አዲስ መረጃ - Addis Mereja
Статистикаበኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ የሚከሰቱ ወቅታዊ ጉዳዮችን፣ እውነተኛ ዜናዎችን እና ትንታኔዎችን በፍጥነት የሚያገኙበት ታማኝ የዜና ቻናል። ለማስታወቂያና ጥቆማ👉 t.me/Bini_Kasa Addis Ababa, Ethiopia Buy ads: https://telega.io/c/AddisMerejaEth
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 19
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 4 063
- 1/48двое суток
- 4 921
- 1/72трое суток
- 5 307
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
«ምርኮኛም፣ ዳንሰኛም አይደለሁም!» — ጄነራል ባጫ ደበሌ በኬኒያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ከጋዜጠኛ ኤርሚያስ ለገሰ ጋር ባደረጉት ገጽ ለገጽ ቃለ ምልልስ፣ በስማቸው ዙሪያ ለዓመታት ሲናፈሱ የቆዩ ወሬዎችንና ውንጀላዎችን አጥብቀው አስተባበሉ። በተለይም «ሻዕቢያ ማርኮ በሳሕል በረሃ ያስደንሳቸው ነበር» በሚል ስለ እሳቸው የሚነገረውን ሃሜት ውድቅ ያደረጉት ጄነራሉ፤ «ባጫ ዳንሰኛ ነው» የሚለውና በሰፊው የሚሰራጨው ትርክት ምንም ዓይነት ማስረጃ የሌለው፣ በሟቹ ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የተቀናበረ ምናባዊ ፈጠራ መሆኑን ገልጸዋል። «ጄነራልነትን የሰጠኝ ብሔራዊ ቲያትር አይደለም፤ የሜዳው ተጋድሎዬ እንጂ!» ያሉት አምባሳደር ጄነራል ባጫ፤ እሳቸውን በምርኮኝነትም ሆነ በዳንሰኝነት የሚወነጅል ወገን ካለ «የማረከኝ አካል ካለ ይውጣና ማስረጃውን ያቅርብ፣ በአደባባይም ይናገር!» ሲሉ ጠንካራ ጥሪ አቅርበዋል። ሀሳብዎን ያካፍሉን?
⚡️ Discover ALEXATOR Original electronic music created to inspire, motivate and energize. 🌐 alexator.com Listen & download for free. 📲 t.me/alexator_music Follow for new music, videos & updates. 🎬 Watch in 4K on YouTube ▶️ GENESIS (001) ▶️ AWAKENING (002)
ቀን 07/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ 📞09 03 01 00 06 📞09 57 97 40 82 🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption ✨ደመወዝ===150dollar ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ===10&12 🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/ ✨ደመወዝ===200-600 dollar ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ ልምድ===0-5አመት ✨የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ 🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport ✨ደመወዝ===13500+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የ/ት ደረጃ===10 🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ ✨ደመወዝ===13000+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ===8+ 🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ ✨ደመወዝ===14500 ✨ዖታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት=== ደረጃ-10+ 🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/ ✨ደመወዝ===15000+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===አይጠይቅም ✨የት/ደረጃ===6-12 🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/ ✨ደመወዝ-15000+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ==8-12 🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ ✨ደመወዝ===15000+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ===10 🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ ✨ደመወዝ===12500+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም 🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች ✨ደመወዝ===15000+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ0===0አመት ✨የት/ት ደረጃ==8-12 🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ ✨ደመወዝ===14000 ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ===8ኛ-12 🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/ ✨ደመወዝ===12000+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0-1አመት ✨የት/ትደረጃ ==8-12 🇪🇹position👉አምፖል ማምረት ✨ደመወዝ===13,000 ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ===8+ 🇪🇹position👉ሹፌር ✨ደመወዝ 14-22000 ✨ፆታ===ወ ✨ልምድ=2አመት ✨የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/ 🇪🇹position👉አካውንታት ✨ደመወዝ=14500+ ✨ፆታ===ወ ✨ልምድ===0-5አመት ✨የት/ት ደረጃ===digree 🇪🇹position👉ሆስተስ ✨ደመወዝ===25000 ✨ፆታ=/ሴት ✨ልምድ===0-አመት ✨የት/ት ደረጃ10-12 🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ ✨ደመወዝ===13500 ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0-1አመት ✨የት/ት ደረጃ==8-12 🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ ✨ደመወዝ===16000 ✨ዖታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===አይጠይቅም ✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም 🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ ✨ደመወዝ===10000+ ✨ዖታ===ወ/ ✨ልምድ===0-አመት ✨የት/ት ደረጃ==8-12 🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል 🔶ደመወዝ===18,000 ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0-2 ✨የት/ት ደረጃ===digree ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው ☎️ 📞09 57 97 40 82 📞 09 03 01 00 06 አድራሻ መገናኛ መተባበር ህንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421 https://t.me/familyWorke
በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ። ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል። በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል። * በሲጋራ፣ * በአልኮልና * በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል። የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ በሰጡት አስተያየት፣ እነዚህ አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ሆኖም መንግሥት አገራዊ ገቢውን ለማሳደግ ሲል ውሳኔዎቹን በቁርጠኝነት እንደሚተገብራቸው ይጠበቃል ብለዋል። Via ሊዲያ ደሳለኝ ©️Ethio FM @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
