tgindex
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ Ministry of Revenues Adama Branch

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ Ministry of Revenues Adama Branch

Статистика
@AdamaRevenuesMoRsанглийский

#Ministry_of_Revenues #Adama_Branch_Office ☎️ 0222113474

Последний пост
18 нояб.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 117
0 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 988
20 постов
Вовлечённость
357,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 18 нояб.2 83486

    без подписи

  • без подписи

  • 6 июл. 2025 г.3 3211124из Taxation_in_Ethiopia

    በገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ ላይ የተዘጋጀ መግለጫ Note on Income Tax Proclamation Amendment #የንግድ_ስራ_ገቢ_ግብር #Income_Tax #አዋጅ_Proclamation #ማሻሻያ_Amendment @Taxation_in_Ethiopia

  • መመሪያ ቁጥር 1064/2017 የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣ መመሪያ Investment Incentives Directive No 1064/2025

  • የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከአዳማ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና ከከተማው ገቢዎች ጋር በመተባበር (በቅንጅት) በአዳማ ከተማና አካባቢው ለሚገኙ የሂሳብ ባለሙያዎች በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 (የተካተቱ አዳዲስ ለውጦችን) ፤የታክስ ሂሳብ መዝገብ አያያዝ ፤መመሪያ ቁጥር 8/2011 (የካፒታል ብቶችን በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ ስለሚከፈል ግብር)፤ በመመሪያ ቁጥር 188/2017 (የደረሰኝ አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ ማሻሻያ) እና ሌሎች ጠቃሚ የታክስ ህጎች ላይ በ23/07/2017 እና 24/07/2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት የስልጠና አዳራሽ ውስጥ ለመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡ ስለዚህ በአዳማ ከተማና አካባቢው የምትገኙ የሂሳብ ባለሙያዎች በዚህ ስልጠና ላይ እንድትሳተፉ እየገለጽን ይህ ስልጠና ለሂሳብ ባለሙያዎችም ሆነ ለግብር ከፋይ ደንበኞቻቸው በተለይም በግብርና ታክስ ዙሪያ ለሚነሱ ችግሮች መሠረታዊ መፍትሄ የሚሰጥና የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም የሂሳብ ባለሙያዎች በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እስከ ቀኑ 11፡30 በትኩረት እንድትሳተፉ በአጽንኦት እንገልጻለን፡፡ ይህ ጥሪ ለሁሉም የሂሳብ ባለሙያ እንዲዳረስ የሰማ ሰው ላልሰማ አንዲያስተላልፍ እናሳውቃለን፡፡ ከገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

  • 6 мар. 2025 г.3 29065из moreastaa

    ውድ ግብር ከፋዮቻችን የታክስ እንቅስቃሴ ለውጥ ላይ ከሆነ በመመሪያ 143 /2011 መሰረት ለውጥ የተካሄደባቸውን እንቅስቃሴዎች ያሳውቁ ማንኛውም ድርጅት ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የመተዳደሪያ ደንብ፣ የሽርክና ማህበር ስምምነት ወይም ሌላ የመመስረቻ ወይም የምዝገባ ሰነድ ቅጂ ለባለሥልጣኑ መቅረብ አለበት፡፡ እነዚህ ሰነዶች ላይ ማንኛውም ለውጥ ሲደረግ ድርጅቱ ለውጡ በተደረገ በ30 ቀናት ውስጥ ለውጡን በጽሑፍ ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ አለበት፡፡ ሀ. በንግድ ድርጅቱ ስያሜ ላይ የተደረገ ለውጥ፤ ለ. በድርጅቱ ስም የተመዘገበ፡- i. ቋሚ የንግድ ሥራ፣ የቢሮ እና የመኖሪያ አድራሻ ለውጥ፣ ii. በማምረቻ ቦታ ወይም ታክስ ከፋዩ በሚጠቀምበት መጋዘን ላይ የተደረገ የአድራሻ ለውጥ፤ iii. በፖስታ ወይም በመደበኛ እና በተንቀሳቃሽ ሰልክ፣ ፋክስ ወይም ኢ-ሜል አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤ ሐ. በዋነኛ የሥራ እንቅስቃሴው ወይም በቅርንጫፍ ወይም በንግድ ሥራው ዘርፍ ወይም መስክ ላይ የተደረገ ለውጥ፤ መ. በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ወይም የመመስረቻ ጽሑፍ ወይም የሽርክና ስምምነት ላይ የተደረገ ለውጥ፤ ሠ. በአክሲዮን ባለድርሻ አባላት ላይ የተደረገ ለውጥ፤ ረ. በድርጅቱ ወይም በታክስ እንደራሴው የባንክ ሂሳብ ወይም የባንክ ቅርንጫፍ አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤ ሰ.በታክስ እንደራሴው እና ከሚኒስቴሩ ጋር ግንኙነት በሚያደርግበት የኤሌክትሮኒክስ አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤ ሸ. በተመዘገበና በተከፈለ ካፒታል ላይ የተደረገ ለውጥ፤…………….. ሙሉን ለማግኘት ከላይ የተቀመጠውን መመሪያ ያንብቡ እናመሰግናለን !!

