𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
Статистикаስለ ቴክኖሎጂ እና እስልምና በቻልኩት አቅም አሳዉቃለሁ። በነፃ ለመማር (Frontend web development) 👉 t.me/abukiweb/615 አላማችን: 👉 t.me/abukiweb/88 ኮምፒዉተር ለመግዛት 👉 t.me/Abuki_Computer ዌብሳይት ለማሰራት፡ 👉 t.me/abukiweb/583 ለጥያቄና ለአስተያየት 👉 @Abukiweb_bot
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 36
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Технологии
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 246
- 1/48двое суток
- 1 427
- 1/72трое суток
- 1 540
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሞባይል ባትሪያችን ሲድክም እንደሚያሳስበንና እንደምንጨነቀው ሁሉ ... ለነፍሣችንም፣ ለኢማናችንም ከዚያ በላይ ልንጨነቅ ይገባል፡፡ ብዙ ነገራችን አይናችን እያየ ተንደርድሮ ወደ ዜሮ ሲወርድ ዝምብለን አንመልክተው፤ እስኪያልቅ ድረስም አንጠብቀው፡፡ ቶሎ ብለን ቻርጅ ላይ እናድርገው፣ እንሙላው፡፡ ወደነበረበት እንመልሰው፡፡ ተስፋ ስንቆርጥ፣ ስንወድቅ፣ ስንደክም፣ ስንጠፋ፣ ስንሳሳት፣ ኃጢኣት ስንሠራ፣ ስንታመም፣ ስንቆስል፣ ራሣችንን በራሣችንን እናክም፡፡ ብሥራት፣ ተወኩል፣ ኢማን፣ የቂን፣ ተስፋ፣ ቁርኣን፣ ሶላት፣ ተፋኡል፣ መልካም እሳቤ፣ ዚክር፣ ዒባዳ፣ ሶደቃ፣ ብርታት፣ ዱዓ፣ ጥንካሬ፣ እጅ አለመስጠት፣ ከደጋጎች ጋር መዋል፣ ማንበብ፣ ማስተንተን፣ በየዕለቱ ራሣችንን የምንሞላባቸው የዕለት ተዕለት ቻርጀሮቻችን ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ስንጎድል ዝምብለን ራሣችንን አንመልከት፣ ስንወርድ እስክንሞት ድረስ አንጠብቅ፡፡ ሰባሐል ኸይር Abx
የወጣትነት ሁለት ገፆች ~ ወጣትነት ፀጋ ነው። ለስራም ሆነ ለእውቀት ከየትኛውም የእድሜ ክልል በተለየ መነሳሳት የሚኖርበት ምቹ ጊዜ ነው። ወጣትነት በባህልም ይሁን በእምነት የመጡ ብልሹ ውርሶችን ለማራገፍ፣ የተዛነፉ ትርክቶችን ለማቃናት የተሻለ ድፍረትና ወኔ የሚገኝበት እድሜ ነው። ወጣቶች በኢስላም ታሪክ በተለያዩ የአለም አፅናፋት የእውቀትን ችቦ የለኮሱ የእውቀት ቀንዲሎች፣ የጥጋበኞችን እብሪት ያስተነፈሱ የነብር ጣቶች፣ በተለያዩ ዘርፎች ላይ አለምን በመልካም ያነቃነቁ የለውጥ ሞተሮች፣ ታሪክ በደማቅ ብእር የሚያወሳቸው አሻራዎቻቸውን ለትውልድ ያሻገሩበት የእድሜ ክልል ነው። ወጣትነት ሌሎችም በዋጋ የማይተመኑ በርካታ ውድ ፀጋዎች አሉት። በሌላ በኩል ወጣትነት በጥንቃቄ ካልያዙት ራስን፣ አልፎ ሌሎችንም የሚበላ እሳት ሊሆን ይችላል። በወጣትነት ውስጥ በእድሜና በተሞክሮ የሚገኝ ልምድ የለም። የእውቀት ማጠር ይጠበቃል። መንቀዝቀዥ ወይም የስክነት መቅለል፣ ጥሬነት ወይም የብስለት ማነስ፣ በተለያየ ዘርፍ ጤነኛ ያልሆነ ወሰን ያለፈ ድፍረት ወይም ጀብደኝነት፣ ራስን አለማሸነፍ፣ አደጋ ላይ የሚጥል ጉጉት፣ ስሜታዊነት፣ ... ይጎላበታል፣ ወጣትነት። በወጣቶች የተቀሰቀሱ ወይም ወጣቶች ፊታውራሪ የሆኑባቸው ዳፋቸው ሺህ አመታትን አቋርጦ ለዛሬም የተረፉ ብዙ ፈተናዎች ደርሰዋል። በወጣቶች ታላላቅ ኸሊፋዎችና በጀነት የተመሰከረላቸው እንቁዎች ህይወታቸው ተቀጥፏል። እልፍ አእላፍ የኡማው ብርቅየ ፍሬዎች አልቀዋል። ሃገራት ፈርሰዋል። የዑሥማን ግ.ድ. ያ ፣ የኸ.ዋ.ሪ.ጅ ንቅናቄ፣ የዘመናችን የተ^ ክ^ ፊ^ ር ጥንስስና መስፋፋት፣ ... ላይ የጉርምስና ግለት ድርሻው ከባድ ነበር። ሌላው ቀርቶ የዑሥማኒያ (የኦቶማን ተርክ) አገዛዝ ራሱ በከማል አታቱርክ ኦፊሻሊ መፍረሱ ከመታወጁ በፊት አውሮፓ ተምረው በመጡ ወጣቶች ሴራ ቀድሞውኑ ጣእረ ሞት ላይ ደርሶ ነበር። እነዚህ ጥራዝ ነጠቅ ወጣቶች "ኸሊፋዎቹን" በራሳቸው እስከመቀየር፣ ጥርስ የሌለው ውሻ አድርገው እስከ ማንገላታት ደርሰው ነበር። ብዙ ሰው ይህንን እውነታ አያውቅም። ስለ ኦቶማን ተርክ አገዛዝ የሚያወራው ቡድናዊ አላማ ያነገቡ አካላት የሚያቀርቡትን የሂደቱን የመጨረሻ ክፍል ብቻ ነው፣ ያውም በተዛነፈ መልኩ። ይህንን ማወቃችን በወጣትነት የሚገኘውን ኸይር በወጣትነት ዘመን የሚመጡ ሸሮች እንዳያጠፉት ለመጠንቀቅ ይረዳል። ዑመር ብኑል ኸጧብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ለአንዱ ወጣት እንዲህ ይሉታል፦ «قد يكون في الرجل عشرة أخلاق، تسعة منهن حسنة وواحدة سيئة، فتفسد الواحدة التسع، فاتَّقِ طيرات الشباب». "በአንድ ሰው ላይ አስር የስነ ምግባር ቀንዘሎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ዘጠኝ መልካምና አንድ መጥፎ። ያቺ አንዷ ቀንዘል ዘጠኞቹን ልታጠፋ ትችላለችና የወጣነት ጥሬነቶችን ተጠንቀቅ።" [ሸርሑል ዑምደህ፣ 5/22] #ከደጋጎቹ_ቀዬ = https://t.me/IbnuMunewor
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
ካወቅኩህ ጊዜ ጀምሮ ... አንተን መውደድ፣ የወደዱህን መውደድ፣ የወደድክልኝን መውደድ፣ ካንተ የሆነውን ሁሉ መውደድ፣ ሥራዬ ሆኗል። ያ ረብ። ኢላሂ ለአፍታ እንኳን ቢሆን እኔን ለኔ አትተወኝ እጠፋለሁ ። ሰባሐል ኸይር Abx
የሚደረስባቸው ግቦች መቅረጽ፦ ከአቅማችን በላይ የሆኑ እጅግ የተለጠጡ ግቦች መቅረጽ ላለአስፈላጊ ጭንቀት ይዳርጉናል። የምንፈልገውን ውጤት ከማምጣት ይልቅ እራሳችንን እንድንወቅስና እንድንፀፀት ያደርጉናል። የምንቀርጻቸው ግቦች አቅማችንን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው። በዙ ጊዜ ቁጭ ብለን ስናስብ በአዕምሮአችን የሚመጣው ሀሳብ፣ በ24 ሰዓት ብዙ ነገር ማከናወን እንደምንችል ነው። ይህ ደግሞ ከእውነታው ይርቃል። በጣም የተለጠጡ እና