የ YBS ድርጅት መስራች አቶ ወልደጊዮርጊስ፣ ሰዎች ኢንቨስት ያደረጉትን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ይዞ ተሰውሯል በሚል በማህበራዊ ሚዲያና በተለያዩ አካላት ሲሰራጭ የነበረውን መረጃ አጥብቆ አስተባበለ። አቶ ወልደጊዮርጊስ እንደገለፀው፣ አንዳንድ አካላት በቅንጅትና ገንዘብ ተከፍሏቸው በኢንተርኔትና በተለያዩ መንገዶች ስሙን ለማጥፋት በከፈቱት የሀሰት ዘመቻ ምክንያት በድርጅቱ ላይ ኢንቨስት ያደረጉ ደንበኞቻቸው ለከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት መዳረጋቸውን ተናግሯል። ከ8 ሺህ በላይ ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ ኢንቨስት ያደረጉበትን ይህንን ፕሮጀክት በተመለከተ የተነሱትን ስጋቶች ያሰረዳው መስራቹ፣ “እኔ ብሞት እንኳን ይህንን ፕሮጀክት ለሀገሬ አስረክባለሁ” ሲል ቁርጠኝነቱን ገልጿል። ብዙ ሲነገርለት የቆየውን ይህንን ድርጅት በቅርቡ አስከፍቶ ወደ ሥራ እንደሚገባ አቶ ወልደጊዮርጊስ የገለፀ ሲሆን፣ የተነሳውን ወሬዎችና ስጋቶች በቅርቡ በተግባር ምላሽ እንደሚሰጥ አረጋግጧል። @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
አንድ iPhone 17 Pro ለመግዛት የስንት ቀን ደሞዝዎ ያስፈልጋል? 📱🌍 በዓለም ዙሪያ የ iPhone 17 Pro ሽያጭ ዋጋ ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እውነተኛው ዋጋ የሚወሰነው በምንኖርበት ሀገርና ባለን የገቢ መጠን ነው! ለምሳሌ ያህል፡ - በስዊዘርላንድ፦ የአብዛኛው ሰው የ3 ቀን ደሞዝ ብቻ ይበቃል። - በፊሊፒንስ፦ የ101 ቀን ደሞዝ ይጠይቃል። - በሕንድ፦ የ160 ቀን ደሞዝ ይፈልጋል። - በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፦ ሙሉ የ540 ቀን (ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ) ደሞዝ ያስፈልጋል! አንድ አይነት ስልክ፣ ተመሳሳይ የገበያ ዋጋ... ነገር ግን ከተወለድንበት ሀገር የኢኮኖሚ አቅም አንጻር አንዳንዶች በጥቂት ቀናት ገቢያቸው የሚገዙት፣ ለሌሎች ደግሞ የዓመታት ድካም ዋጋ የሚጠይቅ ሆኗል። ይህ ቀላል የቴክኖሎጂ ውጤት የዓለማችንን ግዙፍ የኢኮኖሚና የሀብት ክፍተት በግልጽ የሚያሳይ እውነታ ነው! @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው እያስመዘገበች ያለውን አህጉራዊ አርአያነት ተመልክተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ለመኖር ማሰብ የሚጀምሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) Via FBC @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
የአውሮፓ ረጅሙ የድንግል ማርያም ሐውልት ሊመረቅ ነው። በአንድ የፖላንድ ቢሊየነር ወጪው የተሸፈነው 182 ጫማ ቁመት ያለው የድንግል ማርያም ሐውልት ግንባታ ተጠናቆ በነሐሴ ወር መጨረሻ ለምረቃ እንደሚበቃ ተገለፀ። ይህ ሐውልት በአውሮፓ አህጉር ትልቁና ረጅሙ የድንግል ማርያም ሐውልት ያደርገዋል። የግንባታውን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሸፈኑት ታዋቂው የፖላንድ ባለሀብት ሮማን ካርኮሲክ እና ባለቤታቸው ግራዚና መሆናቸው ታውቋል። ፕሮጀክቱ ላለፉት አራት ዓመታት ሲያከናውኑ መቆየታቸው ነው የተገለፀው። ይህ መንፈሳዊ ሀውልት በሀብትና በስልጣን ላይ ትኩረት በሚደረግበት በዚህ አለም ውስጥ የሰዎችን አእምሮ ወደ ላቀ መንፈሳዊ እሴትና እምነት የሚያነሳሳ አርማ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል። @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
