𝑨𝒃𝒅𝒖𝒍𝒌𝒆𝒓𝒊𝒎 𝑫𝒆𝒗'𝒔
Статистика𝑨𝒃𝒅𝒖𝒍𝒌𝒆𝒓𝒊𝒎ᴰᵉᵛ'ˢ Learn at https://t.me/Abdulkerim_WebDev/90 Welcome to Abdulkerim Web Development | AI | Tech Insights | Coding Tips. Stay updated with the latest trends!
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 240
- 1/48двое суток
- 275
- 1/72трое суток
- 296
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ከአስር_አመታት_ተሞክሮየ #ክፍል-አንድ ምንም ይሁን አንድ ጉዞ ስትጀምሩ አብሯችሁ የሚጓዝ ሰው ሲኖር ፍጥነታችሁን ያሻሽለዋልዋል። ሰው አዋዋዩን ይመስላል ይባላል አይደል? ሯጮች እንኳን ሪከርድ ማሻሻል ሲፈልጉ pacemaker ይጠቀማሉ። ወደ ዋናው ጉዳይ ስንገባ እኛ ስምንት አመት በስንቅ ስንማር ትልቁ ጉልበታችን የነበረው ህብረታችን ነበር። እዚሁ ቻናል ላይ ያሉት እነ ዶክተር ልደት፣ ሰለሞን ገድፌ ሀይስኩል ስንማር በተፎካካሪነትም በጓደኝነትም ትልቅ ተጽዕኖ አሳድረውብኛል። ጎበዝ ነኝ ብየ እንዳላስብ እነሱ አሉ፣ ሰነፍ እንዳልሆን እነሱ ጋር መፎካከር አለብኝ። ዩኒቨርስቲ እያለንም አሁን ኮሪያ የሚገኘው ፕሮፌሰር ሀምዲ አብዱራህማን፣ አሚር አህመድ፣ ሬድዋን ጀማል፣ አሸናፊና መሰል ከኔ በጣም የተሻለ አቅም ያላቸው ጓደኞች ከጎኔ በመኖራቸው ያተረፍኩት ብዙ ነው። ወደ ስራ አለም ስገባም አዲሳለም ታፈረ ትልቅ ምሳሌየ የነበረ ባለሙያ ነው። ይሄን ሁሉ የምለው የምትመርጡት ጓደኛ ምን ያክል ተጽኖ እንደሚያሳድርባችሁ ለመግለጽ ያክል ነው። አዳር ተሰባስበው አብርሆት ቤተመጽሃፍት የሚያድሩትን ልጆች ሳይ ነገ የሚኖራቸውን እድል የተሻለ ለማድረግ እንቅልፍን መሰዋት፣ ተመሳሳይ ህልምን መጋራትና አብሮ መጓዝ መቻልን መልመድ መቻላቸውን ሳይ ለነሱ ደስ ይለኛል። አዋዋላችሁን፣ የምታነቡትን ኮንተንት በደንብ አስባችሁበት ቢሆን እመክራለሁ @birhan_nega
Follow human needs, not temporary trends.
💼 በአንድ Junior Developer ውስጥ Recruiters በእርግጥ ምን ይመለከታሉ? Recruiters ሁሉንም ነገር የሚያውቅ Developer እየፈለጉ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ❌ሁልጊዜ አይደለም! Junior Developer ስትሆኑ፣ Recruiters ብዙ ጊዜ የሚመለከቱት ከዚህ የበለጠ ተግባራዊ ነገር ነው፦ መገንባት፣ መማር እና ችግር መፍታት ትችላላችሁ? እነዚህ 5 ነገሮች እንድትለዩ ሊያደርጓችሁ ይችላሉ፦ 1️⃣ ትክክለኛ Projects > Certificates Certificate አንድ ኮርስ እንደጨረሳችሁ ያሳያል። አንድ Project ግን በእርግጥ ምን መስራት እንደምትችሉ ያሳያል። ቀላል ቢሆንም እንኳ አንድ ነገርን ስሩ/ገንቡ፦ 🌐 Website 📱 Small App 🤖 AI-powered Tool 📊 Data Dashboard 2️⃣ የተደራጀ GitHub Profile GitHub የኮድ አሰራራችሁን እና የምትማሩበትን መንገድ ሊያሳይ ይችላል። ጥሩ Projects ምረጡ፣ አደራጁዋቸው፣ ግልጽ README ጻፉ። እና እባካችሁ… Projects ሁሉንም “final-final-v2” ብላችሁ አትሰይሙ። 😅 3️⃣ Problem-Solving Skill ሁልጊዜ መልሱን ማወቅ አይጠበቅባችሁም። እና ይሄ ችግር አይደለም። አስፈላጊው ችግሩን፦ → መረዳት → ወደ ትናንሽ ክፍሎች መክፈል → መረጃ መፈለግ → Solutions መሞከር → ከስህተቶች መማር መቻላችሁ ነው። 