tgindex
😷 FKR en GETM💕💕

😷 FKR en GETM💕💕

Статистика

@yen tewlde❤️✅ህይወት ትቀጥላለች አንዱን ከሌላው ድርና ማግ እያደረገች። ❤️✅ውድ የቻናሉ ቤተሰቦች ፍቅርን እንዝራ..ፍቅርን እንስበክ..ፍቅርን እናቀንቅን።..... ❤️✅ያልተነበቡ ድርሰቶችን..ግጥሞችን..ታሪኮችንና ሌሎች መጻጽፎችን ያገኙበታል። Join ብለው ይቋደሱ። . . . . ለማስታወቂያ ስራዎች [For promotion] @yefkrinegri

Последний пост
20 сент. 2022 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 628
−1 за 4 дн.
Сутки
−3
−0,18%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
17,1 тыс
20 постов
Вовлечённость
1049,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 20 сент. 2022 Đł.38,1 тыс35

    ለተወሰኑ ቀናት ነገሮች እንደዛው ባሉበት ቀጠሉ። ልጄ ምንም እንኳን ስለአባቷ ያለውን ነገር ብትቀበልም ለጊዜው ልታገኘው እንደማትፈልግ አስረግጣ ነገረችኝ። እኔ ግን ላገኘው እፈልጋለሁ!! አሁንም የቀረኝ ነገር እንዳለ ነው የሚሰማኝ!! ባገኘው ፣ የሄለንን ያህል እንኳን ወዶኝ ባይሆን አብረን ያሳለፍነው ጊዜ በልቡ ውስጥ የሆነ ቦታ እንደነበረው ማወቅ ከሆነ መታሰሬ የሚፈታኝ ነገር ይመስለኛል። ለልጄ ያልኳት ከልቤ ነው። ይቅርታ እንዲለኝ አይደለም መሻቴ ምክንያቱ እኔን ትቶ ለመሄድ ውሃ ያነሳ እንደነበር ነው ማወቅ የምፈልገው። በሌላ ቋንቋ እሱጋ የነበረኝን ዋጋ ነው ማወቅ የፈለግኩት። በቻልኩት አጋጣሚ እና ጊዜ የባባን እናት እየሄድኩ አያታለሁ። ምንም ለውጥ የላትም። እነግሩም የህክምና ወጪዋን እየሸፈኑ ቢሆንም ከዛ ባለፈ የተነጋገርነው ነገር የለም። ምንም ከመወሰኔ በፊት ሄለን ብትነቃ ውሳኔውን ለሷ ለመስጠት ፈልጌ ይመስለኛል በዝምታ ቀናት ያስቆጠርኩት። አሸናፊ ለባባ ስለእናቱ እንዳልነግረው ቢነግረኝም ያን ማድረጉ ልክ መስሎ ስላልታየኝ ለባባ በእድሜው ሊገባው በሚችል መልኩ እናቱ ለጊዜው መታመሟን ነግሬው የተወሰነ ቀንም ይዤው ሄጄ አሳይቼዋለሁ። ምናልባት እሷ ብታልፍ እንኳን ዋሽቼው ልጄ አላደርገውም። እናቱ እንደሞተች አውቆ ከልጄ ለይቼ የማላየው እናቱ እንደሆንኩ አሳየዋለሁ። እናት እሆነዋለሁ!! የማትዋሸው እናት!! መጀመሪያ የወሰድኩት ቀን እንድትነቃለት ስሟን እየጠራ ሲያለቅስ እንደህፃን አብሬው አልቅሻለሁ!! የዛን ቀን እንቅልፉን ተኝቶ ሁሉ እየቃዠ ይጠራት ነበር። አልጋዬ ላይ አምጥቼው አጠገቤ አስተኝቼው በጭንቀት እና በላብ የተጠመቀ ትንሽዬ ፊቱን እያየሁት ለረዥም ሰዓት እንቅልፍ አልወሰደኝም። እቅፌ ውስጥ ሲሆን እንደምጠብቀው ልቡ ነግሮት ነው መሰለኝ ለጥ ብሎ ተኛ!! ከተከታዮቹ ቀን በአንዱ ከስራ ተመልሼ ከልጄ እና ከባባ ጋር መክሰሳችንን እየበላን በሬ ተንኳኳ። የግሩም እናት ነበሩ። ከመጀመሪያው ቀን በኋላ አይቻቸው ስለማላውቅ እየገረመኝ ወደውስጥ እንዲገቡ ጋበዛኳቸው። "ላናግርሽ ፈልጌ ነበር። በልጆቹ ፊት ባይሆን ጥሩ ነው!" አሉኝ ወንበሩ ላይ እየተቀመጡ። ልጄ እኔ ምንም ከማለቴ በፊት ባባን ይዛው ወደክፍሏ ሄደች። "ምንድነው ሀሳብሽ? ውሳኔሽን ማወቅ እፈልጋለሁ! ልጄ ከዛ ቀን በኋላ ተረጋግቶ ምንም ነገር ማድረግ አልቻለም! ስራውን እንኳን በትክክል እየሰራ አይደለም! እሱ ዓመት ሙሉ ዝም ብትዪም እንደማይጠይቅሽ ስለማውቅ ነው ራሴ የመጣሁት! እየሆነ ያለው ነገር ምንም አልገባኝም! 'እሷ ለራሷም አልተረጋጋችም!' ይለኛል እሱ። መቼ ነው የምትረጋጊው? አንቺ እስክትረጋጊ ከዛሬ ነገ ፖሊስ መጥቶ በሬን አንኳኳ : ልጄን ወሰደብኝ እያልኩ መሳቀቅ ገደለኝ" አሉኝ ያነገቱትን ቦርሳ እንኳን ከትከሻቸው ሳያወርዱ ይቀጥላል .......

  • 20 июн. 2022 Đł.26,9 тыс11

    "አብሮት ማሳደጊያ ያደገ ጓደኛው የነበረ ሰው እንደነበር ? ከሀገር ውጪ ነበር መሰለኝ ለእረፍት በመጣበት ነው የተገደለው።" "ገደለው?" አልኩኝ ሳላስበው። "ምነው ታውቂዋለሽ?" "አዎ! ማለቴ አላውቀውም ግን አሸናፊ ሲያወራ ሰምቻለሁ:: እርግጠኛ ነኝ እሱ ነው!! " አልኩኝ ደሜ ቀዝቅዞ ይቀጥላል እኮ ....

  • 20 июн. 2022 Đł.26,1 тыс9

    "ባንቺ ሁኔታ ስለምግብ ማውራት ቅንጦት ስለመሰለኝ እንጂ ቁርስ እንኳን ሳንበላ ነውኮ ጠዋት የወጣነው!" አለኝ ግሩም! ይቀጥላል ...... እኔ የምለው ዛሬኮ የአባት ሀገር ገና ነው!! በበዓል ግን ቁጭ ብዬ እንደፃፍኩላችሁ ታውቃላችሁ? ያው መውደዴን እንድታውቁት ታክል ነው። በዓሉ ለሚመለከታችሁ። ያማረ በዓል ከምትወዷቸው ጋር ይሁንላችሁ።❤️❤️❤️❤️❤️❤️🤣

  • 20 июн. 2022 Đł.25 тыс8

    "እ? አዎ አይ እርግጠኛ ነኝ! ችግር የለውም!" አልኩኝ ደረቴን በርቅሳ ልትወጣ ይመስል የምትደልቅ ልቤን እንዳያዩብኝ ልብሴን እየነካካሁ። ምንም ባልናገርም ፊቱን ማየት እንደሞት እንዳስፈራኝ ከሁኔታዬ ገብቷቸዋል። አባትየው ለአንደኛው ፖሊስ ሲያስረዳ ሲጨቃጨቁ አጠገባቸው ሆኜ እንደእሩቅ ድምፅ ነው የሚሰማኝ። የማስበው ሳየው ምን እንደምለው ነው! ሊመልስልኝ የሚችለውን መልስ መላ እመታለሁ። ልጅ እኔጋኮ ልጅ አለህ ስለው ይደነግጥ ይሆን? ይፀፀት ይሆን? እና? ቢለኝስ? የሆነ ስም ጠርቶ እገሌ ይጠራልኝ ብሎ አባትየው ሲቀውጠው ፖሊሶቹ አልፈቅድ ብለው እንደሆነ ገባኝ። ከመምጣታችን በፊት አጣርቶ ነው ማለት ነው? ፍርሃቴ ከማየሉ የተነሳ እዚህ ድረስ ከመጣሁ በኋላ እንቢ ብለው ሳላገኘው ብመለስ ብዬ አስቤ ለቅፅበት ደስ እንደሚለኝ ተሰማኝ። ትልቁን ፍርሃቴን ተጋፍጬ ከእውነት ከመጋፈጥ መሸሽ!! የሰው ልጅ በብዙ እንደዛ አይደለ? ፍርሃቱን በመሸሽ ውስጥ ያለውን መንገድ ያውቀዋል። ቢወደውም ቢጠላውም ስለለመደው ይኖራል። ፍርሃቱን ሲጋፈጥ ከተራራው ጀርባ ያለውን ግን አያውቀውም። ሳያውቀው ይፈራዋል። አልለመደውማ! ስለዚህ ፍርሃቱን እሹሩሩ እያለ የለመደውን የተለመደ ህይወት ይኖራል። የተባለው ሰው ተጠርቶ ተጨባብጠው። ሁኔታውን በእርጋታ ከተረዳዱ በኋላ ተስማሙ። ሰውየው አሸናፊ እንዲጠራ ትእዛዝ ሲሰጥ መሮጥ ሁሉ አማረኝ። ብቻ እነግሩም ስለተንቀሳቀሱ እግሬን ወደፊት እየዘረጋሁ ዘለቅኩ። ተጠርቶ ሲመጣ የሚቆምበት ቦታ የሆነ ፖሊስ ነገር እየመራ ወስዶ ሲያደርሰኝ እነ ግሩም ወደኋላ ቀሩ ከጀርባው ለእኔ ከማይታየኝ ከሆነ ሰው ጋር እያወራ እየሳቀ ብቅ አለ። ሲያየኝ እንደመቆም አለ። ፊቱ ግን የገረመው አይመስልም ነበር። የሆነ ቀን እንደምመጣ የሚያውቅ ዓይነት መረጋጋት ነው ያለው። በረዥሙ ቢተነፍስ ትንፋሹ በሚሞቀኝ ዓይነት ርቀት ላይ ደርሶ ሲቆም ለምን ላገኘሁ እንደመጣሁ ፣ ምን ልጠይቀው እንደነበር ሀሳቤ ሁሉ ጭንቅላቴ ውስጥ ተደነባበረ። እልህ ፣እንባ ፣ላለመሸነፍ ትንቅንቅ ..... አፈነኝ። ወዲያው ደግሞ በራሴ ተበሳጨሁ። እንዴት ያለሁ ልፍስፍስ ነኝ ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ እንኳን የበደለኝን ሰው ሳየው ጎብዞ መታየት የሚከብደኝ? እኔ እስካወራ ድረስ ከንፈሩን አላላቀቀም። አይኖቹን እንኳን አልሰበራቸውም። ሳይነቅል ከማየቱ የተነሳ በአይኑ እየቦረቦረኝ ያለ ዓይነት ስሜት ሁላ ነው የተሰማኝ። ለደቂቃ ትንፋሼን ውጬ አይኖቼን አይኖቹ ውስጥ ዘፈዘፍኳቸው። አፌን ለቆ ሲወጣ የሰማሁት ዓረፍተ ነገር "አብረን በነበርንበት ጊዜ ወደኸኝ ታውቅ ነበር?" የሚል ነው። ይቀጥላል እንግዲህ......

  • 20 июн. 2022 Đł.21,2 тыс9

    መጥፎ ሴት አይደለሁም። ግን ደግሞ መልዓክም አይደለሁም። የአሸናፊን ልጅ ልንከባከብ? ራሴን ፈራሁት። እኔ እኮ በእርሱ ምክንያት ማንንም የማላምን ደንባራ ሴት ሆኛለሁ። ሙሽራዋ ከአንድ ዓመት በላይ አብሯት ለመዝለቅ ያልፈለጋት ምንም የሆነች ዓይነት ሴት እንደሆንኩ እየተሰማኝ ታምሜያለሁ። እኔኮ በእርሱ ምክንያት ፍቅርንም ሰው ማመንንም ሰው መቅረብንም አጠገቤ እንዳይደርሱ አርቄ ቀብሬያቸዋለሁ። የእርሱን ልጅ ላሳድግ? እናቱ አይበለውና ብትሞት እናቱ እሆናለሁ? ራሴን ፈራሁት ...... "እማዬስ?" አለኝ ባባ ሳሎን ገብቼ የደነዘዘ ሰውነቴን ሶፋው ላይ እንደጣልኩት። 'እናትህማ እኔን ፍም ላይ ማግዳኝ ሆስፒታል ተኝታለች' ብለው ደስ ባለኝ። "ምነው እማ? ምን ሆንሽ?" አለችኝ ልጄ ተከትላ ..... እንደአዲስ ክው ብዬ ደነገጥኩ .... ምንድነው የምላት??? ምንም ከማለቴ በፊት ባባ "እማዬጋ ውሰጂኝ!" ብሎ እሪታውን አቀለጠው። ይቀጥላል። ...........