ከአቅማችን በላይ የሆኑ ግቦች ለውጤት ከማነሳሳት ይልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ። ብዙ ጊዜ ያለንን ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ዕውቀት እና የመሳሰሉት ሀብቶችን ያላገናዘቡ ዕቅዶች ስለምናቅድ፣ ከዕቅዳችን አንድ ሶስተኛውን እንኳን ማከናወን ከባድ ይሆንብናል። ስለዚህ በልካችን ልንደርስበት የምንችላቸውን ግቦች በመቅረጽ ለስኬት መስራት ይኖርብናል። ይህም ጭንቀትን አርቆ መነቃቃትን ፈጥሮ ለበለጠ ስኬት ያነሳሳናል ኢንሻአላህ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
⌨️ HP EliteBook 835 G8 ⚙️ Processor: Ryzen 5 PRO 5000 Series AMD Ryzen 5 PRO 5650U up to 4.2GHz 6 Cores 12 Threads L3 Cache: 16 MB (Comparable with intel core i5 11th generation) 🎮 Graphics: Radeon™ Graphics For ultra-smooth, stunning visuals 📧 RAM: 16GB DDR4 💽 Storage: 512GB NVMe SSD 🖥 Display: 14.1” FHD 1080p Sharp & vibrant visuals 🤖 Battery: Up to 5+ hours All-day productivity and ✨ Key Features: 🎧 Audio: HD Stereo Speakers Crystal clear sound 💡 Keyboard: White LED Backlit Work in the dark with ease 🛡 Security: Fingerprint Scanner Best for… 🖼 Creatives – Smooth design & photo & video editing 🎓 Students – Study, stream & submit with ease 🔗 Professionals – Fast, secure & office-ready 💼 Business users – Perfect for multitasking & meetings ✈️ Travelers – Slim, light & long battery life 💵 Price: 78,000 Birr ➡️ለማዘዝ እና ለበለጠ መረጃ በውስጥ አናግሩኝ ⬇️⬇️⬇️ @Abukii_Tech @Abukii_Tech ከፈለጋችሁ ደዉላችሁ አናግሩኝ 📞 Call 0920808168 #0920808168 ያሉበት ቦታ እናደርሳለን 🛫😀 Delivery Available✅ Join & Share✅ t.me/Abuki_Computer t.me/Abuki_Computer
አንዳንድ ቀን ቀኑን ሙሉ ስሮጥ እውልና ደክም ብሎኝ እገባለሁ ። ሰውነቴን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ በቁሜ እወድቃለሁ። ድፍት ብዬ አድራለሁ። የማታው ድካም ቶሎ ስለማይለቀኝ ከመሬት ያጣብቀኛል። ቀን ይለወጣል፣ ሕይወትም አትቆምምና ዳግም እታገላለሁ ... ለመነሳት፣ እጅ ላለመስጠት ቀና ለሰላት ለኑሮ ዱዓ እያረኩ እነሳለሁ ። ጌታዬ ሆይ ውሎዬን አሳምርልኝ፣ ሪዝቄን አስፋልኝ፣ ቤተሰቤን ጠብቅልኝ፣ ወዳጅ ዘመዴን ሁሉ በእዝነትህ እይልኝ በተለይ በስደት ያሉትን። ዱንያ ከባድ ናት። የትናንቱ ድካም ሳይለቀን ለዛሬው አጀንዳ ደግሞ እንነሳለን፣ ለመኖር መታገል በመታገል መኖር። እኛ እናልቃለን እንጂ ዱንያ ሐጃዋ አያልቅም። አለመታገል ደግሞ ዋጋ ያስከፍላ። ሰባሐል ኸይር የምወዳችሁ። ታገሉ። ABX