ሰበር በብሉ ናይል ግዛት ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢ አዲስ ውጊያ ተቀሰቀሰ! ከአንድ ወር በፊት የሱዳን ጦር ስትራቴጂካዊቷን ኩርሙክን መቆጣጠሩ ይታወቃል፡፡ ጦሩ በወቅቱ ከተማዋን ሲቆጣጠር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ታጣቂዎች ወደኋላ አፈግፍገው ነበር፡፡ ዛሬ በወጣ መረጃ፣ በሸረሪናው ውጊያ ተሳትፏል በሚል የተወነጀለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በሱዳን ጦር ላይ አዲስ የመልሶ ማጥቃት ከፍቷል፡፡ ይህን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህ ቀጠና የሕወሓት የጦር አሃዶች ከአልቡርሃን ጎን ሆነው እንደሚዋጉ ይታወቃል፡፡ @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
በአበሽጌ ወረዳ በሦስት ወጣቶች ላይ የተፈጸመ አሰቃቂ ግድያ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አገና በተባለ ስፍራ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሦስት ወጣቶች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና እንዲወርዱ ከተደረገ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል። ወጣቶቹ "ፋኖ ናችሁ" በሚል ውንጀላ ከተያዙ በኋላ እጃቸው ወደኋላ ታስሮ እንግልት እንደተፈጸመባቸው እና በስተመጨረሻም ጭንቅላታቸውን በጥይት ተመተው በግፍ መረሸናቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ገልጸዋል። ይህ ድርጊት የተፈጸመው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአካባቢው የአበሽጌ አገና ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ከግድያው በኋላም የሟቾቹን አስከሬን በትውልድ ቀያቸው በናቻ ቀሊት ቀበሌ ጥለው ማንም እንዳያነሳና እንዳይቀብር ዕገዳ ጥለው እንደነበር ተጠቅሷል። በዚህም ምክንያት አስከሬኖቹ እጃቸው ሳይፈታ ለሦስት ሙሉ ቀናት በሜዳ ላይ ተጥለው እንዲቆዩ መደረጉና ድርጊቱም በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንና ስጋት መፍጠሩ ተመልክቷል። ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን🙏 Via Meseret media @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለሕፃናት የሚሰጡ ክትባቶችን ብዛት የሚቀንስ እንዲሁም በአንድ ክትባት ይሰጡ የነበሩት የጆሮ ደግፍ፣ የኩፍኝ እና የጉድፍ መከላከያዎች (ኤምኤምአር) ለየብቻ እንዲሰጡ የሚመክር ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ፈርሙ። "ከአስርተ ዓመታት በፊት [የተወለዱ] ሕፃናት የወሰዱት ክትባት ዛሬ ከሚያስፈልቸጋው በጣም ጥቂት ነው" ያሉት ትራምፕ፣ በዚያን ጊዜ ሰዎች የተሻለ ጤናማ እንደነበሩ እና አሁን የሚታየው ከፍተኛ የኦቲዝም ችግር እንዳልነበር ገልጸዋል። ዘ ዴይሊ ኮለር የተሰኘው ሚዲያ ያገኘው የዋይት ሀውስ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ይህ ትዕዛዝ የኩፍኝ፣ ጆሮ ደግፍ እና ሩቤላ ክትባት በሶስት የተለያዩ ቀጠሮዎች ተነጣጥሎ እንዲሰጥ ይመክራል። በተጨማሪም የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ መምሪያ የክትባት ምርምርን እንዲያሻሽል ያዛል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ውስጥ ለልጆች የሚሆኑ የተነጣጠሉ የኩፍኝ፣ ጆሮ ደግፍ እና ሩቤላ ክትባቶች አይገኙም። ሰኞ ዕለት በኦቫል ኦፊስ ስለ ትዕዛዙ የተናገሩት ትራምፕ፣ የአንድ ዓመት ህጻናት ክትባታቸውን በአምስት የተለያዩ ቀጠሮዎች ተከፋፍሎ መውሰድ እንዳለባቸው ገልጸዋል፤ ነገር ግን ይህ ማብራሪያቸው ህጻናቱ የሚወስዷቸውን ሁሉንም ክትባቶች ወይስ የተወሰኑትን ብቻ የሚመለከት መሆኑ ግልጽ አልነበረም። @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
