሚል ሀሳብ ነበር። እኔ 👉 እና ከመድረኩ ምን ጭብጥ አገኛችሁ? እሷ 👉 እንግዲህ በውይይታችን መሰረት የትግሬ ወንዶች ግብረ ስጋ በጣም ይወዳሉ። የደቡቦቹ ደግሞ ነገርያቸው አንደኛ ነው። ኦሮሞዎች ለትዳራቻው ታማኝ ሲሆኑ አማራዎች በበኩላቸው በአልጋ ላይ ጨዋታ የሚደርሳቸው የለም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። እኔ 👉 እንተዋወቅ ገብረ መድህን 👉 እርገጤ 👉 ገመቹ 👉 ሹልቃ እባላለሁ። ታሮስ አለሙ
እኔም ልከተልህ ጀምበር በሚለው ዜማው ትዝታን ይቀሰቅሳል የጥንቷን ኢትዮጵያን መናፈቁን ያወሳል "ፀሀዬ ደመቀች" በሚለው የአምባ ልጆች መዝሙር በካራማራ ሜዳ ለሀገራቸው የወደቁ ጀግኖች ልጆች ድምፅ ያስተጋባል ያ ዜማ ትላንትን ያስናፍቃል ። ዛሬ አናታችን ላይ ሰፍሮ ያሰቃየንን ጎጠኝነት " ደመና ፣ክረምት የጨፈገገ" ይለዋል ። "ብርሀን አውሰኝ "ብሎ ይማፀናል አዲስ ተስፋ አዲስ ብርሃን ይማፀናል የጠራቸው ወራት የሰኔ እና የግንቦት ተከታዮች ናቸው ምናልባትም ብርሀን አውሰኝ የተባለው ደርሶ ብርሀን እናይ ይሆናል። በመጨረሻም ተነሳ ተራመድ ብሎ ያከትማል በመሰረተ ት/ት ዘመቻ ለብዙዎች ፊደል ባስቆጠሩ ወጣቶች ዜማ ይደመድመዋል ። የአሁኑ ተነሳ ተራመድ ግን ለ ፊደል ቆጠራ አይደለም ተሸክመን ሰላም የነሳንን መከፋፈል ለመጣል ነው። ቴዎድሮስ ካሳሁን ለጆሮአችን ካሳ ሰጠን ያውም እሱ ላላደማው ጆሮ።
ዳስ ጣል ልቤ (ብሶት ንቀትን ሲወልድ) 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ኢትዮጵ ያሚለው ሙዚቃው ላይ " ይዤ አላነሳም እጄን ከቀሚሷ ፤ እናትኮ ናት ተስፋ አልቆርጥም በሷ" የምትል የአቋም መግለጫ የመሰለች ስንኝ አለችው። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በማለቱ ብዙ ተዘብቶበታል። ቆሞቀር ፣ ቅዠታም ፣ ነጋዴ ተብሎበታል። ግን ሰውየው አሁንም ብቻውን ቆሞ እኔ ልክነኝ እናንተ ናቹ የተሳሳታቹት ብሎ በልበ ሙሉነት ከመላ ሀገሩጋር እየተሟገተ ነው። እንደተናገረው አሁንም ቀሚሷን ይዞ አልለቅም ብሎ ሙጥኝ እንዳለ ነው። የአቋም ሰው መሆን ማለት ይሄ አይደለ? ዳስ ጣልን ሲጀምር እንዲህ ይላል " ለካ እንዲህ ነው ማለቅ እህ እያሉ ነዶ ሀገር የሞተበት የት ያለቅሳል ሄዶ " ዳስ ጣል የሚለው ለራሱ ለልቡ ነው። የጠበቀው ተስፋ እንዳሰበው አልሆን ቢለውም ፣ የሚወዳት ሀገሩ እጁላይ ብትሞትበትም ተስፋ ቆርጦ አልተዋትም። ዳስ ጥሎ ማልቀሱን መርጧል። ግን ደሞ ዳሱን የት ይጣለው? ሀገር ሞታበት ምኑላይ ድንኳን ይዘረጋል?.... ልቡ ላይ። ማንም ጉልበተኛ መሬትላይ ስልጣን ቢኖረውም ልብ ድረስ ገብቶ ድንኳን የማፍረስ አቅም ግን አይኖረውም። ቦታ መረጣው ልዩ ነው። እንደ አንድ የጥበብ ሰውም ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል? ከዛ በጣለው ዳስ ውስጥ እንዲህ እያለ ሙሾውን መደርደር ይጀምራል ያቆምኳትን ሀገር ተፈትኜ በእሳት እንዴት አቀርቅሬ ባንዲራየን ላንሳት። አባይ ለዘዴው በአፍ ይቀድማል አምኖ መከዳት እንዴት ያማል! ወርቅ ያበደረ ደርሶት አለት እንዴት ይችላል ዝም ማለት? ከነገ ዛሬ ይሻል ባልኩኝ የራሴን ጩኸት ተነጠቅኩኝ በሙሾው መሀል ተጠያቂ ያላቸውን። አምኗቸው የከዱትን... "በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር" እያለ ይወርፋቸዋል። እንደ ባህላችን እንደወጋችን የትልቅ ሰው ሞት ላይ ሙሾ ሲወርድ ፉከራ ቀረርቶም ሊኖር ግድነውና እሱም ቀረርቶውን ይጀምራል። " ጀግኖች ሞተውላት በመርዝ ጋዝ ነፍረው ተንገብግበው በእሳት ዘመን ተገላብጦ እንዴት አቀርቅሬ ባንዲራየን ላንሳት " እዚህ ቀረርቶ ውስጥ ያለውን ቁጭት በሚሰቀጥጥ ቃል ነው የሚያስቀምጠው። በማይጨው ጦርነት የመርዝ ጋዝ ተረጭቶባቸው የሞቱትን አርበኞች አሟሟት " በመርዝ ጋዝ ነፍረው ተንገብግበው በእሳት " ብሎ ነው የሚሰቀጥጠውን ምስል የሚቀርፅብን። ይሄን መስማት በራሱ ግብግብ የሚያደርግ ነገር አለው። እነዛን ጀግኖች እንደዛም ሆነው ከሞቱት ሞት የባሰውን አሁን ነው የሞታችሁት ሲላቸው ደሞ እቺን ይጨምራል "የኢትዮጵያ አርበኞች የጥንት አርበኞች እነ አናብስቱ ሲረገጥ ባንዲራው ገና አሁን ሞቱ" ያኔ እንደዛ በመርዝ ነፍረውንኳ ባንዲራቸውን አላስረገጡም ነበረ። አሁን ግን ከሞታቸው የከፋ ሞት ገጠማቸው። ባንዲራዋ ተረገጠች። ከዛ ከአርበኞቹ መለስ ይልና ወደኛ ይዞራል ደሞ "ካለቦታው ሲሆን ወርቅ አይደለም ዝምታ - ለበግም አልበጃት አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት" ይለናል። ከስነ ቃሎቻችን ሁሉ አሁን ላይ በትክክል እየተገበርናት ያለችው " ዝምታ ወርቅ ነው " የምትለዋን ነው። እሱም የሚሞግተን በሷ ነው። በርግጥ እንደ ሁኔታችን በግ መባል ሲያንሰን ነው! በመጨረሻ በሀዘን አንጀቱ አሮ ስለደበነ ብሞትም ልሙት እንጂ ገዳይዋን እያየሁ ዝም አልለውም የሚልበት ደረጃላይ ይደርሳል። እንኳን እኔ ሀገርስ ይሞት የለ ብሎ ማለት ነው። "ፍቅርን ብየ እንጂ ተግቼ ለሰላም እኔስ መታገሴ መች ከሀገር ይበልጣል እኔስ አንድ ነፍሴ" እያለ ይፎክራል። ከዚህ በኋላ ያለው በሀዘን አእምሮው ተቃውሶ ከጉልበተኛውጋር ጫማ የሚለካካበት ነው። የቋጠረው ብሶት ንቀት ወልዷል። ይሄም ከሀያላኑጋር አንተ ማነህና ወደሚል እሰጣገባ ይከተዋል። ንቀቱንም መደበቅ የማይችልበት ደረጃላይ ስለደረሰ እንደ ህፃን ነው የሚያዋራው። " ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን! " አንተም ሰው ሆነህ የሚል ይመስላል... " ወይድ አታስቆጥረኝ ዘር አጥንቴን እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን! " ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን! በሀዘናችን ላይ እየተገኙ ሀዘናችንን ማራከስ ልምዳቸው አይደለ? ለዚ ነው መጥቶ የአዞ እንባውን እንዳያፈስበት ዞር በልልኝ አሁን አርፌ ላልቅስበት። ሀዘኔን አታራክሰው። በምን እንዳዘንኩ እኔ አውቀዋለሁ መተህ አትዘላብድብኝ የሚለው። ይልቅ ባንዲራዬን ላንሳበት ወግድድልኝ ነው ነገሩ። አጀብ ! እናትህ ወንድ ወለድኩ ትበል!
