tgindex
[

ይህ Channel በአላህ ፈቃድ የክርስትና አስተምህሮዎች የሚፈተሹበት፤ ጥያቄ የሚቀርብበት፤ አንዳንድ ሃሳቦችንም የምንማማርበት ይሆናል። *...* ምስጋናም ለአላህ ለሰማያት ጌታ ለምድርም ጌታ ለዓለማት ጌታ የተገባው ነው፡፡[45•36]

Последний пост
29 июл.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
146
0 Са 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
361
20 постов
Вовлечённость
247,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
1
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
317
1/48двое суток
363
1/72трое суток
391

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • /ለጠቅላላ እውቀት/ በክርስትና ውስጥ ቅዱስ የሆኑ "አባ ደንቆሮ" የሚባሉ(ስማቸው ነው😁) አባት እንዳሉ ታውቃላችሁ? ስም ነው ወይስ ስድብ ወገን?😭 "ዮሐንስ አፈ ወርቅ" የሚባል ውብ ስም በፈለቀባት ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ "አባ ደንቆሮ" ሚባሉ ቅዱስ አባት አሉ ቢባል ማን ያምናል?ÂĄ https://t.me/Christianity_With_History

  • 🗂የቅዱስ ኢራንየስ ሦስት ቅዱስ ውሸቶች! ኢራንየስ በ2ተኛ ክፍለ ዘመን የኖረ የቤተ-ክርስቲያን አባት ሲሆን ከፖሊካርፕ እግር ሾር እንደተማረ ይነገራለታል፤ ፖሊካርፕ ደግሞ የሐዋሪያው ዮሐንስ ደቀ-መዝሙር እንደነበረ በቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ይነገራል።¹ ይህ ማለት ኢራንየስ ከዮሐንስ ደቀ-መዝሙር የተማረ ነው ማለት ነው:: ይህ ሁኖ ሳለ ይህ አባት Bible ላይ ሦስት አስገራሚ ውሸቶችን ሲዋሽ ወይም ሲሳሳት እናገኘዋለን.. አንድ ክፍል(ምዕራፍ/paragraph) ላይ ብቻ ነው ይህ የሆነው!! [A₁] የመጀመሪያው ግልጽና ከበድ ያለ Theological ለውጥ የሚፈጥር ቅጥፈት ነው፤ ዘፍጥረት 1፥1 ላይ ሁላችንም እንደምናውቀው 'ኤሎሂም' በመጀመሪያ(בְּרֵאשִׁ֖ית) ሰማይና ምድርን "እንደፈጠረ" የሚዘግብ ንባብ ነው፦ Genesis 1 አማ - ዘፍጥረት 1: "በመጀመሪያ እግዚአብሔር" ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። ነገር ግን ኢራንየስ በግልጽ ኢየሱስን በግድ አምላክ ለማድረግ በሚመስል መልኩ የለሌን ንባብ አስገብቶ "በመጀመሪያ ወልድ" ብሎ ተርጉሞታል:: ይሄንን ትርጉም የተረጎመው ከሁለት የዕብራይስጥ ቃል ነው "በረሺት" "בְּרֵאשִׁ֖ית" እና "ባራ" "בָּרָ֣א'' የሚሉ ቃላትን "በመጀመሪያ ወልድ" ብሎ ተርጉሟቸዋል:: ትርጉሙ ፈጽሞ የውሸት እና የማያስኬድ መሆኑን የምታውቁት ቀጥሎ ትርጉሙ ላይ "Established Then The heaven and The Earth" ብሎ በመተርጎሙ ነው። በእጃችን የሚገኘው የእብራይስጡ ንባብ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ባራ" ከሆነ፤ ይህንን "ባራ" የሚል ቃል "ወልድ" ብሎ ከፈታው ሁለተኛ "ፈጠረ(Established)" ብሎ የፈታበት የዕብራይስጥ ቃል የት አለ? ከየቱ አመጣው?* ይህ ትልቁ ቅጥፈቱ ነው፤ ለማንኛውም ክፍሉን አንብቡት:- ÂŤMoses, who prophesied first, says in Hebrew, "Baresith bara Elovim basan benowam samenthares," and this is translated < ... > "A Son [in] the beginning God established then heaven and earth."Âť 📕(Demonstration of Apostolic preaching 43; Irenaeus) በረሺት የሚለውም ቃል ቢሆንም መጀመሪያ የሚል ትርጉም ነው ያለው እንጂ ልጅ የሚል ትርጉም የለውም፤ በግሪኩ LXX ውስጥም የተተረጎመው አርኼ "αρχη" መጀመሪያ ተብሎ ነው። አዲስ ኪዳን ላይ ክርስቲያኖች የሚኮርበት የኢየሱስ አምላክነት ተገልጦበታል ብለው የሚያምኑበት የዮሐንስ ወንጌል ክፍል ላይ "ዮሐ 1፥1" ላይ ልሹ ልጅ ተብሎ አይተረጎምም/አልተተረጎመም በግሪኩም በዕብራይስጡም:: ስለዚህ ኢየሱስን ከማሪያም ከመወለዱ በፊት Pre-existence እንዳለው አድርጎ ለማቅረብ የተደረገ ግልጽ ቅጥፈት መሆኑ ግልጽ ነው። [B₂] ኢራንየስ እዚሁ ክፍል ላይ ሌላ ጥቅስ አሳስቶ ሲጠቅስ እናገኛለን። በኤርሚያስ የማይገኝን ንባብ በኤርሚያስ ነው የተባለው በማለት ያስቀምጣል፦ ÂŤJeremias the prophet also witnesses this, saying thus, "Before the morning star I begot you, and your name [is] before the sun,"Âť 📕(Demonstration of Apostolic preaching 43; Irenaeus) ክፍሉ በትክክል ባይጣቀስም ኤርሚያስ ላይ ሳይሆን "መዝሙረ ዳዊት" ላይ የሚገኝ ክፍል ነው፦ Psalms 110 አማ - መዝሙር 3: ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ። ኢራንየስን ከስህተት ባያድነውም ጥቅሱ Mixed Quotation እንደሆነ የሚገልጹ ምሁራን እንዳሉ ሳልጠቁም ማለፍ አልፈልግም:: ያው ቁም ነገሩ ኢራንየስ "ኤርሚያስን ብቻ" ስለጠቀሰ ከመሳሳት አያተርፈውም! [C₃] ተጨማሪ በኤርሚያስም በሌሎች ቀኖናዊ የባይብል ክፍሎችም የማይገኝን ንባብ በኤርሚያንስ እንደሚገኝ አድርጎ አስፍሯል፦ ÂŤ"And again he says, "Blessed is He who was before He became man,,,Âť 📕(Demonstration of Apostolic preaching 43; Irenaeus) ይህ ክፍል በኤርሚያስ ክፍልም ሆነ ቀኖናዊ በሆኑ አሁን ክርስቲያኖች እጅ በሚገኙ የባይብል ክፍሎች ውስጥ ፈጽሞ የሚገኝ ንባብ አይደለም::² ባይሆን ይህ ንባብ በቤተ-ክርስቲያን ከቀኖና በተገለሉ ጥንታዊ ወንጌላት ውስጥ ይገኝ ነበር፤ "በፊልጶስ ወንጌል" ውስጥ ንግግሩን ጌታ እንደተናገረው ተደርጎ ተዘግቧል፦ ÂŤThe Lord Said, “Blessed is he who is before he came into being. For he who is has been and shall be.”» 📕(Gospel Of Philip 64:10) በቶማስ ወንጌል ውስጥ ደግሞ ንግግሩን ኢየሱስ እንደተናገረው ተደርጎ ተዘግቧል፦ ÂŤJesus Said,“Blessed is he who came into being before he came into being. ...”» 📕(Gospel Of Thomas 19) ዋነው ነጥብ በኢራንየስ እይታ ክፍሎቹ የኢየሱስን pre-existence የሚያንጸባርቁ ከመሆናቸው አንጻር ኢራንየስ ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ በራሱ የሌሉ ንባቦችን ሲፈበርክ እንደነበረ ግልጽ ነው ይህ ደግሞ በቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እየሱስን "በግድ አምላክ ለማድረግ" ከልክ በላይ ጥረት ይደረግ እንደነበረ አንዱ ማሳያ ነው:: ይህ በአንድ በኩል Textual Criticism ላይ 'ጭማሪዎች' ተብለው ክርስቲያኖች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ አባቶችን እንደ ተዓማኝ ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ እንደማያዋጣ ወይም "ለማስረጃነት ብቁ እንዳልሆኑ" አንዱ ማሳያ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አይ ኢራንየስ አልቀጠፈም ብላችሁ የምትመልሱ ከሆነ «ባይብል ተበርዟል፤ Bible *የጠፉ* እና *የተለወጡ* ክፍሎች አሉት» እያላችሁን ስለሆነ እናመሰግናለን። አንድ ታላቅ ደረጃ የተሰጠው አለፍ ሲልም ልሹ በተደጋጋሚ በሚገልጸው መሠረት ትምህርቱ ከራሱ ከእየሱስ ከሐዋሪያትም የመጡ መሆናቸውን ከመግለጹ አንጻር³፤ በአንድ ትንሽዬ paragraph ውስጥ 2 ግልጽ ቅጥፈት እና አንድ ቀላል የማይባል ስህተት ከሰራ እንዴት ነው በነዚህ አባቶች ትምህርት ውስጥ እምነት የሚጣለው? በክርስትና አስተምህሮ እንዴት እምነት ይጣላል? /ማጣቀሻ/ ................................................. * ከጅምሩ "ባራ" የሚለው ቃል "መፍጠርን" የሚያሳይ ነው ወልድ ተብሎ ሊተረጎም አይችልም ግስ እንጂ ስምም አይደለም፤ ኢራንየስ የዕብራይስጡ "ባራ" እና የአራማይኩ "ባር"/"ልጅ" ተምታቶበት ነው እንዳልል እንኳን እዛው ላይ መፍጠርንም ወልድ የሚለውንም ትርጓሜ ነው ሰጥቶ የተረጎመው፤ ይህ ደግሞ አያስኬድም:: 1]-የእግዚአብሔር መንግሥስት ታሪክ በምድር ላይ በቀ/ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገ/አማኑኤል ገጽ 199. 2]-Demonstration Of Apostolic Preaching; Introduction and Notes by J. ARMITAGE ROBINSON, D.D p.22. 3]-Demonstration of Apostolic preaching 98; Irenaeus. https://t.me/Christianity_With_History