''በአማራ የብዙዎች ህይወት ተቀጥፏል፣ ኦሮሚያ እየደማች ነው! ቴዎድሮስ አድሃኖም'' ቴዎድሮስ አድሃኖም የኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ስጋት ያሳስበኛል አሉ። የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረኢየሱስ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት እንዲቆምና በአስቸኳይ ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በዛሬው ዕለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት "ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ተጨማሪ ጦርነት አይደለም" በማለት አገሪቱ ያለችበትን አስከፊ የጸጥታ ሁኔታ አመልክተዋል። ቴዎድሮስ በዝርዝር በገለጹት ነጥብ በአማራ ክልል ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት መቅጠፉን ገልጸዋል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው ደም መፋሰስ መቀጠሉን በትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግልጽ ጦርነት የመግባት ስጋት መኖሩን እንዲሁም የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭትና በዓመጽ ውስጥ መቆየታቸውን በአጽንኦት ጠቁመዋል። በቃ በማለት ጠንከር ያለ መልዕክት ያስተላለፉት ዋና ዳይሬክተሩ የፌዴራል መንግሥቱም ሆነ የክልል መሪዎች ከጦር መሣሪያ ይልቅ ለውይይት ቅድሚያ እንዲሰጡና እውነተኛ ፖለቲካዊ መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አሳስበዋል። ጦርነት በዜጎች ላይ የሚያስከትለውን ሰብዓዊ ቀውስ የገለጹት ዶክተር ቴዎድሮስ ግጭት የሞት ፣ የውድመት ፣ የመፈናቀል እና የከፋ እጦት ምንጭ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመጨረሻም "ኢትዮጵያውያን ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ሕይወት ይገባቸዋል" ሲሉ ገልፀዋል። Via:- BBC @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
ሰበር! “የክልል ልዩ ኃይል ይፍረስ በምክክር ኮሚሽኑ የተነሳ አጀንዳ” የአማራ ልዩ ሀይል ብቻ እንደፈረሰ ተረጋግጧል። የክልል ልዩ ኃይል ይፍረስ ፣ ሀገር አቀፍ ሚሊሻ ይደራጅ የሚሉ አጀንዳዎች ቀርበዋል። ልዩ ሀይል ይፍረስ በሚል ዘመቻ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ብቻ እንደተበተነ እና እደፈረሰ በምክክር ኮሚሽኑ ተሳታፊዎች ሀሳብ ተነስቷል። ተሳታፊዎች እንዳሉት የክልሎች የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንዲፈርስ የተወሰነ ቢሆንም፤ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች በተለያየ መልክና ስያሜ የልዩ ኃይል ሠራዊታቸውን ሳይበትኑ ማስቀጠላቸውን ያነሱ ተመካካሪዎች፤ ውሳኔው በሁሉም ክልሎች በዕኩልነት ተግባራዊ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ተሰምቷል። Via:- ዋዜማ ሀሳብዎን ያካፍሉን? @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
🇧🇷 ብራዚል ውስጥ፡ እስረኞች መጽሐፍትን በማንበብ የእስር ጊዜያቸውን መቀነስ ይችላሉ። እያንዳንዱን መጽሐፍ አንብበው ካጠናቀቁ በኋላ በተሳካ ሁኔታ ሲተነትኑ፡ ከእስር ቤት ቆይታቸው ላይ አራት ቀናት ይቀነስላቸዋል። የፕሮግራሙ መሪ ቃል “በማንበብ ይቅርታን ማግኘት” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፡ እስረኞች የተፈቀዱ መጽሐፍትን እንዲያነቡ የበርካታ ሳምንታት ጊዜ ይሰጣቸዋል። መጽሐፉን አንብበው ሲያጠናቅቁ፡ የመጽሐፉን ይዘት በትክክል እንደተረዱት ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ማለት አብዛኛውን ጊዜ ሪፖርት መጻፍ፣ ሌላ የተፈቀደ ግምገማ መከለስ ወይም ማጠናቀቅ ማለት ነው። ግምገማው ተቀባይነትን ካገኘ፡ ከእስር ፍርዳቸው ላይ የ4 ቀናት እፎይታ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፡ እስረኞቹ በየዓመቱ ቢያንስ እስከ 12 መጻሕፍት ድረስ አንብበው የማስገምገም ዕድል ያገኛሉ ተብሏል። ይህም ማለት፡ መጽሓፍትን በአግባቡ ማንበብ፡ ከእስር ቤት የቆይታ ጊዜ ላይ በዓመት እስከ 48 ቀናት ሊቀንስ ይችላል ማለት ነው። ይህ ሃሳብ፡ ሰዎች መጽሐፍን ከፍተው በማየታቸው ብቻ የሚሰጣቸው የሽልማት ሂደት ሳይሆን፡ እስረኞች ጊዜያቸውን በብቃት እንዲጠቀሙበት አድርጎ በማበረታታት በመስጠት፡ የማንበብ ባህላቸውን፣ የዕውቀት ደረጃቸውንና የአስተሳሰብ ስርዓታቸውን ለማሻሻልና ለማዳበር የተነደፈ ዘዴ ነው። በአንድ መጽሐፍ፡ የአራት ቀናት ነፃነት!!! @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
