የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ
Статистика"ክብርን ለሚገባው ክብርን ስጡ" ሮሜ 13፡7 ተብሎ እንደተጻፈ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳንን ታከብራለች።የዚህ ቻናል አላማም ስለ ድንግል ማርያም፣ፃድቃን፣መላእክት፣እና ሰማዕታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 39
- 1/48двое суток
- 44
- 1/72трое суток
- 48
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
https://youtu.be/pfhJHaPjuAQ?si=MpwMJQQT46mq2suf
без подписи
የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት እና ምልጃቸው አይለየን🙏 እናታቸው አላቀፈቻችውም፤ ጡትም አልጠቡም ወላጆቻቸው ልጅ አጥተው ሠላሳ ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ታላቅ ክብር ያለው ልጅ እንደምትወልድ የሚናገር ድምጽ ሰማች፡፡ በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ ግብጽ ንሂሳ በምትባል ቦታ ወለደች፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ “የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን” አላት፡፡ ሕፃኑ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ “ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን” አለ፡፡ ከዚህ በኋላ እናታቸው አላቀፈቻችውም፤ ጡትም አልጠቡም፡፡ ሦስት ዓመት ሲሞላቸውም ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ እስከ ሰባቱ ሰማይ አውጥቶ በሥሉስ ቅዱስ ፊት አቅርቦት አስባረከው፡፡ እመቤታችን፣ ቅዱሳንም ሁሉ ባረኩት፡፡ አምላካችን እግዚአብሔርም አጸናው አበረታው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደው እርሱም አስተምሮ ካሳደገው በኋላ ዲቁና በኋላም ምንኩስናና ቅስና ሰጠው፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸው፡፡ ከሰው ተለይተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር እንዲኖሩ፣ እንስሳቱም የእግራቸውን ትቢያ እየላሱ እንደሚኖሩ ነገራቸው፡፡ ሰውነታቸውም ሁሉ በጠጉር ተሸፈነ፡፡ በፍጹም ተጋድሎም ከኖሩ በኋላ በቀንና በሌሊት የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ስለኃጥአንም ጥፋት እንባቸውን እያፈሰሱ ይጸልዩ ነበር፡፡ ሦስት መቶ ዓመት ሲሆናቸውም ቅዱስ ገብርኤል በነፋስ ሠረገላ ጭኖ ከ60 አንበሶችና ከ60 ነብሮች ጋር ወደ ኢትዮጵያ አምጥቶ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ደብር ቅዱስ ወደሚባለው ዝቋላም ሔደው የኢትዮጵያን ሕዝብ ማርልኝ ብለው ለአንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ስጋቸው እስኪያልቅ ጸልየዋል፡፡ ጌታችንም መጥቶ ኢትዮጵያን ምሬልሀለሁ ብሎ ታላቅ ቃል ኪዳን ሰጣቸው፡፡ አባታችን በሀገራችን 262 ዓመታት ኖረው በተወለዱ በ562 ዓመታቸው በዕለተ እሁድ አርፈዋል፡፡
https://youtu.be/nKH70kyfxXE?si=ZZ8Edjg7RvBqFHhD
без подписи
https://youtu.be/hdD5dyZ3GAE?si=65vV8uGRWw0pfrDd
🤱 ፮. እርሱን ከወለድሽ በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኑረሻልና የክርስቶስ እናቱ ተባልሽ፡፡ ድንቅ በሚያሰኝ ተዋሕዶ አማኑኤልን ወልደሸዋልና ባለመለወጥ አጸናሽ፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን መምህር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለማንም ሴት ያልተሰጠ ለድንግል ማርያም ብቻ የተሰጠ ድንግልና ከእናትነት ጋር አስተባብራ ስለ መገኘቷ ሲገልጥ “ወሰቦሂ ወለደቶ ዐቀበ ድንግልና፣ ዘእንበለ ርኩስ ከመ በፀንሳ መንክር ትኩን