አዎን ገንዘብ ወሣኝ ነው፡፡ ዲናችንም ቢሆን ድህነትንና ደካማነትን አይመክርም፡፡ ዛሬ ላይ በተለይ ኢማን ተዳክሞ ቁሳዊ ነገሮች ትልልቅ ዋጋ ባገኙበት ሰዓት ይዞ መገኘት መልካም ነገር ነው፡፡ ኢማን በሌላቸው ሰዎች ዘንድ፤ ያለዉና የሌለው ሰው በእኩል ዐይን እየታየ አይደለም፡፡ ቁሳዊነት በነገሰባት ዓለም፤ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ ቦታ አላቸው፡፡ ገንዘብ ከሌለህ በድሮ ጓደኞችህ ጭምር ትገፋለህ፡፡ - ስልክህ ቶሎ አይነሳም፤ ንግግርህ ለጆሮ አይስብም፣ ወሬህ ዉሃ አይነሳም፣ ቀጠሮህ አይከበርም፣ ሽምግልናህ አይደመጥም ~ውዱ ነቢያችን የኸድጃ ገንዘብ እንደጠቀመኝ የማንም አልጠቀመኝም ይላሉ፡፡ የሚስታቸው። እነ ኸሊፋ ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን በገንዘባቸው የሙስሊሙን ጦር ታድገዋል፡፡ ታላቁ የዒልም እና የሐዲሥ ሰው ዐብዱላህ ኢብኑ አል-ሙባረክ ሀብታም ነጋዴ ነበሩ፡፡ ዒልም ፈላጊዎች ዐይናቸው ወደ ዓለማዊ ጉዳይ እንዳያማትርና ሥራቸው ዒልም ብቻ እንዲሆን ብለው በከፍተኛ ሁኔታ ይደጉሟቸው ነበር፡፡ ትልቅ ስፖንሰር ሺፕነት ይሏል ይህ ነው፡፡ ለዲን የሚሠራን ሰው ከጀርባ ሆኖ ማሠራት፡፡ አንዳንዴ ራስህን ለማስከበርና ለእልህም ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል!! t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan
ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል ! የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡ “ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡ የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡ “የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” “ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” “ አሏህን ያዝ ሰበቡን አድርስ የተሻለ ነገር ታገኛለህ ፤ ሁሉም ነገር ከጥረት ጋር መሆኑን ላፍታም ቢሆን አትዘንጋ ” ©
To get money -> you need skills. To gain skills -> you need learning. To start learning -> you need passion. To turn passion into action -> you need effort. To sustain effort -> you need consistency. Agree? ©