  • 20 июн. 2022 Đł.20,7 тыс7

    አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው #2 "የገጨሃት ቦታ ውሰደኝ ምናልባት ሰፈሯ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ስልኳን እዛ ጥላው ሊሆን ይችላል። የሚያውቃት ሰው ሊኖር ይችላል!" በውስጤ ምናልባት ጎዳና ላይ ቢሆንስ የምትኖረው ብዬ አስቤያለሁ ጮክ ብዬ አላወራሁትም እንጂ ምናልባት ከነአካቴው ስልክም አልነበራት ይሆናል። መታወቂያዋ ላይ ያለውን ቀበሌና የቤት ቁጥር ተከትዬ ቀበሌ ሄጄ ቤቷን ፍለጋ አስቤዋለሁ። ቀላል እንደማይሆን ግልፅ ነው። ቀበሌ አልወድም!! "በፍፁም እኔ አልነዳም። ህም ...በጭራሽ መሪ አልይዝም። ታክሲ .....ራይድ ይጠራ" ሲል አሳዘነኝ ማንም ትኩረት ሰጥቶ እሱን ያየው የለም እንጂ እሱም ከባድ ድንጋጤ ላይ ነው። አሁንም እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ነው። ሲያወራ መሸሻ ያጣ አይነት ዓይኖቹ መሬቱን ይምሳሉ። ይሄን እያለኝ ድርብብ ያሉ የሴት ወይዘሮ የሚያነክስ እግራቸውን በጌጠኛ ከዘራ እያገዙ የሚራመዱ ሰውዬ አስከትለው ወደ ክፍሉ ገቡ። "ኪያዬ ......ደስ አላለኝም ! በለሊት አትጓዝ እያልኩህ ...." እያሉ እያገላበጡ ሲስሙት እና ደህና መሆኑን ሲያረጋግጡ ልጃቸው ተገጭቶ እንጂ እሱ ገጭቶ አይመስልም። እሱም እናቱን ሲያይ የሆነው የልጅ መሆን ካቀፍኩት ህፃን አይለይም ነበር። በኋላ እሱም ገብቶት ነው መሰለኝ ከእናቱ እቅፍ ወጥቶ በማፈር ሲያየኝ ነው ገና ሰው እንኳን መኖሩን እናትየው ያዩት። "እባክሽ ልጄ አንድ ልጄ ነው በሽምግልና እንጨርሰው? (ባጌጠ ልብሳቸው እግሬ ስር ሲንበረከኩ ክብራቸው አላሳሰባቸውም። እናት ናቸዋ! ደንግጬ ደነዘዝኩ። ካሰብኩት በላይ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደተዘፈቅኩ ገባኝ። ከተንበረከኩበት ላነሳቸው እየሞከርኩ ከአፌ ግን ቃል አይወጣልኝም።) ካሱ የምንባለውን እንክሳለን። እናትየው እስኪሻላት ህፃኑንም ቢሆን ወስጄ እንከባከባለሁ። እባክሽ ልጄን አሳልፈሽ አትስጪብኝ?" ለደቂቃ ህፃኑን ሰጥቻቸው ጭልጥ ብዬ መጥፋት ሁሉ አሰብኩ። ባባ ቀልቡ የነገረው ይመስል ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ። የተገጨችው እህቴ ብትሆን ምንድነበር የምወስነው? ብትሞት የእነሱ ካሳ የህይወት ካሳ ይሆናል? እሺ ጥፋቱ የሷስ ቢሆን? እንዳለው እሷ ብትሆንስ ዘው ብላ የገባችበት? ኸረ ምን አይነቷ ሴት ናት ግን እዚህ ጣጣ ውስጥ ዘፍቃኝ ማን እንደሆነች እንኳን የማላውቃት "እባኮትን ይነሱ። እኔ ለራሴ ዞሮብኛል።" የተፈጠረውን አስረዳኋቸው። አባትየው መታወቂያው ላይ ባለው አድራሻ ቤቱን ሊያፈላልጉ ሀላፊነት ወሰዱልኝ። ማን እንደሆነች እና ከእኔጋር የሚያዛምዳትን ነገር እስክደርስበት ባባ እኔጋ እንዲቆይ ወሰንኩ። እነርሱም የሚያስፈልገውን ሊያሟሉለት እና ሊጠይቁት ቃል ገቡልኝ። አንድ ላይ በእነርሱ መኪና እናትየው እየነዱ አደጋው የደረሰበት ቦታ ሄድን:: ምንም ነገር የለም። ከአልፎ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ ውጪ በአካባቢው ማንም አይታይም። የመኖሪያ ሰፈርም አይደለም። ዓይኔ መሬቱ ላይ ካለ አንድ ብር ሳንቲም ላይ አረፈ። ደም ነክቶታል። ለምን እንዳነሳሁት አላውቅም ግን አነሳሁት። የሷ ይሆን? በእጇ ይዛው ነበር? ወድቆባት ልታነሳ ስትል ይሆን መኪናውን ያላየችው? ወይስ ሌላ ሰው የጣለው ሳንቲም ነው? ስልኬ ሲጠራ ባላወቅኩት ምክንያት ደንግጬ ዘለልኩ "አይዞሽ አይዞሽ" አሉኝ እናትየው መደንበሬን ሲያዩ "እማ በጠዋት የት ሄደሽ ነው? " ልጄ ናት። ቤቴን ረስቼዋለሁ። ሰዓቱን ረስቼዋለሁ። ዛሬ ቅዳሜ መሆኑንም እረስቼዋለሁ። "መጣሁ እናቴ! ለባብሰሽ ጠብቂኝ" አልኳት ቅዳሜ ጠዋት ሁል ጊዜ እናትና አባቴ ጋር ነው ቁርስ የምንበላው። እነርሱ ስልክ ተቀያይረን እቤት አድርሰውኝ ተመለሱ። የማልዋሸው በዛው ቢጠፉስ ብዬ አስቤያለሁ። ሰው ለማመን ቅርብ አይደለሁም። የመኪና ታርጋቸውን መዝግቤ መታወቂያቸውን ፎቶ ኮፒ አደረግኩ። "እማ ትልቅ ሰው የሚበላውን ምግብ ይበላል ኸረ ጥርስኮ አለው" ትለኛለች ልጄ ለባባ ምግብ ምን ልስጠው ብዬ ስባዝን እየሳቀችብኝ። ልጄ 15 ዓመቷ ነው። በስንት ዓመቷ ምን እንደበላች ጠፍቶኛል። ለመጨረሻ ጊዜ ገላዋን መች እንዳጠብኳት ረስቼዋለሁ ..... ባባን አጣጥቤ እነእማዬጋ ተያይዘን ሄድን:: "እግዚአብሄር የሆነ ነገር ሊያስተምርሽ ነው ይሄን ህፃን ወደ ህይወትሽ ያመጣው" አለችኝ እናቴ የሆነውን ሁሉ ከነገርኳቸው በኋላ። ከቤተሰቡ አንድ ሰው እንኳን ድንገት ቢያውቃት ብዬ አስቤ ነበር:: ማንም አያውቃትም። (እናቴ ምን ማለቷ እንደሆነ አውቃለሁ። ማግባት አለብሽ ልጅ መድገም አለብሽ ነው ቅኔው። ወንድሜ በሚያስቀና ትዳር ሶስተኛ ልጁን ሰልሷል። የእኔ ያለባል መቅረት ያሳስባታል:: ) "እማ ደግሞ እግዚአብሄር እኔን ስለሚወደኝ እኔን ለማስተማር ይሄን ህፃን አይቀጣም! የሆነችን ሴት በመኪና አስገጭቶ ለኔ ትምህርት አይሰጥም። እነርሱምኮ ፍጡሮቹ ናቸው እኔን ለማስተማር ህይወታቸውን የሚያዘባርቅባቸው አሻንጉሊቶች አይደሉም!!" አልኳት። ወንድሜና አባቴ ተያይተው ጨዋታውን ቀየሩት። ከእማዬጋ እንዲህ አይነት ወሬ ከጀመርን ማባሪያ የሌለው ጭቅጭቅ እንደሆነ ያውቃሉ:: እዛው ቤተሰቦቼ ቤት ሆኜ ወደ ከሰዓት ስልኬ ጠራ ባባ ኩርምት ብሎ ከተኛ ሰዓታት አልፈውታል። "አብርሃም ነኝ" "አብረሃም? አብረሃም?" "የግሩም አባት! ልጅቷን የገጫት ልጅ አባት... " "እእ ....እሺ " "የምትኖርበትን ቤት አግኝተነዋል። አከራዮችዋን አናግረን የእሷ ቤት መሆኑን አረጋግጠናል።" "በዚህ ፍጥነት? እንዴት? ያውም በቅዳሜ?" "ብዙም አስቸጋሪ አልነበረም:: የቤት ቁጥሩ የአከራዮችዋ ቤት ነው:: ደግሞስ የልጄ ጉዳይ አይደል? ይልቅ መምጣት ሳይኖርብሽ አይቀርም። ከባሏ ውጪ ማንም ዘመድም ሆነ የቅርብ ሰው እንደሌላት ነው የነገሩን።" "ታዲያ ባሏ እያለ እኔን ምን ቤት ናት ብላ ነው የፃፈችኝ?" "ባሏ ከታሰረ ሁለት ዓመት አልፎታል።" "እሺ እኔ ምን ቤት ነኝ መታወቂያዋ ላይ የተገኘሁት? ወይ ፈጣሪ ! " "እኔ ምን አውቄው ብለሽ? (እኔ አልፃፍኩሽ የሚል አንድምታ ባለው ለዛ) ምናልባት በባለቤትዋ? እስር ቤት ያለ የቅርብ ሰው ወይ ዘመድ የለሽም?" "በፍፁም ኸረ እኔ ጭራሽ የታሰረ የሩቅም ሰው አላውቅም። " "ምናልባት አከራዮችዋ ከሚነግሩሽ ነገር ፍንጭ ልታገኚ ስለምትችዪ ብትመጪ መልካም ይመስለኛል:: ብዙ አመት ኖራለች አብራቸው.... እ.... ባለቤቷ ... አሸናፊ ይባላል ነው ያሉኝ .......እንደው ካወቅሽው " ከጀርባዬ የሆነ ነገር ማጅራቴን በሀይል የደለቀኝ ነገር መሰለኝ .........ጭው አለብኝ። አይሆንም። እሱማ አይሆንም! ሊሆን አይችልም።... ስም ተመሳስሎ ነው.... ማሰብ ተሳነኝ!! "ምነው ሴትየዋ ሞተች እንዴ?" ትለኛለች የወንድሜ ሚስት ...... ይቀጥላላ ምን ታፐጣላችሁ??? 🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️