"በኤዲስ ትሞ^ታለህ፥ ከአስር ዓመት በኋላ ኤድስ ይይዝሃል" የፍርሃት ቡጢ ነረተን። ባለንበት ደርቀን ቀረን። አስፈሪ አይኖቿን መመልከት ከብዶን አቀረቀርን። "መዳፋችሁን አምጡ፥ እጣ ፈንታችሁን እነግራቸዋለሁ" ስትለን የታዘዝናት እየሳቀን ነበር። መዳፍ አንብባ የተሰማትን ስትነግረን ግን ድንጋጤ በጥፊ አጮለን። የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ነበርን። ከትምህርት ቤት መልስ እንደ ዘወትር ልማዳችን ከአርሰናል እና ከማንችስተር ማን እንደሚበልጥ እየተከራከርን ወደ ሰፈራችን ስናዘግም ነበር። የሳምራዊትን ጡ^ት ውበት እና የከድጃ ቂ^ጥ ግዝፈት እያደነቀን ፥ ባዮሎጂ አስተማሪያችን ላይ እየተሳለቅን... ወደ ሰፈራችን ጉዞ ጀመርን። "የሳምራዊት ጡ^ት ሲያምር ፥ የከድጃ ቂ^ጥ ሲያምር" እየተባባልን... ኤልሳ አስቆመችንና መዳፋችንን እንደንዘረጋላት ጠየቀችን። ሳናመነታ ተስማማን። "መዳፍ ተመልክታ እጣ ፈንታ ትናገራለች" ሲባል ሰምተናል። አራት ጓደኛሞች እየተበሻሸቅን ወደ ሰፈራችን ስናዘግም አስቆመችን። የመተናኮል ልማድ እንደሌላት ስለምናውቅ ቆምንላት። መዳፋችንን እንድንዘረጋ ስትጠይቀን ታዘዝናት። ከሁላችንም ቀድማ የመሳፍንትን መዳፍ ተመለከተች። ለግማሽ ደቂቃ ያህል ብቻ መዳፉን እንደነገሩ ካየች በኋላ ፊቱን በጥንቃቄ መረመረች። "ማነው ስምህ?" በጎርናና ድምጿ ጠየቀችው "መሳፍንት" እየሳቀ መለሰላት "ኤዲስ ይይዝሃል። ከአስር አመት በኋላ ኤዲስ ይይዝሃል። መሞቻህ እሱ ነው" ሁላችንም እኩል ደነገጥን። ድንጋጤያችን ስሜት አልሰጣትም። ኤልሳ ስመ-ጥር እብ^ድ ናት። ቁመቷ ግዙፍ ነው። ሁሉም ሰው ተንጠራርቶ የሚመለከታት ብቅል አውራጅ ናት። ረጅም የወታደር ካፖርት ትለብሳለች። ከስክስ ጫማ ትጫማለች። መልኳ ብስል ቀይ ፥ድምጿ እንደ ወንድ ጎርናና። ረጅም ቀይ ወንድ ትመስላለች። በጨርቅ የተቋጠረ ቡቱቶዎቿን በረጅም ሽመል ቋጥራ ፥ በጀርባዋ ትይዛለች። አጠገቤ የቆመውን ተባረክ መዳፍ አፈፍ አደረገች። መዳፉን በጥንቃቄ መረመረች። "ማነው ስምህ?" እንደ ቀደመው በጎርናና ድምጿ ጠየቀችው "ተባረክ እባላለሁ" ድምፁ ተንቀጠቀጠ "አተኩረህ ተመልከተኝ። አይኔ ስር ተመልከት" እንደታዘዘው አደረገ። "ስንተኛ ክፍል ነህ?" "ስምንተኛ ክፍል ነኝ። ዘንድሮ ሚኒስትሪ እፈተናለሁ" ከፍርሃቱ እየታገለ እንደሆነ ድምፁ ያስታውቋል። "ሚኒስትሪ አትፈተንም። ከፈተናው በፊት ትሞታለህ" የተንገዳገደ መሰለኝ። ወይንም ተንገዳገደ። ኤልሳ ግድ አልሰጣትም። የበሀይሉን መዳፍ አፈፍ አደረገች። ሊሸሻት ፈልጎ ነበር። አልተሳካለትም። "ማነው ስምህ?" "በሀይሉ" "ከሁለት አመት በኋላ ታብ^ዳለህ" ልሸሻት ፈለግሁ። እጣ ፈንታዬን ማወቅ አስፈራኝ። ወዴት እንደምሸሽ ማሰላሰል ጀመርሁ። መሮጥ የተሻለው አማራጭ እንደሆነ ባውቅም ባለሁበት ደንዝዤ ቀረሁ። ትከሻዬ ላይ እጇን አኖረች። ጉልበቴ ዛለ። መቆም ከበደኝ። "ቀና ብለህ እየኝ" እየፈራሁ አይኖቼን ወደ አይኖቿ ላክሁ። "ፈርተኻል" "አዎ ፈርቻለሁ" ትታን ሄደች።