Against Falsehood¤
Статистика□ቻናሉ በአላህ ፈቃድ የክርስትና አስተምህሮዎች የሚፈተሹበት ይሆናል። □ሥላሴ፣ የእየሱስ አምላክነት፣ የባይብል ተዓማኒነት፣ በጥቅሉ የክርስትና አስተምህሮዎች ከጥንት እስከ ዛሬ በባይብል፣ በታሪክ እንዲሁም በአዋልድ መጽሐፍቶቹ የሚዳሰሱ ይሆናል፤ ሌሎች ጉዳዮችንም የምንዳስስበት ይሆናል።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 117
- 1/48двое суток
- 134
- 1/72трое суток
- 144
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ጥያቄ:⁉ ፈርድ ሰላት በቀን ስንት ጊዜ ይሰገዳል⁉ በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጡ ቻናል ነው ተቀላቀሉ➢@mustefa_Apologetics
"አህያን እንምሰላት" አህያን እንምሰላት ስል በደስታ ነው😂 አላለም..! የሚጠፋ!
ጥበበኛ እባብ ሁኑ.. የሚጠፋ!
ይቺ 99% በጣም ተደጋገመች ክርስቲያኖች ሃጢአትን ብቻ ሳይሆን አላዋቂነትንም ነው መሰለኝ በዘር የሚወርሱት..😭! ውይይቱ ላይ ዲያቆኑ ስለ እደ-ክታባት ብዛት ሲያወራ ብልጭ ብሎብኝ😀 ከውይይቱ ቡሃላም ሌሎች ዲያቆናት በልበ ሙሉነት ያለ ሃፍረት ይደጋግሙታል ከዚህ በፊትም ሲደጋገም ሰማለሁ... ሲጀመር በTextual Criticism ጥናት ውስጥ የManuscrpits ብዛት ሳይሆን ጥራት(date¹+Accuracy²) ነው *ቅድሚያ የሚታየው* ይህን Textual Criticism በቅርቡ ማጥናት የጀመረ ግለሰብ የሚያውቀው ተራ ሐቅ ነው:: የሁለቱ ኮዴክሶች "ጥራትና ጥንታዊነት" ደግሞ ሚዛን የሚደፋ ነው(ይሄን ካላበዱ አይክዱትም😁):: 99% የምትሏቸው እደ-ክታባት ብዙዎቹ የት ክፍለ ዘመን ላይ እንደሚገኙ አጣሩ ሲጀመር ብዙዎቹ እደ-ክታቦቻችሁ መጤ ናቸው ትንሽዬ ናቸው በነ ኮዴክስ ቫቲካነስ በተቀራራቢ ጊዜ የሚገኙት:: እመኑኝ ሌሎቹን ልናነሳቸው የምንችላቸውን ሙግቶች ትተናቸው ይሄ የራሳችሁ ከልክ ያለፈ አላዋቂነት የተሞላበት ባዶ ወሬአችሁ ብቻ አንገታችሁን ያስደፋችሁዋል! Textual Criticism🫲ዲያቆናት🫱
"አባ ደንቆሮ"😁 ሙሉ ምስሉን ከዚህ ቻናል ይቅዱ፦ https://t.me/Christianity_With_History ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' 🖌Against Falsehood¤ '''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
🗂የቅዱስ ኢራንየስ ሦስት ቅዱስ ውሸቶች! ኢራንየስ በ2ተኛ ክፍለ ዘመን የኖረ የቤተ-ክርስቲያን አባት ሲሆን ከፖሊካርፕ እግር ስር እንደተማረ ይነገራለታል፤ ፖሊካርፕ ደግሞ የሐዋሪያው ዮሐንስ ደቀ-መዝሙር እንደነበረ በቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ይነገራል።¹ ይህ ማለት ኢራንየስ ከዮሐንስ ደቀ-መዝሙር የተማረ ነው ማለት ነው:: ይህ ሁኖ ሳለ ይህ አባት Bible ላይ ሦስት አስገራሚ ውሸቶችን ሲዋሽ ወይም ሲሳሳት እናገኘዋለን.. አንድ ክፍል(ምዕራፍ/paragraph) ላይ ብቻ ነው ይህ የሆነው!! [A₁] የመጀመሪያው ግልጽና ከበድ ያለ Theological ለውጥ መፍጠር ቅጥፈት ነው፤ ዘፍጥረት 1፥1 ላይ ሁላችንም እንደምናውቀው 'ኤሎሂም' በመጀመሪያ(בְּרֵאשִׁ֖ית) ሰማይና ምድርን "እንደፈጠረ" የሚዘግብ ንባብ ነው፦ Genesis 1 አማ - ዘፍጥረት 1: "በመጀመሪያ እግዚአብሔር" ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። ነገር