  • 20 июн. 2022 Đł.17,6 тыс8

    አታምጣው ስለው .... አምጥቶ ቆለለው (ርዕስ ነው) የስልኬ ጥሪ ነው ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ። ከንጋቱ 12:10 "ከሆስፒታል ነው የምንደውለው!! ዶክተር ፈቃደ እባላለሁ።" "በየሱስም! እናቴ ምን ሆነች?" ብድግ ብዬ ቁጭ አልኩ:: ማታ ስኳሬ ከፍ ብሏል ስትለኝ ነበር። "ወይዘሮ ሄለን አበራ አደጋ ገጥሟቸው ...." "ሄለን አበራ? በስመአብ! (ልቤ ጉሮሮዬጋ ደርሳ ነበር ምልስ ብላ አቃፊዋ ውስጥ ስትገባ ታወቀኝ) ምነው እያጣራችሁ ብትደውሉ? በዚህ ጠዋት ያልታመምኩትን ሴትዮ በድንጋጤ ልትገሉኝ ነው እንዴ? ተሳስታችኋል!! እኔ ሄለን አበራ የምትባል ሴት አላውቅም! " "ወይዘሮ ፌቨን አዳነ አይደሉም?" "ነኝ!" አሁን ግራ ገባኝ። ስልኬን ቢሳሳት ስሜን ግን አስተካክሎ ሊጠራ አይችልም። "የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ተብለው የተመዘገቡት እርሶ ኖት!" ከአልጋዬ በደመነፍስ ወረድኩ "እህ እኔ እንዲህ የምትባል ሴት አላውቅማ? ቆይ የሆነውን አስረዳኝ ምን አይነት ሴት ናት? ምን አይነት አደጋ ነው የገጠማት?" "የመኪና አደጋ ነው። ለጊዜው conscious አይደለችም:: ቦርሳዋ ውስጥ ባገኘነው መታወቂያ ላይ የእርሶን ስልክና ስም ነው ያገኘነው።" "እሺ መጣሁ!" አልኩኝ ነገሩ ምንም ስሜት ሳይሰጠኝ ..... አደጋ ደርሶ ነው እየተባልኩ ከዛ በላይ ጥያቄ ማብዛት ክፋት ነገር መሰለኝ። የእኔን ስም የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ብሎ ሊመዘግብ የሚችል ዘመድ አሰብኩ ........ ምናልባት በቤት ስሟ የማውቃት ዘመድ ..... ጭንቅላቴ እዚህም እዛም እየረገጠ የተባልኩት ሆስፒታል ደረስኩ እና የተባለውን ዶክተር አገኘሁት። የተባለችው ሴት የተኛችበት ክፍል ወሰደኝ። ሰውነቷ በአብዛኛው በፋሻ ስለተጠቀለለ የማውቃት ሴት እንኳን ብትሆን መለየት አልችልም ነበር። "የማውቃት አይመስለኝም!" አልኩት ግራ ገባቶኝ። ከጋውን ኪሱ መታወቂያዋን አውጥቶ ሰጠኝ። ሲገለባበጥ ሌላ ምስል ያሳየኝ ይመስል እያገለባበጥኩ አየሁት። በፍፁም አላውቃትም! ስሜና ስልክ ቁጥሬ ግን የመታወቂያው ጀርባ ላይ ቁልጭ ብሎ ተፅፏል። እድሜ 30 .... ቆንጅዬ ወጣት ናት። ፎቶዋ ላይ ጥርሷን ሳትገልጥ ፈገግ ብላለች። በወፋፍረሙ ተገምዶ ደረቷ ላይ የተዘናፈለ ፀጉር አላት ..... በፍፁም አይቻት አላውቅም። "ማነው ሆስፒታል ያመጣት?" አልኩኝ ትክክለኛ ጥያቄ ይሁን ሳልረዳ "አደጋ ያደረሰባት ሰው ነው ይዟት የመጣው። መጠበቂያ ክፍል ተቀምጧል ልታገኚው ከፈለግሽ? " ብሎ መልሴን ሳይጠብቅ በሩን ከፍቶ ወጣ ተከተልኩት የተባለው ሰው ከዶክተሩ ጋር ወደክፍሉ ስገባ ሲያየኝ ዘሎ ከመቀመጫው ተነሳ ..... አጠገቡ ተቀምጦ የነበረ በግምት የ4 ዓመት የሚሆን ህፃንም ተከትሎት ብድግ አለ። "ቤተሰቧ ነሽ? ምን ማድረግ እንደነበረብኝ አላወቅኩም ነበር! እጄን ለፖሊስ ልስጥ? እሰጣለሁ በቃ! (መላ አካሉ ይንቀጠቀጣል።) ከየት መጣች ሳልላት ነው ዘው ብላ የገባችብኝ በቦታው የነበረ ሰውም አልነበረም። አልነጋምኮ .... የሞተች መስሎኝ ነበር !" ድንጋጤው እንዳለ ነው የለበሰው ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ በደም እንደተነከረ ነው። እጆቹ ላይ የቀረውን የደረቀ ደም ሊጠርገው ግድ ያለው አይመስልም ወይም ከነጭራሹ ደም እጁ ላይ መኖሩንም አላስተዋለውም። ግራ ገባኝ። ምንም በማላውቀው ክስተት ውስጥ የተነከርኩት እኔ ምን ልበል? አይኖቼ ህፃኑ ላይ መንቀዋለላቸውን ሲያይ "ልጇ ነው። አብረው ነበሩ። እማ ብሎ ሲጮህ ነው ያየሁት እኔ እንጃ ምን እንደተፈጠረ። እሱ የእግረኛ መንገድ ላይ ነበረ። ቤተክርስቲያን እየሄዱ መሰለኝ ነጠላ ለብሳ ነበር። .... ቤተክርስትያን ለመሄድ ራሱ በቅጡ አልነጋም ነበር:: " ምን እንደማደርግ ሳላውቅ ህፃኑጋ ተጠግቼ በርከክ አልኩ። ደነበረ። ትንንሽ እጆቹን ልይዛቸው እጄን ስዘረጋ ሰበሰባቸው። "ስምህ ማነው?" አልኩት እናቱን መኪና ሲገጫት በአይኑ ካየ ሁለት ሰዓት ላልሞላው ህፃን የእኔ ጥያቄ ምኑ ነው? እኔስ ምኑ ነኝ? ዓለምስ ራሱ ምኑ ናት? "ባባ" አለኝ የደረቁ ከንፈሮቹን እያላቀቀ "ባባዬ እኔን ታውቀኛለህ?" አልኩት የማይጠየቅ ጥያቄ እንደሆነ እያወቅኩ። በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ። "አባትህ የት እንደሆነ ታውቃለህ?" አሁንም በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ። ግራ ገባኝ! ይህቺ ሴት ማናት? ለምንስ ነው የማላውቃት ሴት መታወቂያ ላይ የእኔ ስም የሰፈፈረው? "ዶክተር እሷ ያለችበትን ሁኔታ ንገረኝ? ትድናለች አይደል? " እንድከተለው ምልክት ሰጥቶኝ ወደ ቢሮ ይዞኝ ሄደ። ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለመገመት አልተቸገርኩም። "ተጨማሪ ምርመራዎች አዝዣለሁ። ውጤቶቹ እስኪመጡ እርግጠኛ የሆነ ምላሽ ልሰጥሽ አልችልም። ጭንቅላቷ በሃይል ተጋጭቷል። እንዳልኩሽ ሁሉም ውጤት ሳይመጣ ብዙም ማለት አልችልም።" "የምትድን ይመስልሃል ግን? የምትነቃ ይመስልሃል?" "ይቅርታ ይሄን አሁን መናገር አልችልም።" "እሺ እኔ ምን ላድርግ? አላውቃትምኮ? ህፃኑንስ ምን ላድርገው? ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት?" "የማታውቂያት ከሆነ ሆስፒታሉ ለፖሊስ የማሳወቅ ግዴታ አለበት" አለኝ። አላውቃትም ያልኩትን ግን ያመነኝ አይመስልም። "እሺ የገጫትስ ሰውዬ?" "ቤተሰብ ቢገኝ ወይ በሽምግልና ያልቃል ወይ ይከሱታል። እንደምትዪው የማታውቂያት ከሆነ ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ ግዴታችን ነው። ሰውየው የማምለጥ ሀሳብ የለውም። ሲገጫት ማንም አላየውም ጥሎ መሄድ ይችል ነበር። ይልቅስ ያላነሰ ብር ከፍሎ የግል ሆስፒታል ሊያሳክማት ፈቃደኛ ከሆነ በህግ ይዳኝ በሽምግልና ቤተሰብ ነው የሚወስነው።" ሁሉንም ጥዬ መሄድ ፈለግኩ። ምን አገባኝ እና ነው እዚህ ጣጣ ውስጥ የምገባው ብዬ ..... ወደመጠበቂያው ክፍል ስመለስ ህፃኑ የምስራች የምነግረው ይመስል ከተቀመጠበት ዘሎ ተነስቶ በተስፋ አይን አይኖቼን ሲያየኝ እግሬ የሚቀጥለውን እርምጃ መራመድ አቃተው:: አጠገቤ ደርሶ ትንሽዬ ፊቱን ወደ ላይ አንጋጦ እያየኝ ሊያለቅስ ጉንጩ እየተንቀጠቀጠ "እማዬስ?" አለኝ:: እንባው ከፊደሎቹጋ ከአይኑ እየወረደ..... ከሱ ብሼ እንደህፃን ማልቀስ አማረኝ:: አቅፌ ብድግ እያደረግኩት በዛች ቅፅበት አብሬው እማገዳለሁ እንጂ እሳት ውስጥ ጥዬው እንደማልሄድ አወቅኩ። ... ይቀጥላል ........ እንዴት ናችሁልኝ ግን እናንተ? ❤️❤️❤️❤️

  • 20 июн. 2022 Đł.15,5 тыс8

    "እ? አዎ አይ እርግጠኛ ነኝ! ችግር የለውም!" አልኩኝ ደረቴን በርቅሳ ልትወጣ ይመስል የምትደልቅ ልቤን እንዳያዩብኝ ልብሴን እየነካካሁ። ምንም ባልናገርም ፊቱን ማየት እንደሞት እንዳስፈራኝ ከሁኔታዬ ገብቷቸዋል። አባትየው ለአንደኛው ፖሊስ ሲያስረዳ ሲጨቃጨቁ አጠገባቸው ሆኜ እንደእሩቅ ድምፅ ነው የሚሰማኝ። የማስበው ሳየው ምን እንደምለው ነው! ሊመልስልኝ የሚችለውን መልስ መላ እመታለሁ። ልጅ እኔጋኮ ልጅ አለህ ስለው ይደነግጥ ይሆን? ይፀፀት ይሆን? እና? ቢለኝስ? የሆነ ስም ጠርቶ እገሌ ይጠራልኝ ብሎ አባትየው ሲቀውጠው ፖሊሶቹ አልፈቅድ ብለው እንደሆነ ገባኝ። ከመምጣታችን በፊት አጣርቶ ነው ማለት ነው? ፍርሃቴ ከማየሉ የተነሳ እዚህ ድረስ ከመጣሁ በኋላ እንቢ ብለው ሳላገኘው ብመለስ ብዬ አስቤ ለቅፅበት ደስ እንደሚለኝ ተሰማኝ። ትልቁን ፍርሃቴን ተጋፍጬ ከእውነት ከመጋፈጥ መሸሽ!! የሰው ልጅ በብዙ እንደዛ አይደለ? ፍርሃቱን በመሸሽ ውስጥ ያለውን መንገድ ያውቀዋል። ቢወደውም ቢጠላውም ስለለመደው ይኖራል። ፍርሃቱን ሲጋፈጥ ከተራራው ጀርባ ያለውን ግን አያውቀውም። ሳያውቀው ይፈራዋል። አልለመደውማ! ስለዚህ ፍርሃቱን እሹሩሩ እያለ የለመደውን የተለመደ ህይወት ይኖራል። የተባለው ሰው ተጠርቶ ተጨባብጠው። ሁኔታውን በእርጋታ ከተረዳዱ በኋላ ተስማሙ። ሰውየው አሸናፊ እንዲጠራ ትእዛዝ ሲሰጥ መሮጥ ሁሉ አማረኝ። ብቻ እነግሩም ስለተንቀሳቀሱ እግሬን ወደፊት እየዘረጋሁ ዘለቅኩ። ተጠርቶ ሲመጣ የሚቆምበት ቦታ የሆነ ፖሊስ ነገር እየመራ ወስዶ ሲያደርሰኝ እነ ግሩም ወደኋላ ቀሩ ከጀርባው ለእኔ ከማይታየኝ ከሆነ ሰው ጋር እያወራ እየሳቀ ብቅ አለ። ሲያየኝ እንደመቆም አለ። ፊቱ ግን የገረመው አይመስልም ነበር። የሆነ ቀን እንደምመጣ የሚያውቅ ዓይነት መረጋጋት ነው ያለው። በረዥሙ ቢተነፍስ ትንፋሹ በሚሞቀኝ ዓይነት ርቀት ላይ ደርሶ ሲቆም ለምን ላገኘሁ እንደመጣሁ ፣ ምን ልጠይቀው እንደነበር ሀሳቤ ሁሉ ጭንቅላቴ ውስጥ ተደነባበረ። እልህ ፣እንባ ፣ላለመሸነፍ ትንቅንቅ ..... አፈነኝ። ወዲያው ደግሞ በራሴ ተበሳጨሁ። እንዴት ያለሁ ልፍስፍስ ነኝ ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ እንኳን የበደለኝን ሰው ሳየው ጎብዞ መታየት የሚከብደኝ? እኔ እስካወራ ድረስ ከንፈሩን አላላቀቀም። አይኖቹን እንኳን አልሰበራቸውም። ሳይነቅል ከማየቱ የተነሳ በአይኑ እየቦረቦረኝ ያለ ዓይነት ስሜት ሁላ ነው የተሰማኝ። ለደቂቃ ትንፋሼን ውጬ አይኖቼን አይኖቹ ውስጥ ዘፈዘፍኳቸው። አፌን ለቆ ሲወጣ የሰማሁት ዓረፍተ ነገር "አብረን በነበርንበት ጊዜ ወደኸኝ ታውቅ ነበር?" የሚል ነው። ይቀጥላል እንግዲህ......

