Abu Menal || አቡ መናል
Статистикаበአቡ መናል የሚሰጡ ደርሶች እና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ። t.me/AbuMenal
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 12
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 305
- 1/48двое суток
- 349
- 1/72трое суток
- 376
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
🏷️...በመከራና በችግር ጊዜ መታገስ ጥሩ ነው፤ ከእርሱ ይበልጥ በላጭና ከባድ የሚሆነው ደግሞ አላህ ክልክል (ሐራም) ካደረገው ነገር ራስን መግታትና መታገስ ነው። የሐራም ስሜትን መታገስ የነፍስን ነፃነት ያጎናጽፋል።...🏷️ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ 📚 ሹዐብ አል-ኢማን 10 : 40 ❤️ t.me/AbuMenal
🔖..ቁርአን የወረደው እንድናነበው ብቻ ሳይሆን እንድናስተነትነውና በህይወታችን እንድንተገብረው ነው፤ ቁርአንን ማንበብ የልብ መድኃኒትና የህይወት መሪ ነው። ቁርአንን በምናነብበት ጊዜ አላህ በቀጥታ እኛን እያናገረን እንደሆነ ማሰብ አለብን። ትእዛዝ ሲመጣ እንታዘዝ፣ ክልክል ሲመጣ እንራቅ፣ የጀነትና የእሳት ዜና ሲነገር ደግሞ ተስፋና ፍርሃታችንን እናድስ። በየቀኑ ከቁርአን የተወሰነ ድርሻ (ዊርድ) ይኑርህ፤ ቁርአንን የተወ ሰው ህይወቱ በጨለማና በጭንቀት የተሞላ ይሆናል። በቂያማ ቀን ቁርአን ለአንባቢውና ለተጋሪው አማላጅ ሆኖ ይመጣል፤ 🔖አንብብ፣ ደረጃህንም ከፍ አድርግ🔖 ይባላል። ቁርአንን በቃሉ የሸመደደና በእሱ የሰራ ሰው ወላጆች በቂያማ ቀን ከፀሐይ ብርሃን በበለጠ የሚያበራ ዘውድ ይጫንላቸዋል። ስለዚህ ቁርአንን የህይወትህ የዘወተር አጋር አድርገው። ...🔖 ኢብኑል ጀውዚ 📚 ሲፈቱ'ሰፍወህ 1:284 🌟 t.me/AbuMenal
🔖..የልብህ መረጋጋትና ..ሕይወት ያለው መሆኑ የሚለካው ከአላህ ዚክር ጋር ባለው ቁርኝት ነው። የአላህ ዚክር የሌለበት ልብ ልክ ውኃ እንደራቀው ዓሣ ነው፤ ውኃ ያጣ ዓሣ መሞቱ እንደማይቀረው ሁሉ፣ አላህን የማያስታውስ ልብም በድንቁርናና በመዘናጋት ይሞታል። ብዙ ሰዎች የዱንያ ጭንቀትና ድብርት ያጠቃቸዋል፤ ምክንያቱን ሲፈልጉም የውጭ ነገሮችን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እውነተኛው ችግር ያለው ከውስጥ ነው—ልብ ከአላህ ዚክር በመራቁ። አላህን ማስታወስ (ዚክር ማድረግ) ሲባል በምላስ ብቻ ማወደስ ሳይሆን፣ በልብ አላህን ማወቅ፣ ውሳኔውን መውደድና በሁሉም እንቅስቃሴ ውስጥ እሱን መፍራት ነው። በዱንያ ላይ ትልቅ ሀብት ቢኖርህ እንኳ ልብህ ከዚክር ጋር ካልተያያዘ ደሃ ነህ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በዱንያ ምንም ባይኖርህ ነገር ግን ልብህ በዚክር የረጋ ከሆነ አንተ ሀብታም ነህ። ስለዚህ ምላስህንና ልብህን በአላህ ዚክር ሁልጊዜ እንዲረጥቡ አድርግ፤ አላህ 'እነሆ አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ' ብሏልና።..🔖 ኢብኑል ቀይም 📚አል ዋቢል አስ-ሰይብ: 63 🔶 t.me/Abu_Menal