To get money -> you need skills. To gain skills -> you need learning. To start learning -> you need passion. To turn passion into action -> you need effort. To sustain effort -> you need consistency. Agree? ©
ጊዜው ነጉዶ በማህበረሰቡ ዘንድ "ትልቅ ሰው" ተብለን ልንጠራ እንችላለን። ነገር ግን ይህ "ትልቅነት" አብዛኛውን ጊዜ በፍላጎታችን የመጣ ሳይሆን፣ ትከሻችን ላይ በወደቀው የህይወት ሀላፊነት የተጫነብን ጭንብል ነው። በየቀኑ የምንሸከመው ሸክም፣ የምንወስደው ውሳኔ፣ የምናስበው ስለ ነገ እና የምንጨነቅለት የቤተሰብ፣ የትምህርት ወይም የስራ ነገር በግድ ረጋ እንድንልና አዋቂ እንድንመስል ያስገድደናል። ነገር ግን ከዚህ የሀላፊነት እና የቁምነገር ጭንብል ጀርባ፣ እያንዳንዳችን ስሜት ውስጥ ገና ያልጨረስነው፣ ያልተጫወትነው እና ያልጠገብነው ህጻን ልጅ አለ። ሀላፊነት እንጂ ትልቅ ያደረገን ፣ ያልጨረስነው ልጅነት አለን። t.me/abdu_rheman_aman
ወዳጄ ! ሕይወት ለጨለመበት መብራት ለመሆን ሞክር፣ መንገድ የጠፋበትን እጁን ይዘህ ምራ፣ ሐዘን የገባዉን አጽናናው፣ የደከመዉን ደግፈው፣ ግራ የገባውን መውጫ አሳየው፣ ውድቀቱ የበዛውን በተስፋ ሙላው። ሰውን ግማሽ መንገድ ላይ ትተህ አትጥፋ .. ከቻልክ እጁ ይዘህ አንሳው፣ ወይም ምርኩዝህን አቀብለው፣ ካልሆነም መልካም ቃላትን በመለገስ እርዳው። የሚገርመው ይህ ሁሉ ምንዳ ያለው ሶደቃ መሆኑ ነው። ሌሎችን ስናኖር እንኖራለን፣ ሌሎችን ስንደግፍ እንቆማለን፣ ለሌሎች ስናበራ ይበራልናል። ፈገግ በልና የሌሎችን ፈገግታ መልስ። ABX
ሰሞኑ ትንሽ ያልተመቻቸልኝ ነገር ስላለ ነው በ አላህ ፍቃድ በቅርቡ እመለሳለሁ!
የሚወድ ልብ ያላችሁ፣ ሰውን ለመውደድም የማትቸጋገሩ፣ ቀልባችሁ ንፁህ የሆነ፣ ውስጣችሁ ጥላቻ የሌለ ሁሉ እንኳን ደስስስስ አላችሁ ። "ሙእሚን የሚወድም የሚወድድም/ በቀላሉ የሚለምድም የሚለመድም ነው። " ብለዋል ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ. መውደድ ወጪ አያስወጣም፣ አያለፋም። የሰውን ድካም የምትጋሩ፣ ሸክማቸውን የምታቀሉ፣ የቤት ሥራዎቻቸውን የምትካፈሉ፣ የማትከብዱ የማታካብዱ ቀለል ያለ ተግባቢ ሰው ሁኑ ይላል እስልምናችን። የጀነት መንገዱም ይኸው ነው። ABX
ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት የሕክምና ዶክተሮች አሉ? ወደ 20,000 ገደማ። ይሄም 0.15 ሐኪም ለ 1,000 ሰዎች ማለት ነው። የሚመከረው መጣኔ 2.3 ለአንድ ሺህ ሰዎች ነው። Ok, 2 ሐኪም ለ 1,000 ጥሩ ነው ብለን እናስብ። እዚህ ላይ ለመድረስ አሁን ያሉንን የሐኪሞች ቁጥር በ 13.33 እጥፍ መጨመርና 266,000 ሐኪሞች መድረስ አለብን። ይህ ቁጥር ራሱ የሕዝብ ቁጥራችን ከ 130 ሚሊየን በላይ አያድግም ብለን አስበን ነው። በብዙ ምክንያቶች