ግን ኢራንየስ በግልጽ ኢየሱስን በግድ አምላክ ለማድረግ በሚመስል መልኩ የለሌን ንባብ አስገብቶ "በመጀመሪያ ወልድ" ብሎ ተርጉሞታል:: ይሄንን ትርጉም የተረጎመው ከሁለት የዕብራይስጥ ቃል ነው "በረሺት" "בְּרֵאשִׁ֖ית" እና "ባራ" "בָּרָ֣א'' የሚሉ ቃላትን "በመጀመሪያ ወልድ" ብሎ ተርጉሟቸዋል:: ትርጉሙ ፈጽሞ የውሸት እና የማያስኬድ መሆኑን የምታውቁት ቀጥሎ ትርጉሙ ላይ "Established Then The heaven and The Earth" ብሎ በመተርጎሙ ነው። በእጃችን የሚገኘው የእብራይስጡ ንባብ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ባራ" ከሆነ፤ ይህንን "ባራ" የሚል ቃል "ወልድ" ብሎ ከፈታው ሁለተኛ "ፈጠረ(Established)" ብሎ የፈታበት የዕብራይስጥ ቃል የት አለ? ከየቱ አመጣው?* ይህ ትልቁ ቅጥፈቱ ነው፤ ለማንኛውም ክፍሉን አንብቡት:- «Moses, who prophesied first, says in Hebrew, "Baresith bara Elovim basan benowam samenthares," and this is translated < ... > "A Son [in] the beginning God established then heaven and earth."» 📕(Demonstration of Apostolic preaching 43; Irenaeus) በረሺት የሚለውም ቃል ቢሆንም መጀመሪያ የሚል ትርጉም ነው ያለው እንጂ ልጅ የሚል ትርጉም የለውም፤ በግሪኩ LXX ውስጥም የተተረጎመው አርኼ "αρχη" መጀመሪያ ተብሎ ነው። አዲስ ኪዳን ላይ ክርስቲያኖች የሚኮርበት የኢየሱስ አምላክነት ተገልጦበታል ብለው የሚያምኑበት የዮሐንስ ወንጌል ክፍል ላይ "ዮሐ 1፥1" ላይ ራሱ ልጅ ተብሎ አይተረጎምም/አልተተረጎመም በግሪኩም በዕብራይስጡም:: ስለዚህ ኢየሱስን ከማሪያም ከመወለዱ በፊት Pre-existence እንዳለው አድርጎ ለማቅረብ የተደረገ ግልጽ ቅጥፈት መሆኑ ግልጽ ነው። [B₂] ኢራንየስ እዚሁ ክፍል ላይ ሌላ ጥቅስ አሳስቶ ሲጠቅስ እናገኛለን። በኤርሚያስ የማይገኝን ንባብ በኤርሚያስ ነው የተባለው በማለት ያስቀምጣል፦ «Jeremias the prophet also witnesses this, saying thus, "Before the morning star I begot you, and your name [is] before the sun,"» 📕(Demonstration of Apostolic preaching 43; Irenaeus) ክፍሉ በትክክል ባይጣቀስም ኤርሚያስ ላይ ሳይሆን "መዝሙረ ዳዊት" ላይ የሚገኝ ክፍል ነው፦ Psalms 110 አማ - መዝሙር 3: ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ። ኢራንየስን ከስህተት ባያድነውም ጥቅሱ Mixed Quotation እንደሆነ የሚገልጹ ምሁራን እንዳሉ ሳልጠቁም ማለፍ አልፈልግም:: ያው ቁም ነገሩ ኢራንየስ "ኤርሚያስን ብቻ" ስለጠቀሰ ከመሳሳት አያተርፈውም! [C₃] ተጨማሪ በኤርሚያስም በሌሎች ቀኖናዊ የባይብል ክፍሎችም የማይገኝን ንባብ በኤርሚያንስ እንደሚገኝ አድርጎ አስፍሯል፦ «"And again he says, "Blessed is He who was before He became man,,,» 📕(Demonstration of Apostolic preaching 43; Irenaeus) ይህ ክፍል በኤርሚያስ ክፍልም ሆነ ቀኖናዊ በሆኑ አሁን ክርስቲያኖች እጅ በሚገኙ የባይብል ክፍሎች ውስጥ ፈጽሞ የሚገኝ ንባብ አይደለም::² ባይሆን ይህ ንባብ በቤተ-ክርስቲያን ከቀኖና በተገለሉ ጥንታዊ ወንጌላት ውስጥ ይገኝ ነበር፤ "በፊልጶስ ወንጌል" ውስጥ ንግግሩን ጌታ እንደተናገረው ተደርጎ ተዘግቧል፦ «The Lord Said, “Blessed is he who is before he came into being. For he who is has been and shall be.”» 📕(Gospel Of Philip 64:10) በቶማስ ወንጌል ውስጥ ደግሞ ንግግሩን ኢየሱስ እንደተናገረው ተደርጎ ተዘግቧል፦ «Jesus Said,“Blessed is he who came into being before he came into being. ...”» 📕(Gospel Of Thomas 19) ዋነው ነጥብ በኢራንየስ እይታ ክፍሎቹ የኢየሱስን pre-existence የሚያንጸባርቁ ከመሆናቸው አንጻር ኢራንየስ ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ በራሱ የሌሉ ንባቦችን ሲፈበርክ እንደነበረ ግልጽ ነው ይህ ደግሞ በቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እየሱስን "በግድ አምላክ ለማድረግ" ከልክ በላይ ጥረት ይደረግ እንደነበረ አንዱ ማሳያ ነው:: ይህ በአንድ በኩል Textual Criticism ላይ 'ጭማሪዎች' ተብለው ክርስቲያኖች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ አባቶችን እንደ ተዓማኝ ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ እንደማያዋጣ ወይም "ለማስረጃነት ብቁ እንዳልሆኑ" አንዱ ማሳያ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አይ ኢራንየስ አልቀጠፈም ብላችሁ የምትመልሱ ከሆነ «ባይብል ተበርዟል፤ Bible *የጠፉ* እና *የተለወጡ* ክፍሎች አሉት» እያላችሁን ስለሆነ እናመሰግናለን። አንድ ታላቅ ደረጃ የተሰጠው አለፍ ሲልም ራሱ በተደጋጋሚ በሚገልጸው መሠረት ትምህርቱ ከራሱ ከእየሱስ ከሐዋሪያትም የመጡ መሆናቸውን ከመግለጹ አንጻር³፤ በአንድ ትንሽዬ paragraph ውስጥ 2 ግልጽ ቅጥፈት እና አንድ ቀላል የማይባል ስህተት ከሰራ እንዴት ነው በነዚህ አባቶች ትምህርት ውስጥ እምነት የሚጣለው? በክርስትና አስተምህሮ እንዴት እምነት ይጣላል? /ማጣቀሻ/ ................................................. * ከጅምሩ "ባራ" የሚለው ቃል "መፍጠርን" የሚያሳይ ነው ወልድ ተብሎ ሊተረጎም አይችልም ግስ እንጂ ስምም አይደለም፤ ኢራንየስ የዕብራይስጡ "ባራ" እና የአራማይኩ "ባር"/"ልጅ" ተምታቶበት ነው እንዳልል እንኳን እዛው ላይ መፍጠርንም ወልድ የሚለውንም ትርጓሜ ነው ሰጥቶ የተረጎመው፤ ይህ ደግሞ አያስኬድም:: 1]-የእግዚአብሔር መንግሥስት ታሪክ በምድር ላይ በቀ/ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገ/አማኑኤል ገጽ 199. 2]-Demonstration Of Apostolic Preaching; Introduction and Notes by J. ARMITAGE ROBINSON, D.D p.22. 3]-Demonstration of Apostolic preaching 98; Irenaeus. https://t.me/Christianity_With_History
¶..“አንጀቴ እንደ መሰንቆ¶ ትጮኻለች”🙇♂
Against Falsehood¤ pinned «▪︎《በዚህ Channel ክርስትና ላይ የተጻፉ ጹሁፎች》 86)-🔺አስማት! 87)-🔺ሰይጣን!² 88)-🔺የእየሱስ ፍቅር! 89)-🔺የእየሱስ ፍቅር!² 90)-🔺ለታሪክ ይቀመጥ! 91)-🔺ባይብል የአምላክ ቃል አይደለም! 92)-🔺የክርስትና አሳፋሪ ታሪክ!'¹ 93)-🏴☠እየሱስ ፍጡር ነው! 94)-🔺ወልድ ለሥጋ የሚሳሳ ስለሆነ ተቅለብልቦ መጣ? //ይህ ማውጫ በየጊዜው አዳዲስ ጉዳዮች ሲለቀቁ የሚስተካከል ነው//…»
🔺በልመና እንጀራ ያደገው 'እግዜር'?² እናቱ እንጀራ በራሱ በእግዜር ስም እየለመነች ያሳደገቺው ክርስቲያኖች ዘንድ እንደ አምላክ የሚታየው አካል በአንድ ወቅት እናቱ ጀርባ ላይ ተቀምጦ እናቱ እንጀራ በምትለምንበት ወቅት ኮቲባ የተሰኘች 'ጀግኒት' ይህንን አምላክ ተብሎ የሚታመን አካል ከእናቱ ጀርባ ላይ መንጭቃ ከመሬት ቀላቀለቺው፤ ይህም የፍጥረት ጌታ ተብሎ የሚታሰበው አካል 'ትክን ትክን' ብሎ አለቀሰ፦ “ኮቲባ የተሰኘችው አገልጋይ ደርቡን እያናወጠች ወርዳ ዮሴፍን በጥፊ ቃጥታ ጌታን ከእመቤታችን ጀርባ ነጥቃ ከመሬት ቀላቀለችው፤ ሕጻኑ ትክን ትክን ብሎ ሲያለቅስ እመቤታችንም ጩኸት እና ድንጋጤ የከበበው ብርቱ ለቅሶን አልቅሳለች::” 📔(ሕይወተ ማርያም ድንግል ገጽ 151) ጫማው የተወሰደበትንም ፓርት እዩት ምስሉ ላይ..! ወገን ጫማውን ያልጠበቀ አካል አንተን ሊጠብቅ ነው ምታስበው? ተረታቸውን መልሱ አፋቸውን በዳቦ አብሱ.. ግን አለቃቀሱ አንጀት ይበላል አደል 'ትክን ትክን' ብሎ Part🙇♂..¡ እኮ እግዜርን 'ትክን ትክን' አስብላ አስለቀሰቺው? ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' 🖌Against Falsehood¤ '''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
🔺በልመና እንጀራ ያደገው 'እግዜር'? ይህን በልመና እንጀራ ያደገ እግዜርን እናቱ ስለ እሱ እንጀራ በምትለምንበት ወቅት ደቃቅ ፍጡራን ከእናቱ ላይ መንጭቀው መሬት ላይ ይፈጠፍጡት እንደነበረ ኦርቶዶክስ ትረግረናለች፦ ፱“እናቴ ሆይ ስለ እኔ እንጀራ በለመንሻት ጊዜ ኮቲባ ከእጅሽ ነጥቃ በምድር ላይ ብትጥለኝ የታገስኩትን መታገስ አላየሽምን?” 📔(ድርሳነ ኪዳነ ምሕረት ዘሐሙስ 9) ወደዚህ ማንነት "የእለት እንጀራችንን ስጠን" ብለው የሚለምኑ አሳዘኑኝ¡ ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' 🖌Against Falsehood¤ '''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
💭☁️እግዜር ጸሎት እንዳይደርሰው በደመና Intercept አደረገው¿? ክርስቲያኖች ሆይ ክረምትም እየገባ ነው ያልጨረሳችሁት ጸሎት ካለ በጊዜ ጨርሱ፦ “ጸሎታችን እንዳያርግ ራስህን በደመና ከደንህ።” — ሰቆቃው ኤርምያስ 3:44 እሰቡት እግዚአብሔር ጸሎት እንዳይደርሰው ወይም ወደ እርሱ እንዳያርግበት በደመና ሲከላከል😭! ይህ አይነቱ የሚሳኤል ሳይሆን የጸሎት interceptor ለሚስኪን…
🔺እጣን ጸሎት ማሳረጊያ! “የሚያጥኑትስ ምንድን ነው ቢሉ የጻድቃን ጸሎት፣ የሰማዕታት ገድል፣የደጋግ ሰዎች ምግባር በእናንተ እየታጠነ ወደ እኔ ያርግ/ይድረስ/ ብሏቸዋል::” 📔(መጽሐፈ አክሲማሮስ ገጽ 51) ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' 🖌Against Falsehood¤ '''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
🔺እጣን ጸሎት ማሳረጊያ! Video'ው የተኮረጀው😌፦ https://t.me/Facethetruth22 ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' 🖌Against Falsehood¤ '''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
ጳውሎስ 'በመስጊድ' ሰበከ!