ለፈገግታ .. " የሆነ ጊዜ ቲቪ ላይ ነው የሰማሁት ኡስታዝ ሲናገሩ ጃሚዓ ተመድበን እንደገባን ካፌ ገብተን በ ሹካ የሚበላ ምግብ አዘን የመጣልን ግን ማንኪያ ነበር እና ሹካ በ አረብኛ ምን እንደሆነ ስለማናቅ መናገር ከብዶን ማንኪያ "ሚልአቃ"እንደሚባል ትዝ ሲለን ምን አምጣልን አልን አለ "ሚልአቀቱል መቅዱዳ" #copy
በሰው ዘንድ ያለንን አማና በአግባቡ መጠበቅ የሙስሊም ዋና መለያ ነው። አላህ 🤍▫️..አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዝዛችኋል..▫️ ብሏል ሱረቱ አን-ኒሳእ: 58 ነቢም🤍 ▫️አማና የሌለው ሰው እምነት (ኢማን) የለውም▫️ ብለዋል ሙስነድ አሕመድ: 12383 ከዚሁ ጋር በተገናኘ አል ኢማም አሽ-ሻፊዒ ✏️▫️ታማኝነት የክብሮች ሁሉ መሰረት ነው▫️ ብለዋል 📚አዳብ አሽ-ሻፊዒ ወመናቂቡህ፣ 94 🔶 @AbuMenal
"⚪️ከሰዎች ሁሉ በላጩ ፦ የነቢን ﷺ እና የልዩ ሰሐቦቻቸውን መንገድ የተከተለ ሰው ነው..." ኢብኑ ረጀብ |📚 አል-መሐጃህ ፊ ሰይሪ አ'ዱልጃህ (49) ▫️ t.me/Abu_Menal
"በሙስጠለሑል-ሐዲስ ፈን አንድ ኪታብ እኔ የሰጠሁትን ደርስ በትክክል የሚማር እና ከዚያም ፈተና የሚወስድ ሰው ኢጃዛ እሰጠዋለሁ።"...ብለዋል ሸይኽ አ'ራ-ዚሂይ حفظه الله ሸይኻችን በሙስጠለሁል-ሐዲስ ያስተማሯቸው ደርሶች በዚህ ቅደም ተከተል ብትቀሩ መልካም ነው 1. አል-ሙኽተሰር ፊ ሙስጠላሕ አህል አል-አሰር (የሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ ድርሰት)። https://t.me/AliAlrazihi/2759 2. ቱሕፋቱል ሙብተዲ ቢሸርሒ አል-በይቁኒያ (እንዲሁም የሸይኹ ድርሰት)። https://t.me/AliAlrazihi/8664 3. አል-ሙቂዛህ የዘሀቢይ። https://t.me/AliAlrazihi/8945 4. ኢኽቲሳሩ ዑሉም አል-ሐዲስ። https://t.me/AliAlrazihi/9457 5. ኑዝሐቱ አን-ነዘር። https://t.me/AliAlrazihi/5866 6. ደዋቢጡ አል-ጀርሕ ወት-ተዕዲል። https://t.me/AliAlrazihi/3791 7.ሸርሕ ዐሊል አት-ቲርሚዚ – በኢማም ኢብን ረጀብ። https://alrrazihi.al3ilm.net/13237 منقوله -من صفحة أخى وأستاذي عبدالرزاق باجي خفظه الله
📗 ተውጂሀት ወተንቢሀት ደርስ 1 🎤በወንድም አቡ መናል በተሻለ ጥራት ➡️ t.me/AbuMenal
📗 ተውጂሀት ወተንቢሀት ደርስ 1 🎤በወንድም አቡ መናል በዝቅተኛ ጥራት ➡️ t.me/AbuMenal
Live stream finished (47 minutes)
3:00 ነው የምንጀምረው
ይሰማል?
ልንጀምር ነው ግቡ 💬