በተለይ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ሕክምና ለማጥናት ፍላጎት የሚያሳየው ተማሪ ቁጥር እየቀነሰ ይመስለኛል። (በእርግጥ በጥናት የተደገፈ ነገር የለኝም)። ባልተለመደ ሁኔታ በሜዲካል ሳይንስ የተመረቁ ወጣቶች ሕክምናውን ትተው ወደ ሌላ ቢዝነስ መግባት የጀመሩም አሉ። አገር ጥለው ለመሔድ ልባቸው የተንጠለጠለውንም ጨምሩበት። እና የሐኪሞች ቁጥር እንዳይቀንስ አትሰጉም? Assume that ያሉት ሐኪሞች ሁሉ ደመወዝተኞች ናቸው እንበል። የሐኪሞች ደመወዝ ዝቅተኛው 60,000 ብር ከፍተኛው 80,000 ብር ቢሆን ቅር የሚለው አለ? የለም! በአማካይ 70,000 ብር ቢሆን X 12 ወራት X 20,000 ሐኪሞች = የዓመት ደመወዝ 16.8 ቢሊየን። በዚህ ዓመት በሙስና ያጣነው almost 100 ቢሊየን። እና 50 ፐርሰንት ሙስናዎችን በየዓመቱ ማስቀረት ብንችል ሌላ ተጨማሪ ወጪ ሳይጠይቅ የ3 ዓመት ከምናምን የሐኪሞችን ደመወዝ መሸፈን እንችል ነበር። ያለምንም የበጀት ጫና! ተጨማሪ በጀት ቢያስፈልግ እንኳን 16.8 ቢሊየን ምን አላት? Non-productive ለሆኑ ነገሮች ከምናወጣው ወጪ አንፃር? እ? ጤናው የተጠበቀ ዜጋ ያላት ሐገር በሁሉም ረገድ አትራፊ ናት። -------------------------- ማሳሰቢያ: - ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን አላካተትኩም። - ቁጥሮቹ በኔ assumption ብቻ የተሰሉ ናቸው። ጥናት ወሳኝ እንደሆነ እርረዳለሁ። - 'ሐኪሞች ብቻ ለምን? እኛስ' የሚሉትን ከግምት አላስገባሁም። ሁሉም ሙያ fair ክፍያ ቢገባውም ከሕክምና ጋር ማወዳደር ተገቢ ነው ብዬ አላስብም። Priority! ✍️Hawlet
የትኛውን ሼር (አክሲዮን) ልግዛ? ውዱን ወይስ ርካሹን? ወይስ ጀማሪውን? 🤔📈 ======== አክሲዮን ገበያ ውስጥ ስንገባ ብዙ ጊዜ ግራ የሚገባን ነገር ቢኖር የትኛውን ኩባንያ እንምረጥ የሚለው ነው። አዲሱን እና ጀማሪውን ኩባንያ? ወይስ ስሙ የገነነውን ውዱን? ወይስ ዋጋው ርካሽ የሆነውን? ✅ ጀማሪውን፡ ለጊዜው በፍጹም አትሞክሩት፤ ምክንያቱም ገና በገበያ ውስጥ አልተፈተነም (High Risk)። ✅ ውድና ርካሹን ግን፡ ቀለል ባለ የነጋዴ ሒሳብ እንሥራው! የራይድ (Ride) መኪና ምሳሌ እንውሰድ፦ በ1.5 ሚሊዮን ብር ቪትዝ (Vitz) እና በ3 ሚሊዮን ብር ኮሮላ (Corolla) ገዛችሁ እንበል። ሁለቱንም ራይድ ብታሠሯቸው፡ 👉 ቪትዙ በቀን 1,500 ብር ያመጣል። 👉 ኮሮላው በቀን 2,000 ብር ያመጣል። ታዲያ የቱ ያዋጣል? እስቲ በፋይናንስ ስሌት (በዓመት 365 ቀናት ይሠራል ብለን) እናስላው፦ 1️⃣ የማካካሻ ጊዜ (Payback Period)፡ (ዋናውን ገንዘብ ለመመለስ የሚፈጀው ጊዜ) ቪትዝ፡ 1,500,000 ብር ÷ 1,500 ብር = በ1,000 ቀናት (ወይም 2 ዓመት ከ9 ወር ገደማ) ውስጥ የገዛችሁበትን ዋጋ ይመልሳል። ኮሮላ፡ 3,000,000 ብር ÷ 2,000 ብር = በ1,500 ቀናት (ወይም 4 ዓመት