4️⃣ Communication በቴክኒክ ጥሩ መሆን ብቻ በቂ አይደለም። የገነባችሁትን Project በቀላል ቋንቋ ማስረዳትም መቻል አለባችሁ። Projects ስታስረዱ ይህንን መዋቅር ሞክሩ፦ “ይህን Project የገነባሁት ___ ምክንያት ነው። ትልቁ ችግር የነበረው ___ ነው። የፈታሁትም ___ በመጠቀም ነው። ተጨማሪ ጊዜ ቢኖረኝ ___ አደርግ ነበር።” 5️⃣ የመማር ፍላጎት Technology ሁልጊዜ እየተቀየረ ነው። Junior Developer ስትሆኑ ሁሉንም ነገር ማወቅ አያስፈልጋችሁም። የማታውቁት ነገር ሲያጋጥማችሁ፣ እንዴት መማር እንዳለባችሁ ማወቃችሁ ነው አስፈላጊው። 💡 ግባችሁ Senior Developer መስሎ መታየት አይደለም። ግባችሁ ለመማር፣ ለማደግ እና የተሻለ Developer ለመሆን ዝግጁ የሆነ Junior Developer መሆናችሁን ማሳየት ነው። 🚀 Build. Learn. Improve. Repeat. @riseuptech
ኮድ መጻፍ የሃሳብ እና የመርህ ስራ እንጂ የጉልበት ስራ አይደለም። አእምሮ ሲደክም ቀላል Logical Errorዎችን እንኳን ማለፍ የተለመደ ነው። ያስቸገረንን አንድ ስራ ለሰዓታት ስክሪን ላይ አፍጥጦ ከመቀመጥ፣ ኮምፒውተሩን ዘግቶ መተኛት የተሻለ መፍትሄ ያመጣል። አእምሯችን በእንቅልፍ ሰዓት መረጃዎችን ስለሚያቀነባብር፣ ጠዋት ንጹህ አእምሮ ይዘን ስንነቃ ትላንት ማታ የጠፋብን መፍትሄ በቀላሉ ቁልጭ ብሎ ይታየናል። Software Engineer መሆን የረጅም ርቀት ሩጫ (Marathon) እንጂ የአጭር ርቀት (Sprint) አይደለም። ያለ በቂ እረፍት በተከታታይ መስራት መጨረሻው ለአእምሮ ዝለት (Burnout) ይዳርጋል። በቂ እንቅልፍ ማግኘት በሙያው ለረጅም አመታት ስኬታማ ሆኖ ለመቀጠል ዋናው ቁልፍ ነው። እኔም ብዙ እንደማልተኛ እናንተም እኔም እናውቃለን፣ ማስታወሱ ግን ተገቢ ነው ብየ አስባለሁ።
🍽 Coding ከRestaurant ጋር ምን ግንኙነት አለው?🤔 በመጀመሪያ ስናየው ምንም የማይገናኝ ሊመስል ይችላል። ግን አንድ Website እንዴት እንደሚሰራ በRestaurant ምሳሌ ብንመለከት በጣም ቀላል ይሆናል። የምትወዱትን ሬስቶራንት 🍽 አስቡ... 👨🍳 Backend የሬስቶራንቱ ኩሽና ነው። ከዓይን ውጭ ያለው ሁሉም ስራ እዚያ ይሰራል፤ ምግብ ይዘጋጃል። በተመሳሳይ ሁኔታ በዌብ አፕሊኬሽን ውስጥ Backend መረጃን ያስተናግዳል፣ ሎጂኩን ያከናውናል እና ሁሉንም ከጀርባ ያስተዳድራል። 🧑🍽 Frontend ደግሞ የመመገቢያው ቦታ ነው። ደንበኛው የሚያየውና የሚጠቀምበት ሁሉ እዚህ ነው። በድረ-ገጽ ወይም በሞባይል መተግበሪያ ውስጥ የምታዩት ገጾች እና ዲዛይኖች ሁሉ Frontend ናቸው። 🧑💼 API ደግሞ አስተናጋጁ (Waiter) ነው። ትዕዛዛችሁን ከጠረጴዛ ወደ ኩሽና ያደርሳል፣ ከዚያም የተዘጋጀውን ምግብ መልሶ ያመጣል። በፕሮግራሚንግም API በFrontend እና Backend መካከል ጥያቄ (Request) እና መልስ (Response) ያስተላልፋል። 📋 API Endpoints የምግብ ዝርዝር (Menu) ናቸው። በሜኑው ላይ ያለ እያንዳንዱ አማራጭ አንድ አገልግሎትን ይወክላል። ለምሳሌ፦ 🛍 ምርቶችን ማየት (View Products) 🔐 መግባት (Sign In) 🛒 ትዕዛዝ መስጠት (Place an Order) 👤 ፕሮፋይልን ማስተካከል (Update Your Profile) 📦 Database የማከማቻ ክፍል ነው። በሬስቶራንት ውስጥ እቃዎችና ግብዓቶች እንደሚቀመጡበት ማከማቻ፣ Database ደግሞ የተጠቃሚዎችን መረጃ፣ የምርቶችን መረጃ፣ ትዕዛዞችን እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያከማቻል። 