  • በሐምሌ ወር የተወለድሽ ሴት ክርስቲያን ሆይ ነይ ጉድሽን ተመልከቺ!😁 እንደ ኦርቶዶክስ ጥንቁልና ከሆነ ባለዚህ ኮከብ ሴቶች በእርግጥ አሳዛኝ ናችሁ🥲... «ህይወትሽ የመከራ እንደሆነ ተጠንቁሎልሻል... በ30 እና 50 አመትሽ ልትሞቺ ትችያለሽ ተብለሻል... ያው አንድ መጽናኛሽ ሃብትሽ ነው ሃብት አለሽ ተብለሻል😁... እና ከበሽታሽ ለመዳን ደግሞ ቡሃ በግ አሳርደሽ በ❝ፈርስ❞ መታጠብ ፍቱን መዳኒት እንደሆነ ተጠንቁሎልሻል..።» ምንጭ፦📔(ዓውደ ነገሥት ወፍካሬ ከዋክብት ገጽ 15) ፈርስ ታቃላችሁ አይደል?.. በነገራችን ላይ ቃላቶቹ ወጣ ያሉ ናቸው😁! ጥርሷ ላይም ምልክት አላት ተብሏል የምትፈልጓት ካላችሁ😒😁 https://t.me/Christianity_With_History

  • ከመጋቢት 14 ጀምሮ የተወለዳችሁ ክርስቲያን ሴቶች ኑ እስቲ ጉዳጉዳችሁን ስሙ!😁 ❝፩ኛው  ኮከብ  ሐመል  እሳት።  ሐመል እሳት የእሳት ነበልባል ማለት ነው ከመጋቢት 14 ቀን ጀምሮ ማታ ማታ ይወጣል❞ ምንጭ፦📔(ዓውደ ነገሥት ወፍካሬ ከዋክብት ገጽ 4) ይህ ኮከብ ያለባት ሴት «እግረ ወልሻሻ» ነች! እድሜዋ ለልሹ ተወስኗል ይታወቃል 70 አመት ነው ተብላችሁዋል! ምንጭ፦📔(ዓውደ ነገሥት ወፍካሬ ከዋክብት ገጽ 5) https://t.me/Christianity_With_History

  • 13 февр.39831иС AGAINST_CHRISTIANITY

    3ተኛ የአለም ጦርነት ብቻ ሳይሆን "በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ግዙፍ ተጠባቂ ውጊያ አለ" እየተባለ ነው ሰዎች... :: 🖌Against Falsehood¤

  • 🖌እሰልምና ከነቢዩ ሙሐመድ  በፊት! ምንም እንኳን እኛ ሙስሊሞች ግልጽ የሆነ በቂም የሆነ ማስረጃ ያለን ብንሆንም ለእኛ ለሙስሊሞችም ከምንም የማንቆጥራቸው ለክርስቲያኖች ግን ታማኝ የሆኑ ትላልቅ ቦታ የሚሰጣቸው መጽሐፍቶች እንደሚገልጹት ከሆነ እስልምና ከነብዩ መሐመድ በፊት የነበረ እንደሆነ ይመሰክራሉ። "ድርሳነ ዑራኤል" ይህ ድርሳን እንደ ክርስቲያናዊ ምንጮች ከሆነ ከነቢዩ ሙሐመድ  በፊት የተጻፈ ነው፤ ምንጭ፦ '<መጽሐፈ ግዮን> አዘጋጅ፦መምህር በትረ ማርያም አበባው'። ድርሳኑ እንደሚገልጸው ከሆነ በሐዋሪያው ጴጥሮስ ዘመን አንድ 'እስላም' እንደነበረና ይህን እስላምም ክርስቲያን ለማድረግ ጥረት ሲደረግ እንደነበረ እናነባለን፦ "7፤ በማግስቱ ያ 'ተንባላታዊ' ወደ ኤጲስ ቆጶሳት አለቃ ወደ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ሄደና በራእይ ያየውን ነገረው። 8፤ ያን ጊዜ ጴጥሮስ ደስ አለውና የክርስትናን ሃይማኖት ለብዙ ቀን አስተማረው። 9፤ ከሦስት ወር በኃላም ጴጥሮስ ተጠመቅና ክርስቲያን ሁን ቢለው ክርስቲያን ብሆን ምን አገኛለሁ ምንስ ይጠቅመኛል ሲል 'እስላሙ' መለሰለት።" (ድርሳነ ዑራኤል ዘሚያዝያ ገጽ 173) "ተንባላት" ማለት በግዕዝ "እስላም" ማለት ነው፤ ለዚህም ተጨማሪ ማስረጃዎችን መመልከት እንችላለን ለምሳሌ ያክል *ፍካሬ ሃይማኖት* በሚለው መጽሐፍ ላይ "ተንባላት" የሚለውን ቃል በሕዳጉ ላይ *ዲያቆን ዳንኤል ክብረት* "ግዕዙ ተንባላት የሚላቸው ሙስሊሞችን ነው" ብሎ አብራርቶታል፦ "31- ወደ መስቀል የወጣው እርሱ አይደለም፤ ተሰቅሎ የተቸነከረው እርሱን የሚመስል ነው, በማለት ለእኛ ሕይወት መድኃኒት በሆነን በመከራው የሚያፍር ቢኖር እንደ ተንባላት'116 የተወገዘ ይሁን።" 116 ግእዙ ተንባላት የሚላቸው ሙስሊሞችን ነው። ይኼ አስተምህሮ በእስልምና በኩል የሚገኝ ነው። (ፍካሬ ሃይማኖት በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሐተታ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገጽ 43) ሌላው 2ተኛው መሠረታዊ ነጥብ እዚሁ ሕዳግ ላይ "ይኼ አስተምህሮ በእስልምና በኩል የሚገኝ ነው።" የሚል ንግግር እናገኛለን ዲያቆኑ ይህ አስተምህሮ እያለ ያለውን ለመረዳት ከላይ መለሾ ብሎ ማንበብ ይቻላል፤ ይህ አስተምህሮ ብሎ ያብራራው ባጭሩ መከራውን(ስቅለቱን) የሚቃወሙትን ወይም "ተሰቅሎ የተቸነከረው እርሱን የሚመስል ነው" የሚለውን ትምህርት ነው። እናም ይህ ትምህርት በእስልምና በኩል የሚገኝ እንደሆነ ዲያቆኑ ገልጿል። ቁርኣንም "አልገደሉትም አልሰቀሉትምም" ካለ ቡኃላ እንደተመሰለባቸው ይገልጽልናል፦ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا [ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 157 ] «እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡ መልካም እንደ ራሳችሁ የቤተ-ክርስቲያን መምህር ገለጻ ይህ አስተምህሮ በእስልምና በኩል የሚገኝ ከሆነ የሚገርመው ነገር ይህ አስተምህሮ 1ደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ይገኝ ነበር። "አግናጢየስ[A.D. 30–107.]" የተባለው የቤተ-ክርስቲያን አባት የእየሱስ መከራውን(ስቅለቱን) መመሰል ነው የሚሉ አካላት እንዳሉና እነዚህን አካላትም እንደሚቃወማቸው በጹሁፉ ውስጥ ይገልጻል፦ "ነገር ግን አምላክ የሌላቸው፣ ይኸውም የማያምኑት ሰዎች እንደሚሉት፣ እርሱ መከራን የተቀበለ የመሰለ እንደሆነ..." (The Epistle of Ignatius to the Trallians Chapter X) ይህ ቁርኣን ከገለጸው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው ቁርኣንም "ለእነርሱ ተመሰለ" ነው የሚለው፤ እነዚህ አግናጢየስ እየተቻቸው ያሉት አካላትም መከራው *የተመሰለ* እንጂ እውነተኛ እንዳልሆነ እንደሚያምኑ ጽፏል። ይህ አይነቱ አስተምህሮ ደግሞ በእስልምና በኩል እንደሚገኝ እነሆ የራሳችሁ ክርስቲያን መምህር መመስከሩን ከላይ አይተን መጥተናል። ይህ ማለት አሁንም "እስልምና" በራሳችሁ የቤተ-ክርስቲያን መምህር እንዲሁም ቅዱስ በምትሉት በቤተ-ክርስቲያን አባት መሠረት በ1ደኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያለ ሐይማኖት መሆኑን አረጋገጥን ማለት ነው! ይህ ግልጽ በሆነ መልኩ ኢስላም ከነቢዩ ሙሐመድ  በፊት እንዳለ በገዛ ብዕሮቻቸው የመሰከሩት ነው። በተመሳሳይ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎችን መትተናል... "የእየሱስ አለመሰቀል" ከአንደኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሚታመን ጉዳይ እንጂ ነቢዩ ሙሐመድ  ከመጡ ቡኃላ የመጣ አዲስ አስተምሮ አለመሆኑን መገንዘብ ቀላል ነው። https://t.me/AGAINST_CHRISTIANITY