  • 20 июн. 2022 Đł.14,8 тыс8

    አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው #2 "የገጨሃት ቦታ ውሰደኝ ምናልባት ሰፈሯ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ስልኳን እዛ ጥላው ሊሆን ይችላል። የሚያውቃት ሰው ሊኖር ይችላል!" በውስጤ ምናልባት ጎዳና ላይ ቢሆንስ የምትኖረው ብዬ አስቤያለሁ ጮክ ብዬ አላወራሁትም እንጂ ምናልባት ከነአካቴው ስልክም አልነበራት ይሆናል። መታወቂያዋ ላይ ያለውን ቀበሌና የቤት ቁጥር ተከትዬ ቀበሌ ሄጄ ቤቷን ፍለጋ አስቤዋለሁ። ቀላል እንደማይሆን ግልፅ ነው። ቀበሌ አልወድም!! "በፍፁም እኔ አልነዳም። ህም ...በጭራሽ መሪ አልይዝም። ታክሲ .....ራይድ ይጠራ" ሲል አሳዘነኝ ማንም ትኩረት ሰጥቶ እሱን ያየው የለም እንጂ እሱም ከባድ ድንጋጤ ላይ ነው። አሁንም እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ነው። ሲያወራ መሸሻ ያጣ አይነት ዓይኖቹ መሬቱን ይምሳሉ። ይሄን እያለኝ ድርብብ ያሉ የሴት ወይዘሮ የሚያነክስ እግራቸውን በጌጠኛ ከዘራ እያገዙ የሚራመዱ ሰውዬ አስከትለው ወደ ክፍሉ ገቡ። "ኪያዬ ......ደስ አላለኝም ! በለሊት አትጓዝ እያልኩህ ...." እያሉ እያገላበጡ ሲስሙት እና ደህና መሆኑን ሲያረጋግጡ ልጃቸው ተገጭቶ እንጂ እሱ ገጭቶ አይመስልም። እሱም እናቱን ሲያይ የሆነው የልጅ መሆን ካቀፍኩት ህፃን አይለይም ነበር። በኋላ እሱም ገብቶት ነው መሰለኝ ከእናቱ እቅፍ ወጥቶ በማፈር ሲያየኝ ነው ገና ሰው እንኳን መኖሩን እናትየው ያዩት። "እባክሽ ልጄ አንድ ልጄ ነው በሽምግልና እንጨርሰው? (ባጌጠ ልብሳቸው እግሬ ስር ሲንበረከኩ ክብራቸው አላሳሰባቸውም። እናት ናቸዋ! ደንግጬ ደነዘዝኩ። ካሰብኩት በላይ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደተዘፈቅኩ ገባኝ። ከተንበረከኩበት ላነሳቸው እየሞከርኩ ከአፌ ግን ቃል አይወጣልኝም።) ካሱ የምንባለውን እንክሳለን። እናትየው እስኪሻላት ህፃኑንም ቢሆን ወስጄ እንከባከባለሁ። እባክሽ ልጄን አሳልፈሽ አትስጪብኝ?" ለደቂቃ ህፃኑን ሰጥቻቸው ጭልጥ ብዬ መጥፋት ሁሉ አሰብኩ። ባባ ቀልቡ የነገረው ይመስል ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ። የተገጨችው እህቴ ብትሆን ምንድነበር የምወስነው? ብትሞት የእነሱ ካሳ የህይወት ካሳ ይሆናል? እሺ ጥፋቱ የሷስ ቢሆን? እንዳለው እሷ ብትሆንስ ዘው ብላ የገባችበት? ኸረ ምን አይነቷ ሴት ናት ግን እዚህ ጣጣ ውስጥ ዘፍቃኝ ማን እንደሆነች እንኳን የማላውቃት "እባኮትን ይነሱ። እኔ ለራሴ ዞሮብኛል።" የተፈጠረውን አስረዳኋቸው። አባትየው መታወቂያው ላይ ባለው አድራሻ ቤቱን ሊያፈላልጉ ሀላፊነት ወሰዱልኝ። ማን እንደሆነች እና ከእኔጋር የሚያዛምዳትን ነገር እስክደርስበት ባባ እኔጋ እንዲቆይ ወሰንኩ። እነርሱም የሚያስፈልገውን ሊያሟሉለት እና ሊጠይቁት ቃል ገቡልኝ። አንድ ላይ በእነርሱ መኪና እናትየው እየነዱ አደጋው የደረሰበት ቦታ ሄድን:: ምንም ነገር የለም። ከአልፎ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ ውጪ በአካባቢው ማንም አይታይም። የመኖሪያ ሰፈርም አይደለም። ዓይኔ መሬቱ ላይ ካለ አንድ ብር ሳንቲም ላይ አረፈ። ደም ነክቶታል። ለምን እንዳነሳሁት አላውቅም ግን አነሳሁት። የሷ ይሆን? በእጇ ይዛው ነበር? ወድቆባት ልታነሳ ስትል ይሆን መኪናውን ያላየችው? ወይስ ሌላ ሰው የጣለው ሳንቲም ነው? ስልኬ ሲጠራ ባላወቅኩት ምክንያት ደንግጬ ዘለልኩ "አይዞሽ አይዞሽ" አሉኝ እናትየው መደንበሬን ሲያዩ "እማ በጠዋት የት ሄደሽ ነው? " ልጄ ናት። ቤቴን ረስቼዋለሁ። ሰዓቱን ረስቼዋለሁ። ዛሬ ቅዳሜ መሆኑንም እረስቼዋለሁ። "መጣሁ እናቴ! ለባብሰሽ ጠብቂኝ" አልኳት ቅዳሜ ጠዋት ሁል ጊዜ እናትና አባቴ ጋር ነው ቁርስ የምንበላው። እነርሱ ስልክ ተቀያይረን እቤት አድርሰውኝ ተመለሱ። የማልዋሸው በዛው ቢጠፉስ ብዬ አስቤያለሁ። ሰው ለማመን ቅርብ አይደለሁም። የመኪና ታርጋቸውን መዝግቤ መታወቂያቸውን ፎቶ ኮፒ አደረግኩ። "እማ ትልቅ ሰው የሚበላውን ምግብ ይበላል ኸረ ጥርስኮ አለው" ትለኛለች ልጄ ለባባ ምግብ ምን ልስጠው ብዬ ስባዝን እየሳቀችብኝ። ልጄ 15 ዓመቷ ነው። በስንት ዓመቷ ምን እንደበላች ጠፍቶኛል። ለመጨረሻ ጊዜ ገላዋን መች እንዳጠብኳት ረስቼዋለሁ ..... ባባን አጣጥቤ እነእማዬጋ ተያይዘን ሄድን:: "እግዚአብሄር የሆነ ነገር ሊያስተምርሽ ነው ይሄን ህፃን ወደ ህይወትሽ ያመጣው" አለችኝ እናቴ የሆነውን ሁሉ ከነገርኳቸው በኋላ። ከቤተሰቡ አንድ ሰው እንኳን ድንገት ቢያውቃት ብዬ አስቤ ነበር:: ማንም አያውቃትም። (እናቴ ምን ማለቷ እንደሆነ አውቃለሁ። ማግባት አለብሽ ልጅ መድገም አለብሽ ነው ቅኔው። ወንድሜ በሚያስቀና ትዳር ሶስተኛ ልጁን ሰልሷል። የእኔ ያለባል መቅረት ያሳስባታል:: ) "እማ ደግሞ እግዚአብሄር እኔን ስለሚወደኝ እኔን ለማስተማር ይሄን ህፃን አይቀጣም! የሆነችን ሴት በመኪና አስገጭቶ ለኔ ትምህርት አይሰጥም። እነርሱምኮ ፍጡሮቹ ናቸው እኔን ለማስተማር ህይወታቸውን የሚያዘባርቅባቸው አሻንጉሊቶች አይደሉም!!" አልኳት። ወንድሜና አባቴ ተያይተው ጨዋታውን ቀየሩት። ከእማዬጋ እንዲህ አይነት ወሬ ከጀመርን ማባሪያ የሌለው ጭቅጭቅ እንደሆነ ያውቃሉ:: እዛው ቤተሰቦቼ ቤት ሆኜ ወደ ከሰዓት ስልኬ ጠራ ባባ ኩርምት ብሎ ከተኛ ሰዓታት አልፈውታል። "አብርሃም ነኝ" "አብረሃም? አብረሃም?" "የግሩም አባት! ልጅቷን የገጫት ልጅ አባት... " "እእ ....እሺ " "የምትኖርበትን ቤት አግኝተነዋል። አከራዮችዋን አናግረን የእሷ ቤት መሆኑን አረጋግጠናል።" "በዚህ ፍጥነት? እንዴት? ያውም በቅዳሜ?" "ብዙም አስቸጋሪ አልነበረም:: የቤት ቁጥሩ የአከራዮችዋ ቤት ነው:: ደግሞስ የልጄ ጉዳይ አይደል? ይልቅ መምጣት ሳይኖርብሽ አይቀርም። ከባሏ ውጪ ማንም ዘመድም ሆነ የቅርብ ሰው እንደሌላት ነው የነገሩን።" "ታዲያ ባሏ እያለ እኔን ምን ቤት ናት ብላ ነው የፃፈችኝ?" "ባሏ ከታሰረ ሁለት ዓመት አልፎታል።" "እሺ እኔ ምን ቤት ነኝ መታወቂያዋ ላይ የተገኘሁት? ወይ ፈጣሪ ! " "እኔ ምን አውቄው ብለሽ? (እኔ አልፃፍኩሽ የሚል አንድምታ ባለው ለዛ) ምናልባት በባለቤትዋ? እስር ቤት ያለ የቅርብ ሰው ወይ ዘመድ የለሽም?" "በፍፁም ኸረ እኔ ጭራሽ የታሰረ የሩቅም ሰው አላውቅም። " "ምናልባት አከራዮችዋ ከሚነግሩሽ ነገር ፍንጭ ልታገኚ ስለምትችዪ ብትመጪ መልካም ይመስለኛል:: ብዙ አመት ኖራለች አብራቸው.... እ.... ባለቤቷ ... አሸናፊ ይባላል ነው ያሉኝ .......እንደው ካወቅሽው " ከጀርባዬ የሆነ ነገር ማጅራቴን በሀይል የደለቀኝ ነገር መሰለኝ .........ጭው አለብኝ። አይሆንም። እሱማ አይሆንም! ሊሆን አይችልም።... ስም ተመሳስሎ ነው.... ማሰብ ተሳነኝ!! "ምነው ሴትየዋ ሞተች እንዴ?" ትለኛለች የወንድሜ ሚስት ...... ይቀጥላላ ምን ታፐጣላችሁ??? 🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️

  • 20 июн. 2022 Đł.13,2 тыс14

    አታምጣው ስለው .... አምጥቶ ቆለለው #1(ርዕስ ነው) የስልኬ ጥሪ ነው ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ። ከንጋቱ 12:10 "ከሆስፒታል ነው የምንደውለው!! ዶክተር ፈቃደ እባላለሁ።" "በየሱስም! እናቴ ምን ሆነች?" ብድግ ብዬ ቁጭ አልኩ:: ማታ ስኳሬ ከፍ ብሏል ስትለኝ ነበር። "ወይዘሮ ሄለን አበራ አደጋ ገጥሟቸው ...." "ሄለን አበራ? በስመአብ! (ልቤ ጉሮሮዬጋ ደርሳ ነበር ምልስ ብላ አቃፊዋ ውስጥ ስትገባ ታወቀኝ) ምነው እያጣራችሁ ብትደውሉ? በዚህ ጠዋት ያልታመምኩትን ሴትዮ በድንጋጤ ልትገሉኝ ነው እንዴ? ተሳስታችኋል!! እኔ ሄለን አበራ የምትባል ሴት አላውቅም! " "ወይዘሮ ፌቨን አዳነ አይደሉም?" "ነኝ!" አሁን ግራ ገባኝ። ስልኬን ቢሳሳት ስሜን ግን አስተካክሎ ሊጠራ አይችልም። "የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ተብለው የተመዘገቡት እርሶ ኖት!" ከአልጋዬ በደመነፍስ ወረድኩ "እህ እኔ እንዲህ የምትባል ሴት አላውቅማ? ቆይ የሆነውን አስረዳኝ ምን አይነት ሴት ናት? ምን አይነት አደጋ ነው የገጠማት?" "የመኪና አደጋ ነው። ለጊዜው conscious አይደለችም:: ቦርሳዋ ውስጥ ባገኘነው መታወቂያ ላይ የእርሶን ስልክና ስም ነው ያገኘነው።" "እሺ መጣሁ!" አልኩኝ ነገሩ ምንም ስሜት ሳይሰጠኝ ..... አደጋ ደርሶ ነው እየተባልኩ ከዛ በላይ ጥያቄ ማብዛት ክፋት ነገር መሰለኝ። የእኔን ስም የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ብሎ ሊመዘግብ የሚችል ዘመድ አሰብኩ ........ ምናልባት በቤት ስሟ የማውቃት ዘመድ ..... ጭንቅላቴ እዚህም እዛም እየረገጠ የተባልኩት ሆስፒታል ደረስኩ እና የተባለውን ዶክተር አገኘሁት። የተባለችው ሴት የተኛችበት ክፍል ወሰደኝ። ሰውነቷ በአብዛኛው በፋሻ ስለተጠቀለለ የማውቃት ሴት እንኳን ብትሆን መለየት አልችልም ነበር። "የማውቃት አይመስለኝም!" አልኩት ግራ ገባቶኝ። ከጋውን ኪሱ መታወቂያዋን አውጥቶ ሰጠኝ። ሲገለባበጥ ሌላ ምስል ያሳየኝ ይመስል እያገለባበጥኩ አየሁት። በፍፁም አላውቃትም! ስሜና ስልክ ቁጥሬ ግን የመታወቂያው ጀርባ ላይ ቁልጭ ብሎ ተፅፏል። እድሜ 30 .... ቆንጅዬ ወጣት ናት። ፎቶዋ ላይ ጥርሷን ሳትገልጥ ፈገግ ብላለች። በወፋፍረሙ ተገምዶ ደረቷ ላይ የተዘናፈለ ፀጉር አላት ..... በፍፁም አይቻት አላውቅም። "ማነው ሆስፒታል ያመጣት?" አልኩኝ ትክክለኛ ጥያቄ ይሁን ሳልረዳ "አደጋ ያደረሰባት ሰው ነው ይዟት የመጣው። መጠበቂያ ክፍል ተቀምጧል ልታገኚው ከፈለግሽ? " ብሎ መልሴን ሳይጠብቅ በሩን ከፍቶ ወጣ ተከተልኩት የተባለው ሰው ከዶክተሩ ጋር ወደክፍሉ ስገባ ሲያየኝ ዘሎ ከመቀመጫው ተነሳ ..... አጠገቡ ተቀምጦ የነበረ በግምት የ4 ዓመት የሚሆን ህፃንም ተከትሎት ብድግ አለ። "ቤተሰቧ ነሽ? ምን ማድረግ እንደነበረብኝ አላወቅኩም ነበር! እጄን ለፖሊስ ልስጥ? እሰጣለሁ በቃ! (መላ አካሉ ይንቀጠቀጣል።) ከየት መጣች ሳልላት ነው ዘው ብላ የገባችብኝ በቦታው የነበረ ሰውም አልነበረም። አልነጋምኮ .... የሞተች መስሎኝ ነበር !" ድንጋጤው እንዳለ ነው የለበሰው ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ በደም እንደተነከረ ነው። እጆቹ ላይ የቀረውን የደረቀ ደም ሊጠርገው ግድ ያለው አይመስልም ወይም ከነጭራሹ ደም እጁ ላይ መኖሩንም አላስተዋለውም። ግራ ገባኝ። ምንም በማላውቀው ክስተት ውስጥ የተነከርኩት እኔ ምን ልበል? አይኖቼ ህፃኑ ላይ መንቀዋለላቸውን ሲያይ "ልጇ ነው። አብረው ነበሩ። እማ ብሎ ሲጮህ ነው ያየሁት እኔ እንጃ ምን እንደተፈጠረ። እሱ የእግረኛ መንገድ ላይ ነበረ። ቤተክርስቲያን እየሄዱ መሰለኝ ነጠላ ለብሳ ነበር። .... ቤተክርስትያን ለመሄድ ራሱ በቅጡ አልነጋም ነበር:: " ምን እንደማደርግ ሳላውቅ ህፃኑጋ ተጠግቼ በርከክ አልኩ። ደነበረ። ትንንሽ እጆቹን ልይዛቸው እጄን ስዘረጋ ሰበሰባቸው። "ስምህ ማነው?" አልኩት እናቱን መኪና ሲገጫት በአይኑ ካየ ሁለት ሰዓት ላልሞላው ህፃን የእኔ ጥያቄ ምኑ ነው? እኔስ ምኑ ነኝ? ዓለምስ ራሱ ምኑ ናት? "ባባ" አለኝ የደረቁ ከንፈሮቹን እያላቀቀ "ባባዬ እኔን ታውቀኛለህ?" አልኩት የማይጠየቅ ጥያቄ እንደሆነ እያወቅኩ። በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ። "አባትህ የት እንደሆነ ታውቃለህ?" አሁንም በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ። ግራ ገባኝ! ይህቺ ሴት ማናት? ለምንስ ነው የማላውቃት ሴት መታወቂያ ላይ የእኔ ስም የሰፈፈረው? "ዶክተር እሷ ያለችበትን ሁኔታ ንገረኝ? ትድናለች አይደል? " እንድከተለው ምልክት ሰጥቶኝ ወደ ቢሮ ይዞኝ ሄደ። ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለመገመት አልተቸገርኩም። "ተጨማሪ ምርመራዎች አዝዣለሁ። ውጤቶቹ እስኪመጡ እርግጠኛ የሆነ ምላሽ ልሰጥሽ አልችልም። ጭንቅላቷ በሃይል ተጋጭቷል። እንዳልኩሽ ሁሉም ውጤት ሳይመጣ ብዙም ማለት አልችልም።" "የምትድን ይመስልሃል ግን? የምትነቃ ይመስልሃል?" "ይቅርታ ይሄን አሁን መናገር አልችልም።" "እሺ እኔ ምን ላድርግ? አላውቃትምኮ? ህፃኑንስ ምን ላድርገው? ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት?" "የማታውቂያት ከሆነ ሆስፒታሉ ለፖሊስ የማሳወቅ ግዴታ አለበት" አለኝ። አላውቃትም ያልኩትን ግን ያመነኝ አይመስልም። "እሺ የገጫትስ ሰውዬ?" "ቤተሰብ ቢገኝ ወይ በሽምግልና ያልቃል ወይ ይከሱታል። እንደምትዪው የማታውቂያት ከሆነ ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ ግዴታችን ነው። ሰውየው የማምለጥ ሀሳብ የለውም። ሲገጫት ማንም አላየውም ጥሎ መሄድ ይችል ነበር። ይልቅስ ያላነሰ ብር ከፍሎ የግል ሆስፒታል ሊያሳክማት ፈቃደኛ ከሆነ በህግ ይዳኝ በሽምግልና ቤተሰብ ነው የሚወስነው።" ሁሉንም ጥዬ መሄድ ፈለግኩ። ምን አገባኝ እና ነው እዚህ ጣጣ ውስጥ የምገባው ብዬ ..... ወደመጠበቂያው ክፍል ስመለስ ህፃኑ የምስራች የምነግረው ይመስል ከተቀመጠበት ዘሎ ተነስቶ በተስፋ አይን አይኖቼን ሲያየኝ እግሬ የሚቀጥለውን እርምጃ መራመድ አቃተው:: አጠገቤ ደርሶ ትንሽዬ ፊቱን ወደ ላይ አንጋጦ እያየኝ ሊያለቅስ ጉንጩ እየተንቀጠቀጠ "እማዬስ?" አለኝ:: እንባው ከፊደሎቹጋ ከአይኑ እየወረደ..... ከሱ ብሼ እንደህፃን ማልቀስ አማረኝ:: አቅፌ ብድግ እያደረግኩት በዛች ቅፅበት አብሬው እማገዳለሁ እንጂ እሳት ውስጥ ጥዬው እንደማልሄድ አወቅኩ። ... ይቀጥላል ........ እንዴት ናችሁልኝ ግን እናንተ? ❤️❤️❤️❤️

  • 20 июн. 2022 Đł.12,3 тыс42

    ነፍስ ይማር ስለ'ኔ ስላንቺ ካህናት በወረብ ፣ ሼሆች በመንዙማ ባርምሞም በጩኸት፤ ይቀኛሉ ቅኔ ፣ ይዜማሉ ዜማ ቅዱስ ለፍቅራችን ቅዱስ ለጠባችን ቅዱስ ለፍጻሜው በ'ንባሽ ታንቆ ፍቅር ፣ ላለቀበት እድሜው ስብሃት ሶስቴ ላንቺ ፣ ስብሃት ደግሞ ለ'ኔ ለደከመው አካል ፣ ለደቀቀው ጎኔ ፍትሃት ለዛ ፍቅር ፣ ፍትሃት ለዛ ተስፋ በኩርፊያሽ ተዳፍኖ ፣ በእምባሽ ለጠፋ ወዩ ለትግስትሽ ፣ ሞቷል መጠበቄ ነፍስ ይማር ለሳቅሽ ፣ ነፍስ ይማር ለሳቄ [ቶማስ ትግስቱ]

  • 20 июн. 2022 Đł.11,9 тыс10

    ስህተት ልክነት ልክነት ስህተት የእኔ ‘የልክነት ጥግ‘ ነው ብዬ ያመንኩበት ‘እውነት‘ ለወዳጄም ‘እውነቱ‘ መሆን አለበት ብዬ ወዳጄን በተሳሳች ሂሳብ መዳኘት ከቂልነቴ ባሻግር የጠበበ የሀሳብ ምህዳሬን ገልቦ አደባባይ ማስጣት ይመስለኛል። ወዳጄ የቆመበትን ጫማ ‘ስህተት‘ ብዬ ለመዳኘት ለመሆኑ የእኔ ‘ልክ‘ በየትኛው ሚዛንና በማን ዳኝነት ተሰፍሮ ነው ልክነቱ የተረጋገጠው? አይደለም ለሌላ ሰው ለራሴ እንኳን ‘ልክ ነው‘ ያልኩትን እምነቴን ጊዜ አላንጓለለብኝም? የዛሬ ምናምን ዓመት በፊት የእውነትና የእምነት ጫፍ የመሰለኝ ዛሬ አልተቀየረም? በጠበበም ወይ በሰፋ አስተሳሰቤ 'ልክነቴ'ን አልቀየርኩም? እንዴት ነው በጊዜ፣ በመረዳቴ መጠን፣ በቦታና በበሽቃጣ የህይወት ክስተቶች እንደማይቀየር ዋስትና በሌለኝ ‘ልክነቴ‘ ወዳጄን በስህተት የምዳኘው? ሊቀያየር ቢችልም እንደብዙዎች የራሴ አቋምና እምነት አለኝ። እንደራሴ ‘ልክ‘ እና ‘ስህተት‘ የምላቸው ሁነቶች አሉኝ። …… የኔ ‘ስህተት‘ ውስጥ ተዘፍቀህ ሳገኝህ… … ልልህ የሚገባው ‘ይመስለኛል‘ ብቻ መሰለኝ። ምክንያቱ ደግሞ የእኔ ልክ የልክ ጣሪያ ሊሆን አይችልም። የሆነ ቦታ……የሆነ ጊዜ… … ለሆነ ሰው ስህተቱ ሊሆን ይችላል።…… እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። …… ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው። …… ቀኝ ይሄ ነው…… ግራ ይሄ ነው… … ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ። …… እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል። …… እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል። …… ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ።…… የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ። ……… በየራሳችን እውነትና እምነት መከባበርና እና መዋደድ በአብሮነት ብዙ ያስጉዘናል። እየሆነ ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝ❤️❤️❤️❤️❤️

  • 1 июн. 2022 Đł.11,9 тыс15

    አንዴ ጓደኛዬ ራሴን አጠፋለሁ ብሎ ተነሳ፡፡ ሁሉም ይመክረው ጀመር፡፡ ግን እሱ አሻፈረኝ አለ - ራሴን አጠፋለሁ አለ፡፡ ቤተሰቦቹ ጨነቃቸው፡፡ አባቱ እየሮጡ መጡና፣ “ይሄን ልጅ አልቻልነውም፤ ከእኛ አቅም በላይ ሆኗል…” አሉኝ፡፡ አባቱ አይወዱኝም ነበር አሁን ግን “ያለው ብቸኛ አማራጭ ይሄ ነው” ብለው አስበዋል…“ችግር የለውም እመጣለሁ” አልኳቸው፡፡ ቤታቸው ሄጄ ነገሩን ከሰማሁ በኋላ “ይሄውልህ…” አልኩት፣ “ሐሳብህ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ትክክል ነው ብዬ አላስብም፡፡ ቢሆንም ግን ራሴን አጠፋለሁ ብለህ ከተነሳህ መቼስ ምን ማድረግ እችላለሁ፡፡ ጓደኛዬ ስለሆንክ ረዳሃለሁ፡፡ ራሴን ካላጠፋሁ ካልክ - ጥሩ!! ውሳኔህ ትክክል አይመስለኝም ምክንያቱም እኔ ባንተ ቦታ ብሆን ጨርሶ ራሴን አላጠፋም ነበር፡፡ ምክንያቱም ሞኝነት ነዋ፡፡ አንዲት ሴት እምቢ ስላለችህ ራስህን ታጠፋለህ? በሚሊየን የሚቆጠሩ ሴቶች እያሉ አንዲት ሴት እምቢ አለችኝ ብለህ ራስህን ማጥፋት ተገቢ ውሳኔ አይደለም፡፡ በወር ውስጥ ረስተሃት ሌላ ማፍቀርህ አይቀርም ነበር፡፡ ግን ራሴን አጠፋለሁ ካልክ ምን ማድረግ ይቻላል …ጥሩ!! የራስህ ሕይወት የራስህ ነው…” አባትዬው ይህን ሲሰሙ በጣም ተረበሹ፡፡ “ጭራሽ ራስህን አጥፋ ትለዋለዋህ እንዴ… እኛ እኮ ያመጣንህ ይሄን ሐሳቡን ታስተወዋለህ ብለን ነው” አሉ አባትዬው፡፡ “እኛ ምን ስለሆንን ነው የምንረዳው?እርስዎ ሲወልዱት ጠይቀውታል እንዴ… ወደዚህች ምድር መምጣት ትፈልጋለህ ወይ ብለው ጠይቀውት ነበር? እና አሁን ለምንድነው ራሴን ላጥፋ ሲል የምትከለክሉት? ራሴን ላጥፋ ካለ ፍቀዱለት” ወደ ቤቴ ይዤው ሄድኩ…“ና እንሂድ… ራስህን ልታጠፋ አይደለ እስኪ እስከዛው ዘና እንበል እንዝናና፡፡ እስቲ አንድ ለሊት አብረን አናሳልፍ፡፡ እኔጋ እደር፡፡ ምናልባት የሆነ ቦታ እንገናኝ ይሆናል ምናልባትም ከዚህ በኋላ መቼም ላንገናኝ እንችላለን” አልኩት፡፡ እኔ ቤት ሆነን ቀስ በቀስ ማሰብ ጀመረ፡፡ ምክንያቱም እኔ በምንም መልኩ ሀሳቡን ለማስቀየር አልፈለግኩም፡፡ “አሁን የሚጮህ ሰዓት እንሙላና እንተኛ…” አልኩት፣ “ሌሊት 10 ሰዓት ሲሆን ተነስተን አንድ የሚያምር ቦታ እወስድሃለሁ፡፡ በጣም የሚያምር ቦታ ነው፡፡ ከዚያ ቦታ ላይ በቀላሉ ዘልለህ ወንዙ ውስጥ መፈጥፈጥ ትችላለህ። ከእኔም ጋር እዛው እንሰነባበታለን” ልክ 10 ሰዓት ላይ ሰዓቱ ሲጮህ ከአልጋው ጎትቼ ሳስነሳው፣ “አንተ ቆይ ምን አረግኩህ…” አለ ጮሆ፤ “ጠላቴ ነህ ወይስ ምንድነው? በቃ ራሴን ማጥፋት አልፈልግም!! “ይሄማ ትክክል አይደለም… አንዴ ወስነህ የለ እንዴ… የምን መወላወል ነው” “እንዴ በቃ ራሴን አላጠፋም!!እንድሞት ፈልገህ ነው። አልሞትም… በቃ… አልፈልግም ራሴን አላጠፋም… ሕይወቴን እወዳታለሁ” “እምቢ ካልክ አላስገድድህም” አልኩት… እናም ራሱን አላጠፋም!!! አሁን አግብቶ ልጆች ወልዷል፡፡ መንገድ ላይ ካየኝ መንገድ አሳብሮ ነው የሚጠፋው፡፡ “አሁን ምን ተገኘና ነው” እለዋለሁ መንገድ ላይ ሳገኘው፣ “መቼም አላፈቅርም ብለኸኝ አልነበረም እንዴ… እንደገና አፍቅረህ አረፍከው!!!” እሱም እንዲህ ይለኛል፣ “በዕውነቱ እንኳንም ያቺ ልጅ እምቢ አለችኝ፡፡ ለእኔ አትሆነኝም ነበር ታሳብደኝ ነበር፡፡ እኔ አሁን የተሻለች ልጅ ነው ያገባሁት ። (ኦሾ) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @yefkrinegri ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @yenhiwet