መራሂተ ለሃይማኖት ዐባይ - ከድንግል ተወለደ፤ በወለደችውም ጊዜ ድንግልናዋ ያለመለወጥ አጸና፡፡ ድንቅ የሚኾን ፅንሷ ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ” በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን ስትወልድው ማኅተመ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ጌታም ሰው ሲኾን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ፣ እርሷ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባል እንደምትኖር አካላዊ ቃል ክርስቶስም አምላክ ወሰብእ (ሰው የኾነ አምላክ) ሲባል የሚኖር የመኾኑን የተዋሕዶ ልዩ ምሥጢርን ያወቅንባት የተረዳንባት እርሷ ብቻ መኾኗን አስተምሯል /ሃይ.አበ.፷፮፡፴፪/፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ 🪜 ፯. ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት፣ በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖት ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲-፳፪/፡፡ ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰውም ከኾነ በኋላ የማይመረመር እርሱን በተፈትሖ በማይታወቅ በማኅፀንሽ ችለሸዋልና እኛን ስለማዳን ከአንቺ ሰው ከኾነ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰዋስው (አማላጅ) ኾንሽን፡፡ እኛን ስለማዳን ከአንቺ ሰው ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ⛪ ፰. ጽርሐ ንጽሕት ሆይ! እነሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ኹሉ በቸርነቱ ብዛት ያድን ዘንድ ከአንቺ ተወለደ፡፡ ቸር ሰው ወዳጅ ነውና በአፍአ በውስጥ እናመስግነው፡፡ ቸር ሰው ወዳጅ ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ✨ ፱. አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ድንግል ምልዕተ ክብር ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ከእናትሽ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ጠብቆሻልና የዓለም ኹሉ መክበሪያ ንጽሕት ጽዋዕ ነሽ (ከሥላሴ ለምንጠጣው ክብር ምክንያት አንቺ ነሽ)፡፡ 🕯️ እንደ ደብተራ ኦሪቷ ማለትም ሙሴና አሮን በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት አብርተው በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት እንደሚያጠፏት ፋና ያይደለሽ የማትጠፊ ፋና ነሽ /ዘጸ.፳፭፡፴፩-፵/፡፡ 🏰 እንደ ቀደመችው የኦሪት ቤተ መቅደስ ያይደለሽ የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ /፩ኛ ነገ.፯፡፵፰-፶/፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫም፡- “አንቲ ውእቱ መቅደስ ዘሐነጸ ሰሎሞን ወአስቀጸላ በሜላትሮን ወለበጠ ዳቤራ በውሳጥያተ መቅደስ፤ … - ሰሎሞን ያሠራት እንደ ዝናር እንደ ዐምድ ባለ ወርቅ የጠፈሯን ዙርያ ያስጌጣት፤ በመቅደስ ውስጥ ያለቺውን ቅድስተ ቅዱሳንዋን ዐውደ ምሕረቷን ግድግዳዋን በጥሩ ወርቅ ያስጌጣት፤ ቁመቱ ሃያ ክንድ፤ ክንፉ ዐሥራ አምስት ክንድ የሚኾን ኪሩብን በውስጧ ያሣለባት ቤተ መቅደስ አንቺ ነሽ” በማለት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ሰሎሞን ባሠራት የወርቅ ቤተ መቅደስ መስሎ ኹለንተናዋ በንጽሕና በቅድስና ያጌጠች የተዋበች መኾኗን አስተምሯል /አርጋኖን ዘዐርብ/፡፡ ዳሩ ግን እመቤታችን በንጽሕናዋ በቅድስናዋ በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ብትመሰልም ሊቁ (ኤፍሬም) እንዳለው ክብሯ የላቀ ነው፤ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናትና የማትፈርስ መቅደስ ናት /መዝ.፹፮፡፩-፭/፡፡ 🙏 የማትለወጥ የቅዱሳን ሃይማኖታቸው (ቅዱሳን የሚያምኑበት ክርስቶስን የወለድሽላቸው አንቺ) ነሽ፡፡ ድንግል ሆይ! በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ ይቅር ይለን ዘንድ፣ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ 🙌 አነሣሥቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈጸመን ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን!! 🙏 የመዝጊያ ጸሎት፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን፤ በጸሎቷም ከክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን። የልጇ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት፣ ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን! 🕊️ #ውዳሴ_ማርያም #የቅዳሜ_ውዳሴ_ማርያም #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #እመቤታችን #ድንግል_ማርያም #OrthodoxTewahedo #EthiopianOrthodox #Spiritual #Viral #Orthodox #Tewahedo #በረከት
✨ የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ✨ 🕊️ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጠፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናዉን ጀምሯል፡፡ 🌸 ፩. ንጽሕት ነሽ፤ ብርህት ነሽ፡፡ በአፍአ በውስጥ ንጽሕት ነሽ፡፡ ሊቁ “ዲያተሳሮን” በተባለው የወንጌል ትርጓሜ መጽሐፉ የእመቤታችንን ንጽሕና ሲናገር፡- “የማርያም ሰውነት የምድር ላይ መቅደስ ነው፡፡ በዚሁ መቅደስም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በኀጢአት፣ በሞትና በርግማን ፈንታ የበረከትን ዘር ሊዘራ መጣ፡፡ የኤልሳቤጥም ሰላምታ ይህንን አረጋገጠ፡፡… አንተና እናትህ ብቻ በማንኛውም ረገድ ንጹሐን ናችሁ፡፡ ጌታ ሆይ! በአንተ ውስጥ ምንም ነቅዕ የለም፤ በእናትህም ውስጥ ምንም ምልክት የለም” ብሏል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Tatian’s Diatesaron, pp 91-92/፡፡ 💖 ጌታን በማኽል እጅሽ የያዝሽው ሆይ! ምልዕተ ክብር ሆይ! (ተፈስሒ) ደስ ይበልሽ እያሉ ፍጥረት ኹሉ ከአንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ከአንቺ ጋር አንድ ባሕርይ ቢኾን ባለሟልነትን አግኝተሻልና (ተፈስሒ) ደስ ይበልሽ፡፡ ግርምት ድንግል ሆይ! ክብርሽን ገናንነትሽን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እናመሰግናለን (እናደንቃለን)፡፡ ከማኅፀንሽ ፍሬ የባሕርያችን ድኅነት ተገኝቷልና ከመልአኩ ጋር እንደ መልአኩ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ የማኅፀንሽ ፍሬ ከአባቱ ጋር አስታርቆናልና እንደ መልአኩ ምስጋና እናቀርብልሻለን፡፡ ሊቁ ቅድም በጠቀስነው መጽሐፉ፡- “… መልአኩ ወደ አንዲት ድንግል ተላከ፡፡ ወደ እርሷ ገብቶም “እነሆ ድንግልናሽ ሳይነዋወጽ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት/ሉቃ.፩፡፴፩//፡፡ ይኸውም በሥጋ ተገልጦ ሊመጣ ስላለው ስለ አካላዊ ቃል ሲናገር ነው፡፡ ሲነግራት “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት እንጂ “ኢየሱስ የተባለው” እንዳላላት ልብ በሉ፡፡ ይኸውም የሰው ልጆች ወልደ እግዚአብሔር በለበሰው ሥጋ የሚድኑበት ስም መኾኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ማለት በዕብራይስጥ “መድኅን” ማለት ነውና፡፡ መልአኩ “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” ሲላት መድኅን ትዪዋለሽ ማለቱ ነው፡፡ ለምን? ሕዝቡን ኹሉ ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና” ብሏል /ማቴ.