💡 ምግብ ሲያዝዙ የሚካሄደው ሂደት ሁሉ በተመሳሳይ በዌብሳይት ይከናወናል፦👇 Frontend ➜ API ➜ Backend ➜ Database ➜ Backend ➜ API ➜ Frontend ይህ ብዙ ዘመናዊ ድረ-ገጾችና የሞባይል መተግበሪያዎች የሚሰሩበት መንገድ ነው! 💚 በRiseUp Tech ውስብስብ የቴክኖሎጂ ሀሳቦችን ከዕለታዊ ህይወት ምሳሌዎች ጋር በማያያዝ ለሁሉም ቀላል እና ግልጽ እናደርጋለን። 🚀 እንደዚህ ያሉ ቀላል፣ ተግባራዊ እና ለጀማሪዎች ተስማሚ የኮዲንግ ትምህርቶችን ለማግኘት RiseUp Techን ይከተሉ! 💬 ቀጣዩን በዕለታዊ ህይወት ምሳሌ እንድናብራራው የምትፈልጉት የቴክኖሎጂ ርዕስ ምንድን ነው? በኮመንት አጋሩን! 👇 @riseuptech
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
@SoloDevChronicles built EthioDeploy, a very easy way to start deploying your sites. Think Vercel but slightly diff architecture and also allows payments in birr. This took a long time in the making. Congrats to brook on this, not only for his own progress but for us as a community - this is a milestone!! It's got automatic stack detection, preview deployments, Managed PostgreSQL and Redis, Custom domains, Built-in analytics and so much more. This's the first version, so much is yet to come. Super excited! #CommunityShowcase #EthioDeploy @Dagmawi_Babi
To get money -> you need skills. To gain skills -> you need learning. To start learning -> you need passion. To turn passion into action -> you need effort. To sustain effort -> you need consistency. Agree? ©
የ Mathematics ሙሉ ኮርስ በ 2 ሰዓት ብቻ ለመስራት ደፍሪያለሁ 😊 Yeah... I did it. AI የሚጀምሩ ልጆች የሚጠይቁኝ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምን ያክል Math ያስፈልጋል የሚል ነው። Yeah... AI በ Math ነው የተሰራው። ስለዚህ እንዲትጀምሩት ሙሉ mathematics ዘርፎችን ቲዮረቲካሊ ሄጀበታለሁ። ከዚህ ተነስታችሁ በ ዋናነት 4ቱን ዋና ዋናዎቹ ደሞ በራሳችሁ ብትሂዱበት ታተርፋላችሁ! - Linear Algebra - Calculus - Probability and Statistics - Optimization theories. እነዚህን ካደማችሁ በቂ ነው። ቀጣይ ብዙ ኢትዮጵያውያን Ai Engineers እናያለን። ይሄኛውን የማትስ ኮርስ ግን ማንኛውም ሰው ቢያየው ይጠቀማል። Maths ሲባል የምትጠሉ ሰዎች እራሱ ይሄን ቪድዮ ካያካችሁ በኋላ በ ፍቅሩ ትወድቃላችሁ! Btw...የ ስንት አመት ኮርስን በ 2 ሰዓት ለማሳጠር በጣም ከባድ ነው። እኔ ይሄን ቪድዮ እንደ ታች ክላስ የተማራችሁትን እንደ ክለሳ ክላስ አስቡት! እስኪ እዩት!.... 👇👇👇 https://youtu.be/wa65bGkElzg
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи