- Последний пост
- 2 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 15
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 5 584
- 1/48двое суток
- 6 399
- 1/72трое суток
- 6 901
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ኢትዮጵያው ቢሊየነር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ክለብ ተመለሱ 📈 ቢሊየነሩ ከያዝነው የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ሀብታቸው የ19.7% ወይም 1.67 ቢሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን የብሉምበርግ የቢሊየነሮች መለኪያ አመልክቷል። 🤩 ሀምሌ 25 ይፋ በሆነው የቅርብ ጊዜ ደረጃ፤ ሼሁ ከዓለም 375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የስዊዲኑ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ 'ፕሪም' የአል-አሙዲ ዋና የሀብት ምንጭ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በሳዑዲ አረቢያ እና በኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት፣ በንብረት፣ በግብርና፣ በኃይል እና በማዕድን ዘርፎች ኢንቨስትመንቶች እንዳሏቸውም የሚታወቅ ነው። 👉 ይህ አዲስ ምዕራፍ ሳዑዲ አረቢያ እ.ኤ.አ በ2017 ባካሄደችው የፀረ-ሙስና ዘመቻ፤ ከበርካታ የሳዑዲ መሳፍነት፣ ሚኒስትሮች እና ታዋቂ ነጋዴዎች ጋር መታሰራቸውን ተከትሎ በሀብታቸው ዙሪያ ከተፈጠረው አሻሚ ሁኔታ ማገገማቸውን ያመላከተ ነው። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በአፍሪካ የIMF ብድር የሌለባቸው ሃገራት 3 ብቻ ናቸው! ምክንያታቸው እና አሁን ያሉበት ሁኔታ.....https://youtu.be/t9S1qV1EFfc
🇮🇷 Millions pay tribute to Ayatollah Khamenei during farewell ceremony in Iran Staggering crowds flood Tehran's Grand Mosalla as mourners gather for the funeral prayer of the martyred leader and his family. IRGC commanders and top officials joined the mourners, with senior leadership present at the front. Memorial events will be held in cities across Iran through July 9. 📌Subscribe to @SputnikInt
Former #Japan finance minister said they were threatened with an #Earthquake Machine
የእናቶች ለቅሶ‼️ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አፈሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከላይ የሚታው ምስል ለወታደራዊ ስልጠና የታፈሱ ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ሲሳፈሩ የሚያሳይ ሲሆን ከጀርባው ልጆቻቸው የተወሰዱበቸው እናቶች ለቅሶ ይሰማል።
видео или голосовое, без подписи
ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የቀረቡ ስምንት አጀንዳዎች በዝርዝር:- አጀንዳ ቁጥር 1 1. የሀገር ግንባታ 1.1 የማንነት እና የሀገር ባለቤትነት ጉዳዮች 2. ታሪክ እና ማንነት 3. የጋራ ሀገራዊ ማንነት እና እሴቶች (እሴቶችንም የሚመለከቱ ጉዳዮች) 4. ሀገር ግንባታና ብዝሀነት አስተዳደር ጉዳዮች 5. የቋንቋ ጉዳዮች 1.6 የባህል፣ታሪክና ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች አጀንዳ ቁጥር 2 2. የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም የፖለቲካ ስርአት፣የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት 2.1 የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ 2.1.1 የመንግስት አደረጃጀት፣አስተዳደር ስርአት አይነት 2.1.2 የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት (በቅንፍ ውስጥ ሲቲዝንሺፕ ዜግነት) ህዝባዊ...