እጣዬን ሳትነግረኝ ጉዞ ጀመረች። እፎይ አልኹ ቀናት መደበኛ ጉዟቸውን ሲጀምሩ ሁሉም ነገር የተረሳ መሰለ። የኤልሳን አጀንዳ ዘነጋነው። ትኩረታችን ሚኒስትሪ አልፈን የሀይስኩል ተማሪ ለመሆን መመኘት ሆነ። በየለቱ ስለ ሚኒስትሪ እንወያያለን። ቀጥለን የሳምራዊትን ጡ^ት እና የከድጃን ቂ^ጥ እናወድሳለን። የሚኒስትሪ ፈተና ሁለት ቀን ሲቀረው በሀይሉና መሳፍንትን አስከትዬ እነ ተባረክ ቤት ሄድን። እንዴት ባለ መንገድ እንደምንኮራረጅ ልንወያይ እነ ተባረክ ሰፈር አቀናን። ሰፈራቸው ስንደርስ መንደሩ ታውኳል። በማመንታት ወደ ቤታቸው ስንቃረብ የለቅሶ ድምፅ ሰማን። መሳፍንት በቆመበት እንባው ፈሰሰ። "የኤልሳ ትንቢት ተፈፀመ" አለኝ ከእንባ ጋር። ድጋሚ ጉልበቴ ዛለ። መቆም ተሳነኝ። ምድር በፍጥነት መሽከርከር የጀመረች መሰለኝ። ጓደኛችን ተባረክ ከሚኒስትሪ ፈተና በፊት ሞ^ተ። ምን እንደገ^ደለው አናውቅም። "ለሊቱን ሞ^ቶ አደ^ረ" ተባልን የተባረክ ሞ^ት በሀይሉ ላይ የፈጠረውን ድንጋጤ ልዘነጋ አልችልም። "እኔም እንደማ^ብድ ነግራኛለች" አለኝ እያለቀሰ። መሳፍንት በጭንቀት ከአጠገባችን ሸሸ። የምለውን አጥቼ ዝም አልኹ። ወራት አለፉ፥ የበሀይሉ ቤተሰቦች ከተማ ቀይረው ወደ አዲስ አበባ ገቡ። ከበሐይሉ ጋር ተራራቅን። እኔና መሳፍንት "የውሾን ነገር ያነሳ..." ተባብለን የኤልሳን ትንቢቶች ላናነሳ ወሰነን። ስለ ሚኒስትሪ ውጤት ከማውራት የሚተርፈንን ጊዜ ስለከድጃና ሳምራዊት በመወያየት እናሳልፋለን። "የከድጃ ቂ^ጥ የሳምራዊት ጡ^ት" እንላለን። ከእለታት በአንዱ መሳፍንት ቤታችን መጣ። አይኑ ደም ለብሷል። እጁ ይንቀጠቀጣል። "በኤድስ እንዳልያዝ ምን ላድርግ?" አለኝ። ጥያቄው ግራ አጋባኝ። "ስለ በሐይሉ ሰምተሃል?" አለኝ "ምን ሆነ?" ልቤ ደረቴን በጥሳ ልትወጣ ታገለች። "የአእምሮ ህመም ገጥሞት አማኑኤል ሆስፒታል ገብቷል። ከድጃ ናት የነገረችኝ" የድንጋጤ ቡጢ ነረተኝ። የመሳፍንት ጉንጮች ላይ እንባ ተራመደ "የማለቅሰው ለራሴ ነው፤ እኔም በኤዲስ እንደምሞት ነግራኛለች" አለኝ። የማፅናኛ ቃል ስላልነበረኝ ዝም አልኹ። ከድጃን ጠላኋት። ሆነ ብላ መርዶ የነገረችን መሰለኝ። አመታት እንደ ዋዛ አለፉ። ኤልሳም ተሰወረች። "ጅ^ብ በልቷት ሞታለ^ች" ይላሉ አንዳንዶች። ሌሎች ደግሞ "ተሽሏታል" ይላሉ። ከተማ ስለመቀየሯም የሚናገሩ አሉ። እኔና መሳፍንት ከኤልሳ ትንቢቶች ጋር አለን። መሳፍንት Hiv በደሙ ውስጥ እንዳለ ካረጋገጠ አምስት አመታት ተቆጥረዋል... ተስፋአብ ተሾመ