  • 4 док.3395иС AGAINST_CHRISTIANITY

    🔺ግድያ እና ክርስትና! በክርስትና ካህንን የሰደበ ያቃለለም እንደሚገደል ያውቃሉ? እግዚአብሔር ያስነሳው ቆስጠንጢኖስ የተባለ ክርስቲያኖችን የሚወድ ንጉስ ካህናትን የሚሰድቡ አካላት በሞት እንዲቀጡ ሕግ አውጥቶ ነበር፦ "ለካህናትም የሚሰድቧቸውና የሚያቃልሏቸው በሞት ሳይቀር ይቀጣሉ በማለት ተገቢው ክብር እንዲሰጣቸው አደረገ።" (ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋሪያዊ ሕይወቱና ትምህርቱ በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ገጽ 11) አውዱ ላይ ጸሃፊው "ተገቢው ክብሬ እንዲሰጣቸው አደረገ" ማለቱ እነሱን ለሰደበ የሞት ቅጣት መሰጠቱ ተገቢ ተግባር እንደሆነ ያሳያል። ይህ የሞት ቅጣት በብሉይ ኪዳን እንደቀረ ለሚያስቡ የዋህ ክርስቲያኖች ጥሩ ትምህርት ይሆናል..። በእውነቱ አንድ ካህን ተሰደበ ብሎ የሞት ቅጣት ሰዳቢው ላይ የሚያስተላልፍ ሃይማኖት ይዞ ለትችት መቅረብ አግባብ ነው ወይ? .. https://t.me/AGAINST_CHRISTIANITY

  • [ዘረኝነት]~ክፍል 2~ እንደ ባይብል ዲቃላዎች የእግዚአብሔር ግባኤ መግባት አይችሉም፦ ኦሪት ዘዳግም 23፤2 23፤2 ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። Pulpit Commentary ላይ እስከ አስር ትውልድ የሚለው *ለዘላለም* ማለት እንደሆነ ተብራርቷል፦ "To his tenth generation; i.e forever," (pulpit Commentary…