  • For further information join this channel via link:-https://t.me/tax12

  • 19 авг. 2024 г.3 8409из tax12

    ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን በተመለከተ ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም(የገቢዎች ሚኒስቴር) ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን በተመለከተ ከገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተላለፈ ሰርኩላር፡፡

  • https://t.me/tax12

  • ቀን 8/12/2016 ማስታወቂያ ለገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ግብር ከፋዮች በሙሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 እስከነ ማሻሻያው በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 የተተካ ሲሆን አዲሱ አዋጅ ከቀድሞ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ የተለያዩ ለውጦችን ይዟል፡፡ ከእነዚህ ለውጦች መካካል በድሮው የአዋጅ፤ደንብ፤መመሪያ እና ሰርኩላር ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ተደርገው የነበሩት የእቃና አገልግሎት አቅርቦቶች የተሻሩ መሆኑን አውቃችው በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 አንቀጽ 10 እና በአዋጁ አባሪ ሁለት በተያያዘው ከታክሱ ነጻ ተደረገው ከተዘረዘሩት አቅርቦቶች በስተቀር ሌሎች የእቃና አገልግሎት አቅርቦቶች ታክሱ የሚከፈልባቸው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ማሳሳቢያ፤- በአዲሱ አዋጅ ታክሱ የሚመለከታችው ግብር ከፋዮች 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት ቡድን ቀርባቹ ሪፖርት እንድታረጉ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ፡-ስ.ቁ 022-211-15-19 ወይም 022-211-43-34 TELEGRAM ADRESS; - TAX EDUCATION ADAMA LINK: - https://t.me/tax12 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ከታክስ ከፋዮች ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት ቡድን

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቅን ይመለከታል። ለሁሉም ግብር ከፋዮቻችን በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1157/2011 መሰረት የሂሳብ ጊዜ በማናቸውም የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የተከናወነ ሽያጭ ከብር 70 ሚሊዮን በላይ እያንዳንዱ ወር ፤ ከብር 70 ሚሊዮን በታች ለሆነ ታክስ ከፋይ 3 ወር ተብሎ የተተረጎመው በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጠር 1341/2016 መሰረት “የሂሳብ ጊዜ” በቀን መቁጠሪያ ሰነድ የተመለከተው እያንዳንዱ ወር ተብሎ የተተርጎመ በመሆኑ ከዚህ በፊት በየሶስት(3) ወሩ የተጨማሪ እሴት ታክስን የምታስታዉቁ ግብር ከፋዮቻችን በየወሩ መሆኑን አውቃችሁ የሃምሌ ወር 2016 የሂሳብ ጊዜን የምታስታውቁት ከነሃሴ 1/2016 እስከ ጳጉሜ 5/2016 መሆኑን አውቃችሁ በጊዜው እንድታስታውቁ እናሳስባለን።

  • የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ግብር ከፋዮቻችን በመመሪያ ቁጥር 1006/2016 ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ የእህል እና ጥራጥሬ ፣ የግብርና ግብአቶች እንዲሁም የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች/መጠጦችን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

  • ለማንኛውም የታክስ ዕውቀትዎን ለማስፋት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ https://t.me/tax12

  • ለገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ፅ/ቤት ግብር ከፋዮች በሙሉ

  • ማስታወቂያ ለመላው ግብር ከፋዮች በሙሉ ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓትን በመገንባት ላይ የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር የኢ-ፔይመንት የክፍያ ስርዓት የማስፋፊያ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህ መነሻ ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማሻሻያዎች በስራ ላይ የሚሉ መሆኑን ግብር ከፋዮቻችን እንድታውቁና የሚፈለግባችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ስንል እናሳወቃለን፡፡ የተደረጉ ማሻሻያዎች 1. በአንድ የዶክመንት (ሰነድ) ቁጥር በከፊል (partiale) እና በተደጋጋሚ ጊዜ (multiple times) ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚቻል መሆኑ፣ 2. ዘግይተው የሚደረጉ ክፍያዎች (late payments) ፍሬ ግብረ፣ ቅጣትና ወለድን ጨምሮ ለመክፈል የሚያስችል መሆኑ፣ 3. ውዝፍ ክፍያዎች፣ የኦዲት ውሳኔ የታክስ ክፍያዎች፣ የታክስ ዕዳ ክፍያዎች እና ሌሎች ክፍያዎችንም ለመክፈል ማስቻሉ፣ 4. ቅድሚያ ክፍያ(Advance payment) ለመክፈል የሚያስችል መሆኑ፣ 5. በወረቀት የሚያልቁ የታከስ ክፍያዎች በሲግታስ እንዲስተናገዱ ማስቻሉ፣ 6. የታክስ ውሳኔዎችና ሌሎች ማንኛውም አይነት ሰነዶች በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለግ/ከፋዩ ተደራሽ እንዲሆኑ ማስቻሉ እና 7. የሠራተኞች ዝርዝር መረጃ ለማስገባት እንዲያስችል መደረጉ ናቸው እንዚህን የተደረጉ ማሻሻያዎች በተሟላ መልኩ በስራ ላይ ለማዋልና በአግባቡ ተፈፃሚ ለማድረግ ግብር ከፋዮቻችን በዋናነት የሚከተሉትን ተግባራት ሊፈፀሙ ይገባል፡፡ 1. በትክክል የሚገኙበትንና የሚጠቀሙባቸውን ትክክለኛ የኢ-ሜይል አድራሻ እና የሞባይል ስልክ ቁጥር ለባለስልጣ መ/ቤቱ አንዲያሳውቁ፤ 2. ይህንኑ አረጋግጠው የሰጡትን የኢ-ሜይል አድራሻ እና የሞባይል ስልክ ቁጥር በአግባቡ እንዲጠቀሙበትና ዘውትር ከፍተው እንዲያዩ፣ 3. የኢ-ሜይል አድራሻ እና የሞባይል ስልክ ቁጥር ለውጥ ካደረጉም ወዲያው ለባለስልጣን መ/ቤቱ እንዲያሳውቁ፣ 4. ለኢ-ፋይሊንግ ያልተመዘገቡ ግ/ከፋዮች ትክክለኛውንና የሚገኙበትን የኢ-ሜይል አድራሻ እና የሞባይል ስልክ ቁጥር በሲግታስ ላይ ሊያስመዘግቡ የሚገባ መሆኑን፣ ይህን ያላደረጉ ግ/ከፋዮች የታክስ ክፍያውን መፈፀም የማይችሉ መሆናቸውን፣ 5. ግ/ከፋዮች ከዚህ በፊት በኢ-ፋይሊንግ አሳውቀው የሚከፍሉበት የዶክመንት(የሰነድ) ቁጥር አሁን ላይ ለታክስ ክፍያ የማያገለግሉ(የማይጠቅም) መሆኑን ሊገነዘቡ የሚገባ መሆኑ፣ 6. ከፍያ የሚፈፀሙበት የዶክመንት(የሰነድ) ቁጥር በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) በሞባይል ስልካቸው ላይ የሚደርሳቸው ሲሆን፣ ግ/ከፋዮች ይህንን የተላከውን ቁጥር ተጠቅመው የታክስ ክፍያቸውን በቴሌ ብርም ሆነ በባንክ በኩል ለመክፈል የሚችሉ መሆናቸው፣ 7. ይህ ክፍያ የሚፈፀምበት የሰነድ ቁጥር በኢ-ፋይሊንግ የአጭር ጽሁፍ መልዕክት(EMS) ሴንተር ላይም ስለሚገኝ ግ/ከፋዮች ከዛም ማግኘት የሚችሉ መሆኑን በተጨማሪም 8. ኢ-ፋይሊንግ ተጠቃሚ የሆኑ ግ/ከፋዮች የታክስ ክፍያውን ሲፈጽሙ ክፍያው የተፈፀመበት ደረሰኝ በኢ-ሜይል አድራሻቸው እና በኢ-ፋይሊንግ የአጭር ጽሁፍ መልዕክት (SMS) ሴንተር የሚደርሳቸው መሆኑን እና የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክትም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) በሞባይላቸው የሚደርሳቸው መሆኑን ግንዛቤ እንዲይዙ የሚያስፈልግ ናቸው፡፡ ገቢዎች ሚኒስቴር በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169 በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።

  • https://www.facebook.com/ERCA.info/videos/743155257315536/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