አንድ 2.1.3 የብሄር ብሄረሰቦች ትርጓሜ (አንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ህገ መንግስቱ) 2.1.4 የፌደራል መንግስት እና የክልል መንግስታት መሪዎች የስልጣን ዘመን 2.1.5 የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት። የስልጣን ክፍፍል፣የፌደራልና የክልል መንግስት። የፊሲካል ፌደራሊዝምና የሀብት ክፍፍል 2.1.6 የክልል አስተዳደር እና ወሰኖች፤ የአዳዲስ ክልሎች አመሰራረት። የክልል አስተዳደራዊ ወሰኖች 2.1.7 የህግ አውጪው አካል ወይም ፓርላማ አወቃቀርና ሚና 2.1.8 ህገ መንግስትን የመተርጎም ስልጣን 2.1.9 የህገ መንግስት ማሻሻያ ስርአት (አንቀጽ 104ና 105) 2.2 የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርአት ጉዳዮች 2.2.1 የሀገሪቱ የምርጫ ስርአት 2.2.2 የመድብለ ፓርቲ ስርአት 2.2.3 የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት 2.2.4 የመንግስትና የገዢ ፓርቲ ሚና መለያየት 2.2.5 የምርጫ ክልሎች አወቃቀር 2.2.6 የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስት ሀብት አጠቃቀም አጀንዳ ቁጥር 3 3. የፌደራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) 3.1 የአዲስ አበባ ጉዳይ 3.1.1 የአዲስ አበባ ህጋዊ አቋም። አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት የአዲስ አበባ ከተማ የበጀት ድርሻ ጉዳይ 3.1.2 የፌደራል ዋና ከተማ ጉዳይ 3.1.3 የአዲስ አበባ ፖሊስና ፍ/ቤት ጉዳይ 3.1.4 የአዲስ አበባ ወሰንና የቦታዎች ስያሜዎች 3.1.5 የአዲስ አበባ የስራ ቋንቋ 3.1.6 የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች፣አካታችነት ጉዳይ 3.2 የድሬዳዋ ጉዳይ 3.2.1 የድሬዳዋ ህጋዊ አቋም 3.2.2 የድሬዳዋ የወደፊት አስተዳደራዊ ሁኔታ፣የህዝቦቿ ውክልናና ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጋር ያላት ግንኙነት 3.2.3 የድሬዳዋ በፌደራል መንግስት ውክልና። ድሬዳዋ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚኖራት ውክልና ጉዳይ አጀንዳ ቁጥር 4 4. የሃይማኖት ጉዳዮች፣ታሪካዊ ቅሬታዎች እና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች 4.1.1 በሴኪውላሪዝምና በሃይማኖት ነጻነት መካከል ጤናማ ሚዛን መጠበቅ 4.1.2 የሃይማኖት ነጻነትና ገደቦቹ 4.1.3 አናሳ የተከታይ ቁጥር ያላቸው ሃይማኖት ተቋማት ጥበቃ 4.1.4 ከባህል እና ከሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር የሚጋጩ ድርጊቶች ጉዳይ 4.2 ታሪካዊ ቅሬታዎችና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች 4.2.1 ታሪካዊ መገለል እና ልዩ ተጠቃሚነት 4.2.2 የእርቅና እውቅና የመስጠት ሂደት 4.3 በሃይማኖቶች መካከል ስላለው ግንኙነት እና አብሮ መኖርን በተመለከተ 4.3.1 በሃይማኖቶች መካከል ያሉ ውጥረቶችና መፍትሄዎቻቸው 4.3.2 በሃይማኖቶች መካከል የውይይት እና ምክክር ዘዴዎችን ማጠናከር 4.4 ሃይማኖት በህዝብ ህይወት እና ማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ያለውን መስተጋብር በተመለከተ 4.4.1 በህዝብ ተቋማት ውስጥ የሃይማኖት ሚና 4.4.2 የሃይማኖት መድረኮች፣ሚዲያና ህዝባዊ ውይይቶች 4.4.3 የሃይማኖት ተቋማት የድምጽ አጠቃቀም እና የህብረተሰብ መብት አጀንዳ ቁጥር 5 5. የተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነትና ሰብአዊ መብቶች 5.1 የሰብአዊ መብቶች 5.1.1 ህገ መንግስታዊ እና ህጋዊ ማእቀፍ ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ 5.1.2 በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች መብቶች 5.1.3 አካል ጉዳት፣ተጋላጭና የተገለሉ ቡድኖች መብቶች 5.1.4 የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በግጭት እና በጸጥታ ሁኔታዎች ውስጥ 5.1.5 ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማዊ ማእቀፎች የማጠናከር ጉዳይ 5.1.6 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ (ዳያስፖራ)። የጥምር ዜግነት መብት እውቅና እና ሌሎች ጉዳዮች 5.2 የህግ የበላይነት 5.2.1 የህግ የበላይነት (ህጋዊነት) 5.2.2 በህግ ፊት እኩልነት 5.2.3 ተጠያቂነት 5.2.4 የፍትህ ተደራሽነት 5.3 የተቋማት ግንባታ 5.3.1 የዲሞክራሲያዊ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ነጻነትና ተደራሽነት 5.3.2 የፍትህ ተቋማት ነጻነትና ተጠያቂነት 5.3.3 የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ነጻነት፣ ገለልተኝነትና አደረጃጀት 5.3.4 የሶስቱ የመንግስት አካላት ሚዛን፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት 5.3.5 የመገናኛ ብዙሃን ተቋማዊ ገለልተኝነት፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት 5.3.6 የሲቪል ማህበራት ነጻነት፣ ሚናና ተጠያቂነት አጀንዳ ቁጥር 6 6. ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች 6.1 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች 6.1.1 የሴቶች ጉዳይ እና ተያይዘው የቀረቡ ጥያቄዎች 6.1.2 የሀብት አስተዳደር እና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል 6.1.3 የመሬት ይዞታና ባለቤትነት 6.1.4. የህዝብ ቆጠራ ውክልና እና አካታች አስተዳደር 6.1.5 ማህበራዊ አገልግሎቶች (ጤና፣ ትምህርትና የኑሮ ደረጃ) 6.1.6 የሰራተኛ መብቶች እና ፍትሀዊ የስራ ሁኔታ 6.1.7 ዘላቂ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ። 6.1.8 የተፈጥሮ ሀብት መብቶችና ጥቅም መጋራት 6.1.9 አካታች ኢኮኖሚ፣ኢንቨስትመንት እና ምርታማነት 6.1.10 ማህበራዊ ደህንነትና የስራ እድል 6.2. የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይ 6.2.1 የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ተሳትፎና እኩልነት ተጠቃሚነትን የማሳደግ ጉዳይ 6.2.2 የግብርና ግብአቶች ወቅታዊና ፍትሀዊ ተደራሽነትን በተመለከተ። 6.2.3 የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 5ና አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 8 ላይ የተጠቀሰውን 'ዘላን' የሚለውን ስያሜ ማስተካከል 6.2.4 ነጻ የገበያ እድልና የገበያ ትስስር መፍጠር 6.2.5 የአርሶ አደርና አርብቶ አደር ማህበረሰቦች የጋራ መልማትና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ 6.2.6 የአርብቶ አደሮች የኑሮ ዘይቤያቸውን ያማከለ የልማት ፖሊሲ አጀንዳ ቁጥር 7 7. ሙስና እና መልካም አስተዳደር 7.1 የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሙስና ጉዳዮች። 7.2 የጸረ-ሙስና ስርአት ግንባታ 7.3 የመልካም አስተዳደር ስርአት ግንባታ 7.4 ፍትሀዊ ፓብሊክ ሰርቪስ 7.4.1ፍትሀዊና አካታች ፓብሊክ ሰርቪስ 7.4.2 በብቃት ላይ የተመሰረተ የሰው ሀብት አመዳደብ እና ቅጥር አጀንዳ ቁጥር 8 8. ሰላም ግንባታ 8.1የግጭት መንስኤዎች እና አፈታት መንገዶች ግጭቶችንና መሳሪያ ያነሱ አካላትን በሚመለከቱ 8.3 የዘላቂ ሰላም መሰረቶች 8.4 ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች እውቅና፣ ማጠናከር እና ዘመናዊ ውህደት 8.4.1 ባህላዊ እውቅና እና ህጋዊ ማእቀፍ 8.4.2 የእርቅና ይቅርታ ጉዳይ 8.4.3 የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነቶች 8.4.4 የሽግግር ፍትህ 8.5. ሃይማኖት ተቋማት ሚና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
#አስቸኳይ ማሳሰቢያ‼️ ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች የተሰጠ አስቸኳይ ማሳሰቢያ‼️ ከሰኔ 4 እስከ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በአስቸኳይ መረጃችሁን እንድታረጋግጡ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል። ይህ ራስን የማረጋገጥ ሥራ (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድ ሲሆን፥ ዋና ዓላማውም የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ (Fayda) ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ነው። በመሆኑም ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የምትወስዱ ተፈታኞች በሙሉ የ FAN ቁጥራችሁን በመጠቀም እና የግል መረጃችሁን በማሟላት የራሳችሁን መለያ ማረጋገጫ በአስቸኳይ ማጠናቀቅ ይጠበቅባችኋል። መረጃን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ቅደም-ተከተሎች ይከተሉ፦ ⨳ መጀመሪያ ወደ ድረ-ገጹ ይግቡ ➡️ https://verify.ethernet.edu.et/ ⨳ በመቀጠል "Exit Examination" የሚለውን ምርጫ ይጫኑ። ⨳ ከዚያም "Continue Verification" የሚለውን በመጫን የሚጠየቁትን መረጃዎች በትክክል ይሙሉ።
World Cup 2026 Calendar File⚽️⚽️