  • 19 нояб.2902иС Murad11145

    ባይብል ተጠብቋልን? _ክፍል ሁለት_ ወደ ክርስትናው ስንመጣ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የክርስትና ቀደምት ቅዱሳን አባቶችና ሊቃውንቶች በባይብል ዙሪያ ያላቸው አቋም ከሌሎች አባቶች ጋር ከመጋጨቱ በተጨማሪ የዛሬውን ባይብል ገደል የሚከት የጋራ አቋምም ነበራቸው። በክርስትና ታሪክ ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ አንድ ወጥ የሆነ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ባይብል እንደለለ ይታወቃል። ለምሳሌ ፕሮቴስታንቶች 66 ሲቀበሉ ኦርቶዶክሶች 81 ይቀበላሉ ካቶሊኮች ደግሞ 73 ይቀበላሉ። ነገር ግን ከነዚህ መጽሃፍት ውጪም የነበሩ እንደ አምላክ ቃልነት ተቀባይነት የነበራቸው መጽሐፍት ነበሩ፤ ከነዚህ መካክል ሆነው ደግሞ በጥንት አባቶች ተቀባይነት ያልነበራቸው ነበሩ። ለምሳሌ ዛሬ ላይ ሦስቱም የክርስትና ሴክቶች በሚቀበሏቸው ባይብል ዘንድ የማይገኘውን "የሔርማስ መልዕክትን" ->ኢራንየስ(2 Century)[1] ->ቀሌሚንጦስ ዘአሌክሳንደሪያ(2-3 Century)[2] ->ጠርጡሊያኖስ(2-3 Century)[3] ልክ እንደ መለኮታዊ ራዕይ ወይም እንደ Scripture አድርገው ይቀበሉት ነበር። /በዝርዝር ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንመልከት/ የአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ ዛሬ ባይብል ላይ የለሉትን እነ Didache'ን ጨምሮ የሔርማስ'ን መልዕክት ልክ እንደ በመለኮታዊ መሪነት እንደተጻፉ ነበር የሚያያቸው፦ "በግብፅ፤ የአዲስ ኪዳን ቀኖና ታሪክ ከእስክንድርያው ቀሌምንጦስ (ከ217 ዓ.ም በኋላ ያረፈ) በፊት የነበረው ሁኔታ ግልጽ አይደለም። ቀሌምንጦስ፣ ምናልባት ከያዕቆብ፣ ከ2ኛ ጴጥሮስ እና ከ3ኛ ዮሐንስ በስተቀር፣ በኋላ ላይ የተወሰኑትን 27ቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ ያውቃቸው እንደነበር ይገመታል። ሆኖም ለሌሎች በርካታ መጻሕፍትም ከፍተኛ ሥልጣን (ተቀባይነት) ሰጥቶ ነበር። ከእነዚህም መካከል እንደ ዲዳኬ (Didache)፣ ሄርማስ እረኛው (Shepherd of Hermas)፣ የጴጥሮስ ስብከት (Kerygma of Peter) እና ምናልባትም 1ኛ ቀሌምንጦስን የመሳሰሉትን በመለኮታዊ መሪነት እንደተጻፉ (divinely inspired) አድርጎ ይቆጥራቸው ነበር።" (New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.30-1) ኢራንየስ'ም(2 Century) የእብራዊያን መልዕክትን የጳውሎስ መሆኑን አይቀበልም ነበር፤ ከአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ በተመሳሳይ የሔርማስ መልዕክትንም እንደ Scripture ነበር የሚቀበለው፦ "ወደ ፊልሞን የተላከውን መልእክት አይጠቅስም፤ እንዲሁም ወደ ዕብራውያን የተላከውን መልእክት ቢያውቀውም፣ ጸሐፊው ጳውሎስ መሆኑን አይቀበልም። 'እረኛው ሔርማስ' (Shepherd of Hermas) የተሰኘውን መጽሐፍ 'መጽሐፍ እንዲህ ይላል' (Scripture says) በሚለው አገላለጽ ያስተዋውቀዋል።" (New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31) Hippolytus'ም 21 የአዲስ ኪዳን መጽሐፍቶችን የሚቀበል ሲሆን ከመምህሩ ኢራንየስ በተመሳሳይ የእብራዊያን መልዕክትን የጳውሎስ እንደሆነ አይቀበልም ነበር ለእርሱ ይህ መጽሃፍ ቀኖናዊ አልነበረም፦ "የኢራንየስ ደቀ መዝሙር የሆነው የሮሙ ቅዱስ ሂፖሊተስ (በ235 ዓ.ም. ያረፈ)፣ የሁለቱን ኪዳናት ቅዱሳት መጻሕፍት 'የክርስቶስ ሁለት ጡቶች' ሲል ይጠራቸዋል፤ ይህም በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃል ውስጥ ያለውን የጠበቀ የምግብ (የምገባ) ግንኙነት ያመለክታል። የእርሱ አዲስ ኪዳን ቢያንስ 21 መጻሕፍትን ያካትታል። የዕብራውያንን መልእክት የጳውሎስ እንደሆነ አድርጎ ስለማይቆጥር፣ ለእርሱ ቀኖናዊ (የመጽሐፍ ቅዱስ አካል) አይደለም። [በጽሑፎቹ ውስጥ] ፊልሞንን፣ 2ኛ ወይም 3ኛ ዮሐንስን፣ ያዕቆብን ወይም ይሁዳን አይጠቀምም።" (New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31) በተጨማሪ Philip schaff'ም ጥንታዊ አባቶች "የሔርማስ መልዕክት" መለኮታዊ እንደሆነ እንደሚያምኑ ተናግሯል። ለምሳሌ ያክል ኢራንየስ፣ የአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ እንዲሁም አርጌንስ  የሔርማስ መልዕክት መለኮታዊ መሆኑን በጹሁፎቻቸው መግለጻቸውን አስፍሯል፦ "የጥንት ጸሐፊዎች መጽሐፉ በእርግጥም በመንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ ያምናሉ። ኢራኒየስ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ ይጠቅሰዋል፤ የእስክንድርያው ቀሌምንጦስ ስለ መጽሐፉ ሲናገር አባባሎቹ "መለኮታዊ" እንደሆኑ ይገልጻል፤ አርጌንስም ቢሆን፣ አንዳንድ አገላለጾቹ በአንዳንዶች ዘንድ ጥርጣሬን የሚያሳዩ ተደርገው ቢታዩም፣ እርሱ ግን "በመለኮታዊ አነሳሽነት እንደተጻፈ" ያለ ጥርጥር አስተያየቱን ይሰጣል።" (Fathers of the Second Century by Philip Schaff p.8) የሔርማስ መልዕክት 4ተኛ ክፍለ ዘመን ላይ እንደተጻፈ የሚገመተውና እጅግ ጠቃሚ ከሚባሉ የባይብል እደ-ክታባት መካከል የሚመደበው Codex Sinaiticus ውስጥም የሚገኝ ነው።[4] የMuratorian ቀኖናም እንደ New Catholic Encyclopedia 22/23 የአዲስ ኪዳን መጽሐፎች ብቻ ነው የያዘው(24 የሚሉም ምሁራኖች አሉ)፦ "በኢጣሊያ፤ ምናልባት ከ180 እስከ 190 ዓ.ም. ገደማ (ምናልባትም በሂፖሊተስ) የተዘጋጀው የሙራቶሪያን ፍራግመንት (Muratorian Fragment) ቀኖና፣ (ጸረ-ማርሲዮናዊ የሆኑትን የወንጌላት መቅድሞች ካልቆጠርን) የቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን ቀኖና ዝርዝር ነው። ይህም 22 (ወይም 23) የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ይዘረዝራል።" (New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31) ይህ የMuratorian Canon በተመሳሳይ ማለትም ልክ እነ ኢራንየስ እነ ሂፖላይተስ የእብራዊያን መልዕክትን እንደ ጳውሎስ መልዕክት እንደማይቀበሉት ሁሉ ይህ ቀኖናም የእብራዊያንን መልዕክት ከቀኖና ገለል ያደረገ ነበር።[5] 3ተኛ ክፍለ ዘመን አካባቢም ላይ የኖረው ጠርጡሊያኖስ የእብራዊያን  መልዕክትን አይቀበልም ነበር፦ "በአፍሪካ፣ ተርቱሊያን ከ2ኛ ጴጥሮስ እንዲሁም ከ2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስ በስተቀር ሁሉንም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ይጠቀም ነበር። ምንም እንኳን የዕብራውያን መልእክት በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውል ቢቀበልም፣ የጻፈው በርናባስ ነው በማለት ከቅዱሳት መጻሕፍት (ከቀኖና) ያስወጣዋል።" (New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.32) ታዲያ ይህ ሁሉ የቤተ-ክርስቲያን አባት እንደ አምላክ ቃል የተቀበለውን መጽሐፍ አሁን ማስወገድ ያስወገዱትን ደግሞ መቀበል የጤና ነው? ስጀምር "የዛሬውን ባይብል ገደል የሚከት የጋራ አቋምም ነበራቸው" ያልኩት ለዚህ ነው! የቤተ-ክርስቲያን ታላላቅ አባቶች፣ ሊቃውንቶች በዚህ መልኩ አሁን ካለው ባይብል ጋር ፈጽሞ የራቀ አቋም ነበራቸው የሚገርመው ልዩነታቸው ግዝፈቱ *በመጽሃፍት* ደረጃ ነበር የሚለያዩት። ከአሁኑ የባይብል ቀኖናዎች ጋርም እርስ በራሳቸውም ሲጋጩ ነው የኖሩት። ለዘመናት ምንም ወጥ ያልሆነ በገዛ ቅዱሳን አባቶቹና ሊቃውንቶቹ ዘንድ ውድቀትን መለያየትን ያስተናገደ መጽሐፍ እንደ ባይብል ማን አለ? ማንም!  1] Irenaeus Against Haer; 4.20.2 2] Clement of Alexandria Stromata; 1.17.29 3] Tertullian De Orat; 16 4] Fathers of the Second Century by Philip Schaff p.9 5] The text of New testament p.49 https://t.me/Murad11145

  • قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ [ ሱረቱ አል-አንዓም፣ - 14 ] «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ *የሚመግብ የማይመገብም* ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)Âť በላቸው፡፡ فَلِلَّهِ الْحَمْدُ رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَرَبِّ الْأَرْضِ رَبِّ الْعَالَمِينَ [ ሱረቱ አል-ጃሢያህ - 36 ] ምስጋናም ለአላህ ለሰማያት ጌታ ለምድርም ጌታ ለዓለማት ጌታ የተገባው ነው፡፡ ምስጋናም ለአላህ ለሰማያት ጌታ ለምድርም ጌታ ለዓለማት ጌታ የተገባው ነው። እኛ ሙስሊሞች *የሚመግብ የማይመገብ* የሆነ አምላክ እንጂ ሌላን አንይዝም[የሚመገብ አምላክም የለም]። አስተዋይና እውነትን ፈላጊ ክርስቲያኖች ሆይ እኛ የምንጠራችሁ *የሚመግብ የማይመገብ* ወደ ሆነው ኃያሉ አንድና ብቸኛው አምላክ አላህ ነው። ክርስትና የሚመገብን አካል ማምለክን የሚያስተምር ሃይማኖት ነው፦ “ተቀብሎም በፊታቸው በላ።” — ሉቃስ 24፥43 የሚመገብ አካል ከማምለክ ትላቀቁና ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት እስልምና መጥታችሁ ትድኑ ዘንድ የምን ጊዜም ጥሪያችን ነው። https://t.me/AGAINST_CHRISTIANITY

  • 18 нояб.1792иС AGAINST_CHRISTIANITY

    🔺የባይብል ብርዘት! ~ክፍል ሁለት~ የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ "በኤርምያስ የተባለው" በማለት በትንቢተ ዘካሪያስ የሚገኝን ጥቅስ አሳስቶ ጠቅሷል፦ “በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው፦ ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥”   — ማቴዎስ 27፥9 ይህ ክፍል ትንቢተ ዘካርያስ 11፥12-13 ላይ የሚገኝ ነው፦ ዘካርያስ 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹² እኔም፦ ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፤ ያለዚያ ግን ተዉት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። ¹³ እግዚአብሔርም፦ የተስማሙበትን የከበረውን ዋጋዬን በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው አለኝ። እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኖርሁት። 🖇እዚህ ክፍል ላይ ስህተቱን ለማረም የተደረጉ ተጨማሪ ሸፍጦችን፣ የቀደምት የቤተ-ክርስቲያንን ምሁራን ምስክርነት እንዲሁም የዘመኑ የምሁራንን ምልከታ እንመልከት! ፩፤ የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ የተሳሳተውን አሰቃቂ ስህተት ለማረም የተደረገ ሸፍጥ! ከ25 በላይ ምሁራን ባዘጋጁት NET bible ላይ የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ በትንቢተ ዘካርያስ የሚገኝን ጥቅስ በኤርሚያስ እንደሚገኝ አድርጎ ማቅረቡ ስህተት እንደሆነ የገባቸው አንዳንድ የባይብል ገልባጮች "ኤርሚያስ" የሚለውን ወደ "ዘካሪያስ" ቀይረው ተጨማሪ ቅጥፈትን እንደቀጠፉ። ለምሳሌ "ኮዴክስ 22" ዘካርያስ ብሎ መቅጠፉን፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ኤርሚያስ የሚለውን ስም በማስወገድ መቅጠፋቸውን እናነባለን።[1] *ታቲያን(2 Century)* እንዳዘጋጀው የሚታመነው የአራቱ ወንጌላት ስብስብ የሆነው እደ-ክታብም "Diatessaron of Tatian"ንም "ኤርምያስ" የሚለውን ክፍል በመተው ቀጥፏል[2]። ላለማንዛዛት እንጂ በጣም ብዙ የሆኑ እደ-ክታቦች ናቸው "ኤርሚያስ" የሚለውን ስም ያስወገዱት። ይህ በአጋጣሚ ረሱት ወይም "ዘካሪያስ" ወደ ሚል ስም ቀየሩት የሚለውን ማስረጃ ቢስ probability የሚዘጋ ነው። ይህም ጉዳይ ባይብል መበረዙን የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊም አሳስቶ መጥቀሱን ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው። ተሳስቶ ባይጠቅስ ኖሮ የባይብል ገልባጮቹም "ከኤርሚያስ" ወደ "ዘካሪያስ" የሚቀይሩበት ምክንያት አይኖርም ነበርና። ፪፤ ቀደምት የቤተ-ክርስቲያን ምሁራን ምስክርነት ክፍሉ የሚገኘው ትንቢተ ዘካሪያስ ላይ እንደሆነና ያጣቀሰውም ከዘካሪያስ መጽሃፍ እንደሆነ የሚናገሩ! *ጄሮም(4-5 Century)* ጄሮም በባይብል ልዩነቶች ጉዳይ ሰፊ እውቀትና ልምድ ካላቸው ታላላቅ የቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንት መካከል ነው።በተጨማሪም የራሱን የሆነ የባይብል ትርጉምም ያዘጋጀ ለቤተ-ክርስቲያን ትልቅ ውለታ የዋለ የቤተ-ክርስቲያን ምሁር ነው። ይህ ሰው የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ ከኤርሚያስ እንዳላጣቀሰው ከዛካርያስ እንዳጣቀሰው አስረግጦ ይሞግታል።[3] ፫፤ የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ በኤርሚያስ እንደተጠቀሰ አድርጎ ያስቀመጠው ክፍል ትንቢተ ኤርሚያስ ላይ እንደማይገኝና ኮፒዎች ላይም ይሄን ስህተት ለማረም ቃላትን እንደለዋወጡ የተሰጠ የምሁራኖች ምስክርነት! *Metzger* ታዋቂው የNew Testament scholar Bruce M. Metzger እንዲሁ "ከኤርሚያስ" ወደ "ዘካሪያስ" የቀየሩትንም "ኤርሚያስ" የሚለውንም ስም ያስወገዱትን ብዙ እደ-ክታባት በዘረዘረበት ጹሁፉ ላይ የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ ያጣቀሰው ጹሁፍ "ኤርሚያስ" ላይ እንደማይገኝ ተናግሯል።[4] *NET bible* ይህ ባይብል እንደገለጽኩት ከ25 በላይ ምሁራኖች የተሳተፉበት ባይብል ሲሆን የማቴ ወንጌል ዘካሪያስ ላይ የሚገኝ ጥቅስን ከኤርሚያስ እንደተገኘ አድርጎ መጥቀሱ ገልባጮች ባይብልን ለተጨማሪ ብርዘት እንዳጋለጡት ያጋለልጣል፦ "The problematic citing of Jeremiah for a text which appears to come from Zechariah has prompted certain scribes to alter it. Codex 22 has Ζαχαρίου (Zacariou, “Zechariah”) while Φ 33 omit the prophet’s name altogether." (NET BIBLE FIRST EDITION p.1863) እነዚህ ምስክርነቶችና የእደ-ክታቦቹ ቅሰጣዎች የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ ከዘካርያስ አይደለም ያጣቀሰው(i.e የማቴ ወንጌል ጸሃፊ አልተሳሳተም) የሚለውን የአንዳንድ አላዋቂ ክርስቲያን ሃሳብ(ሙግት ማለት ይከብዳል) አመንምኖና አኮስምኖ የሚቀር ነው። በእርግጥም በባይብል እደ-ክታባት መካከል አንድን ስህተት ለማረም ሌላ ቅጥፈት መቅጠፍ የተለመደ ነው። ይህ አይነቱ የባይብል ገልባጮች አካሂያድ ባይብል ይበልጥ መበረዙን የሚያሳይና አምላካዊ ጹሁፍ እንዳልሆነም የሚገልጽ ነው። 🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚🪚 1]NET BIBLE FIRST EDITION p.1863 2]ANF09 (The Diatessaron of Tatian p.196) 3]Commentary On matthew 4.27 4]Texual Commentary On The Greek New testament By Bruce M. Metzger p.66-7 https://t.me/AGAINST_CHRISTIANITY