  • 18 мая 2022 Đł.11,5 тыс86

    መለየት ( በእውቀቱ ስዩም ) የለም ! የለም ! መለየት ሞት አይደለም ሞትም መለየት አያክለው መለየትም ሞትን አይመስለው ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው አንቺም እኔም ጅረት ኾነን ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን በራሳችን ፈለግ ፈስሰን አገር ምድሩን አድርሰን ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ሞት በሚሉት ውቅያኖስ አንድ ስንኾን ተዋሕደን ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን የለም ! የለም ! መራቅ መለየት አይደለም ሰው በሰዎች ግዞት ችግር መከራ ይዞት አገር ቀዬውን ጥሎ ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው ከተጓዘ አኑሮ ሰው አሁን ይኼ መለየት ነው ? የለም የለም ! መለየት ይህ አይደለም ትርጓሜያቸው እንቀይረው ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው ከፊቴ ቁጭ ብለሽ ከፊትሽ ቁጭ ብዬ ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ የምታወሪው ሳይገባኝ የማወራሽ ሳይገባሽ ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @yefkrinegri ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @yenhiwet ❥❥__⚘_❥❥

  • 12 мая 2022 Đł.17,9 тыс3

    ፅናት ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ( የሸዋ ልጅ) ክፍል 10 . . . ፨ ሹፌሩ በጣም ተደናግጦ የሚያረገው ጠፋው መንደሩን ዞር ዞር ብሎ አየው በሰአቱ ሰው አደለም ነብስ ያለው ፍጥረትም አልታየውም ከዛም ፅናትን በጥድፊያ ያ በጣም የሚስፈራት ድባብን የተላበሰ ጊቢ ተሸክሞ ይዟት ገባ። ሊባኖስ ከእሩቅ አይታው በፍጥነት ሮጣ ወደ ሹፌሩ በመምጣት ተባብረው አንድ አነስ ያለች የጭቃ ቤት ውስጥ አስገቧት ቤቷ ስትታይ ልትወድቅ ያሰፈሰፈች ትመስላለች በፈጥነት አንድ የሽቦ አልጋ ላይ አስተኑዋት። ፨ በክፍሉ ውስጥ ፅናት ከተኛችበት ትይዩ ካለው ግድግዳ አጠገብ አንድ ተጨማሪ የሽቦ አልጋ ይታያል። በእዚህ አልጋ ላይም በፀሎትን በደረቷ አስተኝተው የጭንቅላቷን ደም ለማስቆም እየጣሩ ያሉ አንድ የእድሜ ባለ ፀጋ ይታያሉ። እኒ ሰው ፀጉራቸው ሙሉ ሽበት ሲሆን ልክ እንደ ባህታዊ ፀጉረ ተቆጣጥሮ ወገባቸው ላይ የተንዠረገገ ነው ። ጥቁረ መነፀረ እና የመነቸከ ነጭ ባረኒጣ አረገዋል። ልብሳቸውም እንደነገሩ ነው ልክ እንደ ኮፍያቸው ነጭ ሆኖ ነገረ ግን የመነቸከ ሰፋፊ ሹራብ እና ሱሪ አድረገዋል። በጣም አጭረ ቁመት እና ቀይ መልክን ተላብሰዋል። ፨ የትግስትን የጭንቅላት ደምን በያዙት መጣጭ ጨረቅ ላይ የሆነ ፈሳሽ ውሀ መስል ነገረ እያረጉ ካፀዱ በኋላ ደሙ ሲቆም አንድ አረጓዴ የተጨቀጨቀ ነገረ ከብልቃጥ አውጥተው የበፀሎት የተጎዳ ጭንቅት ላይ በዳበሳ አረገው ቀቡትና በፋሻ ጠቀለሉት። ከዛም ከእሳቸው የማይጠበቅ ጉልበት እና ቅልጥፋና ተጠቅመው በፀሎትን በእፍታ ፍጥነት በጀረባዋ አስተኙዋት።እኒ ሰው አንድ ሰው እያከሙ ሳሉ የሚያወራቸን ሰው አጥብቀው የሚጠሉ ናቸው። ፨ ልክ በፀሎትን አክመው እንደጨረሱ ሊባኖስ "አባ በሬሳ የእሷ እህትም ተጓድታለች እራስዋን ስታ ነው" አለች። ሊባኖስ ፅናት ፅናትን እያየች ምን ሆና? ለምን እንዲ ሆነች? ብለውም ሳይጠይቁ ወዲያው ከዛች ጭቃ ቤት ወጡ።ሊባኖስ ፈገግ አለች። አባ በሬሳም አፍታ ሳይቆዩ የፈላ ውሀ እየተግለበለበ ይዘው መጡ። የፈላ ውሀውን ከመሬቱ ላይ ካስቀመጡ በኋላ በኪሳቸው የያዙትን በፌስታል የተቋጠረ ቢጫ ዱቄት ሊያረጉ እየፈቱ ሳለ ሊባኖስ ክፍሉን ለቃ ወጣች እና በሩን ዘጋችው ። ፨አባ በሬሳ ስራቸውን ቀጠሉ። የፈላው ውሀ ላይ ቢጫ ዱቄቱን ሲጨምሩት ውሀው ይበልጥ መፈላት ጀመረ።ከዛም ቤቱ በእንፋሎት መታጠን ሲጀምረ እሳቸውም ያቺን የጭቃ ቤት ለቀው ወጡ። ፅናት እና በፀሎትም በጭቃ ቤቷ ውስጥ የሚሸታቸው ጠረን ሰአታት አስቆጥሮ በእኩል ሰአት አስነቃቸው። ሲነቁ ደና ሆነው ነበረ። ፅናት ብድግ ብላ ወደ በፀሎት ሄደች።በፀሎት ግራ ገብቶት "ፅናቴ የት ነው ያስተኛሽኝ ፍራሻችን ዛሬ ደሞ ትንሽ ምቾት አለው። ደሞ ምንድነው የሚሸተኝ" አለቻት። ፅናት ግራ ተጋባች። ፨ በአይኑዋ የቤቱን ዙሪያ ቃኘችው። የቆመችበት መሬት ያለችበት ቤት የት እንደሆነ አታውቅም ፈጠን ብላ ወደ በሩ ሆደች። በሩ ከውጪ ተቀረቅሯል። ግራ ገባት። ወደ እህቷ ሄዳ። እጇን ያዘቻት ፍረሀት ሰውነቷን በሀያሉ ወረራት። ፅናት ቤቱ ውስጥ ከ ሁለቱ አልጋዎች እና ተንጋላ ከተኛችው በፀሎት እንዲሁም ከእራሷ ውጪ ምንም ሊታያት አልቻለም ።ፈራች በፈጥነት በፀሎት የተኛችበት አልጋ ላይ ወጥታ አቀፈቻት። አሁን በፀሎት በተራዋ ግራ ገባት። ልክ የፅናት ግራ መጋባት ወደ ፍራቻ ሲዞረ። ፨ በፀሎት ፅናትን በዳበሳ እየነካካቻት "ፅናቴ ምነው ዝም አልሽ" አለቻት። ፅናት በፀሎትን በደንብ እቅፋ እያረገቻት "በፀሎቴ ፈራው" አለቻት በፀሎት በአሁንም ግራ ገብቷት "እንዴ ለምን አለቻት" ፅናት አሁን በፀሎትን ይበልጥ እያቀፈቻት። "ቤታችን አደለንም" ስትላት። በፀሎት ፈገግ ግረም እያለች "እና የት ነን" ስትላት። አላውቅም ብላ ሊባኖስ ቤታቸው ከመጣች ጀምሮ ያለውን ሁሉ እስከምታስታውሰው እራሷን የሳተችበት ቅፅበት ነገረቻት አሁን በፀሎትም በጣም ፈራች። እረብሽብሽ አለች። ፨ተቃቅፈው በጭንቀት ሳሉ ያሉበት ክፍል በሩ ቡዋዋዋ ብሎ ተከፈተ ፅናት ብረግግ ብላ ተነሳችና ቁጭ አለች። በፀሎት የፅናትን እጅ አጥብቃ ያዘቻት።ፅናት አይኖቿን ወደ በሩ ወረውራ አየች። አባ በሬሳ ነበሩ ወደ እነ ፅናት ጠጋ ማለት ሲጀምሩ የፅናት ልብ ምት ፈጠነ። ጠጋ አሉ ፅናት ፈራች። አባ በሬሳ "ተነሽ" አሉዋት ፅናትን።ፅናት በድንጋጤ በረግጋ ከበፀሎት እጇን አላቃ ከአልጋው ወረዳ ቀጥ ብላ ቆመች። ፨ አባ በሬሳ ወደ በፀሎት በመሄድ የበፀሎትን ሁለት እጆች በመያዝ "ተነሽ" አሉዋት ቁጣ በተሞላበት ድምፀት በፀሎት ብድግ አለች። ፅናት ግራ ገባት ከሰአታት በፊት ከጭንቅላቷ ደም በሀያሉ እየፈሰሳት እራሷን እማታውቀው እህቷ ምንም እንዳልተፈጠረ ብድግ ብላ መነሳቷ። ፅናት የሚሆነውን በአትኩሮት ማየት ጀመረች። አባ በሬሳ በፀሎትን አልጋው ላይ ቁጭ ካረጉዋት በኋላ በሁለቱ እጃቸው ጉንጭ እና ጉንጮን ይዘው በሀይል ካወዛወዙዋት በኋላ ልቅቅ ሲያረጉዋት በፀሎት ወደ ኋላ ወደቀች። ፅናት ጩከቷን አቀለጠችው። ፨ የሚመጣ ሰው ግን አልነበረም አባ በሬሳ "ዝም ብለሽ ተቀመጭ" አሉዋት። ፅናት መሬቱ ላይ ተቀምጣ የሚሆነውን ማየት ጀመረች። ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ በፀሎት "ፅናቴ እህቴ" ስትላት ሰማች። ፅናት ፈጠን ብላ ወደ እህቷ አመራች ጋሽ በሬሳም በግረምት በተራቸው ቆመው ሁኔታውን ማየት ጀመሩ። በፀሎት ያለ ማንም ድጋፈ ተነስታ ቁጭ አለች። ፅናት ህልም ላይ ያለችም መሰላት ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ባይገባትም እህቷ ስለተሻላት ግን ተደስታለች። ተቃቅፈው አለቀሱ ረዥም ደቂቃዎች አነቡ። ፨ ጋሸ በሬሳ እረጅና ባንቀጠቀጠው ድምፃቸው "በቃ ተላቀቁ" አሉና አላቀቋቸው። ጋሽ በሬሳ በፀሎት ጭንቅላት ላይ ያለውን ፋሻ አነሱላት። ከዛ በቃ "ከእዚህ በኋላ ህመም የለም ህክምናሽን ጨረሰሻል። አሁን ስለመሸ ተኙ ነገ ጠዋት ቤታቹ ትሄዳለቹ። ልጅ ሊባኖስ የምትመገቡትን ይዛላቹ ትመጣለች" አሉና ወደ ፅናት ዞር ብለው ልጄ እህትሽን እንድትንቀሳቀስ እረጃት ሲሉ ፅናት "ግን እኮ እህቴ መሄድ አትችልም በዊልቸረ ነው የምትንቀሳቀሰው" አለች ። አባ በሬሳ አውቃለው አውቃለው ልጅ ሊባኖስ ነግራኛለች ግን ሰው በእግሩ ብቻ ሳይሆን በአይምሮም መጓዝ እና መንቀሳቀስ ይችላል አዝናኛት በወሬ ለማት ነው" ብለው ወጡ። ፨ ፅናት በፍጥነት በሩን ከውስጥ ሸንጉራ በፀሎት ጋረ በመጠጋት የበፀሎትን ፓንክ ቁረጥ ፀጉር እና ጭንቅላቷን ዳበሰችው ምንም የለም ለምልክትም የተቀነጠ አንዳች ጠባሳም የለም። ፅናት ግራ ገባት። "በፀሎቴ ጭንቅላትሽ ላይ ምንም አይነት የቁስል ወይም የጠባሳ ምልክት የለም እሺ ጠባሳው ቆይቶ ነው ሚመጣው ግን ቁስሉስ" አለች።በፀሎትም "እንዴት ሆኖ ቆይ የት ነን?" ስትልላት።"አላውቅም ሽማግሌው እኮ እህትሽ እንድትቀሳቀስ እረጃት ሲሉኝ መቼም በአንድ ጊዜ እንዲ ጤነኛ ካረጉሽ መራመድም እንድትችይ ያረጉሽ መስሎኝ በጣም ልቤ በደስታ እየመታ ነበር"አለች እንዲ እያወሩ በሩ ተንኳኳ ፅናት ማነው አለች። መልስ የለም ግን የሆነ የሚያስጨንቅ እንጉረጉሮ ይሰማታል ሁለቱም ፋረሀት ወረራቸው። ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @yenhiwet ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @yefkrinegri ❥❥__⚘_❥❥