፩፡፳፩/፡፡ ከአባቱ ጋር ካስታረቀን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ 👑 ፪. አባ ሕርያቆስ፡- “እግዚአብሔር አብ በሰማይ ኾኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንና ደቡብን ዳርቻዎችንም ኹሉ በእውነት ተመለከተ፤ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም፡፡ የአንቺን መዓዛ ወደደ፤ የሚወደው ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ” እንዲል /ቅዳ.ማር. ቁ.፳፬/ እንደ ሰርግ ቤት አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ኾነሽ ቢያገኝሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና፤ ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ለብሷልና አንድም መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ ግብራት ከልክሎሻልና ኃይለ ልዑል ወልድም ከሦስቱ ግብራት ከልሎሻልና ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃልን ወለድሽልን /ሃይ.አበ.፻፲፡፳፱/፡፡ ሰው ኾኖ ከኃጢአት አዳነን /ማቴ.፩፡፳፩/፡፡ ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ✝️ ፫. መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ አንቺ ነሽ /ሉቃ.፩፡፴፪/፡፡ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ከአብ ባሕርይ ዘእም ባሕርይ አካል ዘእም አካል የተወለደ፣ ተቀዳሚ ተከታይ (ታላቅም ታናሽም) የሌለው አካላዊ ቃል ባሕርዩን በሥጋ ሠወረ፡፡ ከአንቺም አርአያ ገብርን ነሣ /ፊል.፪፡፯/፡፡ 💡 ከእናንተ መካከል፡- “አካላዊ ቃል አርአያ ገብርን ነሥቶ (የባሪያን መልክ ይዞ) በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ባዶ አደረገ ሲል ምን ማለት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ራሱን ባዶ አደረገ ሲል የእኛን ባሕርይ ገንዘብ ባደረገ ጊዜ ባሕርየ መለኮቱ ተለውጧል ማለት አይደለም፡፡ ባሕርየ መለኮቱን ትቶ መጣ ማለትም አይደለም፤ በፈቃዱ ደካማ ባሕርያችንን ገንዘብ አደረገ ማለት ነው እንጂ፡፡ ወልደ እግዚአብሔር ራሱን ባዶ ያደረገው በመቅድመ ወንጌል “ከጥንት ዠምሮ በባሕርያችን እስኪሠለጥን ድረስ ሰይጣን በተንኰል በሥጋ ከይሲ እንደተሠወረ፤ እኛም ከፍዳ መዳናችን ቃለ እግዚአብሔር በባሕርያችን በመሠወሩ ኾነ” ተብሎ እንደተጻፈ የእኛን ባዶነት በጸጋው ለመሙላት ነው፡፡ ሰው የኾነው እኛን አማልክት ዘበጸጋ ያደርገን ዘንድ ነው፡፡” የባሪያውን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ስለ እኛ ብሎ ራሱን ባዶ ካደረገ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ☀️ ፬. አደፍ ጉድፍ ሳይኖርብሽ አምልክን የወለድሽው እመቤታችን ሆይ! በኃጢአት ብርድ የተያዘውን ዓለም ኃጢአቱን ያርቅለት ዘንድ ፀሐየ ጽድቅ ጌታ ከአንቺ ተወልዷልና፤ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው እንደተናገሩም ዘር ምክንያት ሳይኾንሽ፣ መለወጥ ሳያገኝሽ ወልደሸዋልና ከምድር በላይ ያለሽ ኹለተኛ ሰማይ አንቺ ነሽ፡፡ ኢትዮጲያዊው ቄርሎስም፡- “ኦ ሰማይ ዳግሚት ዘወለደቶ ለፀሐየ ጽድቅ ዘውእቱ ብርሃነ ቅዱሳን ዘሰደዶ ለጽልመት - ጨለማን ያሳደደውን (ያስወገደውን) የቅዱሳን ብርሃን የሚኾን አማናዊ ፀሐይን የወለደች ኹለተኛይቱ ሰማይ ሆይ! …” እያለ ያወድሳታል /አርጋኖን ዘረቡዕ/፡፡ ዘር ምክንያት ሳይኾንሽ ከወለድሽው ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ⛺ ፭. ከተለዩ የተለየሽ፣ ከከበሩ የከበርሽ በውስጧም ሕግ የተጻፈበት ኪዳን ያለብሽ የተሠወረ መና ያለበት መሶበ ወርቅ ያለብሽ ደብተራ (ድንኳን) አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፮፡፩-፴/፡፡ ይኸውም መና የተባለው ሰው ኾኖ በማኅፀንሽ ያደረው ወልደ እግዚአብሔር ነው፡፡ መተርጕማኑ ይህን የበለጠ ሲያብራሩት፡- “ድንኳኗ የእመቤታችን ምሳሌ፤ ቅድስት የነፍሷ፤ ቅዱሳን የሥጋዋ፤ ታቦቱ የመንፈስ ቅዱስ፤ ጽላት የልቡናዋ፤ ቃሉ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጸላት ምሥጢር ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ቅዱሳን የሥጋዋና የነፍሷ፤ ቅድስት የልቡናዋ፤ ታቦት የማኅፀኗ፤ ጽላት የትስብእት፤ ቃሉም የመለኮት ምሳሌ ነው” ይላሉ /ውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው፣ ገጽ ፻፸፬/፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በአርጋኖን ዘሐሙስ ላይ፡- “ተፈሥሒ ኦ ደብተራ ብርሃን ማኅደሩ ለዐቢይ ሊቀ ካህናት - የታላቁ ሊቀ ካህናት ማደርያ የብርሃን ድንኳን ሆይ! ደስ ይበልሽ” በማለት የሊቀ ካህናት የባሕርይ አምላክ የክርስቶስ እናት አማናዊት ድንኳን መኾኗን አስተምሯል፡፡ 🐑 አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ የክብር ባለቤት እርሱን በዚህ ዓለም ወለደችው፡፡ ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃል ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ አድኖናልና ሰው ኾኖ ያዳነን የነባቢ በግዕ (የሚናገር በግ የክርስቶስ) እናቱ ደስ ይላታል /ዮሐ.፩፡፳፱/፡፡ ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃል ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
без подписи
https://youtu.be/JsSYPBUWGrI?si=MwkAFT7Z_wiFvjgI
без подписи
አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! እናትህን ቅድስት ድንግል ማርያምን በክብር እንዳስነሣሃትና እንዳሳረግሃት፤ እኛንም በንስሐ ታጥበን፣ ከኃጢአት ሞት ተነሥተን ቅዱስ ሥጋህንና ክቡር ደምህን እንድንቀበል አድለን። ቅድስት እናትህ ድንግል ማርያም ሆይ! አዕምሮውን፣ ለብዎውን ሳይብን አሳድሪብን፤ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ከልጅሽ አማልጅን። ሀገራችንንና ሕዝባችንን በሰላም ጠብቂልን፤ አሜን! (ይህንን አስተማሪና ጥልቅ የሆነ የፍልሰታ ጽሑፍ ለወዳጅ ዘመድዎ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ!) ✍️ ሀምሌ 30 2018 ዓ.ም #ጾመ_ፍልሰታ #ፍልሰታ_ለማርያም #ፆመ_ፍልሰታ #ድንግል_ማርያም #የማርያም_ጾም #OrthodoxTewahedo #EthiopianOrthodox #Filseta #Tewahedo #ViralOrthodox #ሰዐሊ_ለነ_ቅድስት #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #መንፈሳዊ_ዕውቀት 🕊️✨
https://youtu.be/hEcCsnF2JWc?si=Ak58NZtYRW8c_F33 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ 🕊️ "ሞት በጥር... በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል?" ፦ የቅዱስ ቶማስ ምስጢር፣ የድንግል ማርያም የክብር ዕርገትና የጾመ ፍልሰታ ጥልቅ መንፈሳዊ ጉዞ! 🕊️ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ፍቅር፣ የቅዱሳን ሐዋርያትን ጽናትና የትንሣኤዋን ክብር የሚያስረዳን ታላቁ "ጾመ ፍልሰታ" እነሆ ደርሷል! ከሕፃናት እስከ አረጋውያን በታላቅ ተጋድሎና ፍቅር የሚጾሙት ይህ ጾም፣ በውስጡ እጅግ ጥልቅ የሆኑ መንፈሳዊ ምስጢራትን አቅፏል። የዚህን ጾም ታሪክና በረከት ከታች ባለው ጽሑፍ አብረን እንመልከት፤ ለሌሎችም በማካፈል የበረከቱ ተካፋይ እንሁን! 👇 🌿 የ"ፍልሰታ" ትርጓሜና የድንግል ማርያም የሕይወት ጉዞ «ፍልሰታ» የሚለው ቃል «ፈለሰ» (ተሰደደ፣ ተገለጠ፣ መከፈት፣ መገለጥ) ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ነው። ፍልሰት ማለት ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ሲያመለክት፣ «ፍልሰታ ለማርያም» ሲባል ደግሞ እመቤታችን ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን (ማረጓን)፣ በኋላም ሥጋዋ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው። እመቤታችን በምድር ላይ ፷፬ (64) ዓመታትን አሳልፋለች፦ 📍3 ዓመት በእናት በአባቷ ቤት 📍12 ዓመት በቤተ መቅደስ 📍9 ወር በዮሴፍ ቤት 📍 33 ዓመት ከ 3 ወር ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር 📍 14 ዓመት በወንጌላዊው በዮሐንስ ቤት 📍ከዚህ ሁሉ የዓለም ውጣ ውረድና ድካም በኋላ፣ በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን አረፈች። 🔥 የአይሁድ ዓመፃና የመልአኩ ቅጣት ቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ሊቀብሩ ወደ ጌቴሴማኒ ሲጓዙ፣ ጌታችንን የሰቀሉት አይሁድ “እንደ ልጇ ‹ተነሣች፤ ዐረገች› እያሉ እንዳያውኩን በእሳት እናቃጥላት” ብለው በክፋት ተነሡ። ከእነርሱም መካከል 'ታውፋንያ' የሚባል አይሁዳዊ የአልጋውን አጎበር ይዞ አስከሬኗን ሊያወርድ ሲሞክር፣ የእግዚአብሔር መልአክ በሰይፍ ሁለት እጆቹን ቀጣው! ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ጨምሮ እመቤታችንን በደመና ነጥቆ ወደ ገነት ወስዶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣት። ☁️ "ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል?" (የቅዱስ ቶማስ ምስክርነት) ቅዱሳን ሐዋርያት እናታቸው ተሰውራባቸው ዝም ብለው አልተቀመጡም። እመቤታችን ያለችበት ቦታ እንዲገለጥላቸው ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ገቡ። ሁለት ሱባዔ ከጾሙ በኋላ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን ሰጥቷቸው በክብር በጌቴሴማኒ ቀበሯት። በሦስተኛው ቀንም (ነሐሴ 16) ትንሣኤ ዘጉባኤን ሳትጠብቅ በልጇ ሥልጣን ተነሥታ ወደ ሰማይ አረገች! በዚህ ጊዜ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ወንጌልን ሲሰብክ ቆይቶ በደመና ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ፣ እመቤታችን ወደ ሰማይ ስታርግ ጠፈር ላይ አገኛት። ቶማስም “ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን?” ብሎ በኀዘን ከደመናው ሊወድቅ ሲል፣ እመቤታችን፦ 🗣️ "አይዞህ! አትዘን፤ ባልንጀሮችህ ሐዋርያት ያላዩትን ትንሣኤዬን አንተ አይተሃልና ደስ ይበልህ!" ብላ ከሙታን መነሣቷንና ማረጓን ለሐዋርያት እንዲነግራቸው አዝዛ፣ የተገነዘችበትን ሰበን ሰጥታው ወደ ሰማይ አረገች። ወደ ሐዋርያት ሔዶም “የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ?” ቢላቸው፣ “አግኝተን ቀበርናት” አሉት። እርሱም “አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል?” አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ መቃብሯን ቢከፍት ሥጋዋን አጣው። በዚህ ጊዜ ቶማስ የተሰጠውን ሰበን አሳያቸው። ይህ ሰበን ሐዋርያት ሕሙማንን የፈወሱበት ሲሆን፣ ዛሬም በቤተክርስቲያናችን ዲያቆናት በመስቀል ላይ የሚያስሩት፣ ካህናትም በራሳቸው ላይ የሚጠመጥሙት ነጭ ሻሽ የዚሁ ሰበን በረከት ምሳሌ ነው! 👑 የሐዋርያት መንፈሳዊ ቅናትና የነሐሴው ጾም መጀመር በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት “ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?” ብለው ሱባዔ ይዘው ጌታችንን ጠየቁት። ጌታም ልመናቸውን ተቀብሎ ነሐሴ 16 ቀን ወርዶ፣ እመቤታችንን መንበር፤ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፤ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቆረባቸው! እነርሱም እርሷን በዓይናቸው አዩ፣ ሥጋና ደሙንም ተቀበሉ። ይህን መሠረት በማድረግ ነው ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከነሐሴ 1 እስከ 15 የሚጾመውን ጾመ ፍልሰታን የሠራችልን። 📖 "በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።" (መዝሙር 44፥9) 📖 "ሰዐሊ ለነ ቅድስት" ወይስ "ሰአሊ ለነ ቅድስት"? በጾመ ፍልሰታ በስፋት ከሚጸለዩት ጸሎቶች አንዱ፣ ቅዱስ ኤፍሬም 64ቱን የእመቤታችንን የዕድሜ ዘመናት አስቦ የደረሰው ውዳሴ ማርያም ነው። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም መጨረሻው ላይ “ሰዐሊ ለነ ቅድስት / ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለውን ጨምሮበታል። በዐይኑ ‘ዐ’ ሲጻፍ፦ አዕምሮውን፣ ለብዎውን (ማስተዋሉን) ሳይብን አሳድሪብን ማለት ነው። በአልፋው ‘አ’ ሲጻፍ፦ ከተወደደው ልጅሽ ሥርየት እንድናገኝ ለምኝልን ማለት ነው። ⚠️ ለወጣቱ የተላለፈ የሕይወት ጥሪ! የፍልሰታ ጾም የገዳማውያን ብቻ ሳይሆን የዓለማውያንም የሱባዔ ጊዜ ነው። ብዙ ጊዜ ኦርቶዶክሳውያን ሕፃናት በዚህ ወቅት ሥጋወደሙን ይቀበላሉ። ነገር ግን በሕግ የተከለከለ እስኪመስል ድረስ ወጣቶች ሥጋወደሙን ከመቀበል ሲርቁ ይስተዋላል! አረጋውያንና ሕፃናት ብቻ ሳይኾኑ ወጣቶችም ጭምር ራሳችንን ገዝተን፣ ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል መንግሥቱን ለመውረስ መዘጋጀት ይኖርብናል። ጌታችን በማይታበል ቃሉ እንዲህ ብሏልና፦ 📖 "ሥጋዬን የሚበላ፤ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።" (ዮሐንስ 6፥54) 📖 "ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።" (ማቴዎስ 18፥20) 📜 የፍልሰታ ምስጢር ፦ (ልዩ መንፈሳዊ ግጥም) 📜 በጥር ሀያ አንድ፣ ከዓለም ድካም ስታርፍ፣ አይሁድ ተነሡ፣ ሥጋዋን ሊያጠፉ በሰይፍ። ታውፋንያ ሲዘረጋ፣ እጁን በድፍረት፣ መልአኩ ቀጣው፣ ሥጋዋም አረገ ወደ ገነት። ሐዋርያት አዘኑ፣ እናታቸው ተሰውራ፣ ሱባዔም ጀመሩ፣ ነሐሴን በጾም አደራ። አሥራ አራት ቀን፣ በጸሎት ሲተጉ በአንድነት፣ ጌታ ሥጋዋን ሰጣቸው፣ ተቀበረች በክብር በጌቴሴማኒ መሬት። ነሐሴ አሥራ ስድስት፣ እንደ ልጇ ትንሣኤ፣ ተነሥታ ዐረገች፣ ተፈጽሞ ታላቁ ሱባዔ። ቶማስ ከደመና፣ ምስጢሩን ሲያይ በዓይኑ፣ አጽናናችው እናቱ፣ ሰጥታው የክብር ሰበኑ። “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር” ብሎ ሲጠይቃቸው፣ መቃብሩ ባዶ ሆነ፣ ጴጥሮስም በአድናቆት አያቸው። ጌታችን ወረደ፣ እናቱን መንበር አድርጎ፣ ሐዋርያትን አቆረበ፣ የሰማይ ጸጋን ዘርግቶ። ወጣቶች እንነሣ፣ ንስሐ ገብተን በቶሎ፣ ሥጋና ደሙን እንቀበል፣ ሕይወት እንዲኖረን ሞልቶ። ድንግል ትለምንልን፣ አእምሮውን ታሳድርብን፣ የፍልሰታው በረከት፣ ዛሬም ይድረሰው ለሁላችን! 🙏 የመዝጊያ ጸሎት 🙏
без подписи
https://youtu.be/IJU1wNJkGz8?si=w0nCimiZORl6PfL0 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ #መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!! " በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።" ማቴ. ፫፥፩-፪ /3፥1-2/ ❤ በቅድስናው ገና ሳይፀነ የተመረጠው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የጌታውን መንገድ ሲጠርግ ኖረ ❤ ብዙዎችን በንስሐ ጥምቀት እያጠመቀ ከኃጢአት እና ከአመጻ ይርቁ ዘንድ አስተምሯል የሰማዕቱ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ምልጃና በረከት በእኛ ላይ ይደርብን። #መጥምቁ #ዮሐንስ
без подписи
https://youtu.be/nbEKEPMCdKw?si=MUs-y7KBqXODO_df ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ ኃጢያቴ ነው እንጂ ከአንተ የሚያሸሸኝ🎤 በደሌ በዝቶ እንጂ አንገት የሚያስደፋኝ አምላኬ ይዞኛል ሰፊው መዳፍህ በበዛው ቸርነት ምሕረት ይቅርታህ🙏💖 † † † እኔ ራሴን ካልጣልኩ አታውቅም ጥለህኝ እኔ ራሴን ካልጣልኩ አታውቅም ጥለህኝ ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር የምታየኝ ‹‹አታውቅም ጥለኸኝ››