  • йоС пОдписи

  • 🔺ባሪያ በክርስትና! ከክርስትና አሰቃቂ ሕጎች መካከል አንድ ሰው ባሪያ ገዝቶ ቢኮበልልበትና ሲኮበልል ቢያገኘው ወደ ቤት መመለሾ አይጠበቅበትም በቃ ገድሎ ሥጋውን ለውሾች መስጠት ነው የሚጠበቅበት ይህንንም ቢያደርግ ነፍሰ ገዳይ አይባልም አስቀድሞ በገንዘቡ ስለገዛው፦ "10 *ነቢዩ ሲራክ እንደ ተናገረ* ሰው ከቤቱ ወርቅ ብር አውጥቶ የሚያገለግለው ባሪያ ይገዛል ያ ባሪያ ሲኮበልል ጌታው ቢያገኘው ወደ ቤቴ መልሼ ልግዛው አይልም ገድሎ እንዲበሉት ሥጋውን ለውሾች ይጥለዋል እንጂ። 11 *ከገደለውም ቡኋላ ነፍሰ ገዳይ አይባልም አስቀድሞ በገንዘቡ ገዝቶታልና*.." (ድርሳነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ዘመስከረም 10) አሁን ቆይ ምን ይባላል በዚህ ልክ ክፋትና ጭካኔ? ምን ብዬ ልግለጸው ..ገድሎ ሥጋውን ለውሾች እስከመስጠት?..🌚 ይሄን ጉድ አይቶ ክርስትና ትክክል ነው ብሎ መከተል ልሹ ከባድ ነው። ማሳሰቢያ፦ይህ ድርሳን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ ነው! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ዘንድ ትልቅ ቦታ ከሚሰጠው አባት *ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ* ከተደረሱት ድርሳኖች መካከልም ነው[1]። ድርሳናት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፉ ናቸው[2]። ያው ምንም አይነት መጽሐፉን የማውገዝ እርምጃ ተቀባይነት የለውም ለማለት ያክል ነው🌝። 📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎 1] ድርሳነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ መግቢያ ገጽ 5 2] አምደ ሃይማኖት ገጽ 37 https://t.me/Christianity_With_History

  • 🔺የሎዶቅያ መልዕክት? ጳውሎስ ወደ ሎዶቅያ የላከው በፊት ላይ ተቀባይነት የነበረው ዛሬ ላይ ግን የተወገደ መልዕክት እንደነበረው ያውቁ ኖሯል? ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ በላከው መልዕክቱ ላይ ወደ ሎዶቅያ የላከው መልዕክት እንዳለ ጽፏል፦ “ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።”   — ቆላስይስ 4፥16 አንዳንድ የእንግሊዘኛ ትርጉሞች በግልጽ "የጻፍኩላቸውን መልዕክት/the letter I wrote to them" ብለው አስቀምጠውታል፦ Colossians 4:16 (NLT) "After you have read this letter, pass it on to the church at *Laodicea* so they can read it, too. And you should read the letter I wrote to them." አውዱ ላይ "የጻፍኩላቸው" እያለ ያለው ለሎዶቅያ እንደሆነ ግልጽ ያለ ፍንትውም ያለ ጉዳይ ነው። ይህም ለሮሜ፣ ለኤፌሶን፣ ለቆሮንጦስ ሰዎች ለሌሎችም መልዕክታትን ጽፎ እንደነበረው ሁሉ ለሎዶቅያ ሰዎችም መልዕክትን ጽፎላቸው እንደነበረ ማሳያ ነው። "Commentary Critical and Explanatory on the Whole Bible" የተባለ የባይብል ማብራሪያም "ከሎዶቅያ የምትገኘውን መልዕክት" የሚለውን የጳውሎስን ንግግር "the Epistle which I wrote to the Laodiceans" በማለት *ለሎዶቅያ(ሰዎች) የጻፍኩት መልዕክት* ማለቱ እንደሆነ አብራርቶታል። በዚህ ብቻ አያበቃም ይህ መልዕክት በጣም ብዙ በሆኑ ከ6-15ተኛ ክፍለ ዘመን በሚገኙ የባይብል እደ-ክታባት ውስጥ የሚገኝ ነው[1]።ለአብነት ያክል በVictor አማካኝነት Capua ላይ የተዘጋጀው Codex Fuldensis(541-546 A.D) ውስጥ ይህ መልዕክት ይገኛል[2]&[5]። በጣም የሚገርመው ነገር ኤጲፋንየስ የተባለው የ4ተኛ ክፍለ ዘመን የቤተ-ክርስቲያን አባትም ይሄንን መልዕክት የጳውሎስ መሆኑን አጽድቆታል[3]።በተጨማሪም ኤጲፋንየስ የሎዶቅያ መልዕክትን ከጳውሎስ መልዕክታት መካከል 15ተኛ አድርጎ እንደመደበው ታዋቂው የNew Testament scholar የሆነው Bart D. Ehrman ያረጋግጣል[4]። ይህ መልዕክት በዋናነት በሁለተኛው የኒቂያ ጉባኤ(787 CE) ላይ ውድቅ ተደርጓል። ሆኖም በጉባኤ ደረጃ ውድቅ ከተደረገ ቡሃላ ለልሹ በብዙ የባይብል እደ-ክታባት ላይ ተካቷል፤ German bibles ከሉተር በፊት ተካቷል, Czech Bibles ላይ በቆላስይስ እና በ1ደኛ ተሰሎንቄ መልዕክት መካከል ከአስራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ተካቷል[5]። እንግዲህ ይህ መልዕክት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተቀባይነት ነበረው በተለይ በምዕራብ የተከበረ መልዕክት ነበር፤ በትርጉሞች ሳይቀር ተካቶ የነበረ ነበር። ይህ ከሆነ አሁን ማስወገድ ምን አስፈለገ? ይህ የሚያሳየን ባይብል እጅግ ሲበዛ ተዓማኒነት የጎደለው መጽሐፍ መሆኑን ነው፤ ማንም ተነስቶ የሚጨምርበት የሚቀንስበት የሆነ መጽሐፍ መሆኑን ያሳየናል። ሲያሻቸው የጳውሎስ ጹሁፍ አድርገው ይቀበሉታል ከሌሎች የባይብል ክፍሎች ጋር አካተው ቅዱስና የፈጣሪ ቃል ከሚሏቸው ጹሁፎች መካከል ያስቀምጡታል፤ ሲያሻቸው አሽቀንጥረው ይጥሉታል ይህ የሚያሳየው የፈጣሪ መልዕክት ነው ተብሎ የሚታሰበው ባይብል ላይ በዘመናት ውስጥ ሲጨመርበት ሲቀነስበት እንደኖረ ነው። ወጥ የሆነም ባይብል እንዳልነበረ አሁንም እንደለለ አለም አቀፋዊ ሐቅ ነው። በፊት ላይ እንደ ፈጣሪ ቃል ሲነበቡ የኖሩ አሁን በጉባኤና በተወሰኑ ሰዎች አማካኝነት የተወገዱበት ባይብል በምንም ሂሳብ ተዓማኝ ሊሆን አይችልም! 📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎 1] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.798 2] The Text Of The New Testament p.108 3] The panarion of Epiphanius of salamis Book 1 p.315 4] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.799 5] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.800 https://t.me/Christianity_With_History