  • 28 апр. 2022 Đł.16,7 тыс59

    ጥቂት ነው ምኞቴ እኔ በህይወቴ ጥቂት ነው ምኞቴ ከድፍና ከግፍ የጠዳ ፡ በረንዳ እዚያ ላይ መቆየት ፥ ከሚደምን ዛፍ ላይ ፥ ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤ አኔ በህይወቴ ጢኖ ነው ምኞቴ ለከርስ ጤፍ እንጀራ ለነፍስ ባለንጀራ ድክመቴን ስናዘዝ ፥ተግቶ ሚያዳምጠኝ በደሌን መዝኖ ፥ ቀኖና እማይሰጠኝ፤ እኔ በህይወቴ ጥቂት ነው ምኞቴ ሊሞላ የቃጣው፥ ደርበብ ያለ ኑሮ በስዊዝ ቤተ-ንዋይ፥ ሶስት መቶ ሺህ ዩሮ ደሞ ከተቻለ፥ ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ እግዜርና ሰይጣን ፥ተጋግዘው የሳሏት ቢቻል ትንሽ ቪላ ፥አስር ክፍሎች ያሏት ግና ምኞቴ ሆይ ፥ እንዲያው ለመሆኑ ጥቂት ብሎ ነገር ፥ስንት ነው መጠኑ?

  • 😘ፅናት😘 ✍ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) 🔥ክፍል 9 . . . ፨ ማን ያንሳቸው በወደቁበት ቦታ ሰአታት ተቆጠሩ ከወደቁ ከ 3 ሰአት በኋላ ፅናት ነቃች። አይኗን ጨፈገጋት እንደምንም ተነሳች ደረቷ ላይ የበፀሎት እጅ አለ። ድንጋጤው እብደትን ደምሮባት ባነነች። በፀሎት ወድቃለች ፅናት ብድግ አለች እጇን በአፏ ጭና ቀረች። የምታደረገው ሁሉ ግራ ገባት ብቻ ግን አይኖቿ እንባ አቅረርዋል። ተንበረከከች በፀሎትን ልታነሳት ከ ጭንቅላቷ ብድግ ልታረጋት ስትሟክር የበፀሎት የጭንቅላቷ ደም እጇን ተነካካት ። ፅናት ፈራች አታነሳት ነገር አትችላትም ፨ ፅናት እንደምንም ጥራ እና ተጣጥራ ጭንቅላቷ ላይ ባስረችው ምሽ የፅናትን ጭንቅላት አሰረችላት።ብትጮክም የሚደረስላት እንደሊለ አውቃ የበፀሎትን መንቃት መጠባበቅ ጀመረች። እጇን አንጠራርታ በጆግ ያለውን ውሀ ካመጣሽ በኋላ ለበፀሎት አስራላት ከጫፉ በተረፈው ምሽ የጆጉን ውሀ አድረጋ ጭንቅላቷ ላይ እያደረገች ማልቀስ ጀመረች።ፅናት በፀሎትን አቀረቅራ አየቻት የፅናት የእንባ ዘለላ የበፀሎት የአይን ቆብ ላይ አረፈ በድጋሜ ጠብ አለ። የበፀሎት የእጆቿ ጣቷች መንቀሳቀስ ጀመሩ። ፨ ፅናት ግን አላስሰተዋለችም ፅናት ከወገቧ ታጥፋ በፀሎትን አቅፋት እያለቀሰች ነው። ፅናት የበፀሎት ትንፍሽ ሙሉ በሙሉ አንገቷ ላይ እያረፈ ነው። ትግስት ሹክሹክታ በሚመስል ድምፅ እና ደሞ በደከመ ድምፅ ፅናቴቴ አለቻች። ፅናት እህቴ ብላ ከ አንገቷ ቀና ልትል ስትል በፀሎት የቀኝ እጇን ፅናት አንገት ላይ አሳረፋ ግጥም አድረጋ አቀፈቻት። ፅናት "እህቴ በፀሎቴ ደና ነሽልኝ" አለቻት በፀሎትም ደና ነኝ አለቻት። ፨ረዥም ሰአት ተቃቅፈው ቆዩ። ከዛም በፀሎት ስትረጋጋ ፅናት ሄዳ ፍራሻቸውን እየጎተተች በፀሎት ያለችበት ጋረ አደረሰችውና "በፀሎቴ ፍራሹን አምጥቼልሻለው ቆይ ትንሽ ላግዝሽና ፍራሹ ላይ ውጪ" አለቻት። በፀሎትም "እሺ ፅናቴ" አለችና ተንጠራታ ፍራሹ ላይ ሆነች። ፅናት አመቻችታ አስተኛቻት።ፅናት "አየሽ እህቴ ብንሞትም ማንም አይደረስልንም ይህ ሁሉ የአባታችን ጥፋት ነው። እሱ ክፉ ነው በጣም" አለችና አለቀሰች ስቅስቅ እሪሪሪሪሪ አለችና በፀሎት ደረት ላይ ተደግፋ ማልቀስ ጀመረች። ፨ በፀሎትም ድምፅ ባታወጣም ስቅስቅ ብላ ነው ያለቀሰችው። በፀሎት ክንዶን ዘረግታ "ነይ ክንዴ ላይ ደገፍ በይ" አለችና ፅናትን አስደገፈቻት። ፅናት ሳታስበው እንቅልፍ ጣላት። ለጥጥጥ አለች። በፀሎትም በተመሳሳይ። ግን ደም መፈሰሱን ሳያቆረጥ ትራሱን ማረጠብ ጀምሯል በፀሎት አቅም እያጣች ነው። አልቻለችም ደክማለች በጣም ደክማለች። ፨ ፅናትም ተኝታለች ፅናት በእንቅልፍ በፀሎት ደሞ በሞት እና በህይወት መካከል ሆነው ደቂቆች ለጉድ ሄደው ሰአታት ተተካ በፀሎት የጣር ድምፅ አወጣች "ፅናቴቴቴቴ እህቴቴቴቴቴ ህይወቴቴቴቴቴቴ ልዩዬዬዬ" ፅናት አልሰማችም። ተኝታለች በፅናትም አቅሏ ተሞጦ እራስዋን ስታለች። ከ30 ደቂቃ በኋላ ፅናት ውሀ ጠምቷት ተነሳች። የተፈጥሮ ነገር ግን አይገረምም? ውስጣችን ያለው ስሜት ስአቱን ጠብቆ ከሞት ታናሽ ወንድም ሲያነቃን እና ሲያባንነን ሊላ ሰው ግን ጭንቅ ላይ ሲሆን አለመንቃታችን። ፨ፅናት አይኑዋን ስትገልፅ ያየችውን ማመን አቃታት ህልምም መሰላት። የቤታቸው አነስተኛ ዱካ ላይ ሊባኖስ ተቀምጣ ነበር። ተፈናጥራ ተነሳች አይኖቿን በእጆቾ አሻሽታ በድጋሜ ለማየት ሞከረች እውነት ነው ሊባኖስን በአይኗ እንጂ በምናቦ አላየቻትም። ልትጠጋት ብላ ፈራች ግን ደሞ ውጧ እቀፊያት እቀፊያት ይላታል የእዛ ሊባኖስን አውቃታለው ባይ ስው ንግግረም ያቃጭልባታል። ግን ሊባኖስ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከልቧ ላትወጣ በፅናት ልብ ውስጥ ተቀረፆለች። ፨ከፈራሿ ብድግ ብላ ፈገግ ብላ ከምታያት ሊባኖስ ጋር ተጠምጥማ እንባዋ ይፈስ ጀመረ። የበፀሎትም ደም እየፈሰሰ ነው። ፅናት በፀሎትን ለመቀስቀስ ወደ እሷ ተጠጋች ፈገግ እያለች። የበፀሎትን እጆች ያዘቻቸው።"እህቴ በፀሎቴ ማን እንደመጣ ብታይ??"አለች በፀሎት ግን በተራዋ ፅናትን አልስማቻትም ፅናት አሁንም ፈገግ ብላ በፂ እናቴቴቴ አልስማሽኝም ሊባኖስ መጥታለች መልስ የለም። ፨ ፅናት ግራ ገባት የበፀሎትን እጅ ብድግ አደረገችው ዝሏል የፈጣሪ ያለ ፅናት ክው አለች። እጆቿን ለቀቀቻት እጆቿ ተልፈስፈሰው ውድቅቅ አሉ። ሊባኖስ ፈጠን ብላ ወደ እነሱ ተጠጋች። ሊባኖስ የበፀሎትን ጉንጭ እና ጉንጭ ይዛ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ አዘዋወረችው ፅናት እና ሊባኖስ ተያዩ ደነገጡም።ፅናት በፀሎትን ከጭንቅላቷ ቀና ለማድረግ እጆቿን ከትራሱ እና ከበፀሎት ጭንቅላት ሾር ሰረሾል አስገባቻቸው እጆቿን እረጠባት ደነገጠች። ፈጠን ብላ አወጣቻቸው እጆቿ በደም ተለውሰዋል።ፅናት ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ግራ ገባት ሊባኖስ የፅናትን እጆች ስታየው ጣረ ሞት ያየችም ትመስል ነበር። "ምንድነው ሚጢጢዋ" አለቻት የድንጋጤ ፊት እያሳየች። ፅናትም " እኔ ለእራሱ ምንም አላውቅም"። አለችና "ቆይ ቆይ" ብላ የተፈጠረውን ነገረቻት። ሊባኖስ በፍጥነት ስልኳን አንስታ ደወለች።" ሄሎ የት ነክ አሁኑኑ ዛሬ ያደረስከኝ ቤት ና" ስልኩን ዘጋችው። ፨ ፅናት እየተንቀጠቀጠች ነው። በሲኮንድ ፍጥነት ሰውየው ደረሻለው ብሎ ሊባኖስ ጋር ደወለ። ከዛም ተቀበለችውና በፀሎትን አብረዉት ከመጡት ግብራበሮቹ ጋር መጥተው ከ እነ ሊባኖስ እና ፅናት ጋረ ጭኗቸው አንፖላንሱን እያስቦረቀ ነዳው።"ደረሰናል" አለ ሹፌሩ ፅናት ግራ ገባት። ምንም አይነት የህክምና ጣቢያ ስላላየች። ጋቢና የተቀመጠችው ፅናት ወደ ኋላ ዞራ እህቶን ማየትም አልቻለችም። ፅናት ፈራች "እንውረድ" አለና ሹፌሩ ወረደ ከዛም ሲወረዱ ፅናት ፈጠን ብላ ወደ ኋላኛው የህሙማን መጫኛ ቦታ የመኪናውን ሻተር ከፍታ ስታይ ከቦታው ላይ ሊባኖስም ሆነ እህቷ በፀሎት እንዲሁም እነዛ ሰዎች በቦታው የሉም ። ፨ ፅናት ያ ሊባኖስን በደንብ አውቃታለው ያለውን ስው ንግግር አንድ በአንድ አስታወሰች። በሀዘን እና በድንጋጤ ጊዜ ጭንቅላቶ ፈፅሞ መቆቆም የማይችለው ፅናት ልክ እንድ ሁል ጊዜው እራዋን ልትስት ሲያንገዳግዳት ሹፌሩ ተሯሩጦ ደገፋት ከዛ ፅናት የሹፌሩ ክንድ ላይ ወደቀች። ይቀጥላል.... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @yefkrinegri ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @yenhiwet ❥❥__⚘_❥❥

  • 7 мар. 2022 Đł.12 тыс35

    ራስህን ካልሆንክ _አንተ አልኖርክም ! ሁሉንም ለመምሰል ከጣርክ _አንተ አልኖርክም ! የማታምንበትን እያረግክ ከሆነ _አንተ አልኖርክም። ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @yefkrinegri ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @yenhiwet ❥❥__⚘_❥❥