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት ነገ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፦ ⏰ ከጠዋቱ 2:00-12:00 👉 በአዳማ ሪጅን አዳማ ቆርቆሮ፣ ⏰ ከጠዋቱ 2:00-11:00 አዳማ ፈትል ፋብሪካ፣ ሬድሬስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ፣ አህዋን ፋብሪካ ⏰ ከጠዋቱ 2:30-9:00 👉 በአዳማ ሪጅን ከአዋሽ መልካሳ ወደ አዱላላና አሮሪቲ፣ ⏰ ከጠዋቱ 2:30-7:00 👉 በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን አስኮ ገብርኤል፣ ሳንሱሲ፣ እያሱ ምንጭ፣ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም፣ ከታ አፍያ ዴቄት፣ ⏰ ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ 👉 በደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ፣ ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ አስቱ ዩኒቨርስቲ እና ኢንዱስትሪ መንደር፣ ዋልያ ቢራ ⏰ ከጠዋቱ 6:00-9:00 👉 በምዕረብ አደስ አበባ ሪጅን ስልጤ ሰፈር፣ አጃምባ ኮንዶሚኒየም ⏰ ከቀኑ 7፡00- 11፡00 👉 በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ፣ ሸጎሌ መንደር-7፣ ፊናንስ፣ አበበ ቢቂላ፣ ኳስ ሜዳ፣ መሳለሚያ ⏰ ከቀኑ 7:30-10:30 👉 በሽረ ረጅን እደጋ አርቢ፣ ማይ ቐንታል ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻች የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ኢዜማን ምረጥ ያለው ኢህአዴግ በእስራት ተቀጣ... በደቡብ አሪ ወረዳ፣ ገድር ቀበሌ በምርጫ ዕለት የተከለከለ የፖለቲካ ቅስቀሳ በማድረጉ የተከሰሰው አቶ ኢህአዴግ ኃይሉ የ6 ወር ቀላል እስራት ተፈረደበት። የዐቃቤ ህግ ክስ እንደሚያስረዳው፣ ተከሳሹ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ ጣቢያ አቅራቢያ ድምፅ ለመስጠት ወደ ጣቢያው ይሄድ የነበረን ወጣት ለኢዜማ ድምፅ እንዲሰጥ በመገፋፋት በምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተደነገገውን ክልከላ ጥሷል። ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የደቡብ አሪ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ የዐቃቤ ህግን የሰው ምስክሮች እና የተከሳሹን የእምነት ክህደት ቃል ካዳመጠ በኋላ ተከሳሹ መከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ጥፋተኛ ብሎታል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የሦስት ልጆች አሳዳጊ መሆኑን እንደ ማቅለያ በመቀበል፣ በቀጣይ ለሌሎችም ማስጠንቀቂያ ይሆን ዘንድ በ6 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል። ፍርዱ ለሁለት ዓመት በግልጽ ገደብ እንዲፈጸም ታዟል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ላይ ጫና ሳይፈጥሩ ኢንቨስትመንትና ንግድን ለማሳለጥ ያስችላል ያለውን “የፍራንኮ ቫሉታ ገቢ ዕቃዎች መመሪያ ቁጥር FVD/01/2026” የተሰኘ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል። ይህ አዲስ መመሪያ ከዚህ ቀደም በፍራንኮ ቫሉታ አሠራር ላይ ይታዩ የነበሩ የቁጥጥር ክፍተቶችን ለመድፈንና ግልጽነትን ለማስፈን ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ባንኩ በመመሪያው መግቢያ ላይ እንደገለጸው፣ ከዚህ ቀደም አጠቃላይና ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ባለመኖሩ ምክንያት በፍራንኮ ቫሉታ ስም ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ የተዛባ ሪፖርት አቀራረብ እና የውጭ ምንዛሬ ቁጥጥርን የማለፍ አዝማሚያዎች ሲታዩ ቆይተዋል። በአዲሱ መመሪያ መሠረት በፍራንኮ ቫሉታ ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው አካላት በዝርዝር ተቀምጠዋል። እነዚህም:- • የሀገር ውስጥ (በኢኮኖሚ ቀጠናዎች ያሉ)፣ የዲያስፖራ እና የውጭ ሀገር ባለሀብቶች፣ • በውጭ ባለሀብቶች የተያዙ የማኑፋክቸሪንግ እና የኢንዱስትሪ ተቋማት፣ • ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው የልማት ፕሮጀክቶች፣ • ዲፕሎማቶች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGOs)፣ • ዕርዳታ የሚቀበሉ የሃይማኖት እና የሲቪክ ማኅበራት፣ እንዲሁም የግል ንብረቶቻቸውን የሚያስገቡ ግለሰቦች ናቸው። ከእነዚህም በተጨማሪ የግል ንብረቶቻቸውን የሚያስገቡ ግለሰቦችና በቋሚነት ወደ ሀገር የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንም ተጠቃሚ ይሆናሉ። ለሰው ሕይወት አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶች ያለምንም የዋጋ ገደብ በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ የተፈቀደ ሲሆን፤ የማምረቻ ጥሬ ዕቃዎች፣ የካፒታል ዕቃዎችና የቴክኖሎጂ መሣሪያዎችም በመመሪያው ውስጥ ተካተዋል። የጉምሩክ ኮሚሽን ሁሉንም የፍራንኮ ቫሉታ ግብይቶች "FEMoUS" በሚባለው የውጭ ምንዛሬ ክልከላና ቁጥጥር ሥርዓት ውስጥ የመመዝገብ ግዴታ ተጥሎበታል። ተጠቃሚዎችም ትክክለኛ የንግድ ፈቃድ የመያዝ፣ አስፈላጊ ሰነዶችን ለጉምሩክ የማቅረብ እና ኦዲት ሊደረጉ የሚችሉ መዝገቦችን በሥርዓቱ የመያዝ ግዴታ አለባቸው። በመመሪያው ላይ የተቀመጡ ደንቦችን በመተላለፍ የተሳሳተ መግለጫ መስጠት፣ አሠራሩን ለሕገ-ወጥ ተግባር ማዋል እና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማለፍ መሞከር ጥብቅ ቅጣት እንደሚያስከትል ተደንግጓል። ማንኛውም ጥፋት ፈጽሞ የሚገኝ አካል በገንዘብ ቅጣት፣ ንብረቱ በመወረስ አልፎ ተርፎም በብሔራዊ ባንክ አዋጅ መሠረት በወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆን መመሪያው ያስረዳል። ይህ አዲስ የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ ከዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (May 29, 2026) ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሆኗል። በብሔራዊ ባንክ መመሪያ (አንቀጽ 2.4) ላይ በተቀመጠው ትርጓሜ መሰረት እንዲሁም የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ትርጉም መሰረት "ፍራንኮ ቫሉታ" ማለት አንድ አስመጪ ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ (ለምሳሌ ዶላር ወይም ዩሮ) ከሀገር ውስጥ ባንኮች ሳይጠይቅ፣ በራሱ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ዕቃዎችን ወደ ሀገር የሚያስገባበት አሠራር ነው። ምንጭ ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን የነጻ ትምህርት ዕድል ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰልጣኞች በሩሲያ የነጻ ትምህርት ዕድል ማመቻቸቱን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለ2026/27 የትምህርት ዘመን በሩሲያ በሚገኙ ስመጥር የሳይንስና የምህንድስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ብቁ አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል። የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች በኒውክሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ሲሆን እነዚህን ዘርፎችንም ያካትታል ፡- - Nuclear Power Engineering and Heat Physics (BSc & MSc) - Nuclear Physics and Technology (BSc) - Nuclear Power Plants Design, Operation and Engineering (BSc) - Heat Power Engineering (BSc) - Management in Technological Systems (MA) የመወዳደሪያ መስፈርቶች ? • ለመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት ያልበለጠ እና የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አማካኝ ውጤታቸው 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ። • ለሁለተኛ ዲግሪ (MSc/MA) ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት ያልበለጠ እና በሳይንስና ምህንድስና ዘርፍ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ። ሴት አመልካቾች ለዘርፉ እንዲበረታቱ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። መስፈርቱን ምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በPDF በማዘጋጀት በኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ enecinfo@enec.gov.et መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
የቢቢሲ ስፖርት ተንታኞች ዴክላን ራይስን የፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች አድርገው መርጠውታል።
የ ማንችስተር ዩናይትድ የ መሃል ሜዳ ሞተር ብሩኖ የቴሪ ሄነሪ እና ዴብሩይነ የአሲስት ሪከርድ ሰበረ 21 አሲስት
የአርሰናል የዋንጫ ድርቅ ተመታ‼️❗ በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከ22 አመታት በኋላ አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2025/26 ሻምፒዮን ሆኗል። ይህ የሆነው ማንችስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ አቻ በመለያየቱ ነው። የአርሰናል ደጋፊዎች(እኔን ጨምሮ) እንኳን ደስ አላችሁ። ለንደን ቀውጢ ሆናለች። ቪዲዮ:- የአርሰናል ተጨዋቾች በልምምድ ቦታቸው የማንችስተር ሲቲ እና በርንማውዝ ጨዋታ ፊሽካ ከተነፋ በኋላ፣ጭፈራ። just enjoy it,this is your moment in 20+Years❗ አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s