ከ1 ወር ገደማ) ይፈጅበታል። የቪትዙ የገዛንበትን ዋጋ ለመመለስ በእጅጉ ይፈጥናል! **** 2️⃣ የትርፍ ምጣኔ (Earnings / Dividend Yield)፡ (ዓመታዊ ትርፉ ከዋናው ካፒታል አንጻር ሲሰላ) ቪትዝ፡ በቀን 1,500 x 365 = በዓመት 547,500 ብር። (547,500 ÷ 1,500,000) x 100 = 36.5% ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔ አለው። ኮሮላ፡ በቀን 2,000 x 365 = በዓመት 730,000 ብር። (730,000 ÷ 3,000,000) x 100 = 24.3% ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔ አለው። በ3 ሚሊዮን ብር አንድ ኮረላ ከመግዛት፣ በዚያው ብር ሁለት ቪትዝ መግዛት ይሻላል የምንለው ለዚህ ነው! 2 ቪትዞች በቀን 3,000 ብር (በዓመት 1,095,000 ብር) ሲያመጡ፣ 1ዱ ኮሮላ ግን የሚያመጣው 2,000 ብር (በዓመት 730,000 ብር) ብቻ ነው። 📊 ይህ ከአክሲዮን ገበያ (Securities Market) ጋር እንዴት ይገናኛል? አንድ አክሲዮን "ውድ" ወይም "ርካሽ" የሚባለው በመሸጫ ዋጋው (Share Price) ብቻ አይደለም፤ ወደ ኪሳችን ከሚያስገባው የጥሬ ገንዘብ ፍሰት (Cash inflow) እና ከሚያመጣው የትርፍ ክፍፍል (Dividends) አንጻር እንጂ! አንዳንድ ጊዜ ዋጋው ርካሽ የሆነ አክሲዮን (እንደ ቪትዙ) ከፍ ያለ የትርፍ ምጣኔ (High Dividend Yield) ሊኖረው እና የፈሰሰበትን ካፒታል በፍጥነት ሊመልስ (Short Payback Period) ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ስሙ የገነነ እና ውድ የሆነ አክሲዮን (እንደ ኮሮላው) የሚያመጣው ትርፍ ከዋጋው አንጻር አነስተኛ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አክሲዮን ስትገዙ የኩባንያውን ስም ገናናነት ወይም የአክሲዮኑን ዋጋ መወደድ ብቻ አትዩ። "በስንት ገዝቼ ስንት ይመልስልኛል? በስንት ጊዜስ ዋናውን ገንዘቤን እመልሳለሁ?" የሚለውን በተግባር አስሉ። ከእጅ ቶሎ መውጣት ፣ ለዋስትና ማስያዝ፣ Time value of money, interest rate የሚሉ ሌሎች ማመሳከሪያዎችን አላስገሁም:: ======= AKN: ትክክለኛ ትምህርት፣ እውነተኛ ንብረት፣ የፋይናንስ ነፃነት (Right Education. Real Assets. Financial Freedom.) ©
👉🎴ቴሌግራም በመጠቀም እንዴት ህይወታችንን እንመራለን? 👉🎴ቴሌግራም ላይ እንዴት ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን እንችላለን? 👉🎴ቴሌግራም ላይ እንዴት ገቢ እናገኛለን? 👉🎴ቴሌግራም ላይ እንዴት ወጥ ሆነን ስራችን እንሰራለን። 👉🎴ቴሌግራም ከመደበሪያነት እንዴት ወደ እንጀራነት እንለዉጠዋለን? 👉አሁን ላይ የብዙ ወጣቶች ህይወት በቴሌግራም እየተቀየረ ነዉ!! ግን እንዴት? 👉ብዙ ሰዎች ብዙ ተከታይ አፍርተዉም…