Matthew 4 አማ - ማቴዎስ 2: አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ "ተራበ።" ክርስቲያኖች እየሱስ መለኮት ነው እንደምትሉ ይታወቃል፤ በዚህ ጥቅስ መሠረት መለኮት ተርቧል ማለት ነው? የሚራብስ አካል ነው የምታመልኩት?
በተዋሕዶ ጊዜ ወልድ ብቻ ሳይሆን ሦስቱም የስላሴ አካላት ወይም "አብም፣ ወልድም፣ መንፈስ ቅዱስም" በማርያም ማህጸን አድረው እንደነበረ ኦርቶዶክስ ትሰብካለች:: 📔/ጌራ መድሃኒት በዲያቆን አባይነህ ካሴ ገጽ 74/ የወልድ ሳያንስ ሦስቱም አንዲት ደቃቅ ፍጡር ሴት ማሕጸን ውስጥ አድረው(ተቀምጠው) ነበርን? በአንድ ወቅት ተሰባስበው በአንዲት ሴት ማሕጸን ያደሩን ሦስት አካት ታመልካላችሁ? አግባብ ነው? ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' 🖌Against Falsehood¤ '''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
አሁንም በድጋሚ ሌላ እድል ልስጣችሁ...! አግናጢየስ፣ ኢራንየስ፣ ቀለሚንጦስ(የሮሙ) ከነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችሁ ደስ ያላችሁን አንዱን መርጣችሁ ዛሬ የሚሰበከውን ሥላሴ ሰብከዋል ብላችሁ የምታስቡ ንገሩኝ ከዚያ ጊዜውን ተነጋግረን Live ከፍቼ መጥታችሁ ሞግቱኝ!! ሥላሴን በባይብል ይቅርና በ'አባቶቻችሁ' አታገኙትም!!
ከቅድመ ኒቂያ አበው መካከል "አንድ ነጠላ ማንነት የሆነ አምላክ" የሰበኩ አሉ ብዬ እሞግታለሁ! "አንድ አካል በብቸኝነት አልሰበኩም ሁሉም የሥላሴ አማኝ ናቸው የሰበኩት አሁን የሚሠበከውን የሥላሴ አስተምህሮ ነው!" ብሎ የሚያስብና የሚሞግት አካል ካለ በደስታ እቀበላለሁ! ከስር በጹሁፍ ይግለጽና(አለሁ ይበልና) Live አንድ አባት ላይ እናወራለን፤ ጊዜ አመቻችተን! አታሳፍሩኝም ብዬ እገምታለሁ🥲..!
🔺የያህዌህ ዘረኝነትና አጥማሚነት! ያህዌህ እስራኤልን ብቻ እንደመረጠና ከእስራኤል ውጪ ያሉትን በሙሉ ከእርሱ(ከያህዌህ) እንዲርቁ ወይም እንዲስቱ አጋንንትን እንዳሰለጠነባቸው ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ? መጽሐፈ ኩፋሌ 12:44 አማ2000 [44] ሕዝብ ይሆኑት ዘንድ እስራኤልን ለይቶ መረጠ። ብዙ አሕዛብና፥ ብዙ ሕዝብ ሁሉ የእርሱ ናቸውና፥ ሁሉም ለእርሱ ይገባልና ከሰው ልጆች ሁሉ ለይቶ ሰበሰበው። *ነገር ግን ከእርሱ በኋላ ያስቱአቸው ዘንድ መናፍስትን በሁሉ ላይ አሠለጠነ።* "ነገር ግን ከእርሱ በኋላ ያስቱአቸው ዘንድ መናፍስትን በሁሉ ላይ አሠለጠነ" የሚለው ይሰመርበት ይህ ንግግር በቀጥታ ያህዌህ ከእራኤል ውጪ ያሉትን ሕዝቦች እንዳሳታቸው እንደማይፈልጋቸውም ጭምር ያሳየናል። ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላችሁ ይሄንን ክፍል በእንግሊዘኛ እትሞች ላይ ኩፋሌ(Jubilees) 15:31 ታገኙታላችሁ፦ Jubilees 15:31 [31]And He sanctified it, and gathered it from amongst all the children of men; for there are many nations and many peoples, and all are His, and over all hath He placed spirits in authority to lead them astray from Him. "over all hath He placed spirits in authority to lead them astray from Him" የሚለው ይሰመርበት ይህ ንግግር ያህዌህ በግልጽ *በሁሉም ላይ* ከእርሱ ከራሱ ያስቱ ዘንድ አጋንንትን እንዳስቀመጠ ነው የሚናገረው።(1980 እትሙ *አጋንንት* ብሎ አስቀምጦታል!) ሙሉ አውዱን ብትመለከቱት እስራኤልን ብቻ እንደመረጠ ሌሎቹን እንዳልመረጠ ታነባላችሁ ለምሳሌ በአማርኛው እትም ላይ ቁጥር 43-44 ተመልከቱ፤ ይህ በራሱ ከዘረኝነት የሚመደብ ነው። አንድን ሕዝብ ብቻ ነጥሎ መምረጥና ሌሎቹን በሙሉ ከእርሱ መንገድ እንዲያፈነግጡ መናፍስት መላክ ምን የሚሉት ነው?? ምን እንበለው? በዚህ ብቻ አያበቃም የመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ጸሃፊ ያህዌህ ከእስራኤል ውጪ ያሉትን "እንደ ምራቅ ይመሰላሉ" ብለኻል ሲል ይወርፋቸዋል፦ እዝራ ሱቱኤል 4፥55-59(አማ2000) 55“አቤቱ፥ ይህን ሁሉ በፊትህ ተናገርሁ፤ *ይህን ዓለም ሰለ እናንተ ፈጠርሁት ብለሃልና።* 56*ከአዳም የተወለዱ ሌሎች አሕዛብ* ግን *እንደ ኢምንት ናቸው*፤ *እንደ ምራቅም ይመስላሉ*፤ *እንደ አፍሻት ጠብታም ናቸው*፤ *ደስታቸውም እንደ ኢምንት ነው*። 57አሁንም እነሆ *እንደ ኢምንት ናቸው ያልሃቸው* እነዚያ አሕዛብ እነሆ በእኛ ላይ ሠለጠኑ፤ ረገጡንም። 58የምወደው የበኸር አንድያ ልጄ ያልኸን እኛ ወገኖችህ ግን በአሕዛብ እጅ ገባን። 59ነገር ግን ዓለምን ስለ እኛ ከፈጠርኸው ዓለማችንን ለምን አንወርስም? ይህስ እስከ መቼ ድረስ ነው?” እንግዲህ ተመልከቱ ከአዳም የተወለዱትን ሌሎች ሕዝቦችን ማለትም ከእስራኤል ውጪ የሆኑትን ሕዝቦች "እንደ ኢምንት ናቸው"፤ "እንደ ምራቅ ይመስላሉ"፤ "እንደ አፍሻት ጠብታም ናቸው"፤ "ደስታቸውም እንደ ኢምንት ነው" በማለት ዘርጥጦ ዘርጥጦ ይጥላቸዋል። ከዚህ በላይ ዘረኝነት ከየት ይመጣል? አንድን ሕዝብ መርጦ ወግኖ ሌሎቹን "ምራቅ ትመስላላቹ" እያለ መወረፍ ምን ይባላል? ጭራሽ አንድን ሕዝብ ብቻ መርጦ ወዶና መርቶ ሌሎቹን ሕዝቦች በሙሉ በጅምላ ማሳሳትና መጥላት ምን ይባላል? ያህዌህ አንድን ሕዝብን ነጥሎ መርጦ ከማሳሳት በተጨማሪም "እንግዚአብሔርን ለማወቅ ያልወደዱትንም" የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ዓመጻን፣ ግፍ፣ መመኘትን ክፋትን ይሞላባቸዋል፦ Romans 1 አማ - ሮሜ 28: "እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን" እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ 29: ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት "ሞላባቸው"፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥ በመጽሐፋችሁ መሰረት ያህዌህ እንዲህ አይነት ጽንፍ የረገጠ የዘረኝነት ጥግ እና ሰዎችን ያለ ፈቃዳቸው ጎጥና ጎራ ለይቶ የማጥመም ችሎታውን እያሳያችሁ በምን ሞራል ነው ክርስቲያን የሆናችሁት? በምንስ ሞራል ነው እስልምና ላይ ጥያቄ ምታነሱት? ከጅምሩ "ከጠማማ ጋር *ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ*" የተባለን አካል ነውኮ የምታመልኩት፦ Psalms 18 አማ - መዝሙር 26: ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ። ላለማንዛዛት እዚሁ ጋር እንቋጨው እንጂ ብዙ ማስረጃዎች ሞልተዋል! ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' 🖌Against Falsehood¤ '''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''