  • እየሱስ ለምን አላማ መጣ? መልስ ከእየሱስ፤፦ የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ፦ “ኢየሱስም፦ የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ አለ።” — ዮሐንስ 9፥39 እየሱስ የሚያዩ እንዲታወሩ ነው የመጣው🫤!Âż https://t.me/Christianity_With_History

  • ... ወዙ እየተንጠፈጠፈ ወደ ጸለየ አካል እንደ መጸለይ የሚያስገርም ነገር አለ? ሉቃስ 22 ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ ⁴³ ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው። ⁴⁴ በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ። ወዙ በምድር ላይ እስኪወርድ ድረስ የጸለየ አካልን በምንም መልኩ ማምለክ አግባብ ሊሆን አይችልም! https://t.me/Christianity_With_History

  • [ጠንቋዩ የኢየሱስ ልጅ?] "ባር ኢየሱስ" ወይም "የኢየሱስ ልጅ" ተብሎ የሚጠራ ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ እንዳለ ታውቃላችሁ? እንግዲያውስ ክፍሉ ይኸውና አንብበው ይፍረዱ፦ “ደሴቲቱንም ሁሉ እስከ ጳፉ በዞሩ ጊዜ፥ "በርያሱስ" የሚሉትን *ጠንቋይና *ሐሰተኛ *ነቢይ የሆነውን አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኙ፤” — ሐዋርያት 13፥6 Acts of the Apostles 13:6 13:6 διελθοντες δξ την νΡσον αχρι παφου ευρον τινα Οιγον ψευδοπροφητην ιουδαιον ω ονοΟι "βαριησους" በአማርኛው "በርያሱስ" ብለው ያስቀመጡት የግሪኩ ቃል "ባርኤሱስ" "βαριησους" ማለት ሲሆን ባር እና ኤሱስ ከሚሉ ቃላት የተዋቀረ ሲሆን ኤሱስ ማለት በጥቅሉ ኢየሱስ ማለት ነው፤ ቃሉ በጥቅሉ "የኢየሱስ ልጅ" ማለት ነው። እሩቅ ሳንሄድ የእንግሊዘኛ ትርጉሞች BarJesus ብለው አስቀምጠውታል፦ “And when they had gone through the isle unto Paphos, they found a certain sorcerer, a false prophet, a Jew, whose name was "Barjesus":” — Acts 13:6 (KJV) □እየሱስ የፍጡር ስም መሆኑን አምናችሁ የእየሱስን ፍጡርነት መቀበል ይሻላችሁዋል ወይስ እየሱስ ጠንቋይ ልጅ እንዳለው ታሪክን ተጣርሳችሁ ታምናላችሁ? https://t.me/Christianity_With_History

  • “*ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል*፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ *የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ #ልጆችህን እረሳለሁ።*” — ሆሴዕ 4፥6 ..

  • በዚች አጭር እና ትንሽ እድሜዬ እንደ ጋዛዊያን ጽኑ፣ ጀግናዎች፣ ግፍን የተቋቋሙ፣ በገዛ ወንድሞቻቸው ሳይቀር የተከዱና የተረሱ ሕዝቦች አይቼ አላውቅም። የሚሆነው ነገር በሙሉ ያማል! ዱዐ እናድርግላቸው!

  • 19 окт. 2025 Đł.28323иС AGAINST_CHRISTIANITY

    🔺ገራሚው ሕግ! ክርስቲያኖች ግንባራችሁ ላይ "አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ" የሚል ጻፉ ተብለው እንደታዘዙና ያልጻፈ ካለ ቤታቸው ይበረበርና ይቀጡ እንደነበረ ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ? ክፍሉን ሙሉውን አንብቡት ግራ እጅና ቀኝ እጅ ላይ ሁሉ የሚጻፍ ረጃጅም ጹሁፍ ታዞ ነበር። ምንጭ፦ "የኢትዮጵያ ታሪክ ገጽ 158" Hhh እኔ ምለው ይሄን ረጅም ስም የሚይዝ "ግንባር" አለ ይሆን❔ https://t.me/AGAINST_CHRISTIANITY