  • ₀ ₀ ₀ ዳረጎት ₀ ₀ ₀ #_ አንድ ✍🏾 አሃድ ሔኖክ ⨳ ⨳ ⨳ ገና በቅጡ እንኳን ሳይነጋ ነበር ስልኬ መንጨርጨር የጀመረው። "ማን ነው ደግሞ በዚህን ሰዓት" እያልኩ እየተነጫነጭኩ አይኔን ሳልገልጥ አነሳሁት። "ወ/ሪት ህሊና ነሽ አይደል" አለ ከወዲያኛው ጫፍ የሚመጣ ድምፅ "አ....ዎ ነኝ ማን ልበል" አልኩት በእንቅልፍ ምክንያት በጎረነነው ድምፄ "ኢንስፔክተር ሲሳይ እባላለሁ ....አንድ ነገር ልናሳውቅሽ ነበር አቶ ሳሙኤል ሞቷል ማለቴ ዛሬ ጠዋት ቢሮው ውስጥ ተገድሎ አግኝተነዋል " የሰማሁት ነገር ከአልጋዬ አስበርግጎ አስነሳኝ። "እኮ ሳሙኤል" ስል ለልሴ ያልኩ ነበር የመሠለኝ። "አዎን አቶ ሳሙኤል አሰፋ" በስልክ በኩል ያለው መርማሪ ቃላቶቹን ረግጦ አረጋገጠልኝ። ከዛን በኋላ የሚለኝን ለመስማት ጆሮዎቼ አልተከፈቱም። ባለሁበት ደርቄ ለስንት ጊዜ እንደቆየው አላወቅሁም። ከድንዛዜዬ ያነቃኝ በእጄ ጨብጬ ይዤው የነበረው ስልክ ንዝረት ነው። "ወ/ሪት ህሊና የት ሄደሽ ነው" አለኝ ስልኩን እንዳነሳሁት "ይ..ቅ...ር....ታ ደንግጬ ነው " አልኹ እምባዬ ከአንድ አይኔ አፈትልካ አየወረደች። "ፈጣሪ ያፅናሽ...." "አመሠግናለሁ .......የምረዳችሁ ነገር ካለ" ሳያስጨርሰኝ "አዎ ቢሮዋችሁ አካባቢ ብትመጭልን" "እሺ መጣሁ"...... ከሆነው ነገር ጋር አልተግባባሁም። ወይ አልነቃሁም ይሆን? እራሴን በጥፊ አጮልኹት። እነደዛው ነበርሁ። እየተጎተትኩ ልብሴን ለበስኹና ልጄን ለማየት ወደ አልጋው ተመለስኩ። በደረቷ እንደተኛች ድብን ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነች። ጠጋ ብዬ ትንፋሿን አዳመጥኹና ግምባሯን ስምያት ወጣሁ። እንዴት እንደተራመድኹም ሆነ እንዴት እንደደረስኹ አላስታውስም ፣ ብቻ ቢሮ ደርሼ ይጠብቁኝ ከነበሩት ፖሊሶች ጋር እየተጨባበጥኹ ነበር። "ቁጭ በሉ" ብዬ ፊት ለፊታቸው ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥኹኝ። ውሸት እንደሆነ እንዲነግሩኝ ነበር ካፋቸው የምጠብቀው ። "እኔ ነበርኹ ያናገርኩሽ እና......" ብሎ ጀመረ አንደኛው ፖሊስ። "የግድያውን ሁኔታ ለማጣራት አንዳንድ ጥያቄዎችን መጠየቅ ስላለብን ነው።" "ይገባኛል ቀጥሉ" "እሺ....አቶ ሳሙኤል ምንሽ እንደሆነ ከመረዳት እንጀምራለን" "የስራ ባልደረባዬ ነው" "ከዛ የዘለለ ግንኙነት የላችሁም " "ያው...ከስራ ውጪም ጓደኛዬ ነው" በድጋሚ እምባዬ አነቀኝ። "ምን ያህል ጊዜ ሆናችሁ አብራችሁ መስራት ከጀመራችሁ " "ወደ 6..7..አመት ይሆናል " ጥያቄዎቹን በደመነፍስ ነበር የምመልሳቸው። አምሮዬ በሌላ ጫፍ የሳሚን መገደል እና አለመገደል ለማመን ይጣጣራል። ሰው እንዴት ማታ አብሮ ወጥቶ ጠዋት ተገድሏል የሚል መርዶ ሊሠማ ይችላል?...ደግሞ ማነው ሳሚን ሊገል የሚችል? እኔ የማላቀው ጠላት አለው እንጂ..... "ትላንት ማታ ስትለያዩ የተለየ ያስተዋልሽው ነገር ነበር?" ጥያቄው ቀጥሏል። "ኧረ በፍፁም...ፀሃፊያችን እረፍት ላይ ስለነበረች እና ዶክመንቶችን ረድፍ የሚያሲዝልን ስለሌለ ሰሞኑን ስናደርግ እንደነበረው አምሽተን ሰርተን ወጣን...ይኼው ነው....በምን ተዓምር ወደ ቢሮው እንደተመለሠ አልገባኝም " በነዚህ መሳይ ጥያቄዎች ሲያደርቁኝ እና ማስታወሻቸው ላይ ሲሞነጫጭሩ ቆይተው "ፈጣሪ ያፅናሽ!" እያሉ ተራ በተራ ጨብጠውኝ ወጡ። ቆሜ ከነበረበት ዘፍ ብዬ ተቀመጥኹኝ። በፈጣሪ ምንድነው እየሆነ ያለው?......... ° ° ° እውነትም ሳሙኤል ሞተ አልኹኝ። ቀብሩ ላይ ቆሜ እንኳን የሚመለስ ይመስለኝ ነበር። ምንም እንዳልተፈጠረ የስራ ገበታዬ ላይም ተገኝቼ ነበር። ከአሁን አሁን የቢሮዬ በር ተንኳክቶ "ህሉ በናትሽ እነዚህ ወረቀቶች ጭንቅላቴን ሊያፈነዱኝ ነው መላ ትይኝ..." የሚለኝን የሳሚን ድምፅ ጠብቃለሁ። ቡና እንጠጣ የሚለኝም ለካ ሳሚ ነበር። በቃ ሳሚ የለም፣ ድጋሚ አይመጣም፣ ላይመለስ ሄዷል የሚሉትን እውነታዎች ለልሴ መንገር ፈርቼ ሾሸሽ እውነታው ግን ፊት ለፊቴ እየመጣ ሽሽቴን አከበደው። እውነታው እያሸነፈኝ ሲመጣ ህመም ተሰማኝ። የሆነ ሆዴ ውስጥ ስል የሆነ ቢላ እየገዘገዘ እየገባብኝ እንደሆነ ነገር ያመኛል። ሳሚን በየቀኑ ከጎኔ ማየት ብቻ በቂዬ ነበር ማለት ነው?....ግን ታዲያ እንዲህ መታመሜ ገፄ ላይ አይነበብም እንዴ...ከሰብሊ(የልጄ ሞግዚት ናት) ውጪ እኮ ደህና ነሽ የሚለኝ የለም። እኔም እንደባለቤቱ ሃዘን መቀመጥ ነበረብኝ?....ወይኔ! ለካ የቀብር ቀን የሄድኩ ነኝ መሄድ አለብኝ ባለቤቱ ጋር... . . . "ደህና ነሽ? በረታሽ?" አልኹ ለሆኑ ደቂቃዎች በዝምታ ሳያት ቆይቼ "ከመበርታት ውጪ ምን አማራጭ አለኝ" አለች ቀይ ፊቷ ከማልቀሷ ብዛት በጣም ቀላልቷል። ቀጣይ ምን ልበላት? "አንቺስ በረታሽ?" ጠየቀች ቀና ብላ ሳታየኝ። "ደህና....ደህና ነኝ ምንም አልልም" ትጠይቀኛለች ብዬ ስላልጠበቅኹ ድምፄ ተቆራረጠብኝ። "አይዞሽ በርቺ" ብላኝ ከአጠገቤ ተነሳች። ትንሽ ቆየት ብላ ቆሎ በሠሃን ይዛ መጥታ ዘረጋችልኝ። ዘገንኩ። "ፓሊሶቹ ምን የነገሩሽ አዲስ ነገር አለ" "ምንም..ከዛን ወዲህ አልደወሉልኝም" "አይ ማዘን ይዟቸው ለኔ ካልነገሩኝ ብዬ ነው" ብላኝ አቀረቀረች። "ትርሱ ግን እኔ ጥያቄ ሆነብኝ እኮ...ሰርተን ወጣን በምን ምክንያት ተመለሰ ምን ቢገጥመው"....ምንም ሳትለኝ እንዳቀረቀረች ቆየች። "እሺ ይመለስ ግን የተመረዘ ውሃ...." ሳልጨርስ እምባዬ አነቀኝ። "ሳሚ እኮ ጠላት የለውም" ለልሴ አንሾካሾኽኩ። "እኔም አልገባኝም ህሉ እኔም አልተረዳውትም...."ብላ ማልቀስ ስትጀምር "በቃ ትርሱዬ በናትሽ ልቀሰቅስብሽ አይደለም..." "ሁሌም እንዳሰብኹት ነው ህሉ...ይሰማኛል፣አስበዋለሁ የዛን ቀን ምን ታይቶኝ ላየው መጣሁ?...ናፍቆኝ ነበር ብታዪ (በግድ ፈገግ ብላ) የዛን ቀን ባልመጣ ሳላየው ይሞትብኝ አልነበር?...ደሞኮ ደወልኹለት አመሸህብኝ ብለው እየመጣሁልሽ ነው የኔ ቆንጆ እያለኝ.....ወይኔ ሳሚዬ ...ብቻዬን ትተኸኝ " መንሰቅሰቅ ጀመረች። እንዴት እንደማባብላት ግራ ገብቶኝ የኔም እንባ ይፈሳል። ገድቤው ስለነበር ነው መሠለኝ ቃል ማውጣት እስኪያቅተኝ ተንሰቀሰቅኹ። ሳሚ ግን ማን ላይ ለሞት የሚያደርስ በደል ፈፀመ?ማን ላይ???....... ይቀጥል አይደል?...👍 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @yefkrinegri ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @yenhiwet ❥❥__⚘_❥❥

  • ተነሳች። ጊዜው የ10ረኛ ክፍልን ፍተና ተፈትና በጥሩ ውጤት አልፋ ክረምት ላይ ነበር። ፅናት ለእራስዋ እሷን አበረትታ እህቷን ማበረታት እንጂ ማስነፍ እንደሊለባት ተረዳች። ከዛም የምትሸጣቸውን ምግቦች በብዛት እየሰራች ለቀን ሰራተኞች ለመሸጥ ወሰነች ለእህቷም አማክራት ተስማሙ።ከዛም ሄዳ የሄለን ኪለርን መፅሀፍ በቅናሽ ገዛች። ፨ ከዛም እህቷን መጥታ እህቴ እኛ ጠንካሮች መሆን አለብን ከእኛም የባሰ አለ እኮ እየውልሽ ዛሬ ሾለ ሄለን ኪለር አነብልሻለው በቃሌ ከነገርኩሽ ይበልጥ እንድታውቂው ነው። በፀሎት የፅናት በአንድ ጀንበር መቀየር አስገርሞት። እሺ ፅናቴ የእኔ ፅናት አለቻት። ፅናት የበፀሎትን እጆች እየዳበሰች። እና ደሞ አሁን እረፍት ስለሆንኩኝ ሁሌም ቤተክረስቲያን እንሄዳለን ልክ እንደ ድሮዋችን አባባና እማማንም እንጎበኛቸዋለን አሁን ምግብ የመሽጫ ሰአቴ ሳይደረስ ሾለ ጠንካራዋ ሄለን ኪለር አስታውሺ እህቴ ይህቺ ሴት ማየትም መስማትም መናገርም ጭራሽ የማትችል ሴት ናት ግን ደሞ ጠንካራ ናት። አየሽ እህቴ ያለንን እናመስግን የሚመጣውን ፈጣሪ ያውቃል ሊላው ደሞ መፅሀፍ ቅዱስም አነብልሻለው ሀይምሮዋችን ከጠነከረ ሊላው ትርፍ ነው። ፨ ያቺ የጫት ቤቱ አያት ጠንቋይ ናቸው ብላ ለሰፈሩ ተናግራ ከዛም ይሄው የማይሉት ነገር የለም እህቴ ግን እንጠንክር አለቻት።በፀሎት ለፅናትን ማደግን በአንደበቷ አስተውላ እጅግ ተደሰተች እና ነይልኝ ብላ እጆን ዘረጋችላት ፅናትም ብድግ ብላ ልታቅፍትወደፊቷ ተጠጋች ነገር ግን ከፊቷ የሚታየው ድንግዝግዝ የሚል ነገር ነው ሰውነቷ እንደመዛል አረጋትፅናት እራስዋን ሳተች። በፀሎት ደንግጠች ከዊልቸሩ ልትወርድ ስትሞክር አብራት ወደቀች። ፨ማን ያንሳቸው? መራመድ የማትችለው በፀሎት ወይስ እራስዋን ስታ የወደቀችው ፅናት መንቀሳቀስ የማትችለውን በፀሎት ማንም ማንንም ማንሳት አለቻለም። ጮሀውም ጎረቤት መጥራት አልቻሉም ምክያቱም ፅናት ራስዋን ስታለች በፀሎትም ስትወድቅ ጭንቅላቶን የመታት ዘነዘና ጭንቅላቷን አድምቷል በፀሎት እንየፅናት ራሷን ሳተች። ማን ይድረስላቸው ታዲያ.. ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @yefkrinegri ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @yenhiwet ❥❥__⚘_❥❥