  • ማሳሰቢያ ለግብር ከፋዮቻችን! ታህሳስ 30፣ 2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በኢ-ፔይመንት የክፍያ ስርዓት ላይ የተለያዩ የማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን ማንኛውም የታክስ ውሣኔዎች እና ሌሎች ደብዳቤዎች ለግብር ከፋዩ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ተደራሽ እንዲሆን፤ በተጨማሪም ማንኛውም ለግብር ከፋዩ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የተላከ የታክስ ውሣኔ እና ሌሎች ደብዳቤዎች በኢ-ሜይል የተላኩ መሆናቸውን የሚገልፅ አጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) በሞባይል የስልክ ቁጥሩ እንዲደርሰው፤ እንዲሁም ባለሥልጣን መ/ቤቱ ይህንኑ የተላከ የታክስ ውሣኔና ሌሎች ደብዳቤዎች ተደራሽ የተደረጉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥበት ስርዓት ለምቶ ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ግብር ከፋዮቻችን ይህንኑ አውቃችሁና ተገንዝባችሁ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ እንድትፈጽሙ ማለትም፡- 1. በትክክል የምትገኙበትና የምትጠቀሙበትን ትክክለኛ የኢ-ሚይል አድራሻና የሞባይል ስልክ ቁጥር ለባለሥልጣን መ/ቤቱ እንድታሳውቁ፣ 2. ይህንኑ አረጋግጠው የሠጡትን የኢ-ሜይል አድራሻና የሞባይል ስልክ ቁጥር በአግባቡ መጠቀም የሚኖርብዎት ሲሆን ዘወትርም ከፍተው ይዩት፤ 3. የኢ-ሜዳል አድራሻ እና የሞባይል ቁጥር ለውጥ ካዳረጉም ወዲያው ለባለሥልጣን መ/ቤቱ በማሳወቅ የዜግነት ግዴታዎን እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡ በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169 በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።

  • 1 нояб. 2023 г.1 53333из AdamaRevenuesMoRs

    ለቅ/ጽ/ቤታችን ግብር ከፋዮች በሙሉ እንኳን ለ2016 በጀት አመት አመታዊ የግብር ማስታወቂያ ጊዜ በሰላምና ጤና አደረሳችሁ እያልን፡- · የበጀት አመቱን ግብር በኢፋይሊንግ በማሳወቅ ክፍያውን በኢፕይመንት እንድትከፍሉ እያሳሰብን ያዘጋጃችሁትን የተሟላ የሂሳብ መግለጫ መረጃ ሀርድ ኮፒ ክሊራንስ አገልግሎት ለመውሰድ ከመጠየቃችሁ 14 ቀናት በፊት ቢሮ ቁጥር 203 እንድታቀርቡልን · ለቅ/ጽ/ቤቱ የምታቀርቡት የተሟላ የሂሳብ መግለጫ ሀርድ ኮፒ ሊይዛቸው የሚገቡ ዝርዝር አባሪ መረጃዎች ከምስሉ ላይ ይመልከቱ

  • 5 окт. 2023 г.1 24057из AdamaRevenuesMoRs

    ለቅ/ጽ/ቤታችን ግብር ከፋዮች በሙሉ እንኳን ለ2016 በጀት አመት አመታዊ የግብር ማስታወቂያ ጊዜ በሰላምና ጤና አደረሳችሁ እያልን፡- · የበጀት አመቱን ግብር በኢፋይሊንግ በማሳወቅ ክፍያውን በኢፕይመንት እንድትከፍሉ እያሳሰብን ያዘጋጃችሁትን የተሟላ የሂሳብ መግለጫ መረጃ ሀርድ ኮፒ ክሊራንስ አገልግሎት ለመውሰድ ከመጠየቃችሁ 14 ቀናት በፊት ቢሮ ቁጥር 203 እንድታቀርቡልን · ለቅ/ጽ/ቤቱ የምታቀርቡት የተሟላ የሂሳብ መግለጫ ሀርድ ኮፒ ሊይዛቸው የሚገቡ ዝርዝር አባሪ መረጃዎች ከምስሉ ላይ ይመልከቱ

  • ለቅ/ጽ/ቤታችን ግብር ከፋዮች በሙሉ እንኳን ለ2016 በጀት አመት አመታዊ የግብር ማስታወቂያ ጊዜ በሰላምና ጤና አደረሳችሁ እያልን፡- · የበጀት አመቱን ግብር በኢፋይሊንግ በማሳወቅ ክፍያውን በኢፕይመንት እንድትከፍሉ እያሳሰብን ያዘጋጃችሁትን የተሟላ የሂሳብ መግለጫ መረጃ ሀርድ ኮፒ ክሊራንስ አገልግሎት ለመውሰድ ከመጠየቃችሁ 14 ቀናት በፊት ቢሮ ቁጥር 203 እንድታቀርቡልን · ለቅ/ጽ/ቤቱ የምታቀርቡት የተሟላ የሂሳብ መግለጫ ሀርድ ኮፒ ሊይዛቸው የሚገቡ ዝርዝር አባሪ መረጃዎች ከምስሉ ላይ ይመልከቱ