በኩርሙክ የጅምላ መቃብር ተገኘ‼️ በኢትዮጵያ ድንበር በሱዳን ብሉ ናይል ክልል በምትገኘው ኩርሙክ ከተማ የ25 ሰላማዊ ሰዎችን አስከሬን የያዘ የጅምላ መቃብር መገኘቱን የከተማዋ ባለሥልጣን አስታወቁ። በመቃብሩ የተገኙት አስከሬኖች የሴቶች፣ የሕፃናት እና የሆስፒታል ሠራተኞች መሆናቸው ተገልጿል። የኩርሙክ ከተማ ኮሚሽነር አብደል አቲ ሞሐመድ አል-ፋኪ እንዳሉት፣ የሱዳን ሠራዊት ከተማዋን ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ነፃ ካወጣ ከአንድ ወር በኋላ በተካሄደ የማጽዳት ሥራ ወቅት በከተማዋ ሰሜን ምሥራቃዊ ክፍል መቃብሩ ተገኝቷል። ባለሥልጣኑ እንደገለጹት፣ ተጎጂዎቹ በከተማዋ ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት RSF የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ለማስወንጨፍ ይጠቀምበት ከነበረው ጄበል ፋንካት ኮረብታ አቅራቢያ መገኘታቸውን ተናግረዋል። የጅምላ መቃብሩ መገኘቱ በሱዳን በቀጠለው ጦርነት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች እየተጋለጡ መሆናቸውን ያሳያል። በኩርሙክ የተገኘው መቃብር ከዚህ ቀደም በካርቱምና በጌዚራ ግዛቶች ከተገኙ ተመሳሳይ የጅምላ መቃብሮች ጋር ተያይዞ በሱዳን ጦርነት የሚደርሰውን የሰላማዊ ሰዎች ሰቆቃ እንደገና አጉልቶ አሳይቷል። @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth
በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት እና የቤት ማፍረስ እንቅስቃሴ በርካታ ነዋሪዎችንና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ከነበሩበት አኗኗርና የሥራ ቦታ ያፈናቀለ ትልቅ ሁነታ ሆኖ አልፏል። በቢቢሲ አማርኛ በኩል የቀረበው የዚሁ ሰዓሊና የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ዮናስ መኳንንት ታሪክም፣ ከዚሁ የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ከገጠመው መፈናቀል በኋላ የህይወቱን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ በመቀየር የአእምሮ ሰላሙንና ጥበባዊ ነጻነቱን ፍለጋ ከኮንክሪት ህንጻዎች ውካታ ወጥቶ ወደ ተፈጥሮ ያደረገውን አስደናቂ ጉዞ ያመላክታል። ዮናስ፤ በኮሪደር ልማቱ ምክንያት የነበረበትን ማደሪያና የስዕል ስቱዲዮ አጥቶ ከከተማዋ ከተፈናቀለ በኋላ፣ በከተማዋ የመልሶ ማቋቋም ውካታ ውስጥ ከመቆየት ይልቅ ወደ ሐይቅ ዳርቻና ወደ ተፈጥሮ አካባቢ ማመራትን መርጧል። አሁን በሚኖርበት ተፈጥሯዊ አካባቢ በፈረስ ግልቢያ፣ በጸጥታና በንጹህ አየር የተከበበ ሕይወት መጀመሩ ያጋጠመውን የመፈናቀል ስጋትና እንግልት ወደ አዲስ ጥበባዊ መነቃቃት እንዳቀየረው ያስረዳል፦ ሰላም ለኪነ-ጥበብ ሰው የመጀመሪያውና ዋናው ግብአት መሆኑን በማስመስከር። “አዲስ አበባ እንደ እንግዳ ካልሆነ ከዚህ በኋላ ለመኖር የምመጣ አይመስለኝም” ሲል በቁርጠኝነት የተናገረው ዮናስ፣ የልማት እርምጃዎች ያስከተሉትን ተፅዕኖ ተቋቁሞ የህይወት ቅደም ተከተሉን በመቀየር በነጻነትና በሰላም መኖር የሚያስችለውን አካባቢ መምረጡ ለኪነ-ጥበብ ጉዞው አዲስ መንፈስ እንደሰጠው ገልጻል። ይህ አጋጣሚ በከተሞች ፈጣን እድገትና በልማት ስም በሚከሰቱ መፈናቀሎች መካከል የዜጎችና የባለሙያዎች ህይወት እንዴት እንደሚቀየርና የራሳቸውን ሰላም ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያሳይ ጥልቅ አገራዊ ታሪክ ነው። @AddisMerejaEth @AddisMerejaEth